የዶርዜ ማርያም
አስፋ ጫቦ
1. ዶርዜ ዴሬ (አገር) የዶርዜ ማርያም የለችም። ያሉ ሁለቱ አድባራት የጥንቱ ፣የጥዋቱ የዶርዜ ጊዮርጊስና የዶርዜ ሚካኤል ናቸው።ሚካኤል ከጨንቻ በልጅ እግር ከ30-45 ደቂቃ ቢወስድ ነው። በምን ሊከድ ኖሯል!? ልጅ ሆኜ አንድ ሁለቴ ሚካኤልን ለማንገስ መሔዴ ትዝ ይለኞል።ማንገሱ ሳይሆን የዶርዜ ዘፈኑ መስለኝ የሚጠራኝ።ታላቅ የሙዚቃ ትዕይንትና ቲያትር አደራሽ እንደመግባት ይሰማኛል። አዳራሹ ሜዳው መሆኑ ነው። ዶርዜ ማርያም ብትኖርም እንኳ ዶርዜ ማራሞ ነው የምንለው። ታሪካዊዋንን የዜናሁ ለጋለ ፤የአባ ባሕርይ መጽሐፍ መፍለቂያ የብርብር ማርያም ደብረ ነች። ያችን እኛ ቢርቢራ ማራሞ እንላለን። ዚኒ ከማሁ፤ኤሌ ጋብሬሌ፤ዶርዜ ሚካሌ ነው የምንለው።