የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ ተካሄዷል ብለን አናምንም!
ከአንድነት ፓርቲ
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ምርጫ ቦርድ ነፃና ገለልተኛ እንዳልሆነ የሚገነዘብ ቢሆንም ባለፈው ታህሳስ 12/04/2007 ዓ.ም የተካሄደው የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ በሀገራችን የምርጫ ቦርድ አለ ወይ?! እንዲል አድርጎታል። የታህሳሱ 12/04/2007 ዓ.ም የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ ነፃና ገልልተኛ አልነበረም ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የምርጫ ህጉን ተከተሎ ያልተካሄደ ሌላው ይቅርና የራሱ የምርጫ ቦርድ መመሪያን እንኳን ያልተከተለ ከመሆኑ አንፃር ተካሄዷል ብለን አናምንም። እንዲህ ዓይነቱ ድምዳሜ እንድንደርስ ያደረጉን ምክንያቶች ብዙ ቢሆኑም በዋናነት የሚከተሉት ነጥቦች ከግምት ውስጥ አስገብተናል።