ወያኔዎች አዲስ አበባን ከተቆጣጠሩ በኋላ የነበሩትን ዕለታት ክንውኖች በሥርዓት የመመዝገብ ልምድ ያለው ሰው የሚያሰፍራቸው ልዩ ልዩ ሁኔታዎች ይኖሩታል። ከመጀመሪያው ዕለት አንስቶ። የእኔን የመጀመሪያ ዕለት አጭር ማስታወሻ ልንገራችሁ። በማለዳ ተነስቼ ጋቢዬን አጣፍቼ ከበሬ ላይ ቆሜ ሥፍር ቁጥር የሌላቸው አህዮች ወደ መሐል ከተማው (አዲስ አበባ) ሲጓዙ አያለሁ። ያንኑ ያህል ባራባሶ ጫማ የተጫሙ፣ የአካል ዝለት የሚታይባቸውና ከእህል ጋር […]

ብጹዕ አቡነ ዮሐንስ በሊቅነታቸው፣ በቆራጥነታቸው፣ ለየት ባለ አስተሳሰባቸውና ለነገሮች በሚሰጡት አስደናቂ ምላሽ የሚታወቁ የትግራይ ሊቀ ጳጳስ ነበሩ፡፡ እስካሁንም እርሳቸውን በተመለከተ የሚተረኩ እጅግ አስገራሚ ታሪኮች አሏቸው፡፡ አንዱ እንዲህ ይላል፡፡ አቡነ ዮሐንስ በዓላትን በተመለከተ የነበራቸው አስተሳሰብ ከብዙው ሰው ለየት ያለ ነበር፡፡ ‹‹በዓል መከበር ያለበት በሥራ ነው›› ብለው ያምኑ ነበር፡፡ በአንድ ወቅት እንዲያውም በቀዳሚት ሰንበት ሥራ ሲሠሩ ያያቸው ሰው ‹‹እንዴት ጌታ ባረፈበት ቀን ይሠራሉ›› ቢላቸው ‹‹እርሱኮ ያረፈው ሥራውን ጨርሶ ነው፡፡ እኔ መች ሥራዬን ጨረስኩ ብለህ ነው›› ብለው መመለሳቸው ይነገራል፡፡

‹‹የበዓላትን ቀናት ለበዓሉ የሚስማማ ሥራ በመሥራት እንጂ እጅና እግርን አጣጥፎ በመቀመጥ፣ መጠጥ ቤትና ጭፈራ ቤት በመዋል ማክበር ከማክበር አይቆጠርም፡፡ ሰው ምንጊዜም መቦዘን የለበትም፡፡ በየዕለቱ ለዕለቱ ተስማሚ የሆነ ሥራ መሥራት አለበት›› ብለው ያም ይህንንም ያስተምሩ ነበር፡፡

ታድያ በአንድ ወቅት በበዓል ቀን ቤተ ክርስቲያን ሲያሠሩ ውለው ለጉዳይ ወደ ሌላ ቦታ ይሄዳሉ፡፡ ለአቤቱታ ወደ እርሳቸው ዘንድ ከገጠር የመጣ አንድ ካህን እርሳቸውን ፍለጋ ወደሚያሠሩት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ይመጣል፡፡ ሲመጣ እርሳቸው የሉም ነገር ግን ሠራተኞቹ በሥራ ተጠምደዋል፡፡ ተገረመም፣ ተናደደም፡፡ ‹‹እንዴት በበዓሉ ቀን ትሠራላችሁ›› ሲል ጠየቃቸው፡፡ እነርሱም ያዘዟቸው አቡነ ዮሐንስ መሆናቸውን ነገሩት፡፡ እርሱ ግን አልተቀበለውም፡፡ ከኖረበትና ከተማረው ውጭ የሆነ ነገር ሲፈጸም እያየ ዝም ማለቱን ኅሊናው አልተቀበለውም፡፡ በርግጥ ያዘዙት ሊቀ ጳጳሱ ናቸው፡፡ ነገር ግን ሊቀ ጳጳሱም ቢሆኑ ሊሳሳቱ ይችላሉ አለና አሰበ፡፡

አስቦም አልቀረ ወደ ሠራተኞቹ ሄደና ‹‹በሉ ሥራችሁን አቁሙ›› አላቸው፡፡ እነርሱ ግን ሊቀ ጳጳሱ ያዘዙትን እንደማያቆሙ ነገሩት፡፡ በዚህ ጊዜ መስቀሉን አወጣና አወገዛቸው፡፡ ያን ጊዜም ሠራተኞቹ ሥራቸውን አቆሙና ቁጭ አሉ፡፡ እርሱም ሊቀ ጳጳሱን ፍለጋ ሄደ፡፡

አቡነ ዮሐንስ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ሲመጡ ሠራተኞቹ ሁሉ ቁጭ ብለዋል፡፡ ‹‹ለምን ሥራ ፈትታችሁ ተቀመጣችሁ?›› አሏቸው፡፡ ‹‹አንድ ካህን መጥቶ አወገዘን›› አሉና መለሱላቸው፡፡ ካህኑ ይጠራ ተባለና ተፈልጎ መጣ፡፡ ‹‹አንተ ነህ ወይ ያወገዝካቸው›› አሉት፡፡ ‹‹አዎ›› አለ፡፡ ‹‹ለምን?›› ሲሉ መልሰው ጠየቁት፡፡ ‹‹አባቶቻችን ያቆዩትን ሥርዓት ጥሰው ለምን በዓል ይሽራሉ ብዬ‹‹ አላቸው፡፡ ‹‹ያዘዝኳቸውኮ እኔ ነኝ›› አሉት፡፡ ‹‹ቢሆኑም ስሕተት ነው፡፡ ስሕተቱን እያየሁ ዝም ማለትም ሌላ ስሕተት ነው›› አላቸው፡፡

አቡነ ዮሐንስ ተገረሙ፡፡ ካህኑን በመኪናቸው አሳፈሩና ወደ ቤታቸው ወሰዱት፡፡ ‹‹በል ያንተን ጉዳይ በጉባኤ ነው የማየው፤ እስከዚያ እዚሁ እኔ ቤት እየበላህ እየጠጣህ ተቀመጥ›› አሉት፡፡ አቡነ ዮሐንስ ለጉዳይ የሚመጣ የገጠር ሰው ከገጠማቸው ከተቻለ ጉዳዩን ዕለቱኑ ይፈጽሙለታል፡፡ ካልተቻለ ደግሞ እዚያው ራሳቸው ቤት አስቀምጠው ጉዳዩ እስኪያልቅ ያስተናግዱታል፡፡ ክሱ የሚቀርበው በእርሳቸው ላይ ቢሆንም ሰውዬው በቤታቸው መስተናገዱ ግን አይቀርም፡፡

ቀን ተቀጠረና በሀገረ ስብከቱ አዳራሽ ጉዳዩ ታየ፡፡ የመቀሌ ከተማ ሕዝብ፣ ካህናትና ሊቃውንት ተሰበሰቡ፡፡ አቡነ ዮሐንስ በሚሰጡት ለየት ያለ ፍርድ፣ በሚናገሩት ዘመን ተሻጋሪ ንግግር ይታወቃሉ፡፡ በአንድ ወቅት ወደ እርሳቸው የመጣ ሰው ‹‹ተማር›› ቢሉት ‹‹ምን እየበላሁ ልማር›› አላቸው፡፡ እርሳቸውም ‹‹ታድያ የደነቆርከው ምን እየበላህ ነው›› ብለው ጠይቀውታል ይባላል፡፡

ያ ካህን ቀረበ፡፡ ‹‹ለምንድን ነው ሠራተኞቹን የገዘትካቸው?›› ተብሎ ተጠየቀ፡፡ ‹‹አባቶቻችን ባቆዩን ሥርዓት በበዓል እንዲህ ያለ ሥራ መሠራት የለበትም ብዬ ነው›› አላቸው፡፡ ‹‹ያዘዝኩት እኔ ነኝ፣ አንተ ይህንን ስታደርግ ሊቀ ጳጳሱ ይቀጡኛል፣ ከሥራ ያባርሩኛል፣ ክህነቴን ይይዙብኛል ብለህ አላሰብክም›› አሉት፡፡ ‹‹ቢያባርሩኝም፣ ክህነቴን ቢይዙብኝም መቀበል ነው እንጂ ምን ይደረጋል፡፡ ስሕተት እያየሁ ግን እንዴት አልፈዋለሁ፡፡›› አላቸው፡፡ ‹‹እና የሚመጣብህን ሁሉ ለመቀበል ተዘጋጅተሃል›› አሉት ‹‹ከመጣ ምን ይደረጋል›› አለ ካህኑ፡፡ ‹‹ከምቀጣህ ለምን ግዝትህን አታነሣም›› አሉት፡፡ ‹‹እርሱማ አቋም ነው፡፡ እምነቴ ነው፡፡ ቃሌ ነው፡፡ ይኼማ ከእርስዎ የባሰ ስሕተት መሥራት ነው›› አላቸው፡፡

ያን ጊዜ አቡነ ዮሐንስ ተነሡ፡፡ ሕዝቡም ምን ሊፈርዱበት ይሆን? እያለ በጉጉት ጠበቀ፡፡ ግማሹ እንዲያ ግማሹም እንዲህ አሰበ፡፡ አቡነ ዮሐንስም የመጣበትን አውራጃ ጠየቁት፡፡ ነገራቸው፡፡ አሁን ሕዝቡ የቅጣቱ ደብዳቤ ለአውራጃው እንደሚጻፍ አረጋገጠ፡፡ አቡነ ዮሐንስም አውራጃውን ከሰሙ በኋላ ‹‹እገሌ የተባለው የዚህ አውራጃ ሊቀ ካህናት እንዲህ ወደተባለ አውራጃ ተዛውሯል›› አሉ፡፡ ያን ጊዜ ሕዝቡ ‹‹የኃጥኡ ዳፋ ጻድቁን ያዳፋ›› ብሎ ተረተ፡፡ በዚህ ካህን ዕዳ ሊቀ ካህናቱ በመቀጣቱ አዘነ፡፡ አቡነ ዮሐንስም ቀጠሉ፡፡ ‹‹የዚህ አውራጃ ሊቀ ካህናት ግን ይህ ቄስ ይሆናል›› ሲሉ ሕዝቡ በአግራሞት አጨበጨበ፡፡ካህኑም ግራ ገባው፡፡ የጠበቀውና ያገኘውም ተለያየበት፡፡ ሕዝቡም በጥያቄ ተወጠረ፡፡ ለምን?

‹‹አያችሁ ወገኖቼ›› አሉ አቡነ ዮሐንስ፡፡ ይህ ሰው ሊቀ ጳጳሱን አወገዘ፡፡ እንደ ሥርዓታችን ልክ አልነበረም፡፡ ቢያንስ ለምን እንደዚያ እንዳደረግን እንኳን መጠየቅ ነበረበት፡፡ ነገር ግን በአቋሙ ትክክል ነው፡፡ ሰው ማለት፤ ጀግና ማለት፣ ጎበዝ ማለት አቋም ያለው ሰው ነው፡፡ የበላዩን የማይፈራ፤ ፈጣሪውን ብቻ የሚፈራ፡፡ ላመነበት እውነት የሚቆም፡፡ በአቋሙ ምክንያት የሚመጣበትን ሁሉ ለመቀበል ዝግጁ የሆነ፡፡ አሁን እኔ ሥልጣኑን ልይዝበት፣ ከሥራ ላግደው፣ ጨርሶም ላወግዘው እንደምችል ያውቃል፡፡ ይህንን ሁሉ እያወቀ ግን ላመነበት እውነት መጽናቱ ጀግና ያደርገዋል፡፡ ማክበር ያለብን የሚፈሩንን፣ ቅዱስ ቅዱስ የሚሉንን፣ የሠራነውንም ያልሠራነውም የሚያደንቁልንን፣ የሚያወድሱንን ብቻ መሆን የለበትም፡፡ ይህማ የማንም ሰው ጠባይ ነው፡፤ አክባሪውን የማይወድ ማን አለ፡፡ እኛም ጀግና የምንሆነው የሚገሥፁንን፣ የሚቆጡንን፣ ስሕተታችንን በድፍረት የሚናገሩንን፣ ሥልጣናችንን ሳይፈሩ ያመኑበትን እውነት የሚመሰክሩልንን ጭምር መውደድና ማክበር አለብን፡፡

እናንተ እንደምቀጣው ነው የጠበቃችሁት፡፡ የሚገሥጹንን ሁሉ ግን መቅጣት የለብንም፡፡ ያመኑበትን ስሕተታችንን የሚነግሩንን፣ በአቋም የሚሞግቱንን ሁሉ መቅጣት የለብንም፡፡ እንዲያውም መሸለም አለብን፡፡ ለዚህ ካህን ክህነቱን የሰጠሁት እኔ ነኝ፡፡ ስሰጠውም ‹ደኻ ተበደለ ፍርድ ተጓደለ በል› ያልኩት እኔ ነኝ፡፡ ያን የሰጠሁትን እኔ ላይ ሲፈጽመው መናደድ የለብኝም፡፡ ፍርደ ገምድል መሆንም የለብኝም፡፡ እንዲያውም እንዲህ ያለ ልጅ በማድረሴ ልኮራ ይገባል፡፡ ሞኞች የሚገሥጽዋቸውን አይወዱም፡፡ ግን ቢሆንም እየመረረን እንኳን መቀበል አለብን፡፡ አሠራሩ ስሕተት ቢሆንም አቋሙ ግን ልክ ነው፡፡ ቆራጥነቱ ግን ልክ ነው፡፡ ማንንም አለመፍራቱ፣ ላመነው እውነት ብቻ መቆሙ፣ የሚመጣበትን ለመቀበል መዘጋጀቱ ግን ልክ ነው፡፡ ስለዚህ ሸልሜዋለሁ፡፡

አዳራሹ በጭብጨባ ተሞላ፡፡ ካህኑም መሬት ወድቆ እጅ ነሣ፡፡ ታሪክም ለእኛ እንዲህ ሲል አቆየን፡፡

 © ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው

በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር አባል ፤የውህደት ጉዳዮች ፀሀፊና የፋይናንስ ክፍል ሀላፊ በሆኑት በአቶ ፀጋዬ አላምረው የተመራው ከፍተኛ ልኡካን ቡድን ከባለፈው ሳምንት ሀሙስ ማለትም ከግንቦት 7ቀን 2006ዓ. ም ጀምሮ በሰሜን ቀጠና የሚገኙ የፓርቲውን አደረጃጀት መዋቅሮች በመገምገም ላይ ሲሆን በተለይ በመኢአድና በአንድነት ፓርቲዎች የውህደት ጉዳይ በደጀን በደብረማርቆስና በባህር ዳር ከተማ ከሚገኙ የመኢአድ አባላት በቀረበ ጥያቄ […]

የጀርመን ድምጽ ራዲዮ በእንወያይ መድረኩ፣ የሕወሃት አባት ተብለው የሚታወቁት አቶ ስብሐት ነጋ፣ የመኢአድ ሊቀመንበር አቶ አበባዉ መሐሪ፣ ብቸኛ የተቃዋሚ ፓርቲ የፓርላማ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉና፣ በቅርቡ አንድነት ፓርቲን የተቀላቀሉት ደራሲና አክቲቪስት አቶ አስራት አብራሃ፣ በግንቦት ሃይ ዙሪያ ዉይይቶች በማድረግ ላለፉት 23 አመታት የነበረዉን ሁኔታ የቃኘ ሲሆን፣ በዉይይቱ ማብቂያ ላይ ኢሕአዴግን እና ተቃዋሚዎች ለአገር ጥቅም ሲባል […]

ሲሞላ ሲሞላ ጨዋታቸችን ሌላ፤ ሲጎድል ሲጎድል ሰው አንቀን ልንገድል። የአማርኛ አባባል እንደ መንደርደሪያ ጀሚላ የትግራይ ልጅ የሆነች የኢሕአሠ(የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ሠራዊት) አባል ነበረች። በኢሕአፓ ታሪክ ውስጥ ከሚጠቀሱ ጀግና ሴቶች መካከል አንዷ ነች። የደርግን ፋሽሽታዊ መንግሥት በመቃወም በተደረገው ትግል ወቅት ወልቃይት ውስጥ ነበረች። በኢሕአፓ/ ኢሕአሠ በወቅቱ የነበረው ትግል ድርብ ነበር። ይኸውም ከፋሽሽታዊ መንግሥትና ከዘረኛና ከአገር ገንጣዮች […]

ሲሞላ ሲሞላ ጨዋታቸችን ሌላ፤ ሲጎድል ሲጎድል ሰው አንቀን ልንገድል። የአማርኛ አባባል እንደ መንደርደሪያ ጀሚላ የትግራይ ልጅ የሆነች የኢሕአሠ(የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ሠራዊት) አባል ነበረች። በኢሕአፓ ታሪክ ውስጥ ከሚጠቀሱ ጀግና ሴቶች መካከል አንዷ ነች። የደርግን ፋሽሽታዊ መንግሥት በመቃወም በተደረገው ትግል ወቅት ወልቃይት ውስጥ ነበረች። በኢሕአፓ/ ኢሕአሠ በወቅቱ የነበረው ትግል ድርብ ነበር። ይኸውም ከፋሽሽታዊ መንግሥትና ከዘረኛና ከአገር ገንጣዮች […]

በዛሬው የሙዚቃ ቃና ፕሮግራም በአሜሪካ የቢል ቦርድ ሰንጠረዥ ላይ ከመቶዎቹ ምርጥ ዜማዎች መካከል በዚህ ሳምንት ከአንድኛ እስከ አስረኛ ደረጃ የወጡትን ምርጥ ዜማዎች እና ሙዚቃ ነክ ዜናዎችን ያጠቃልላል፡፡

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

በየአምሥት ዓመቱ የሚደረገው የአውሮጳ ምክር ቤት እንደራሴዎች ምርጫ የፊታችን ሐሙስ በኔዘርላንድስ እና በብሪታንያ የሚጀመር ሲሆን፣ እስከ ፊታችን እሁድ ባሉት ቀናት በ28 ቱ የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት ውስጥ ይጠናቀቃል።

በባልካን አካባቢ ሃገራት ካለፈው ቅዳሜ አንስቶ በተከሰተ የጎርፍ መጥለቅለቅ የሟቾቹ ቁጥር እየጨመረ ነው። አንዳንድ ድርጅቶች ተጨማሪ የውሃ ሙላት አደጋ እንደሚያስከትል እያስጠነቀቁ ነው።

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የትንሳዔን በዓል ምክንያት በማድረግ በተለያዩ እስር ቤቶች የሚገኙ ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች እንዲሁም የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን በያሉበት እስር ቤቶች ፕሮግራም አውጥቶ በቡድን በቡድን በመሆን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክቶችን ለማድረስ ችሎ ነበር፡፡ ከእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታችን በተጨማሪ ከፍተኛ አመራሩ አላማ ያሉበትን የአያያዝ ሁኔታ ለመረዳት ጭምር ነው፡፡ በዚህም መሰረት በተለይ በዝዋይ በፖለቲካ እስረኞችና ጋዜጠኞች ላይ […]

ተመስገን ደሳለኝ Temesegen Desalegnተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ) 

ኢህአዴግ ያነበረውን ቋንቋንና ዘውግን መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝም አደገኛነት በተመለከተ በርካታ ምሁራን፣ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች … ሳያሰልሱ ለመምከርና ለማስጠንቅቅ መዋተታቸውን አልዘነጋሁም። እኔም ከ“ፍትህ” ጋዜጣ እስከ “ፋክት” መጽሔት ድረስ ችክ ያልኩበትም ሆነ ዛሬ በዚህ ተጠየቅ የተመለስኩበት ምክንያት ችግሩ እያደር እየተባባሰ በመምጣቱና ከምንጊዜውም በላይ አዘናግቶ ወደተፈራው የእርስ በእርስ እልቂት ሊዘፍቀን እየተንደረደረ በመሆኑ፣ ቅድሚያ ሰጥተን በሕብረ-ድምፅ ‘የሀገር ያለህ!’ ብለን መጮህ እንዳለብን ስለማምን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ሰርዓት ሲኖር ተጠቃሚ የሚሆኑት ለዚህ ሲሉ ክቡር ህየይወታቸውን ለመሰዋዕትነት ያዘጋጁትና ይህንን መራራ ፅዋ በክብር የከፈሉት ብቻ አይደሉም፡፡ ይልቁንም የነፃነት፣ የዲሞክራሲ፣ የፍትህ ሰርዓት መሰፈን ደስ የሚያሰኘው የተጠቃሚ ምርጫ ለመሰዋዕትነት በመዘጋጀት እና በመክፈል አድልዖ ያለማድረጉ ነው፡፡ ከዚህ ዓይነት ሰርዓት የሚጠቀሙትም እነዚህን መሰረታዊ የሰው ልጅ መብቶችን ለማስከበር በሚደረግ ትግል ወቅት እራሳቸውን በፍርሃት ውስጥ ያኖሩትን ብሎም እራሳቸው […]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

አንድ የሱዳን ፍርድ ቤት፣ በአንዲት የ 27 ዓመት ሴት፣ ከልጅነቷ አንስቶ የ ወላጅ እናቷን ሃይማኖት ስተከተል መኖሯን በይፋ ብትገልጸም ፣ ያላሳደጋትን ሙስሊም አባቷን ሃይማኖት እንደለወጠች በመቁጠር ሙት-በቃ በመፍረዱ፣ በዛ ያሉ ምዕራባውያን መንግሥታትና የሰብአዊ መብት ድርጅቶች፣

የሶሪያ ሕዝብ ጉልበት፤ሐብቱ ሞልቶ የተረፋቸዉ የሚችሉትን እስኪያደርጉ መጠበቅ አልቻለም።ያልቃል።ከመቶ ሐምሳ ሺሕ እስከ ሁለት መቶ ሺሕ የሚደርስ ህዝብ ተገድሏል።ሌላዉ ይሰደድ-ይፈናቀላል።ከአምስት ሚሊዮን በላይ ተሰዷል ወይም ተፈናቅሏል።ቀሪዉ ይሸማቀቃል።

እስራኤል አይሁዳዉያንን ከኢትዮጵያ ዳግም መዉሰድ መጀመርዋ ተገለፀ። ባለፈዉ ሳምንት 64 ቤተ- እስራኤላዉያን፤ እስራኤል መግባታቸዉን ሃይፋ የሚገኘዉ ወኪላችን ግርማዉ አሻግሬ ገልጾልናል።

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ የሩጫ ውድድሮች ድል ተቀዳጅተዋል። አትሌቲኮ ማድሪድ ከ18 ዓመታት በኋላ የስፔን ላሊጋ አሸናፊ ሆኗል። የጀርመኑ ባየር ሙንሽን ተቀናቃኙ ቦሩስያ ዶርትሙንድን ድል ነስቶ ዋንጫውን በእጁ አስገብቷል። የጣሊያን ሴሪኣ ዋንጫን ጁቬንቱስ ጨብጧል። የእንግሊዝ «FA-Cup» ዋንጫን መድፈኞቹ ለንደን ይዘው ገብተዋል።

ሱዳን የኤሌትሪክ ኃይል ከኢትዮጵያ ለመግዛት ዝግጅት ላይ መሆንዋ ይታወቃል። ባለፈዉ ሰምን አንዳንድ የብዙሃን መገናኛ ድረ-ገፆች እንደዘገቡት ደግሞ፤ ሱዳን ለኤርትራ የኤሌክትሪክ ኃይል ልትሸጥ በዝግጅት ላይ ናት።

ከሰሜናዊ አፍሪቃ ሜዲትራንዬን ባህርን አቋርጠዉ ወደ ሀገርዋ የሚገቡባት ኢጣልያ ፤ ስደተኞችን ለማስተናገድ ከሌሎች አዉሮጳዉያን ሀገራት ርዳታ ይደረግልኝ ሥትል ጠየቀች። ወደ ኢጣልያ የሚገቡት የጀልባ ሥደተኞች ቁጥር እየጨመረ መሄዱ ተመልክቶአል።

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

በባልካን ሃገራት እና መካከለኛው አውሮጳ ውስጥ በደረሰዉ ከፍተኛ የዉሃ መጥለቅለቅ የሟቾች ቁጥር ከ 30 በላይ መድረሱ ተነገረ። በደቡብ ምሥራቅ አዉሮጳ ከሚገኙ ነዋሪዎች መካከል ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በዉኃ መጥለቅለቁ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

መወቃቀሱ ከልዩነትም አልፎ እንዳወዛገበ አነሆ ሃያ-ሦስተኛ ዓመቱን አለፈ። የሃያ ሦስት ዓመቱ ጥቅል ሒደት፤ የዉዝግቡ መሠረታዊ ምክንያትና የወደፊቱ ፖለቲካዊ ጉዞ እንዴትነት የዉይይታችን ትኩረት ነዉ።

መወቃቀሱ ከልዩነትም አልፎ እንዳወዛገበ አነሆ ሃያ-ሰወስተኛ ዓመቱን አለፈ።የሃያ ሰወስት ዓመቱ ጥቅል ሒደት፤የዉዝግቡ መሠረታዊ ምክንያትና የወደፊቱ ፖለቲካዊ ጉዞ እንዴትነት የዉይይታችን ትኩረት ነዉ።

Journalist Tsion Girma, ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ
ጽዮን ግርማ
[email protected]

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ለዛሬ የተቀጠሩትን ሦስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች አቤል ዋበላ፣ በፍቃዱ ኃይሉና ማኅሌት ፋንታሁን መዝገብ ለማየት የተሰየመው የተጠርጣሪዎቹ ቤተሰቦች ችሎት ሳይገቡ ነበር። ከመጀመሪያው ችሎት በኋላ ችሎቱ ባለው ቦታ ልክ ቤተሰብ እንዲገባ ተፈቅዶ የነበረ ቢኾንም ዳኛዋ የዕለቱን ሥራ ሲጀምሩ ስለዚህ ጉዳይ የሚያውት ነገር ያለ አይመስልም። ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጪ የሚሰየሙት ዳኞች ተረኛ ዳኞች በመኾናቸው የዛሬዋ ዳኛም ለመዝገቡና ለጉዳዩ አዲስ ነበሩ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

“የሥነልቡና ጫና ደርሶብኛል” ጋዜጠኛ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ “ከሌሊቱ 8 ሰዓት እየተወሰድኩ ድብደባ፣ ማስፈራራት እና ወከባ ተፈጽሞብኛል” አጥናፍ ብርሃኔ “ለምርመራ የምጠቀምበት አንድ ኮምፒውተር ነው ያለኝ፤ ጊዜ ይሰጠኝ” ፖሊስ ቅዳሜ ግንቦት 9፣ 2006 በቀጠሯቸው መሠረት አራዳ ምድብ ችሎት የቀረቡት 3 ጋዜጠኞች እና 3 ብሎገሮች ነበሩ፡፡ ፖሊስ የተጠርጣሪዎቹን ጉዳዩ ከወንጀል ወደ ሽብር በማሻሻሉ እና ምርመራዬን አላጠናቀቀኩም በማለቱ የ28 ቀን […]


ዛሬ በዋለው ችሎት ከተለመደው ሰአት ቀደም ብለው ከከባድ ጥበቃ ጋር ፍርድ ቤት የደረሱት የዞን 9 ጦማርያን በፍቃዱ ሃይሉ ማህሌት ፋንታሁን እና አቤል ዋበላ ላይ ፓሊስ ከትላንትናው ጋር ተመሳሳይ የሆነ 28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ የጠየቀ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ 14 ቀን ፈቅዶለታል፡፡

ፓሊስ የጸረ ሽብር አዋጁን በመጥቀስ በሽብር ክስ ለማቅረብ ስላሰበ 28 ቀን እንዲሰጠው የጠየቀ ቢሆንም ዳኛዋ ያለምንም የተለየ ተጨማሪ ነገር ከመነሻ ጥርጣሬ ለመቀየር ፓሊስ አሳማኝ ምክንያት ባለማቅረቡ 14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ብቻ ፈቅደዋል።
ጦማርያኖቹ ጓደኖቻችን ምንም አይነት የወንጀል ተግባር ላይ ተሰማርተው የማያውቁ መሆኑን እያስታወስን መንግስት እንዲፈታቸው አሁንም በድጋሚ ጥሪ እናቀርባለን

#‎FreeZone9bloggers #‎FreeTesfalem #‎FreeEdom #‎FreeAsemamaw #‎Ethiopia

በዛሬው እለት ማለትም 09/09/2006 ዓ.ም በጠዋቱ ፈረቃ የአንድነት ፓርቲ መሰረታዊ መርሆዎችና ፓርቲው የሚመራበት ርዕዮት አለም፤የመሬት ፖሊሲ፤ፌደራሊዝም እና የኢኮኖሚ ስርዓት እንዲሁም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ፕሮግራሞችና የአንድነት ፓርቲ ርዕዮት አለምን በንፅፅር ያቀረቡት አቶ ሀብታሙ አያሌው የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሲሆኑ ኃላፊው በመቀጠል የኢህአዴግ እና የአንድነት ፓርቲ ፕሮግራም መሰረታዊ ልዩነቶችን በማነፃፀር ለሰልጣኞች አስረድተዋል፡፡ ፓርቲው አሁን ያለበትን […]

Journalist Tsion Girma, ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ
ጽዮን ግርማ
[email protected]

ቀኑ ቅዳሜ በመኾኑ ፒያሳ በሚገኘው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ግቢ ውስጥ ከዘጠኙ ተጠርጣሪ ቤተሰቦች ውጪ መደበኛ ችሎት ሊከታተል የመጣ ሌላ ሰው አልነበረም። ከሁለት ሰአት ተኩል ጀምሮ ሲጠራቀም የቆየው የችሎት ተከታታይ ቀስ በቀስ በርከት ብሎ በግቢው መታየት ጀመረ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጽዮን ግርማ ([email protected](በፋክት መጽሔት የታተመ)
የታሰሩት ስድስቱ ጦማሪያንና (Bloggers) ሦስቱ ጋዜጠኞች 3 jailed journalists and 6 bloggers
ሚያዚያ 17 እና ሚያዚያ 18 ቀን 2006 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር የዋሉት ስድስቱ ጦማሪያንና (Bloggers) ሦስቱ ጋዜጠኞች በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ) ከታሠሩ ዛሬ ሃያ ሦስተኛ ቀናቸውን ይዘዋል። በእነዚህ ጊዜያት ውስጥም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ሁለት ጊዜ ቀርበዋል። እሁድ ሚያዝያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም. ለመጀመሪያ ጊዜ ሲቀርቡ ብቻቸውን በመኾኑም የፍርድ ቤቱ ድባብ ምን ይመስል እንደነበር የሚያውቅ አንድም ታዛቢ ሰው አልነበረም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ፈረንሳይ ፓሪስ ላይ የተደረገዉ ፀረ- ሽብር ጉባኤ፤በተለይ በናይጀርያ በሚንቀሳቀሰዉ አሸባሪ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ቦኮ ሃራም ላይ ማነጣጠሩ ተመለከተ። የናይጀርያዉን አሸባሪ ቡድን ለመዉጋት፤ በተሻለና በተቀናጀ መንገድ የትብብር ሥራ ወሳኝ መሆኑም ዛሬ ፓሪስ ላይ በተካሄደዉ የደኅንነት ጉባኤ ላይ ተመልክቶአል።

የቅዱስ ሲኖዶሱን የአመራር፣ የአስተዳደር፣ የቁጥጥርና የመወሰን ብቃት ያግዛሉ የቅዱስ ሲኖዶሱን አካላት ለማቀናጀትና አሠራራቸው ጥንካሬ እንዲኖረው ያስችላሉ ምልዓተ ጉባኤው በአጭር ጊዜ የሚይዛቸው በርካታ አጀንዳዎች የተጠና ውሳኔ ያገኛሉ የኦዲትና ኢንስፔክሽን አገልግሎት ተጠሪነት ለቅዱስ ሲኖዶሱ ይኾናል (አዲስ ጉዳይ፤ ቅጽ ፰ ቁጥር ፪፻፲፮፤ ግንቦት ፳፻፮ ዓ.ም.) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመጨረሻውና ከፍተኛው የሥልጣን ባለቤት ለኾነው ቅዱስ ሲኖዶስ÷ ቤተ …

በደቡብ ሱዳን ካለፈው ታህሳስ ወር ወዲህ በፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር መንግሥት ጦር እና በቀድሞው ምክትል ፕሬዚደንት ሪየክ ማቸር በሚመሩ ዓማፅያን መካከል የቀጠለው ውጊያ እና ያስከተለው መዘዝ የአካባቢው ሃገራት መረጋጋትን እንዳያናጋ ማስጋቱ ተነገረ።