ግርማ ጌታቸው ካሳ

አይኖቼ በደም ቀሉ። ልቤ ተሰበረ። ከሳውዲ አረቢያ፣ ከባህር ማዶ፣ የወገኖቼ ጩኸትና ሮሮ፣ ከጣራዬ በታች የመነጨ ይመስል፣ በጆሮዬ በቅርበት ያቃጭላል። በርግጥ እንደ አገር፣ እንደ ሕዝብ፣ እንደ ኢትዮጵያዊ መዋረዳችንን አየሁ። በተለይም ደግሞ በአሁኗ ሰዓት፣ እንደ ወገን ምንም ማድረግ ባለመቻሌ ውስጤ ደበነ። የማድርገውን ሳጣ መሬት ተንበረከኩ። አይኖቼን ወደ ላይ አንስቼ፣ እጆቼን ዘረጋሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ቦጋለ ዳኜ – ከካሊፎርንያ
ቅኔ፤ ግጥምና የተለያዩ ድርሰቶች ባጠቃላይ ሲጠሩ ‘ሥነ ጽሑፍ’ ይባላሉ። ሥነጽሑፍ የሚለው ሐረግ ጥሬ ትርጉም ‘የጽሑፍ ውበት’ ማለት ነው። ለሥነጽሑፍ ይህ ስያሜ የተሰጠበት አንዱ ምክንያት ድርሰቶች ሲጻፉ በቃል አመራረጥ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ መሆኑን፤ ሥነ ጽሑፍ መዋብ እንደሚገባው ለመግለጽ ጭምር ይመስለኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ላለፉት ሰባት ዓመታት በዐረብ ሀገር የኖረችና ከአራት ወራት በፊት ነዋሪነቷን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገች ወጣት ኢትዮጵያዊት፣ ከኢትዮቲዩብ ጋር ባደረገችው ቃለምልልስ በዐረብ ሀገር የነበራትን ቆይታ፣ በሀገር ቤትም ያለውን ችግር፣ የኢትዮጵያን ኤምባሲ በተመለከተ በግሏ የደረሰባትን ስትገልጽ ልብ ትሰብራለች። ትናንት ኅዳር 5 ቀን 2006 ዓ.ም. (ኖቨምበር 14፣ 2013 እ.ኤ.አ.) ዋሽንግተን ዲሲ በሳዑዲ ዐረቢያ ኤምባሲ በርካታ ኢትዮጵያውያኖች የተቃውሞ ሰልፍ ባደረጉበት ወቅት ነበር ኢትዮቲዩብ ያናገራት። 

 

የህግ ባለሙያው ዶ/ር ሸክስፒር ፈይሳ ንግግር ያደርጋል

አሁንም የኢትዮጵያዊያኖች የድረሱልኝ ጥሪ እየተሰማ ነው(ቪድዮዎችን ይመልከቱ)

Ethiopia Zare (ሐሙስ ኅዳር 6  ቀን 2006 ዓ.ም. November 30, 2013)በካናዳ የንግድ መናገሻ በሆነችው ቶሮንቶ ከተማ በሳኡዲት አረቢያ በኢትዮጵያዊያኖች ላይ የሚፈጸመውን ግፍ በመቃወምና በአሰቃቂ ሁናቴ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የሻማ ማብራት ስነስርአት ነገ አርብ እንደሚካሄድ ይፋ ተደረገ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

(ተመስገንደሳለኝ)
…ኢሠፓ መራሹ መንግስት በኢህአዴግ ከተተካ ጥቂት ወራት ቢያልፈውም፣ የተራዘመው የእርስ በእርስ ጦርነት ያልደረሰባቸው በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙ አንዳንድ ከተሞችን ገና በቅጡ አልተቆጣጠራቸውም፤ በአናቱም በኢሠፓ መንግስት ሽንፈት ሳቢያ እንዲበተን ከተገደደው የ ገሪቱ መደበኛ ወታደር፣ አብዛኛው ከእነ ትጥቁ የትውልድ መንደሩንና ቤተሰቡን መቀላቀሉ በ ገሪቱ ላይ ከባድ ፍርሃት አንብሯል፤ በሰላም ወጥቶ ለመመለስ እርግጠኛ መሆን የማይቻልበት ከበባዊ አየርም አስፍኗል፡፡ በበርካታ ቦታዎች ተጠንተውና ታቅደው የሚፈፀሙ ወን ሎችም፣ ከአምስት እስከ አስራ አምስት በሚደርሱ ወታደሮች የተደራጁ ልዩ ልዩ ህገ-ወጥ ቡድኖች በየማዕዘኑ እያቆጠቆጡ መሆኑን አመላክቷል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

ነብዩ ሲራክ

የማለዳ ወግ

በሪያድ መንፉሃ በተከሰተው ሁከት ግራም ነፈሰ ቀኝ ተጎጅዎች እኛ ነን! እንኳንስ ሰው ተደብድቦ ፣ ሞቶባቸው፣ እንኳንስ መኪና ተሰብሮባቸው እንዲያውም እንዲው ናቸው። ከማለዳ እስከ ሌሊት የዘለቀውን ሁከት መቆጣጠር ይቻል ዘንድ ገና ሲ መር አቅጣጫውን አይተው የመንግስት ተወካዮችን የመከሩ በርካታ ነበሩ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ክንፉ አሰፋ

ወገናችንን በጥይት ሲደፉት በራሱ ላይ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ባንድራችንን ጠምጥመውበታል። ጭካኔ በተሞለበት መንገድ የተገደለው ይህ ኢትዮጵያዊ አስከሬኑም በሰላም አላረፈም። በአካሉ ላይ ያረፈውን ጨርቅ በሴንጢ እየቆራረጡ በሰብአዊ ፍጡር ላይ ሊደረግ የማይገባውን ሁሉ አደረጉበት። ድርጊቱ ናዚዎች በኦሽዌትስ ይፈጽሙት የነበረውን አሰቃቂ ግፍ ያስታውሰናል። በ21ኛው ዘመን እንዲህ አይነቱ ክስተት ይደገማል ብሎ የሚያስብ የለም። እነሆ ሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየፈጸመችው ነው። በስውር ሳይሆን በግልጽ። እንደ ኦሽዊትስ በታጠረ የማጎርያ ካምፕ ሳይሆን በአደባባይ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጠበቃ ስቴላ ያርዴእንቅስቃሴውን የጀመሩት ስዊድናዊ ጠበቃ ከኢትዮጵያውና ጋር ውይይት አደረጉ
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ኅዳር 3 ቀን 2006 ዓ.ም. Nov. 12, 2013)፦ ባለፈው ቅዳሜ ጥቅምት 23 ቀን 2006 ዓ.ም. (ኖቬምበር 2 ቀን 2013) የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ መድረክ በስዊድን የወያኔን መንግሥት በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ለማቅረብ የተጀመረውን ክስ መነሻ በማድረግ የክሱን ሂደት ከሚመሩት ከስዊድናዊው ጠበቃ ከስቴላ ያርዴ እና ከሌሎች እንግዶች ጋር በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ወይይት አደረገ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በተለያዩ ዐረብ ሀገራት በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው በደልግሩም ተ/ኃይማኖት
ይድረስ ያልኩት በቀጥታ ባይደርሶትም መስማትዎ እንደማይቀር እገምታለሁ። ሰላም የምሎት ሰላምታ የእግዚአብሔር በመሆኑ ነው። እንጂ ጫንቃችን ላይ ተጎብራችሁ የዜግነት ክብንርን አውርዳችሁ የዜግነት ክብር የምታዘምሩ በሆናችሁ፣ በብሔር፣ በጎሳ ከፋፍላችሁ … ሰብዓዊ መብታችንን ገፋችሁ … ኑሮን መቋቋም እንዳንችል አድርጋችሁ ለስደት ስለዳረጋችሁን ሰላምስ ማለት አይገባም ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የስደተኛው ማስታወሻ በተስፋዬ ገብረአብ Yesedetegnaw Mestawesha by Tesfaye Gebreabበይምርሐነ ክርስቶስ ጣራ ላይ የሚገኘው የዳዊት ኮከብዳንኤል ክብረት

ባለፈው ሳምንት ተስፋዬ ገብረ አብ አቡነ ተክለኃይማኖትን በተመለከተ ያነሣቸውን ነጥቦች ማየት ጀምረን ‘የሦስቱን ተክለ ሃይማኖቶች’ ጉዳይ ለዛሬ አቆይተነው ነበር። እንቀጥል።

1) የሰባተኛው መክዘ ተክለኃይማኖት
ተስፋዬ የጠቀሳቸው የሰባተኛው መክዘ ተክለኃይማኖት የሉም። እስካሁንም እንደርሱ ፈጠራቸውን የሚናገሩ እንጂ ማስረጃ ያመጡ አልተገኙም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሀገሬ

በዚህ ዓመት በኢትዮጵያ ሙስናን አስመልክቶ ይሀ ለሰባተኛ ጊዜ ያቀረብኩት ትችት በማዕድኑ ዘርፍ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ በሙስና ላይ ያቀረብኳቸውን ሌሎችን ትችቶች “Al Mariam’s Commentaries” የሚለውን ድረ ገጽ በማየት ግንዛቤ መውሰድ ይቻላል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

ዳንኤልክብረት
ተስፋየ ገብረ አብ ‹የስደተኛው ማስተዋሻ› የተሰኘ መጽሐፍ ማውጣቱንና ባነበው መልካም እንደሆነ ገልጦ አንድ ወዳጄ ‹ስስ ቅጅውን› ከ ገረ አሜሪካ ላከልኝ፡፡ ከዚህ በፊት ሌሎች መጻሕፍቱን አንብቤያቸዋለሁ፤ በአጻጻፍ ችሎታው የምደሰተውን ያህል እንደ አበሻ መድኃኒት ነገሩን ሁሉ እርሱ ብቻ የሚያውቀው ምስጢር ስለሚያደርገው፤ በአንዳንድ ጉዳዮችም ሆን ብሎም ሊያናጋቸው የሚፈልግ ኢትዮጵያዊ እሴቶች ያሉ ስለሚመስለኝ፤ ተስፋዬ ለምን እንደዚህ ይጽፋል? እያልኩ የምጠይቃቸው ነገሮች ነበሩ፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

Normal
0

false
false
false

MicrosoftInternetExplorer4

/* Style Definitions */
table.MsoNormalTable
{mso-style-name:”Table Normal”;
mso-tstyle-rowband-size:0;
mso-tstyle-colband-size:0;
mso-style-noshow:yes;
mso-style-parent:””;
mso-padding-alt:0cm 5.4pt 0cm 5.4pt;
mso-para-margin:0cm;
mso-para-margin-bottom:.0001pt;
mso-pagination:widow-orphan;
font-size:10.0pt;
font-family:”Times New Roman”;
mso-fareast-font-family:”Times New Roman”;
mso-ansi-language:#0400;
mso-fareast-language:#0400;
mso-bidi-language:#0400;}

(ፕ/መስፍንወልደ ማርያም)

 

ወያኔና የነፖሊቲካ አጋሮቹ የሚያደርጉትን ለእነሱ የሚመች አከፋፈል ትተን አበሻን ለሁለት እንክፈለው፤ ሆድ ያለውና ሆድ የሌለው፤ ወይም የሚበላና የማይበላ፤ ዛሬ የምናገረው ሆድ ስላለው ወይም ስለሚበላው አበሻ ነው፤ አታውቁት እንደሆነ ተዋወቁት፤ በአጠቃላይ ስንመለከተው ግን የአበሻ ፍቅርም ሆነ ጠብ ለሆድ ነው፤ አበሻን የሚያጣላው፣ የሚያነታርከው፣ የሚያቧጭቀው የሆድ ነገር ነው፤ ለመብላት ነው፤ አንዳንዴም ሎሌውን ለማብላት ነው፤ ግብር ለማግባት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

(ተመስገን ደሳለኝ)
ገራችን መንግስታዊ አስተዳደር የ‹‹ቁማር ህግ››ን ችግር መፍቻ አድርጎ መጠቀም የ መረበትን ጊዜ ለማስላት ንጉሰ ነገስት ዳግማዊ ምንሊክ እንደ”ተበሉበት” ከሚነግረን የሽኩሹክታ ታሪካችን አንስቶ አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት… እያልን ለመቁጠር እንገደዳለን፡፡ ይሁንና ባለሙያ (በንባብ የደረ ) ቁማርተኛ ፖለቲከኛ እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛበት ድንገቴ ክስተት የ1966ቱ አብዮት ዋዜማ ነው ቢባል ወደ እውነታው ይጠጋል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

Ethiopia Zare (አርብ ጥቅምት 23 ቀን 2006 ዓ.ም November 1, 2013):- ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል በእስር ላይ የሚገኘውን የብእር ሰው፣ ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ ባለቤቷን እስክንድር ነጋን ተለይታ ከምትኖርበት ዋሽንግተን ዲሲ የሀገሯን የመጨረሻ ስንብት በሚመለከት ለህሊና እስረኞች ለሆኑት ታሳሪዎች ያስተላለፈችው መልእክት ይፋ ተደረገ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Ethiopia Zare (አርብ ጥቅምት 23 ቀን 2006 ዓ.ም November 1, 2013):- ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል በእስር ላይ የሚገኘውን የብእር ሰው፣ ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ ባለቤቷን እስክንድር ነጋን ተለይታ ከምትኖርበት ዋሽንግተን ዲሲ የሀገሯን የመጨረሻ ስንብት በሚመለከት ለህሊና እስረኞች ለሆኑት ታሳሪዎች ያስተላለፈችው መልእክት ይፋ ተደረገ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Prof. Al Mariam ፕ/ር ዓለማየሁ ገብረማርያም ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም፦ ነጻነት ለሀገሬ)
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ሕገመንግሥት በሕግ ከለላ ጥላ በቁጥጥር ስር የሚውሉ ዜጎችን አስመልክቶ የሚከተሉትን መብቶች ያጎናጽፋል። “በሕግ ከለላ ጥላ በቁጥጥር ስር የዋለ ማንኛውም ሰው በሕግ አግባብ መብቱ ተጠብቆ ይያዛል። ማንኛውም ሰው በሀሰት ለመረጃ ጠቀሜታ ተብሎ በማስገደድ እንዲያምን ወይም የተባለውን እንዲቀበል አይገደድም። ማንኛውም በማስገደድ የተገኘ መረጃ ተቀባይነት አይኖረውም።” ይላል አንቀጽ 19(2)(5)። እውነታው ሲታይ ግን ይህ የይስሙላ ሙበት የተጻፈበትን ወረቀት ዋጋ ያህል የለውም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

 

ኢትዮጵያዊያን በፍርዱ ረክተዋልወ/ሮ ሙሉመቤት ረታ (በሲያትል ኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀመንበር)

በእኔ አስተያየት ፍትህ ተበይኗል፤ ዳኛዋም ሆኑ ፍርድ ሰጭዎቹ (ጁሪዎቹ) በትክክል ጉዳዩን አይተው ወስነዋል ብየ አምናለሁዶ/ር ሸክስፒር ፈይሳ

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥቅምት 20  ቀን 2006 ዓ.ም. October 30, 2013)፦ ከሁለት ዓመት በፊት ሃና ዊሊያምስ የተባለችውን ታዳጊ በቅዝቃዜ ደጅ ላይ በማዋልና በማሳደር አሰቃይተው ገድለዋል የተባሉት አሳዳጊዎቿ ኬሪ ዊሊያምስና ባለቤቷ ላሪ ዊሊያምስ የ37 ዓመትና የ29 አመት ጽኑ እስራት የተወሰነባቸው ሲሆን በሲያትል አካባቢ የሚኖሩ ትዮጵያዊያን በፍርዱ መደሰታቸውን በተለይ ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የአውራምባ ታይምሱ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ Dawit Kebede of Awramba Timesጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ከስደት ለምን ተመለሰ?
“እኔ ወደ ሀገሬ ለመምጣት ከማንም ጋር አልተደራደርኩም” ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ

የአውራምባ ታይምሱ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ወደ ሀገር ቤት መመለሱን ኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ መዘገቧ አይዘነጋም። ዳዊት ኢትዮጵያ ከገባ በኋላ በሀገር ውስጥ የሚታተመው ሰንደቅ ጋዜጣ በ8ኛ ዓመት ቁጥር 425 የረቡዕ ጥቅምት 20/2006 ዓ.ም. ዕትሙ ከዳዊት ጋር ያደረገውን ቆይታ እንደወረደ እንደሚከተለው አቅርበነዋል። ቃለምልልሱን ያደረገው ጋዜጠኛ ዘሪሁን ሙሉጌታ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የፓርላማው አባል የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕግ አማካሪ ሆኑ

በዮሐንስ አንበርብር

(ሪፖርተር ረቡዕ ጥቅምት 20 ቀን 2006 ዓ.ም. Oct. 30, 2013)፦ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አቅራቢነትና በፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ አማካይነት የጄኔራል መኮንኖች ሹመት ከተካሄደ በኋላ፣ በመከላከያ ሠራዊቱ አመራሮች ላይ የኃላፊነት ሽግሽግ ተካሄደ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አቶ በረከት ስምኦን Bereket Simonየሹመቱ አግባብነት ጥያቄ አስነስቷል
አፈጉባዔ አባዱላ ጠ/ሚኒስትሩ በሹመቱ ላይ ማብራሪያ ለመስጠት አይገደዱም አሉ

በፍሬው አበበ
(ሰንደቅ ጋዜጣ ረቡዕ ጥቅምት 20 ቀን 2006 ዓ.ም. Oct. 30, 2013)፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ለኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሥራ አመራር ቦርድ ኃላፊነት ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ ያቀረቡትን ሹመት ተቀብሎ አጸደቀ። በዚሁ መሠረት ድርጅቱን ለረዥም ጊዜ በቦርድ ኃላፊነት ባገለገሉት በአቶ በረከት ስምኦን ምትክ አቶ ሬድዋን ሁሴን የድርጅቱ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሹመዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ዳዊት ከበደ እና ተስፋሁን ጫመዳ Dawit Kebede and Tesfahun Chemedaአቤ ቶኪቻው

ዳዊት ከበደ እና ተስፋሁን ጫመዳ

ተስፋሁን ጫመዳ የተባለ አንድ ወጣት ኢትዮጵያዊ ነበር። የገዢው ግንባር ኢህአዴግ ነገረ ሥራ አልመችህ ቢለው በተለያየ አጋጣሚ “ተው!” ማለት ጀመረ። ኢህአዴግዬ ግን ተው ባይ አይወድምና በክፉ ዓይኑ ተመለከተው። ይሄኔ ተስፋሁን የሚመጣበትን ጦስ ሸሽቶ መጪው ጊዜ መልካም እንደሚሆን ተስፋ አድርጎ ‘እስኪያልፍ ያለፋል’ ብሎ ሀገሩን ትቶ ተሰደደ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ከቡርቃ ዝምታ እስከ የስደተኛው ማስታወሻ

Yesedetegnaw Mestawesha by Tesfaye Gebreab የስደተኛው ማስታወሻ በተስፋዬ ገብረአብመስፍን አማን (ከሃርለም፣ ኔዘርላንድ)

ከጥቂት ሳምንታት በፊት አንድ ቅዳሜ ሻይ ቡና ለማለት አምስተርዳም ከወዳጆቼ ጋር በነበረኝ ቀጠሮ ላይ እንደአጋጣሚ ተስፋዬም በመሃላችን ተገኝቶ ነበር። የባጥ የቆጡን ስናወራ፣ ስለአዲሱ የተፋስዬ መጽሐፍ አንስቶ የውይይታችንን አቅጣጫ ቀየረው። በመሃሉ ተስፋዬ፣ ከመጽሐፉ ውስጥ አንዳንድ የማልወዳቸው ምዕራፎች ቢኖሩ ትችቶቹን የምቀበል ስለመሆኔ አስረግጦ ጠየቀኝ?።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይሄይስ አእምሮ

“የአፄ አብርሃም ያዬህን ጽሑፍ አንብበን ስንጨረስ ነገር ማብላላታችንን ትተን ዝም ብለን መጋደም አልቻልንም። ዘመናችን ብዙ የሚሠራበት ሣይሆን ብዙ የሚወራበትና የሚጻፍበት መሆኑን እናውቃለንና አግራሞታችን ወሰን አልነበረውም። ጥሎብን “ሌላ ሥራ የላቸውም ወይ?” እስክንባል ድረስ በዬቀኑ ብዙ እናነ(ብ)ባለን፤ ስለዚህም ሲሆን በምታዘበው ሁሉ እናነባለን።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ – ከአዲስ አባባ

እነሆ ይቺ ገር ኢትዮጵያ ናትና የመብት (የለውጥ) ጥያቄዎች፣ እንደ አህጉር ተጋሪዎቿ ሁሉ መልስ የሚያገኙት ከአደባባይ ጩኸት ብቻ ይሆን ዘንድ ባህል ሆኖአል፡፡ ትውልድ ተሻጋሪ ታሪኳም የሚነግርህ በየወቅቱ ከተፈራረቁ ገዥዎቿ አንዳቸውም እንኳ ለህዝብ ፍላጎትና ውሳኔ ተገዝተው አለማወቃቸውን ነው፤ ጠመንጃ አሊያም ተፈጥሮ ወደ ግብአተ መሬት ካልሸኛቸው በቀር

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ Journalist Dawit Kebede(ቪዲዮ አለው)

“እጅግ አስደንጋጭ ዜና ነው” ሀገር ቤት ያሉ ጋዜጠኞች

Ethiopia Zare (ዓርብ ጥቅምት 15 ቀን 2006 ዓ.ም. Oct. 25, 2013)፦ በሀገር ቤት ይታተም የነበረው “አውራምባ ታይምስ” ጋዜጣ እና የድረ ገጹ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ከሁለት ዓመት በሰሜን አሜሪካ የስደት ቆይታ በኋላ በዛሬው ዕለት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚበር ገለጸ። በጉዳዩ ላይ ከአቶ ያሬድ ጥበቡ ጋር በቪዲዮ ቃለምልልስ አድረጓል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Prof. Al Mariam ፕ/ር ዓለማየሁ ገብረማርያም ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)
ታላላቅ የአፍሪካ መሪዎች ህልም አላቸው፤ ቀሪዎቹ በቅዠት የተሞሉ ናቸው።

በቅርቡ የአፍሪካ መሪዎች ቢያንስ በአፍሪካ ህብረት ስልጣን ያላቸውና የእነርሱ ጋሻ ጃግሬዎች ስለህግ ልዕልና፣ ስለዘር ማደን (ማሳደድ) የማያቋርጡ አስደንጋጭ የቅዠት ሪፖርቶች በገፍ እያቀረቡ ነው። ቅዠታቸውም የፍትህ ጎራዴ ስያሳድዳቸው በላብ ተጠምቀው ከእንቅልፍ ይነቃሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም Prof. Mesfin Woldemariamፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

በአሥራ አምስተኛው ምዕተ-ዓመት ግድም ሆላንድ የታወቀ የባሕር ኃይል ሆኖ ከደቡብ አፍሪካ እስከደቡብ አሜሪካ፣ የኔዘርላንድ የቆዳ ስፋት 41 526 ኪ.ሜ. ካሬ ወይም የትግራይ ግማሽ ነው፤ የሕዝቡም ቁጥር አሥራ ስድስት ሚልዮን ተኩል አይሞላም። የትግራይን ግማሽ በሚሆን መሬት ላይ የትግራይን ሦስት እጥፍ ግድም የሚያህሉ ሰዎች ይኖሩበታል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ወ/ሮ አዜብ መስፍን Azeb Mesfinኢዮብ ይስኃቅ

ከዕለታት አንድ ቀን ባልተለመደ ድፍረት የሙስና ኮሚሽን ሰይፉን ትላልቅ የወያኔ ባለሥልጣናት ላይ አሳረፈ። እንደመድኃኒት ብልቃጥ እዚህም እዚያም ተወሽቆ የነበረ ብርና ንብረት እያስቆጠረ ወንጀለኞቹን ዋስ እየከለከለ ወደ ወህኒ ወረወረ። ሚኒስትሮች ከቦታቸው ተፈናቀሉ፤ የሙስና እናት የሚለውን ሜዳሊያ ያጠለቀችው ወ/ሮ አዜብ ከኤፈርት ተባረረች። ያዲሳባ ከንቲባነትም ሱሚ ነው ተባለች። ከሁለት ብቻ ሳይሆን ከብዙ ያጣች ሆነች። ህዝቡ እልል ለማለት ቢፈልግም ወያኔን ስላላመነ መጨረሻውን ለማየት መጠባበቅ ያዘ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አቶ አብርሃም ያየህ Abraham Yayehውይይት ከግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ
ክፍል ሁለት፣ ምዕራፍ ሁለት
አብርሃም ያየህ

“አቶ ኢሳያስ አፈወርቂና ሌሎች የህዝባዊ ግንባር ለፍትህና ለዲሞክራሲ መሪዎች በሁለቱ ሀገሮች [ኢትዮጵያና ኤርትራ] መካከል ያለው ወሰን ትርጉም የሌለው በመሆን ላይ ነው እስከማለት ደርሰው ነበር። ጥቂት የግንባሩ ከፍተኛ ካድሬዎች በመጨረሻ ኤርትራና ኢትዮጵያ በፌደሬሽን መሰረት ላይ የሚተባበሩበት [የሚተሳሰሩበት] ሁኔታ እስከሚፈጠር ድረስ የውህደትና የኮንፌደሬሽን መዋቅሮች እየተጠናከሩ መራመድ እንደሚኖራቸው ሃሳብ ሰጥተዋል”

ሙሉውን አስነብበኝ …

“ህወሓት መለስ ከነበረበት በጣም የጠነከረ ድርጅት ይሆናል”አቶ ስብሃት ነጋ
አቶ ስብሃት ነጋ Sibhat Nega

Ethiopia Zare (እሁድ ጥቅምት 10 ቀን 2006 ዓ.ም. Nov. 20, 2013)፦ ሰሞኑን በአሜሪካ ለሚገኙት የህወሓት መስራችና የቀድሞ ሊቀመንበር ለአቶ ስብሃት ነጋ የዘኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ደረጀ ደስታ እስከዛሬ ተጠይቀው የማያውቋቸውን ጥያቄዎች አቅርቦላቸዋል። ቃለምልልሱን ጋዜጣው ላይ በቅርብ ይዞት የሚወጣ ሲሆን፣ ይኸንኑ ቃለምልልስ ለኢትዮጵያ ዛሬ በድምፅ ልኮልናል። ከተጠየቋቸው ጥያቄዎ ውስጥ ከህወሓት ማዕከላዊ አባልነት እንዴት ወደ ተራ አባልነት እንደተሻገሩ፣ ከወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር ያላቸውን ጠብ፣ ከአቶ መለስ ጋር የነበራቸውን አለመግባባት፣ የአቶ መለስ ደካማ ጎን፣ ሙስኝነትን፣ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ላይ ያላቸውን ውግዘት፣ ስለፕሬሱ፣ … ይገኙበታል። (ለማዳመጥ የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!)

{play}images/doc/audio/2013/131020-sibehat-nega-interview-with-zethiopia.mp3{/play}

አብርሃም ያየህ (ክፍል ሁለት)
ላንዳንድ ሰዎች፣ ወይንም ለበርካታ ሰዎች ማለት ይቻላል፣ ሀገር ማለት ጮማ የሚቆርጡበት፣ ጠጅ የሚጋቱበት፣ ለሽርሽር የሚሄዱበት፣ ወንዙን ተራራውን እየጠሩ በግጥምና በስድንባብ የሚመፃደቁበት፣ የሚጨፍሩበትና የሚዘሉበት፣ ወዘተ ብቻ ይመስላቸዋል። በጣም የሚገርመውና የሚያሳዝነው ደግሞ፤ ሌላው የፖለቲካ ሱስ ያለበት ይመስል፣ ከፖለቲካ ገለልተኛ ነኝ፣ ፖለቲካ አልወድም፣ ኃይማኖተኛ ነኝ፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዋጋ የለውም ወዘተ. የሚሉ ጉዶች አሉ። አንዳንዶቹማ፣ መታገሉንና ላገር መቆርቆሩ ቀርቶ፤ ነብሳቸውን ሽጠው ከሚታገሉ ሰዎች ጋር ላለመታየት እንኳ ሲንጰረጰሩ ማየት ትውልዱ ምን ያህል እንደከሰረ የሚያመለክት ነው። ይቺን አጋጣሚ ተጠቅሜ፣ ባለፈው ዓመት እዚህ ከምኖርበት ዴንማርክ ያጋጠምኝን አብነታዊ ክስተት ላካፍል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አብርሃም ያየህ (ክፍል አንድ)

የኤርትራን ነፃነት በተመለከተ የወያነ መሪዎችና ቲፎዞዎቻቸው ሁሌም ሊያስረዱን የሚፈልጉት፣ ኤርትራ ነፃነቷን ያገኘችው በነሱ ፍላጎት ሳይሆን፤ ሻዕቢያ ኢትዮጵያን በጦርነት አሸንፎ ኤርትራን ስለተቆጣጠረ ምንም ማድረግ የሚቻል ነገር ያለመኖሩን ነው። ይሁን እንጂ ይህ ትክክለኛ መግለጫ አይደለም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ወለላዬ ከስዊድን (ክፍል አራት)

The Secret ሚስጢሩ

ሚስጢሩ አሁን በኃይለኛ ሂደት ላይ ወቷል። እርስዎም የውለታ ምስጋናን፤ የሚፈልጉትን ነገር በዓይነ ህሊና አስቀድሞ ማየትን፤ የተግባር ኃይልን ሂደቶች የሚረዱበት ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል ማለት ነው። ለመሆኑ አስቀድመው ይሄን ሁኔታ የተሸጋገሩ ምን ይላሉ?

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይሄይስ አእምሮ

በሀገራችን የስም አወጣጥ ወግና ልማድ እልም ያለችዋ ጥሩራ ባሪያ “አልማዝ” ወይም “ፀሐይ”፣ በነጭናጫነቷና በምግባረ ብልሹነቷ መንደርተኛው ሁሉ የሚያውቃት ሴት ወይዘሮ “ዐመለወርቅ” ወይም “አበቅየለሽ”፣ እልም ያለው ቦቅቧቃ “ደም መላሽ” ወይም “ሺመክት”፣ ቤሣቤስቲን የሌለው የኔቢጤው መናጢ ድሃ “ሀብታሙ” ወይም “አዱኛ”፣ እንዴት ያለው ንፉግና ክፉ ሰው “ቸሩ” ወይም “ደጉ”፣ … ተብሎ ሲጠራ እናውቃለን።

ሙሉውን አስነብበኝ …

 

 ከፕሮፌሰር መስፍን /ማርያም

እንደ ኢትዮጵያ ባለ ኋላቀር አገር አገር ውስጥ መሠልጠን ብዙ ችግር አለበት፤ እኔ ራሴ በኮምፒዩተር መጻፍ ከጀመርሁ ሠላሳ ዓመት ሊሆነኝ ነው፤ ታዲያ መብራት ጠፋና የምሠራው ባጣ የቆዩ ወረቀቶችን ሳገላብጥ አንድ እአአ በዲሴምበር 26 1965 ከዱሮ ተማሪዬ የተጻፈልኝን ደብዳቤ አገኘሁ፤ በዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በነበረ ከአንድ በጣም ጎበዝ ወጣት የተላከልኝ ነበረ፤ ከተመረቀ በኋላ በአንድ ኩባንያ ውስጥ ተቀጥሮ ለጥቂት ዓመታት ሠርቶ ትምህርቱን ለመቀጠል ወደ አሜሪካ ሄዶ በሎዝ አንጄለስ አካባቢ ከሚገኝ ትምህርት ቤት ገብቶ ነበር፤ ደብዳቤውን የጻፈልኝ ከዚያ ነው፤ ደብዳቤው ሰባት ገጾች አሉት፤ ከሰባቱ ገጾች አምስቱ ስለኢትዮጵያ ያለውን ስጋት የሚገልጽ ነው፤ በሎዝ አንጀለስ አካባቢ ካሉ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት በሚያደርግበት ጊዜ ሁሉ ብዙዎቹ የሚያሳዩት የመንደረኛነት ስሜት እያበሳጨው የተማሩት ሰዎች በእንደዚህ ያለ ማኅበረሰባዊ ኋላቀርነት ውስጥ ሆነው ኢትዮጵያ የምትባለው አገር እንዴት መራመድ ትችላለች? እያለ ይሰጋ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አሌክስ አብረሃም

እናት አገርን የሚያሳምረው ህንፃ ይመስለኝ ነበርአገርን የሚያሳምረው መንገድ ይመስለኝ ነበር አገርን የሚያሳምረው ዛፍና ቅጠል ይመስለኝ ነበር ….አገርን የሚያሳምረው ለካ ለአንድ አላማ የተሰለፈ በአንድነትና በአብሮነት ስሜት ፈገግታና እልሁ ፊቱ ላይ የሚንቀለቀል ህዝብ ነው !! አገሬ ቆንጆ ናት ድህነት ብስቁልና መገፋት የጋረደው ፈገግታችን እንዲህ እንደ ዛሬ ከችግራችን በላይ ፈክቶ ሲታይ አልኩ …… ኢትዮጲያ እች ናት፤ አገሬ እችናት !!

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተመስገንደሳለኝ

‹‹ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም
እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም›› ማን ነበር ያቀነቀነው? …ብቻ ማንም ይሁን ማን፤ እኔም እደግመዋለሁ፡- ሀገሬን የደፈረ ይውደም!! …እነሆ ከፉከራው ወደ አጀንዳችን እንለፍ፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን፣ በሚቀጥለው ዓመት በብራዚል በሚካሄደው የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ለመሳተፍ፣ ከናይጄሪያ ጋር የደርሶ መልስ ግጥሚያ ብቻ ቀርቶታል፡፡ በነገው ዕለትም የመጀመሪያውን ጨዋታ በአዲስ አበባ ያደርጋል፡፡ በዚህ ፅሁፍ የማነሳው ሃሳብም፣ ስለጨዋታው ሳይሆን፣ ጨዋታውን
የሚያደምቀው ሰንደቅ-ዓላማን (ባንዲራን) በተመለከተ ይሆናል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

በግል ስልኩ የተቀረጸ የቪድዮ ምስል ይመልከቱ!

Ethiopia Zare (አርብ ጥቅምት 1  ቀን 2006 ዓ.ም. October 11, 2013)የሙስሊም ራዲዮ ጋዜጠኛ እና በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጥያቄዎች ላይ ትንተናዎችን በመስጠት የሚታወቀው ሳዲቅ አህመድ በአሜሪካን ሀገር ይፋዊ ያልሆነ ጎዞ ላይ ከሚገኙት የህወሃት ባለስልጣናት መሀከል አቶ ስብኃት ነጋን በአካል አግኝቶ በግል ስልኩ እየቀረጸ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ጥያቴ አቀረበ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ደራሲ፤ ዓለማየሁ ገላጋይ
ቅኝት፤ መስፍን ማሞ ተሰማ

መንደርደሪያ
ሰቀቀን ጭንቀታቸውን እንደ ተጋቦ የሚያጋቡ፤ ግፍና በደሉን ጠኔና ጣዕሩን እንደ ሾተል አሹለው፤ ከልብ የሚቸክሉ ከአእምሮ ጓዳ የሚቀብሩ፤ አዝነው የሚያሳዝኑ፤ ተቃጥለው የሚያሳርሩ…ፍትህ ተሟጋች፤ ነፃነት ተፋራጅ፤ ጧፍ ነዳጅ…ደራሲያን፤ ቀመረ ቃላት ጠቢባን…ቢኖሩም…የብዕር ትሩፋታቸው ጨለማን ተጋፍቶ ጨለማን ተዋግቶ የወጣው – ‘ኢምንቱ’ ነው። እነርሱም ቢሆኑ ታዲያ፤ በጨለማ እንደሚተኮስ ርችት ወጋጋናቸው አድማስ ካድመስ የሚያሳይ ብርሃን ሆኗልና፤ እሰየው!!

ሙሉውን አስነብበኝ …

በተመስገን ደሳለኝ

የኢህአዴግ ታጋዮች የመንግስት ‹‹ጠንካራ ይዞታ›› የሚባሉ ከተሞችን ሳይቀር መቆጣጠር ችለዋል፤ ወደ አዲስ አበባ የሚያደርጉት ግስጋሴም ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃ/ማርያምን እንቅልፍ ነስቷል፡፡ በአንዳች ተአምር ግስጋሴውን መግታት ካልቻሉ፣ በጥቂት ወራት ውስጥ ሁሉም ነገር ታሪክ እንደሚሆን በማወቃቸው፣ መላ በማፈላለጉ ላይ ተጠምደዋል፡፡ በዚህ ጊዜም ነበር (የሃሳቡ አመንጪ ተለይቶ ባይታወቅም) ‹‹ለዩንቨርስቲ ተማሪዎች የአጭር ጊዜ ስልጠና ሰጥቶ፣ ከገሪቱ ሠራዊት ጎን ማሰለፍና የ‹ወንበዴ›ውን ጦር መድረሻ ማሳጣት›› የሚለው ሃሳብ እንደ መፍትሄ የተወሰደው፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

ክንፉአሰፋ

ትላንት ምሽት። እለተ እሁድ፤ ኦክቶበር 6 2013ታማኝ በየነ እና ቴዲ አፍሮ በስልክ ያወራሉ። ንግግራቸው ከወትሮው የተለየ አልነበረም። እንደ ቀድሞው እየተቀላለዱ ይሳሳቃሉ። ታማኝ ከዴንቨርኮሎራዶ፣ ቴዲ ደግሞ ከሲድኒ– አውስትራሊያ በስራ ላይ ነበሩ። በዚህ የሶስትዮሽ የስልክ ጨዋታ ላይ እኔና ጴጥሮስ አሸናፊም ገብተናል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተክለሚካኤል አበበ (ቶሮንቶ ካናዳ)

የኛ ነገር፡ ክፍል 16፤ ከኔ ማእዘን፤

 

እንደ መግቢያ

 

1.       ይህ ጽሁፍ ሲታሽ፤ ሲሰቃይ እዚህ የደረሰ የቁጭት ጽሁፍ ነው፡፡ ወዲህም ግንቦትሰባትየምወደውበሱ ግን ደስ ያላለኝ ፓርቲስለሆነና፤ ዲባቶ ብርሀኑ ጋ ለኢሳት ዝግጅት ወደቶሮንቶ ስለሚዘልቅ፤ ያንዳንዶቻችንን ቁጭትና ጭንቀት ለመገለጽ የተሰናዳ ጽኁፍ ነውቀደም ያሉት የራስን የሆነን አካል የተቸሁባቸው ጽሁፎቼ ባንዳንድ ወዳጆቼ ዘንድ ቅሬታ ፈጥረዋል፡፡ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ወዳጅን የሚያስቀይመውን ንጥረ ነገር ለመሽረፍ ጥረት አድርጌያለሁ፡፡ ቀድሞውንስ በግል መንገሩ አይሻልም ወይ ለምን መጸፍ አስፈለገ ለሚሉት መልሱን ወደመጨረሻ እሰጣለሁ፡፡ ደግሞስ ፖለቲከኞች ወደ አደባባይ ሲወጡ ለመተቸት ተዘጋጅተው አይደለምን? ስለዚህ የሌሎችን ሀሳብ እተቻለሁ፤ የእኔም እንዲተች እነሆኝ፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

ዩሱፍ ያሲን

በየታሪክ መጋጠሚያው የሚወጥር ጥያቄ

በተለያዩ የሀገራችን ወሳኝ የታሪክ ምዕራፎች ኢትዮጵያ ለመፃኢ እድሏ ዕጣ ፈንታ ወሳኝ በሆነ መስቀለኛ የታሪክ መጋጣሚያ ላይ ትገኛለች ሲባል ደጋግመን ሰምተናል። በርካታ ጊዜያት መንታ መንገድ ላይ ናት ተብሎ ሲነገር እንሰማለን።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሄኖክ የሽጥላ (ገጣሚ)

ከምን ልጀምር? እንደው ይጨንቃል፤ ደሞ ዝም ቢሉት ያንቃል። አሁን ይሄን የምጥፈው ለማስተማር ነው ለማካረር? በልጅነቴ አንድ አብሮ አደጌ በጣም የሚወዳቸው እናቱና አባቱ እየተጋጩ ቢያስቸግሩት፣ ሄኒ አሁን አንተ በኔ ቦታ ብትሆን ማንን ትጠላለህ? ብሎ የጠየቀኝ ትዝ አለኝ። ማንን ልጥላ? ለማን አግዤስ ማንን ላውግዝ? ማንንስ ልውቀስ? ማንንስ ልጥቀስ? ሲደብር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የተከበሩ ግርማ ሠይፉ ማሩ, Girma Seifuይህንን የማፊያ ቡድን በማፍረስ ታሪክ ይስሩ!

ግርማ ሠይፉ ማሩ

በ2005 ዓ.ም. የምክር ቤት ዘመን መጨረሻ ላይ የደህንነት መስሪያ ቤቱን በሚኒስትር ደረጃ ለማዋቀር የሚረዳ አንድ አዋጅ ለምክር ቤት ቀርቦ ፀድቆዋል። ይህ አዋጅ ሲፀድቅ ከነቅሬታዬ ያለኝን ድጋፍ መስጠቴ ይታወቃል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

(ከወልደሚካኤል መሸሻ)

ውድ አንባቢያን ይህን ጽሑፍ ጀምሬ ያጠናቀቅሁት ወደ እ . ኤ. አ በ2012 መጀመሪያ ነው። ለምን እስከአሁን አቆየኸው? የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀሬ ነው ታዲያ። ተገቢ ጥያቄ ነው። የተለያዩ አቅጣጫዎችን የማየትና የማሰላሰል ሁኔታ በአንድ በኩል፣ በሌላ ደግሞ በአነሰኛ መጽሐፍ መልክ ባሳትመውስ የሚል አሳብ እየተደቀነብኝ መጥቶ ነው። ሁለቱም ተራ በተራ ተፈታተኑኝ። የትኛውን እንደምመርጥ ማውጣት ማውረዱን ቀጠልሁ። ጽሑፍን እንድያዩትና አሳባቸውን እንዲሰጡኝ ለጥቂት ወዳጆቼ ላክሁ። አንዳንዶቹ ቶሎ ጽሑፉ እንዲወጣ የሚገፋፋ አሳብ ሰጡኝ። አንዳንዶች ከማስጠበቅ ውጭ ላያልፉ ሆኑ። በዚህ ላይ እያለሁ ለጽሑፉ መሠረት የሆነው የእምዬ ጠላት በመርዘኛ ብዕሩ ብቅ ማለቱን ሰማሁ። ወዳጆቹ ከወዲህ ወዲያ እያሉ መሆኑንም አዳመጥሁ። እርሱም የእምዬ ልጆችን የማባላቱን ሥራ ማጠናቀቁን ከወብሳይቱ ተመለከትሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተመስገን ደሳለኝ

ኢህአዴግ ከቀድሞ ሊቀመንበሩ አቶ መለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ በተከሰተበት ውስጣዊ ልዩነት በተለዋዋጭ የኃይል ሚዛን ሥር ለማደር በመገደዱ የስልጣኑን መዘውር የሚያሽከረክረውን አካል ለመለየት አዳጋች ነበር። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ይህ ሽኩቻ መፍትሄ ማግኘቱን የሚያመላክቱ ሁናቴዎች መፈጠራቸውን የውስጥ አወቅ መረጃዎች ጠቁመዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ላይፍ መጽሔት Life magazine“ለአማርኛ ስነፅሁፍ ቅርብ ነኝ ለማለት አልችልም። የሚታተሙ መጻሕፍትን እንደልቤ ለማግኘት ስለምቸገር ስለታተሙ መጻሕፍት በልበ ሙሉነት አስተያየት ለመስጠት እቸገራለሁ። በጥቅሉ ግን የአማርኛ ስነፅሁፍ አደጋ ላይ የወደቀ ሆኖ ይሰማኛል። አማርኛ በአዲሳባና በአማራ ክልል ቋንቋነት ብቻ ተወስኖ እንዲቀር ብዙ ተሰርቶበታል። ይህ ሁኔታ የአማርኛ ስነፅሁፍን ክፉኛ ጎድቶታል። አማርኛ ቋንቋ ጠላት ስለበዛበት ስነፅሁፉም ባለቤት አጥቶአል። ይህ አሳዛኝ እውነት ነው።” ተስፋዬ ገብረአብ ከላይፍ መጽሔት ጋር ባደረገው ቃለምልልስ

 

ሙሉውን አስነብበኝ …

የህወሓትን ፀረ-ኢትዮጵያ አካሄድና ዓላማ በመቃወም የሕይወት ማስዋዕትነት የከፈሉ አመራር ነበሩ ወይ? ከነበሩስ እነማን ናቸው?

ገብረመድህን አርኣያ ከአስውትራሊያ

ገሰሰው አየለ፣ አግአዚ ገሰሰ፣ ሙሴ መሃሪ ተክሌ፣ አጽብሃ ዳኛው እና ዶ/ር አታክልት ቀጸላ Gessesew Ayele, Agazi Gessese, Musse Mahri Tekle, Atsbeha Dagnachew and Dr. Atakilt Ketswela

ከዚህ ቀጥለን የምንመለከተው ትኩረት ያልተሰጠውን ተሸፍኖ የነበረውን እና የህወሓት መሪዎች፣ በሕይወት ያሉትም የሞቱትም፣ ከወያኔ የተባረሩ አመራርም ጉዳዩ ወደ ውጭ እንዳይወጣ ተዳፍኖ እንዲቀር ከባድ ጥረት እያደረጉበት ያለውን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …