ለሰላማዊ ዜጎች ጥያቄ ጥይት መፍትሄ አይሆንም!

ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ መግለጫ

በባህርዳር ከተማ ለዘመናት የእምነት ቦታ ሆኖ ለአምልኮ አገልግሎት ሲውል የነበረ የህዝብ ይዞታ በማያውቁትና ባልመከሩበት ሁኔታ ባለሀብት እንዲያለማው በከተማው መስተዳድር ተሰጥቷል መባሉን ተከትሎ የከተማዋ ነዋሪዎች ባዶ እጃቸውን ሆነው በሰላማዊ መንገድ ባሰሙት የተቃውሞ ድምጽ መንግስት የህዝቡን ጥያቄ ለማፈን በወሰደው ዘግናኝና አሰቃቂ በጥይት የታገዘ የኃይል እርምጃ እስካሁን የአምስት ንፁኃን ዜጎች ህይወት ተቀጥፏል፡፡ ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑ አዛውንት እማሆይንና አካል ጉዳተኛ ጨምሮ በርካቶችን በማቁሰል የአካል ማጉደል ደርሶባቸዋል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …