ደራሲ፣ ገጣሚና ባለቅኔ ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው) አረፈ
“… እንደ ኪሩብ ሁሉ – ክንፍ አካል ቢኖረኝ፣መች እጠበስ ነበር – በዚህ ዓለም በቃኝ፣
ስላጣሁ ብቻ ነው – መሸሻ መድረሻ፣
በዚች በሽት ዓለም – የኖርኩ እንደውሻ …፣”
“… በሥጋዬ ብቻ ውጪ – ሀገር እስካለሁ፣
እወቁልኝ በርግጥ – አልኖርኩም ሞቻለሁ! …
ኃይሉ (ገሞራው)
“… እንደ ኪሩብ ሁሉ – ክንፍ አካል ቢኖረኝ፣ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም – በነጻነት ለሀገሬ)
እ.ኤ.አ በ1984 የተከሰተው የኢትዮጵያ ታላቁ ረኃብ ሲታወስ (ክፍል 2)
ባለፈው ሳምንት ባቀረብኩት ትችቴ (እ.ኤ.አ በ1984 የተከሰተው የኢትዮጵያ ታላቁ ረኃብ ሲታወስ፡ ክፍል1)፣ ላለፉት በርካታ ዓመታት ረኃብን በማስመልከት ሳቀርባቸው በነበሩት ትችቶች የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ እና አሁን በህይወት የሌለው መሪው መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ ከ1991 ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት ረኃብ የለም በማለት ሙልጭ አድርገው በመካድ ሲያደርጉት የነበረውን ተራ ቅጥፈት በማጋለጥ በተጨባጭ መረጃዎች ላይ በመመስረት ስሞግት የቆየሁባቸውን ዋና ዋና ጭብጦች በማካተት ክለሳ ማድረጌ ይታወሳል፡፡
ፍኖተ ነፃነት
በዛሬው ዕለት ወደ ቂሊንጦ የተዛወሩትን የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ወደ ስፍራው በማምራት አቶ ሀብታሙ አያሌውን፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺንና ሌሎችን የፖለቲካ እስረኞችን ማነጋገራቸውን ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡
ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም- በነጻነት ለሀገሬ)
እውነታው ከልብወለድ በላይ እንግዳ ነገር ነው!
እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 7/2014 “ድፍረት፡ የፊልም ጠለፋ በኢትዮጵያ ” በሚል ርዕስ ባወጣሁት ትችት ድፍረት በሚለው ፊልም ላይ የኢትዮጵያ መሪ ተዋንያን ሆና በሰራችው የውርጃ ድርጊት ላይ የነበረኝን ቁጣ ገልጨ ነበር፡፡ በአበራሽ በቀለ እውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተሰራው ያ ፊልም በአሁኑ ጊዜ ጠለፋ እየተባለ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለአቅመ አዳም ባልደረሱ ልጃገረዶች ላይ የሚፈጸመውን እውነተኛ ኢሰብአዊ እና ኋላቀር ልምድ በማጋላጥ እየተሰራ ያለውን የትወና ታሪክ ይተርክልናል፡፡
ነቢዩ ሲራክ
በገዥው ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ክንፍ የደ.ህ.ዴ.ን ፖለቲካ ፖርቲ አባላት ወዳጆቸ ባደረጉልኝ ግብዣ መሰረት በደ.ህ.ዴ.ንን 22ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ተገኝቸ ነበር ። እንደ ዛሬው የደ.ህ.ዴ.ን በዓል ፍሪዳ ተጥሎ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ድርጅቶች የልደት በዓላቸውን ሲያከብሩ እግር ጥሎኝ ስገኝ በምባረርበት የጅዳ ቆንስል ግቢ በሚገኘው የኮሚኒቲ አዳራሽ ተገኝቸም ኬክ እስኪቆረስና ሙዚቃው እስኪጀመር ያለውን ፕሮግራም ተከታትያለሁ። በልደት ፕሮግራሙ በቀረበው የድርጅቱ የትግልጉዞ “የስምጥ ሸለቆው ታጋዮች ” የሚል ስያሜ የተሰጠውን የደቡብ የነጻነት ታጋዮች ከህወሃት ጋር ተቀዳጅተው በቅድመ ደርግ ያደረጉትን ትግል ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር የሰማሁት።
ጋዜጠኛ አንተነህ መርዕድ
በዙህ ጉዳይ ላይ ለመጻፍ በሁለት ምክንያቶች ከራሴ ጋር ብዙ ታግያለሁ። መጀመርያ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም አይደለም ለራሳቸው፤ ለሌላም የሚተርፍ አንደበት አላቸውና ራሳቸው መልስ ይስጡ በማለት ሲሆን ሁለተኛው ምክንያቴ ደግሞ ትልልቅ አገራዊ ጉዳይ እያለ በዚህ ጠባብ ነገር መጠመድ ለማን ይበጃል በሚል ነበር።በሁለቱም ትክክል አልነበርሁም።
ከአቢይ አፈወርቅ
– ደማቅ ውይይትም አድርገዋል።
ዕውቁ የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና ምሁር ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም ባለፈው እሁድ ኦክቶበር 26 ቀን በሲድኒ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጋር ደማቅ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ልዩ የምስጋና ስጦታም ተበርክቶላቸዋል። በዕለቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያዊያን ተገኝተው አዳራሹ በመሙላቱ የተወሰኑ ታዳሚዎች ከፊትና ከኋላ ባሉ በረንዳዎች ላይ ተደርድረው ፕሮግራሙን ለመከታተል መገደዳቸው ይህ ሪፖርተር ተመልክቷል።
ደማቅ ውይይትም አድርገዋል
አቢይ አፈወርቅ
ዕውቁ የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና ምሁር ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ባለፈው እሁድ ኦክቶበር 26 ቀን በሲድኒ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጋር ደማቅ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ልዩ የምስጋና ስጦታም ተበርክቶላቸዋል። በዕለቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያዊያን ተገኝተው አዳራሹ በመሙላቱ የተወሰኑ ታዳሚዎች ከፊትና ከኋላ ባሉ በረንዳዎች ላይ ተደርድረው ፕሮግራሙን ለመከታተል መገደዳቸው ይህ ሪፖርተር ተመልክቷል።
በአቤ ቶኪቻው
ወዳጃችን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፤ ከተከሰሰባቸው ክሶች በአንደኛው ሶስት አመት ጽኑ እስራት ተፈረደበት።
በሌሎቹ ክሶች ምን እንደሚፈረድበት ቀጥሎ የምናየው ቢሆንም ተሜ እና ሌሎች ወንጀለኛ ያልሆኑ ሰዎችን… (ይሄን ግዜ አንዳድ አብዝተው የዋህ የሆኑ ሰዎች እና አብዝተው የኢህአዴግ ዝምድናን የተጋመዱ ግለሰቦች ፍርድ ቤት ወንጀለኛ ያላቸውን ሰዎች ከወንጀል ነጻ ናቸው ማለት ተገቢ ነውን… እያሉ ሊሞግቱን ጣታቸውን ሲያሞጠሙጡ ይታየኛል…
ነቢዩ ሲራክ
ወንድሜ ሆይ ማምሻውን ” … አሁን የማወራው ስለ ብትቱው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሳይሆን ስለ ሆደ ባሻዋ እና ርህሩዋ እናታችን ነው! ” በማለት ስለ እናትህ ጭንቀት የጻፍከውን ሳነበው ፣ ስለ እናትህ ልቤ በሃዘን ተጎዳ ፣ ስለ ጀግኖች ሳይሆን ስለ ጀግና እናቶች መከራ አነባሁ ፣ እንደ ሰው በእልህ ሰውነቴ ጋለ ፣ ተናደድኩ …በቁጭት ግን አልቆዘምኩም …!
ነቢዩ ሲራክ
ወንድሜ ሆይ ማምሻውን ”… አሁን የማወራው ስለ ብትቱው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሳይሆን ስለ ሆደ ባሻዋ እና ርህሩዋ እናታችን ነው!” በማለት ስለ እናትህ ጭንቀት የጻፍከውን ሳነበው፣ ስለ እናትህ ልቤ በሃዘን ተጎዳ፣ ስለ ጀግኖች ሳይሆን ስለ ጀግና እናቶች መከራ አነባሁ፣ እንደ ሰው በእልህ ሰውነቴ ጋለ፣ ተናደድኩ … በቁጭት ግን አልቆዘምኩም …!
ስለ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
በዓለማየሁ ገላጋይ
የጉብኝት ጉዞው በማለት ተጀምሯል፤ ያለንበት መኪና ወደ አዲስ አበባ ደቡብ አፍንጫውን ቀስሯል፤ በመካከላችን ጸጥታ ረብቧል… ዕጣ ፈንታህ በዘመን እጅ ነው ዘመን ሲፈቅድ የዘመንህ ‹‹ ጉዱ ካሳ›› ትሆናለህ፤ ስውር እስር ቤት ትገባለህ፤ እንደ እብድ ትታያለህ፤ በመገለል ዘብጥያ ባመደመጥ ዋርድያ ስር ትሆናለህ፡፡ እውነትህ እንደቅራቅንቦ ይቆጠራል ይናቃል…
… ወይም ….
በጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ
‹‹መለስ በህይወት ቢኖር ራሱ የሚቃወማቸው ይመስለኛል››
‹‹አቶ ኃይለማርያም፣ የራሱን አመለካከት አሳድራለሁ ያለ ቀን፤ ወደ እነአንዱአለም ጎራ ይቀላቀላል፤ መለስ ቢኖርም ባይኖርም!!!››
አቶ ሀብታሙ አያሌው /የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ/
አሁን በእስር ላይ ማዕከላዊ ሆኖ እና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በእግር ህመም እየተሰቃየ የሚገኘው የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ፤ አቶ ሀብታሙ አያሌው ከመታሰሩ 10 ቀናት ቀደም ብሎ ለ‹‹ቀዳሚ ገጽ›› ጋዜጣ እኔ እና ባልደረባዬ አናንያ ሶሪ በ‹‹መለስ ራዕይ›› ዙሪያ ሰፋ ያለ ቃለ ምልልስ አድርገንለት ነበር፡፡ ቃለ-ምልልሱም በጋዜጣው ላይ ተስተናግዷል፡፡ ቃለ-ምልልሱን ማንበብ ላልቻላችሁ ወገኖቼ ታነቡት ዘንድ የተወሰነውን እንዲህ አቅርቤዋለሁ፡-
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ/ወያኔ እያለ በሚጠራው እና ትግሉን በሰለጠነ መልኩበጠረጴዛውይይት እናየሀሳብ የበላይነት ሳይሆን ከጫካ በመግባት ብረትን የኃያልነት ዋስትናበማድረግ በንጹሀንዜጎች ደም ላይ ተረማምዶየጫካ ባህሪውን ከነግሳንግሱ እንዳለ ተሸክሞከህዝቦች ፈቃድ ውጭ በኃይልበህዝቦች ጫንቃ ላይ ተፈናጥጦ በሚገኘውየሽፍታ ቡድን የበላይነትየሚመራው በኢትዮጵያ ያለው ገዥአካል በአፍሪካ ወደር የማይገኝለት አምባገነን እናአረመኒያዊስብስብ እንደሆነ በተደጋጋሚ ስገልጽቆይቻለሁ። ዴሞክራሲ በህዝብ ለህዝብ የተቋቋመ ህዝባዊአስተዳደርከሆነ የወሮበላ አገዛዝ መንግስትደግሞ በዘራፊዎች እና በወሮበላዎች ለዘራፊዎች እናለወሮበላዎች የተቋቋመ የማፊያቡድን ነው።
ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም
በግዞትም ቤት አደባባይ ታስሮ ሳለ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደኤርምያስ መጣ፡– ሂድ ለኢትዮጵያዊውም ለአቤሜሌክ እንዲህ በለው፤ — የእሥራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤- እነሆ ለበጎነት ሳይሆን ለክፋት ቃሌን በዚህች ከተማ ላይ አመጣለሁ፤ በዚያም ቀን በፊትህ ይፈጸማል፤ በዚያ ቀን አድንሃለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ በምትፈራቸው ሰዎች እጅ አልሰጥህም፤ ፈጽሜ አድንሃለሁ፤ ነፍስህም እንደምርኮ ትሆንልሃለች እንጂ በሰይፍ አትወድቅም፤ በበእኔ ታምነሃልና ይላል እግዚአብሔር፡፡ ትንቢተ ኤርምያስ 39/15-18
ኑዛዜ ኤርምያስን አነበብሁ፤ጉድ ነው! አንድ የማውቀውን ነገር አረጋግጥሁ፤ ብዙ የማላውቃቸው ነገሮችን አወቅሁ፤ የማውቀው ነገር ሂሳብ የተማረ ሰው ምን ጊዜም ጭፍን ሎሌ መሆን የማይችል መሆኑን ነው፤ሂሳብ የተማረውን ሰው ለጭፍን ሎሌነት የሚቀጥረው ሰው ግን አንጎሉ የፈረጠ ነው።
በጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ
‹‹ተመስገን፣ ጥሩ ታጋይ እና ሰው ሆኖ ከእስር ይወጣል››
‹‹ተመስገን፣ የህዝብ ልጅ ነው፤ ነገም ከነገወዲያም የህዝብ ልጆች ይፈጠራሉ››
እስክንድር ነጋ ‹‹ስለተመስገን ደሳለኝ ሃሳቤን አስተላልፍልኝ›› ካለኝ የተወሰደ
ከትናንት በስትያ፣ ሰኞ ዕለት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የአንድነት ፓርቲ ጸሐፊ የሆነውን አቶ አንዷለም አራጌን በ2007 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ላገኛቸው ችዬ ነበር – ለአቤል አለማየሁ ጋር። ባለፈው ሳምንት የ‹‹ባንዲራ ቀን›› በተከበረበት ዕለት ቃሊቲ ከወዳጄ እዩኤል ፍስሐ ጋር ሄጅ እነስክንድርን መጠየቅ ሳንችል ተመልሰን ነበር።
የምሰራበትን የሚዲያ ተቋም ወክዬ በተለያዩ የፕሬስ መግለጫዎች ላይ እካፈል ነበር፡፡ በዚህም አጋጣሚ ከተለያዩ ነባርና አዳዲስ የሙያ አጋሮቼ ጋር የመተዋወቅ ዕድሉ አጋጥሞኛል፡፡ ከጋዜጠኛ ሚልዮን ሹርቤ (የማራኪ መጽሔት ባለቤት) ጋር ግን እንደሌሎቹ ተቀራርቤ ባልግባባውም በተገናኘኝ ቁጥር የአንገት ሠላምታ ከመስጠት አልቦዘንኩም፡፡
‹‹ለእስረኛ ማልቀስ/ ማዘን ሳይሆን የእስረኛውን መንገድ መከተል ነው››
‹‹የእስክንድር ሃሳብ ትክክል ነው›› ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ከነገረን የተወሰደ
‹‹ፍትሕ›› ጋዜጣ ላይ በተስተናገዱ ሶስት ጽሑፎች ተከስሶ ለሁለት ዓመት ያህል የክስ ሂደቱ ሲታይ ቆይቶ በትናንትናው ዕለት በከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት ‹‹ጥፋተኛ›› ከተባለ በኋላ ከትናንት ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበረውን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ዛሬ ጥዋት ላይ ከእስከዳር አለሙ፣ ይድነቃቸው ከበደ እና ስለሺ ሀጎስ ጋር ሄደን ጠይቀነው ነበር፡፡
ክንፉ አሰፋ
የፈረንሳዩ አንባገነን ገዥ የነበረው ናፖሊዮን ቦናፓርት በአንድ ወቅት ስለ ነጻ ፕሬስ ሲናገር “ከአንድ ሺህ ሻምላዎች ይልቅ አራት ጋዜጦች የበለጠ መፈራት አለባቸው።” ነበር ያለው።
አቤ ቶክቻው
ትላንት ለንደን ነበርኩ። እኔ ካለሁበት ማንችስተር ከተማ ለንደን ለመሄድ ወደ ስምንት መቶ ሰው ጭኖ በሰዓት እስከ ሁለት መቶ ኪሎ ሜትር ድረስ በሚወነጨፈው ቨርጂን ባቡር የፈጀውን ይፍጅ ብዬ ከተሳፈርኩ ሁለት ሰአት ከ ሃያ ደቂቃ ብቻ ነው የሚወስድብኝ።
ግርማ ሰይፉ (የፓርላማ አባል)
የወታደራዊ እና/ወይም አንባገነናዊ መንግሰታት መገላጫ በመኖሪያ አካባባያቸው ይገለፅ እንደሆን በሚል፡፡ ከዚህ ቀጥዬ የማነሳቸውን የወታደር መኖሪያዎች እና የቤተ መንግሰት ሁኔታን ይመለከታል፡፡ ዘወትር እነዚህን ግቢዎች ባየኋቸው ቁጥር የሚመጣብኝ አሳብም ስለሆነ ነው፡፡ ለነገሩ የዚህ ዓይነት አስተሳሰብ አዲስ አይደለም፡፡ የኢኮኖሚክስ ትምህርት መጀመሪያ የሆነው አንድ በላተኛ፣ አንድ አቅራቢ፣ አንድ ገበያ የሆነው ከአንድ ሰው ጀምሮ፣ ወደ ቤተሰብ እና ሀገር የሚያድገው ሞዴል ተፅህኖሞ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገሮችን ከቀላል በመነሳት ወደ ውስብሰብ ደረጃ ለማጥናት ይረዳል የሚል እምነትም አለኝ፡፡
አንተነህ መርዕድ
ላለፉት አርባ አመታት በአምባገነኖች መዳፍና በካድሬዎች ቁጥጥር ስር ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘላቂ ነፃነት እስካላገኘ ድረስ የስርዓት መቀየር ብቻ ለነፃነቱ ዋስትና አልሆነውም፤ አይሆነውምም። አምባገነኖች ጉልበቱን ከመበዝበዝ፣ ከማሰርና ከመግደል አልፎ ስብዕናውን በመግፈፍ የጎደፈ አስተሳሰባቸውንና ፍልስፍናቸውን በዜጎች አዕምሮ በመሙላት አገዛዛቸውን ዘላቂ ያደረጉ ይመስላቸዋል። የሚገርመው ደርግ ሆነ ወያኔ የህዝብ መሰረት ሲያጡ፣ ዙርያ ገባው ገደል ሲሆንባቸው፤ በካድሬዎቻቸው ህዝቡን ሰብስቦ በፕሮፓጋንዳቸው ማጥመቅ ልትበጠስ የደረሰችውን በስልጣን ዘመን የሚያራዝምላቸው ይመስላቸዋል።
በልጅግ ዓሊ
ባለፈው ዓመት ሃገራችንንም በሚመለከት አስደሳችም፣ አስከፊም፣ አስደናቂም፣ አናዳጅም ተግባሮች ተፈፅመዋል። አሮጌው ዓመት ለአዲሱ ዓመት ቦታውን ሲለቅ ፈጣሪ አምላክ አዲሱ ዓመት የሠላም፣ የፍቅር፣ የመግባቢያና ችግሮቻችንን ሁሉ የምንፈታበት ዓመት ይሁን ማለታችን አልቀረም። ግን የዚህ ምኞታችን ፍፃሜ ከቅርብነቱ ሩቅነቱ በክፍፍላችን ምክንያት የጎላ ነው።
በቅድሚያ መጽሓፉን ጊዜ ሰጥተህ በማንበብ አስደማሚ ምልከታ በመስጠትህ ከልብ አመሰግናለሁ ። የተጻፈበትም አንዱ አላማ ይህ ስለሆነ። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በእይታህ ላይ እነዚህ ጉድለት ይታይባቸዋል ብለህ ያነሳኸው እና የወደፊት ግምቶችህ ላይ የተወሰነ አስተያየት ለመስጠት የሚጋብዙ ስለሆነ ትንሽ ማለት ፈለኩ። በዚህ አጋጣሚ ሌሎች በመጵሀፉ ይዘት ላይ ዝርዝር ግምገማ ላደረጉ ሰዎች ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። ለእያንዳንዱ አስተያየት መስጠት ከጊዜ አኳያ በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ የማልዘልቅበትን መንገድ ልጀምረው አልፈለኩም።
ተመስገን ደሳለኝ
በዚህ ተጠየቅ ጨርፈን የምንመለከተው በኮሙኑዮኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ የነበረውና ዛሬ በስደት የሚገኘው የአቶ ኤርሚያስ ለገሰን “የመለስ ትሩፋቶች፣ ባለቤት አልባ ከተማ” የተሰኘው መጽሐፍን ነው፡፡ የመድብሉ ጻሐፊ ኤርሚያስን በግል አላውቀውም፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በአካል ያየሁት አቶ በረከት ስምዖን እርሱን እና ሽመልስ ከማልን ምክትሎቹ አድርጐ በሚኒስቴር ዲኤታ ማዕረግ መሾሙን በግዮን ሆቴል ለጋዜጠኞች ይፋ ባደረገበት ዝግጅት ላይ ነው።
ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
መግቢያ
ለአዘማሪ ሙያ ተስማሚ የግብር መግለጫ መሆን ያለበት የቱ ነው? አዘማሪ ወይስ አርቲስት? በሚል በአቶ ዓለም ነጻነት ሬድዮ የቀረበው ውይይት ለዚህች ጦማር መነሻ ሆኖኛል። ከቀደሙ አባቶች እንደሰማሁት አዘማሪ ብቻውን የቆመ አይደለም። ከብዙ ነገሮች ጋራ ከቅኔያችን፣ ከዜማችንና ከስሜታችን ጋራ የተያያዘ ነው። አዘማሪ የሚለውን ቃል ከነዚህ ነጥሎ ለማቅረብ መሞከር ያዘማሪን ክብርና ቦታ ዝቅ ያደርገዋል የሚል ስጋት አለኝ።
ወንድሙ መኰንን
የለንደኖቹልማታዊ “ካኅናት”ወያኔያዊዘጋቢፊልምአቀናበሩብን!
ኢንግላንድ መከረም ፯ቀን ፪፲፻፯ ዓ.ም
መግቢያ
እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ። መባል ስላለበት ነው። ያለፈውማ ዓመትአንደኛውን ጥቁር ዓመት ተብሏል። ሲያንሰው ነው። ወያኔ ከመቼው በበለጠ ጥቃቷን በኢትዮጵያ ልጆች ላይ በሁሉም አቅጣጫ ያጧጧፈችበት ዓመት ነበር። ነጻውን መገናኛ ብዙሀን ከጨዋታ ውጪ አድርጋለች። ብዙ ጋዜጠኞች በማሠሯ ወህኔ ቤቱ ጠቧል መሰለኝ፣ አሁን አሁን የያዘችው ዜዴ፣ በቁጥጥሯ ሥር ከሌሉ፣የፋሺን ጋዜጠኞችም ሳይቀሩ ማዘዣ ሳይደርሳቸው፣ በሬዲዮዋና በጋዜጦቿ “ከስሼአቸዋለሁ!” በማለት ፣ ነጭ ሽብር እየነዛችባቸው በርግገው ከአገር እንዲጠፉ ማሳደዷን በሰፊው ተያይዛቸዋለች።
ባለፈው ሳምንት በማህበራዊ ሚዲያው ‹‹ጥቁር ሳምንት›› (black week) በሚል ለአምስት ቀናት ዘመቻ (campaign) መካሄዱ ይታወሳል፡፡ በዚያ የጥቁር ሳምንት ዘመቻ ወቅት በመጨረሻው ቀን አስተባባሪዎቹ አዲስ አመትን በማስመልከት ‹አዲስ አመት በዓልን ከነጻነት ታጋዮች ጋር› በሚል የታሰሩ የነጻነት ታጋዮች እንዲጠየቁ ጥሪ መተላለፉ አይዘነጋም፡፡ በመሆኑም የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችና የነገረ ኢትዮጵያ ዝግጅት ክፍል ጳጉሜ 5 ቀን 2006 ዓ.ም በቂሊንጦ የሚገኙ የዞን 9 የጡመራ ቡድን አባላትንና የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን በመጠየቅ የዘመቻውን አካል አከናውነዋል፡፡ ቀጥሎም የጥቂት እስረኞችን መልዕክት በአጭር በአጭሩ አቅርበናል።
ነቢዩ ሲራክ
አዲስ የነበረውና ዛሬ ገና 12 ወር ከ5 ቀኑ “ያረጀ ያፈጀ ” የምንለው 2006 ዓ.ም ለመገባደድ ጥቂት ሰአታት ብቻ ነው የቀሩት። 2006 ዓ.ም በሳውዲ ለምንገኝ ኢትዮጵያውያን ልዩ የማይጠፉ ትዝታዎቸን አስተናግደንበታል።
* ፍጹም የማይረሱኝ ትዝታዎች …
በ2006 ተከስተው የማይረሱኝ የተለያዩ ክስተቶች እና አስደሳችና መራራ ትዝታዎች ብዙ ቢሆኑም የተጨመቁትንና ፍጹም ከአዕምሮየ የማይጠፉት በአዲሱ አመት መግቢያና በአሮጌው አመት መሸኛ የመጨረሻ ሰአታት ላድታውሳቸው ግድ አለኝ …
ይህ አመት አንደተለመደው አይነት አመት ቢሆን ኖሮ በዚህ ወቅት የዞን9 ጦማርያን በጦማሪት ማህሌት አስተባባሪነት ፣ በአጥናፍ ብርሃኔ እና በጆማኔክስ ካሳዬ ትብብር የአመቱን ታላላቅ ክስተቶች አሰባስበው ከመታተሙ በፊት ለቡድኑ ክለሳ የሚያቀርቡበትና የተረሱ እና ለክስተትነት የማይበቁ የምንላቸውን ሁነቶች የምንለይበትና የአመቱን የጊዜ መስመር የምናወጣበት ወቅት ነበር።
እንደሰማሁት ከሆነ ጥቁር ሳምንት በሚል የተጀመረው ዘመቻ ጥሩ ዘመቻ ነው፡፡ በማህራዊ ሚዲያው ሲንቀሳቀሱ የነበሩትም ሆነ ጋዜጠኞች በመታሰራቸው እንቅስቃሴው አለመዳከሙ ያስደስታል፡፡ መጭው ዘመን የነጻነት ይሆን ዘንድ ኢትዮጵያውያን ይህን የመሰሉ እንቅስቃሴዎችን መደገፍ፣ ማበረታታትና መቀላቀል አለባቸው፡፡ በተለይ በአሁኑ ዘመን ማህበራዊ ሚዲያው ትልቅ ለውጥ እያመጣ ነው፡፡ በግብጽና ቱኒዚያ ማህበራዊ ሚዲያው ቀላል የማይባል ለውጥ አምጥቷል፡፡
ጋዜጠኛ አንተነህ መርዕድ
ህወሃት በሻዕብያ ታዝሎ* ምኒልክ ቤተመንግስት ከገባና ኦነግንም ሆነ ሌሎቹን ጠፍጥፎ የሰራቸውን መናኛ ድርጅቶች እንኳ ሳያስቀርብ በብቻው የተያያዘው ዘረፋ፣ ሁሉን ለእኔ ብቻ ያለ ሂደቱ ያላስደነገጠው ኢትዮጵያዊ አልነበረም። ያለፉትን ስርዓቶች የተሻገሩ ሁለት አንጋፋ ጓደኛም ጋዜጠኞች ሲጨዋወቱ በቦታው ነበርሁ። አንደኛው ወያኔ ነፃ አወጣዋለሁ ከሚለው ከኩሩው ኢትዮጵያዊ ከትግራይ ህዝብ አብራክ የተገኘ ነበርና “ወንድሜ ይሉኝታ በትግርኛ ምንድን ነው የሚባለው?” ሲል ጠየቀው። “ይሉኝታ..ይሉኝታ…” እያለ ቃሉን ማፈላለግ ሲጀምርና ፈጥኖም ቃሉን ማግኘት ሲሳነው “ተወው ወንድሜ የሌለውን ነው የጠየቅሁህ ቃሉ ከሌለ ወያኔዎች ከየት ይማሩታል ብዬ ልጠብቅ” በማለት ሁላችንንም አሳቀን።
ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ
‹‹እኛታስረንም፣በኢትዮጵያጋዜጠኝነትእናጋዜጠኞችላይየሆነውነገርእጅግቅስምይሰብራል ( It’s really heart breaking!)››
ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ
‹‹እስርደግምነገርነው›› ጋዜጠኛ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ
‹‹የነጻነትትግልላይእንዳለሁያወኩትእስርቤትነው›› ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ
‹‹መጽሔቶችመታተምመቆማቸውያሳዝናል፡፡አማራጩምንይሆን?››
አህመዲን ጀበል (የሙስሊሞች ጉዳይ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል)
ከትናንት በስትያ፣ ሰኞ ነሐሴ 26 ቀን 2006 ዓ.ም በጣም የናፈቁኝን ታሳሪ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን ለመጠየቅ በማቀድ፣ ረፋድ ላይ ወደቂሊንጦ እስር ቤት አመራሁ። በቃሊቲ ወህኒ ቤት ዋና በር ጋር በታክሲ ሳልፍ፣ ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ እና ኤዶምን ካሳዬ፣ ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁንን፣ አቶ አንዷለም አራጌን፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና ሌሎች የማውቃቸውን እስረኞች በሀሳቤ መጥተው ነበር።
አንዱዓለም ተፈራ (የእስከመቼ አዘጋጅ)
ባለፈው ጽሑፌ ኢትዮጵያዊነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ፤ ከልቤ ያማምንበትን በጥቅሉ አስፍሬ ነበር። በዚያ፤ ኢትዮጵያዊያንን መውደድ ማለት፤ ታሪካቸውን፣ ባህላቸውን፣ ቋንቋቸውን፣ መላ የኑሮ ሁኔታቸውን ጨምሮ ማለት ነው።
ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ)
“እኛ ትክክለኛ እና ጠቃሚ የሆኑ በርካታ ነገሮችን አከናውነናል፣ ሆኖም ግን ከዚህ በተለዬ መልኩም ህዝብን አሰቃይተናል፣ ከእሴቶቻችን ጋር ተጻጻሪ የሆኑ ነገሮችን ፈጽመናል። ከፍ ወዳሉ የምርመራ ስልቶች ስንገባ ማለትም ማሰቃየትን ጨምሮ ማንም ሚዛናዊ የሆነ አስተሳሰብ ያለው ሰው እንደሚያስበው እና እንደሚያምነው የምናደርገው ድርጊት ማሰቃየት ሆኖ ሲገኝ መስመሩን አለፍን ማለት ነው። እናም ይህ ጉዳይ ግንዛቤ ሊወሰድበት እና ተቀባይነትንም ማግኘት አለበት“ በማለት ፕሬዚዳንት ኦባማ ከጥቂት ቀናት በፊት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገልጸዋል።
(አጭር ልብወለድ)
ማትያስ ከተማ (ወለላዬ ከስዊድን)
እግሬ እንደተነፋች ዶሮ ጢል ብሎ አብጧል። ጫማዬን ወጥሮት ማቆም እያቃተኝ ነው። ይኼን አሳዛኝ ሁኔታ ኃላፊው ማወቅ አለበት። ሄድኹኝ ምንም ሳልናገር ጫማዬን አውልቄ አሳየሁት። እሱም ምንም ሳይናገር ወደ ጓዳ ገብቶ ተመለሰ። የፕላስቲክ ነጠላ ጫማ አንጠልጥሏል።
የገዥው ፓርቲ ቅድመ ምርጫ የጽዳት ዘመቻ
Ethiopia Zare (ቅዳሜ ነሐሴ 17 ቀን 2006 ዓ.ም. August 23, 2014)፦ በአምስት ሣምንታዊ መጽሔቶችና አንድ ጋዜጣ ላይ የተመሰረተውን ክስ ተከትሎ አስራ አንድ ጋዜጠኞች ለስደት ተዳረጉ። አስራ አንዱ ጋዜጠኞች የተሰደዱት በፍትህ ሚኒስቴር ሐምሌ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. “የዐመጸ ቅስቀሳና የሐሰት ወሬዎችን በመንዛት ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመናድ ጥረት አድርገዋል” በተመሰረተባቸው ክስ መሆኑን ለኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ የደረሰን መረጃ ያስረዳል።
አንዱዓለም ተፈራ (እስከመቼ)
“ ኢትዮጵያዊነት ማለት፤ ኢትዮጵያዊያንን መውደድ፣ ኢትዮጵያን ማፍቀር፤ የኢትዮጵያን መንግሥት በተገቢው መንገድ መደገፍና፤ ይህ መንግሥት የተሳሳተ መንገድ ሲይዝ መቃወም ማለት ነው። በሥልጣን ላይ ያለው ክፍል ፀረ-ኢትዮጵያዊያንና ፀረ-ኢትዮጵያ ሲሆን፤ ያንን ክፍል በማንኛውም መንገድ ማስወገድ፤ የያንዳንዱ ኢትዮጵያዊና የያንዳንዷ ኢትዮጵያዊት፤ ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው።”
ኤፍሬም ማዴቦ
ባለፈው ሰሞን ቻይና አፍሪካ ውስጥ ሰላሳ አመት በማይሞላ ግዜ ውስጥ ያደረገችው የኤኮኖሚና የፖለቲካ መስፋፋት ያሳሰባቸው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ምነው ምን አድረግናችሁና ነው ፊታችሁን ያዞራችሁብን ብለው ለመጠየቅ በርከት ያሉ የአፍሪካ መሪዎችን ቤተ መንግስታቸው ድረስ ጋብዘዋቸው ነበር።

Ethiopia Zare (ረቡዕ ሐምሌ 14 ቀን 2006 ዓ.ም. August 20, 2014)፡- በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም በሚገኘው የደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን የደብረታቦር በዓል ሁኔታ በትናንትናው ዕለት በደማቅ ተከበረ። ጸሎትና የትምህርቱ በኃይማኖት አባቶች ለምዕመናኑ ከተሰጠ በኋላ፣ ከምሽቱ አንድ ሰዓት (13፡00 ሰዓት) ላይ የበዓሉ መገለጫ የሆነ ችቦ በርቷል።
በፍቃዱ ኃይሉ (የዞን 9 ብሎገር ከቂሊንጦ እስር ቤት)
”ታዲያ ጥፋቴ ምንድን ነው ትላለህ?!”፣ ብሎኛል አንዱ መርማሪዬ ስለዞን ዘጠኝ እና እኔም እራሴ እንደጦማሪም እንደአራማጅ ተራማጅም ሠራሁ የምላቸውን ነገሮች ዝርዝር ነግሬው ሳበቃ። በኋላ ላይ በእስር ቤት ቋንቋ ከ”አባሪዎቼ” ጋር መገናኘት ከተፈቀደልን በኋላ ስንጠያየቅ ለካስ ሁላችንም ይቺኑ ጥያቄ ተጠይቀናል።
በፍቃዱ ኃይሉ (የዞን 9 ብሎገር ከቂሊንጦ እስር ቤት)
”ታዲያ ጥፋቴ ምንድን ነው ትላለህ?!”፣ ብሎኛል አንዱ መርማሪዬ ስለዞን ዘጠኝ እና እኔም እራሴ እንደጦማሪም እንደአራማጅ ተራማጅም ሠራሁ የምላቸውን ነገሮች ዝርዝር ነግሬው ሳበቃ። በኋላ ላይ በእስር ቤት ቋንቋ ከ”አባሪዎቼ” ጋር መገናኘት ከተፈቀደልን በኋላ ስንጠያየቅ ለካስ ሁላችንም ይቺኑ ጥያቄ ተጠይቀናል።
በክንፉ አሰፋ
ደራሲ – ኤርምያስ ለገሰ
ብዛት – 406 ገጾች
አሳታሚ – ነጻነት አሳታሚ ድርጅት
እንደ መንደርደርያ
በስፋት ሲወራለት የነበረውን ይህን መጽሃፍ ሙኒክ-ጀርመን ላይ ገዝቼ ለማንበብ እያፈላለግኩ ሳለሁ፤ አንድ ወዳጄ ይዞት አየሁ። የደበዘዘ የመለስ ፎቶ ያለበትን ይህንን መጽሃፍ የኦስሎው አበበ እጅ ላይ ነበር። ገና ሰላምታ ሳንለዋወጥ ነበር መጽሃፉን ከእጁ ላይ የነጠቅኩት። ታማኝ በየነም እዚያው አብሮን ስለነበር አስተያየቱን ጣል አደረገ። “መነበብ ያለበት መጽሃፍ” እንደሆነ አበክሮ ነገረኝ። ታማኝ ኢትዮጵያን የሚመለከቱ መጻህፍት በሙሉ እንደማያመልጡት አውቃለሁ። በዚህ አዲስ መጽሃፍ ላይ አንዳች አዲስ ነገር እንደሚኖር ከንግግሩ ለመረዳት አያዳግትም።
ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም
አንዳንድ እንደዘረኝነት፣ ጐሰኝነትና የሃይማኖት ጥላቻ ስለመሳሰሉ አጸያፊ ክስተቶችና ሕዝባዊ ግንኙነቶች ማንሳትና ስለእነርሱም መጻፍ የሚቀፍ ከመሆኑም በላይ፤ ያልሆነ ስም ሊያሰጥና በዘረኝነት ተጠቃሚ የሆኑ አካላትንም ሊያስከፋ ይችላል። ሆኖም ሳይመሽ አገርን ከውድቀት ለመታደግ እና ሕዝብን ከጥፋት አፋፍ ለመመለስ ሲባል፤ ከአገርና ከሕዝብ የሚበልጥ የለምና ይሉኝታን ዋጥ አድርጐ በፍርሃት ሳይገደቡ፣ በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ ሳይሽሞነሞኑ እነዚህን አገር በታኝ ክስተቶችን በአደባባይ አፍርጦ ለማውጣት ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን ሰው መሆንም በቂ ነው።
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም
በቅርቡ ከአንድ ወዳጄ ጋር ስለኢየሩሳሌም ማኅበር ስናወራ መሥራቹ አቶ መኮንን ዘውዴ ትዝ አሉኝና ስለሳቸው ውለታ ሳወራ ነበር፤ ከሳቸው ጋር ተያይዞም ከዚህ በፊት አይ አበሻ! በሚል አጠቃላይ ርእስ አበሻና ልመና ወዘተ. እያልሁ መጻፍ ጀምሬ የነበረው ትዝ አለኝ፤ አንዳንድ ስላልገባቸው ነገር ሁሉ መጻፍ የሚወዱ ሰዎች አቅጣጫውን ሊለውጡት ሙከራ ሲጀምሩ ትቼው ነበር፤ አሁን የመክሸፍን ጉዳይ ደግሜ ለመጻፍ ስጀምር አንዳንድ በጣም መሠረታዊ የሆኑ የመክሸፍ መገለጫዎችን ስጽፍ በመጽሐፍ መልክ እስኪወጣ አላስችል አለኝና አንዱን ሀሳብ አደባባይ ለማውጣት ወሰንሁ፤ በዚያውም አቶ መኮንን ዘውዴን ማስታወሻ ይሆነኛል።
በዳዊት ሰለሞን
ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣን ዛሬ አነበብኳት ፡፡የጋዜጣዋ ባልደረባ የሆነው በላይ ማናዬ በቅርቡ ለእስር የተዳረገው የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ የሆነው የሺዋስ አሰፋ ቤት ተገኝተው የየሺዋስን ሁለት ህጻናት ልጆች ማግኘታቸውንና ህጻናቱም ስለ አባታቸው የሚያስቡትን እንደነገሩት ይተርካል፡፡
ሳምሶን አስፋው – አውስትራሊያ
የአቶ አንዳርጋቸው ቃልና የወያኔ ፕሮፓጋንዳ
ሰሞኑን በወያኔ መንግስት የፖሊስ ፕሮግራም የቀረበው “አቶ አንዳርጋቸው ለመንግስት ጠቃሚ መረጃ ሰጡ” የሚለው ዜና ኢትዮጵያዊውን ሁሉ እያነጋገረ ያለ ጉዳይ ነው። የዜናው አነጋጋሪነት የሚነሳው ለዜናው አብይ ግብአት እንዲሆን፤ በወጉም ሳይታሰብበት ተለጣጥፎ የቀረበው የቪዲዮ ክሊፕ የዜናውን ጩኸት አለማስተጋባቱ ነው። በመጀመሪያ የምናነሳው ጥያቄ የወያኔ ባለስልጣናት ይህንን በተራ ግለሰብ እንኳ ቢቀርብ የሚያሳፍር ደካማ የማስመሰል ስራ በመንግስት ደረጃ ለማቅረብ ያስገደዳቸው ምንድነው? የሚለውን ጥያቄ ይመስለኛል። ለዚህ ደግሞ የተለያዩ መላምቶችን መሰንዘር እንችላለን።
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም
ለእኔ ፖሊቲካና የግለሰብ ጠባይ እንደውሃና ዘይት የማይደባለቁ ነገሮች ይመስሉኛል፤ አጼ ምኒልክ ‹‹አመልህን በጉያህ›› ያሉት ለዚህ ሳይሆን አይቀርም፤ ዘይትና ውሀ በባሕርያቸው የሚለዩትን ያህል ፖሊቲካና ግለሰብም የባሕርይ ልዩነት አላቸው ማለት ነው፤ የወያኔ መሪዎች ምንም ነገር የማይሰምርላቸው፣ ከመጀመሪያውኑ እነዚህን ሁለት የማይደባለቁ ባሕርዮች አደባልቀው በመንሣታቸው ነው፤ ፖሊቲካ ለማኅበረሰቡ መቆርቆር ነው፤ ለሕዝቡ መቆርቆር ነው፤ ለአገር መቆርቆር ነው፤ የፖሊቲካ መነሻም ይኸው መሆን አለበት፤ ዓላማውም የማኅበረሰቡ፣ የሕዝቡ ልማት እንጂ ጥፋት አይደለም፤ የነበረውንና ያለውን ማጥፋት የፖሊቲካ ዓላማ ሊሆን አይችልም።
አቶ ግርማ ሰይፉ
የመንግሰትን ቀጣይ እርምጃ የሚያሳዩ ተከታታይነት ያላቸው በግል ሚዲያዎች ላይ የሚደረጉ ዘመቻው ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ መልክቶች እየታዩ ነው። በቀጣይ ለሚቀርበው ዶክመንተሪ ተጋባዥ አንግዳ ሆኜ ለቆርጦ ቀጥሉ ኢቲቪ ቃለ ምልልስ እንደሰጣቸው ጥያቄዎቹ ደረስውኝ ተመልክቸዋለሁ። የጥያቄዎቹን ዝርዝር እንተወው እና ዓላማው ግን ባለፈው ከቀረበው ዘጋቢ ፊልም የተለየ ነገር የለውም። በነገራችን ላይ ባለፈው የቀረበውም ዘጋቢ ፊልም ላይ እንድሳተፍ ተጠይቄ እንደማይሆን ገልጨላቸው ነበር። ውሳኔዬ ትክክል መሆኑን ዘጋቢ ፊልሙን ካየሁ በኋላ ገብቶኛል።