ኦብነግ ኦጋዴን ውስጥ ጥቃት መሠንዘሩን ይናገራል፤ መንግሥት “ኦብነግ የለም” ይላል
የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃአውጭ ግንባር በካሉብ አካባቢ ሰሞኑን በርካታ ጥቃቶች ፈፅሜ ብዙ ጉዳት አደረስኩ ይላል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት ግን የኦጋዴን ነፃ አውጭ ግንባር ብሎ እራሱን የሚጠራው ድርጅት ሕልውናው ያከተመ ነው፤ የተፈፀመ ጥቃትም፣ የደረሰ ጉዳትም የለም ብሏል፡፡
የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃአውጭ ግንባር በካሉብ አካባቢ ሰሞኑን በርካታ ጥቃቶች ፈፅሜ ብዙ ጉዳት አደረስኩ ይላል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት ግን የኦጋዴን ነፃ አውጭ ግንባር ብሎ እራሱን የሚጠራው ድርጅት ሕልውናው ያከተመ ነው፤ የተፈፀመ ጥቃትም፣ የደረሰ ጉዳትም የለም ብሏል፡፡
የዘጠኙ አምደኞችና ጋዜጠኞች ጠበቆች ላቀረቡት የክስ መቃወሚያ አቃቤ ሕግ የበኩሉን ምላሽ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።
ከተከሳሾቹ መሃል ሁለቱ ሴት እሥረኞች ያቀረቡት አቤቱታ የሚመለከተው የማረሚያ ቤት ባለሥልጣን ሳይገኝ ቀርቷል።
ፍርድ ቤቱ የሰጣቸውን ትዕዛዞች ጠቅሶ ዘጋቢያችን መለስካቸው አምሃ ዘግቧል፤ ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
አዋሽ ሞልቶ ባስከተለው መጥለቅለቅ ሳቢያ ከሰላሣ ሺህ በላይ ሰው ተፈናቅሏል፡፡
በሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ፤ ለጊዜው መጠኑ ባልታወቀ ንብረት ላይ ግን ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡
ለውኃ ሙላቱ ምክንያት የሆነው በአካባቢው ደጋማ ሥፍራዎች የጣለውን ከባድ ዝናም ያስከተለው ጎፍርፍ መሆኑ ታውቋል።
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
ጥቅምት ፭(አምት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በአዲስ አበባ ለሚገኙ ዜጎቹ ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ አልሸባብ በቦሌ አካባቢ ጥቃት ለመፈጸም እየተዘጋጀ መሆኑን አስተማማኝ መረጃ እንደደረሰው ገልጿል። ኤምባሲው አዲስ መግለጫ እስከሚወጣ ድረስ ዜጎቹ ከሆቴሎች፣ ምግብ ቤቶች፣ የማምለኪያ ቦታዎች፣ ከገበያ ቦታዎችና የመዝናኛ ቦታዎች እንዲርቁ መክሯል። ጥቃቱ የሚፈጸምበት ትክክለኛ ቦታ ባይታወቅም ፣ የአሜሪካ ዜጎች …
ጥቅምት ፭(አምት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዞን 9 እየተባሉ የሚጠሩት ጸሃፊዎች እና ጋዜጠኞች ፍርድ ቤት ቢቀርቡም ፍርድ ቤት ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት አሰናብቷቸዋል። የተከሳሽ ጠበቆች ላቀረቡት የክስ መቃወሚያ አቃቢ ህግ ምላሽ የሰጠ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ መልስ ለመስጠት ለጥቅምት 25 ቀጠሮ ይዟል። ተከሳሾቹ ነጭ ልብስ ለብሰው መቅረባቸውን፣ በጥሩ መንፈስና ጥንካሬ ላይ የሚገኙ መሆናቸውን ዘጋቢያችን …
ጥቅምት ፭(አምት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰንደቅ እንደዘገበው ማህበሩ ጥቅምት 1 ቀን 2007 ዓ.ም. በአድራሻ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በግልባጭ ደግሞ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ለኾኑት ለሁሉም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ባሰራጨው ደብዳቤ ማህበሩ” በማያውቀው፣ ጥፋትም ካለ ተጠርቶ ባልተጠየቀበትና መልስ ባልሰጠበት ኹኔታ ፓትርያርኩ ባሉባቸውና በተለያዩ ጊዜያት …
የዞን9 ጦማርያኑ እና የወዳጅ ጋዜጠኞች የፍርድ ቤት ውሎ
ከሁለት ወር ቆይታ በኋላ በነሶልያና ሽመልስ የሽብር ወንጀል የክስ መዝገብ ልደታ ፍርድ ቤት የቀረቡት ስድስቱ የዞን9 ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች ቀጠሮ ችሎቱ ከ20 ቀን በኃላ እንዲቀርቡ ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት ተጠናቀቀ።
ፍርድ ቤቱ በዛሬው ውሎው የተከሳሽ ጠበቆች ክሱ ላይ ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ አቃቤ ህግ አይቶ ምላሽ እንዲሰጥበት የተቀጠረ ሲሆን በዚያም መሰረት ለተከሳሽ ጠበቆች የክስ መቃወሚያ አቃቤ ህግ የፅሁፍ ምላሽ ሰጥቷል ።
ፍርድ ቤቱም የጠበቆችን የክስ መቃወሚያ እና የአቃቤ ህግን ምላሽ መርምሮ በክሱ ሂደት ላይ ብይን ለመስጠት ለተጨማሪ ሃያ ቀን ለጥቅምት 25 ቀጠሮ ሰጥቷል።
በተጨማሪም የሴት ተከሳሾችን በጓደኛና በቤተሰብ አለመጎብኘት ተከትሎ ያቀረቡትን አቤቱታ እንዲያስረዳ የማረሚያ ቤቱ እንዲገኝ ጥሪ ቢደረግም አለመገኘቱን እና በፓሊስ በኩል ምላሽ ይዞ መቅረቡን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ በሚቀጥለው ቀጠሮ የማረሚያ ቤቱ ሃላፌ እንዲገኙ ትእዛዝ አስተላልፎ ነበር። ነገር ግን ሴት ተከሳሾች በተለይ ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳየ የመጎብኘት መብት መሰረታዊ መብታቸው በመሆኑ 20 መቆየት እንደማይገባ በመጠየቃቸው ፍርድ ቤቱ የሴት ተከሳሾችን የጉብኝት መብት አስመልክቶ ለማየት ለጥቅምት 11 አጭር ቀጠሮ ሠጥቷል ።
በዛሬው እለት ነጭ በመልበስ የተገኙት ተከሳሾች በመልካም ፈገግታ እና በጠንካራ መንፈስ የነበሩ ሲሆን በፈገግታ ወዳጅ እና ጓደኞቻቸውን ሰላም ሲሉ ተስተውለዋል።
በመጨረሻም የሚቀጥለው ቀጠሮ ለጥቅምት 25 የተወሰነ ሲሆን የሴት ታሳሪዎችን የጉብኝት መብት ጥያቄ አስመልክቶ በጥቅምት 11 ችሎቱ ቀድሞ ይሰየማል ተብሎ ይጠበቃል።
የዞን9 ጦማርያን የክሱን ፈጠራነት፣ የጦማርያኑን እና ጋዜጠኞቹ በመአከላዊ ምርመራ ያለፉበትን የመብት ጥሰት እያስታወስን የፍትህ ስርአቱ የሚታማበትን የፓለቲካ መጠቀሚያነት ክስ ወዳጅ ጋዜጠኞችን እና ተከሳሽ ጦማርያንን በነፃ በማሰናበት ፍርድ ቤቱ ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ እንደሚጠቀምበት ተስፋ እናደርጋለን።
በቅርቡ ሐገሩን ጥሎ ወደ ኬንያ የተሰደደዉ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹርቤ ከትናንት በስተያ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። የጋዜጠኛ ሚሊዮን ባልደረቦች እና ጓደኞች እንደሚሉት ሚሊዮን ያረፈዉ ለሁለት ሳምንት ያሕል ከታመመ በሕዋላ ነዉ።
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
በዓለም ዙሪያ ፣ የዓለም የምግብ ዋስትና ዕለት ታስቦ ይውላል። በኢትዮጵያም በዋዜማው ይታሰባል። ጥቅምት 6 ወይም (Oct 16) የሚታሰበው ፤ በመጪው 2015 ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 70 ዓመት የሚደፍነውን ፣ የተባበሩት መንግሥታትን የምግብና የግብርና ድርጅት ምሥረታ መንስዔ በማድረግ ነው።
በአንድ ሳምንት ዉስጥ ሁለት ጠቅላይ ሚኒስትሮች የተለዋወጡባት የመን ዛሬም የተረጋጋች አትመስልም። ከሰንዓ የሚወጡ የተለያዩ የዜና ወኪሎች ዘገባ እንደሚለዉ በሁቲ አማፅያንና በአልቃይዳ ታጣቂዎች መካከል የተካሄደዉ ዉጊያ ቢያንስ የ12 ሰዎችን ህይወት አጥፍቷል።
በላይቤሪያ የተከሰተው የኤቦላ ወረርሽኝ ታማሚዎችን ብቻ ሳይሆን የጤና መኮንኖችዋን እና ሀኪሞችዋን ጭምር ስጋት ላይ ጥሎዋል። የጤና መኮንኖቹ እና ሀኪሞቹ በኤቦላ የተያዙትን ሰዎች በማስታመሙ ተግባራቸው ላይ
“ልዩነት የግድ ጥላቻን ወይም ድብድብን ማስከተል አለበት ብለው የሚያምን እና የሚያስብ በድርጊቱም የሚገፉ ካለ ከባድ ስዕተት ነው፡፡ ፣ልዩነትን በአንድ ጊዜና ሙሉ በሙሉ ማጥፋት ባይቻልም በሰለጠነና በሰከነ አካሄድ በውይይትና በሀሳብ ልውውጥ ማጥበብ ይቻላል፡፡” ለዚህም ይመስላል አንድነት ፓርቲ ውስጣዊ ችግሩን ሙሉ ለሙሉ ባይባልም መሠረታዊ ችግሩን በሰለጠነ መንገድ ለመፍታት የቻለው፡፡ የዚህም ጥሩ ማመላከቻ የሚሆነው ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው በገዛ […]
ይህ በአቶ ነሲቡ ስብሃት የተፃፈ መጽሓፍ በደርግ ዘመን በኢትዮጵያ በነበረው አረመኔያዊ ሥርዓትና ሥርዓቱን ሲታገል በነበረው ኢሕአፓ የተመራው ቆራጥ ትውልድ መካከል የተካሄደው መራራ ትንቅንቅን በዝርዝር መረጃዎች አስደግፎ ያቀርባል። ስለሆነም፤ በዛን ጊዜ የነበረውን የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ማለት፣ በአንድ በኩል ላገርቷ አንድነት፣ ለህዝቧ ነፃነት፣ ፍትሕና እኩልነት ለመታገል ቆርጦ የተነሣ ትውልድ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የህዝቡን ትግል አጨናግፎ የራሱ ፍላጎት በህዝቡ […]
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ጥቂት አማሳኞች በማንጨብጨብ ሲከተሏቸው፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ጨምሮ ብዙኃን ጉባኤተኞች በድንጋጤና በተደምሞ አዳምጠዋቸዋል፡፡ ፓትርያርኩ በቀቢጸ ተስፋ ውስጥ እንዳሉም አመላካች ኾኗል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን÷ በጉባኤያት፣ በኅትመትና በኤሌክትሮኒክስ የስብከተ ወንጌል ስርጭት፣ በቅዱሳት መካናት ልማት፣ በአብነት ት/ቤቶችና በካህናት ማሠልጠኛዎች ድጎማና ሞያዊ እገዛዎች ያከናወናቸው ተግባራት በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ሪፖርት በስፋት ተዳስሰዋል፤ ጉባኤተኞች ማኅበሩ ላስመዘገባቸው የሥራ ፍሬዎች ደማቅ ድጋፋቸውን ገልጸዋል፡፡ …![]()
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ በጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ የሚካሔደው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ መደበኛ ስብስባ ዛሬ ይጀመራል፡፡ ዘንድሮ ለ፴፫ኛ ጊዜ የሚካሔደው ይኸው ዓመታዊ ስብሰባ፣ ከጥቅምት ፭ – ፯ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. የሚቆይ ሲኾን ከ50 አህጉረ ስብከት የተውጣጡ ከ800 ያላነሱ ልኡካን ይገኙበታል፡፡ የመንበረ ፓትርያርኩ መቀመጫ ከኾነው ከአዲስ አበባ፣ የሀገረ ስብከቱን ተወካዮች ጨምሮ …![]()
በስደት ላይ የሚገኘው የማራኪ መጽሔት ማኔጂንግ ኤዲተር ሚልዮን ሹርቤ ባደረበት ህመም በትላንትናው እለት አረፈ።
ሚልዮን፤ “በኢትዮጵያ መንግስት ወከባ እየደረሰብን ነው፤” ባሉት ወከባ ሳቢያ በቅርቡ ከአገር ተሰደው ወደ ጎረቤት አገሮች ከኮበለሉ የመጽሔት አዘጋጆችና አሳታሚዎች አንዱ ነበር።
ሚልዮን የሕክምና እርዳታ ያገኝ ዘንድ በጓደኞቹ አማካኝነት በቀረበለት ጥያቄ መሠረት እገዛ ያደረገው ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት CPJ የምሥራቅ አፍሪቃ ቢሮ ተጠሪ Tom Rhodes በጋዜጠኝነት ሥራ በተሰማሩበት በሚገጥማቸው ወከባ ሳቢያ አገራቸውን ጥለው ለመኮበልል የሚገደዱ ጋዜጠኞች ብዙዎቹ ለተለያዩ በሽታዎችና ለባሰ እንግልት ይጋለጣሉ፤ ይላል። አንዳንዱ በቀላሉ ሊታከሙ የሚችሉ የበሽታ ዓይነቶች ቢሆኑም እንዲህ እንዳሁኑ የከፋ ውጤት የሚያስከትሉበት ጊዜ ግን…
የተማሩ ናቸው። አገራቸውን የሚወዱ። በሕዝባቸውና በአገራቸው ዉስጥ የሚደረገዉ ግፍ እንዲቆም በጽሁፋቸው የሚመክሩ። ማንም ላይ ጥላቻ የሌላቸው። ኢፍትሃዊነትን የሚጠሉ ። አምባገነንነትን እንጂ ማንንም የማይጸየፉ። በጽሁፋቸው ፍቅርን ሰብከዋል። ነጻነትን አውጀዋል። «ዜጎች እንደ እንስሳ ታስረዉና ታፍነው መኖር የለባቸውም። ነጻነታቸውና ስብእናቸው ሊጠበቅላቸው ይገባል» እያሉ ተከራክረዋል። ለሰብአዊነት ተሟግተዋል። ሰው ሲከብር እንጂ ሲዋረድ፣ ሲነሳ እንጂ ሲወድቅ፣ ሲድን እንጂ ሲሞት፣ ሲበለጸግ እንጂ […]
ጥቅምት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ50 በላይ የመንግስት ፖሊሶች፣ ወታደሮችና ታጣቂዎች የተገደሉበት የደቡብ እና ጋምቤላ ድንበሮች አዋሳኝ በሆነው ጉራፈርዳ ወረዳ አካባቢ የተጀመረው ግጭት ወደ ጋምቤላ ከተማና አቦቦ ወረዳ መዛመቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። ትናንት ምሽት በጋምቤላ ከተማ በተነሳ ግጭት ከ3 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ ዛሬ ከተማዋ በመከላከያና ፖሊሶች ተወራለች። የመንግስት ስራና ትምህርትቤቶች ዝግ ሆነው …
ጥቅምት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ የተነሳ የአዋሽ ወንዝ በመሙላቱ በአሚባራና ዱላሳ ወረዳዎች ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች ገለጹ። ነዋሪዎች እንደሚሉት በአሚባራ አካባቢ ከ5 ሺ ሄክታር በላይ የታረሰ መሬት መውደሙን፣ የ7 ቀበሌ ሰዎች በውሃ መከበባቸውንና ንብረታቸው በውሃ መወሰዱን እንዲሁም አንድ የእርሻ ምርምር ማእከል በውሃ መወሰዱን ገልጸዋል። እስካሁን የሞቱ …
ጥቅምት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሳምንታት የችሎት መቋረጥ በሁዋላ ስራ የጀመረው ፍርድ ቤቱ፣ አንድ ምስክር እንካ በአግባቡ ሳያዳምጥ መብራት ሄደ በሚል ምክንያት እንዲቋረጥ መደረጉን ገልጿል። ሰኞ በነበረው ችሎት አቶ አህመድ ኡመር የተባሉ ምስክር እየተናገሩ ባለበት ጊዜ ምስክርነታቸው ሳይጠናቀቅ መብራት በመሄዱ ለማክሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ቢሰጥም ዛሬ ማክሰኞ በተመሳሳይ ሁኔታ ችሎቱ ሳይካሄድ መቅረቱን ድምጻችን ይሰማ …
ጥቅምት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-“ህገመንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርአቱን በሃይል ለማፍረስ ” በሚል ወንጀል የተከሰሰው እውቁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ከተባለ በሁዋላ፣ ውሳኔውን በእስር ላይ ሆኖ እንዲሰማ ፍርድ ቤት ባዘዘው መሰረት ወደ እስር ቤት ተልኳል። ጋዜጠኛ ተመስገን የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በመሆን ሲሰራ ” ድህረ ምርጫ 1997 ዓምን ተከትሎ ህገመንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን …
ጥቅምት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ለ3 ወታደራዊ አዛዦች የሌተናል ጄኔራል ማእረግ ሲሰጥ ለቀሪዎቹ ደግሞ የሜጀር ጄኔራል መእረግ ሰጥቷል። ማእረጉ ከተሰጣቸው ጄኔራሎች ውስጥ 4ቱ የትግራይ አንዱ የአማራና አንዱ የኦሮሞ ተወላጅ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ መኮንኖቹ ባስመዘገቡት ውጤት ማእረግ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል። ግንቦት7 ከአራት አመት በፊት ያወጣውን የወታደራዊ መኮንኖች የብሄር ተዋጽኦ ጥናት ክለሳ መሰረት …
ዘወትር ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ኢትዮጵያና ኤርትራ ውስጥ ለሚገኙ አድማጮች በአማርኛ የሚተላለፉ ዜናዎች፣ ቃለመጠይቆችና ሌሎችም ትኩስ ዘገባዎች፤ እንዲሁም በባሕል፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በቤተሰብና በወጣቶች፣ በፖለቲካ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በተፈጥሮ አካባቢ፣ በሣይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በስፖርት፣ በሌሎችም አካባቢያዊና የመላ አፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መደበኛ ዝግጅቶች የተካተቱባቸው የአንድ ሰዓት ዕለታዊ ሥርጭቶች
የኢትዮጵያ መንግሥትን መርሕና አሠራር የሚተቹ መጣጥፎችን በማፃፍና በማሳተም የሚታወቀዉ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ታሰረ።
የሴቶችና እናቶችን የስነተዋልዶ ጤና ለማሻሻል ከሚረዱ እንቅስቃሴዎች አንዱ ነፍሰ ጡር እናቶች በሚገላገሉበት ጊዜ በተገቢዉ መንገድ በሰለጠኑ አዋላጆች መረዳት መቻላቸዉ ነዉ። ይህን እድል ያላገኙና የማያገኙ ደግሞ በተራዘመ ምጥ ምክንያት ለፊስቱላ ተጋልጠዉ የከፋ ህይወት ለመግፋት ይዳረጋሉ።
በርካታ አፍሪቃዉያን ወደ አዉሮጳ ለመሰደድ በባሕር ሙከራ ሲያደርጉ ብዙዎች ሰምጠዉ የደረሱበት እንኳ የማይገኘዉ ቁጥራቸዉ የትየለሌ ነዉ።
ኢትዮጵያ በመጪው ጥር ወር መጀመሪያ ላይ የዓለም የካፒታል ገበያን እንደምትቀላቀል ሮይተርስ የገንዘብ ሜኒስቴር ቃል አቀባይን ጠቅሶ ባለፈዉ ሳምንት ዘግቧል። ውሳኔው መንግስት የሚያከናውናቸውን የመሰረተ-ልማት ግንባታዎች ለመደገፍ የሚያስችል
የኢትዮጵያ ሴቶች ማሕበራት ቅንጅት ሶስት መቶ ገጾችን ያካተተ በፎቶግራፎች የተደገፈ መጽሐፍ አሳትሞ አስመርቆአል። መጽሐፉ ሴቶች ከጥንት ጀምሮ በኢትዮጵያ
የኢቦላ በሽታ ከምዕራብ አፍሪካ እስከ ሰሜን አሜሪካ ድረስ ዓለምን እያተራመሰ ነው። በተኅዋሲው የተያዘ ሰው ከከስድስት እስከ አስራ ስድስት ባሉ ቀናት ዉስጥ ከታደለ ከህመሙ ይፈወሳል።አብዛኞቹ ግን ይሞታሉ። ለዓለም ሰላምና መረጋጋት ጠንቅ ነው የተባለው የኢቦላ ወረርሽኝ በተባበሩትመንግስታትድርጅትየአስቸኳይጊዜግብረ-ሃይል ተቋቁሞለታል።
ጥቅምት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ባለፈው ቅዳሜና እሁድ የፌደራል ፖሊሶችን ልዩ ሃይልንና መከላከያን ባቀፈው የመንግስት ጦርና፣ መሳሪያ በታጠቁ የብሄረሰቡ ተወላጆች መካከል በተደረገው ውጊያ ከ40 በላይ የፌደራል ፖሊስ አባላትና ከ10 ያላነሱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ 4 ታጣቂ ሚሊሺያዎችና 3 የወረዳ ፖሊሶች ተገድለዋል። የሟቾቹ አስከሬን በሚዛን አማን ሆስፒታል እንዲገባ ከተደረገ በሁዋላ፣ ዘመድ ያላቸው …
ጥቅምት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊ ክልል በፕሬዚዳንቱና በ7 የስራ አስፈጻሚ አባላት መካከል ተፈጥሮ የቆየውን ውዝግብ ለመፍታት ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሁሉንም ወገኖች አዲስ አበባ ቢጋብዙም፣ ፕሬዚዳንቱ አቶ አብዲ ሙሃመድ የጠ/ሚሩን ጥሪ ውድቅ በማድረግ የራሳቸውን ጉባኤ በመጥራት አዲስ የስራ አስፈጻሚዎችን ሾመዋል። ባለፈው መስከረም 24 ቀን በፊቅ ከተማ በተደረገው ጉባኤ፣ ፕሬዚዳንቱ የራሳቸውን ደጋፊዎችና ዘመዶቻቸውን በስራ …
ጥቅምት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሚሰጡት ደካማ አመራር ከፍተኛ ትችት ሲድርስባቸው የቆዩት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው ፣ ስልጣን በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ካሳወቁ በሁዋላ የብሄራዊ ምክር ቤት አባላት ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩትን አቶ በላይ ፈቃዱን ሊቀመንበር አድርጎ ሾሟል። ኢ/ር ግዛቸው በተመረጡ በወራት ውስጥ በርካታ የስራ አስፈጻሚ አባላት በመሪው አመራር ደስተኛ ባለመሆን ራሳቸውን ከሃላፊነት አግለለው …
ጥቅምት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአስተዳደሩ የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ጽ/ቤት ቅዳሜ ዕለት ይፋ ባደረገው የጨረታ ውጤት መሠረት በቦሌ ክፍለከተማ ለአንድ ካሬሜትር መሬት ቦታ አሸናፊ የሆነው ግለሰብ ለካሬሜትር 55ሺህ 597 ብር ከ65 ሳንቲም የሰጠ ሲሆን ግለሰቡ አሸናፊ የሆኑበት 403 ካሬሜትር ገንዘብ ሲሰላ 22 ሚሊየን 405ሺህ 852 ከ95 ሳንቲም ሆኗል፡፡ በዚሁ ክፍለከተማ ለጨረታ ከቀረቡት 38 …
ጥቅምት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና ወስደው የውሎ አበል ያልተከፈላቸው የመጀመሪያ አመትና ነባር ሶስተኛ ዙር ሰልጣኞች ‹‹የውሎ አበላችን ይሰጠን›› በሚል ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣታቸው በትናንትናው ዕለት በፌደራል ፖሊስ መደብደባቸውን ተማሪዎቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ሰላማዊ ሰልፉን አደራጅታችኋል የተባሉ በርከት ያሉ ተማሪዎች መታሰራቸውንም ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ስልጠናው አርብ መስከረም 30/2007 ዓ.ም የጨረሱት ተማሪዎች …
የዓለም ባንክ ለሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ጉዳይ ቅድሚያ እንዲሰጥና ተጠያቂነትም እንዲኖረው ያሳሰቡ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ የሆኑ እንዲሁም የሌሎችም ሃገሮች ሰልፈኞች ከትናንት በስተያ ቅዳሜ ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው የባንክና የዓለምአቀፉ የገንዘብ ተቋም – አይኤምኤፍ ጠቅላይ መሥሪያ ቤት ፊት ለፊት የተቃውሞ ጥሪ አሰምተዋል፡፡
ሰልፈኞቹ የዓለም ባንክ ለሰብዓዊ መብቶችና ለተፈጥሮ ጥበቃ ቅድሚያ እንዲሰጥ፣ አምባገነን መንግሥታትን እንዳይረዳ፣ መፈናቀልና የሰብዓዊ መብቶች ረገጣዎችን የሚፈፅሙ ፕሮጀክቶችን እንዳይደግፍ ጠይቀው ፅህፈት ቤቱን እየዞሩ መፈክሮቻቸውን አሰምተዋል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
Protests against the WB
UDJ leadership change