የ“ምርጫ” ወግ እና የውይይት ማስታወቂያ
ተክለሚካኤል አበበ (ቶሮንቶ – ካናዳ)
1- የዚህ ጽሁፍ ዓላማ፤ የአንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ መሪዎች፤ አሁድ ድሴምበር 28 ቀን ከሰአት በኋላ 2pm ላይ፤ በውጭ ለምንገኝ ኢትዮጵያውያን ያዘጋጁትን የስልክ ውይይት ማስተዋወቅ ነው። ይሁን እንጂ ማስታወቂያውን እርቃኑን ባሰፍረው፤ አይማርክም በሚል፤ አንዳንድ ተያያዥ ነገሮችን ላለብሰው ፈቀድኩ። መለመላውን ከሚቀርብ የስልክ ጉባኤ ማስታወቂያ ይልቅ፤ ትንሽ ውዝግብ የለበሰ ማስታወቂያ ቀልብ ይስባል፡፡