ጸጋዬገ ብረመድኅን አርአያ

“ መኳንንቶቼ፣ ልጆቼና ሕዝቦቼ ሆይ! እኔ ስለ እናቴ ኢትዮጵያ ሕይወቴን ልሰዋላት ሙሉ ፈቃድ አለኝ። በእኔ ልብ ያለው አሳብ በትክክል በእናንተም ልብ በመታሰቡ በጣም ደስ ብሎኛል። “ እንግዲህ አሳባችን አንድ ከሆነ ጠንክሩ እንጂ አትፍሩ። ለዘመቻውም አዋጅ አናግራለሁና አይዞአችሁ አትፍሩ! “ አገሬ ሆይ ስሚ! መኳንንቶቼ፣ ወታደሮቼ፣ ሕዝቦቼ ስሙ…..ወደፊት ገስግሱ እንጂ ወደኋላ አትቅሩ! “ የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ! ልብ አድርገህ ተመልከት ኢትዮጵያ የተባለችው አንደኛ እናትህ ናት! ሁለተኛ ዘውድህ ናት! ሦስተኛ ሚስትህ ናት! አራተኛ ልጅህ ናት! አምስተኛ መቃብርህ ናት! እንግዲህ የእናት ፍቅር፣ የዘውድ ክብር፣ የሚስት ደግነት፣ የልጅ ደስታ፣ የመቃብር ከባቲነት እንደዚህ መሆኑን አውቀኸው ተነሳ!”

አንበሳው አጼ ዮሐንስ- ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (ከአዲስ አበባ)

ልዕለ ኃያሏ ሀገረ-አሜሪካን ዛሬ ለተጎናፀፈችው የሕግ የበላይነት የተከበረበት ሥርዓት መሰረት የጣሉት እነ ቶማስ ጃፈርሰን በነፃነት አዋጃቸው ላይ ‹‹ሁሉም ሰዎች በእኩልነት የተፈጠሩ ናቸው›› በማለት ሲደነግጉ፤ እንግሊዛዊው ደራሲ ጆርጅ ኦርዌል ደግሞ “Animal Farm” በሚለው መፅሐፉ፣ ጉልበታም ‹‹ገዥ›› አድርጎ በሳላቸው ገፀ-ባሕሪያት አማካኝነት ‹‹…አንዳንድ እንስሳት (ሰዎች) ግን የበለጠ እኩል ናቸው›› ይለናል። በርግጥ ሁለቱም አይነት አስተዳደሮች መሬት ወርደው ዓለማችንን ዲሞክራት እና አምባ-ገነን በማለት በሁለት ጎራ የከፈሉ የመሆናቸው ጉዳይ አከራካሪ አይደለም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

አንድ በሀርቫርድ የኒቨርሲቲ ያጋጠመኝን ነገር መግቢያ ላድርገውና ልቀጥል፤ በአንድ ሴሚናር (የጥናት ውይይት) ላይ አንድ ጥቁር አሜሪካን ፕሮፌሰር ወደአሜሪካ በባርነት በመጡት አፍሪካውያን ላይ የተፈጸመውን ግፍ በመዘርዘር አስረድቶ አሁን ለእነሱ ልጆችና የልጅ ልጆች ካሣ መከፈል አለበት የሚል ክርክር አነሣ፤ ካሣውን የመክፈል ግዴታ የሚጣለው ማን ላይ ነው? ካሣውንስ የመቀበል መብት የሚሰጠው ለማን ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን ሳናነሣ ብዙ ሌሎች ጥያቄዎች ይኖራሉ፤

ሙሉውን አስነብበኝ …

Ethio-telecom sucks!ክንፉ አሰፋ

“የደወሉላቸው ደንበኛ ለግዜው ጥሪ አይቀበሉም። …” የምትለዋ አሰልቺ የቴሌ መልዕክት ያላጋጠመው ቢኖር ወደ ኢትዮጵያ ስልክ ደውሎ የማያውቅ ሰው ብቻ መሆን አለበት። ኮ/ል መንግሥቱ ኃይለማርያም ወደ ቀድሞ ወዳጆቻቸው መደዋወል ጀመሩና በመሃል ተስፋ ቆረጡ አሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ስቅለትከሆሳዕና እስከ ማዕዶት

ሰሎሞን ተሰማ ጂ.

በየዓመቱ የትንሣኤ በዓል ተከብሮ የሚውለው፣ በዕለተ እሑድ ነው። ጌታችንና መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳው በዕለተ እሑድ-መጋቢት 29 ቀን ነው። የግዕዝ ቋንቋ ሊቃውንት እንደሚተረጉሙት ከሆነ፣ “ትንሣኤ ማለት-መነሳት ማለት ነው።” ሞትን ድል አድርጎ፣ ከሙታን ተለይቶ መነሳት ማለት ነው። “ሕይወት ማግኘት፣ ነፍስ መዝራት፣ ሕልው መሆን” ማለት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ)

የ1994 የሩዋንዳ የጭፍጨፋ እና የእልቂት ጸጸት በ2014 የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ሰማይ ላይ እያንዣበበ ነው!

ባለፈው ሳምንት የሩዋንዳ ህዝብ እርስ በእርስ የተራረደበትን 20ኛውን ዓመት የሩዋንዳ የዘር ፍጅት መጥፎ ገጽታ ለማስታወስ የሀዘን ሳምንት አውጆ ድርጊቱን በመራር ሀዘን ዘክሮታል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ግርማ ካሳ

ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 19 ቀን ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ እንደጠራ አነበብኩ። ገረመኝ። መጋቢት 28 ቀን በአንድነት ፓርቲ ሰልፍ ይደረጋል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። የአዲስ አበባ አስተዳደር ሕጉን ባፈረሰ መልኩ በመጋቢት 28 ቀን ሰልፍ ማድረግ እንደማይቻል ገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በግርማ አንድሪያስ  (ኔዘርላንድ፡ ኣምስተርዳም)

”….ጋዜጠኞችና ኣስታሚዎች በጥብቅ መታሰርና በገንዘብ መቀጣት የጀመሩት የፕሬስ ኣዋጁ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣ ከሶስት ወር በኋላ  ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ የካቲት 1984 በአትዮጵያ ኣቆጣጠር። ታስረው በፕሬስ ህጉ የተከሰሱና ለመጀመሪያ ጊዜ በፍርድ ቤት ተከራክረው ነጻ የወጡት፣ በመንግስት ባለቤትነት የሚተዳደረው የአዲስ ዘመን ጋዘጣ ኣዘጋጆች ናቸው። ኣዘጋጆቹ የታሰሩትና የተከሰሱት በጋዜጣው ላይ በ ኢትዮጵያ የዲሞክራሲን ጎጂና ጠቃሚ ገጽታዎች የሚዳስስ  ጽሑፍ በማውጣታቸው ነው።”

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)

በዚህ ርዕስ ሥር ባለፈው ሳምንት በይደር ካቆየሁት ተከታይ ጽሑፍ በፊት አንድ እርምት የሚያሻው ጉዳይን በአዲስ መስመር ላስቀድም፡፡

ሬዲዮ ፋና እና “አምደኞቹ”

በ1988 ዓ.ም በኤፈርት ባለቤትነት ስርጭቱን አሀዱ ያለው “ሬዲዮ ፋና”፣ ከምስረታው አንስቶ ዛሬም ድረስ ልክ እንደ በረሃው ዘመን ሁሉ የሥርዓቱ ቀኝ እጅና የርካሽ ፕሮፓጋንዳው ማስተላለፊያ ቱቦ ሆኖ መዝለቁ ለወዳጅም ለጠላትም የማያከራክር ገሀድ የወጣ ሐቅ ነው፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

በተመስገንደሳለኝ (አዲስ አበባ)

– ከ253, 336 ከ42 ሳንቲም ዩሮ በላይ ኪሳራ ደርሷል ተብሏል

– የአእምሮ ችግር እንዳሌለበትም ተረጋግጧል

ፍትሕ ሚኒስቴር በረዳት አብራሪ ኃይለመድን አበራ ላይ የካቲት 9 ቀን 2006 ዓ.ም ሌሊት የበረራ ቁጥር ET 702 የሆንን ቦይንግ አውሮፕላንን ከእነ 202 ተሳፋሪዎቹ ወደ ሮም በሚበርበት ወቅት ጠልፎ ሲውዘርላንድ አሳርፏል በማለት በከፍተኛው ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ክስ መመስረቱን የፍትሕ ሚኒስቴር ምንጮቼ አረጋግጠውልኛል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተክለሚካኤል አበበ (ቶሮንቶ)

የማርቆስ ብዙነህ ደብዳቤ፤

1-       “በርካታ ትምህርት ቤቶች፤ ዩኒቨርስቲና የመንግስት ተቋማት በሚገኙበት አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ የማይቻል በመሆኑ፤ የተጠየቀው የሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ጥያቄ ተቀባይነት ያላገኘ መሆኑን እንገልጻለን” ይላል፤ በአዲስ አበባ መስተዳድር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቅ ክፍል ሀላፊ፤ በአቶ ማርቆስ ብዙነህ ማንደፍሮ፤ መጋቢት 23 ቀን 2006/2014 የተፈረመው ደብዳቤ፡፡ አንድነት፤ ሰልፉን ለማድረግ ያቀረባቸው መስመሮች 3 ሲሆኑ፤ ሶስቱም መስመሮች ከቀበናው የአንድነት ጽ/ቤት ይነሳሉ፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)

ባለፉት አራት አስርታት ሀገሪቱ አያሌ ተግዳሮቶችን መጋፈጧ ባይዘነጋም፤ በተለያየ ጊዜ ሚሊዮኖችን ካረገፈው አሰቃቂው ረሃብ በማይተናነስ መልኩ ሕዝቦቿን ዋጋ ያስከፈለ ጉዳይ ቢኖር የፍትሕ አለመከበር ያስከተለው ሁለንተናዊ ምስቅልቅሎሽ ነው ብሎ ለመናገር የሚያስደፍሩ በርካታ ማሳያዎች አሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም

የአዲስ አበባን መኪናዎች በተለይም በጫት የሚሽከረከሩት ታክሲዎችን በማንኛውም መስቀልኛ መንገድ ላይ ለአምስት ደቂቃ ቆሞ የተመለከተ ሰው በቀላሉ እንደሚረዳው ‹እኔ ካላለፍሁ ማንም አያልፍም!› በሚል መመሪያ መኪናዎቹ ተቆላልፈው እንዲቆሙ ማድረግ ነው፤ እንደሚመስለኝ የአባቶቻችንን ዕዳ እየከፈልን ነው፤ ዱሮ በደጉ ዘመን ሁለት ኢትዮጵያውያን መስቀልኛ መንገድ ላይ ሲገናኙ አንተ-እለፍ አንተ-እለፍ እየተባባሉ የሰማዕታቱንና የቅዱሳኑን ስም እየጠሩ ይገባበዙ ነበር!

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ

ግፍ ከበዛበት ወህኒ የአክብሮት ስላምታየ ይድረሳችሁ!

እነሆ ለሁለተኛ ጊዜ ለአፍታ ያህል እድሉን አግኝቸ ወህኒ የመውረዴን እውነታ ላስረዳችሁ ግድ አለኝ ። ዛሬ አስረግጨ የምነግራችሁ ወህኒ የመውረዴ ምክንያት ሚስጥር ግምሽ እድሜየን ህግና ስርአቷን አክበሬ የኖርኩባትን የሳውዲት አረቢያን ህግ ተላልፊ አይደለም ! የስደተኛው ጉዳይ ያገባኛል በሚል የማቀርበው መረጃ ቅበላየ የማይመቻቸው ፣ ያመማቸው ከተሴረውና እየተሴረ ካለው እገታ ጀርባ ስለመኖራቸው አልጠራጠርም ። … ዛሬ በዚህ ዙሪያ ብዙ አልልም!

ሙሉውን አስነብበኝ …

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም;- በነጻነት ለሀገሬ

ታላቅወንድም በአንክሮ እየተመለከቷችሁ ነው! በሚስጥር፡ የሚንሾካሾከው ወሮበላ መንግስት 2014ኢትዮጵያ 

በኢትዮጵያ ያለው ሚስጥር አነፍናፊው ገዥ አካል በጉአዳ ውስጥ የተደበቁ የኢትዮጵያውያንን/ትን ሚስጥሮች መርምሮ ለማውጣት በጣም ውድ የሆኑ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን በመጠቀም የስለላ ፕሮግራሞችን በመተግበር በታላቅ ፍርሀት ውስጥ ተዘፍቆ በመንፈራገጥ ላይ ይገኛል፡፡ ከፍርሀታቸው የተነሳ ህዝቡ በእነርሱ ላይ ምን ለማድረግ እንደሚችል ስጋት ውስጥ በመውደቅ እራሳቸውን በማስጨነቅ እንቅልፍ አጥተው ሲባንኑ ያድራሉ፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)

ማሕበረወያኔ

በኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም የሚመራው መንግስት ከናቅፋ እስከ ጉና ተራራ ያሉ ምሽጎቻቸውን ከሰማይ በጦር አይሮፕላን፣ ከምድር እሳት በሚያዘንቡ ቢ.ኤሞችና መድፎች ሳያቋርጥ ቢደበድብም፤ በሀገሪቱ ሰሜናዊ አካባቢ ከቀን ወደ ቀን ግዛታቸውን እያሰፉ የተጠናከሩት ‹‹ወንበዴዎች›› ራስ ምታት ሆነውበታል። የኤርትራ ‹‹ነጻ አውጪ›› ቤዝ-አምባው በተወሰነ መልኩም ቢሆን ለጥቃት የመጋለጥ እድሉ አናሳ በሆነው የሳህል በረሃ በመሆኑ አብዛኛው የአመራር አባል መሸሸጊያው አድርጎታል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አምስት የአንድነት ፓርቲ አባላት ታስረዋል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ መጋቢት 20 ቀን 2006 ዓ.ም. March 29, 2014)፦ ዛሬ ገዥው ፓርቲ በጎንደር ከተማ አደባባይ እየሱስ በጠራው ስብሰባ ለእያንዳንዳቸው ተሰብሳቢዎች 8ሺህ ብር ብድር በመስጠት መጭውን ምርጫ ግን ኢህአዲግን እንዲመርጡ በመቀስቀስ ላይ ባለበት ወቅት ምርጫን በገንዘብ መግዛት አይቻልም ብለው ጥያቄ ያቀረቡ አምስት የአንድነት ፓርቲ አባላት መታሰራቸውን አቶ ሃብታሙ አያሌው ዛሬ ይፋ አደረገ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ከፕሮፌሰር አለማየሁገ ብረማርያም

ትርጉምበነጻነት ለሀገሬ

ማዳም ክላሬ አሸንፈዋል! እንኳን ደስ ያለዎት፣ ማዳም ክላሬ!

ባለፈው ሳምንት የ አምራች ኢንዱስትሪዎች የግልጽነት ተነሳሽነት/Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) ሊቀ መንበር የሆኑት ማዳም ክላሬ ሾርት ስልጣናቸውን ከህግ አግባብ ውጭ በመጠቀም እና በማስፈራራት በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል የሙስና ማጋበሻ ቡድናቸው አባል እንዲሆን ለማስቻል የEITI የቦርድ አባላት ድምጻቸውን እንዲሰጡ በማድረጉ ጥረት ሲያካሂዱት የቆዩት ዥዋዥዌ ጨዋታ ተሳክቶላቸዋል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

ከጸጋዬ ገ.መድኅን አርአያ
በአጤ ኀይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት (በ1960 አካባቢ) ኤድመንድ መሪ የተባለ አሜሪካዊ የዕለታዊው ኢትዮጵያ ሔራልድ ጋዜጣ አማካሪ ሆኖ ይሰራ ነበር። እኛም እንጠረጥረው እንደነበረ ሁሉ የአሜሪካ ስለላ ድርጅት ሠራተኛ (ኮንታክት ማን) ነው። (እግዜሩ ይይላቸውና ለካ በእኛም መሐል ሰዋቸውን ይተክሉ ነበር) ኤድ መሪ የሥነ ጽሑፍ ሰው ስለሆነ በማስታወቂያ ሚኒስቴር “ተረፈ ዜና” የምንለውን – የማይታተመውንና የማይታወጀውን (በራዲዮና በቴሌቪዥን) በንጥረ ነገሩ መውሰጃ ሥፍራ የተነፈስነውን ሁሉ ሰብስቦ ካገጣጠመው በኋላ ወደ አሜሪካ ሲመለስ Kulubi የሚል መጽሐፍ አወጣ። እንግዲህ ተረፈ ዜና የገባችሁ ይመስልኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
(ይህ “ኑ! እንዋቀስ” የሚለው ስር ነቀል የለውጥ ጥሪ ቀጥታ የሚያነጣጥረው በኢህአዴግ አባላት ላይ ብቻ ነው፤ አመራሩን በፍፁም አይመለከትም) ኢህአዴግ ራሱ በይፋ ሲናገር እንደተደመጠው፣ በአሁኑ ጊዜ የአባላቱ ቁጥር ወደ ሰባት ሚሊዮን ገደማ ደርሷል። ይህም የአገሪቱ ቁጥር አንድ ግዙፍ የፖለቲካ ፓርቲ ያደርገዋል። በርግጥ ግዙፍ እንጂ ጠንካራ እንዳላልኩ ልብ ይሏል። ምክንያቱም ጥንካሬ የሚለካው በአባላት ቁጥር ሳይሆን በድርጅት ፍቅር፣ በዓላማ ፅናትና በሚሰጡት ልባዊ አበርክቶ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም፦  በነጻነትለሀገሬ

“ከዚህ በኋላ ትዕግስታችን ተሟጧል!”

ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮጵያ እንደገና ወኔ የተሞላበት የትግል መንፈሱን በማደስ ጥንካሬውን አሳየ !

እ.ኤ.አ ማርች 9/2014 የተከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች በዓል ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ ተዘጋጀቶ በነበረው የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶችም ተሳትፎ አድርገው ነበር፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

… በማስመሰል ታጥሮ መሆን በጠፋበት
ምን አገባኝ የሚል በተከማቸበት
የባይተዋር መንፈስ ከሞላ ባገሩ
ዘመኑን ማወቂያ ይሄ ነው ሚስጥሩ
ይሄን ጊዜ ጠርጥር እንደጠፋ ዘሩ።
(ገጣሚ ደምሰው መርሻ/ያልታተመ)
አዎን፣ ገጣሚ ደምሰው እንዳለው እኔም በዚህ ዘመን “ዘሩ እንደጠፋ” አሊያም ሊጠፋ እንደተቃረበ እጠረጥራለሁ፡፡ ስለምን? ቢሉ …በኢትዮጵያችን ለህሊናው፣ ለሕዝብና ለሀገሩ የሚቆረቆር፣ የእውነት ተሟጋችና የሞራል ልዕልናን የተቀዳጀ ሙሉ ሰው ፈልጎ ማግኘት እጅግ አተካች ሆኗልና።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም

ወያኔ/ኢሕአዴግ ጥሩምባ ነፍቶ የብሔሮች፣ የብሔረሰቦችና የሕዝቦች ነጻነት ብሎ ከአወጀና ሁሉንም ለሃያ ሁለት ዓመታት በተስፋ ከአስፈነደቀ በኋላ ችግር ተፈጠረበት፤ ችግሩ ምንድን ነው? ችግሩ የቆጡንአወርድብላየብብቷንጣለች የሚባለው ነው፤ ችግሩ አፍ ከሚችለው በላይ ለመጉረስ ከራስ ጋር መተናነቅ ሆነ፤ ችግሩ የማሰብ ድርቀት ነው፤ ችግሩ ከአሜሪካና ከአውሮፓ መንግሥታት ጀምሮ እስከቀበሌ መዋቅር ያሉትን ሁሉ በአንድ ዘዴ እያባበሉና እያታለሉ ማደናበር ነው፤ ችግሩ በሃያ ሁለት ዓመታት ውስጥ ዘዴው ሻግቶ ዓላማው ደብዛው መጥፋቱ ነው፤ ቸግሩ የዘዴው መሻገትና የዓላማው መክሸፍ መጋለጡ ነው፤ ችግሩ ወያኔ የተቀመጠበት የሥልጣን ወንበር መቆርቆር መጀመሩ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አትክልት አሰፋ (ቫንኩቨር)

ነገሩ የሆነው ዲላ ዩኒቨርሲቲ ነው። ቆነጃጅት ወጣት ሴት ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውጭ ባሉ የከተማው ደለላዎች ጋር በመተባበር እጅግ ዘግናኝ ስራ ይሰራሉ። ደላሎቹ የቆነጃጅቶቹን ተማሪዎች ፎቶ የያዘ ትልቅ ካታሎግ ይዘው ከአዲስ አበባም ሆነ ከአቅራቢያው ከተሞች አለዚያም ከዚያው ከዲላ ከተማ ብቅ የሚሉ ሃብታም ደንበኞቻቸውን የተማሪ ኮረዶችን ፎቶ በመስጠት ያስመርጣሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በዉጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ በአካል ርቆ ቢገኝም ልቡ አገር ቤት ነዉ።ኢ/ር ግዛቸው 

 አንድነት ፓርቲ በ450 የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ለመወዳደር እቅድ አለው

Ethiopia Zare ሰኞ ካቲት 24 ቀን 2006 ዓ.ም. March 3, 2014)፦ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር፣ በአሜሪካ ካሉ የድጋፍ ማህበራት ጋር ወደ ሁለት ሰዓት የሚጠጋ ሰፊ ዉይይት በቴሌኮንፈራንስ አደረጉ። ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራዉ ፣ የአንድነት ፓርቲ እያደረጋቸው ስላለው ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች ሰፋ ያለ ሃታተ የሰጡ ሲሆን፣ ከስብሰባው ተሳታፊዎች በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጠዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

(ተመስገን ደሳለኝ)
በ2004 ዓ.ም የካቲት 23 ቀን በታተመችው ‹‹ፍትሕ›› ጋዜጣ ላይ፣ ‹‹የፈራ ይመለስ!›› በሚል ተመሳሳይ ርዕስ፣ ከሰላማዊ አብዮት ውጪ አማራጭ ካለመኖሩም ባለፈ፣ ኢህአዴግ ቢያንስ ሕገ-መንግስታዊ ጥበቃ ላላቸው ሕዝባዊ ጥያቄዎች ምላሽ የመስጠት አቅምም ፍላጎትም እንደሌለው ለመሞገት ሞክሬ ነበር፡፡ ግና፣ አገዛዙ ለእንዲህ ያሉ ግዴታዎች የተዘጋጀ ባለመሆኑ ከማድመጥ-መዳ–መጥን፤ ከመመከር-መከራን፤ ከማሰብ-ቃሊቲ መሰብሰብን፤ ከመሻሻል-ከሀገር ማሸሽን፤ ከማመን-መርገጥን… በመምረጡ፤ ዛሬም ድረስ ነፃነት ናፋቂው ዘመነኛ ትውልድ፣ በፀጥታ አርምሞ ወደተዋጡት አደባባዮች ከማማተር ያለፈ አማራጭ እንዳያገኝ ገፊ-ምክንያት ሆኖ ቀጥሏል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

"እኛና አብዮቱ" በሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስስሜነህ ታምራት (ስዊድን)
የቀድሞው ባለሥልጣን ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ “እኛና አብዮቱ” በሚል ርዕስ አንድ መጽሐፍ ለንባብ አብቅተዋል። ይህንኑ መጽሐፍ መነሻ አድርገው፤ ወይም የቆየ የፖለቲካ መስመር ልዩነት አነሳስቷቸው ይሁን ብቻ አቶ ሰለሞን ገ/የስ በኢትዮ-ሚዲያ ድረ-ገጽ ላይ “የመጽሐፍ ግምገማ” በሚል ርዕስ የጻፉትን አንብቤ እንደጨረስኩ ሁለት ሀሳቦች መጡብኝ። 

ሙሉውን አስነብበኝ …

ከአንተነህ መርዕድ

እነሆ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ኩራት የሆነውን የአድዋን ድል 118ኛ ዓመት ልናከብር ተዘጋጅተናል። ይህንን ታላቅ ቀን ባንድ ትንሽ ማስታወሻ ብዙ ማለት ባይቻልም ለድሉ አስተዋጾ ካደረጉት ታላላቅ ኢትዮጵያውያን አሉላል ላነሳ ፈለግሁ። አሉላ አባ ነጋ ትግራይ ውስጥ በተንቤን አውራጃ መናዌ በምትባል መንደር እንግዳ ቁቤ ከተባሉ ገበሬ ነው የተወለዱት።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ክንፉ አሰፋ

በብሄራዊ ትያትር አካባቢ አንዲት አነስተኛ ምግብ ቤት ነበረች። «ገሊላ ምግብ ቤት» ትባል ነበር። በአዲስ አበባ «ቁምራ» ከመግባቱ በፊት በአካባቢው ያሉ  የመንግስት ሰራተኞች በምሳ ሰዓት ይህችን ምግብ ቤት ያጨናንቋት ነበር። ቁምራን የማታውቁ ካላችሁ፤ ለጽድቅ የሚደረግ መንፈሳዊ ጾም እንዳይመስላችሁ። እድገ ትና ትራንስፎርሜሽኑ ያመጣው አዲስ ክስተት ነው – ቁርስ ምሳና ራት በአንድ ጊዜ የመመገብ ዘዴ። «ኑሮ በዘዴ ፣ ጾም በኩዳዴ» ይባል ነበር። ይህ አባባል አሁን መኖ በዘዴ በሚል ተቀይሯል። መቼም ሁሉም ነገር በነበር እየቀረ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ከግርማ አንድሪያስ (ኔዘርላንድ -ኣምስተርዳም)

”…ልብ በሉ ልጆች የምነግራችሁን ኣድምጡ። ችሎታችሁ ምንም ጥርጥር የለውም። መሮጥ ከጀመራችሁ – ካልጨረሳችሁ አንደማታቆሙ ኣውቃለሁ። የምትሮጡት አንደባለፈው ጃፓን -ቶኪዮ ላይ ኣይደለም። ኣይደለም።  የኣሁኑውድድራችሁ ጣሊያን ጣሊያን ጣሊያን ጣሊያን ሮም ነው። ነው። ነው። ጣሊያኖች ችሎታችሁን ስለማይችሉት ሊተኖኮሎኣችሁ ይችላሉ።  በውድድር ላይ ሆናችሁ ቢመቱዋችሁ አንኩዋን መልስ ኣትስጡ። ለማዘናጋት ለማሰናከልና ስህተት አንድትሰሩ ስለሚፈልጉ  የሚጠቀሙበት ተንኮላችው ተንኮላችው ተንኮላችው ተንኮላችው ተንኮላችው ነውና ነውና ነውና ኣደራ ኣደራ ኣደራ !… ይድነቃቸው ተሰማ ነበሩ። ነበሩ። አነ ኣበበ ቢቂላን ወደ ሮም ለሩጫ ከመውሰዳቸው በፊት  በዝግጅት ላይ የተናገሩት።  (ድሮ መጽሔት ላይ ቃል በቃል ባይሆንም በግርድፉያስታወስኩትን ያሰፈርኩት ነው።)

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተመስገን ደሳለኝ (አዲስ አበባ)
‹‹…የውሳኔ አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት ተጠናቀቀ፡፡ የባሕር መዝገቡም ተዘጋ፡፡ …ቀፋፊ ምሽት ነበር፡፡ በእያንዳንዳችንም ፊት ፈገግታ አይታይም፡፡ ከአዳራሹ ሳንርቅ ከራሳችን ጋር ብቻ እየተነጋገርን በሃሳብም ርቀን እየሄድን አመሸን፡፡ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ወደ አዳራሹ እንድንገባ ተነገረን፡፡ በፍጥነት ገብተን ቦታችንን ያዝን፡፡ ሊቀ-መናብርቱም ቦታቸውን ያዙ፡፡ ‹ዛሬ ስለወሰድነው እርምጃ ለጦር አዛዦች ማሳወቁ ይበጃል በማለት ጠርተናቸው እዚሁ ይገኛሉ› ብለው ወደ አጃቢዎቻቸው ፊታቸውን ዘወር አድርገው ‹አስገቧቸው!› የሚል ትዕዛዝ ሻለቃ መንግስቱ ሰጡ፡፡ ጄነራል ጃጋማ ኬሎ፣ ጄነራል ግዛው በላይነህ፣ ጄነራል ታደሰ ገብሬ፣ ጄነራል ወርቁ መኮንን ተከታትለው ገቡ…››

ሙሉውን አስነብበኝ …

ለአቶ ተክለሚካኤል አበበ፤ ጥያቄዎች ምላሽ ቢሆን

ያሬድ ኃይለማርያም
በመጀመሪያ በአቅርቡ በተከታታይ ለአንባቢያን ያቀረብኩዋቸውን ሁለት ጽሁፎች አንብበህና ጊዜህንም ወስደህ በዝርዝር ላቀረብከው የሙግት ሃሳብ ምስጋናዮ የላቀ ነው። ለነገሩ የጽሑፌም ዋና አላማ ጉዳዩን ሕዝብ እንዲያውቀው ብቻ ሳይሆን በተነሱት ነጥቦችም ዙሪያ በአንባቢዎች ዘንድ የውይይት ሃሳብንም በማጫር ጉዳዩ ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኝም ጭምር ስለሆነ ያንተ ምላሽ እኔንም በዚሁ ጉዳይ ላይ በድጋሚ እንድመለስበት አድርጎኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሰዓሊ ለማ ጉያ Lemma Guyaገዛኸኝ ድንቁ (ከጀርመን)
ሥዕል ከሥነ ጥበብ የፈጠራ ሥራዎች ሙያ ዘርፎች አንዱ ነው። በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የካቲት 1993 ዓ᎐ም. ባሳተመው ጥልቅ የሥነ ቋንቋ ጥናት የአማርኛ መዝገበ ቃላት ላይ ስዕል ቀጥተኛ ትርጉሙን እንዲህ ሲል ይፈታዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አርቲስት አይናለም ተስፋዬን ጨምሮ 12 ሰዎች ብቻ ወደ አዳራሹ ገብተዋል

Ethiopia Zare (ሰኞ የካቲት 14 ቀን 2006 ዓ.ም Feb 17, 2014):- በአውስትራሊያዋ ሲድኒ በአምባሳደር አረጋ ሃይሉ የተጠራው ልማታዊ ውይይት በሲድኒ ነዋሪ ኢትዮጵያዊያን ተቃውሞ በማሰማት ላይ መሆንቸውንና የመንግስት ደጋፊዎች በቦታው ለመታየት እንዳልቻሉ ለማወቅ ተቻለ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጠላፊው ለአምስት ዓመታት በአየር መንገዱ አገልግሏል”መንግሥት

”በጠለፋው ሳይሆን ተሳፋሪዎቹን በማገቱ እስከ 20 ዓመት ሊያሳስር የሚችል ክስ ሊመሰረትበት ይችላል”የስዊስ አቃቤ ሕግPolice search passengers after helping them disembark from the hijacked Ethiopian Airlines flight

Ethiopia Zare (ሰኞ የካቲት 10 ቀን 2006 ዓ.ም. Feb. 17, 2014)፦ ዛሬ ጠዋት ሮም ሊገባ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ”ኢቲ 702” በ31 ዓመቱ ረዳት አብራሪ ኃይለመድህን አበራ ተገኝ ተጠልፎ በስዊዘርላንድ፤ ጄኔቭ ከተማ ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ አረፈ። በጣሊያንና ስዊዘርላንድ ድንበር አካባቢ ሲደርስ በሁለት ተዋጊ ጀቶች ታጅቦ የነበረ ሲሆን፣ ረዳት አብራሪው በስዊዘርላንድ ጥገኝነት ጠይቋል። ተሳፋሪዎቹ አውሮፕላኑ መጠለፉን አያውቁም ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Alemayehu Atomssa, አቶ አለማየሁ አቶምሳEthiopia Zare (ሰኞ የካቲት 10 ቀን 2006 ዓ.ም. Feb. 17, 2014)፦ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አለማየሁ አቶምሳ በገዛ ፈቃዳቸው ከኦሕዴድ ሊቀመንበርነታቸው ለቀቁ። በዛሬው ዕለት በተካሄደው የኦሮሞ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ መልቀቂያቸውን ያስገቡት አቶ አለማየሁ አቶምሳ ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቶ ከሥልጣን መነሳታቸው ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጽዮን ግርማ

ሕፃን እዮሲያስ የጓደኛዬ ልጅ ነው። በሰባት ዓመቱ ሁለተኛ ክፍል ገብቷል። ፈጣንና መጠየቅ የሚወድ ታዳጊ ነው። ባገኘኝ ቁጥር በጥያቄ ልቤን ጥፍት ያደርገዋል። አብዛኛው ጥያቄዎቹ ትምሕርት ቤት ከጓደኞቹ ጋራ ከሚያደርጋቸው ጨዋታዎች የሚመነጩ ናቸው። ባለፈው ሰሞን እንዲህ ብሎ በእንቆቅልሽ መልክ ጠየቀኝ። ለእኔም አጠያየቁ ልጅነቴን ስላስታወሰኝ በትዝታ ፈገግታ ታጅቤ “ምናውቅልህ” አልኩት። ”እ … ቢሄዱ፣ ቢሄዱ የማይሰለቻቸው?” አለኝ። ጥያቄውን እኔ ከለመድኩት የልጅነት የእንቆቅልሽ መልስ ጋራ ለማዛመድ የዱር አልቀረኝ የቤት መንገድ አይሰለቻቸውም ስል ያሰብኳቸውን እንስሳት ማሰላሰል ቀጠልኩ። የመሰሉኝንም ስማቸውን ደረደርኩለት፤ አልተሳካልኝም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ለአቶ ያሬድ ኃ/ማርያም አንዳንድ መልሶች

ተከልሚካኤል አበበ – ቶሮንቶ

እንደመግቢያ፤ ያሬድና ጽሁፉ

1-         አቶ ያሬድ ሀይለማሪም (ያሬዶ) ለሰብአዊ መብት መሟገት አመል ሆኖበት (አመሉ፤ አዎንታዊ በሆነ መልኩ ማለቴ ነው)፤ ከጥቂት ቀናት በፊት አንድ ጽሁፍ አውጥቶ ነበር፡፡ ያንን ጽሁፍ ተከትሎ አንዳንድ በብእር ስም ጀርባ የተደበቁ ተቺዎች አበሳጩት መሰለኝ ሌላ ተከታይ ሁለተኛ ጽሁፉም ጽፎዋል፡፡ የኔ አስተያየት በመጀመሪያው ጽሁፍ ላይ ነው፡፡ ከሞላ ጎድል ጽሁፉ፤ ግንቦት ሰባት፤ ለኢትዮጵያ እንታገላለን ብለው ኤርትራ የገቡ ወጣቶች ላይ፤ ከኤርትራ መንግስት ጋር በመተባበር፤ ብዙ ግፍ እየፈጸመ ወይንም እያስፈጸመ ሲሆን፤ መገናኛ ብዙሀን ይሄ ግፍ ሲፈጸም እያዩ ዝም ማለታቸው፤ አግባብ አይደለም የሚል ነው፡፡ የያሬዶ ጽሁፍ ሸጋ ነበር፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

አሰግድ ኣረጋ (ኮለምበስ – ኦሃዮ)
ጤፍ Teff. Photo by Peter Bregg

ሰሞኑን ስለጤፍ ምርታችን የባዕዳኑ ብዙኀን መገናኛ አጀብ እያሉን ነው፤ ለዘመናት የተደበቀው የዘሩ ገመና መጋለጡን እየነገሩን ነው፤ ስለያዘው ንጥረ ነገር፣ ስለጤናማነቱ፣ በምዕራቡ ገበያ ስለመፈለጉ፣ ከሁለም በላይ ስለ ውጭ ምንዛሪ ምንጭነቱ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም Prof. Al-Mariamፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም – ነጻነት ለሀገሬ)

ፈረሰኛው ረሃብ ኢትዮጵያ ላይ አያነጣጠረ ነው!
ባለፈው ሳምንት ኤንቢሲ/NBC የተባለው የዜና ወኪል በኢትዮጵያ እየተንፏቀቀ በመጣው ረኃብ ላይ ያደረገውን ጥናታዊ ዘገባ ዋቢ በማድረግ በማርቲን ጌይስለር አማካይነት ከዚህ በታች የተመለከተውን ሀተታ ለአየር አብቅቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) Ethiopian People's Congress for United Struggle (Shengo)Ethiopia Zare (ረቡዕ የካቲት 5 ቀን 2006 ዓ.ም. Feb. 12, 2014)፦ የአማራ ክልል ም/ፕሬዝዳንት አቶ አለምነው መኮንን በአማራው ላይ የሰነዘሩትን ፀያፍና በዘር ጥላቻ ላይ ያዘነበለ ስድብ በማውገዝ፤ “የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ” ትናንት የካቲት 4 ቀን 2006 ዓ.ም. መግለጫ አወጣ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ነጋ ዓለማየሁ

ሰሞኑን የአማራ ክልል ባለሥልጣን ናቸው የተባሉ ሰው በአማራው ሕዝብ ላይ የጅምላ ስድብ ሲሳደቡ ተደምጠዋል። ሰውየውን ስሙንም ሰምቼው አላውቅም። እንዲህ አይነቱን ሰው አንቱ ማለትም የሚገባ አልመሰለኝም። ሀገሪቱን የሚመራው መንግሥት ከየት አምጥቶ እንዳስቀመጠው እራሱ ነው የሚያውቀው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አስገራሚው የሳውዲው “ኮራጅ ” አባት ምክር

ነቢዩ ሲራክ
ነገሩ እንዲህ ነው፤ ከ20 ዓመት በፊት ሳውዲው ወጣት ራሱን ለሁለተኛ ደረጃ ፈተና ከማዘጋጀት ይልቅ በረቀቀ መንገድ ለፈተናው መልስ የሚሆነውን ማጭበርበሪያ የመልስ ወረቀት አዘጋጅቶ ለፈተና ይቀርባል። ፈተናውን በረቀቀ መንገድ አጭበረብሮ ሰርቶታልና ፈተናውን በተገቢ ውጤት አልፎ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ለማለፍ በቃ!

ሙሉውን አስነብበኝ …

አማኑኤል ዘሰላም

“ስልክ ጠላፊው ሰላይ ‘ጋዜጠኛ'” የሚል አንድ ጽሁፍ አነበብኩ። ሲያትል የሚኖር አንድ ኢትዮጵያዊ ናቸው የጻፉት። የአውራምባ ታይምስ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደን አጠንክረው ይተቻሉ። በቅርቡ በድረ ገጾችና ፌስቡክ የተለቀቀው፣ አቶ አበበ ገላው የተናገሩትን አንዳንድ አባባሎችን የያዘ ኦዲዮ ነው። ይህ ኦዲዮ አቶ አበበ፣ ሳያውቁት የተቀዳ ነው። ይህ አይነቱም ንግግርን በሚስጠር የመቅዳት የፓፓራዚ ተግባር በጣም አሳዛኝ ከመሆኑም በተጨማሪ ነውርም ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ግርማ ካሳ

አዲሱ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው፣ ለገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ የሰላምና የእርቅ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል። “ኢሕአዴግ እኛን እንደ ጠላት እና ሽብርተኛ ማየቱን ማቆም አለበት። እኛም ደግሞ ኢሕአዴግን እንደ አውሬ ማየት ማቆም አለብን። ከጥላቻ ፖለቲካ በመውጣት ችግሮቻችንን በሰላም መፍታት መማር አለብን” ሲሉ ነበር፣ ለአገር በሚጠቅሙ በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ከኢሕአዴግ ጋር ለመስራት፣ ያሉትን ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታት አንድነት ፍላጎት እንዳለው የገለጹት።

ሙሉውን አስነብበኝ …

የእነ “… ወይም ሞት” ፖለቲካ

ያሬድ ኃይለማርያም ከብራስልስ
ከ1960ዎቹ የተማሪዎች ንቅናቄ ጀምሮ የአገራችንን ፖለቲካ የተጠናወተው የ”…. ወይም ሞት” አስተሳሰብ ከአስርት አመታት በኋላም አለቅ ብሎን ዛሬም እኔ ከምደግፈው ፓርቲ ወይም የፖለቲካ ቡድን ወይም አስተሳሰብ ውጭ ያለው መንገድ ወይም አማራጭ ሁሉ ገደልና ሞት ነው ብለው የሚያስቡ ፖለቲከኞችና ዓጃቢዎችን ቁጥር በብዙ እጥፍ አባዝቶ ቀጥሏል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

(ሊያነቡት የሚገባ ሰፊ ትንታኔ)

 በኃይሌ ላሬቦ

የኔልሶን ማንደላን ለቅሶና ቀብር ሳይ በጣም ተገረምሁ ብቻ ሳይሆን እፍሪቃዊ መሆኑ ራሱ አኰራኝ። ከዚህም ተነሥቼ፣ታሪክን ወደኋላ መለስ ብዬ በኅሊናዬ መስተዋት ቃኝቼ ሳበቃ፣ ጊዜው እንደዛሬ ሁኖ ቢያመችለት ኖሮ፣ እንደሳቸው ሊለቀስ የሚገባ ሰው በአፍሪቃ ምድር ከዚህ በፊት ታይቶ አይታወቅምን ብዬ ራሴን በራሴ ደጋግሜ ጠየቅሁ። ማንዴላ የሚደነቁት፣ በቀለሙ በመጀነንና፥ በዘመናዊ መሣርያው በመተማመን፣ በበላይነት ረግጬው ልግዛው ብሎ፣ ለብዙ ዘመናት በሥልጣን ላይ ሁኖ ያሠቃይ የነበረውን ጨቋኙን የነጮች ግዛት ከነሥርዐቱ አሸንፈው፣ ለሀገራቸው ጥቊር ሕዝብ የድል ዋንጫ አጐናፅፈው፣ ነፃነቱንና ክብሩን ስለመለሱለት ነው። ግፈኞቹን የድሮ ጠላቶቻቸውንም እንደመበቀል ፈንታ በፍቅር ያዟቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጥቂት አሳቦች በሞገደኛው ተክሌ ወሥርጉተ ሥላሴ ጽሑፎች ላይ (ክፍል-፩-)

ዲ/ን ኒቆዲሞስ ዕርቅ ይሁን

ሥርጉተ ሥላሴ የተባሉ ጸሐፊ በተለያዩ ጊዜያት የሚጽፏቸውን በአብዛኛው ታሪካዊ የሆኑ፣ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርስ አዘል፣ በኃይለኛው አገራዊ/ኢትዮጵያዊ ዘዬ፣ ትውፊትና ባህል የተጫነው የሚመስለውንና፤ እንዲሁም ምክርና ትችት ዘመም የኾኑ፣ እንዲያም ሲል “የኢትዮጵያዊነት ወኔና ስሜት” በእጅጉ ጎልቶ የወጣበትንና ያየለበትን መጣጥፎቻቸውን ለማንበብ ዕድሉ ገጥሞኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

መስፍን ወልደማርያም (ፕ/ር)

ሰሞኑን እንደአዲስ ሆኖ የሚወራው ስለጥርነፋ ነው፤ ጥርነፋ ከዲያብሎስ ፋብሪካ የወጣ የክፋትና የጭቆና መሣሪያ ነው፤ ሰዎችን በመጨቆንና በማሰቃየት፣ ምቾትና እንቅልፍ በማሳጣት፣ ፍርሃትንና ስጋትን በማሰራጨት ሕዝብን ለጥ-ጸጥ አድርጎ ለመግዛት የሚፈልጉ ጠርናፊዎች፣ አምባ-ገነኖች፣ ጨቋኞች፣ አፋኞች፣ ዘራፊዎች፣ ወሮበሎች፣ ምድራዊም ሆነ ሰማያዊ ሕግ የማይገዛቸው፣ አምላካቸው አድርገው የሚያገለግሏቸው ሎሌዎችን በሆዳቸው ገዝተው የሚያሰልፉ ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ …