በጀርመን፣ፍራንክፈርት የተደረገው ሰላማዊ ስልፍ ስኬታማ እንደነበር ተገለጸ
ጋዜጠኛ ዮሐንስ ደሳለኝ – (ጀርመን)
Ethiopia Zare ቅዳሜ ጥር 10 ቀን 2007 ዓም January 17,2015:– ባሳለፍንው ሰኞ በፍራንክፈርት የሚገኙ ኢትዩጽያዊያን በአሁኑ ሰዓት በአገራቸው የሚደረገውን የመብት ጥሰት ለተለያዬ ተቁማት ለማሳወቅ ሁለት ሰዓት የፈጀ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ። መነሻውን ከዋናው የባቡር ጣቢያ አንድ ጣቢያ (station)አልፉ በሚገኘው ታውንስላገን አካባቢ ከዋናው ደች ባንክ አጠገብ ያደረገው ሰልፍ፣ ረፈዱ 11፡00am ላይ ተጀምሮ የእንግሊዝ ኤምባሲን አካሎ ምሳ ሰዓት ላይ (1፡00pm) ፍራንክፈርት የሚገኘው ኢትዬጽያ ቆንጽላ ጽ|ቤት በመገኘት በተለመደው ኢትዬጵያዊ ጨዋነት ተጠናቁል።