ኑሮ በአዲስ አበባ

ነፃነት ዘለቀ (ከአዲስ አበባ)
ትናንት ሲያቀብጠኝ ከአንድ ጓደኛየ ሞባይል እነዚያ አይሲስ የሚባሉ ጉግማንጉጎች እነዚያን 21 ክርስቲያን የግብፅ ዜጎች በሊቢያ አንድ የባሕር ዳርቻ ላይ አንገታቸውን ሲቀሉ የሚያሣይ ቪዲዮ አየሁ – እስከመጨረሻው መዝለቅ አልቻልኩምና ግን ዋናው ባራኪ በግራ እጁ የያዘውን ጩቤ ወደ እኛ ወደተመልካቾቹ ዘርግቶ እያስፈራራ ሲዝት አጠፋሁት።

ነፃነት ዘለቀ (ከአዲስ አበባ)
ትናንት ሲያቀብጠኝ ከአንድ ጓደኛየ ሞባይል እነዚያ አይሲስ የሚባሉ ጉግማንጉጎች እነዚያን 21 ክርስቲያን የግብፅ ዜጎች በሊቢያ አንድ የባሕር ዳርቻ ላይ አንገታቸውን ሲቀሉ የሚያሣይ ቪዲዮ አየሁ – እስከመጨረሻው መዝለቅ አልቻልኩምና ግን ዋናው ባራኪ በግራ እጁ የያዘውን ጩቤ ወደ እኛ ወደተመልካቾቹ ዘርግቶ እያስፈራራ ሲዝት አጠፋሁት።
የማለዳ ወግ
ነቢዩ ሲራክ
ወንድም ራያ ጀማል የ5 ወንድ እና የ3 ሴት ልጆች ጎልማሳ አባት ነው። ወደ ሳውዲ የመጣው ድህነት፣ የኑሮ ውድነት፣ የፖለቲካው ሙቀት አልያም የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ገፍቶት አይደለም። ሳውዲ የመጣው፣ የእስልምና እምነቱ በሚያዘው መሰረት በህይወት ዘመኑ የሚጠበቅበትን ለማድረግ ከብቶቹን ሽጦ የሃጅ ጸሎት ለማድረግ ነበር …
“አሁን ገና ኢትዮጵያዊ ሆንኩ!” ዶ/ር ዳኛቸው
Ethiopia Zare (ማክሰኞ መጋቢ 8 ቀን 2007 ዓ.ም. March 17, 2015)፡- በውጪ /፤‹›አገር ለሠላሳ ዓመታት የቆዩትና ለሰባት ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት የሰሩት ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ከስራ መባረራቸውን ገለጹ። ዶ/ር ዳኛቸው፣ ኢትዮጵያዊ ማለት መብቱ የሚረገጥ ማለት በመሆኑ፣ አሁን ገና ኢትዮጵያዊ ሆንኩ በማለት በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ገልጸዋል።
ዩሱፍ ያሲን (ኦስሎ)
በቅርቡ ኤርትርያን የጎበኙት የኢሳት ጋዜጠኞች ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፍወርቂ ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ ብዞዎቻችንን እያነጋገረ ነው። እንደገና የሁለቱ አገራትና ሕዝቦች ዝምድናና የወደፊቱ እጣ ተጣማሪነት በተለያዩ ሚዲያዎች መነጋገሪያ አጀንዳ እየሆነ መጥቷል። ልክ እንደ በፊቱ እያወዛገበ ነው ማለቱ ሳይሻል አይቀረም።
ዶ/ር አበባ ፈቃደ
ጥንታዊት ቅድስት ኢትዮጵያ አገራችንን ከገጠማት ብሄራዊ ቀውስና ካንዣበበባት ሕልውናዋን ፈታኝ አደጋ ለመታደግ ምን መደረግ አለበት የሚለው ጥያቄ መመለስ ከመቸውም ግዜ በበለጠ የወቅቱ ዋናና አጣዳፊ ጉዳይ መሆኑ ለሚመለከተንና ለምንቆረቆር ሁሉ አጠያያቂ አይደለም።

Ethiopia Zare (ዓርብ መጋቢት 4 ቀን 2007፣ March 13, 2015)፡- የመጀመሪያው ዙር የምርጫ ክርክር እንዲያደርጉ የተመረጡት አቶ በረከት ስሞኦን ከምርጫ ክርክሩ እራሳቸውን ማግለላቸው ተረጋገጠ። አቶ በረከት ለዚህ የሰጡት ምክንያት እንደሌለ ታውቋል።

Ethiopia Zare (ዓርብ መጋቢት 4 ቀን 2007፣ March 13, 2015)፡- የአይሲስ ዋንኛ አራማጅ ነው የተባለው ጆን (መሐመድ ኤምዋዚ) የቅርብ ጓደኛው እንግሊዛዊው ዓሊ አድሮስ ኢትዮጵያ ውስጥ በእስር እንደሚገኝ በተለያዩ የብዙኀን ዜና ማሰራጫዎች እየተናፈሰ ይገኛል። መሐመድ ኤምወዚ በማለት ራሱን ሰይሞ የቆየው ይህ ግለሰብ፣ የኩዌት ዝርያ የሆነ እንግሊዛዊ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን፤ አንገት ቀልቶ ገዳዩ በሎንደን ከተማ ኮሌጅ ውስጥ ይማር እንደነበር ታውቋል።

Ethiopia Zare (ዓርብ መጋቢት 4 ቀን 2007፣ March 13, 2015)፡- የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም፤ ብሪቱ ጃለታ የተባለች የ14 ዓመት ታዳጊ ወጣት የተሸለመችውን 20 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር ለበጎ አድራጎት ሥራ አዋለች በማለት ዓይን ያወጣ ውሸት እንደዋሹ በጋዜጠኛ አበበ ገላው መረጋገጡን ተከትሎ፤ ከ10 በላይ የሆኑ የማኅበራዊ ድረገጽ ባለቤቶች አንድ ላይ በመሆን ሚንስትሩ ከዚህ አይነት ውሸት እንዲቆጠቡ ማሳሰቢያ እንዲደርሳቸው አድርገዋል።

Ethiopia Zare (ዓርብ መጋቢት 4 ቀን 2007፣ March 13, 2015)፡- የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፤ ብሪቱ ጃለታ የተባለች የ14 ዓመት ታዳጊ ወጣት የተሸለመችውን 20 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር ለበጎ አድራጎት ሥራ አዋለች በማለት ዓይን ያወጣ ውሸት እንደዋሹ በጋዜጠኛ አበበ ገላው መረጋገጡን ተከትሎ፤ ከ10 በላይ የሆኑ የማኅበራዊ ድረገጽ ባለቤቶች አንድ ላይ በመሆን ሚንስትሩ ከዚህ አይነት ውሸት እንዲቆጠቡ ማሳሰቢያ እንዲደርሳቸው አድርገዋል።
<
Ethiopia Zare (ዓርብ መጋቢት 4 ቀን 2007፣ March 13, 2015)፡- የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ አብዲ መሐመድ በዋሽንግተን ዲሲ ለደረሰባቸው ተቃውሞ የሰጡት መልስ ከባለሥልጣን አንደበት የማይወጣ አስነዋሪ እንደነበረ ተገለጸ። ሥርዓቱ እንዲህ አይነት ሰዎችን ያቀፈ ነው ያሉት ታዛቢዎች ከተቃዋሚዎች ጋር የተደረገውን አንባጓሮ በቪድዮ በመቅረጽ ለህዝብ አቅርበዋል።
ይሄይስ አእምሮ (ከአዲስ አበባ)
ይህ ኢትዮጵያዊነት በስንት ረገድ ቁጭት ውስጥ እየከተተን እንደሆነ እናንተም አስቡት። በእጅጉ የሚገርም ሁኔታ ውስጥ እየከተተን ነው ያለ። በዚህች ሌሊት ሰባት ሰዓት ገደማ ያነበብኩት ጽሑፍ እንኳን ክፉኛ ዕንቅልፍ ነስቶኝ ከሌሊቱ አሥር ሰዓት ላይ ከሚጥመው መኝታየ ተነስቼ ይሄውና መዶግዶግ ያዝኩ – ለነገሩ ሳለ ወያኔ ምን የሚጥም መኝታ አለና!
አዲስ አበባ የሚገኝ ቤታቸውን ለፌስቱላ ሆስፒታል ለግሰዋል
Ethiopia Zare ማክሰኞ መጋቢት 01 ቀን 2007 ዓም March 10, 2015፦ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ፤ የኢትዮጵያን የባንክ አገልግሎት ስርአት ካሳደጉት ሰዎች አንዱ የሆኑትና በመድህን ድርጅት፤ በሲቪል አቪየሽንና በተለያየ ሀላፊነት ሀገራውንና ህዝባቸውን ያገለገሉት አቶ ተፈራ ደገፌ (ዶክተር)፤ የቀብር ስነ-ስርአት ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 1 ቀን፤ 2007 ዓ.ም. በቫንኩቨር ካናዳ ተፈጸመ።
ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ)
እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ የሚጠራው ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሀሰት እና የሸፍጥ የተውኔት መድረክ የተንጸባረቀበትን ህገመንግስት አርቅቆ እ.ኤ.አ ታህሳስ 8/1994 በማጽደቅ በኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ ጫነ። በህገ መንግስቱ ሰነድ የመጀመሪያ መግቢያ መንደርደሪያ ላይ እንዲህ የሚል ጽሁፍ ሰፍሮ ይገኛል፣ “እኛ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች …
የኢሳት መዝሙር ተበረከተ
Ethiopia Zare: ቅዳሜ የካቲት 11 ቀን 2007 ዓ.ም. (ፌብሪዋሪ 28 ቀን 2015 ዓ.ም.) በስዊድን የተደረገው የኢሳት መርጃ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ተገለጸ። ዝግጅቱ ከቀኑ ሰባት ሰዓት (13፡ 00) የተጀመረ ሲሆን፣ የዕለቱን ዝግጅት የመሩት ወ/ሮ መቅደስ ወርቁ የስዊድን የኢሳት ድጋፍ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና አቶ በረከት ንጉሱ ነበሩ።
ክንፉ አሰፋ
አሁን የምጽፈውን በደንብ አንብቡ። መቶ በመቶ እውነተኛ ነው። እውነተኛ ኩሸት።
“ያልተገባ ነገር እየፃፍን ልጆችን አንጉዳ። ሕጻናት የምታስቡት ፕሮጀክት የተቀደሰ ነው። እንደሚሳካም እምነቴ የፀና ነው። አሁን ዋናው ጉዳይ ህጻናት ህልማቸውን እንድናሳካ የማበረታታትና የመደገፍ ነው። ሕጻናት ሆይ 20 ሚሊዮን ዶላር ባትይዙም ቢሮዬ ብቅ በሉ!”
Ethiopia Zare (እሁድ የካቲት 29 ቀን 2007 ዓ.ም. March 08, 2015፦) የቀድሞ የኢትዮጵ ብሄራዊ ባንክ ገዢ የነበሩትና፤ በኢትዮጵያ ለባንክ ስራ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱት፤ አቶ ተፈራ ደግፌ፤ ባለፈው አርብ ማርች 6 ቀን፤ 2015 ዓ.ም. ቫንኩቨር በሚገኝ ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው፤ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
“ገንዘቡ በኮሚኒስት ሀገር የሚታተም ከሆነ ስራየን እለቃለሁ” አቶ ተፈራ ደገፌ ለደርግ ሰዎች
Ethiopia Zare አርብ የካቲት 27 ቀን 2007 ዓም March 06, 2015፦ የኢትዮጵያ ባንክ ገዥ የነብሩትና ለርዥም ዓመታት ሃገራቸውንና ህዝባቸውን በሙያቸው ያገለገሉት አቶ ተፈራ ደገፌ በቫንኩቨር-ካናዳ በህክምና ሲርዱ ከቆዩ ብኋላ በ88 ዓምታችው ዛሬ አርብ ማርች 6 ቀን 2015 ዓም ከጠዋቱ 5፡30am ማርፋቸው ታወቀ።
ዳንኤል አበራ
1. መቅድም: ይህ የአድዋ 119ኛ አመት መታሰቢያ እኛና አድዋ በተሰኘ ርእሰ ጉዳይ ላይ ያተኩራል። ድርሰቱ ስድስት ንኡሳን ክፍሎች አሉት። ሁላችንም በጦርነቱ በድሉም ወቅት ስላልነበርን የተጻፈ አንብበን ከምናውቀው አመሳክረን ነው ጽሁፉ የተዘጋጀው። የተጻፈ አንብበን ላልኩት የጳውሎስ ኞኞን ምክር ከልቤ አድርጌ ነው።
ጴጥሮስ አሸናፊ
እለተ ሰኞ ፌብሯሪ 17 ቀን 2014 ዓ/ም ማለዳ
አንድ ንብረቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነና በበረራ ቁጥር ET 702 የተመዘገበ ቦይንግ 767 የመንገደኞች ማመላለሻ አውሮፕላን በጣሊያን በኩል አድርጎ ወደ ስዊዘርላንድ የአየር ክልል ይገባል። የስዊዝ የአየር ክልል ጠባቂዎችም በጧት የመጣባቸውን ጥቁር እንግዳ ማንህ ወዴት ነህ ማለት። የአውሮፕላኑን የበረራ ሂደት ሙሉ በሙሉ በብቸኝነት የተቆጣጠረው ረዳት አብራሪ ሃይለመድህን አበራም ቆፍጠን ብሎ እኔ ነኝ ! ማለት። አንተ ማን? ምነው ምን ፈልገህ ነው ወደ አየር ክልላችን የገባኸው? የአየር ክልል ተቆጣጣሪዎቹ ቀጣይ ጥያቄ ነበር።
ሊቁ እጅጉ
በዓለም ታሪክ ውስጥ አምባገነን ገዥዎች ለሥልጣናቸው የሚሰጡት ሕጋዊ ሽፋን ከሁሉም በላይ አዋቂዎች፣ ለሕዝብ ተቆርቋሪዎች፣ የድሆችን እንባ ጠባቂና … ወዘተ ስለሆነም እራሳቸውን ብቸኛ አማራጭ አድርገው ይሰይማሉ። አንዳንድ በአመጽ ሥልጣን ላይ የወጡ ቡድኖችና መሪዎች ብዙ ግዛቶችን በጭካኔ አጥቅተው ከያዙ በኋላ ሰው መሆናቸውን እስከመካድም ደርሰው ነበር። ሆኖም ግን መጨረሻቸው እነሱ እንዳሰቡት ሳይሆን ውጤታቸው ታላቅ ውርደትና በሕዝብ ዘንድ መጠላትን፣ ውድቀትንና የሕዝብ እልቂትን ከማስከተልና የታሪክ አተላ ከመሆን አላመለጡም፣ አላለፉም።
ይሄይስ አእምሮ (ከኢትዮጵያ)
ዛሬ እሁድ የካቲት 22 ቀን 2007 ዓ.ም. የወያኔ 40ኛ ዓመት ክብረ በዓል መዘምዘሚያ በወያኔው አባል በቱጃሩ አላሙዲን የሚሌኒየም አዳራሽ ውስጥ እየተከበረ ነው። ዘፈንና ደስታ አለቅጥ ሲበዛ የሚያስከትለውን ምልኪያዊ ሀዘን የተረዱ አይመስሉም።
ክንፉ አሰፋ
“አንድም ቀን ስቀን አናውቅም!” አሉ ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም። ይህን በሚሉ ጊዜ እፊታቸው ላይ ፈገግታ ይታይ ነበር -ምሬቱ እንዳለ ሆኖ። ኢሳያስ አፈወርቂ ሲስቁ አይተናቸው አናውቅም። ግን ኮስተር ብለው የሚናገሩት ነገር እኛኑ አያሳቀን ነው። “ካሳ ይገባናል! ካሳ ስጡን” ሲሉ አሳቁን።
‹‹የ‹አዲስ ነገር› ጋዜጣን ሳስብ ኩራት ይሰማኛል››
‹‹በዘመኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ጋዜጠኝነትን ለመስራት ምን ያህል ተጠቀምንባቸው?!››
ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ
‹‹በ ‹አዲስ ጉዳይ›› መጽሔታችን ብዙ እንሰራለን ብለን በአጭሩ ተቀጭተናል››
‹‹በሙያችን ለሀገራችን አበርክቶት መስጠት ይጠበቅብናል፡፡››
ጋዜጠኛ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ
‹‹በሀገራችን የነጻነት ጥያቄ ፊት ለፊት ፍጥጥ ብሎ መጥቷል››
‹‹…ብዙዎቻችን የምንሻው ነጻነት የሚመጣው ጥቂቶች በሚከፍሉት ዋጋ ብቻ አይደለም››
ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ
ባሳለፍነው ረቡዕ ጥር 18 ቀን 2007 ዓ.ም ከፍቃዱ ማህተመወርቅ እና ሳሙኤል አበበ ጋር ወደ ቂሊንጦ እስር ቤት አብርተን ነበር፡፡ ፍቃዱም ወደዞን አንድ፣ ሳሙኤል ወደዞን እኔ ደግሞ ወደዞን ሶስት ለጥየቃ ገባን፡፡ ከታሰሩ አንድ ዓመት ሊሞላቸው ያሉትን ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ እና አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ፣ እንዲሁም የዞን 9 ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀን አስጠራኋቸው፡፡
አብርሃ ደስታን መጠየቅ ከጀርባ ሰው ያስከትላል
‹‹ዕድሜያችንን መቼ ሰራንበት፣ ልደት ማክበርም ያስፈራኛል፡፡ እንኳን ተወለድክ ላላችሁኝ በሙሉ ከልብ አመሰግናለሁ››
ጦማሪ እና ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉ
ከዛሬ ከሰዓት በኋላ ከወዳጄ አቤል አለማየሁ ጋር ወደ ቂሊንጦ እስር ቤት አምርተን ነበር፡፡ አካሄዳችን በዞን ሁለት የሚገኙትን አብርሃ ደስታን፣ ጦማሪ እና ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉንና ጦማሪ አጥናፍ ብርሃንን ለመጠየቅ ነው፡፡
አስፋ ጫቦ
1. ዶርዜ ዴሬ (አገር) የዶርዜ ማርያም የለችም። ያሉ ሁለቱ አድባራት የጥንቱ ፣የጥዋቱ የዶርዜ ጊዮርጊስና የዶርዜ ሚካኤል ናቸው።ሚካኤል ከጨንቻ በልጅ እግር ከ30-45 ደቂቃ ቢወስድ ነው። በምን ሊከድ ኖሯል!? ልጅ ሆኜ አንድ ሁለቴ ሚካኤልን ለማንገስ መሔዴ ትዝ ይለኞል።ማንገሱ ሳይሆን የዶርዜ ዘፈኑ መስለኝ የሚጠራኝ።ታላቅ የሙዚቃ ትዕይንትና ቲያትር አደራሽ እንደመግባት ይሰማኛል። አዳራሹ ሜዳው መሆኑ ነው። ዶርዜ ማርያም ብትኖርም እንኳ ዶርዜ ማራሞ ነው የምንለው። ታሪካዊዋንን የዜናሁ ለጋለ ፤የአባ ባሕርይ መጽሐፍ መፍለቂያ የብርብር ማርያም ደብረ ነች። ያችን እኛ ቢርቢራ ማራሞ እንላለን። ዚኒ ከማሁ፤ኤሌ ጋብሬሌ፤ዶርዜ ሚካሌ ነው የምንለው።
ኣስራት ኣብርሃ
በዘመነ አፄ ልብነድንግል ጦርነት በመጥፋቱ ንጉሱ ጦርነት አውርድ ተብሎ በየቤተክርስቲያኑ ፀሎት እንዲደረግ ትዕዛዝ አውርዶ ነበር እየተባለ በአፈ ታሪከ ይነገርለታል፤ 24 ዓመት የሞላው የህወሀት/ኢህአዴግ ስርዓትም ጦርነት አውርድ፣ መዓት አውርድ እያለ እንደሚገኝ ከደርጊቶቹ ሁሉ መረዳት የሚቻል ነው።
ተክለሚካኤል አበበ
በርእሱ እንዳትሸወዱ
1- ይሄ የኔ ርእስ አይደለም፡፡ የዛሬ 15 ቀን ተክለጊዮርጊስ በተባሉ (የብእር ይሁን የምር ስም አይታወቅም) ሰው የተጻፈን ስም አጥፊ ጽሁፍ የለጠፈው ኢትዮፍሪደም ድረገጽ ወይም የጽሁፉ ደራሲ፤ የአንባቢን ትኩረት ለመሳብ ይመስላል፤ የተጠቀሙበት የመግቢያ ሀይለቃል እንጂ፡፡ ጸሀፊው ለድረገጾች ያላቸውን ቅርበት በመጠቀም፤ እንዲሁም ወያኔ የተባለው ቃል ከተጠራ አንባቢ አያጣራም፤ ወይም ግለሰቡ ላይ ዘሎ ይረባረብበታል በሚልና፤ የስም ማጥፋቱ ሰለባ የሆኑት ሰው፤ ጨዋና እንዲህ ያለው እንከሰላንቲያ ውስጥ ገብተው አይመልሱም በሚል እሳቤ ይመስላል፤ ይሄንን ርእስ ተጠቅመዋል፡፡
አዜብ ጌታቸው
የአርቲስት ሜሮን ጌትነት “አትሂድ” የተሰኘው ግጥም ሌላውንም አርቲስት እያነቃቃ ነው። ግጥሙ መቼም የአመቱ ምርጥ ግጥም ነው ብል አካበድሽ! አልያም የጾታ አድልዎ ነው እንደማልባል ተስፋ አደርጋለሁ። ብባልም ግድ የለኝም። ለለውጥ ያህል “የሴት ትምክህተኝነት” ይጀመር መሰለኝ።
‹‹ለአሸባሪ ፓርቲ ቢሮ ብታከራዩ ተጠያቂነቱን ትወስዳላችሁ›› የቂ/ክ/ከ ወረዳ 8 ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ
ነገረ ኢትዮጵያ
የቤት ደላሎች ለሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ እንዳያከራዩ ከቀበሌ ባለስልጣናት ጥብቅ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ተደራጅተው በመስራት ላይ የሚገኙት ደላሎች የቂ/ክ/ከ ወረዳ 8 ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢኒያም ከበደ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ አሸባሪ ፓርቲ ነው፡፡ ለአሸባሪ ፓርቲ ቢሮ ብታከራዩ ተጠያቂነቱን ራሳችሁ ትወስዳላችሁ›› ብለው ጥብቅ ማስጠንቀቂያ እንደሰጧቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
አንድነት -መግለጫ
ጥር 21/2007 ዓ.ም በኢትዮጵያ ታሪክ የምርጫ ቦርድ የሚባል ተቋም ያለበትን ደረጃ ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ በዚህ ደረጃ እንዲዋራድ ከጀርባ ሆኖ አመራር የሚሰጠው ገዢ ፓርቲም ሆነ መንግሰት በዚያው ልክ የሚገባቸውን የተዋረደ ደረጃ የያዙበት ዕለት ነው ብለን እናምናለን፡፡ አንድነት ፓርቲ አንድም የህግ ጥሰት ሳይፈፅም የሚያደርጋቸውን ሁሉ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብና በሀገሪቱ ህግ እየፈፀመ ባለበት ሁኔታ በህግ ሽፋን የገዢው ፓርቲ ልሳን የሆነው ፋና ሬዲዮ፣ የመንግሰት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ከምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር የከፈቱት ዘመቻ የመጨረሻ የሆነውን አንድም ህጋዊ መሰረት የሌለውን ህገወጥ ውሳኔ በአንድነት ፓርቲ እና አባላት ላይ አሰተላልፈዋል፡፡
አንድነት – መግለጫ
ጥር 21/2007 ዓ.ም በኢትዮጵያ ታሪክ የምርጫ ቦርድ የሚባል ተቋም ያለበትን ደረጃ ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ በዚህ ደረጃ እንዲዋራድ ከጀርባ ሆኖ አመራር የሚሰጠው ገዢ ፓርቲም ሆነ መንግሰት በዚያው ልክ የሚገባቸውን የተዋረደ ደረጃ የያዙበት ዕለት ነው ብለን እናምናለን። አንድነት ፓርቲ አንድም የህግ ጥሰት ሳይፈፅም የሚያደርጋቸውን ሁሉ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብና በሀገሪቱ ህግ እየፈፀመ ባለበት ሁኔታ በህግ ሽፋን የገዢው ፓርቲ ልሳን የሆነው ፋና ሬዲዮ፣ የመንግሰት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ከምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር የከፈቱት ዘመቻ የመጨረሻ የሆነውን አንድም ህጋዊ መሰረት የሌለውን ህገወጥ ውሳኔ በአንድነት ፓርቲ እና አባላት ላይ አሰተላልፈዋል።
ገዢው ፓርቲና መንግሰት በምርጫ ቦርድ በኩል እንዲነበብ ያደረጉት የፖለቲካ ውሳኔ በኢትዮጵያ ሀገራችን የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ከወረቀት አልፎ በተግባር እንዳይታይ ግብዓት መሬቱን ፈፅመዋል። በዚህ ፀያፍ ተግባር ከፊትም ሆነ ከጀርባ ሆነው የተሳተፉ ግለሰቦችም ሆኖ ተቋማት በታሪክ ተገቢው የውርደት ቦታ እንደሚይዙ እምነታችን ነው። ይህ ህገወጥ አካሄድ ህጋዊ መሰመር እንዲከተል የበኩላቸሁን ድርሻ የተወጣችሁ የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች በሀገር ውሰጥም ሆነ በውጭ የምትገኙ ሁሉ በተለይ በገዢው ፓርቲ እኩይ ሴራ በሀስት ተወንጅላችሁ በወህኒ ቤት ለምትማቅቁ ታጋዮች ታሪካችሁ በወርቅ ቀለም ተፅፎዋል። በቀጣይም ያለምንም መዘናጋት እና ተሰፋ መቁረጥ በምናደርገው ሰላማዊ ትግል በሀገራችን ኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ሰርዓት ትንሳኤ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለንም።
የምርጫ ቦርድ ተብዬው ተቋም በህገወጥ መንገድ ለሆዳቸው ባደሩ ጥቂት አንድነት ፓርቲ አባላት እና በአንድነት አባልነት በማይታወቁ የገዢው ፓርቲ ጥርቅሞች ለተደረገ ጠቅላላ ጉባዔ ዕውቅና ሰጥቻለሁ ማለቱን በምንም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን፣ የአንድነት ፓርቲ አባላት ያነገብነው የነፃነት መንፈስ በምርጫ ቦርድ በሚሰጥ ሰርተፊኬትና ዕውቅና ማዕቀፍ ውስጥ የሚገኝ ስለአልሆነ ለነፃነት የምናደርገውን እልህ አስጨራሽ ትግል የምንቀጥል ሲሆን፤ በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የአንድነት መዋቅሮች እና የአንድነት አባላት ለዚህ ህገወጥ ቡድን በግልፅ እውቅና እንዲነሱ እንጠይቃለን። ፓርቲያችን በመጨረሻ ሰዓት እንኳን ተፈትነው ለወደቁ ተቋማት እድል ለመስጠት ወደ ፍርድ ቤት ለመሄድ ወሰኖ እንቅሰቃሴ በማድረግ ላይ ቢሆንም፤ በዛሬው ዕለት ጥር 22/ 2007 ከቀኑ ሰባት ሰዓት ጀምሮ የፓርቲያቸን ፅ/ቤት በፖሊስ ተወሮ የፓርቲው ንብረት ያለምን ህጋው ርክክብ በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጎዋል። በአሰተዳደር የተሰጠን ውሳኔ በፍርድ ቤት የማሰለወጥ ህጋዊ ሰርዓት እንዳለ ቢታወቅም ህገወጥ አስተዳደራዊ ውሳኔን በፖሊስ ወረራ ለማሰፈፀም የተሄደበት መስመር ገዢው ፓርቲና መንግሰት አሁንም ከጫካ አሰተሳሰብ ያለመውጣቸውን እና የአውራ ፓርቲ ፍልስፍናቸውን በማናለብኝነት ለመተግበር መቁረጣቸውን የሚያሳይ ነው። በዚህ ህገወጥ ድርጊት ተጠያቂው ትእዛዙን ያስተላለፈው ክፍል መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል። ሰለሆነም በሀገር ውስጥ እና በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን፣የሰብዓዊ መብት ተማጋች ድርጅቶች፣ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ እንዲሁም በኢትዮጵያ ሀገራችን የመድበለ ፓርቲ ሰርዓት እንዲጎለብት ፍላጎት ያለችሁ ሁሉ ይህን እኩይ ተግባር በማውገዝ ተጨባጭ እርምጃ እንድትወሰዱ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ድል የህዝብ ነው!!!
ጥር 22/ 2007 ዓ.ም.
አንድነት – መግለጫ
ጥር 21/2007 ዓ.ም በኢትዮጵያ ታሪክ የምርጫ ቦርድ የሚባል ተቋም ያለበትን ደረጃ ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ በዚህ ደረጃ እንዲዋራድ ከጀርባ ሆኖ አመራር የሚሰጠው ገዢ ፓርቲም ሆነ መንግሰት በዚያው ልክ የሚገባቸውን የተዋረደ ደረጃ የያዙበት ዕለት ነው ብለን እናምናለን። አንድነት ፓርቲ አንድም የህግ ጥሰት ሳይፈፅም የሚያደርጋቸውን ሁሉ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብና በሀገሪቱ ህግ እየፈፀመ ባለበት ሁኔታ በህግ ሽፋን የገዢው ፓርቲ ልሳን የሆነው ፋና ሬዲዮ፣ የመንግሰት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ከምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር የከፈቱት ዘመቻ የመጨረሻ የሆነውን አንድም ህጋዊ መሰረት የሌለውን ህገወጥ ውሳኔ በአንድነት ፓርቲ እና አባላት ላይ አሰተላልፈዋል።
ገዢው ፓርቲና መንግሰት በምርጫ ቦርድ በኩል እንዲነበብ ያደረጉት የፖለቲካ ውሳኔ በኢትዮጵያ ሀገራችን የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ከወረቀት አልፎ በተግባር እንዳይታይ ግብዓት መሬቱን ፈፅመዋል። በዚህ ፀያፍ ተግባር ከፊትም ሆነ ከጀርባ ሆነው የተሳተፉ ግለሰቦችም ሆኖ ተቋማት በታሪክ ተገቢው የውርደት ቦታ እንደሚይዙ እምነታችን ነው። ይህ ህገወጥ አካሄድ ህጋዊ መሰመር እንዲከተል የበኩላቸሁን ድርሻ የተወጣችሁ የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች በሀገር ውሰጥም ሆነ በውጭ የምትገኙ ሁሉ በተለይ በገዢው ፓርቲ እኩይ ሴራ በሀስት ተወንጅላችሁ በወህኒ ቤት ለምትማቅቁ ታጋዮች ታሪካችሁ በወርቅ ቀለም ተፅፎዋል። በቀጣይም ያለምንም መዘናጋት እና ተሰፋ መቁረጥ በምናደርገው ሰላማዊ ትግል በሀገራችን ኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ሰርዓት ትንሳኤ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለንም።
የምርጫ ቦርድ ተብዬው ተቋም በህገወጥ መንገድ ለሆዳቸው ባደሩ ጥቂት አንድነት ፓርቲ አባላት እና በአንድነት አባልነት በማይታወቁ የገዢው ፓርቲ ጥርቅሞች ለተደረገ ጠቅላላ ጉባዔ ዕውቅና ሰጥቻለሁ ማለቱን በምንም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን፣ የአንድነት ፓርቲ አባላት ያነገብነው የነፃነት መንፈስ በምርጫ ቦርድ በሚሰጥ ሰርተፊኬትና ዕውቅና ማዕቀፍ ውስጥ የሚገኝ ስለአልሆነ ለነፃነት የምናደርገውን እልህ አስጨራሽ ትግል የምንቀጥል ሲሆን፤ በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የአንድነት መዋቅሮች እና የአንድነት አባላት ለዚህ ህገወጥ ቡድን በግልፅ እውቅና እንዲነሱ እንጠይቃለን። ፓርቲያችን በመጨረሻ ሰዓት እንኳን ተፈትነው ለወደቁ ተቋማት እድል ለመስጠት ወደ ፍርድ ቤት ለመሄድ ወሰኖ እንቅሰቃሴ በማድረግ ላይ ቢሆንም፤ በዛሬው ዕለት ጥር 22/ 2007 ከቀኑ ሰባት ሰዓት ጀምሮ የፓርቲያቸን ፅ/ቤት በፖሊስ ተወሮ የፓርቲው ንብረት ያለምን ህጋው ርክክብ በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጎዋል። በአሰተዳደር የተሰጠን ውሳኔ በፍርድ ቤት የማሰለወጥ ህጋዊ ሰርዓት እንዳለ ቢታወቅም ህገወጥ አስተዳደራዊ ውሳኔን በፖሊስ ወረራ ለማሰፈፀም የተሄደበት መስመር ገዢው ፓርቲና መንግሰት አሁንም ከጫካ አሰተሳሰብ ያለመውጣቸውን እና የአውራ ፓርቲ ፍልስፍናቸውን በማናለብኝነት ለመተግበር መቁረጣቸውን የሚያሳይ ነው። በዚህ ህገወጥ ድርጊት ተጠያቂው ትእዛዙን ያስተላለፈው ክፍል መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል። ሰለሆነም በሀገር ውስጥ እና በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን፣የሰብዓዊ መብት ተማጋች ድርጅቶች፣ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ እንዲሁም በኢትዮጵያ ሀገራችን የመድበለ ፓርቲ ሰርዓት እንዲጎለብት ፍላጎት ያለችሁ ሁሉ ይህን እኩይ ተግባር በማውገዝ ተጨባጭ እርምጃ እንድትወሰዱ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ድል የህዝብ ነው!!!
ጥር 22/ 2007 ዓ.ም.
ጋዜጠኛ ዮሐንስ ደሳለኝ – (ጀርመን)
Ethiopia Zare ቅዳሜ ጥር 10 ቀን 2007 ዓም January 17, 2015:- ባሳለፍንው ሰኞ በፍራንክፈርት የሚገኙ ኢትዩጽያዊያን በአሁኑ ሰዓት በአገራቸው የሚደረገውን የመብት ጥሰት ለተለያዬ ተቁማት ለማሳወቅ ሁለት ሰዓት የፈጀ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ። መነሻውን ከዋናው የባቡር ጣቢያ አንድ ጣቢያ (station)አልፉ በሚገኘው ታውንስላገን አካባቢ ከዋናው ደች ባንክ አጠገብ ያደረገው ሰልፍ፣ ረፈዱ 11፡00am ላይ ተጀምሮ የእንግሊዝ ኤምባሲን አካሎ ምሳ ሰዓት ላይ (1፡00pm) ፍራንክፈርት የሚገኘው ኢትዬጽያ ቆንጽላ ጽ|ቤት በመገኘት በተለመደው ኢትዬጵያዊ ጨዋነት ተጠናቁል።
ጋዜጠኛ ዮሐንስ ደሳለኝ – (ጀርመን)
Ethiopia Zare ቅዳሜ ጥር 10 ቀን 2007 ዓም January 17,2015:– ባሳለፍንው ሰኞ በፍራንክፈርት የሚገኙ ኢትዩጽያዊያን በአሁኑ ሰዓት በአገራቸው የሚደረገውን የመብት ጥሰት ለተለያዬ ተቁማት ለማሳወቅ ሁለት ሰዓት የፈጀ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ። መነሻውን ከዋናው የባቡር ጣቢያ አንድ ጣቢያ (station)አልፉ በሚገኘው ታውንስላገን አካባቢ ከዋናው ደች ባንክ አጠገብ ያደረገው ሰልፍ፣ ረፈዱ 11፡00am ላይ ተጀምሮ የእንግሊዝ ኤምባሲን አካሎ ምሳ ሰዓት ላይ (1፡00pm) ፍራንክፈርት የሚገኘው ኢትዬጽያ ቆንጽላ ጽ|ቤት በመገኘት በተለመደው ኢትዬጵያዊ ጨዋነት ተጠናቁል።
ጋዜጠኛና መምህርት ርእዮት ዓለሙ- (ከቃሊቲ እስር ቤት)
በግል የህትመት ዉጤቶች አማካኝነት በሀገሬ ዉስጥ የምመለከታቸዉን ችግሮች ለህዝብ ማቅረብና እንደዜጋም መፍትሔ ይሆናሉ ብዬ የማስባቸዉን ሀሳቦች መጠቆም ከጀመርኩ አምስት አመታት አለፉ፡፡ የመጀመሪያ ፅሑፌን ያዘጋጀሁት ” “ስህተቶችን” ለማረም የተፈፀሙ ስህተቶችና የስህተት ማረሚያ እርምጃዎች” በሚል ርዕስ እንደነበረ አስታዉሳለሁ፡፡ በዚህም ፅሑፍ የፕሬስ፣ የፖለቲካፓርቲዎች ምዝገባና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የተመለከቱ አዋጆች የወጡበት ምክንያትና እንደሀገር የሚያሳድሩትን ተፅእኖ ለመዳሰስ ብሎም ኢህአዴግ ከስህተቶቹ እንዲታረም ለመምከር ሞክሬያለሁ፡፡
ዳዊት ከበደ ወየሳ
የመከላከያ ሰራዊት በትግራይ እና አማራ ተዋጊዎች መካከል ሰፈረ (ከዚያስ?)
በሰሜን ጎንደር, አርማጭሆ አውራጃ ልዩ ስሙ “ገ’ጨው” በተባለው ስፍራ የመከላከያ ሰራዊት ከትላንት ጀምሮ እንዲሰፍር ተደርጓል፡፡ ማዶ እና ማዶ ሆነው እየተዋጉ ባሉት የትግራይ ወታደሮች እና በአማራ ህዝብ መካከል መከላከያ ሰራዊት ከሰፈረ በኋላ ጦርነቱ አሁን ለጊዜው ጋብ ብሏል፡፡ የቀድሞ የህወሃት ወታደሮችን ሁመራ ላይ በማስፈር አካባቢውን ለራሱ ያደረገው ህወሃት – አሁን ደግሞ በአርማጭሆ መስፋፋት በመጀመሩ ነው – በአካባቢው ከሚኖረው የአማራ ህዝብ ጋር ግጭቱ የተቀሰቀሰው፡፡
በእያንዳንዱ ሀገር ያለ ገዥ መንግሥት የየራሱ መረጃ ለህዝቡና ለዓለም-ዓቀፍ ማኅበረሰብ የመስጠት ባህሪ፣ ልምድና ባህል አለው፡፡ ወሳኝ የሆኑ ሀገራዊ፣ መንግሥታዊና ኅብረተሰባዊ መረጃዎች በሚመለከታቸው የመንግሥታት የመረጃ ሰጪ አካላት በኩል መረጃው ለሚያስፈልገው ሁሉ መድረስ እንደሚያሻ እሙን ነው – በተለይ በዘመነ ግሎባላይዜሽን እና በ21ኛው ክ/ዘመን! ኢትዮጵያን በተለያዩ ጊዜያት ያስተዳደሩ መንግሥታት ‹‹እየመራነው ነው፤ እያስተዳደርነው እንገኛለን›› ለሚሉት ሕዝብ መረጃን የሚሰጡበት የየራሳቸው አካሄድ ነበራቸው፡፡ በአሁን ወቅት ሀገራችንን እያስተዳደረ የሚገኘው ገዥ ፓርቲ ኢህአዴግ ነውና በእሱ ላይ ማተኮር ተገቢ ነው፡፡
የቤት ኣከራየ የጋሽ ጣሰው ኣገር እየመጣሁ ነው፡፡ ወደ ኣዲስ ኣበባ እየመጣሁ ነው፡፡እናቶች ኣባቶች ልጆች ኦርጅናሎች ሰልቫጆች! እኔ ሳልመጣ ውጊያውን እንዳትጀምሩት ኣደራ፡፡ ኣጭርና ጣፋጭ ይሁን እንጂ በማንኛውም ትግል ላይ ለመሳተፍ ዝገጁ ነኝ፡፡የጥይት መከላከያ ቆብ ሹራብና ሱሪ እንዲሁም ፈንጅ የማይበትነው ጫማ ከተሰጠኝ ኣንድ ሻለቃ እመራለሁ፡፡ኣነሰ ከተባለ ኣንዲት ኮረብታ እቆጣጠራለሁ፡፡ በጦር ምህንድስና ላይ እሳተፋለሁ፡፡ ባሩድ ኣገነፋለሁ፡፡ የታንክ ጎማ እነፋለሁ፡፡በሰላሙ ቀን ለሞባይል፤ በቀውጢው ቀን ለሽጉጥ ማስቀመጫ የሚሆን ሰገባ እሰፋለሁ፡፡
ተክለሚካኤል አበበ (ቶሮንቶ – ካናዳ)
1- የዚህ ጽሁፍ ዓላማ፤ የአንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ መሪዎች፤ አሁድ ድሴምበር 28 ቀን ከሰአት በኋላ 2pm ላይ፤ በውጭ ለምንገኝ ኢትዮጵያውያን ያዘጋጁትን የስልክ ውይይት ማስተዋወቅ ነው። ይሁን እንጂ ማስታወቂያውን እርቃኑን ባሰፍረው፤ አይማርክም በሚል፤ አንዳንድ ተያያዥ ነገሮችን ላለብሰው ፈቀድኩ። መለመላውን ከሚቀርብ የስልክ ጉባኤ ማስታወቂያ ይልቅ፤ ትንሽ ውዝግብ የለበሰ ማስታወቂያ ቀልብ ይስባል፡፡
∙‹‹ለማን አቤት ይባላል?›› ሀብታሙ አያሌው
ዛሬ ታህሳስ 15 ቀን 2007 ዓ.ም በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮችን ጨምሮ 10ሩም ተከሳሾች በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ 19ኛው ወንጀል ምድብ ችሎት ቀርበው ነበር፡፡ የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች የሆኑት አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና አቶ አብርሃ ደስታ እንዲሁም አንደኛ ተከሳሽን ጨምሮ ስድስት ተከሳሾች ተሟልተው ፍርድ ቤት ተገኝተዋል፡፡
ከአንድነት ፓርቲ
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ምርጫ ቦርድ ነፃና ገለልተኛ እንዳልሆነ የሚገነዘብ ቢሆንም ባለፈው ታህሳስ 12/04/2007 ዓ.ም የተካሄደው የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ በሀገራችን የምርጫ ቦርድ አለ ወይ?! እንዲል አድርጎታል። የታህሳሱ 12/04/2007 ዓ.ም የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ ነፃና ገልልተኛ አልነበረም ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የምርጫ ህጉን ተከተሎ ያልተካሄደ ሌላው ይቅርና የራሱ የምርጫ ቦርድ መመሪያን እንኳን ያልተከተለ ከመሆኑ አንፃር ተካሄዷል ብለን አናምንም። እንዲህ ዓይነቱ ድምዳሜ እንድንደርስ ያደረጉን ምክንያቶች ብዙ ቢሆኑም በዋናነት የሚከተሉት ነጥቦች ከግምት ውስጥ አስገብተናል።
ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ መግለጫ
በባህርዳር ከተማ ለዘመናት የእምነት ቦታ ሆኖ ለአምልኮ አገልግሎት ሲውል የነበረ የህዝብ ይዞታ በማያውቁትና ባልመከሩበት ሁኔታ ባለሀብት እንዲያለማው በከተማው መስተዳድር ተሰጥቷል መባሉን ተከትሎ የከተማዋ ነዋሪዎች ባዶ እጃቸውን ሆነው በሰላማዊ መንገድ ባሰሙት የተቃውሞ ድምጽ መንግስት የህዝቡን ጥያቄ ለማፈን በወሰደው ዘግናኝና አሰቃቂ በጥይት የታገዘ የኃይል እርምጃ እስካሁን የአምስት ንፁኃን ዜጎች ህይወት ተቀጥፏል፡፡ ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑ አዛውንት እማሆይንና አካል ጉዳተኛ ጨምሮ በርካቶችን በማቁሰል የአካል ማጉደል ደርሶባቸዋል፡፡
ዮሃንስ ደሳለኝ (በርሊን -ጀርመኒ)
Ethiopia Zare ሐሙስ ኅዳር 24 ቀን 2007 ዓም December 4, 2014 ከደች ባንክ ብድር ለመጠየቅ ረቡዕ ለታ ከጀርመኗ ቻንስለር መርከል ጋር ውይይት ለማድረግ ወደ ስፍራው ያቀኑት ጠ/ሚር ኃይለማርያም ደሳለኝን በመቃወም በርካታ ኢትዮጵያዊያን በቦታው በመገኘት ተቃውሟቸውን ማስማታቸው ታወቀ፡፡
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም :- በነጻነት ለሀገሬ
ባለፈው ሳምንት በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን/ት ቤተሰቦች ከዘመዶቻቸው እና ከጓደኞቻቸው ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ታሪክ በመጥፎ ገጽታው ሲታወስ የሚኖረውን እ.ኤ.አ ኖቬምበር 14/1974 በኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸመውን የእልቂት ሰለባዎች ለማስታወስ በአንድ ላይ ተሰባስበው የጸሎት ስርዓት አድርገዋል፡፡ በዚያ የጥላቻ ዕለት የወታደራዊው አምባገነን ስብስብ ተራ ስብሰባ በማድረግ 60 ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኖችን፣ የመንግስት ሰራተኞችን፣ አርበኞች ከፍተኛ ማዕረግ ያላቸውን ወታደራዊ መኮንኖችን፣ የተማሩ ወታደራዊ ባለስልጣናትን እና የግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ስላሴን ልዩ የጥበቃ አባላት ያካተተ የግድያ እልቂት ለመፈጸም ተራ እና አስደንጋጭ ውሳኔን አሳለፈ፡፡
እንዲያው ዘው ተብሎ አይገባ ነገር! ” ቤቶች!” ተብሎ” ደጆች!” ተብሎ “ይግቡ/ግባ!” ተብሎ ነው እንጅ። ጠፍቼ ስነበትኩ።ከርምኩ ሳይሻል አይቀርም።”ለመሆኑ አስፋ ጫቦ የት ገባ” ብለው በአደባባይ ከጠየቁት ወሰንሰገድ ገ/ኪዳንንና እንዳለ ጌታ ከበደን ሌሎች እዚህ በስም ያልጠቀስኳቸዉን ሁሉ አመስግናለሁ።ለክፉም ለደጉም ጠያቂ አያሳጣችህ! እኔማ ሌላ ምን እላለሁ ! የቤት ክህነት አባቶች እንደሚሉት ሱባዔ ገብቼ ነበር።ከዚያው ከቤተክህነት ተውሸ፤(ነበርኩብትምና) “ዘኀሀለፈ ሥርየት ወለዘይመጽዕ እቅበት” እላለሁ። ነጠላ ትርጉሙ “ያለፈው ይሰረዝ ይደለዝ ለመጭው መታቀብን/መቆጠብን ስጠኝ/ስጠን!” እንደማለት ነው።በምወደው መጽሐፍ Gone with Wind ስካርሌት ኦሐራ (Scarlet O’Hara) Tomorrow is Another Day ትላለች።። “ነገም ሌላ ቀን ነዉ” ብሎታል ተርጏሚው ነብይ መኮንን።እኔም እንድያ እንዳልኩ ይቆጠርልኝ!
በላይ ማናዬ
‹‹መብቴን አሳልፌ አልሰጥም፤ የትም ብሆን ስለመብቴና ሀገሬ ያገባኛል፡፡ እዚህ ከሚጠይቁኝ ሰዎች ጋር የፈለኩትን ማውራት እችላለሁ፡፡ እናንተ ከፈለጋችሁ በር ላይ መልሷቸው እንጂ እኔ ጋር ከመጡ በኋላ ስለሀገሬ ከእነሱ ጋር መነጋገር መብቴ ነው፡፡ አዎ የትም ቦታ ብሆን፣ መቼም ቢሆን ስለ ሀገሬ ያገባኛል!››
ከፕሮ/ር አለማየሁ ገብረማርያም – ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ለአራት አስርት ዓመታት እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ የሚጠራው እና በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ ከህዝብ ፍላጎት ውጭ በኃይል በስልጣን ወንበር ላይ ተፈናጥጦ የሚገኘው የወሮበላ የማፊያ ቡድን ኢትዮጵያን ለማጥፋት ቀጣይነት ያለው እና የማያቋርጥ የፖለቲካ፣ የማህበራዊ እና የባህል ጦርነት በመክፈት ዕቅድ አውጥቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡
ግርማ ሰይፉ ማሩ
መረጃ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ጠቃሚ ነው ብሎ መንገር ለቀባሪ እንደማርዳት ነው፡፡ የተሟላ መረጃ የሰውን ልጅ ሙሉ ያደርገዋል፡፡ መረጃን አጣሞ ማቅረብ ደግሞ የሰውን ልጅ ውሳኔ ለማጣመም ካልሆነ በስተቀር ግቡ ምን ሊሆን እንደሚችል አይገባኝም፡፡ በሰሞኑ ሰው በላው የኢትዮጵያ ፖለቲካ በጥርሱም በጥፍሩም ዘመቻ የጀመረው እኔ ላይ ነው፡፡ ዓላማው ግልፅ ነው፡፡ በነፃነት የማሰብ መብቴን ለድርድር እንዳቀርብ ነው፡፡ ለነፃነቴ ያለኝን ዋጋ የማያውቁ ሰዎችን ይህንን ለማድረግ ቢሞክር ካላቸው የመረጃ እጥረት ወይም ማወቅ ባለመፈለጋቸው ነው፡፡
ደራሲ:- ኤርምያስ ለገሰ
ቅኝት:- መስፍን ማሞ ተሰማ
መንደርደሪያ
በድሮ ዘመን የኖሩ እንስሳት እንዲህ ዘመሩ።
የእንግሊዝ አራዊት፤
የአየርላንድ አራዊት፤
የየሀገሩ ሁሉ አራዊት፤
ተሳተፉ የደስታዬን ምንጩን፤
ስለመጪው ብሩህ ዘመን!
ይዘገያል ወይ ይፈጥናል፤
ያ! ቀን ግን ይመጣል፤
ጨቋኙ ሰው ይገረሰሳል! . . . ዘምረው ዝም አላሉም። ዘምረው አመፁ። አብዮት አፈነዱ፤ የእንስሳት አብዮት። በሚኖሩበት ሀገር – በእነሱ አጠራር፤ የእርሻ ጣቢያ – ለዘመናት በጭቆና ቀንበር ረግጦ ሲገዛቸውና ሲመዘብራቸው በኖረው የሰው ዘር ገዢያቸውና ግብረ አበሮቹ ላይ ሆ! ብለው ተነሱ። ቀንበር በቃን። ባርነት በቃን። ብዝበዛ በቃን። … ነፃነት እንጂ።