ዓባይ ወልዱ፡- ህወሓትን ለድል ያበቃው የውጭና የሌሎች ድጋፍ ሳይሆን የጠራ ሕዝባዊ መስመር ነው
«ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት ) እና የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ ጭቁን ህዝቦች ጋር በመሆን ያካሄዱትን የትጥቅ ትግል በድል ያጠናቀቁት የውጭና የሌሎች ድጋፍ አግኝተው ሳይሆን የጠራ ህዝባዊ መስመር በመያዛቸው ነው» ሲሉ የህወሓት ሊቀመንበር አስታወቁ። ህወሓት የትጥቅ ትግል የጀመረበትን የደደቢት በረሃና ሌሎች ታሪካዊ ስፍራዎች በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገቡ ጥረት እንደ ሚያደርጉ ታሪካዊ ስፍራዎችን የጎበኙ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ገልጸዋል። የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በመጪው የካቲት የሚከበረውን የህወሓት 40ኛው ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ በክልሉ የትጥቅ ትግል የተካሄደባቸውን ስፍራዎችና የማዘዣ ጣቢያዎችን ለአንድ ሳምንት ያህል ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የህወሓት ሊቀመንበር አቶ ዓባይ ወልዱ የጉብኝቱን መርሐ ግብር መጠናቀቅ አስመልክቶ ትናንት ማምሻውን በመቀሌ በተዘጋጀው የማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ እንደገለጹት፤ ህወሓትና የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ ጭቁን ህዝቦች ጋር በመሆን የትጥቅ ትግሉን በአሸናፊነት ሊወጡ የቻሉት የጠራ ህዝባዊ መስመር በመያዛቸው ነው። የክልሉ ህዝብ ቀደም ሲሉ በነበሩትና በደርግ ሥርዓቶች ሲደርስበት የቆየውን ብሔራዊ ጭቆና ለማስወገድ ህወሓት የትጥቅ ትግሉ መጀመሩን ገልጸው፤ በወቅቱ የተሳሳተ ዓላማ ያነገቡ ኃይሎች ትግሉን ገና ከጅምሩ በእንጭ ጩ ለማኮላሸት ተንቀሳቅሰው እንደነበር አስታ ውሰዋል። «ህወሓት የያዘውን ህዝባዊ ዓለማና ትክክለኛ መስመር የሚደግፉ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎችን ከጎኑ እያሰለፈ ህዝቡን የትግሉ ባለቤት ማድረጉ ትግሉን በአሸናፊነት እንዲወጣ አስችሎታል» ብለዋል። ሊቀመንበሩ እንዳሉት ህወሓት በወቅቱ ሲያጋጥሙት የነበሩትን በርካታ ተግዳሮቶችና እንቅፋቶችን ተቋቋሞ ትግሉን በአሸናፊነት ሊወጣ የቻለው የጠራ ህዝባዊ መስመር በመያዙና ባለው የዓላማ ፅናት ነው። ህወሓትና የትግራይ ህዝብ የትጥቅ ትግሉን ያካሄዱት ይደርስባቸው የነበረውን […]