ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም

ሰው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ነው፤ ሕይወቱ ክቡር ነው፤ ክቡር ሕይወቱን ለመጠበቅ ብዙ ፍላጎቶቹን ማሟላት አለበት፤ አንዳንዶቹ ፍላጎቶች በየዕለቱ የሚከሰቱና የሚጎተጉቱ ናቸው፤ ስለዚህም ወዲያው ካልተስተናገዱ በጤንነት ላይ መጥፎ ውጤትን ያስከትላሉ፤ምግብና መጠጥ ግዴታዎች ናቸው፤ ልብስና መጠለያም ግዴታዎች ናቸው፤ ሰው ሁሉም ነገር ከተሟላበት ከገነት ከተባረረ በኋላ በግንባርህ ላብ ብላ ተብሎ ተረግሟል፤ በሰላም በሕግ ጥላ ስር የመተዳደር ፍላጎትም አለ፤ በአለው አቅምና ችሎታ አነዚህን ፍላጎቶች ለማሟላት ይጥራል፤ ይህ ቀላል አይደለም፤ ቀላል የማያደርጉት ብዙ ምክንያቶች አሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጽዮን ግርማ
ከአምስት ወራት በፊት ከኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት የስልክ ጥሪ ደረሰኝ፡፡ በሞያው ውስጥ ሰንበት ብያለኹና ከአብዛኞቹ የጣቢያው ዘጋቢዎች ጋራ እንተዋወቃለን፡፡ ጥሪው የደረሰኝም በላይ ኃድጎ ከተባለ ከማውቀው ጋዜጠኛ ነበር፡፡ ለሥራ ጉዳይ በስልክ ሳይኾን በአካል መገናኘት እንደሚፈልግ ነገረኝ፡፡ ባለመመቻቸት ሳንገናኝ ቀናት ቢቆጠሩም በመጨረሻ ተገናኘን፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም
በሃያኛው ምዕተ-ዓመት ላይ የታወቀ የፈረንሳይ ፈላስፋ ነበረ፤ እሱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ በነበረበት ጊዜ ከእሱ ጋር በዩኒቨርሲቲ ሁለት አፍሪካውያን አብረውት ይማሩ እንደነበሩ ይናገራል፤ እነዚህ አፍሪካውያን የፈረንሳይኛ ቋንቋን ልክ አንደፈረንሳዮች እየተናገሩ፣ እንደፈረንሳዮች እያሰቡ ከፈረንሳዮቹ ተማሪዎች ጋር እኩል በትምህርት እየጎለበቱ ነበር፤ በኋላ እነዚህ አፍሪካውያን ወደአገራቸው ተመልሰው ሥልጣን ላይ ሲወጡ ሰፊ አገራቸው ለሁለቱ የተማሩ አፍሪካውያን የማይበቃ ሆነባቸው፤ ስለዚህም አንደኛው የአገር መሪ ሆነና ሌላውን ገደለው፤ የፈረንሳዩ ፈላስፋን ያሳዘነው ትዝብት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የዐቃቤ ሕግ የመሰረተውን ሙሉ ክስ ይዘናል
የዋስትና መብት ተከልክለው ወደቃሊቲና ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተወሰዱ፣ ለሐምሌ 28 ተቀጠሩ
የታሰሩት ስድስት ጦማርያንና ሦስት ጋዜጠኞች The jailed 6 bloggers and 3 journalists

Ethiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም. July 17, 2014)፡- ዛሬ ጠዋት በ84 ቀናቸው በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተሰየመ ችሎት ስድስቱ ጦማርያን በፍቃዱ ኃይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ አጥናፉ ብርሃኔ፣ ዘለዓለም ክብረት፣ አቤል ዋበላ እና ሦስቱ ጋዜጠኞች አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ኤዶም ካሣዬና ተስፋለም ወልደየስ ዐቃቤ ሕግ የመሰረተባቸው የክስ ፋይል ለመጀመሪያ ጊዜ ደርሷቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Journalist Tsion Girma, ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ
ጽዮን ግርማ
[email protected]

ከዓመታት በፊት የቅንጅት አመራሮች፣ ጋዜጠኞች፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት አባሎችና ሌሎች ሰዎች ተከሰው ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ”የቅንጅት አመራሮች የፍርድ ቤት ውሎ” በሚል ርእስ ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ተከታታይ ዘገባ አቀርብ ስለነበር ችሎቱ እስኪጠናቀቅ አንድም ቀን ከፍርድ ቤት ቀርቼ አላውቅም ነበር። በዚህም የተነሳ ክሱና የክርክር ሂደቱ ምን እንደሚመስል መናገር የሚያስችል መረጃ አለኝ ለማለት እደፍራለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

እስረኞቹ በሽብር መከሰሳቸውን አያውቁም
ጽዮን ግርማ
Jailed journalists and bloggers Tesfalem Weldeyes, Edom Kassaye, Assmamaw Hailegiyorgis, Atnafu Berhane, Mahlet Fantahun, Zelalem Kibret, Natnael Feleke, Befikadu Hailu, Abel Wabela

አንድ ዓመት ከአንድ ወር ኾኖታል። እስክንድር ነጋ ከታሰረ ከዐስራ ስምንት ወራት በኋላ ከባለቤቱ ከጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል እና ከልጁ ከናፍቆት በተጨማሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ሌላ ሰው እንዲጠይቀው በሰኔ የመጀመሪያ ወር ላይ በ2005 ዓ.ም. እንደተፈቀደለት ነው። በወቅቱም እስክንድርን ልጠይቀው ቃሊቲ ወደሚገኘው እስር ቤት አምርቼ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ደራሲ መስፍን ሀብተማርያም Mesfin HabtemariamEthiopia Zare (ማክሰኞ ሐምሌ 8 ቀን 2006 ዓ.ም. July 15, 2014)፦ ከአቶ ሀብተማርያም ሞገስ እና ከወ/ሮ ደስታ አየለ በ1935 ዓ.ም. የተወለዱት ደራሲ መስፍን ሀብተማርያም እሁድ ሐምሌ 6 ቀን 2006 ዓ.ም. በ71 ዓመታቸው በአዲስ አበባ ከተማ አረፉ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም

ዮሐንስ ታደሰ አካ የሚባል ወጣት ስደተኛ የተስፋው ነጸብራቅ የሚል መጽሐፍ እአአ በ2013 በጀርመን አገር አሳትሞአል፤ ሳይፈራ ሀሳቡን የሚገልጽ በመሆኑ ሳይሆን አይቀርም በታወቀው ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያና በቃሊቲም ታስሮ ነበር፤ እሱ እንደሚለው ‹‹በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የመሬት አስተዳደር ባለሥልጣን ውስጥ … የመሬት መሀንዲስ›› ተብሎ በ2000 ዓ.ም. ተቀጠረ፤ ከተቀጠረ በኋላ በቦዘኔነት ደመወዝ እየበላ ቆየ፤ ቀይቶ እንደተገነዘበው ‹‹… ለካስ እንኳንስ የእያንዳንዱ ሠራተኛ የሥራ ድርሻ ተለይቶ ሊታወቅ የመሥሪያ ቤቱም ሥራ አይታወቅም፤ መሥሪያ ቤቱም ሥራውን አያውቅም፤ የመሥሪያ ቤቱም ሃላፊዎች መሥሪያ ቤቱን አያውቁትም፤ ጉድ በል አዲስ አበባ! የምናወራው ስለዝነኛው አዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ነው።›› (ገ. 19)

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጽዮን ግርማ

ኢትዮጵያ በፓርቲ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ ባህል ውስጥ የገባችው የ1960ዎቹን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የተለያዩ ርዮተ ዓለሞች ተፋጭተው ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት ይመሰረትባታል በሚል ተስፋ ቢጣልም የድርጅቶቹ የኋላ ታሪክ እንደሚያስረዳው ለሀገርና ለሕዝብ የሚጠቅም ለውጥ ከማምጣት ይልቅ እርስ በእርስ የመጨራረስ ባህል እንደነበራቸው ነው፡፡ ከበርካታ ንፁሃን ዜጎች ደም መፍሰስና እልቂት በኋላ ህወሓት ኢሕአዴግን መሥርቶ ወደ ሥልጣን ሲመጣም ከሻዕቢያ በስተቀር ሌሎቹ ድርጅቶች እስከ አመራሮቻቸው ደብዛቸው ጠፍቶ ነበር።ኢህአዲግ የሥልጣን ወንበሩን ከጨበጠ በኋላ በሽግግር መንግሥት ምስረታ ፓርቲዎች እንዲሳተፉ ይፋዊ ጥሪ በማስተላለፍ በፓርላማ መቀመጫ እንዲያገኙ በማድረግ ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት የተመሰረተ ለማስመሰል ጥረት ቢያደርግም በተለያየ ምክንያት አባሮ መልሶ ለመበታተን ጊዜ አልወሰደበትም ነበር ፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

“የተፈጠረው ሁናቴ እጅግ ቢያሳዝንም ይህንን አለማቀፍ ህግ የሚጥስ አገዛዝ ለመጣል ሁላችንም ቆርጠን እንድንነሳ ያደርጋል” አቶ ነአምን ዘለቀ

 

Ethiopia Zare (ሐሙስ ሰኔ 26 ቀን 2006 ዓ.ም. July 3, 2014)፦ ከዱባይ ወደ አስመራ በመጓዝ ላይ የነበሩትና የመን ውስጥ ሰንዓ ከተማ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለትራንዚት የወረዱት የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እዛው የመን ታግተው ከቆዩ በኋላ ለኢትዮጵያ መንግሥት ተላልፈው መሰጠታቸው ተረጋገጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ወደ ኢትዮጵያ እንዳይተላለፉ ስጋቱ አይሏል

ኤርትራዊያኖች የየመን አየር መንገድን እንዳይጠቀሙ ማስተባበር ያስፈልጋል አቶ ዳንኤል ጥላሁን (የህግ ባለሙያ)

Ethiopia Zare (ሐሙስ ሰኔ 26 ቀን 2006 ዓ.ም. July 3, 2014)፦ የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለጉዞ መሸጋገሪያ የመን ከገቡ ጀምሮ በአገሪቱ ደህንነቶች ታፍነው መወሰዳቸውን አስመልክቶ ኢትዮጵያዊያን ቁጣቸውን እያሰሙ ሲሆን በተለይ የየመን አየር መንገድን በመቃወም ኤርትራዊያን የጉዞ ማእቀብ እንዲያደርጉ አንድ ተቀማጭነቱን ካናዳ ያደረገ የህግ ባለሙያ ጥሪ አቀረበ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕሮ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
ተናግሬ ነበር ማለት ዋጋ የሌለው የወሬ ማጌጫ ነው፤ እስቲ ፍቀዱልኝና ልጠቀምበት፤ ከወያኔ ዋና ምሁር፣ ከመለስ ጋር ለመጀመሪያና ለመጨረሻ ጊዜ ፊት-ለፊት በቴሌቪዥን በተገኛኘን ጊዜ ‹‹አማራ የሚባል ጎሣ የለም፡›› በማለቴ መለስ ዜናዊና ጭፍሮቹ ብቻ ሳይሆኑ ‹‹አማራ-ነን ባዮች›› በቃልም፣ በጽሑፍም፣ በቴሌፎንም ልክ-ልኬን እየነገሩኝ አንጀታቸውን ቅቤ አጠጥተው ነበር፤ ‹አንዲት ሴት ደውለው እብድና ዘበናይ የልቡን ይናገራል፤› ብለውኛል፤ አንድ ሰው የተናገረው ስሕተት ከሆነ ስሕተቱን በማስረጃ ማጋለጥና የራስን ሀሳብ በማስረጃ መትከል ነው፤ እውቀት የሚዳብረው፣ ሰዎች የሚማሩትና በእድገት ጎዳና የሚጓዙት በተጨባጭ ማስረጃ መነጋገር ሲችሉ ብቻ ነው፤ እኔ አማራ የለም፣ ዜሮ (0) ነው፤ አልሁ፤ አማራ አለ፣ አንድ አለ፤ (1) ነው ያለ ሰው የአንድን ዋጋ ማሳየት አለበት፤ አማራ የለም የሚል ዜሮ ነው ማለቱ ስለሆነ ከሌለ ነገር ምንም አይጠብቅም፤ ከአለ ነገር (ከ1) ብዙ ነገሮችን መጠበቅ ይቻላል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

“የጳጳሳት ስራ ሕዝብን ማጽናናት እንጂ ህዝብን ማሳዘን አይደለም” 

                አቡነ መቃርዮስ (ሊቀጳጳስ)

                       

“እረኛው በጎቹን መፈለግ ትቶ በጎቹ እረኛውን የሚፈልጉበት ግዜ መጣ”

ቶ አስራት ተሸመ (የሰበካ ጉባኤው ሊቀመንበር)

ለላፉት ሶስት አመታት በተለያዩ አለመግብባቶች ሲጓተት የነበረው የቫንኩቨር ጼዴንአ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ቤት በአቡነ መቃርዮስ፤ ሊቀጳጳስ ባራኪነት ተከበረ፤ የቫንኩቨር ምእመናን የደስታ እንባ አነቡ። ባለፈው ቅዳሜ እና እሁድ በተከበረው በዓል ላይ፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቫንኩቨርና አካባቢው ምእመናን፤ ከአመታት ልፋትና ጸሎት በኋላ ሀሳባቸው ሰምሮ የመድሄኔዓለምና የቅድስት ማርያም ጽላት ስለገቡላቸው ደስታቸውን በዝማሬና በእንባ ገልጸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፐሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም

ቴዎድሮስ ካሣሁንን በአካል አላውቀውም፤  በዘፈንና በጭፈራ በእውነት ተደሳች መሆን ካቃተኝ ቆይቷል፤ ከ ኅዳር 1967 ጀምሮ ነው የቆረቆረኝ፤ ይህ ሰው እንደሰውና እንደ ኢትዮጲያዊ በየጊዜው የሚደርስበትን ወደ ግፍ የሚጠጋ በደል ስመለከት ያው የለመድነው ምቀኝነት ነው እያልሁ ሳልፈው ቆየሁ፤ ግን በደሉ አላቆም አለ፤ ማንም ሊደርስለት አለመቻሉ ይበልጥ ያሳዝናል፣ በእሱ ላይ ተከታታይ  የደረሰበት በደል የሕግ ያለህ የሚያሰኝ ነው፤ በቴዎድሮስ ካሣሁን ላይ በተቀነባበረ መንገድ የሚፈፀመው ማሰቃየት ማንንም ሰው የሚያሳስብ ነው፤ ምክንያቱ ምንድን ነው? በግልጽ የታወቀ ነገር የለም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

መዝገቦቹ መልሰው ተቀራረቡ !

ጽዮን ግርማ
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በስድስቱ ጦማሪያንና በሦስቱን ጋዜጠኞች ላይ የፌደራል ፖሊስ የተለያየ ምክንያት እየሰጠ ቀጠሮ የሚያራዝመውን ሁለት መዝገብ አንዴ ሲያቀራርበው መልሶ ደግሞ ሲያራርቀው ቆይቶ አሁን ደግሞ መዝገቦቹን መልሶ አቀራርቧቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Ethiopia Zare (አርብ ህዳር 22 ቀን 2004 ዓ.ም. October 2, 2011)፦ በቫንኩቨር ካናዳ የምትገኘውን የጼዴነያ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት የሚከብርበትንና ታቦተ ህጉን ከመንበሩ ለማስገባት ወደ አካባቢው ሀዋርያዊ ጉዞ የሚያደርጉት ብጹእ አቡነ መቃርዮስ ነገ በስፍራው የወንጌል ትምህርት እንደሚሰጡ ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም

ትርጉም – ነጻነት ገብሬ

በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ወንጀል

ፍፃሜ መሪ ተዋንያን ሆነው ከቆዩ በኋላ በመሰደድ በአሜሪካ እራሳቸውን 

ደብቀው በተቀመጡ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ላይ የዩናይትድ

ስቴትስ አሜሪካ የፍትህ መምሪያ ጥቆማእንዲቀርብለት 

ኢትዮጵያውያንን/ትን በማበረታታት ላይ ይገኛል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ (ከቃሊቲ እስር ቤት)

በጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ

ቅዳሜ ሰኔ 14 ቀን 2006 ዓ.ም ከታች በፎቶግራፍ የምንታይ [ፎቶግራፉን ያነሳው አብነት ረጋሳን ጨምሮ] fጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በዓለም የጋዜጠኞች እና የዜና አታሚዎች ማኅበር የዓመቱ የወርቅ ብዕር የ “pen Golden of freedom 2014″ ተሻላሚ በመሆኑ ‹‹እንኳን ደስ ያለህ›› ለማለት ኬክ አስጋግረን ወደቃሊቲ አምርተን ነበር፡፡
ቁጥራችን መብዛቱ በቃሊቲ ያሉ ፖሊሶችን ግር ማሰኘቱ አልቀረም ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አንዷን ቅዳሜ በፍርድ ቤት
በዛሬው ችሎት ፖሊስ የሃያ ስምንት ቀን የምርምራ ጊዜ ቀጠሮ ተፈቀደለት

ጽዮን ግርማ

ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ፣ ዘለዓለም ክብረት፣ ጋዜጠኛ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ፣ ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ፣ ናትናኤል ፈለቀ እና አጥናፉ ብርሃነ Journalist Tesfalem Weldeyes, Zelalem Kibret, journalist Asmamaw H/ghiorgis, journalist Edom Kassaye, Natnael Feleke and Atnaf Berhane

ለአብዛኛው ወጣት አዲስ አበባ ላይ ”ቅዳሜ” ትርጉም አላት። የሣምንቱን የሥራ ቀናት በየፈርጁ ያሳለፈው ኹሉም ወጣት ”ቅዳሜ”ን ደግሞ እንደየምድቡ ይውልባታል። እንደሰማኹት ከኾነ ለዞን ዘጠኝ አባላትና ጓደኞቻቸውም ቅዳሜ ልዩ ቀን ናት። ለወጣቶቹ አብሮነት የጡመራ መድረኩ ቢያግዛቸውም ከዛ በላይ ግን ጓደኝነታቸው ቤተሰባዊነትን ፈጥሮላቸው አብዛኛውን ቅዳሜ እንደየቅርበታቸው አብረው ያሳልፋሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

(ሊያነቡት የሚገባ)

ከጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ (አዲስ አበባ)

ከትናንት በስትያ ሰኔ 03 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ከቅርብ ጓደኛዬ እና የሙያ ባልደረባዬ ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ ጋር ወደቃሊቲ ማረሚያ ቤት [እስር ቤትም ነው] አምርተን ነበር- ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና የአንድነት ፓርቲ ጸሐፊ የሆኑትን አቶ አንዷለም አራጌን ለመጠየቅ። የተለመደውን የፖሊስ ፍተሻ አልፈን ወደ ውስጥ ስንዘልቅ የሰማያዊ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፈ አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ፣ አቶ ሳሙኤል የተባሉ አባልና የ‹‹ነገረ ኢትዮጵያ›› ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው እስክንድርን ሊጠይቁ ቀድመውን ደርሰው ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጸጋዬገ ብረመድኅን አርአያ

እንደ ልጄ የምቆጥረውና ከበኩር ልጄ ከዩሐንስ ጋር ያደገው ሳምሶን በሕክምና ኮሌጅ ይማር በነበረበት ዘመን በምሽቱ ሰዓት ላይ የ‹‹ፈገግታ ጊዜ›› በምንለው ግማሽ ሰዓት ያጫውተን ነበር፡፡ አዎን ሕይወት ውጥርጥር ባለበትና ጭንቀት ከቀበሌ ከሚወረወር ቀስት፣ ጭንቀት ከየካድሬውና ከየፖለቲካው ኅቡዕ ድርጅት ከሚወረወር ሌላ ቀስት፣ ጭንቀት፣ ከመስሪያ ቤት ጭንቀት፣ ከበላይ አካል ጭንቀት፣ ከበታች አካል ጭንቀት፣ ጭንቀት —- አንድ የድሮ ማስታወቂያ ሚኒስትር እንዳሉት ከላይ ከመሳፍንቱና ከመኳንንቱ በሚለቀቅብህ እሳት፣ ከታች ከሕዝቡና ከሠራተኛው ከሚነድድብህ እሳት የገና ዳቦ ትሆናለህ፡፡ ስለዚህ ‹‹በታይም አውት›› (ፋታ ልበለው) መልክ ከሳሚዬ ጋር የማደርገው የግማሽ ሰዓት ውይይት (ጨዋታ) ለእኔ “ማሳጅ” ነበር፡፡ መታሻ!

ሙሉውን አስነብበኝ …

በታደሰ ብሩ

መንደርደሪያ

ፌስ ቡክ ላይ ህወሓትን (ወያኔን) የሚተች ጽሁፍ ሲወጣ ስድቦችን “በብርሃን ፍጥነት” የሚያዥጎደጉዱ ሃያ ያህል ሠራተኞች ሬድዋን ሁሴን ቢሮ ውስጥ መኖራቸውን ሰምቼ ነበር። ይህ ራሱ እየደነቀኝ እያለ ሰሞኑን ሌሎች ዜናዎች ተከታትለው መጡ። በፌስ ቡክና መሰል ማኅበራዊ ሚዲያዎች ለሚቀርቡበት ትችቶች ፈጣን የስድብ ምላሽ የሚሰጡለት 235 “ባለሙያ ተሳዳቢዎችን” ኢህአዴግ አሠልጥኖ ማስመረቁ ከግንቦት 27 ቀን 2006 ዓም የኢሳት ዜና ሰማሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ኤልያስ ገብሩ ጎዳና (አዲስ አበባ)

 ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብታችን ትልቅ አደጋ ላይ ነው

አርብ ግንቦት 15 ቀን 2006 ዓ.ም ከወዳጄ ጋዜጠኛ ዳዊት ሠለሞን ጋር ቀጠሮ ነበረኝ። ረፋድ 5፡25 ሰዓት ላይ የሞባይል ስልኬ ጠራች። ከአምባሳደር ወደአራት ኪሎ በሚጓዝ ታክሲ ውስጥ ተሳፍሬ ነበር። የመስመር (የቢሮ) ስልክ መሆኑን አየሁትና “ሃሎ” አልኩኝ። ‹‹አቶ ኤልያስ፣ የዕንቁ መጽሔት ዋና አዘጋጅ?›› የሚል የሴት ድምጽ ተሰማኝ፡፡ ‹‹አዎን›› ስል መለስኩላት። ብዙ ጊዜ አንባቢዎች ስለሚደውሉ፣ ምን ዓይነት ግብረ-መልስ (feed back) ይኖራት ይሆን ነበር ሀሳቤ፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)

የዛሬይቱ ኢትዮጵያችን ‹‹አብዮታዊ ሁኔታ›› ላይ ለመድረሷ በብዙሃን ዜጐች ዕይታም ሆነ፤ ሂደቱን በተከታተሉ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ምሁራን ምልከታ የማይታበል ሐቅ ሊሆን መቃረቡ በዚህ ተጠየቅ ለማነሳው አጀንዳ ገፊ-ምክንያት ነው፡፡ በአናቱም ባለፈው ሳምንት ‹‹የ‹ቀለም› አብዮት ናፍቆት›› በሚለው መጣጥፍ ላይ ለማሳያነት የጠቀስኳቸው ፖለቲካዊ፣ ማሕበራዊ እና ነገረ-ንዋያዊ ችግሮች ተደማምረው፣ ሀገሪቷን በርቀት እንደታዘብናት ሶቪየት ሕብረት፣ አሊያም በቅርበት እንዳስተዋልናት ሶማሊያ በመጪዎቹ ጥቂት ጊዜያት የመፈራረሷን አይቀሬነት ማስረገጣቸውን ልብ እንላለን፡፡ ከዚህ ክፉ የታሪክ ዕጣ ለመታደግም ከሁለት አስርታት በላይ ያስቆጠረውን ይሄን አሮጌ ሥርዓት መቀየር ብቻውን ዘላቂ መፍትሔ ሊያመጣ እንደማይችል ዛሬ ግልፅ እውነታ ሆኗል፤ ምክንያቱ ደግሞ ለዘመናት በገዥነት የተንሰራፋው የፖለቲካ ባሕልም አብሮ ካልታደሰ ነገሩ-ሁሉ ‹‹ታጥቦ ጭቃ…›› ከመሆን አለመዝለሉ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጽዮን ግርማ
ሦስተኛዋን ”እሁድ” - በአራዳ ምድብ ችሎት

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ተጠርጣሪዎቹን እሁድ ለሚሰየም ተረኛ ችሎት መቅጠሩን የተለመደ አድርጎታል። ከቀናት በፊት በሦስቱ ብሎገሮች ላይ በተሰጠው የዐሥራ አራት ቀናት የጊዜ ቀጠሮ መሠረት የቀጠሮው ቀን ዛሬ ነበር። ዛሬ በዚህ ፍርድ ቤት ተገኝቼ የነበረውን ሁኔታ መከታተል ባልችልም ምንጮቼ የነገሩኝን ዝርዝር እንዲህ ጽፌዋለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በልጅግዓሊፍራንክፈርት

ብዙ የውጭ ሃገር ሰዎች ሃገራችንን ይወዳሉ። ከነዚህ ውስጥ አንዱ የኦስትርያ ተወላጅ የሆነው ካርልሃይንዝ ቦይም(Karlheinz Böhm ) ነበር። ነገር ግን ካርልሃይንዝ የዓለም ዜጋ(Weltbürger) ነኝ ብሎ ነበር የሚያምነው። ቢሆንም ካርልሃይንዝ 2003 የኢትዮጵያ የክብር ዜግነት ተቀብሏል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ከኢያሱ ዓለማየሁ

ነገርን ነገር ያመጣዋል እንዲሉ በቅርቡ አንዲት የተበሳጨች ኢትዮጵያዊ- የኢሕአፓ ታሪክ እያሉ መጽሃፍ ጻፍን በሚሉ ዋሾዎች በመናደድ–በስም ጠቅሳኝ የድርጅቱን ታሪክ ባለመጻፌ ወቅሳኝና ውቀሱት ስትል መልዕክትና ምሬት ፈረንጆቹ ፌስ ቡክ በሚሉት አማካይነት አሰምታለች። ወጣት ናት በሚል ግምት አንቺ ብያለሁና ከተሳሳትኩ ይቅርታ። ብስጭቷ ቢገባኝም ታሪክ መጻፍን በተመለከተ የተንደረደረችበት ግምትና ሌሎችም የሚያሰሙት ትችት በመሰረቱ የተሳሳተ ነው። ላብራራ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

መስፍን ማሞ (ሲድኒ-አውስትራሊያ)

ለቀደሙት የተባለውን ሰምታችዃል……… ይህም ተፅፏልና!

ለምትበልጠው ፀጋ ቅኑ። እኔም ዳግመኛ እጅግ የበለጠ ሌላ ጎዳና አሳያችዃለሁ፤ በሰዎች ሁሉ ቋንቋና በመላእክት ቋንቋ ብናገር፤ ትንቢትም ብናገር፤ የተሰወረውን ሁሉና የጥበብን ሥራ ሁሉ ባውቅ፤ ተራራም እስካፈልስ ድረስ ሃይማኖት ቢኖረኝ፤ ያለኝንም ሁሉ ለድሆች ባበላ፤ ዳግመኛም ሥጋዬን ለእሳት ቃጠሎ ብሰጥ፤ ፍቅር ከሌለኝ የተጠቀምሁት የለም። ፍቅር ያለው ሰው ሩህሩህ ትዕግስተኛም ነውና።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

ወያኔ ለትግራይ ሕዝብ ሀብትንና ብልጽግናን አመጣ ብለው የሚያምኑ ሰዎች ብዙ ናቸው፤ ወያኔ የሥልጣን ወንበሩ ላይ በመውጣቱ ትግሬዎች ሁሉ አልፎላቸዋል ተብሎ ይታመናል፤ በተለይ በአውሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ ላይ የጠነከረ እምነት አላቸው፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ውጭ ብዙ ውይይትም ይሁን ንትርክ ይደረጋል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ግን የተፈራ ርእስ ነው፤ ውስጥ-ውስጡን እንጂ አደባባይ አይወጣም፤ ይህንን ጉዳይ በኢትዮጵያ ውስጥ አደባባይ ለማውጣት ጊዜው የደረሰ ይመስለኛል፤ አረጋዊ በርሄ፣ ገብረ መድኅን አርአያ፣ አስገደ ገብረ ሥላሴ፣ አብርሃ ደስታ (አሥር ቢሞሉልኝ ደስ ይለኝ ነበር!) እየደጋገሙ ቢያነሡትም ሌሎች በቁም-ነገር የተቀበሉት አይመስልም፤ ሕዝቡ ግን በራሱ መንገድ እየተናገረና ምስክርነቱን እየሰጠ ነው፤ በመቀሌ የተሠራውን የመኳንንት መንደር ሕዝቡ አፓርቴይድ ብሎ ሲሰይመው፣ በአዲስ አበባ የተሠራውን መንደር መቀሌ ብሎ ሲሰይመው እየመሰከረ ነው፤ ‹‹የለሁበትም!›› እያለ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ከጸጋዬ ገብረመድኅን አርአያ

ወያኔዎች አዲስ አበባን ከተቆጣጠሩ በኋላ የነበሩትን ዕለታት ክንውኖች በሥርዓት የመመዝገብ ልምድ ያለው ሰው የሚያሰፍራቸው ልዩ ልዩ ሁኔታዎች ይኖሩታል። ከመጀመሪያው ዕለት አንስቶ። የእኔን የመጀመሪያ ዕለት አጭር ማስታወሻ ልንገራችሁ። በማለዳ ተነስቼ ጋቢዬን አጣፍቼ ከበሬ ላይ ቆሜ ሥፍር ቁጥር የሌላቸው አህዮች ወደ መሐል ከተማው (አዲስ አበባ) ሲጓዙ አያለሁ። ያንኑ ያህል ባራባሶ ጫማ የተጫሙ፣ የአካል ዝለት የሚታይባቸውና ከእህል ጋር ከተለያዩ አያል ቀን የሆናቸው የሚመስሉ “ሰብአዊ ፍጥረቶች” አብረዋቸው ይሮጣሉ። ሲያሳዝኑ! ቆይ ቆይ…ከፓስተር ኢንስቲቱት በር ላይ አንድ ጥይት ተተኰሰ። ሌላ ጥይት- ሌላ ጥይት! ሰዎቹ ካለፉ በኋላ ወጣ ብለን ያየነው ሟች በሰፈሩ እንደ ሕሊና ሕመምተኛ የሚታወቅ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ነቢዩ ሲራክ

በለጋ እድሜዋ ትዳር መስርታ ሁለት ትጉህ መንታ ልጆች የታደለች እህት ከትዳር ጓደኛዋ ችግር ገጠማት። የ “ተበዳይ ነኝ!” ባይ ወዳጀን ምሬት ደጋግሜ ብሰማም ከቀናት በፊት “በደለኝ!” ያለችው የትዳር አጋሯ በኮሚኒቲው ሽምግልና ኮሚቴ በኩል ክስ መስራቱን እና የክስ ጥሪ እንደደረሳት ሰማሁ። ከአሰር አመት በፊት እድሜዋ ገና የ17 አመት እያለ የዛሬ የ12 አመት እድሜ የሆነውን ትልቁን ልጀን ያሳደገችውን እህት የቆየ አብሮነት ትውስታ እያሰብኩ የአለመግባባቱን ሽምግልና ወደሚከወንበት የጅዳ ኮሚኒቲ ሽምግልናውን ለመታዘብ መጓዝ ጀመርኩ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተመስገን ደሳለኝ Temesegen Desalegnተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ) 

ኢህአዴግ ያነበረውን ቋንቋንና ዘውግን መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝም አደገኛነት በተመለከተ በርካታ ምሁራን፣ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች … ሳያሰልሱ ለመምከርና ለማስጠንቅቅ መዋተታቸውን አልዘነጋሁም። እኔም ከ“ፍትህ” ጋዜጣ እስከ “ፋክት” መጽሔት ድረስ ችክ ያልኩበትም ሆነ ዛሬ በዚህ ተጠየቅ የተመለስኩበት ምክንያት ችግሩ እያደር እየተባባሰ በመምጣቱና ከምንጊዜውም በላይ አዘናግቶ ወደተፈራው የእርስ በእርስ እልቂት ሊዘፍቀን እየተንደረደረ በመሆኑ፣ ቅድሚያ ሰጥተን በሕብረ-ድምፅ ‘የሀገር ያለህ!’ ብለን መጮህ እንዳለብን ስለማምን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Journalist Tsion Girma, ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ
ጽዮን ግርማ
[email protected]

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ለዛሬ የተቀጠሩትን ሦስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች አቤል ዋበላ፣ በፍቃዱ ኃይሉና ማኅሌት ፋንታሁን መዝገብ ለማየት የተሰየመው የተጠርጣሪዎቹ ቤተሰቦች ችሎት ሳይገቡ ነበር። ከመጀመሪያው ችሎት በኋላ ችሎቱ ባለው ቦታ ልክ ቤተሰብ እንዲገባ ተፈቅዶ የነበረ ቢኾንም ዳኛዋ የዕለቱን ሥራ ሲጀምሩ ስለዚህ ጉዳይ የሚያውት ነገር ያለ አይመስልም። ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጪ የሚሰየሙት ዳኞች ተረኛ ዳኞች በመኾናቸው የዛሬዋ ዳኛም ለመዝገቡና ለጉዳዩ አዲስ ነበሩ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Journalist Tsion Girma, ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ
ጽዮን ግርማ
[email protected]

ቀኑ ቅዳሜ በመኾኑ ፒያሳ በሚገኘው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ግቢ ውስጥ ከዘጠኙ ተጠርጣሪ ቤተሰቦች ውጪ መደበኛ ችሎት ሊከታተል የመጣ ሌላ ሰው አልነበረም። ከሁለት ሰአት ተኩል ጀምሮ ሲጠራቀም የቆየው የችሎት ተከታታይ ቀስ በቀስ በርከት ብሎ በግቢው መታየት ጀመረ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጽዮን ግርማ ([email protected](በፋክት መጽሔት የታተመ)
የታሰሩት ስድስቱ ጦማሪያንና (Bloggers) ሦስቱ ጋዜጠኞች 3 jailed journalists and 6 bloggers
ሚያዚያ 17 እና ሚያዚያ 18 ቀን 2006 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር የዋሉት ስድስቱ ጦማሪያንና (Bloggers) ሦስቱ ጋዜጠኞች በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ) ከታሠሩ ዛሬ ሃያ ሦስተኛ ቀናቸውን ይዘዋል። በእነዚህ ጊዜያት ውስጥም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ሁለት ጊዜ ቀርበዋል። እሁድ ሚያዝያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም. ለመጀመሪያ ጊዜ ሲቀርቡ ብቻቸውን በመኾኑም የፍርድ ቤቱ ድባብ ምን ይመስል እንደነበር የሚያውቅ አንድም ታዛቢ ሰው አልነበረም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተክለሚካኤል አበበ (ቶሮንቶ-ካናዳ) 

እንደመግቢያ፡ ግንቦት ሰባት ምን ነካው?

፩-      ልረብሽ ነው፡፡ ልክ እንደኢሳት ሁሉ፤  “ግንቦት ሰባትም የኛ ነው” ( “የኔ ነው” የሚለው መፈክር አይመቸኝም)፡፡ የኛ ለሆነ ነገር ደግሞ ፍቅራችንን የምንገልጸው፤ በጭብጨባና በሽብሸባ ብቻ ሳይሆን፤ በተግሳጽና በትችትም ጭምር ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ለድርጅታቸው ካላቸው ጽኑእ ፍቅር የተነሳ፤ ድርጅታቸውም መሪዎቻቸውም ሲሳሳቱ፤ መተቸት የሌለባቸው ብጹአን አድርገው ይወስዱኣቸዋል፡፡ በዚህ አልስማማም፡፡ ስለዚህ፤ ግንቦት ሰባትን/የሊቀመንበሩን ቃለምልልስ ትንሽ ልተች ነው፡፡ ይህንን ነው ረብሻ ያልኩት፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

“ሽፈራው - ሞሪንጋ” በአበራ ለማ "Shiferaw - Moringa" by Aberan Lemmaጋዜጠኛ፣ ገጣሚና ደራሲ አበራ ለማ “ሽፈራው – ሞሪንጋ” የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ አሣተመ። ሞሪንጋ ወይም ባገራችን “ሽፈራው” እያልን በስፋት የምንጠራው ዕጽ፣ እጅግ እውቅናን አግኝቶ የኖረው በእስያ ውስጥ ነው። ሕንዶች ኦሊፌራ የተሰኘው ዝርያ ባለጸጎች በመሆናችው በብዙ መልኩ ሲጠቀሙበት ኖረዋል። ዛሬ ኦሊፌራ የተሰኘው ዝርያ፣ በሰሜንና ደቡብ አሜሪካ፣ በካሪቢያን ደሴቶች፣ በአፍሪካና በኦሴኒያ ውስጥ በብዛት እየለማና እየተስፋፋ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Victory Over Tyranny in Ethiopiaፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ነጻነት ለሀገሬ)

በ2015 በሚካሄደው ፓርላሜንታዊ “ምርጫ” መቅረብና መወሰን ያለበት አንድ ጥያቄ ይህ ነው፤ “የኢትዮጵያ ህዝቦች አሁን እ.ኤ.አ 2014 ያሉበት የኑሮሁኔታ ከቀድሞ 2010 ወይም 2005 ከነበሩበት የኑሮ ሁኔታ ይሻላል ወይ?” ህዝቦች ካለፉት ዓመታት በተሻለ ሁኔታ ላይ የማይገኙ ከሆነ አንደ አሮጌ ሸማ መቀየር መቀየር ይኖርባቸዋል። የፖለቲካ ሰዎችና እንደ አሮጌ ሸማ ናቸው። በየጊዜው ካልታጠቡና ካልተለወጡ ይበሰብሳሉ ይገማሉም። በጣም የሚገርም ነገር ነው! ምስኪን ኢትዮጵያውያ አንድ የበሰበሰ የገማ ሸማ ለሌላ 5 ዓመታት በጠቅላላው ለ25 ዓመታት ስትለብስ አያሳዝንም? 

ሙሉውን አስነብበኝ …

Dr. Shakespear Feyissa ዶ/ር ሼክስፒር ፈይሳ13 may 2014 (EMF) የረዳት ፓይለት ኃይለመድህን አበራን ጉዳይ ለመከታተል ኢትዮጵያዊው የህግ ባለሞያ ዶ/ር ሼክስፒር ፈይሳ ባለፈው ሳምንት ወደ ጄኔቭ-ስዊዘርላንድ ተጉዟል።  

ሙሉውን አስነብበኝ …

Abera Lemma and yehamerewa qonjo ጋዜጠኛ አበራ ለማ ከሐመሯ ቆንጆ ጋራየወለላዬና የአበራ ለማ የግጥም ምልልስ

ደራሲና ጋዜጠኛ አበራ ለማ የሬድዮ ጋዜጠኛ በነበረበት ጊዜ ወደ ጋሞጎፋ
ለሥራ ሄዶ ሳለ፣ በድንገት ካጋጠመችው የሐመር ቆንጆ ጋር የተነሳው ፎቶ ነው። ዘመኑ 1969 ዓ.ም. ሲሆን፣ ፎቶ ግራፍ አንሺው የእርዳታ ማስተባበሪያው ማንተጋፍቶት አጥናፉ ነበር። ምልልሱን ያንብቡ!

ሙሉውን አስነብበኝ …

Journalist Tsion Girma, ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ(የልጆቻችሁ እስር አንጀታችሁን ላሳሰራችሁ)

ጽዮን ግርማ

እኔና ጓደኛዬ (ሊሊ) የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ)ን ደጅ የረገጥነው በጠዋት ነበር። ምግብ ማቀበል እንጂ ማግኘት ስለማይቻል የግቢው በር እንደተከፈተ ለልብ ወዳጃችን የወሰድነውን ቁርስ ሰጥተን ያደረ ተመላሽ ዕቃ እስኪመጣልን ከመግቢያው ፊት ለፊት ባለው ድንጋይ ላይ ቁጭ ቁጭ ብለናል።ቀዝቀዝ ባለው አየር ላይ ጥቂት ካፊያ ስለነበር ቅዝቃዜው ኩርምት አድርጎናል። ጥቂት ቆይቶ አንዲት እናት በስስ ፌስታል አንድ አራት የሚኾን ፓስቲ (ቤት ውስጥ የሚጠበስ ቂጣ መሰል ብስኩት) ጠቅለል አድርገው ይዘው ወደኛ መጡ ፊታቸውን ጭንቅ ብሎታል። 

ሙሉውን አስነብበኝ …

Journalist Tsion Girma, ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ
ጽዮን ግርማ
[email protected]
Journalist Tesfalem Weledeyes, ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ
ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ

የ2012ቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳታዊ ምርጫ ከመከናወኑ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ስለምርጫውና የአሜሪካ የጋዜጠኝነት ኹናቴ እንዲወያዩ በአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት አዳራሽ ከተጋበዙና ከሰማንያ የዓለም አገሮች ከተውጣጡ አንድ መቶ ሠላሣ ተሳታፊ ጋዜጠኞች መካከል አንዷ ነበርኹ። ልምዳቸውን እንዲያካፍሉ ከተጋበዙ የአሜሪካ አንጋፋ ጋዜጠኞች መካከል ታዋቂው የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጠኛ ቦብ ውድዋርድ አንዱ ነበር። 

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሄኖክ የሺጥላ
አዲሱን ( የነበረውን ግን ሰሞኑን የሾረውን ) የ ” ኦሮሞ ወጣቶች ” ግድያ። በነገራችን ላይ ለምንድን ነው ” የኢትዮጵያ ወጣቶች ” የማንለው ? ማለት ስለማንፈልግ ? ወይስ ብንል ባንል ምን ይጠቅማል ( ምንስ ይጎዳል በሚል ሃሳብ ?) ሁለቱንም ያዙልንና እንቀጥል። ሰሞኑን አምቦ ላይ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ ወዳጆች ” ልጅ ሄኖክ በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ ነገር በል እንጂ” ጠላቶች ደሞ ” አንተ ምንትስ አማራ አሁን አማራ ቢሆን ኖሮ ይሄ ሁሉ መከራ የደረሰበት አምሳ ገጽ ጽፈህ ፣ ነገሩን ለውጠሕና ለጥጠህ ባቀረብከው ነበር ” የሚሉ መልዕክቶችን አስቀምጠውልኛል። እኔም እንደ ለገዳዲ ሬዲዮ ” ጦማሪዎችች ሆይ ምልእክታችሁ ደርሶኛል ለሁሉም እንደነገሩ ለመመለስ እንሆ–“

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጫቱን ሲያስገቡ የተያዙት የሦስት ዓመት እስራት ይጥበቃቸዋል
በሕገወጥ መንገድ ከሎንዶን ወደ ስዊድን ሲግባ የተያዘ ጫት Chat, Foto: Scanpix

Ethiopia Zare (ዓርብ ግንቦት 1 ቀን 2006 ዓ.ም. May 9, 2014)፦ 816 ኪሎ ጫት ከሎንዶን በስዊድንዋ የወደብ ከተማ ጉተምበርግ በኩል በመርከብ ተጭኖ ሲገባ አፕሪል ላይ መያዙንና ሁለት ሰዎችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ሜትሮ ጋዜጣ በዛሬው ዕትሙ አስነብቧል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)

በ2005 ዓ.ም መጀመሪያ አቶ ኃይለማርያም “ጠቅላይ ሚኒስትር” ተደርጎ በኢህአዴግ ሲሾም፤ በፓርቲው ውስጥ አክራሪ ብሔርተኛ የአመራር አባላት ከመኖራቸው አኳያ፤ መቼም ቢሆን “ራሱን ችሎ ይቆማል” ብሎ መጠበቁ ተምኔት እንደሆነ በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ይህ ኃይል እንኳን እንደ ኃይለማርያም ላለ የድል አጥቢያ መሪ ቀርቶ፣ ከድርጅቱ ምስረታ ጀምሮ እስከ ምኒሊክ ቤተ-መንግስትም ድረስ ታላቅ የተጋድሎ ታሪክ ለነበረው አቶ መለስም ቢሆን ክፍተት ካገኘ አለመመለሱን የ93ቱ ሣልሳዊ ህንፍሽፍሽ በግልፅ አሳይቶ ማለፉ አይዘነጋም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Journalist Tsion Girma, ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ
ጽዮን ግርማ
[email protected]
Journalist Tesfalem Weledeyes, ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ
ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ

በአነጋገሩ ቀጥተኛና በጠባዕዩ ገራገር ነው። ‹ጥርስ ያሳብራሉ› በሚባሉ ስብሰባዎች፣ በኃይለ ቃል በተሞሉ የኤዲቶሪያል ውይይቶችና ግምገማዎች ሳይቀር ስሜቱን ውጦ በተረጋጋ መንፈስና በለዘብታ ቃል መመላለስ ጸጋው ነው። በኤዲቶሪያል ጠረጴዛዎችና ዴስኮች ዙሪያ በሐሳብ ለመግባባት ከሚደረጉ ግብግቦች ውጭና ባሻገር ቂምና በቀል አያውቅም። በደሙ ውስጥ ከሚዘዋወረውና ራሱን ከሰጠለት የጋዜጠኝነት ሞያውና የጋዜጠኝነት መርሕ የተነሳ ሌላ ዓለም፣ ሌላ ጥቅም፣ ሌላ ኑሮ ያለም አይመስለው። ለእርሱ ኑሮው፣ ለእርሱ ዓለሙ ተጨባጭ መረጃን ከወገናዊነት በጸዳ መልኩ ለሕዝብ ማድረስ ነው – ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጽዮን ግርማ – አዲስ አበባ

ዘወትር እንደምታደርገው ሁሉ በምታዝበት ሬዲዮ ጣቢያ ጓደኞቿን ሰብስባ ወደ ስቱዲዮ የገባችው ሚሚ ስብሃቱ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ስለታሠሩት ሁለት ጋዜጠኞችና ሰባት ጦማሪዎች ከፖሊስ አገኘኹት ያለችውን መረጃ ጠቅሳ ስታወራ ነበር። ኢትዮጵያን ለማተራመስ ከሚሠራው አርቲክል ዐሥራ ዘጠኝ ከሚባል ድርጅት ጋር ሲሠሩ ነበር፣ትልልቅ ሆቴል እየተገናኙ ይወያዩ ነበር፣ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎችን ያደራጁ ነበር፣ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅትና ከአምነስቲ እንዲሁም ከግብጽና ከኤርትራ ገንዘብ ይቀበሉ ነበር፤ የሚሉ ውርጅብኞችን በማውረድ እነርሱን የኢትዮጵያ ጠላት እራሷን ደግሞ የኢትዮጵያ ወዳጅ አድርጋ በመሳል ውንጀላዋን ስታዥጎደጉደው ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጽዮን ግርማ (አዲስ አበባ)

Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዝያ 21 ቀን 2006 ዓ.ም. April 28, 2014)፦ ባለፈው ሳምንት ወደ ማእከላዊ እስር ቤት የተጣሉት ስድስት  የ’ዞን ዘጠኝ’ አባላትና ሶስት ጋዜጠኞች ሁኔታ አነጋጋሪ ሆኖ መሰንበቱ ይታወቃል። በአሁኑ ሰአት እስረኞቹ የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው ሲሆን ክስም እንደተመሰረተባቸው ለማወቅ ተችሏል። ሁኔታውን ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ በፌስ ቡክ ገጿ እንደሚከተለው ዘግባዋለች።

የማዕከላዊ ወንጅል ምርመራ ፖሊስ በትናንትናው (እሁድ) ዕለት ጠዋት አራዳ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት አቅርቦ የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸዋል፡፡ በሦስት መዝገብ የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው ዘጠኝ ጸሐፊዎች አገሪቷን በሶሻል ሚዲያ ለማተራመስ ራሱን የመብት ተሟጋች ነኝ ብሎ ከሚጠራ የውጭ ኃይል ጋር በሐሳብም በገንዘብም ተረዳድተውና ተስማተው በአገሪቷ ላይ የብጥብጥ ቅስቀሳ ለማነሳሳት አቅደው ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸው በቁጥጥር ውለዋል ይህንንም በሚመለከት መረጃ እስክናሰባስብ ጊዜ ይሰጠን በሚል የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸዋል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተመስገን ደሳለኝ – አዲስ አበባ

…ከ97ቱ በእጅጉ የተቀዛቀዘው የ2002ቱ ምርጫ የቀናት ዕድሜ ብቻ ቀርተውታል፤ ከመቼውም በላይ የፖለቲካ ምህዳሩን ያጠበበው ገዢው ግንባር፣ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር የሚያደርገውን የምረጡኝ ክርክር እንደ 97ቱ በቀጥታ ስርጭት እንዲተላለፍም ሆነ በአዳራሹ ታዳሚዎችና ታዛቢዎች እንዲገኙ አልፈቀደም፤ በዚህ ክርክር ላይ ኢህአዴግ እንደተለመደው ለመጀመሪያ ጊዜ ካቀረባቸው ጥቂት አፈ-ቀላጤዎቹ መካከል የተመልካችን ትኩረት በመሳብ ጎልማሳው የወራቤ ፍሬ ሬድዋን ሁሴንን የሚተካከል አልነበረም፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

ልጅ ተክሌ (ቶሮንቶ)

ዘመቻ ነቀምትና ዘመቻ ኢትዮጵያ

፩-      የሲያትሉ ባተሌ ወዳጄ ደውሎ፤ “አንድነት የአዲስ አበባውን ሰልፍ ፈቃድ ተከልክሏል፡፡ ስለዚህ ምን ርምጃ ይውሰድ” በሚል ጥያቄ ሲያደርቀኝ ነበር፡፡ ሳንግባባ ተለያየን፡፡ ከሞላ ጎደል እሱ የሚለው፤ “ቢከለከሉም ገፍተው ይውጡ፡፡ ምክንያቱም፤ በተከለከሉ ቁጥር እሺ ብለው የሚገቡ ከሆነ፤ በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያጣሉ፡፡ ገፍተው ከወጡ ግን፤ መንግስትም ጨክኖ ርምጃ አይወስድም፤ ቢወስድም ግን፤ ትግሉን ያበረታል፤ ሌሎችንን ይቀሰቅሳሉ” ነው፡፡ ኢፍትሀዊ ህግን መጋፈጥ ፍትሀዊነት ነው የሚለውን ይትበሀል ይዞ መሰለኝ የሞገተኝ፡፡ እኔ ደግሞ “የለም ሁሉንም ሰብስቦ ያስራቸዋል፤ ካሰራቸው ደግሞ ሌሎች ሰልፈኞች መውለድ አመታት ይፈጃል፡፡ ስለዚህ ይታገሱ፤ ሲሆን ሲሆን ወደፍርድቤት ይሂዱ፤ ወይም ሌላ ጥበብ ፈጥረው ሂደቱን ያጡዙት፡፡ እንጂ፤ አሁን ገፍተው ሰልፍ ቢወጡ ትግሉን ማጨናገፍ፤ ማስወረድ ነው” ብዬ ሞገትኩ፡፡ አልተስማማንም፡፡  የዚህ ጽሁፍ አብይ ዓላማም ማስታወቂያና ማስታወሻ ቢሆንም፤ የኛ የወጤዎቹ (ዳያስፖራ) ሚና የት ድረስ ነው? ድርጅቶቻችንስ ከመፈክር የዘለለ አመራር ለመስጠት ምን ሸበባቸው? በማለት፤ ከቅዳሜ ኤፕሪል 26ቱ የቶሮንቶ-ነቀምት ዝግጅት ማስታወሻ ጎን ለጎን፤ ሌሎች ጉዳዮችን በስሱ ያሻሻል፡፡ ከዚያ በፊት ግን፤

ሙሉውን አስነብበኝ …