ኢትዮጵያን ከቅርጫ ለማትረፍ ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም፤ ነጻነት ለሀገሬ)

የአሁኑ አስገራሚ ጊዜ ሸክስፒር፣ ጁሊየስ ቄሳር በሚለው ፅሁፉ ላይ ለተናገረው አነጋገር ልዩ ትርጉም ይሰጠዋል፣ “ሰዎች የሰሩት ተንኮል ከመቃበራቸው በላይ ሀያው ሆኖ ይኖራል” ብሎ ነበር ሸክስፒር። በአሁኑ ጊዜ አቶ መለስ ዜናዊ በህይወት በነበሩበት ጊዜ ከሰሩት ተንኮሎችና ጭራቃዊነት የሞላው አስቀያሚ ተግባር ውርስ ጋር ፊት ለፊት ተፋጥጠን እንገኛለን።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ቅዱስ ዩሃንስ

ነፃ- ፕሬስ ለነፃነት፤ ለፍትህና ለእኩልነት የሚኖረውን አስተዋፅኦ የሚገነዘቡ ገዢዎች ፕሬሱ ለአንባገነንነት አገዛዛቸው የሚመች ስለማይሆን ይፈሩታል፤ ይጠሉታል፤ ያጠፉታል። ወያኔም እያደረገ ያለው ይህንኑ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በባህር ዳር ሰልፍ በአድዋና አዲስ አበባ የአድዋ ድል በዓል ዝግጅቶች ይኖራሉ
አማኑኤል ዘሰላም

የአንድነት ፓርቲ፣ በሶስት ከተሞች ታላላቅ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች፣ ለማድረግ መወሰኑን ከሚሊየነሞች ድምጽ ለነጻነት ፌስቡ ገጽ አነበብኩ። እንቅስቃሴዎቹ የሚደረጉባቸው ከተሞች፣ አድዋ፣ አዲስ አበባ እና ባህር ዳር ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ታክሎ ተሾመ
መመካከር፤ መተቻቸት አእምራችንን ያሰፋዋል የሚል እምነት ስላለኝ የተሰማኝን ለማካፈል ስለሆነ ጽህፏ ለምን እንደምትበጅ ሰከን ብላችሁ እንድታነቧት በትህትና አሳስባለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)

በምንወዳት ኢትዮጵያችን ከኑሮ እስከ ሮሮ፤ ከማሕበራዊ እስከ ፖለቲካ፤ ከኢኮኖሚ እስከ ትምህርት ፖሊሲ፤ ከመንፈሳዊ እስከ ዓለማዊ… ያሉ ጉዳዮች ጉራማይሌነት ከቀን ወደ ቀን እየጎላ ነው፡፡ በዚህ ፅሁፍም ጥቂት ያህል ማሳያዎችን በአዲስ መስመር እንመለከታለን።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ክንፉ አሰፋ

ኢትዮጵያዊው ቱጃር ለለውጥ ብለው በኮንትራት ታክሲ በመሄድ ላይ ናቸው። እሳቸውን የጫነው ታክሲ መስቀል አደባባይ ላይ ሲደርስ በድንገት ቀጥ ብሎ ቆመ። ሾፌሩ ተደናጋጠ። መኪናውን እንደገና ለማስንሳት ብዙ ሞከረ። ከብዙ ሙከራ በኋላ ጥረቱ ስላልተሳካለት ቱጃሩን ለትብብር ጠየቃቸው። እንዲህ ሲል። “ወጣ ብለው ይግፉ።” ቱጃሩ በመገረም ሾፌሩን አዩት። “ይግዙ” ማለትህ ነው ሲሉም መለሱለት። እኚህ ሰው መኪናውን ከመግፋት ይልቅ አዲስ መኪና መግዛት ይቀላቸዋል። የቤቶች ድራማ ላይ እከ ደከ አስር ጊዜ “እኔን ነው?” የሚለው ወዶ ይደለም። ማመን የሚቸግሩንን ነገሮች ማጣራት ስንፈልግ እንደጋግማለን።

ሙሉውን አስነብበኝ …

መስፍን ወልደ ማርያም

በ1996 ዓ.ም. የክህደት ቁልቁለት በሚል ጽሑፌ ውስጥ ‹‹ማንነት ምንድን ነው፤ በሚል ንዑስ ርእስ ስር ከገጽ 98 ጀምሮ በተቻለኝ መጠን አፍታትቻለሁ፤ የሪፖርተር ጋዜጠኛ ይህንን ለማንበብ ጊዜ አላገኘም፤ ወይም የተገለጠለት ዱሽ ቅንጫቢ በቅቶት ይሆናል፤ የምጠቅሰውም ለሱ ሳይሆን ለሌሎች ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አንዱዓለም ተፈራ
በተደጋጋሚ ትክክለኛ ያልሆነ ነገር ሲያጋጥማችሁ፤ አሁንስ በዛ! ማለታችሁ አይቀርም። እኔም ይኼው ዕጣ አጋጠመኝ። ታዲያ ዝም ማለቱ ወንጀል ሆነብኝና ይኼን ጻፍኩ። እንዲህ ነው የሆነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፤ ላለንብት የፖለቲካ ምስቅልቅል፤ መፍትሔ ፈላጊዎች የሩጫ ፊታቸውን ወደ ታሪክ አዙረዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይድነቃቸው ከበደ Yedenekachew Kebedeድነቃቸው ከበደ
ከአምስት ወር በፊት የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የአዲስ ዓመት የሥራ ዘመን መጀመር አስመልክቶ በጋራ ባአካሂዱት ጉባዔ አዲሱ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመም ፕሬዚዳንታዊ የመክፈቻ ንግግር ማድረገቸው የሚታወቅ ነው። የፕሬዚዳንቱ የንግግር ይዘት መንግሥት በ2006 ዓ.ም. ትኩረት ሊያደርግባቸው የሚገቡ ዋና ዋና ተግባሮች ላይ ብቻ ያተኮረ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ግርማ ካሳ
«አበው ሲተርቱ ላም ባልዋለበት ኩመት ለቀማ ይላሉ። ሰላም ጠላቱ ከሆነ የአገዛዝ ቡድን ጋራ በሰላማዊ ትግል ገጠሞ ሰለማዊ ድል አስመዘግባለሁ ብሎ ማሰብ ከሰላማዊ ጭንቅላት የሚፈልቅ ሰላማዊ አስተሳሰብ ነው ብዬ አላምንም። …ትግል ሱስ አይደለም። እንደ አቦል ቡና ሱስ አይደለም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም Prof. Al-Mariamየዘገዬ ፍትህ እንደተነፈገ መቆጠር የለበትምን?

ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ነጻነት ለሀገሬ)

በአህጽሮ ቃሉ አይሲሲ/ICC እየተባለ የሚጠራው ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት/International Criminal Court የኡሁሩ ሙጋይ ኬንያታን ጉዳይ አስመልክቶ እያደረገ ያለው ተደጋጋሚ የፍትህ ሂደቱን የማዘግየት ስራ፣ በቀጠሮ የማሳለፍ እና “የውሸት መረጃዎች” እንዲሁም “የሀሰት ምስክሮች” በማቅረብ እንደገና የመታየት ዕድል ለመፍጠር እየተነገረ እና በተግባር እየተፈጸመ ያለው አጠቃላይ ወደኋላ የመንሸራተት ሁኔታ አንቅልፍ ባያሳጣኝም ከፉኛ አሳስቦኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይሄይስ አእምሮ

ለውድቀት ስኬት “የምሥራች!” ወይም “እንኳን ደስ ያለን!” የማይባል ነገር ሆኖብኝ እንጂ ከነዚህ የደስታ ማብሠሪያ አባባሎች በአንደኛው ጽሑፌን መጀመር ቃጥቶኝ ነበር። ለማንኛውም ሀገራችን በማንኛውም ዘርፍ በገባችበት ውድቀትና ኪሣራ ምክንያት ልባችሁ ያዘነና ቅስማችሁ የተሰበረ ወገኖቼን “እግዚአብሔር ያጽናችሁ፤ የሀገራችሁን ትንሣኤም ፈጣሪ በአፋጣኝ እውን እንዲያደርግላችሁ የእግዚአብሔርን ልብ ያራራላችሁ” በሚለው የልመና ቃል ፈጣሪን እየተማጸንኩ ወሬየን ልቀጥል። ትንሽ በንዴት እንድትንጨረጨሩ ፈቃዳችሁ ይሁንልኝ፤ መልካም መንጨርጨር!

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሥርጉተ ሥላሴሥርጉተ ሥላሴ
ይድረስ ብለናል ከወደ ሲዊዘርላንድ ዙሪክ እኔና ብዕሬ ለሞገደኛው ብዕረ ተክሌ …
ጭራሽ ተበዳይ ብዙኃኑ ተወቃሽ ሆነ? ይገርም! ጡር የሚባል ነገር አለ። በፈጠረህ ጡር ፍራ የስሞተኛው ብዕር …

ሙሉውን አስነብበኝ …

በልጅግ ዓሊ
በ ርመን ውስጥ እንደ አውሮፓውያን አቆጠጠር 1971  ምሮ የዓመቱ ምርጥ ቃል ይመረጣል። ይህ በየዓመቱ የሚደረገው ምርጫ አዲስ የተፈጠሩ አባባሎች  ወይም ቃላቶች አሮጌም ቢሆኑ በአለፈው ዓመት ውስጥ የአጠቃቀማቸው ሁኔታ ታይቶ የሚካሄድ ብሂል ነው። ለአሸናፊነት የሚበቃው ቃል በሕብረተሰቡ ውስጥ ተቀባይነት ያገኘው ይሆናል። ምርጫው በኮሚቴ ዳኝነት ተሳታፊዎቹን ቃላቶች አወዳድሮ ከፍተኛ ድምጽ ያገኘውን አሸናፊ ያደርጋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አለማየሁ መሰለ

ውድ አንባብያን፣ ይህ ጽሁፍ ከዚህ ቀደም ከዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ ጋር ተስፋዬ ገብረአብን አስመልክቶ አወጥተን ከነበረው ሪፖርት ጽሁፍ ተከታይ ነው። በዚህ መሰረት ከተስፋዬ ገብረአብ ጋር አብረን ስንኖር እጄ ላይ ከወደቁትን መረጃዎች መሃከል የመ መሪያው ጽሁፍ ተከታይ ይሆናል ብዬ የመረጥኳቸውን ቃል በገባሁት መሰረት ከነማብራሪያቸው አቀርባለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በተክለሚካኤል አበበ

ስለመጪው ሶስተኛ ሪፐብሊክ፤ ካለፈው የቀጠለ፤ ሀ

ትንሽ ወደኁዋላ፤ እንደ መግቢያ

  1. ግንቦት፤ 2003/2011፤ በቶሮንቶ ከተማ፤ ጃዋርና ኦባንግ፤ አሎ አይደሂስና (ሸጋ የአፋር ሰው ነው) አበበ በለው በእንግድነት የተገኙበትን ሕዝባዊ ስብሰባ ተንተርሼ፤ አንድ ወርቅ የሆነ ጽሁፍ ጽፌ ነበር፡፡ ጽሁፉን ያላነበባችሁ ብታነቡት፤ ያነበባችሁትም ብትደግሙት አይቆጫችሁም፡፡ ጽሁፉ ይቀጥላል ብዬ ጊዜ ጠፋና ቀጣዩን ክፍል ሳላቀርብ ቀጠልኩ፡፡ ስለኦባንግ ገጠመኝ ተርኬ፤ ስለጃዋር ጀምሬ ነበር ያቆምኩት፡፡ አሁን መቀጠሉ ወቅታዊ መስሎ ታየኝ፡፡

    ሙሉውን አስነብበኝ …

አንዱዓለም ተፈራ

ወገንተኛው አምባገነን ሕገወጥ መንግሥት፤ ከዕለት ዕለት ሀገራችንን ወደባሰ አዘቅት እየከተታት ነው። ያለጥርጥር ከዚህ መንገድ ቀና የሚልበት የፖለቲካ አንጀት የለውም። እያሽቆለቆለ መሄዱ፤ የመሰንበት ዋስትናውና መጥፊያው ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም
በአለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ ወያኔ-ኢሕአዴግ የሚወቀስበት ሥራ በጣም ቢያመዝንም የሚመሰገንበት ሥራ የጽሑፍ ቁጥጥርን ማስቀረቱ ብቻ ነው። ሁልጊዜም አንድ ጥሩ ነገር የሚያስከትለው አብዛኛውን ጊዜ የማይጠበቅ ነገር ሊኖር ይችላል፤ ለምሳሌ አጠቃላይ ነፃነት ሲመጣ ወንጀለኛነት ይጨምራል፤ እንዲሁም የጽሑፍ ቁጥጥር ሲነሣ ጸሐፊዎች ይበዛሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Ethiopian Sudan border protestበደምና በአጥንት መስዋዕትነት ተከብሮ የቆየ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለባዕድ አሳልፈን አንሰጥም!
ብርሃኔ አሰበ አለሁድረስ
ሀገራችን ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብቷ የታደለች፣ መልካም የአየር ፀባይ ያላት፣ ህዝቦቿ የራሳችን አኩሪ ባህልና ወግ ያለን፤ የራሳችን መልካም መልክዓ ምድራዊና አሰፋፈር ያለን፤ በጋራ ተሳስረን አብረን የኖርንባትና የምንኖርባት በየትኛውም ዘመን ሉዓላዊነቷ ያልተደፈረ ለአፍሪካ ተምሳሌት የሆነች ሀገር ናት።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፎቶ ከኢዜአ Photo from ENAታደሰ ብሩ
በቅድሚያ የሚከተለውን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን (ኢዜአ) ዜና አጣጥሙልኝ።
በባሌ ዞን በንብ ማነብ ፓኬጅ የተሳተፉ አርሶ አደሮች ከ53 ነጥብ 7 ሚሊዮን የሚበልጥ ገቢ አገኙ
ጎባ ጥር 10/2006፦ በባሌ ዞን ከእርሻ ስራ በተጓዳኝ በንብ ማነብ ፓኬጅ የተሳተፉ አርሶ አደሮች ከ53 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ማግኘታቸውን የዞኑ የእንስሳት ሀብት ልማትና ጤና ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ውስጥ

እውነት ቤት ስትሠራ … ውሸት ላግዝ ካለች
ሚስማር ካቀበለች … ጭቃ ካራገጠች
ቤቱም አልተሠራ … እውነትም አልኖረች።

… እንደዚያ ነው በባቢሎን ዘመን። የአንዱ ቋንቋ ከአንደኛው ይዘበራረቃል … መግባባትና መረዳዳት ብርቅ ይሆናል። በጠራ አማርኛ የተጣፈውን በጉግማንጉግኛ በመተርጐም ከውስጡ የሚፈልጉትን ብቻ አለፍ አለፍ እያሉ ያነቡታል። እናም የራሳቸውን ትርጉም ይሰጡታል። ፍየል ወድያ … ቅዝምዝምም ወዲህ ይሆናል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)

የኢህአዴግ መራሹ መንግስት ‹መዝገበ ቃላት› ለነፃነት የሚሰጠው ትርጓሜ ‹አራምደዋለሁ› ከሚለው ግራ-ዘመሙ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ብያኔ አንፃር የሚተነተን በመሆኑ፣ የየትኛውም ተቋም ነፃ ሆኖ የመንቀሳቀስ መብት ላይ ረዣዥም እጆቹን ደጋግሞ እየጫነ ሲጨፈልቅና ሲያስጨፈልቅ ለመኖሩ በርካታ ማሳዎችን ማቅረብ ይቻላል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ክንፉ አሰፋ

የጥምቀት በዓልን ተሰባስበን በምናከብርበት አንድ ቤት ውስጥ ካለወትሮው ፓልቶክ ተከፍቷል። በዚያ የበዓል ድባብ፤ የፓልቶክ ንትርክ መከፈቱ ሳይገርመን፣ ርእሱ የሁላችንንም ቀልብ መሳቡ። በእርግጥ አንድም ቁም ነገር በንግግሩ አልሰማንም። አዲሱን ቋንቋ ልዋስና የፓልቶኩ ተናጋሪዎች ሙድ  የሚያስይዙ ነበሩ። ሰዎቹ በዚህ ከቀጠሉ የእነ ክበበው ገዳን ገበያ መዝጋት እንደሚችሉ አያጠራጥርም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Ethiopia Zare (እሁድ ጥቅምት 11  ቀን 2006 ዓ.ም. Jan 18, 2014)፦ በሳኡዲ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያዊያኖች ያሉበት አሳሳቢ ሁኔታ ያስጨነቃቸው በቫንኩቨር ካናዳ ነዋሪዎች ምሽቱን ባደረጉት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ወደ 10ሺህ ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ማሰባሰባቸው ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተመስገን ደሳለኝ
አምስተኛው ዙር አገር አቀፍ ‹‹ምርጫ›› እንደወትሮው ሁሉ በቀጣዩ ዓመት ሊደረግ በዕቅድ ተይዟል፤ ወሬውም ከወዲሁ ለፖለቲካ ፍጆታነት እየዋለ ነው፤ ኢህአዴግም በበኩሉ ‹አውራ ፓርቲ›ነቱን ከቀደመው በበለጠ አጠናክሮ የሚቀጥልበትን ሴራ ፈትሎ በመግመድ ውሎ ማደሩን ገና በማለዳ እያቀላጠፈው መሆኑን እየታዘብን ነው፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፋሲል የኔዓለም  Engi. Gezachew Shiferawግርማ ካሳ
የኢሳት ባልደረባ አቶ ፋሲል የኔዓለም “የአንድነት ፓርቲ የመጪው ጊዜ ፈተና” በሚል ርዕስ የጻፉትን ዘ-ሐበሻ ድረገጽ ላይ አነበብኩ። አቶ ፋሲል ጽሑፉን ያቀረቡት እንደ ግል አስተያየት እንደመሆኑ፣ ኢሳትን በዚህ ውስጥ ጣልቃ አላስገባም። የአንድነት ፓርቲ አዲሱ ሊቀመንበር፣ ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው፣ ሀገር ውስጥ ለሚታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ ከሰጡት ቃለ ምልልስ፣ የሚከተለውን በመጥቀስ ነበር አቶ ፋሲል ጽሑፋቸውን የጀመሩት፤ 

ሙሉውን አስነብበኝ …

Ethiopians in Saudiየተመላሾች ጉዳይ …
ነቢዩ ሲራክ
ከሳውዲ ወደ ሀገር ቤት የተመለሱ ዜጎችን በሚመለከት የጀርመንና የአሜሪካ ራዲዮን ጨምሮ በርካታ የመገናኛ ብዙኀን አንድ አይነት የሚመስል መረጃ ግፉአን ተመላሾችን እማኝ እያደረጉ መረጃ አቀብለውናል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አንዱዓለም አራጌ Andualem Aragieግርማ ካሳ

“በሕገመንግሥቱ የመደራጀት መብታቸው የተጠበቀላቸው ፓርቲዎችን አልከሰስንም። ፓርቲዎችን ግን ሽፋን አድርገው ሥርዓቱን ወይንም ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመናድ እንንቀሳቀሳለን የሚሉ ኃይሎችን ግን ዛሬም፣ ነገም፣ ሕጉን የማስከበር ግዴታና ኃላፊነት ስላለብን ከመከሰስ አያመልጡም ማለት ነው።”

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይድነቃቸው ከበደ Yedenekachew Kebedeይድነቃቸው ከበደ

“ሕዝቡ እኔ ማን እንደሆንሁ ይላል?” በማለት እየሱስ ክርስቶስ መረጃ ይጠይቃል፤ ደቀመዛምርቶችም ስለሱ የተባለውን አንድም ሳያስቀሩ ይነግሩታል። እሱም መልሱ እንዲህ ይላቸዋል “እናንተስ እኔ ማን እንደሆንሁ ትላላችሁ?” አላቸው። እነሱም መለሱለት። ሙሉ ታሪኩ ሉቃስ ም.9 ቁ.18 ላይ ይገኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ግርማ ሞገስ
ኢትዮጵያ ከውጭ ወረራ ረጅም የነፃነት ዘመን እንዳላት የሀገር ተወላጅ እና የውጭ ሀገር የታሪክ ተመራማሪዎች ያረጋግጣሉ። ይሁን እንጂ በሥልጣኔ ግን ብዙም እንዳልገፋች ይኸው ዛሬ የእኛም ትውልድ ሳይቀር የሚያየው ሕቅ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ግርማ ካሳ
ጆን ኬሪ (ግራ)፣ ቴዎድሮስ አድኀኖም (ቀኝ) John Kerry (L) Tedros Adhanom (R)ኢቲቪ በቅርቡ አንድ፣ በአንድ በኩል አሳዛኝ፤ በሌላ በኩል አስቂኝ ዶኪሚንተሪ ለተመልካቾቹ አቅርቧል። በርካታ ጉዳዮች ተነስተዋል። በዚህ ጽሑፍ የፌዴራል ከፍተኛ አቃቤ ሕግ የሆኑት፣ አቶ ብርሃኑ ወንድማገኝ፣ አንጋፋው ጋዜጠኛ እስክንደር ነጋን በተመለከተ፣ በተናገሩት ላይ ጥቂት ሃሳቦችን ለመገልጽ እወዳለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

(ውስጥ ውስጡን ድመትም ነብር ናት) ክፍል 1
ይድረስ ታሪክ ለምትንሻፈፉ እና በብሔር ለማጋጨረት ለምትጠሩ ሁሉ
ቶሎሣ በቀለ

አባቴ አንድ ነገር ሳይጥማቸው ሲቀር “ኪሳ ኬሳ አዱሬን ቢኒሳ” ይላሉ። በኦሮምኛ፤ “ውስጥ ውስጡን ድመትም ነብር ናት” ማለት ነው። ይህ የኦሮሞን አባባል የተጠቀምኩት የኦሮሞ ልጆች ላይ ነብር መስለው ድመት የሆኑ የተገላበጠ ገመና ያላቸው እንደ እባብ ቆዳቸውን እየሸለቀቁ ወደ እሳት የሚገፉት ስንኩል ሰዎች ስላሉ ነው። ለእነዚህ የታሪክ ዝቃጮች ጥያቄ ማቅረብና እና እውነታውን ማሳየት እፈልጋለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

/መስፍንወልደማርያም

በአሁኑ ጊዜ ወያኔ ሰውን እያፈረሰ፣ ማህበረሰብን እያፈረሰ ሰማይ-ጠቀስ ሕንጻዎችን በሚሠራበት ጊዜ፣ ከትናንት ወዲያ የሰዎችን ቤቶች አፍርሶ ትናንት የመኪና መንገድ ከሠራ በኋላ ዛሬ መንገዱን አፍርሶ የባቡር መንገድ እየተሠራ አዲስ አበባ በትራፊክ መጨናነቅ መኪና መንዳት አደገኛ በሆነበት ጊዜ፣ ዛሬ ባለሥልጣኖች የሚሠሩት ጠፍቶአቸው የጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ የሚባለውን በአማካሪዎች ከሞሉት በኋላ ለሚኒስትሮችም አማካሪ መሾም በተጀመረበት ጊዜ፣ ዛሬ በሳኡዲ አረብያ ኢትዮጵያውያን እንደአደገኛ አውሬ እየታደኑ በሚደበደቡበት፣ በሚታሰሩበት፣ በሚደፈሩበትና በሚገደሉበት ጊዜ፣…

ሙሉውን አስነብበኝ …

እስራኤልን ለአምስት ዓመታት መርተዋል
አርኤል ሻሮን  Ariel SharonEthiopia Zare (ቅዳሜ ጥር 3 ቀን 2006 ዓ.ም. Jan 11, 2014)፦ የእስራኤል የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩትና ሀገሪቷን ለአምስት ዓመታት ያህል የመሩት አርኤል ሻሮን በሰማንያ አምስት ዓመታቸው ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

በኢትዮጵያ ውስጥ ሥልጣን ሳይኖረው ባለሙሉ ሥልጣን፣ እውቀት ሳይኖረው ባለሙሉ እውቀት የሆነ ሰው ስብሐት ነጋ ብቻ ነው፤ እንዲያውም ከዚያም አልፎ ራሱን የቻለ ሉዓላዊ ነጻነት ያለው ግለሰብ ነው ለማለት የሚቻል ይመስለኛል፤ በዚህ ግለሰብ ላይ የማደንቃቸው ሁለት ነገሮች ናቸው፤ በሉዓላዊነቱ የተጎናጸፈውን ሥልጣን ሙሉ በሙሉ ይጠቀምበታል፤ ይቆጣኛል ወይም ይቀጣኛል ብሎ የሚፈራው የለም፤ ስብሐት ነጋ የሚፈራው ምንም ነገር የለም፤ ሁለተኛ በሉዓላዊነቱ ያለውን ሙሉ ነጻነት በሙሉ ልብ ይጠቀምበታል፤ ናስ በላይ ከበደ እንዳለው ‹‹የቅብጠት መዘላበድ›› ሊሆን ይችላል፤ ስብሐት ነጋ የተናገረው ነገር ትክክል ይሁን አይሁን ጉዳዩ አይደለም፤ ዋናው ነገር መናገሩ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ደራሲሣህለ ሥላሴ ብርሃነ ማርያም
ቅኝትመስፍን ማሞ ተሰማ

መንደርደሪያ
ሥነ ፅሁፍ የሀገር ታሪክ ባህልና የህብረተሰብ ህይወት…በቃላት ደርዝ ተደርዘው ላለውና ለሚመጣው ትውልድ የሥነ ፅሁፍ ጠቢባን የሚያበረክቱት ቅርስ ነው። ጥበብ ነው ሥነ ፅሁፍ፤ የሀቅ መልህቅ። ጥበብን ያላሸተ፤ እውነትንና ፍትህን ያላማጠ፤ ያልወለደ ሥነ ፅሁፍ – ምን ቢኳኳል ቃል በቃል፤ ምን ቢቀማጠል፤ ቢያማልል –  እንኳንና ዘመን ከዘመን ተሻግሮ፤ ትውልድን በትውልድ አጥፎ ‘ዘለዓለማዊ ህልው’ ሊያገኝ ቀርቶ – እንደ ጠዋት ጤዛ አረጋገፉ፤ ፋታም አይሰጥ አሟሟቱ። እንዲህ ያሉ – በየዘመኑ የመከኑ ብዕራት፤ በየዘመኑ ነበሩ፤ ዛሬም አሉ፤ ነገም ይኖራሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ደራሲ – ሣህለ ሥላሴ ብርሃነ ማርያም ቅኝት – መስፍን ማሞ ተሰማ
መንደርደሪያ
ሥነ ፅሁፍ የሀገር ታሪክ ባህልና የህብረተሰብ ህይወት … በቃላት ደርዝ ተደርዘው ላለውና ለሚመጣው ትውልድ የሥነ ፅሁፍ ጠቢባን የሚያበረክቱት ቅርስ ነው። ጥበብ ነው ሥነ ፅሁፍ፤ የሀቅ መልህቅ። ጥበብን ያላሸተ፤ እውነትንና ፍትህን ያላማጠ፤ ያልወለደ ሥነ ፅሁፍ – ምን ቢኳኳል ቃል በቃል፤ ምን ቢቀማጠል፤ ቢያማልል – እንኳንና ዘመን ከዘመን ተሻግሮ፤ ትውልድን በትውልድ አጥፎ ‘ዘለዓለማዊ ህልው’ ሊያገኝ ቀርቶ – እንደ ጠዋት ጤዛ አረጋገፉ፤ ፋታም አይሰጥ አሟሟቱ። እንዲህ ያሉ – በየዘመኑ የመከኑ ብዕራት፤ በየዘመኑ ነበሩ፤ ዛሬም አሉ፤ ነገም ይኖራሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተመስገን ደሳለኝ – አዲስ አበባ
ከሩሲያውያኑ ቦልሼቪክና ሜንሼቪክ አንስቶ፣ የእኛዎቹ ኢህአፓና መኢሶን በፊት-አውራሪነት እስከ ተሳተፉበት ድረስ ያሉ በደም የጨቀዩ አብዮቶች በሙሉ በከተሞች የተካሄዱ ሲሆን፣ አብዛኛው አጋፋሪዎቻቸው ደግሞ ልሂቃኖች እንደነበሩ በጉዳዩ ዙሪያ የተፃፉ ድርሳናት ያወሳሉ፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሄኖክ የሺጥላ
“አወይ ጉዴ ወይ መላ ጉዴ
ብቸኛው ልቤ ሰው በመውደዴ”

ነው ያለው አረጋሃኝ ወራሽ አሁን እንደሱ ልፋትና ጥረት ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያ ሙዚቃ የት በደረሰ። ለነገሩ ይሄ ትውልድ የተሠራውን ሁሉ በመናድ፣ የተጣፈውን ሁሉ በመካድ ነው የሚታወቀው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Bedele Beers በደሌ ቢራክንፉ አሰፋ
በጋዜጠኛ ስህተት የወጣች አንዲት ጽሑፍ ምክንያት 18 ሺህ ፊርማ በኢንተርኔት መሰባሰቡን ሰማን። ጽሑፉን ያሳተመው መጽሔት ስህተቱን አረመ። ይቅርታም ጠየቀ። ዘመቻው ግን እንደቀጠለ ነው። ቴዲ አፍሮ ይንን እንዳልተናገረ መግለጫ ቢሰጥም ጉዳዩ እልባት ሊያገኝ አልቻለም። ከቶውንም አንድነታችንን የማይፈልጉ ምዕራባውያን ጭምር ይህችን ምክንያት በመያዝ ጉዳዩን ማራገብ ጀመሩ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Boy Scout ቦይ ስካውትአበራ ለማ
“አስካውት! …”
“ምን ጊዜም ዝግጁ!!!”
ዱሮ ዱሮና በኛም ዘመን የቦይ ስካውት ክለብ (Boy Scout) እንቅስቃሴ ሞቅና ደመቅ ያለ ነበር። ሰላሌ ፍቼ፣ የአበራና አስፋው ወሰን የ1ኛ ደረጃና ወሊሶ የደጃዘማች ገረሱ ዱኪ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ እያለሁ (ከ1953-1960 ዓ.ም.) የቦይ ስካውት ክለብ አባል ነበርኩ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም Prof. Al-Mariamእ.ኤ.አ. የ2013 ዓመት የኢትዮጵያ የአቦሸማኔው (ወጣቱ ትውልድ) መነሳሳት ሲገመገም
ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ)

እ.ኤ.አ በጃንዋሪ 2013 “እ.ኤ.አ 2013 የኢትዮጵያ የአቦሸማኔው ትውልድ ዓመት ይሆናል” በማለት ትንበያ ሰጥቸ ነበር። እንዲህ ስልም ቃል ገብቸ ነበር፣ “የኢትዮጵያ ወጣቶች ለፍትህና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የሚያደርጉትን ትግል ለመደገፍ እና ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ እንዲል የእራሴን ሙሉ አስተዋጽኦ እንደማደርግ እንዲሁም ትግሉ ወደ አዲስ ምዕራፍ እንዲሸጋገር ወጣቱ ትውልድ እንዲነሳሳ ሳደፋፍር ነበር።”

ሙሉውን አስነብበኝ …

ምስጢሩ The Secretወለላዬ ከስዊድን (ክፍል ስድስት)
ጥሩ ግንኙነት ከሰዎች ለመፍጠር
ማወቅ የሚገባህ የሚስጥሩ ተግባር
አመለካከትህ ያለህ አስተያየት
ካፍህ የሚወጣው የንግግር ቃላት
ከፍላጎትህ ጋር ግጭት እንዳይፈጥር
አጢነህ ተመልከት እራስህን መርምር

ሙሉውን አስነብበኝ …

አማኑኤል ዘሰላም
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር፣ አቶ ይልቃል ጌትነት፣ በውጭ ሀገር የሥራ ጉብኝት እያደረጉ እንደሆነ በስፋት እየተዘገበ ነው። ታዲያ “ስለ ሰማያዊ ብዙ እየሰማን፣ የአንድነት ፓርቲ ድምፅ ግን ምነው ጠፋ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Ethiopian ariforceየኢትዮጵያ አየር ኃይል ለዳግመኛ ክህደት እንዳይዳረግ

ግንቦት 83/91 ላይ የኢትዮጵያ ሰማይ ክፉኛ በኀዘን ሲመታ፣ ደመናው ሲጠለሽ፤ ወንዞች መደፈራረስ ሲጀምሩ፤ የሰውን ልብ ባር ባር ሲለው … የክፉው ቀን ጅማሮ፣ የውርደት ሃሌታ፣ የሀገር አልባነት ስሜትና የዜግነት ውርደት ደጃፍ ላይ መውደቃችን እውነት ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ግርማ ካሳ

በሕዝብና በሀገር ላይ ጥቃት ሲሰነዘር የሀገሪቷ መሪ ህዝቡን የመምራትና የማረጋጋት ኃላፊነት አለባቸው። ሳዑዲዎች በኢትዮጵያውያን ላይ አሰቃቂ ግፍ በፈጸሙ ጊዜ፣ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፣ ከመምራት ይልቅ ዝምታን መርጠው፣ አንዴ በካታር፣ ሌላ ጊዜ በፖላንድ ሲሽከረከሩ እንደነበረ ሁላችንም የምናውቀው ነው። “ጠ/ሚኒስትሩ የት ነው ያሉት?” የሚል ጥያቄና ትችት እየጠነከረ በመጣ ጊዜ፣ ከሣምንታት በኋላ ብቅ አሉ። በኢቲቪ ቃለ መጠይቅም አደረጉ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

 

አልክስ አብርሃም

አባቴ ስድስት ልጆቹን ሰበሰበና የመረረ ነገር ሲኖር ብቻ የሚጠቀምበትን ሰማያዊ ሽፋን ያለውን አጀንዳውን ፊቱ ዘርግቶ ስብሰባውን ከፈተ (ስለዚህ አጀንዳው ሌላ ቀን በሰፊው እና ወራለን)! ገና ከመጀመሪያው የእለቱን አጀንዳ ሲያስተዋውቅ ነበር ሁላችንም የደነገጥነው ‹‹ /ማንያህልሻል ተክሌን የሚመለከት ነው ›› ሲል ግራ ተጋባን …… የእናታችን ስም እንዲህ እንደባቡር ሃዲድ ረዝሞ ያውም በአባታችን ሙሉውን ሲጠራ ሰምተን አናውቅም! ማኑየ ….የኔገላ ….ወለላየ ነበር በደጉ ቀን ሲጠራት! ሌላው ያጨናነቀን ነገር አባባ የእናታችንን ስም እንዲህ ያራዘመ ዋናውን ጉዳይማ እስከ ነገወዲያም አይጨርሰው የሚል ስጋ ትነበር!

ሙሉውን አስነብበኝ …

ከእየሩሳሌም አርአያ
ኒቆዲሞስ ዜናዊ የአቶ መለስ ዜናዊ ወንድም ነው። ከወ/ሮ አለማሽ ገ/ልኡልና ከአቶ ዜናዊ አስረሳኸኝ የተወለዱ ወንድማማቾች ናቸው። ኒቆዲሞስ በደርግ ስርአት በክብሪት ፋብሪካ ተቀጥሮ በተራ ሰራተኝነት ይሰራ ነበር። የአካል ጉዳተኛ (አንድ እግሩ) የሆነው ኒቆዲሞስ ከተራ ወዝአደርነት ወጥቶ ሚሊየነር ለመሆን የበቃው ደርግ ወድቆ ሕወሐት/ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተመስገን ደሳለኝ

በድህረ-መለስ ኢትዮጵያ የፖለቲካው ሥልጣን በስርዓቱ ልሂቃን መካከል ከሚደረገው የኃይል መተናነቅ አንጻር፣ ዛሬም ከመፈራረቅ ጣጣው የተላቀቀ የማይመስልባቸው ምልክቶች መታየታቸው እንደቀጠለ ነው፡፡ ከአራት ወር በፊት በዚህ መፅሄት ላይ ‹‹አዲሱ የኢህአዴግ አሰላለፍ›› በሚል ባቀረብኩት ፅሁፍ በገዥው ፓርቲ ውስጥ ተፈጥሮ ከነበረው ክፍፍል የትኛው ቡድን የበለጠ ጉልበት አግኝቶ በአሸናፊነት መውጣት እንደቻለ ከገለፅኩ በኋላ ፅሁፉን የቋጨሁት እንዲህ በማለት ነበር፡-

ሙሉውን አስነብበኝ …

ክንፉአሰፋ

New book by Fkreselase Wegderesፀሃይ አሳታሚ ድርጅት በታኅሣሥ 16, 2006 ዓ/ም (Dec. 25, 2013)  የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩትን የሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስን ‘እኛና አብዮቱ’ የሚል መጽሃፍ  ለገበያ እንደሚያበቃ አስታወቀ። ሻምበል ፍቅረሥላሴ እንደ ደርግ አባልነታቸው በጋራ ያመኑበትን፣ የተማከሩትን፣ የወሰኑትን፣ የሰሩትን፣ የገጠማቸውንና በቅርብ በዓይን ምስክርነት ያዩትን ተንትነው በ‘እኛና አብዮቱ’ ያስነብቡናል። የራሳቸውን ዕይታ ያካፍሉናል።

ሙሉውን አስነብበኝ …