ከ400 አመታት በፊት ከዚህ አለም በሞት የተለየው እንግሊዛዊው ባለቅኔ ዊሊያም ሼክስፒር የራስ ቅል ከመቃብሩ ውስጥ ባልታወቁ ዘራፊዎች መሰረቁ በአርኪዎሎጂስቶች ጥናት መረጋገጡን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ  ዘገበ፡፡እንግሊዛውያን ተመራማሪዎች በስታንፎርድ የቅዱስ ስላሴ ቤተክርስቲያን ውስጥ በሚገኘው የዊሊያም ሼክስፒር መቃብር ላይ ባደረጉት የራዳር ፍተሻ፣ የባለቅኔው …

የእንግሊዛዊው ባለቅኔ ዊሊያም ሼክስፒር የራስ ቅል ከመቃብሩ መዘረፉ ተረጋገጠ Read more »

አድዋ – “ያባከንነው ድላችን!” (ባዩልኝ አያሌው) ይህች ሀገር ብዙ የተከፈለባት ምድር ናት! ለውድቀቷ የተጉ የመኖራቸውን ያህል፣ ብዙዎች ሕይወታቸውን ከፍለው ለዛሬ ያበቋት ሀገር ናት፡፡… እኒህ ባለውለታዎቿ ሰው እንደመሆናቸው፣ የሰው ልጅ በዘመኑ የሚፈጽመውን ስህተት የፈጸሙ ቢሆን እንኳን፣ እናት ላሏት ኢትዮጵያ የከፈሉት ዋጋ …

አድዋ – “ያባከንነው ድላችን!” (ባዩልኝ አያሌው ) Read more »

እንደ መግቢያ አንዳንድ የፍልስፍና መጻህፍት፤ ‹‹እውነት ምንድን ናት?›› በሚለው ጥያቄው ጲላጦስን ያወሱታል፡፡ እነዚህ መጻሕፍት፤ ‹‹መጠየቅ የሚገባውን ወሳኝ የፍልስፍና ጥያቄ አነሳ›› በሚል ስሙን ያነሱታል እንጂ፤ስለ ጲላጦስ ህይወት የሚነግሩን ነገር የላቸውም፡፡ የሮማ ኤምፓየር ታሪክን የሚዳስሱ መፃሕፍት፤ከምሥራቃዊው የሮማ ግዛት እና ከኢየሱስክርስቶስ ጋር አያይዘው …

ከክርስቶስ ሞት ጀርባ ያልተነበቡ የሄሮድስና ጲላጦስ ደብዳቤዎች (ተፈሪ መኮንን) Read more »

ጥንታዊው የኢትዮጵያ ታሪክ ሲነሳ ‹‹የሦስት ሺሕ ዓመት›› የሚለው ጎልቶ ይሰማል፡፡ የሥልጣኔው መንደርደሪያ ከአክሱም ዘመን ሲያልፍም የይሓ እና የደአማት ሥርወ መንግሥትም ይጠቀሳሉ፡ከሦስት ሺሕ ዘመን ጋርም የንግሥተ ሳባና የልጇ ቀዳማዊ ምኒልክ ታሪክ ይነሳል፡፡ በምሥራቅ ትግራይ የቀድሞው ዓጋመ አውራጃ ዋና ከተማ ዓዲግራት በሰሜን …

የኢትዮጵያን ጥንታዊ ታሪክ ከአራት ሺሕ ዓመታት የሚያዘልለው ግኝት – (ሔኖክ ያሬድ ) Read more »

ጌታዬ! ላንተ ያለኝ ፍቅር ላንተ ያለኝ ክብር ምን ያህል እንደሆን… ተወው አልነግርህም ብትሆንም ኩራቴ ምስጢር አርጎት ይቆይ ልጉም አንደበቴ። ስላንተ ‘ሚያወራ የሚናገር አፌ ሰውን ካበሳጨ የፍቅሬ ጥግጋት በቃላት ተሰፍሮ በክፉ ካሳጨ ይቅር አልነግርህም…… እስካልቆረቆረኝ የተፈናጠጥኩት የፍቅርህ ኮርቻ ዝም………… ብዬ ልውደድህ …

*** ምስጢር ነው!*** Tigist Alemneh Read more »

  የኤርትራ ጉዳይ በዚህ ርዕስ ተጽፎ የቀረበው ታሪክ በሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ የተመረኮዘ ነው፡፡ 1ኛ. አብዛኛው የኤርትራ ሕዝብ ፣ ከባዕድ አገዛዝ ለመላቀቅና ወደ መሠረት አገሩ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ኢትዮጵያ ወይ ሞት ብሎ በመታገል ምን ያህል መከራና ፈተና እንደተቀበለ 2ኛ. …

ደራሲ ጋዜጠኛ እና ዲፕሎማት አምባሳደር ዘውዴ ረታ እና መጽሃፎቻቸው Read more »

Bewketu Seyoum ትምርት በጨረስን ማግስት እኔና ፍቅር ይልቃል ፈረንሳይ ለጋስዮን ኣካባቢ በዘጠና ብር ቤት መሰል ነገር ተከራይተን እንኖር ነበር፡፡ በየሳምንቱ ቅዳሜ ወደ ቪድዮ ቤት ጎራ እንላለን ፤ እነኩማር በዜማቸው ወፍ ሲያረግፉ ፤ እነ ቫንዳም በጫማ ጥፍያቸው ጥርስ ሲያረግፉ በመመልከት ራሳችን …

የተቸካዮች ምክር ቤት (በ.ሥ) Read more »

ታላቁ ያገር ባለውለታ ጄኔራል መኮንን በ1927 አመተ ምህረት በበለሳ ወረዳ በሊቦ አውራጃ በጎንደር ክፍለ ሀገር ተወለዱ። የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ መድኃኒዓለም ትምህርት ቤት አጠናቀቁ። በ1945 አመተ ምህረት በኢትዮጵያ አየር ኃይል ውስጥ ተቀጥረው ለአንድ አመት ያህል የሬድዮ መገናኛ ትህምርታቸውን …

ሜጀር ጀኔራል ፋንታ በላይ ላገራቸው ሲሉ የሞትን ዕዋ የተቀበሉ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ጀግና Read more »

ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል ለዚህም ማስረጃው የኢትዮጵያ ታሪክ ትርጓሜን ተመልከቱት የሕወሓት ሰዎች ከጫካ ተስማምተውበት በመጡት ግንዛቤ የኢትዮጵያን ታሪክ መተርጐም ብሎም ለሌሎች ማስተማር ይፈልጋሉ የኦነግ መሪዎችም የሕወሐት አለቆቻቸው ያስተማሯቸውን እና የነገሯቸውን እንደሀይማኖታዊ ቃል ይዘውት ራሳቸውን የታሪክ ሊቅ ብሎም የኢትዮጵያን ታሪክ የ100 …

የኢትዮጵያን ታሪክ የ100 አመት ታሪክ ሲያስመስሉት መታዘብ ከጀመርን ድፍን ሰላሳ አመት ሊሞላን ነው። (ኤርሚያስ ቶኩማ‬) Read more »

የዛሬ አንድ መቶ ሃምሳ አንድ ዓመት በ1857 ዓ.ም በዐፄ ቴዎድሮስ ዘመን እንዲህ ሆኖ ነበር፡፡ የመስቀል በዓል በዋለ በሁለተኛው ቀን በዓሉን ምክንያት በማድረግ ምናልባት በኢትዮጰያ የመጀመርያው የቁንጅና ውድድር በጎንደር ከተማ ተደርጎ ነበር፡፡ ከልደታ ምሥራቅ ለአበራ ጊዮርጊስ ሰሜን ከሆነችው በቀሃ ወንዝ አጠገብ …

በ1857 ዓ.ም በዐፄ ቴዎድሮስ ዘመን በኢትዮጰያ የመጀመርያው የቁንጅና ውድድር በጎንደር ከተማ ተደርጎ ነበር፡፡ Read more »

ከአባይነህ ተገኝ የሰሞኑ የሶርያ እና የኢራቅ ስደተኞች አውሮፓን ማጥለቅለቅ ለአውሮፓውያን ራስ ምታት፣ለአለም ደግሞ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በሗላ ያልታየ አሳሳቢ እና አሳዛኝ ክስተት ሆኗል። በተለይ በተለይ በባህር ዳርቻ ወድቆ ከታየው ከዚያ የብዙዎችን ልብ ከሰበረ ጨቅላ ህጻን ሞት በሗላ አንድ ነገር መደረግ …

ሼህ ሙሃመድ አላሙዲ እንዳይሰሙ Read more »

ኄኖክ ኄኖክ  – የባሕር ኀይላችን(Our Navy) . ከገናናው አክሱምና የካሌብ ቀይ ባህራዊ ሞገድ ደማቅ ታሪክ መነሳቱን ለጊዜው ቸል እንበለውና ወደ ትናንቱ እውነት እንመለስ። . ለእኔና በእኔ ትውልድ አዙሪት ውጥስ የተፈጠርን በሙሉ አልፎ አልፎም ቢሆን በጆሮዎቻችን “አየር ሃይል” እና “ጦር ሃይል” …

የባሕር ኀይላችን(Our Navy) Read more »

ህውሓት ባካሄደችው ጠቅላላ ጉባሄ ከመረጠቻቸው 9 ከፍተኛ አመራሮች መካከል ወ/ሮ አዜብ መስፍን ይገኙበታል፡፡ የወ/ሮ አዜብ መስፍን በከፍተኛ አመራር ደረጃ መመራጣቸው ፣በቀጣይ በድርጅቱ ውስጥ የአቶ መለስ …ዜናዊ “ዕራይ” ከሚዲያ ሽፋን እና ከንግግር ድምቀት ባለፈ የባለቤታቸውን “ራእይ” በተግባር ለመፈፀም እና ለማስፈፀም ከፍተኛ የሆነ ትጋት እንደሚያደርጉ የሚጠበቅ ነው፡፡ ከውሓት ጀርባ ድርጅቱን የሚመሩት አቦይ ስብሓት ነጋ እና የእሳቸውን ቡራኬ […]

መከላከያ ሰራዊቱ ጥቃት ወይም ወረራ ለማድረግ ከፍተኛ ሰራዊት እያከማቸባቸዉ በሚገኙት በሰሜኑ አካባቢዎች አለመረጋጋት ነግሰዋል። በትናንትናዉ እለት አንድ ጓድ መሪ 9 የሰራዊት አባላትን ከመመሪያ ዉጭ ይዞ በመንቀሳቀሱ እርሱን ለመከተል ፍለጋ ላይ የነበረ አነስተኛ የጦር ክፍል የኤርትራን ቀጠና አልፎ በመሄዱ ተደምስሷል። ኤርትራም ያለው ሀይል በኢትዮጵያ በድንበር ላይ ተሰድሮ ዉጥረቱ እጅግ ተባብሶ መቀጠሉን ከስፍራዉ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል። ድል […]

ጥቂት ስለ አቶ መለስ…የክፋት ጭንቅላት መስራት ካቆመ 3 አመቱ = በክፋት የተጨመቁ መሃይማን ግዞት ቀጥሏል:: ‪#‎HappyMelesFreeDay‬ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Meleszenawi‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎TPLF‬ Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – መለስ ዜናዊ ከጅምሩ በክፋት የሰለጠነ መሆኑ እሙን ነው:;ድርጊቶቹ ሁሉ ይመሰክራሉ::አስተዳደጉ እንኳን ብናየው ከቀሪው ኢትዮጵያዊ ላይ …

ጥቂት ስለ አቶ መለስ…የክፋት ጭንቅላት መስራት ካቆመ 3 አመቱ = በክፋት የተጨመቁ መሃይማን ግዞት ቀጥሏል:: Read more »

አገሬ ስንት እዳ አለብሽ!?… ያገለገልኳት አገሬና ህዝቤ የሰጡኝ ምላሽ ይህ ከሆነ …ከነፈር እንዲመጥልኝ… አልሻም.. ሬሳዬ ይቃጠል»= ” ጋሽ ተስፋዬ ለማ።” አንጋፋና እውቅ የኪነጥበብ ሰው ነው። “ኦርኬስትራ ኢትዮጵያ”ን ያቋቋመና የመጀመሪያውን የኪነትና ትያትር ቡድን አሜሪካ ይዞ የሄደ፣ “ህዝብ ለህዝብ” ታሪካዊ ስራ ያዘጋጀና …

አገሬ ስንት እዳ አለብሽ!?… ያገለገልኳት አገሬና ህዝቤ የሰጡኝ ምላሽ ይህ ከሆነ …ከነፈር እንዲመጥልኝ… አልሻም.. ሬሳዬ ይቃጠል» Read more »

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የአድባራቱን ሰፋፊ መሬቶችና የገቢ ማስገኛ ተቋማት እየመዘበሩ ራሳቸውን ያበለጸጉ የአስተዳደር ሓላፊዎች በሕግ እንዲጠየቁ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ መመሪያ ሰጡ፡፡ የአስተዳደር ሓላፊዎቹ የአድባራቱን ሰፋፊ መሬቶችና የንግድ ተቋማት ያለጨረታ ከገበያ ዋጋ በታች ከ15 ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ …

‹‹በመዝባሪ ላይ አልደራደርም፤ እስከ መጨረሻው ከፊት ለፊት ነኝ›› ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ሲሉ በቁርጠኝነት ተናግረዋል፡፡ Read more »

ምኒሊክ ሳልሳዊ  : ፍትህ ካለ ሰላም አለ::ፍትህ ካለ እድገት አለ:;ፍትህ ካለ እስር ቤቶች በንጹሃን አይሞሉም:: ፍትህ ካለ ነጻነት እና መብት አለ:; ፍትህ ካለ የሚሸማቀቅ አይኖርም::ፍትህ ከተረጋገጠ ሕጎች ሁሉ በበላይነት የሕዝብ ይሆናሉ::ይህ ሁሉ የሚረጋገጠው በኛ ለኛ ከኛ ነው::እኛ አዎ እኛ በአሁን …

ህገወጥ አገዛዝን መታገስ በራሱ ወንጀልን ማበረታታት ነው::የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ትግላችን ተጠናክሮ መቀጠል አለበት:; ምኒሊክ ሳልሳዊ Read more »

1. ‘ኤር ፎርስ ዋን’ የአውሮፕላን ስም አይደለም #Ethiopia ኤር ፎርስ ዋን የአንድ አውሮፕላን ብቻ መጠሪያ አይደለም። ማንኛውም ፕሬዚደንቱን እያጓጓዘ ያለ አውሮፕላን ይህ መጠሪያ ስም ይሰጠዋል። ይህ መጠሪያ የሬዲዮ ሞገድ ወይም ጥሪ መለያ ኮድ ሲሆን በዚህ መሰየም ያስፈልገውም በአንድ ቦታ እየበረሩ …

እውነታዎች ስለ አሜሪካው ፕሬዚደንታዊ አውሮፕላን ‘ኤር ፎርስ ዋን’ Read more »

ምንሊክ ሳልሳዊ :- እናት ሃገሬ በናንተ ስም መጠራቷ ለኔ ይሁን ሃገሩን ለሚወድ ሁሉ ትልቅ እፍረት ነው:: ስለ ዲፕሎማሲ እና እንግዳ አቀባበል መማር ያስፈልጋል እንዳይባል አሊያም ትምህርት ቤት እንዳይከፈት ይህ ጉዳይ የተለመደ የፕሮቶኮል ጉዳይ እና በየሚዲያው የሚታይ ነገር ነው:: እንኳን ባለስልጣን …

የሰው መሳቂያ ሆናቹ አገራችንን የሰው መሳለቂያ አደረጋችሁ::የደህንነት ባለስልጣናቱ ተደብቀው ያዩ ነበር:: ምንሊክ ሳልሳዊ Read more »

    ቢቢሲ ባወጣው መረጃ መሰረት አንድ የሊቢያ ባለስልጣን ለቢቢሲ እንደገለፁት በሜዲትራኒያን ባህር በህገወጥ መንገድ ሰዎችን ወደ አውሮፓ አዘዋዋሪዎች ከስደተኞች ጋር ታጣቂዎቹን በመቀላቀል ወደ አውሮፓ እንዲገቡ እያደረጉ ነው ታጣቂ ቡድኑ በሰሜን አፍሪካ ጀልባ ባለቤቶች ስራውን እንዲሰሩ በመፍቀድ ከገቢያቸው ደግሞ 50 በመቶ ያህሉን ይቀበላሉ እንደ ቢቢሲ ዘገባ የአይ ኤስ ታጣቂዎች በባህር በሚደረገው ጉዞ ከሌሎቹ ስደተኞች በምን […]

ዲ/ን ክንፈ ገብርኤል
Hosaena

ሆሣዕና ቃሉ የዕብራይስጥ ሲሆን ትርጓሜውም “አሁን አድን” ማለት ነው። እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት ከፋሲካ/ከትንሳኤ በፊት ያለው እሑድ “የሆሣዕና እሑድ” በመባል ይታወቃል። በዚህ ዕለትም በቤተ ክርስቲያናችን የሚዘመረው መዝሙር፣ ማኅሌቱ፣ ቅዳሴው፣ ምንባቡና ማንኛውም አገልግሎት ሁሉ ዕለቱን በታላቅና እጅግ ደማቅ በሆነ መንፈሳዊ ሥነ – ሥርዓት የሚዘከርበት፣ የሚታሰብበት ነው። ይህ በዓል እጅግ በደማቅና ልብን በሚመስጥ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓትና ድምቀት ከሚከበርባቸው ቅዱሳን ገዳማትና መካናት መካከል የአክሱሟ ርዕሰ አድባራት ጽዮን ማርያም እና በዚህ በአዲስ አበባችን የእንጦጦ ማርያም በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Editor’s note:በቅርቡ ከጄ/ል ጻድቃን ጋር ያደረግነውን ቃለ-መጠይቅ በተከታታይ ማቅረባችን ይታወሳል፡፡ በቃለ-መጠይቁ ከተነሱት ርዕሰ-ጉዳዮች በተወሰኑት ላይ ዶ/ር አረጋዊ በርኸ አስተያየታውን ልከውልናል፡፡ዶ/ር አረጋዊ ከህወሓት መሥራቾች አንዱ ሲሆኑ እስከ1971 በሊቀመንበርነት፣ እስከ1978 ደግሞ በወታደራዊ መሪነት ያገለገሉ ሲሆን፤ የማርክሳዊ ሌኒናዊ ሊግ ትግራይ(ማሌሊት) ምሥረታን ተከትሎ ከተደረገው የአመራር ሽግሽግ በኋላ ድርጅቱን ለቅቀው በአውሮፓ ነዋሪ ናቸው፡፡ ጄ/ል ጻድቃን ገ/ትንሳዔ ደግሞ ከ1971 ጀምሮ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል፣ ከ1978 ጀምሮ ደግሞ የማሌሊት የፖሊት ቢሮ አባል እና የህወሓት ሠራዊት ቺፍ ኦፍ ስታፍ በመሆን እስከትጥቅ ትግሉ ማብቂያ አገልግለዋል፡፡ —- (ዶ/ር አረጋዊ በርኸ) ባለፉት ሳምንታት ህወሓት የተመሰረተበት 40ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የህወሓት መሪዎች ብቻ ሳይሆኑ የኢህኣዴግ ባጠቃላይ መጀመርያ በመቀሌ ቀጥሎ በኣዲስ ኣበባ ተሰባስበው ለኣንድ ወር ሙሉ የሃገሪቱን ሃብት ሲያባክኑና ሲዝናኑበት እንደከረሙ ተገንዝበናል። መቸም የኣምባገነኖች ጭንቀት ማስተንፈሻ ነው መሰለኝ፣ ህዝብ በረሃብና በስራ-ኣጥነት ሲጠቃ፤ ሃገርን በዴሞክራሲያዊ ስርዓት እጦት ስትታፈን ሁሉም ኣምባገነኖች ማስተዳደር ሲያቅታቸው ምክንያት እየፈጠሩ በሃገርና በህዝብ ንብረት እንዲህ መቀለዳቸው የተለመደ ለመሆኑ ሩቅ ሳንሄድ የደርግ ኢሰፓና የነፃድቃን ማሌሊት ምስረታ ፌስታ ማስታወሱ በቂ ነው። ኣሁንም ሃገር በቀልና ዓለምኣቀፍ ጥናቶች እንደሚያስረዱት፣ ኢትዮጵያ የተጠመደችበትን ዙርያ-መለስ ቀውስና ህዝቡ እየደረሰበት ያለው ስቃይ መረኑ ኣልፎ ሃገሪቱ ጭራሽ ስርዓት-ኣልባ ወደ እምትሆንበት ደረጃ እያሽቆለቆለች መሆንዋን በጥናት የተደገፈ መረጃ ቢያቀርቡም፣ ግብዞቹ የኢህኣዴግ መሪዎች መራር ሓቁን ከመጋፈጥ ይልቅ፣ ሃገሪቱ የበለፀገች – ህዝቡ የደላው ይመስል፣ ኣሸሼ-ገዳሜ ሲሉ ይገኛሉ። ህወሓት/ኢህኣዴግ 40ኛ ዓመት-በዓል ብሎ ቅጥ ያጣ ድግስ በጣለበት […]

ዳንኤል አበራ

1. መቅድም: ይህ የአድዋ 119ኛ አመት መታሰቢያ እኛና አድዋ በተሰኘ ርእሰ ጉዳይ ላይ ያተኩራል። ድርሰቱ ስድስት ንኡሳን ክፍሎች አሉት። ሁላችንም በጦርነቱ በድሉም ወቅት ስላልነበርን የተጻፈ አንብበን ከምናውቀው አመሳክረን ነው ጽሁፉ የተዘጋጀው። የተጻፈ አንብበን ላልኩት የጳውሎስ ኞኞን ምክር ከልቤ አድርጌ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Highlights: * “አንድ ቋንቋ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንድ ሕዝብ የሚሉ ሁሉ ህወሓትን ይጠሉታል።” * “ከአሜሪካንና ከእሥራኤል ጋር ያጣላን ፕሮግራማችን ነው።” * “ተወልደ የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር፤ ስዬም የመከላከያ ሚኒስትር እያሉ ኤርትራ ነፃነቷን ስታገኝ የአሰብ ጉዳይ ያለቀለት ጉዳይ ነው። ወንበር ፍለጋ ነው እንጂ የኤርትራ ጉዳይ ሰበብ ሊሆን አይችልም።” * “ህወሓት…… ለስድስት ወር ያህል ዝብርቅርቅ ያለ ፕሮግራም ተቀምጦ ነበር። ኢትዮጵያዊነትም አለ። ትግራይነትም አለ። ይሄ ጉዳይ በስድስት ወር ውስጥ እንዲጠራ ተደረገ።” (ጌትነት ምህረቴ) የመምህርነት ሙያቸውን ትተው ነበር በ1967 ዓ.ም ወደ ትግል የተቀላቀሉት። ከህወሓት ነባር ታጋዮች መካከል አንዱ ናቸው፤ አቦይ ስብሃት ነጋ። ህወሓት የተመሠረተበትን 40ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ዝግጅት ክፍላችን በህወሓት አመሠራረት፣ ዓላማና የትግል አግባብ ዙሪያ ከአቦይ ስብሃት ነጋ ጋር ያደረግነውን ቃለ- ምልልስ የመጀመሪያ ክፍል ይዘን ቀርበናል። አዲስ ዘመን፡- የንጉሡ ሥርዓት ተገርስሶ ወታደራዊ ሥርዓት ሲመጣ የነበረው የፖለቲካ አሰላለፍ ምን ይመስላል? አቦይ ስብሃት፡- የአፄ ኃይለሥላሴን መንግሥት የጣለው ሕዝቡ ነው። የጣለው ደግሞ መውደቅ ስለነበረበት ነው። ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሁኔታው የከፋ ነበር። በሌላው ሀገር ኢንዱስትሪው ማቆጥቆጥ ጀምሯል። የአፄው ሥርዓት በጣም ያከረረ ፊውዳል ስለነበር በሀገሪቷ ልማት የሚባል ነገር አልነበረም። ትምህርትም ቢሆን እንደ ጠበል የሚንጠባጠብ በጣም የተወሰነ እንጂ የሰፋ አልነበረም። ሕክምናም እንደዚሁ። ሀገሪቷ ለማንኛውም አደጋ የተጋለጠች ነበረች። ሕዝቡ በረሃብ እየሞተ «ኢትዮጵያ የአፍሪካ የዳቦ ቅርጫት ናት» ይባል ነበር። ሕዝቡ ኑሮው አስከፊ ሆኖ ሳለ በወቅቱ የሚነገረው ግን ኢትዮጵያ ሀገራችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ያደገች ናት […]

በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ስር የምትታተመዋ ዘመን መፅሄት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሳሞራ የኑስን እንግዳ አድርጋ ዘርዘር ያሉ መረጃዎችን ይዛ ወጥታለች። ከእነዚህ ነባርና አንጋፋ ታጋዮች መካከልም ጄኔራል ሳሞራ ለመጽሄትዋ ከሰጡት መረጃ የተወሰኑትን በመምረጥ እንዲህ አቅርበነዋል። ዘመን፡- እናመሰግናለን ጄኔራል ሳሞራ እንደሚታወቀው የህወሀት 40ኛ ዓመት መከበር ጀምሯል። እርስዎ ደግሞ በትግሉ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነዎትና እንደ ግለሰብ ትግሉን እንዴት ያስታውሱታል፤ ዛሬ ላይ ሆነው ሲያስቡት? ጀኔራል ሳሞራ፡- አርባ ዓመት ረጅም ጊዜ ነው። የትግሉ ሂደትም አንድ ዓይነት አልነበረም። የመጀመሪያዎቹ አስራ ሰባት ዓመታት ጨቋኙን ፋሽስት የደርግ ስርዓት ለማስወገድ የተደረገ የትግል ጊዜ ነበር። ይሔ ትግል ደግሞ በርካታ መስዋዕትነት የተከፈለበት ነው። ብዙ ወጣት ኢትዮጵያውያን የተሰዉበት የትግል ሂደት ነው። ደርግ ከተሸነፈ በኋላ ደግሞ የሰላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ ትግሉ ነው የቀጠለው። እንዳልኩት የመጀመሪያው አስራ ሰባት ዓመት የትግል ዓላማ ጨቋኙን ሥርዓት የማስወገድ ቢሆንም የመጨረሻው ዓላማ ግን ዴሞክራሲን፣ ልማትንና ፍትህን ማረጋገጥ ነበር። እና ትግሉ የመላው ኢትዮጵያ ህዝቦችን ድጋፍ አግኝቶ በተሳካ ሁኔታ ነው የተጠናቀቀው። በትግሉ ውስጥ ትልቁና ወሳኙ ነገር የደርግን ኃይል መደምሰስ ቢሆንም ከዚያ በመቀጠል ለግጭት፣ ለድህነትና ለሰላም እጦት ይዳርገን የነበረው ሁኔታ በ1987 ዓ.ም በፀደቀው ህገ መንግሥታችን መፍትሔ አግኝቷል። በዚህም ያ የተደመሰሰው ሥርዓት ዳግመኛ እንደማይመለስ እርግጠኛ የተሆነበት ሁኔታ ነበር የነበረው፡፡ ለአሁኑ ልማትና ዴሞክራሲያችን መሰረት የሆነውም ይሄው ህገ መንግስታችን ነውና በትግሉ የደርግ ሥርዓትን መደምሰስ አንዱ ጉዳይ ሆኖ ሁለተኛው ደግሞ ህገ መንግስቱ መጽደቁ ነው፡፡ ከዚህ […]

ከ1971 ጀምሮ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት የህወሓት ከፍተኛ አመራር የነበሩት ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ‹‹እኔ የማውቀው ከደርግ ከሚገኘው ንብረት አብዛኛውን ከሕዝብ ስንካፈል እንጂ ከውጭ ለእርዳታ የመጣውን ገንዘብ ከሕዝብ ቀምተን ለጦር መሣሪያ ስናውል አይደለም›› አሉ፡፡ ጄኔራሉ ይህን ያሉት ባለፈው ሰኞ ጥር 30-2007 ባደረግንላቸው ቃለ-መጠይቅ ላይ፡- ለ1977ቱ ረሀብ የመጣው ዕርዳታ ለድርጅት ሥራ እንዲውል ተደርጓል ስለሚለው የዶ/ር አረጋዊ በርኸ ስሞታ ላቀረብንላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ነው፡፡ ዶ/ር አረጋዊ ከቀደምት የህወሓት አመራሮች አንዱ ሲሆኑ የማርክሳዊ ሌኒናዊ ሊግ ትግራይ(ማሌሊት) ምሥረታን ተከትሎ ከድርጅቱ ለቅቀው በአውሮፓ የሚኖሩ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ዶ/ር አረጋዊ ለዕርዳታ ከመጣው ገንዘብ 50 በመቶ ለማሌሊት ማጠናከሪያ፣ 45 በመቶ ለወታደራዊ ወጪ ተመድቦ 5 በመቶ ብቻ ለሕዝብ እንዲውል በማዕከላዊ ኮሚቴ ተወስኖ ተግባራዊ ተደርጓል የሚሉ ሲሆን፤ በወቅቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ ግን የዛሬ 5 ዓመት በአሜሪካ ራዲዮ አማርኛ ፕሮግራም ላይ በሰጡት አስተያየት እንደዚያ ዓይነት ውሳኔ አልተወሰነም በማለት መቃወማቸው ይታወሳል፡፡ በሌላ በኩል በቅርቡ ሌላው የቀድሞ የድርጅቱ አመራር ገብሩ አሥራት በቅርቡ ባሳተሙት መጽሐፍ፡- በወቅቱ ድርጅታዊ ድጋፍ የሚያደርጉ መንግስታት የሚጠቀሙት መሥመር ያንኑ የሰብዐዊ ዕርዳታ የሚመጣበትን መሥመር በመሆኑ እና ሁሉም ገንዘብ አንድ ቋት ውስጥ የሚገባ በመሆኑ ስሞታው የወቅቱን አሠራር ካለመገንዘብ የሚመጣ ነው የሚል አጭር አስተያየት አስፍረዋል፡፡ እነዚህን አስተያየቶች በመጥቀስ ጥያቄ ያቀረብንላቸው በወቅቱ የማለሌሊት/ህወሓት ፖሊት ቢሮ አባል እና የሠራዊቱም ቺፍ ኦፍ ስታፍ የነበሩት ጄኔራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤ ስሞታውን አጣጥለውታል፡፡ በወቅቱ በተለይ በረሀቡ […]

(አዲስ ከድሬዳዋ) የቀድሞ ዩጎዝላቪያ አካል የነበሩት ክሮሺያና ሰርቢያ (የቦስኒያ ሙስሊሞችን እና ሞንቴኔግሮዎችን ጨምሮ) ሶሻሊዝም ሲንኮታኮት ከተበታተኑት የዩጎዝላቪያ ሪፑብሊኮችና ራስገዝ አስተዳደሮች መካከል ናቸው፡፡ እነኚህን ሪፑብሊኮች ቀድሞዉኑ ምን አንድ አደረጋቸው፣ በኋላስ ለምን መለያየት ፈለጉ የሚለው ትንሽ ግራ ያልተለመደ የሚመስል ነገር አለው፡፡ ከዩጎዝላቭ ሪፑብሊኮች በህዝብ ብዛትና ተፅዕኖ የመፍጠር አቅም ቀዳሚ የነበሩት ሰርቦች እና ክሮአቶች ቋንቋቸው የዲያሌክትን(ቀበሌኛን) ያህል እንኳ የማይለያይ ተመሳሳይ ነው፡፡የቋንቋ ምሁራንም ለየብቻ ማስቀመጥ ከብዷቸው ሰርቦክሮአት ይሉት ነበር ቋንቋውን(አሁን ለየብቻ ነው ብዙ ቦታ ላይ የሚፃፈው)፡፡ ዘራቸውም እንደስማቸው ሁለቱም ዩጎ ስላቮች(የደቡብ ስላቮች) ናቸው፡፡ ታሪካቸውን ያየን እንደሆነም ብዙ ነገሮችን ይጋራሉ፡፡ ኢኮኖሚያቸውን ያየን እንደሆነም ከአውሮፓ ድሀ እና በአንፃራዊነት ኋላቀር ከሚባሉ ህዝቦች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ታዲያ በምንድን ነው የሚለያዩት – በሐይማኖት- አለቀ፡፡ በሀይማኖት ብቻ፡፡ ሰርቦች ኦርቶዶክስ ናቸው፣ ክሮአቶች ደግሞ ካቶሊኮች ናቸው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ሰርቦች የኦሮቶዶክሱ ቅዱስ በፈጠረው ሲርሊክ ፊደል ይፅፋሉ፣ ካቶሊኮቹ ክሮአቶች ደግሞ ሮማዊ በሆነው ላቲን ፊደል ይፅፋሉ፡፡ እነዚህ ህዝቦች የደቡብ ስላቭ አንድነት አቀንቃኝ በነበረው ቲቶ አንድ ሆነው ሲኖሩ ቆይተው(አንድነቱ ግን ወደህዝቡ ያልሰረጸ እና በቲቶ ተሰሚነት ላይ የተመሰረተ ስለነበረ) ማርሻል ቲቶ ሲሞት አንደኛው ህዝብ ከሌላኛው ብሔር በወጣ መሪ ለመተዳደር ዝግጁ ስላልነበር ዩጎዝላቪያ በእቁብ መመራት ጀመረች፤ ዘንድሮ ከሰርቢያ፣ ቀጥሎ ከሞንቴኔግሮ፣ ከዚያ ከክሮሺያ፣ ከዚያ ከሜቄዶኒያ፣ ከዛ ከስሎቬኒያ፣ . . .እያሉ በየአመቱ በፈረቃ ዩጎዝላቪያን ሲያስተዳድሩ ቆዩ፡፡ ያው አስተዳደራቸው ራሱ ምንያህል አንድነት እንደሌላቸው የሚያሳይ ነውና ጊዜው ሲደርስ ሁሉም ሪፑብሊኮችና ራስገዝ […]

(ታምራት ኃይሌ) ርዕስ፡- የሶሻሊስቱ ጠንቋይ ጉዳይደራሲ፡- ሀማ ቱማተርጓሚ፡- ሕይወት ታደሰአጭር፡- ሥነ ጽሁፋዊ ምልከታገምጋሚ፡- ታምራት ኃይሌ የሶሻሊስቱ ጠንቋይ ጉዳይ The case of the Socialist Witchdoctor የ 22 አጫጭር ትረካዎች መድብል ሲሆን ትረካዎቹ በሁለት ክፍል ተለይተው ቀርበዋል፡፡ በክፍል አንድ አድራሻቸውን ፍርድ ቤት ያደረጉና በክስ መዝገቦች፤ በክርክሮች፤ በጥፋተኝነት ና በቅጣት ውሳኔዎች ላይ የተመሰረቱ አስራ አንድ ትረካዎች እናገኛለን፡፡ ትረካዎቹ አንድም አስራአንድም ናቸው፡፡ አንድነታቸውንም አስራአንድነታቸውንም በኋላ እመለስበታለሁ፡፡ በክፍል ሁለት እንደዚሁ አስራ አንድ ትረካዎች እናገኛለን፡፡ እንደመጀመሪያው በአንድ ቦታ የሚከናወኑ አይደሉም፡፡ ስለዚህ እነዚህን አንድም አስራ አንድም ናቸው ማለት ባይቻልም ፍጹም አይመሳሰሉም ደግሞ ማለት አይቻልም፡፡ በግድ አንድ ለማድረግ ሳይሆን፤ እንቅልፍ በሚያሳጣ ጸጉር ስንጠቃም ለመለያየት ሳይሆን በዚህ በሁለተኛው ክፍል ውስጥ ከተዘረዘሩት ትረካዎች መካከል በአንደኛው ማለትም “በሽብር ሚዛን አስር” መግቢያ ላይ የምናገኘው ኃይለ ቃል የቀሩትን ትረካዎች የጋራ ፍሬ ነገር በማስረዳት ረገድ ለጥቅስ የሚበቃ ይመስላል፡፡ እንዲህ ይላል፡፡ ትረካ ኢትዮጵያ ውስጥ ተመራጭ የጊዜ ማሳለፊያ ቢሆንም፤አሁንም ጥቂት ተጠራጣሪዎች ከሰማኒያ በመቶ በላይ መሀይም ባለበት አገር ውስጥ ድሮም ሌላ አማራጭ ሊኖር አይችልም በማለት ይናገራሉ፡፡ ለማንኛውም በዕድሜ የገፉ ሰዎች የተካኑበት ትረካ በአሁኑ ሰዓት በከፍተኛ ሁኔታ እንደተለወጠ የማይስማማ የለም፡፡ በአሁኑ ጊዜ አሰቃቂዎቹና አስገራሚዎቹ ታሪኮች የሚተረኩት በሽማግሌና ባልተማሩ ሰዎች ሳይሆን በተማሩ ወጣት ካድሬዎችና መገናኛ ብዙሀን ተብሎ በሚጠራው አካል ነው፡፡በድሮ ጊዜ በአጠቃላይ ታሪኮች ለዘብ ያሉና ልጆችን ለማስፈራራት ያህል መጠነኛ ምትሀታዊ ጉዳዮች ያሉባቸው ነበሩ፡፡ ስለሚያወሩ ጥንቸሎች፤ስለሸረኛ ጦጣዎች ስለታላላቅ አናብስት፤ስለተንኮለኛ ጅቦች፤ […]

(ወልደብርሃን ስሁል) የዛሬ መቶ ሰባ ዓመት አካባቢ አንዲት “ሚጢጢየ” አውሮፓዊት ሃገር ማንም ሳይቀድማት ኢትዮጵያን በጉልበት ይዛ ቅኝ ለመግዛት “ክተት ሰራዊት ምታ ነጋሪት ብላ” ቆርጣ ተሰናዳች። በቆዳ ስፋቷ አንድ ትልቅ ወረዳ እምታክል ናት። አፍሪካ ውስጥ ግን የራሷን መቶ እጥፍ የሚያክል ግዛት መቆጣጠር እሚያስችል አቅምና እብሪት ነበራት። ህልሟን ለማሳካት ፕሮጀክት ቀርፃ feasibility study አካሄደች። እቅዷና ጥናቷ ያነጣጠረውም በዘመነመሳፍንቷ ኢትዮጵያ ላይ ነበር። የቀይ ባህር አካባቢ ደከም ባለ አውሮፓዊ ሃይል እንዲያዝ ትሻ የነበረችው ታላቋ ብሪታንያም ይሁንታ ሰጠቻት፤ በወርራ ቅኝ ልትገዛን ቆርጣ ለተነሳችው ቤልጅየም! ቤልጅየም ለኢትዮጵያ ያሰበችው ፕሮጄክት ብሎንዲል ከሚባል እብሪተኛ ሰው የጀብድ ልክፍት ጋር የተቆራኘ ነበር። ግብፅ በወርኔር ሙዚንጀር፤ ጣልያን በፔትሮ አንቶኖሊ ምን እንዳደረጉን ጠንቅቀን እናውቃለን። ከነሱ በፊት ቀድሞ ስለተሰናዳልን የብሎንዲል Humanitarian Mission ግን ብዙ አናውቅም። ነገሩ ያስገርማል እንጂ አያስቅም። “ገድለ‐ብሎንዲል” በጥቂቱ እንዲህ ነበር፦ የቤልጂግ መንግስት መጀመርያ በ1841 ከፍተኛ በጀት መድቦ ብዛት ያላቸው የስለላ ወኪሎቹን ወደ ግብጽ አሰማራ። ወኪሎቹም “ለሳይንሳዊ ጥናት እና ለሰብአዊ ተልእኮ” በሚሉ ሽፋኖች ካይሮ ላይ ከትመው ስለ ኢትዮጵያ ጥናት ጀመሩ። ማንኛውንም ዓይነት መረጃ በዝርዝር እየቀራረሙ ከሚያቀርቡት ሪፖርት የቤልጂየም ንጉስ ቀዳማዊ ሊዮፖልድ “በውስጧ ሁከት የነገሰባት ኢትዮጵያን” በቀላሉ መውረርና መቆጣጠር እንደሚችል አመነ። ለወረራም ቋመጠናም የሰላዮቹ አስተባባሪ በአካል ወደ ኢትዮጵያ ሂዶ “ሰብዓዊ ተልእኮ” የሚል ስም ያለው ጉብኝት እንዲያካሂድ አዘዘው። ዋናው ተልእኮው ግን ለወረራ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጥር እና ባስቸኳይ እሚተገበር የድርጊት መርሃ ግብር እንዲያዘጋጅ ነበር። […]

«ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት ) እና የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ ጭቁን ህዝቦች ጋር በመሆን ያካሄዱትን የትጥቅ ትግል በድል ያጠናቀቁት የውጭና የሌሎች ድጋፍ አግኝተው ሳይሆን የጠራ ህዝባዊ መስመር በመያዛቸው ነው» ሲሉ የህወሓት ሊቀመንበር አስታወቁ። ህወሓት የትጥቅ ትግል የጀመረበትን የደደቢት በረሃና ሌሎች ታሪካዊ ስፍራዎች በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገቡ ጥረት እንደ ሚያደርጉ ታሪካዊ ስፍራዎችን የጎበኙ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ገልጸዋል። የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በመጪው የካቲት የሚከበረውን የህወሓት 40ኛው ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ በክልሉ የትጥቅ ትግል የተካሄደባቸውን ስፍራዎችና የማዘዣ ጣቢያዎችን ለአንድ ሳምንት ያህል ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የህወሓት ሊቀመንበር አቶ ዓባይ ወልዱ የጉብኝቱን መርሐ ግብር መጠናቀቅ አስመልክቶ ትናንት ማምሻውን በመቀሌ በተዘጋጀው የማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ እንደገለጹት፤ ህወሓትና የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ ጭቁን ህዝቦች ጋር በመሆን የትጥቅ ትግሉን በአሸናፊነት ሊወጡ የቻሉት የጠራ ህዝባዊ መስመር በመያዛቸው ነው። የክልሉ ህዝብ ቀደም ሲሉ በነበሩትና በደርግ ሥርዓቶች ሲደርስበት የቆየውን ብሔራዊ ጭቆና ለማስወገድ ህወሓት የትጥቅ ትግሉ መጀመሩን ገልጸው፤ በወቅቱ የተሳሳተ ዓላማ ያነገቡ ኃይሎች ትግሉን ገና ከጅምሩ በእንጭ ጩ ለማኮላሸት ተንቀሳቅሰው እንደነበር አስታ ውሰዋል። «ህወሓት የያዘውን ህዝባዊ ዓለማና ትክክለኛ መስመር የሚደግፉ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎችን ከጎኑ እያሰለፈ ህዝቡን የትግሉ ባለቤት ማድረጉ ትግሉን በአሸናፊነት እንዲወጣ አስችሎታል» ብለዋል። ሊቀመንበሩ እንዳሉት ህወሓት በወቅቱ ሲያጋጥሙት የነበሩትን በርካታ ተግዳሮቶችና እንቅፋቶችን ተቋቋሞ ትግሉን በአሸናፊነት ሊወጣ የቻለው የጠራ ህዝባዊ መስመር በመያዙና ባለው የዓላማ ፅናት ነው። ህወሓትና የትግራይ ህዝብ የትጥቅ ትግሉን ያካሄዱት ይደርስባቸው የነበረውን […]