የሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 20/2006 ዓ.ም ባደረገው የብሄራዊ ምክር ቤት ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ፡፡ ምክር ቤቱ በሊቀመንበሩ የቀረበውን የ6 ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ያጸደቀ ሲሆን ብሄራዊ ምክር ቤቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ቀጣይ ውሳኔዎችም ተላልፈዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በሊቀመንበሩ የቀረበለትን የስራ አስፈጻሚዎች የቦታ ሽግሽግም ተቀብሎ ያጸደቀ ሲሆን በሽግሽጉ መሰረትም አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ፣ አቶ ዮናታን ተስፋዬ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ፣ አቶ ጌታነህ ባልቻ የጥናትና ስትራቴጅ ኃላፊ እንዲሁም አቶ እያስፔድ ተስፋዬ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ ሆነው እንዲሰሩ አጽድቋል፡፡

ትምህርታቸው የአፈርና ቋጥኝ ፊዚክስ ፤በተለይም የእሳተ ገሞራ ጥናት ነው። ይሁንና ዛሬ ፣ እመኻል አውሮፓ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 21 ሰዓት ከ 56 ደቂቃ ለምርምር ፣ ከባይኖኩር ካዛኽስታን ፤ በሩሲያ ሶዩዝ የጠፈር መንኮራኩር ወደ ዓለም አቀፉ

 ክፍል አንድ
1.1 አጠቃላይ የግእዝ ሥነ ጽሑፋዊ ሀብት

የግእዝ ቋንቋ ከሁለት ሺ ዓመታት በላይ ጊዜ ያስቆጠረ የሥነ ጽሑፍ ሀብት ያለው ቋንቋ ነው፡፡ እስካሁን የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የግእዝ ሥነ ጽሑፍ በተጻፉበት ቁስ በሦስት መልኮች ቀርበዋል፡፡ በድንጋይ ላይ፣ በብራና ላይና በወረቀት ላይ፡፡

  1. የድንጋይ ላይ ጽሑፎች፡- በድንጋይ ላይ የተጻፉት የግእዝ ሥነ ጽሑፎች በአኩስም አካባቢ የተገኙትንና የነገሥታቱን የጦርነት ታሪኮችንና ሌሎች ዘገባዎችን የያዙትን ጽሑፎች ይመለከታል፡፡  የተገኙት የድንጋይ ላይ ጽሑፎች ከአራተኛው መክዘ(ቅልክ) እስከ 8ኛው መክዘ(ድልክ) የሚደርሱ ናቸው፡፡ እስካሁን ባለን መረጃ ጥንታዊው የሚባለው የድንጋይ ላይ ጽሑፍ በመጣራ ኤርትራ በሐውልቲ የተገኘው(5ኛው መክዘ ቅልክ) ጽሑፍ ነው፡፡

‹‹ዝ ሐውልት ዘአገበረ

አገዘ ለአበዊሁ ወሰ

ሐበ ሙሓዛተ አውዐ

አለፈነ ወጸበለነ›› የሚለው ነው፡፡

እነዚህ የድንጋይ ላይ ጽሑፎች አብዛኞቹ ዘገባዎችና ታሪኮች ሃይማኖታውያን አይደሉም፡፡

  1. የብራና ላይ ጽሑፎች፡- ሁለተኛው የግእዝ ሥነ ጽሑፍ የብራና ሥነ ጽሑፎች መልክ ነው፡፡ የብራና ላይ የግእዝ ጽሑፍ ከ6ኛው መክዘ እስከ አሁን ዘመን የቀጠለ ሲሆን በማይክሮፊልም በተነሡት የብራና መጻሕፍት ቁጥር የሄድን እንደሆነ ቁጥራቸው እስከ 12,000 ይደርሳል፡፡ በሰው ሠራሽና በተፈጥሮ አደጋ ጠፍተው የቀሩትን፣ በየቦታው ተደብቀውም አድራሻቸው ያልታወቁትን ሳይጨምር ማለት ነው፡፡ እስካሁን በተገኘው መረጃ ጥንታዊው የሚባለው የብራና የግእዝ መጽሐፍ በእንዳ አባ ገሪማ የሚገኘው ወንጌል ሲሆን የተጻፈውም በ6ኛው መክዘ ነው፡፡

  2. የወረቀት ላይ ጽሑፎች፡- ሦስተኛው የግእዝ ሥነ ጽሑፍ መልክ በወረቀት የታተሙ መጻሕፍት ናቸው፡፡ እነዚህ መጻሕፍት በብራና የሚገኙትን የግእዝ መጻሕፍት ተደራሽ ከማድረግ አንጻር የቀረቡ እንጂ አዳዲስ ድርሰቶች አይደሉም፡፡ የግእዝ የታተሙ መጻሕፍት ታሪክ ጉተንበርግ የግእዙን ዳዊት ጀርመን ላይ ካሳተመበት ጊዜ ይጀምራል፡፡ ይህም የአራት መቶ ዓመታት ታሪክ ይኖረዋል፡፡

 1.2 የሦስቱ የግእዝ ሥነ ጽሑፍ መልኮች ልዩ ባሕርይ
የድንጋይ ላይ ጽሑፎች

የድንጋይ ላይ ጽሑፎቹ የዘገባ መልክ ያላቸው፣ ታሪካዊ መረጃ የሚሰጡና በአብዛኛውም ሃይማኖታዊ ይዘት የሌላቸው ናቸው፡፡ ሃይማኖታዊ መረጃ ቢሰጡንም ነገሥታቱ ፈጣሪያቸውን ሲያመሰግኑ፣ ለፈጣሪያቸው የሰጡትን መሥዋዕት ሲገልጡ፣ ወይም የሙታን መታሰቢያ ሐውልቶቹ ደግሞ እግረ መንገዳቸውን በሚሰጡን መረጃ አማካኝነት ነው፡፡ የድንጋይ ላይ ጹሑፎቹ በሁለት ዓይነት አጻጻፍ የተጻፉ ናቸው፡፡ በጥንታዊና አናባቢ በሌለው ግእዝ ‹‹ሐወለተ፣ አከሰመ›› በሚለው መንገድና አናባቢ በተፈጠረለት ዘመናዊው ግእዝ የተጻፉ ናቸው፡፡ የድንጋይ ላይ ጽሑፎቹ በቅድመ አኩስምና በአኩስም ዘመን የተሠሩ ሲሆኑ የሚያንጸባርቁትም ያንኑ ዘመን ነው፡፡

የብራና ጽሑፎች

የብራና የግእዝ መጻሕፍት ከ6ኛው መክዘ ጀምረው እስካሁን የዘለቁና በሀገራችን የሥነ ጽሑፍ ዘመን በጥንታዊነትም ሆነ ለረዥም ዘመን በመዝለቅ ተወዳዳሪ የሌላቸው ናቸው፡፡ የብራና የግእዝ የጽሑፍ ሀብቶች ሦስት ዓይነት ናቸው፡፡

  1. ሃይማኖታውያን፣

  2. በዋናነት ሃይማኖታውያን ያልሆኑ ጉዳዮችን የያዙና

  3. ደብዳቤዎች

ሃይማኖታውያንየምንላቸው የተጻፉበት ዓላማ ሃይማኖትን ለማስተማር(ዶግማን፣ ቀኖናን፣ ትውፊትን፣ ታሪክን) ወይም ለአምልኮ ሥርዓት መፈጸሚያነት(ለጸሎት፣ ቅዳሴ፣ ውዳሴ፣ ዝማሬ፣ ሃይማኖታዊ ክዋኔ) የሆኑ ጽሑፎች ናቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ጨምሮ አብዛኞቹ የግእዝ የብራና ጽሑፎች ሃይማኖታውያን ናቸው፡፡ እነዚህ ሃይማኖታውያን የግእዝ ጽሑፎች ሦስት እምነቶችን የያዙ ናቸው፡፡ የኦርቶዶክስ፣ የካቶሊክና የይሁዲነት፡፡ የኦርቶዶክስ እምነትን የሚገልጡ መጻሕፍት በብዛትም ሆነ በቀደምትነት የግእዝን ጽሑፎች ይይዛሉ፡፡ ከ16ኛው መክዘ በኋላ ደግሞ የካቶሊክ እምነትን የሚገልጡ የግእዝ የብራና መጻሕፍትን እናገኛለን፡፡ የይሁዲነትን እምነት የሚገልጡት ጽሑፎች በኢትዮጵያ ከሚገኙ የቤተ እሥራኤል ወገኖች ጋር የተያያዙ ሲሆኑ እስካሁን ባሉን መረጃዎች ከመካከለኛው ዘመን ወደ ኋላ የዘለሉ አላገኘንም፡፡

የታተሙ የግእዝ የጽሑፍ ሀብቶች

የታተሙት የግእዝ ጽሑፎች የብራና ጽሑፎች ቅጅዎች ናቸው፡፡ እስካሁን ድረስ በግእዝ የተጻፉ ኣዳዲስ ድርሰቶችን በኅትመት አላገኘንም፡፡ አብዛኞቹ የታተሙ የግእዝ ጽሑፎች ግእዝና አማርኛን፣ ግእዝና ትግርኛን፣ ግእዝና እንግሊዝኛን፣ ግእዝና ጀርመንኛን፣ ግእዝና ስፓኒሽን፣ ግእዝና ፈረንሳይኛን፣ ግእዝና ፖርቹጊዝን ጎን ለጎን ያደረጉ ሲሆኑ ለሁለት ዓይነት ተግባራት የታተሙ ናቸው፡፡ ለሃይማኖታዊ አገልግሎትና ለምርምር አገልግሎት፡፡ ለሃይማኖታዊ አገልግሎት የሚውሉት የግእዝ ኅትመቶች የሚታተሙት በአብዛኛው በኢትዮጵያና በኤርትራ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ትንሣኤ ዘጉባኤ አሳታሚ፣ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፣ ተስፋ ገብረ ሥላሴ፣ አኩስም ማተሚያ ቤት፣ ማኅበረ ቅዱሳንና የየአጥቢያው አብያተ ክርስቲያናት ሲያሳትሟቸው፤ በኤርትራ ዋናው አሳታሚ ማኅበረ ሐዋርያት ፍሬ ሃይማኖት ነው፡፡

ለምርምር የሚውሉት የግእዝ ኅትመቶች በአብዛኛው የሚታተሙት በውጭ ሀገር ዩኒቨርሲቲዎች በኩል ነው፡፡ እነዚህ ኅትመቶች በጥናታዊ መጽሔቶች ውስጥና ራሳቸውን ችለው በመጽሐፍ መልክ የሚወጡ ሲሆኑ ከግእዙ በተጨማሪ የመቅረቢያ ቋንቋውን ትርጉም፣ ስለ ጽሑፉ ዳራና የጽሑፉ ምሁራዊ ሐተታ ይቀርቡባቸዋል፡፡ አብዛኞቹም የተለያዩ ቅጅዎች ንጽጽር አሏቸው፡፡ በዚህ ረገድ የጣልያን፣ የእንግሊዝ፣ የጀርመን፣ የፈረንሳይና የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ብዙ ሥራ ሠርተዋል፡፡ ለጥናት የሚታተሙ የግእዝ ጽሑፎችን በማተም ቤልጅየም የሚገኘውን ፒተርስ አሳታሚ የሚያህለው የለም፡፡

በግለሰብ ደረጃ ከጥንቶቹ እንግሊዛዊው ዋሊስ በጅ፣ ጀርመናዊው ኤድዋርድ ኡልንዶርፍና ኢዮብ ሉዶልፍ፣ ጣልያናዊዎቹ ኮንቲ ሮሲኒ፣ ኤንሪኮ ቼሩሊና ጉይዲ፤ ፈረንሳዊዎቹ ሬኔ ባሴ፣ ዣን ፕሩሶ፤ ራሺያዊውቢ ቱራየቭ ይጠቀሳሉ፡፡ ከዘመናችን ደግሞ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌን የሚስተካከል የለም፡፡

ክፍል ሁለት

ሃይማኖታውያን ያልሆኑ የግእዝ የሥነ ጽሑፍ ሀብቶች

ስለ ግእዝ ሥነ ጽሑፍ ብዙ ጊዜ ሲነገር ከሃይማኖታውያን የጽሑፍ ሀብቶቹ ጋር በተያያዘ ብቻ ነው፡፡ ይህ ሊሆን የቻለውም በሦስት ምክንያቶች ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡

  1. የግእዝ ቋንቋ በአሁኑ ጊዜ የቤተ ክርስቲያን መገልገያ ቋንቋ በመሆኑ

  2. አብዛኞቹ የግእዝ የሥነ ጽሑፍ ሀብቶች ሃይማኖታውያን በመሆናቸው እና/ወይም

  3. ሃይማኖታውያን ስላልሆኑት የሥነ ጽሑፍ ሀብቶች በብዛት ባለመነገሩና ባለመታተማቸው

ምንም እንኳን ከላይ የተገለጠው ግእዝን ከሃይማኖታዊ ድርሰቶች ጋር የማያያዝ ትርክት ጊዜ ጠገብ ቢሆንም በግእዝ ቋንቋ ተጽፈው የምናገኛቸው አያሌ ሃይማኖታውያን ያልሆኑ የሥነ ጽሑፍ ሀብቶች ግን አሉ፡፡ እነዚህ ሃይማኖታውያን ያልሆኑት የግእዝ የሥነ ጽሑፍ ሀብቶች ከሁለት ምንጮች የተገኙ ናቸው፡፡

  1. ከሀገር ውጭ

  2. ከሀገር ውስጥ

ከሀገር ውጭ የምንላቸው ከኢትዮጵያ ውጭ ተደርሰው ወደ ግእዝ ቋንቋ የተተረጎሙ ሲሆኑ እነርሱም ከግሪክ፣ ላቲን፣ ዓረብና ቅብጥ የተተረጎሙ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን መገኛ ቋንቋዎቻቸው እነዚህ ቢሆኑም በእነርሱ በኩል ግን ከምሥራቅ ሕንድ እስከ ምዕራብ ሮም የሚደርሱ ድርሰቶችን አግኝተናል፡፡

ከሀገር ውስጥ የምንላቸው ደግሞ በኢትዮጵያውያን ደራስያን የተደረሱና በግእዝ ቋንቋ የተጻፉ ናቸው፡፡ እነዚህም በተለይ በመካከለኛው ዘመን ተጀምረው እስከ 18ኛው መክዘ የዘለቁ የግእዝ የሥነ ጽሑፍ ሀብቶች ናቸው፡፡ የዚህ ጥናታዊ ጽሑፍ ዋና ዓላማ ይህ በመሆኑ በዚህ ጽሑፍ ላይ የተወሰኑትን እናያቸዋለን፡፡

  1. ፊሳሎጎስ፡- ፊሳሎጎስ ከግሪክ ወደ ግእዝ በ6ኛው መክዘ የተተረጎመ መጽሐፍ ነው፡፡ ፊሳሎጎስ በብዙ ቋንቋዎች የታወቀ መጽሐፍ ሲሆን የስሙ መጠሪያ ‹ፊዚዮሎጎስ› ከሚለው የግሪኩ ስም የመጣ ሆኖ በ200 ዓም አካባቢ በእስክንድርያ ውስጥ በግሪክ ቋንቋ የተጻፈ ነው፡፡ መጽሐፉ 48 ምእራፎች ሲኖሩት 42ቱ በእንስሳት፣ 2ቱ በዕጽዋት፣ 4ቱ ደግሞ በማዕድናት ላይ መሠረት ያደረጉ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ምእራፍ አንድ እንስሳ፣ ዕጽ ወይም ማዕድንን በማንሳት፣ ጠባዩንም በመተንተን ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጋር አጣምሮ የሚያቀርብ ነው፡፡

ይህ መጽሐፍ በትውፊታዊው የኢትዮጵያ ትምህርት ውስጥ የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት ማስተማሪያ ዋና ምንጭ ሆኖ ያገለገለ ነው፡፡

  1. ፈውስ ሥጋዊ፡- ይህ መጽሐፍ በአብዛኛው የሚታወቀው ፈውስ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ በሚል ነው፡፡ ነገር ግን ሁለቱ መጻሕፍት የተለያዩ ናቸው፡፡ ፈውስ መንፈሳዊ ምናልባት ከ13-16ኛው መክዘ ባለው ጊዜ ወደ ግእዝ የተተረጎመ መንፈሳዊ መጽሐፍ ነው፡፡ ዓላማውም በኃጢአት የቆሰለችን ነፍስ በመንፈሳዊ ሕክምና ማከም ነው፡፡ ፈውስ ሥጋዊ ግን በትክክል እስካሁን ያልተጠና ምናልባት ግን ከ17ኛው መክዘ በፊት የተደረሰ(ከሀገር ውስጥና ከውጭ ምንጮች) መጽሐፍ ይመስለኛል፡፡ በውስጡ ለሥጋዊ ሕመም ፈውስ ሊሰጡ የሚችሉ የተለያዩ የዕጽዋትንና የእንስሳትን ውጤቶች የያዘ ነው፡፡

  2. መጽሐፈ አዕባን፡- እስካሁን ባለኝ መረጃ መሠረት ስለዚህ መጽሐፍ ጥናት አልተደረገም፡፡ አንድ ኢትዮጵያዊ ብቻ በዚሁ ስም አንዲት አነስተኛ መጽሐፍ አሳትሟል፡ የተጠቀመው ይህንን ምንጭ ይሁን ወይም ሌላ አልተገለጠም፡፡ መጽሐፉ ለልዩ ልዩ ተግባር ሊውሉ የሚችሉ ድንጋዮችን በተመለከተ የተጻፈ የጂኦሎጂ መጽሐፍ ነው፡፡ አልፎ አልፎም ድንጋዮቹ በምን ዓይነት አካባቢ እንደሚገኙ ይናገራል፡፡ በኋላ ዘመን የድንጋይ ትርጉምና ጥቅም ተብሎ የተተረጎመውና በEMML 6815 የምናገኘው ከዚህ የተወሰደ ሳይሆን አይቀርም፡፡

  3. ዜና እስክንድር፡- ይህ መጽሐፍ በጥንታዊው ዓለም ታሪክ የተጻፈውን የታላቁን የግሪክ ንጉሥ የእስክንድርን ታሪክ በግእዝ የሚያቀርብ ነው፡፡ መጽሐፉ ምንጩ ግሪክ ሲሆን ከግሪክ ወደ ሶርያ፣ ከሶርያ ወደ ዓረብኛ፣ ከዓረብኛ ወደ ግእዝ የተተረጎመ ነው፡፡ የተተረጎመውም በ16ኛው መክዘ ምናልባት በ11ኛው የደብረ ሊባኖስ አበ ምኔት በዕጨጌ ዕንባቆም የመናዊ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለ፡፡ መጽሐፉ ሲተረጎም ርእሱ ‹‹ሑረቱ ለእስክንድር›› የሚል ነበር፡፡

እስክንድርን በተመለከተ በ14ኛው መክዘ እንደዚሁ አንድ ትርጉም ተከናውኖ ነበር፡፡ ‹‹ዜና እስክንድር›› የተባለው ይህኛው መጽሐፍ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ መጽሐፍ ለመጨረሻ ጊዜ የታየው በትግራይ አካባቢ በሚገኙ ገዳማት ውስጥ ነው፡፡ ዜና እስክንድርየእስክንድርን የጀግንነት ታሪክ በክርስትና የሞራል ትምህርት ውስጥ ለማሳየት የሚሞክር ሲሆን ዋናው ዓላማውም ነገሥታቱን፣ መኳንንቱንና ወታደሮችን ማጀገን ነው፡፡

5.       ፍትሐ ነገሥት፡- ፍትሐ ነገሥት ሁለት ክፍል አለው፡፤ ፍትሕ ሥጋዊና ፍትሕ መንፈሳዊ፡፤ ትኩረታችን በፍትሕ ሥጋዊ ላይ ነው፡፡ ፍትሐ ነገሥትን ያዘጋጀው በ13ኛው መክዘ ግብጽ ውስጥ የነበረው እብን- እል አሳል የተባለ ባለሞያ ነው፡፡ መንፈሳዊ ሕግጋቱን ከተለያዩ የቀኖና መጻሕፍት ሲወስድ ሥጋዊ ሕግጋቱን ደግሞ ከሮም፣ ከባዛንታይምና ከሌሎች ሀገሮች ሕግጋት ወስዷቸዋል፡፡

መጽሐፉ ወደ ግእዝ የተተረጎመው በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ሀገሪቱ እስከዚያ ድረስ ትጠቀም የነበረው የኦሪቱን የሕግ መንገድ በመሆኑ ንጉሥ ዘርዐ ያዕቆብ ይህንን ሕግ ለመቀየር በማሰቡ ነው፡፡ ይህንን ሃሳቡን የነገረውና በወቅቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ጴጥሮስ አብደል ሰይድ የተባለ ግብጻዊ ፍትሐ ነገሥትን ንጉሡ ከግብጽ እንዲያስመጣ መከረው፡፡ ጴጥሮስ አብደል ሰይድም በንጉሡ ተልኮ መጽሐፉን ካመጣው በኋላ ወደ ግእዝ ተረጎመው፡፡ እስካሁን ባለን መረጃ ግን ፍትሐ ነገሥት በሥራ ላይ ለመዋሉ ምንጭ የተገኘለት በዐፄ ሠርፀ ድንግል ዘመን ነው፡፡ ፍትሐ ነገሥት ኢትዮጵያ ዘመናዊ ሕግ እስክትቀርጽ ድረስ የተጠቀመችበት ለ600 ዓመታት ያህል ያገለገለ የሕግ ምንጭ ነው፡፡

6.       ዜና ስክንድስ፡- ስክንድስ በክርስትና የመጀመሪያዎቹ ዘመን የነበረ የግሪክ ፈላስፋ ነው፡፡ እናትና አባቱ የፍልስፍናን ነገር እንዲያጠና ወደ አቴንስ ልከውት የተመራመረውን ነገር ነው መጽሐፉ የሚገልጥልን፡፡ ይህ መጽሐፍ በሁለት የምዕራብ ቋንቋዎች(ላቲንና ግሪክ)ና በሦስት የምሥራቅ ቋንቋዎች(ሲርያክ፣ዓረብኛና ግእዝ) ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያው መጽሐፍ ከዐረብኛ የተተረጎመ ይመስላል፡፡ ወደ ግእዝ የተመለሰውም በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን መሆኑን ይገልጣል፡፡

ግእዙ ሦስት ክፍሎች አሉት፡፡ የመጀመርያው ክፍል የስክንድስን ሕይወት ይይዛል፣ ሁለተኛው ደግሞ የ55 ፍልስፍናዊ ጥያቄዎችንና መልሶችን የያዘ ሲሆን ሦስተኛው ክፍል 108 ጥያቄዎችን እያነሣ ያትታል፡፡


7. መጽሐፈ ፈላስፋ ጠቢባን፡- ይህ ከ1503 – 1515 ዓም ባለው ዘመን የተተረጎመው መጽሐፍ በግእዝ ሊቃውንት ዘንድ እጅግ የታወቀ መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፉ የግሪክና የሌሎች ሀገሮች ፈላስፎችን አባባሎችና ትምህርቶች የያዘ መጽሐፍ ነው፡፡


8. በርለዓም ወየወሴፍ፡- በርለዓም ወየወሴፍ የተለያዩ ምሳሌዎችንና ተረቶችን የያዘ የሕንድ መጽሐፍ ነው፡፡ የተወሰደውም ከትውፊታዊው የጉተማ ቡድሐ የሕይወት ታሪክ ነው፡፡ ታሪኩ የፍቅር ታሪክ ነው፡፡ የዚህ መጽሐፍ ቅጅዎች በአይሁድ፣ በማኒያውያን፣ በሙስሊሞችና በክርስቲያኖች ዘንድ ይገኛሉ፡፡


ዋዳጎስ የተባለ እጅግ ባዕለ ጸጋ የሆነ ኃይለኛ የሕንድ ንጉሥ በሕንድ የሚገኙ ክርስቲያኖችን ጨፈጨፈ፡፡ አንድ ቀን ዋዳጎስ የወሴፍ የሚባል ወንድ ልጅ ወለደ፡፡ ኮከብ ቆጠሪዎችና ጠንቋዮች ስለ ልጁ ዕጣ ፈንታ ሲጠየቁ ልጁ ወደፊት ክርስቲያን እንደሚሆንና የክርስቶስን ሃይማኖትንም ከፍ ከፍ እንደሚያደርግ ይናገራሉ፡፡ ይህንን በመፍራት ንጉሡ ልጁን በአንድ ቤተ መንግሥት ውስጥ ወስኖ አስቀመጠው፡፡ ኀዘን፣ ድክመት፣ ሞት የሚባሉትን ነገሮች እንዳያውቅ እርሱንም ከደስታ የሚያወጣውን ነገር እንዳያጋጥመው አደረገው፡፡


እያደገ ሲሄድ ግን መስፍኑ ከዚያ ቤተ መንግሥት ውጭ ያለውን ዓለምም ለማወቅ ፈለገ፡፡ ከቤተ መንግሥቱ ውጭም ኀዘን፣ በሽታ፣ ልቅሶ፣ ረሃብና ሞት መኖራቸውን ዐወቀ፡፡ ታዋቂው መናኝ መምህር በርለዓምም መስፍኑን አገኘው፡፡ ስለ እግዚአብሔርና ስለ ክርስትናም አስተማረው፡፡ ይህንንም ያስተማረው የተለያዩ ታሪኮችንና አባባሎችን በመጠቀም ነበር፡፡


መስፍኑ የወሴፍ ዓለምን ለመካድ ከበርለዓም ጋር ያለውንም ግንኙነት አባቱ ሳይሰማ ለማቆም ፈለገ፡፡ አባቱ ነገሩን ከመስማቱ በፊትም በርለዓም ከእርሱ ተለየ፡፡ ንጉሡም ነገሩን ሲሰማ እጅግ ተበሳጨ፡፡ የወሴፍን ወደ ጥንት እምነቱ ለመመለስም የቻለውን ሁሉ አደረገ፡፡ የመንግሥቱን አንድ ሦስተኛ ለመስጠት ቃል እስከ መግባትም ደረሰ፡፡ የወሴፍ ግን ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ በመጨረሻም ንጉሡ ራሱ ስሕተቱ ገባው፡፡ አማካሪዎቹ ሁሉ ክርስቲያን ከሆኑ በኋላም ንጉሡም ክርስትናን ተቀበለ፡፡


አባቱ ከሞተ በኋላ የወሴፍ መንግሥቱን ተወ፡፡ እጅግ ለሚያምነው ተከታዩ ዙፋኑን በመስጠትም መምህሩ በርለዓም ለመፈለግ ወደ በረሃ ሄደ፡፡ እዚያ በርለዓምን ሲያገኘውም ሁለቱም የምናኔ ሕይወታቸውን እስከ ዕለተ ሞታቸው ቀጠሉ፡፡


መጽሐፉን ያስተረጎመው ዐፄ ገላውዴዎስ ሲሆን የተረጎመው ደግሞ እጨጌ ዕንባቆም ነው፡፡ ትርጉሙም የተከናወነው በ1546 ዓም ነው፡፡ በርለዓም ወየወሴፍ ከሕንድ ተወስዶ በክርስቲያናዊ መንገድ የቀረበ የሥነ ምግባር ማስተማሪያ መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፉ በሦስቱ ዋና ዋና እምነቶች (አይሁድ፣ ክርስትናና እስልምና) ተቀባይነት ያገኘ መጽሐፍ ነው፡፡


9. አቡሻክር

አቡ ሻክር ቢን አቢ ኤል ከሪም ቡጥሮስ ቢን አል ሙሐዲብ ያዘጋጀው የዓለምን ታሪክ የያዘ መጽሐፍ፡፡ የኖረው ከ1200/ 10 እስከ 1295 እኤአ  ካይሮ ውስጥ ነው፡፡ አቡሻክር የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ዲያቆንና የቅዱሳት መጻሕፍት ደራሲ ነበር፡፡ ከእርሱ መጻሕፍት መካከል በኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ዘንድ እጅግ የታወቀው ‹‹ኪታብ – አት – ታዋሪህ›› የተባለውና የዓለምን ታሪክ በአጭር በአጭሩ የሚገልጠው ‹አቡሻክር፣ ሐሳበ አቡሻክር›› እየተባለ የሚጠራው መጽሐፍ ነው፡፡


ከ1626 እስከ 1630 ዓም ባለው ዘመን መካከል የተጻፈ አንድ አቡሻክር እንዲህ ይላል ‹‹ዝንቱ መጽሐፍ ብሩክ ዘደረሰ እግዚእ ትሩፈ ምግባር ማእምረ መጻሕፍት አቡሻክር ወልደ አቡእልከረም ጴጥሮስ መነኮስ እብንልመሐድብ ዘበትርጓሜሁ ወልደ ግሡጽ ወእመአኮ ወልደ ምሁር ዘእሙር በሪሺ ዘተሠይመ ዲያቆነ በቤተ ክርስቲያን ዘመዐልቃ፡፡ እንዘ ይነግር በእንተ ሐሳበ ዐለም፡፡››

የዐረብኛው መጽሐፍ የተጻፈው በ1250 ዓም ነው፡፡ በኢትዮጵያ አንድ የብራና መጽፈፍ ላይ መጽሐፉ የተጻፈው በ6750 ዓመተ ዓለም፣ በ655 ዓመተ ተንባላት (በእስልምና አቆጣጠር) መሆኑን ይገልጣል፡፡ ይህም በ1250 ዓም መሆኑን ያመለክታል፡፡


10.     በአርመንኛ የሚገኙ ቁጥሮች ትርጉም፡- ይህ መጽሐፍ እስካሁን አልተገኘም፡፡ የተጻፈው በ11ኛው የደብረ ሊባኖስ እጨጌ በአቡነ ዕንባቆም የመናዊ ነው፡፡ ከስሙ ለመገመት እንደሚቻለው የአርመንኛ ቁጥሮችን ኮድ የሚተረጉም ይመስላል፡፡ ስለ መጽሐፉ ፍንጭ የሰጠን አልቫሬዝ ነው፡፡


11.       የላቲን ቃላት ዝርዝር፡- ይኼኛውም መጽሐፍ የዕንባቆም መጽሐፍ ነው፡፡ እስካሁን ግን አልተገኘም፡፡ ከስሙ ለመገመት እንደሚቻለው የላቲን ቃላትን የሚዘረዝርና የሚተረጉም ይመስላል፡፡ አልቫሬዝ ዕንባቆም ላቲን እንደሚችል ይነግረናል፡፡ ምናልባትም ጥንታዊ መዝገበ ቃላትም ይሆናል፡፡


12.     በሮማን ዘየ(dialect) የተጻፉ ቁጥሮች ትርጉም፡- ይህ መጽሐፍ የዕጨጌ ዕንባቆም መጽሐፍ ሲሆን የሮምን ቁጥሮችን መንፈሳዊ/ የኮድ ትርጉም የያዘ ይመስላል፡፡ መጽሐፉ እስካሁን አልተገኘም፡፡


13. ዮሐንስ መደብር፡- ይህ መጽሐፍ በግእዝ ሊቃውንት ዘንድ እጅግ የታወቀ የታሪክ መጽሐፍ ነው፡፡ ዲያቆን ቅብርያል በ16ኛው መክዘ የነበረ ግብጻዊ ነው፡፡ ዐረብኛና ግእዝ ይችል ነበር፡፡ በሠራዊቱ አለቃ በአትናቴዎስና በእቴጌ ማርያም ሥና ትእዛዝ ‹‹ዮሐንስ መደብር›› የተሰኘውን የነቅዩስ ጳጳስ የዮሐንስን መጽሐፍ በ1594 ዓም በዐፄ ያዕቆብ ዘመን በአራተኛው ዓመት ተርጉሟል፡፡


በአንድ መጽሐፍ መጨረሻ ላይ እንዲህ ይላል ‹‹ወተርጎምና በአስተሐምሞ ብዙኅ ለዝንቱ መጽሐፍ እም ዓረቢ ለግእዝ አነ ምስኪን ምኑን በኀበ ሰብእ ወትኁት በውስተ ሕዝብ ወዲያቆን ቅብርያል ግብጻዊ ወልደ ሰማዕት ዮሐንስ ዘቀልዩቢ በትእዛዘ አትናቴዎስ ሊቀ ሠራዊት ዘኢትዮጵያ፡፡ ወበትእዛዘ ንግሥት ማርያም ሥና››


14. አንጋረ ፈላስፋ፡- ይህ የተለያዩ ፈላስፎችን አነጋገር የያዘ መጽሐፍ ነው፡፡ የአሪስቶትል(አርስጣጣሊስ)፣ የፕሉቶ (አፍላጦን) የሶቅራጥስ ና የሌሎችንም ፈላስፎች ንግግሮች ይዟል፡፡ መጽሐፈ ፈላስፋ ጠቢባን በመባልም ይታወቃል፡፡


15. ሐተታ ዘርዐ ያዕቆብ አኩስማዊ ወወልደ ሕይወት እንፍራንዛዊ፡- ይህ የ17ኛው መክዘ ኢትዮጵያዊ የፍልስፍና መጽሐፍ ሲሆን በሁለት ኢትዮጵያውያን የተዘጋጀ ነው፡፡ ዘርዐ ያዕቆብ በተባለ የአኩስም ተወላጅና ወልደ ሕይወት በሚባል የጎንደር (እንፍራንዝ) ተወላጅ፡፡ ሁለቱን ያገናኛቸው አመለካከት ነው፡፡ ዘርዐ ያዕቆብ በወቅቱ ይታሰብ ከነበረው የእምነት፣ የባሕልና የአስተዳደር አስተሳሰብ ወጣ ብሎ ነገሮችን በሰላ ዓይን ይመረምር ነበር፡፡ ደቀ መዝሙሩ ወልደ ሕይወትም ይህንኑ መሥመሩን ተከትሎታል፡፡


16. መጽሐፈ ማስያስ፡- አባ ማስያስ በጣና ገዳማት በ15ኛው መክዘ የነበሩ ኢትዮጵያዊ መነኮስ ናቸው፡፡ ስለ ዓለም ነገር ማወቅ ይፈልጉ ነበር፡፡ ይህንንም በጾምና በጸሎት ከፈጣሪያቸ&#481

አሁን በኢትዮጵያ ባለው በቋንቋ ላይ ብቻ የተመሰረተ፣ የብሄረሰብ ፌዴራል አወቃቀርን በተመለተ ከሶስት የኦሮሞ ምሁራን ጋር የአሜሪካን ድምጽ ራዲዮ ያደረገው መደመጥ ያለበት ዉይይት !

ዛሬ ከአገራችን አውራ ችግሮች መካከል ዋናው፣ የተደጋገሙ ውሸቶች ዕውነት የመሰሏቸው ቡድኖች የሚያጎኑት በጥላቻ ላይ የተመሠረተ የዘር ፖለቲካ እና አንድን ነገድ፣ በኢትዮጵያ ተፈጠሩ ለሚባሉ ችግሮች ሁሉ ተጠያቂ የሚያደርገው ነው ብዬ አምናለሁ። አይደለም የሚለኝ ከመጣም የሚለውን ለመስማት ዝግጁ ነኝ። የተደጋገሙ ውሸቶች ሀውልት ሲያስቆሙ እያዬን ነው። የአኖሌን ሀውልት ለአብነት መመልከት ነው። የከተሞችን ስም ሲያስለውጥ እያዬን ነው። አዲስ አበባን […]

ነገረ ኢትዮጵያ የግንቦት 20 ልዩ እትም ጋዜጣዋ የግንቦት 20 ‹‹ፍሬዎች›› ተዳሰውባታል፡፡

በተለያየ ምክንያትጋዜጣዋን ኮፒ በዕለቱ ያላገኛችሁ ይኸው መረጃ ይደርሳችሁ ዘንድ በፒዲ ኤፍ ለቀናታል
PDF ያንብቧት!

ታምራት ታረቀኝ የግንቦት 20 ሰለባ የሆኑትንና ሐኪም አጥተው የሞቱትን እውቁን ሐኪም ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ያስታውሰናል፡፡
የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ስለ ግንቦት 20 ፍሬዎች የራሳቸውን እይታ ገልተውባታል፡፡
የመኢአድ ፕሬዝደንት አቶ አበባው መሃሪ፣
የሰማያዊ ፓርቲ ም/ሊቀመንበር አቶ ስለሽ ፈይሳ፣
የአረና የህዝብ ግንኙነት አቶ አብርሃ ደስታ
እንዲሁም የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ ሰሎሞን ስዩም ስለ ግንቦት 20 ይናገሩባታል፡፡
አቶ ታዴዎስ ታንቱ የግንቦት 20ን እንክርዳድ ለመመንገል ስለሚያስችለው ስልት ጽፈውባታል፡፡
ሰንደቅ አላማውና ግንቦት 20፣ ግንቦትና ግንቦታውያን፣ ግንቦት 20 የበላቸው ቀሽ ገብሩዎች፣ ግንቦት 20 እና ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ ነጻነት….እና በርካታ ጉዳዮች ተዳስሰውበታል፡፡
መልካም ንባብ!

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

በርሊን-ጀርመን የሚሩ ኢትዮጵያዉን ባንፃሩ ኢሕአዴግ ሥልጣን የያዘበትን ሃያ ሦስተኛ ዓመት በተቃዉሞ ሠልፍ ዘክረዉታል። ሠልፈኞቹ ባለፉት ሃያ ሦስት ዓመታት የኢትዮጵያዉን ሰብአዊ መብት መረገጡን፤

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ሐይለ ማርያም ደሰለኝ ዛሬ አዲስ አበባ ስታዲዮም በተከበረዉ በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር «አሸባሪ» ያሏቸዉን ግንቦት ሰባት፤ኦነግ፤ ኦብነግንና የኤርትራ መንግሥትን አዉግዘዋል።

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ እ.ኤ.አ ሜይ 2/2014 ቢቢሲ/BBC እንደዘገበው በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ እንደመዥገር ተጣብቆ የሚገኘው ገዥ አካል የጸጥታ ኃይሎች ከመናገሻ ከተማዋ ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ በኩል በ80 ማይሎች ርቀት ላይ በምትገኘው የአምቦ ከተማ ላይ ቢያንስ 47 የዩኒቨርስቲ እና የሁለተኛ …

በኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ የሚፈፀመው ኢሰብአዊ ወንጀል Read more »

በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ መሠረት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚመራው በቅዱስ ሲኖዶስ በተሾመ ኤጲስ ቆጶስ ወይም ሊቀ ጳጳስ እንጂ በፓትርያርኩ የምደባ ምክረ ሐሳብ አለመኾኑን በመጥቀስ ነው ጥያቄአቸው ተቀባይነት ሳያገኝ የቀረው፡፡ ከዚህም ባሻገር የብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ከሓላፊነት መልቀቅ ምክንያታዊ ማብራሪያ እንደሚያስፈልገው ምልዓተ ጉባኤው ፓትርያርኩን በማሳሰቡ ለአ/አበባ ሀ/ስብከት የሊቀ ጳጳስ ምደባ አልተደረገም፡፡ ምልዓተ ጉባኤው ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በሓላፊነታቸው …

መስፍን ማሞ (ሲድኒ-አውስትራሊያ)

ለቀደሙት የተባለውን ሰምታችዃል……… ይህም ተፅፏልና!

ለምትበልጠው ፀጋ ቅኑ። እኔም ዳግመኛ እጅግ የበለጠ ሌላ ጎዳና አሳያችዃለሁ፤ በሰዎች ሁሉ ቋንቋና በመላእክት ቋንቋ ብናገር፤ ትንቢትም ብናገር፤ የተሰወረውን ሁሉና የጥበብን ሥራ ሁሉ ባውቅ፤ ተራራም እስካፈልስ ድረስ ሃይማኖት ቢኖረኝ፤ ያለኝንም ሁሉ ለድሆች ባበላ፤ ዳግመኛም ሥጋዬን ለእሳት ቃጠሎ ብሰጥ፤ ፍቅር ከሌለኝ የተጠቀምሁት የለም። ፍቅር ያለው ሰው ሩህሩህ ትዕግስተኛም ነውና።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በአምቦ ከተማና በሌሎች የኦሮምያ ክልል ውስጥ የዩኒቭርሲቲዎችና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ያቀረቡት ሕገ-መንግሥታዊ ጥያቄ ያገኘው ምላሽ በጨካኙ የአግዓዚ ጦር አልሞ ተኳሾች በጥይት መደብደብን ስለሆነ፣ ይህንን አሰቃቂ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ፣ ያውም ዛሬ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሰብአዊ መብት መከበር ግምባር ቀደም መመሪያ ሆኖ በዓለማችን ላይ በገነነበት ጊዜ በመፈፀሙ፣ ወንጀለኞች ከተጠያቂነት ሊያመልጡ አይችሉም። ይህንን የተገነዘበው የባእዳንን ዓላማዎች ለማስፈፀም በጫንቃችን […]

 

በአዲስ አበባ የመካከለኛው ምሥራቅ የዜና ወኪል – ሜና ዘጋቢ የነበረውን ሃምዲ ኤል-አናኒን የኢትዮጵያ መንግሥት ማባረሩን የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ከኢትዮጵያ በኩል ግን በጉዳዩ ላይ እስከአሁን የተሰማ አስያየት የለም፡፡
ይፋ ያልሆነ አስተያየት የሚሰጡ አንዳንድ ባለሥልጣኖች ግን ግብፃዊው ጋዜጠኞ “ከመጣበት ዓላማ ውጭ ሲንቀሣቀስ ተገኝቷል” እያሉ ነው፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የእስክንድር ፍሬው አጭር ዘገባ ያዳምጡ፡፡

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ትናንት ቡራዩ ከተማ ፍርድ ቤት ቀርቦ በ500 ብር ዋስ እንዲፈታ ትዕዛዝ ተሰጥቶለት የነበረውን የፖለቲከኛና ደራሲ አስራት አብርሃምን የዋስ መብት አላከብርም በማለት ያሰረው የከተማይቱ ፖሊስ ከቅርብ ሰዓታት በፊት አስራትን በዋስ መልቀቁን ለሰላማዊው ታጋይ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ተናግረዋል፡፡ አስራ ለእስራት የተዳረገው የመድረክ ሰላማዊ ሰልፍን ለመቀስቀስ በቡራዩ የከተማ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አስራ ሁለት ሰዎች በመታሰራቸው ለጥየቃ ባመራበት እንደነበርና ፖሊስም […]

ባለፈው እሁድ በ 28 ቱ የአውሮፓው ሕብረት አባል ሃገራት የተካሄደው ምርጫ ውጤት ፣በአንዳንድ ሃገሮች፤ መራጩ ህዝብ ፣ በሥልጣን ላይ ያሉትን ፓርቲዎች ለማስጠንቀቅ የወሰደው እርምጃ ተደርጎ ሲወሰድ ፤ ከዚያ የባሰ መዘዝ ይኖረዋል

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በመካከለኛው ምሥራቅ ያካሄዱትን የሦስት ቀናት ጉብኝት አጠናቀው ወደ ቫቲካን ተመለስዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጉብኝታቸውን የጀመሩት ባለፈው ቅዳሜ በዮርዳኖስ ነበር። ከዚያም በነጋታው

እአአ ከ 1967 ዓም እሥራኤል የያዘችው የምዕራብ ዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ የእሥራኤል እና የዮርዳኖስን የግዛት ክልል የሚለይ ወሰን ሆኖ ከመታወቁ በተጨማሪ የእሥራኤል የመከላከያ ሠራዊት የምሥራቅ እዝ የጦር ሠፈርም ሆኖ ያገለግላል።

ከግንቦት ፭ – ፲፱ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ለ16 ቀናት የተካሔደውን የምልዓተ ስብሰባ ውሳኔዎች በ17 ነጥቦች የዘረዘረውና ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ላይ የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በፓትርያርኩ ቢነበብም የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ በማኅበረ ቅዱሳን መተዳደርያ ደንብ ላይ የተጀመረው ውይይት ቀጥሎ ውሳኔ እንደሚያሳልፉ ተናግረዋል፡፡ በመግለጫው ተ.ቁ.(12) ላይ የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደርያ ደንብ ማሻሻያ ረቂቅ በተመለከተ በ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. …

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ) እንደሚታወቀው የግንቦት 2ዐን 23ኛ ዓመት ለማክበር ጉድ ጉድ እያለ የሚገኘው ገዥ ፓርቲ ወደ ጠቅላይ አምባገነን ፓርቲነት ከተለወጠ ብዙ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በ1983 ዓ.ም ሀገሪቱን ከመቆጣጠራቸው በፊት በርካቶች ስለ ነፃነት፣ እኩልነት፣ ሰብአዊ መብት መከበርና ዴሞክራሲ ሥርዓት መስፈን ክቡር ህይወታቸውን እንዲገብሩ ተደርጎ በተገኘ የዜጎቻችን መስዋእትነት መንበረ […]

ከግንቦት 9 እስከ 11 ቀን ድረስ በትግራይ ክልል አኩስም ከተማ ‹ሀገር አቀፍ የግእዝ ዐውደ ጥናት ተደርጎ ነበር፡፡ ይህ በዓይነቱ በሀገር ዐቀፍ ደረጃ ሲዘጋጅ የመጀመሪያ የሆነው ዐውደ ጥናት የትግራይ ክልል ባሕል ቱሪዝም ኤጀንሲ ከፌዴራል ባሕል ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመሆን ያዘጋጀው ነበር፡፡




የክልሉ ባሕል ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊዎች እንደገለጡት ይህ ዐውደ ጥናት በትግራይ ክልል ደረጃ ሲከናወን ለስድስተኛ ጊዜ ነው፡፡ የዘንድሮውን ልዩ የሚያደርገው በሀገር አቀፍ ደረጃ መከናወኑ ነው፡፡ በዚህ ጉባኤ ላይ ከጎንደርና ከሌሎችም አካባቢዎች የተጋበዙ ጉምቱ ጉምቱ ሊቃውንት የተገኙ ሲሆን እስከ ዛሬ ትውፊታውያን ሊቃውንት እንዲህ በብዛትና በዓይነት ተገኝተው ከዘመናውያን ምሁራን ጋር ሲገናኙ ዕድል ገጥሞኝ አያውቅም፡፡ በዚህም የክልሉ ባሕል ቱሪዝም ኤጀንሲና የፌዴራሉ ባሕል ቱሪዝም ሚኒስቴር ተመስጋኞች ናቸው፡፡

ከልዩ ልዩ ቦታ የተጋበዙ ምሁራንና ሊቃውንት

ከተለያዩ ዩኒቨረሲቲዎች ባለሞያዎች እንዲጋበዙ፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም እንዲገኙ መደረጉ፤ መርሐ ግብሩ ግንቦት 11 ከሚከበረው የቅዱስ ያሬድ በዓል ጋር እንዲሠምር መደረጉ፣ ለበዓሉም የተሰጠው ቦታ ሊቃውንቱ ሁሉ ቅኔ ሲያዘንቡበት የዋሉት ጉዳይ ነው፡፡ ቅኔ ልብስ ቢሆን ኖሮ የክልሉና የፌዴራሉ ቢሮዎች እስከ እድሜ ልካቸው የሚሆን ልብስ በሁለቱ ቀን ጉባኤ ያገኙ ነበር፡፡ በበዓሉ መጨረሻ የሐን፣ ማይ ኬራህንና ሙራደ ቃልን ለመጎብኘት መርሐ ግብር መዘጋጀቱ ዝግጅቱን ሙሉ አድርጎት ነበር፡፡

በዐውደ ጥናቱ ላይ ልዩ ልዩ ጽሑፎች ቀርበው ነበር፡፡

ዶ/ር ሥርግው ገላው፣ ፕ/ር ባየ ይማም እና ዶ/ር ኃይሉ ሀብቱ

የግእዝ ሥነ ጽሑፍ ሀብት ለኢትዮጵያ ቋንቋዎች ያበረከተው አስተዋጽዖ(ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም)፣ የግእዝ ጥናት ከጥንት እስከ ዛሬ(ዶ/ር አምሳሉ ተፈራ)፣ የግእዝ ቅኔያት ይዘትና ቅርጽ (ዶ/ር ሥርግው ገላው)፣ የ‹‹ትቤ አክሱም መኑ አንተ›› መጽሐፍ ትንታኔ(ዶ/ር ኃይሉ ሀብቱ)፣ በግእዝ ቋንቋ የተጻፉ ሃይማኖታውያን ያልሆኑ መጻሕፍት (ዳንኤል ክብረት)፣ ግእዝና ቅዱስ ያሬድ(መ/ር ተስፋይ ሀደራ) ቀርበው ነበር፡፡ 
መ/ር ደሴ ቀለብ፣ ዶር ታየ አሰፋ እና ዶ/ር አምሳሉ ተፈራ

በመጨረሻም ለወደፊቱ የግእዝ ዓመታዊ ዐውደ ጥናት በምን መልኩ መቀጠል እንዳለበት፣ ግእዝ በሀገር ፖሊሲ ደረጃ እንዴት ሊታቀፍ እንደሚገባው፣ ልዩ ልዩ አካላት ስለሚኖራቸው ድርሻ ሰፊ ውይይት ተደርጎ ነበር፡፡
መሪጌታ ልሳነ ወርቅ ገብረ ጊዮርጊስ

ክልሉም ሆነ የፌዴራሉ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ግእዝን በተመለከተ የያዙት አቋም የሚበረታታና የሚደገፍም ነው፡፡ ግእዝ የሀገሪቱ የእምነት፣ የባሕል፣ የዕውቀት፣ የሥራ፣ የዲፕሎማሲ፣ የፖለቲካ፣ የፍልስፍና፣ የኢኮኖሚና የማኅበራ ግንኙነት ቋንቋ ሆኖ ከ2000 ዓመታት በላይ በመኖሩ በውስጡ የያዛቸውን ዕውቀቶች ፈትሾ ለሀገር ጥቅም ማዋል ይጋባልና በነካ እጃችሁ ወደፊት ቀጥሉ እንላለን፡፡
የጋዜጠኞችና የአዘጋጆች ቡድን
ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ‹‹የጎረቤት ጠበል የቆዳ መንከሪያ ነው›› ብሎ ነው መሰል የአኩስም ዩኒቨርሲቲ ከተሳትፎ መራቁ ሁሉንም ሰው ያስገረመ ነበር፡፡ ከእርሱ ይልቅ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ በግእዝ ተናግረው በግእዝ የሚያሳምኑ እሳት የላሱ ወጣቶችን ይዞ መጥቶ ያሳየው ተሳትፎ እጅን በአፍ ላይ የሚያስጭን ነበር፡፡ ወጣቶቹ ግእዝ ተምረው በግእዝ አፋቸውን የፈቱ እስኪመስል ድረስ ያቀርቡት የነበረው ዲስኩር ተስፋ የሚያለመልም ነበር፡፡

ፓትርያርኩ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ከጨለማው ቡድንና ፖለቲከኞች ጋራ የመከሩበትን የራሳቸው ያልኾነ ሐሳብና አጀንዳ የተቃወሟቸውን የምልዓተ ጉባኤውን አባላት ‹‹በገንዘብ የተገዛችኹ›› እያሉ በመዝለፍ ቅዱስ ሲኖዶሱን ተዳፍረዋል፡፡ አቡነ ማትያስ ለአጥኚ ኮሚቴው የላኩት ባለ24 አንቀጽ ድንጋጌዎችና ግዴታዎች ሳይቀነሱና ውይይት ሳይደረግባቸው በደንቡ ካልተካተቱና ረቂቁ በሌላ ኮሚቴ ዳግመኛ ካልታየ በሚል አጀንዳውን በራሳቸው አቋም ብቻ ለመቋጨት ያደረጉት ሙከራ በፍጹም አንድነት በቆሙት ብፁዓን …

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በተከተ ከፍተኛ የእሳት አደጋ አንድ የተማሪዎች ማደሪያ ህንፃ መውደሙን የመንግስት ሚድያዎች ዘገቡ። የመንግስት ሚድያዎቹ አደጋውን ቀለል በማድረግ በእሳት አደጋው የተጎዱ ተማሪዎች መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል ቢሉም የአይን እማኞች ግን የሚናገሩት በተቃራኒው ነው። በዩኒቨርሲቲው የተነሳ የእሳት አደጋ ከሌሊቱ 10 ሰዓት እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን የአደጋውን መነሻ ፖሊስ እያጣራሁ ነው ብሏል። እሳቱ በሌሊት በመነሳቱ የተነሳ በመኝታ ላይ […]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዓለም የውድድር መድረክ አሸናፊ ሆነዋል። ዝርዝር ይኖረናል። የዓለም ዋንጫ ዝግጅትን እንዲሁም የኢትዮጵያ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ጨዋታን በተመለከተ ዳሰሳ እናደርጋለን። የሚኪና ሽቅድምድምና ሌሎች ስፖርት ነክ ዜናዎችንም አካተናል።

በትናንትናዉ ዕለት የአዉሮጳ ኅብረት ምክር ቤታዊ ምርጫ ብቻ ሳይሆን የተካሄደዉ፤ ባለፉት ወራቶች ምዕራቡን ዓለም እና ሩስያን ስታወዛግብ የቆየችዉ ዩክሬንም፤ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን አካሂዳለች።

በአንድ ሀገር የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የዜጎች በሰብዓዊ መብት፣ በዲሞክራሲ፣ በፖለቲካ እንዲሁም በማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ላይ ያላቸው ንቃተ ህሊና የሚጫወተው ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው። የሲቪክና የፖለቲካ ማህበራት ፣ የጋዜጠኞችና የነፃ ሚዲያዎች በብዛት መኖር ከሰፊ ተሳትፎ ጋር የማህበረሰብ በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ያለውን ንቃተ ህሊና ማሳደግያ መሆናቸው ዕሙን ነው። ነገር ግን የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታን በበጎ መልኩ አይቶ ከማበረታታት […]

የአወሊያ ትምህርት ቤት ኮሌጅና ሀይ ስኩል መምህራኖች ለትምህርት ቤቱ አስተዳደር ያነሱት የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄን ከአመፅ ጋር በማያያዝ ለኮሚቴዎቹ በመሰከሩ መምህራኖች ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ተገለፀ ። FITH RADIO [ፍትህ ሬዲዮ] ከኑሮው ውድነት ጋር ተያይዞ የሚከፈላቸው ደመወዝ ከእጅ ወደ አፍ የሆነባቸው የአወሊያ ትምህርት ቤት መምህራን ግንቦት 4\2006 በአወሊያ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በመሰባሰብ የአወሊያ […]

ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች