በኤርምያስ ለገሠና በዲ/ን ዳንኤል ክብረት በኩል እኛን ማዋራት አሰኘኝ
ይሄይስ አእምሮ (ከአዲስ አበባ)
ይህ ኢትዮጵያዊነት በስንት ረገድ ቁጭት ውስጥ እየከተተን እንደሆነ እናንተም አስቡት። በእጅጉ የሚገርም ሁኔታ ውስጥ እየከተተን ነው ያለ። በዚህች ሌሊት ሰባት ሰዓት ገደማ ያነበብኩት ጽሑፍ እንኳን ክፉኛ ዕንቅልፍ ነስቶኝ ከሌሊቱ አሥር ሰዓት ላይ ከሚጥመው መኝታየ ተነስቼ ይሄውና መዶግዶግ ያዝኩ – ለነገሩ ሳለ ወያኔ ምን የሚጥም መኝታ አለና!