የመለስ “ትሩፋቶች” (ባለቤት አልባ ከተማ)

ደራሲ:- ኤርምያስ ለገሰ
ቅኝት:- መስፍን ማሞ ተሰማ

መንደርደሪያ
በድሮ ዘመን የኖሩ እንስሳት እንዲህ ዘመሩ።
የእንግሊዝ አራዊት፤
የአየርላንድ አራዊት፤
የየሀገሩ ሁሉ አራዊት፤
ተሳተፉ የደስታዬን ምንጩን፤
ስለመጪው ብሩህ ዘመን!
ይዘገያል ወይ ይፈጥናል፤
ያ! ቀን ግን ይመጣል፤
ጨቋኙ ሰው ይገረሰሳል! . . . ዘምረው ዝም አላሉም። ዘምረው አመፁ። አብዮት አፈነዱ፤ የእንስሳት አብዮት። በሚኖሩበት ሀገር – በእነሱ አጠራር፤ የእርሻ ጣቢያ – ለዘመናት በጭቆና ቀንበር ረግጦ ሲገዛቸውና ሲመዘብራቸው በኖረው የሰው ዘር ገዢያቸውና ግብረ አበሮቹ ላይ ሆ! ብለው ተነሱ። ቀንበር በቃን። ባርነት በቃን። ብዝበዛ በቃን። … ነፃነት እንጂ። 

ሙሉውን አስነብበኝ …