ቃላትን ማባከን!
በልጅግ ዓሊ
በ ርመን ውስጥ እንደ አውሮፓውያን አቆጠጠር 1971 ምሮ የዓመቱ ምርጥ ቃል ይመረጣል። ይህ በየዓመቱ የሚደረገው ምርጫ አዲስ የተፈጠሩ አባባሎች ወይም ቃላቶች አሮጌም ቢሆኑ በአለፈው ዓመት ውስጥ የአጠቃቀማቸው ሁኔታ ታይቶ የሚካሄድ ብሂል ነው። ለአሸናፊነት የሚበቃው ቃል በሕብረተሰቡ ውስጥ ተቀባይነት ያገኘው ይሆናል። ምርጫው በኮሚቴ ዳኝነት ተሳታፊዎቹን ቃላቶች አወዳድሮ ከፍተኛ ድምጽ ያገኘውን አሸናፊ ያደርጋል።