ግርማ ሞገስ

የህወሓት/ኢህአዴግ ጠንካራ ጎኑ እስከ ጥርሳቸው ድረስ የታጠቁት ፖሊስ፣ ደህንነት፣ ምድር ጦር፣ አየር ኃይል፣ አየር ወለድ፣ ካድሬ እና ቅጥረኛ ወርበሎችን ያካትታል። የሚያውቀው የፖለቲካ ትግል ዘዴ በጫካ መገዳደልን እንጂ በከተሞች ሠላማዊ ትግሎች ማድረግ አይደለም። ስለዚህ ሠላማዊ ትግል ህወሓት/ኢህአዴግን በማያውቀው የትግል ሜዳ፣ የትግል ዘዴ እና በደካማ ጎኑ እንዲታገል እንደሚያስገድደው እና የህዝብ ድጋፍ የሚያሳጡ ስህተቶች እንደሚያሠራው የአንድነቶች የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ዘመቻ ወለል አድርጎ አስተምሮናል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ቦጋለ ካሣዬ 

“… ግንቦት-7 ሲመሰረት፤ ብዙ ሀገር ወዳድ ዜጋ 500 ዶላር ወይም ኢሮ እያዋጣ ተቀላቅሎት ነበር። ይሁን እንጂ እነአንዳርጋቸው ብራቸውን ከሰበሰቡ በኋላ፤ በመጀመሪያ ከአንድነት ኃይሎች ጋር ለመስራት ፍላጎታቸውን ማሳየት ጀመሩ። ቀስ ብለው ደግሞ ከቅንጅት መንፈስ በመንሽራተት፤ የኦነግንና ኦብነግን ማሽኮርመም ጀመሩ። የአንድነቱ ኃይል አጉረመረመ። እነአንዳርጋቸው ግን ብዙም አልተጨነቁም። ኢሳታቸው ስላለ የፕሮፓጋንዳ የበላይነት አላቸውና፤ የጎሣ ፖለቲካቸውን በታሪካዊ በደል ፈጻሚ (አማራ) እና ሰለባ (ሌለው ጎሣ) እያመካኙ፤ አሁን ኤርትራ ሽባ ሆኖ የቀረውን ከማል ገልቹን፤ እንደ የአንድነት ታጋይ በማግዘፍ ጄኔራል ከማል ገልቹ! ጄኔራል ከማል ገልቹ! እያሉ አናፉብን። …”

ሙሉውን አስነብበኝ …

ወለላዬ

ሰፈራችንን መሀል ለመሀል ሰንጥቆ ከሚያልፈው መንገድ በስተቀኝ ሃያ አንድ መኖሪያ ቤቶች ይገኛሉ። ከነዚህ ቤቶች ነዋሪዎች ውስጥ ከአብዛኛዎቹ ጋር የስጋ ዝምድና አለን። በተለይ በአንድ ግቢ ውስጥ የምንኖረው ስምንት ቤተሰቦች ደግሞ የቅርብ – በጣም የቅርብ ዘመዳሞች ነን።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አብርሃም ያየህ

ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

የግንቦት 7 ዋና ፀሐፊና የድርጅቱ ያመራር አባል የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ፣ ከቅርብ ቀናት በፊት ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ጋር ባደረጉት ሰፊ ቃለመጠይቅ አማካኝነት በሰነዘሯቸው የተለያዩ አብይ ሃሳቦችና፣ ከቃለ-መጠይቁ ውጭ ነገር ግን ተያያዥ የሆኑ ሌሎች ጉዳዮች፣ መሰረት በማድረግ ለመወያየት ወስኛለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አማኑኤል ዘሰላም

በደሴ፣ ጎንደር፣ ባህር ዳር፣ ፍቼ፣ አዳማ/ናዝሬት፣ ሮቢ/ባሌ፣ መቀሌ፣ ወላይታ ሶዳ፣ ጂንካ፣ አርባ ምንጭ … ሰላማዊ ሰልፎችና ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች ተደርገዋል። በአዋሳ፣ ድሬደዋ፣ ወሊሶ፣ አሶሳና ጋምቤላ፣ እቅዱ ውስጥ የነበሩም ቢሆንም በገንዘብ አቅም ምክንያት ለጊዜው ሰልፎች ሊካሄዱ አልቻሉም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Ethiopia ኢትዮጵያSyria ሶሪያሰሎሞን ተሰማ ጂ.
የሶሪያ ጉዳይ ከዕለት ወደ ዕለት እየከፋ መጥቷል። በስልጣን ላይ ያለው ጎሳ “የአላዊት ጎሳ” ይባላል። አላዊቶችና በደዊኖች በሽፍትነትና በባህር ላይ ውንብድና ስማቸው የገነኑ ናቸው። በደዊኖች፣ ሶሪያን ለዘመናት ያህል ሲፈልጧትና ሲቆርጧት ኖረዋል። እንደነሱ ዘረኛ፣ እንደበደዊኖች ጠባብ፣ አክራሪና ቁመኛ ታይቶም-ተሰምቶም አይታወቅም። አላዊቶችም ቢሆኑ “አልሸሹም ዞር አሉ” ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Girma Moges ግርማ ሞገስግርማ ሞገስ 

በክፍል አንድ እንዳነበብነው የዝንጀሮዎቹ አምባገነን ጌታ ተርቦ ከመሞቱ በፊት የሚቀልቡት የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ነበሩት። የፖለቲካ ኃይል ምንጮቹ መድረቅ ተርቦ እንዲሞት አድርገውታል። እንደ ዝንጀሮዎቹ አምባገነን ጌታ መንግሥትም የፖለቲካ ኃይል ምንጮች አሉት።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Girma Moges ግርማ ሞገስየፖለቲካ ኃይል ምንጮች (ክፍል አንድ/2)

ግርማ ሞገስ

የዝንጀሮዎቹ ጌታ አጭር ታሪክ የተወሰደው ቻይናዊው ሊዩ ጂ/ Liu-Ji (1311-1375) ከጻፈው የሞራል ማስተማሪያ መጽሐፍ ነው። ይኽ አጭር ታሪክ የአምባገነን ገዢዎች የፖለቲካ ኃይል ከየት እንደሚፈስላቸው (ምንጩ ምን እንደሆነ) እና እንዴት ምንጩን በመቆጣጠር የአምባገነኖችን አቅም መቆጣጠር አልፎም ምንጩን በማድረቅ አምባገነኖችን ማስራብ እንደሚቻል በምሳሌ አድርጎ ግልጽ ያደርጋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Yedenekachew Kebede ይድነቃቸው ከበደይድነቃቸው ከበደ (የሰማያዊ ፓርቲ የሕግ ጉዳይ ኃላፊ)

የዘመን መለወጫ ክብረ በዓል በየትኛውም ሀገር እንደ አገሩ ወግና ልማድ በድቅመት የሚከበር በዓል ነው፤ በእኛ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ደግሞ ልማድና ወጋቻን እጅግ ከመጠንከሩ የተነሳ ለአዲስ ዓመት ወይም ለዘመን መለወጫ ክብረ በዓል ዝግጅታችንም ሆነ አከባበራችን እጅግ በጣም ጠንካራና ደስ የሚል ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

(ተመስገን ደሳለኝ)

ኢህአዴግ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ (በውስጥም በውጪም ተግዳሮቶች) መገፋቱን በሚያመላክቱ የፖለቲካ አንዳዎች ላይ የሚያጠነጥን አንድ ፅሁፍ (‹የአብዮቱ የምፅዓት ቀን ምልክቶች›› በሚል ርዕስ) አቅርቤ እንደነበር ይታወሳል፤ ይዘቱም በመጪዎቹ ወራት ወይም ዓመት ስርዓቱ ‹ምርጫ› አሊያም ‹ህዝባዊ› እምቢተኝነት ከሚያመጣው ‹ማዕበል› (እንደበረከት ስምዖን አገላለፅ ‹ናዳን በሚገታ ሩጫ›) የማምለጥ ዕድሉ የጠበበ መሆኑን የሚያመላክት ነው፤ ይሁንና አንድ አብዮት ታላቅ (ውጤታማ) ሊባል የሚችለው አምባገነን ስርዓትን በመቀየሩ ብቻ ስላልሆነ (ሥር-ነቀል ለውጥ የሚፈጥር አብዮት ዋጋ የሚኖረው የዲሞክራሲ ተቋማትን መሰረት መጣል ሲችል ነውና) በቀጣይ መፃኢ ዕድሉ ላይ መነጋገሩ አስፈላጊ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተክለሚካኤል አበበ(ቶሮንቶካናዳ)

 የግንቦት ሰባት ርእሰ አንቀጽ

 1.      ከግንቦት ሰባትና የግንቦት ሰባት አመራር አባላት የማደንቅላቸው ድንቅ ነገር ቢኖር ሌሎችን ያለመተናኮስ ባህርያቸው ነው።ሌሎች ቢተነኩሷቸውም እንኳን፤ ምንም ምላሽ ያለመስጠት አቋማቸውን አደንቅላቸዋለሁ። እስካለፈው ሁለት ሳምንት ድረስ። ባለፈው ሁለት ሳምንት ግን፤ በራሳቸው አነሳሽነት አገር ቤት ያሉትን ድርጅቶች ወደ መተንኮስ ያዘነበሉ ይመስላል። በተለይም ሰማያዊ ፓርቲን። ስለዚህም ጥያቄ ተነሳብኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በልጅግ ዓሊ

አርባ ቀኔ ሆነ ከተለየኋችሁ፣

ድምጼን ከሰማችሁ ዓይኔንም ካያችሁ፣

ከጠየቃችሁኝ ካነጋገርኳችሁ፣

አርባ ቀኔ ሆነ ከሄድኩኝ ትቻችሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ግርማ ሠይፉ ማሩ

ሀገራቸን ኢትዮጵያን ለቀው ለስደት የተዘጋጁት ዜጎችን ቁጥር መገመት አስቸጋሪ ቢሆንም በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት መውጣት የቻሉት ግን ላለመመለስ ብዙ ምክንያቶች አሉዋቸው። ይህን የዜጎች (በተለይ የተማሩና ወጣቶች) ስደት ሀገራችንን ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈላት እንደሆነ እና ወደፊትም ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያስከትል ለማወቅ ሊቅ መሆን የሚያስፈልግ አይመሰለኝም።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ እና ልናገረው የከበደኝ ሮሮ

ነቢዩ ሲራክ

በግልም ቢሆን አዲሱን ዓመት በሠላም እና በደስታ መቀበሌ እውነት ነው! መስከረም ጠብቶ ብዙ ቀናት ሳንቆጥር ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚደርሱኝ የስደተኛ ወገን መከራ ግን ከአዲሱ ዓመት ዋዜማ ጀምሮ እስከ መባቻው አላባራም። እያንዳንዱን የወገን ስደት ሰቆቃ መከራ ጨክኜ ከመናገር ለመቆጥብ ያደረግኩት ትግል ላንዲት ቀን ቢሳካም፤ ህሊናዬ ግን እረፍት አላገኘም። በተለይ በአዲሱ ዓመት ዋዜማ “ብሪማን” ተብሎ በሚጠራው የጅዳው ትልቅ ማረሚያ ቤት የደረሰኝ መረጃ ያማል …

ሙሉውን አስነብበኝ …

አቤቶኪቻው

ኮሎኔል ሃይማኖት የአቶገብረዋህድ ባለቤት ናቸው፡፡ ከጫካ ታግለው መጥተው ሹመት በሹመት ሆነውሲሾም ያልበላ ሲሻር ምን ሊበላ ነውብለው ሲበሉ፣ ሲበሉ፣ ሲበሉ… ”የተበሉሴትዮ ናቸው፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይመኩ ታምራት ከሎንዶን

መቶ አርባ-አምስት ዓመት ያስቆጠረውን መቅደላን ስናነሳ መቼም ዓፄ ቴዎድሮስና ታላቁ ጀብዷቸው፤ ሮበርት ናፒዬር እና እንግሊዞች በሀገራችን ላይ ያካሄዱት ከ’ግዳጅ ወሲብ’ ጋር የማይተናነስ ደፈራ እና ብዝበዛ፣ የነደጃች ካሣ ምርጫ ሴራ፤ የልጅ ዓለማየሁ መሰደድና በለጋ ዕድሜው ከሀገርና ከዘመድ ተለይቶ ሳለ የሕይወቱ በአጭሩ መቀጠፍ፣ ወ.ዘ.ተ. ይታወሱናል። ስለዚያ ወቅት ታሪክ በጥልቀት ለሚያጠና፣ አያሌ መጻሕፍትና ማስታወቻዎች፤ አብዛኞቹ በነጮቹ፣ አንዳንድም በኛው ሰዎች ተጽፈው በታሪክ ማኅደር ውስጥ ይገኛሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤልዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
የባሰ አታምጣ! ነው የሚባለው። መቼም የኤርትራ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋዜጣዊ መገለጫ በሰጡ ቁጥር ግርግር ሳይፈጥሩ፤ ጎረበት አገር በውስጠ ወይራ ሳይጎነትሉ፤ ምዕራባውያን መንግሥታት ግልጽና በማያሻማ ቋንቋ ሳይወርፉና ሳይዘነጥሉ፤ ብዙሐን ፈገግ ሳያሰኙ፤ በአንጻሩ ደግሞ የተማረውን ክፍል ሳያስለቅሱና እርር ድብን እስኪል ድረስ ሳያደርጉ አልፉ ማለት ዘበት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Normal
0

false
false
false

MicrosoftInternetExplorer4

/* Style Definitions */
table.MsoNormalTable
{mso-style-name:”Table Normal”;
mso-tstyle-rowband-size:0;
mso-tstyle-colband-size:0;
mso-style-noshow:yes;
mso-style-parent:””;
mso-padding-alt:0cm 5.4pt 0cm 5.4pt;
mso-para-margin:0cm;
mso-para-margin-bottom:.0001pt;
mso-pagination:widow-orphan;
font-size:10.0pt;
font-family:”Times New Roman”;
mso-fareast-font-family:”Times New Roman”;
mso-ansi-language:#0400;
mso-fareast-language:#0400;
mso-bidi-language:#0400;}

              የአርቲስት ሻምበል በላይነህ አገራዊ ስራዎች አርአያነት                        

(ሉሉ ከበደ -ጋዜጠኛና ደራሲ)

 

ውድ ኢትዮጵያን ወገኖቼ እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ። እዲሱ አመት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ታላቅ ብስራት ይዞ የሚመጣ ይሁን። ያለምንም ደም መፋሰስ ይህ ዘረኛ የወያኔ ገዢ ቡድን መቃብር ገብቶ፤ ዘረኝነት፤ ጎጠኝነትና በታኝነት ከምድራችን ጠፍቶ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ተፋቅሮ ተከባብሮ፤ ሲያጠፉ የሚቀጣቸውን የሚሽራቸውን፤  ሲያለሙ የሚሾማችውን የሚሸልማቸውን መሪዎች በድምጹ መርጦ፤ የሚኖርበት፤ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከዘር ማንነቱ በፊት በኢትዮጵያ ሲምል ሲገዘት የምናይበት፤ ዜጎች ሁሉ ለሀገሬ፤….. ለወገኔ.. እያሉ ሲተጉ፤ ለጋራ እድገትና ብልጽግና ሲጓጉ….አንተ ትብስ አንቺ ትብሽ እያሉ አንዳቸው ላንዳቸው ሲሞቱ የምናይበት የተአምር ዘመን ይሁንልን,….ዘረኞች ለአንዴና ለመጨረሻ የሚጠፉበት ዘመን ይሁንልን….2006. አሜን!

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተቃዋሚው ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ መድረኩን ተቆጣጠሮ ያዘ (ቪዲዮ አለው!)

በስዊድን ጉተንበርግ ከተማ ሊደረግ የታሰበው የዓባይ ግድብ የቦንድ ሽያጭ ከሸፈ

ከኢትዮጵያ ዛሬ ሪፖርተር

“ይገርማል!” ብሎ መጀመር ይቻላል። አዎን ይገርማል! ከስቶክሆልም የሄድነው ወደ አዳራሹ የገባነው ጥሪ ባደረጉበት 13፡00 ሰዓት ነበር። እ.ኤ.አ ኦገስት 31 ቀን 2013.። ህዝቡ እስኪሰባሰብ ጥቂት ከተጠበቀ በኋላ ስብሰባው በአንድ የኢህአዴግ/ወያኔ ካድሬ ተከፈተ። እንዲህም አለ፤ “እዚህ እኛን ለመቃወም የመጣችሁ እንዳላችሁ እናውቃለን። ሃሳባችሁን እንድትናገሩ አንከለክልም፤ ነገር ግን ጩኸት፣ አላስፈላጊ ረብሻና ግርግር የምትፈጥሩ ከሆነ ወዮላችሁ! አስቀድመን ባዘዝነው የፖሊስ ኃይል እየተለቀማችሁ ትወጣላችሁ። መውጣታችሁ ብቻ አይደለም፤ ታሪካችሁ ይጠፋል፣ ውርደት ይከተላችኋል። በመለያ ቁጥራችሁም ላይ የሚጻፈው ወንጀል ዕድሜ ልካችሁን ይከተላችኋል።”

ሙሉውን አስነብበኝ …

ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ጅግሳ Dr. Fikre Tolossa ፍቅሬ ቶሎሳ ጅግሳ (ዶ/ር)

ውድ አንባብያን ሆይ! የምሥራች! የምሥራች ስላችሁም በሀገራችን ባህል አጸፋውን “ምስር ብላ!” በሉኝ። ልቤን ወደ ሰማይ እያዘለለ፣ እግሮቼን ጮቤ የሚያስመታ ነገር ሰሞኑን ገጥሞኛልና። እሱውም ከአያሌ ከዘመናት በፊት ዕድሜዬ 19 ሳለ የወለድኩት ልጄ፣ ያውም የበኹር ልጄ፣ ጠፍቶብኝ “በቃ! ሞቷል፣ ተከቷል!” ብዬ እርሜን አውጥቼ እያዘንኩ እኖር ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ጳጉሜን 2 ቀን 2005 ዓ.ም. September 7, 2013) ባለፈው ቅዳሜ ነኀሴ 25 የፌዴራል ፖሊስና የደኅንነት አባላት የሰማያዊ ፓርቲን ጽ/ቤት ጥሰው በመግባት የፈጸሙት ተራ የውብንድና ተግባር ብቻ ሳይሆን የህወሓት/ኢህዴግን ማንነት በግልጽ ያሳየ ለመሆኑ ከማንም በላይ ተግባሩ ራሱ ምስክር ነው በማለት ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ድርጊቱን ኮነነ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አንዷለም አራጌ ዋለ Andualem Aragie Walleክፍል ሁለት

በሀገሬ ሰማይ ስር በሚደረገው የተቃውሞ ፖለቲካ እንቅስቃሴ ከኢዴፓ እስከ አንድነት ፓርቲ ድረስ በመሳተፍ ለአስራ ሦስት ዓመታት ያህል የምችለውን አስተዋጽኦ አድርጌያለሁ። ይህ ኹነትም የፓርቲዎችን ጓዳ ፈትሼ ግንዛቤ እንዳገኝ ስላመቻቸልኝ፣ በቀጣይ ህዝባችን የፖለቲካና ሰብአዊ መብቶቹ ተከብረው ነፃነቱን እንዳያገኝ እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ የማስባቸውን ነጥቦች እንደሚከተለው ለማቅረብ እወዳለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ይድነቃቸው ከበደ (የሰማያዊ ፓርቲ የሕግ ጉዳይ ኃላፊ)ይድነቃቸው ከበደ (የሰማያዊ ፓርቲ የሕግ ጉዳይ ኃላፊ)

ነኀሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ሰማያዊ ፓርቲ ታላቅ የተቃውሞ ሠልፍ መጥራቱ የሚታወቅ ነው፤ ይሁን እንጂ በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት እንደሰፈር ጉልበታኛ ድንኳን ሰባሪ ዘው ብሎ በኃይማኖት ሰበብ ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ቀንና ሰዓት እንዲሁም ቦታ በሕግ አግባብ ሣይሆን በጉልበት ሠልፍ መሰል ሠልፍ ማካሄዱ የሚታወቅ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ፈቃዱ በቀለ

መግቢያ
በዚህ አርዕስት ላይ ለመጻፍ ከአሰብኩ ረዥም ጊዜ ሆነኝ። እንደሚታወቀው አንድ ጥናታዊ ጽሁፍ ለማቅረብ ቀላል አይደለም። የመንፈስ ርጋታን የሚጠይቅ ብቻ ሳይሆን፣ ለአንባቢ የሚቀርበው ጽሁፍ ከርስ በርስ ቅራኔዎች የተላቀቀና አሳማኝ እንዲሆን አድርጎ ለመጻፍና ለማስነበብ ረዥም ጊዜን ይፈጃል። ብዙ ዕውቀትንና ምርምርን ይጠይቃል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አብርሃ ደስታ Abreha Destaአብርሃ ደስታ ከመቐለ

የህወሓት ደጋፊዎች የአቶ አርከበ ሚና መቀነስ በአቶ አባይ ምክንያት እንደሆነ ያስባሉ። እንደኔ ግን አርከበ የተገለለው በአባይ ወልዱ ሳይሆን በመለስ ነው። መለስ ሥልጣን በጣም ከመውደዱ የተነሳ ሥልጣኑን የሚፎካከሩና አደጋ የሚደቅኑ አቅም ያላቸው የህወሓት ሰዎች ሲያርቅና ሲያጠፋ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ክንፉ አሰፋ
በተንጣለለ ቪላ ውስጥ ከበድ ያሉ እንግዶች “ጸዳ” ባሉ ምግብና መጠጦች እየተስተናገዱ ነው። ታዋቂ ግለሰቦች፤ ባለሥልጣናት እና አርቲስቶች የቀረበላቸውን ቡፌ በልማታዊ ወጋቸው እያወራረዱ ሳሉ፤ አንድ እንግዳ ነገር በመሃላቸው ተከሰተ። ሞቅ ባለው የአይቴ ነጋ ገብረእግዚአብሔር ድግስ ላይ ያልተጋበዙ ሁለት ሰዎች ዘው ብለው ከግብዣው ክፍል ገቡ። የፌዴራል ፖሊስ አባላት ነበሩ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ Journalist Temesgen Desalegnተመስገን ደሳለኝ
“በአፍሪካ ትልቁ አምባገነን” የሚል ተቀፅላ የተሰጣቸው የሊቢያው ኮሎኔል መሀመድ ጋዳፊ እና የግብፁ ሆስኒ ሙባረክ በህዝባዊው እምቢተኝነት ከሥልጣን መነሳታቸው በመሰል አገዛዞች ስር ያደሩ ሕዝቦችን ለለውጥ ማነቃቃቱ የሚጠበቅ ነው። በተለይም ከራሳቸው መንግሥት ተኳርፈው አስተማማኝ የዲሞክራሲ ተቋማትን በገነቡ የምዕራብ ሀገራት በብዛት የሚኖሩ ዜጎች ላሏት ኢትዮጵያ ንቅናቄው የፈጠረው ተመሳሳይ መነሳሳት ቀላል ባለመሆኑ ኢህአዴግን ሊወጣው ከማይችለው ቅርቃር ውስጥ ከቶታል። የዚህ ተጠየቅም ቀድሞ እንዲህ አይነት ችግሮች ሲፈጠሩ ድርጅቱ ‘እሳት ማጥፊያ’ ያደርጋቸው የነበሩ አጀንዳዎቹ ያለፈባቸው (Expired) መሆናቸውን ማሳየት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ላይ ኢህአዴግ ከተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ከአንድነት፣ ከሰማያዊ፣ ከመድረክ እና ከኢዴፓ ጋር በቴሌቭዥን ውይይት አካሂዷል። ውይይቱን ሊመለከቱት ይገባል ብለን እናምናለን። ሁለተኛውን ክፍል ቪዲዮ ከክፍል አንድ ቪዲዮ በታች ያለውን “ሙሉውን አስነብበኝ”ን በመጫን ያገኙታል። የማጫወቻ ቁልፉን በመጫን ይመልክቱ!

ክፍል ፩

ሙሉውን አስነብበኝ …

The Secret ሚስጢሩ ወለላዬ ከስዊድን
ስለተከሰተው ሚስጥርና የሚስጥሩን ቀላል መደረግ አሁን የሚጠይቁኝ አይመስለኝም። ይልቁንም አጠቃቀሙ እንዴት ነው? ይሉኝ ይሆናል። ለዚህ በክፍል ሦስት ጽሁፌ መልስ ይዣለሁ። ከዛ በፊት ግን ታላቁ መጽሐፍ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ይላል? የሚስጥሩ ተጠቃሚዎችስ ምን ይነግሩናል? ይሄን አንብበው ወደ ሚስጥሩ አጠቃቀም ይሻገሩ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ሰማያዊ ፓርቲ ቅዳሜ ጳጉሜን 2 ቀን በመስቀል አደባባይ ህዝባዊ የሰላማዊ ሰልፍ ጠራ

Ethiopia Zare (ሰኞ ነኀሴ 27 ቀን 2005 ዓ.ም. September 2, 2013)፦ እሁድ ነኀሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም. ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በዝግጅት ላይ የነበረው የሰማያዊ ፓርቲ ቅዳሜ ነኀሴ 25 ቀን ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ሲቪል በለበሱ ግለሰቦች መሪነት በፖሊሶች ጽሕፈት ቤቱን ጥሰው በመግባት አመራሮቹ መታሰራቸውንና ንብረቶች መወረሳቸውን ፓርቲው ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ግርማ ሠይፉ ማሩ
ሰሞኑን ከፀረ-አሸባሪነት ሕግ በማስቀጠል የአዲስ አበባን ከተማ ነዋሪን በተለይ ሲያምስ ከርሞ አሁንም በማመስ ላይ ያለው የመኖሪያ ቤት ጉዳይ ነው። በአዲስ አባባ የመኖሪያ ቤት ችግር እንዳለ አሌ የሚባል አይደለም። ይህ ችግር እዚህ እንዲደርስ ደግሞ ዋናው ተዋናይ መንግሥት እንደሆነ መዘንጋት የለበትም። ምክንያቱም ለቤት መስሪያ የሚሆነውን ቦታ በቁጥጥሩ ስር አድርጎ ለዜጎች እንዳይደርስ በማድረጉ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

“ከአድባይነት እርግማን ይሰውረን!”

ታክሎ ተሾመ

የኃይማኖት መሪው ቡድሐ የሚሰጠን አንድ እንቆቅልሽ የሚከተለውን ይመስላል። አንድ ነጋዴ ሩቅ ሄዶ ሲመለስ፤ ቤቱ በሽፍቶች ተዘርፎና ተቃጥሎ ይደርሳል። ከቤቱ ከተረፈው ረመጥ – መካከል አንድ ተቃጥሎ የከሰለ የሰው ገላ ያያል። “ይሄ ትንሹ ልጄ መሆን አለበት” አለ። በዚህ ምክንያት ምርር ብሎ አለቀሰ። ደረቱን መታ። ፀጉሩንም ነጨ። ገላውን እንደገና የማቃጠል፤ የሐዘን ሥነ-ስርዓት እንዲካሄድም አደረገ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተክለሚካኤል አበበ – ቶሮንቶ (ካናዳ)

በብርሀኑ ተበሳጨሁ፤ በሰማያዊ ተጽናናሁ፡ በአንድነት ደግሞ ተስፋ አደረግሁ

 

1-      ይህ ጽሁፍ ዓላማው አድናቆት፡ ትችትና ግብዣ ነው።የአንድነት ምሽትበቶሮንቶ ግብዣ። ከአድናቆትና ከግብዣው በፊት ስለፖለቲካ መሪዎችና ስለፖለቲካ ተንታኞች አትቶ፤ የብርሀኑ ነጋን (ዲባቶ) አቀራረብ ይተቻል።የሰማያዊ ፓርቲን ርምጃ ያደንቃል። የአንድነት ዘመቻን ስለማገዝ ያሳስባል። እንደው ተገጣጥሞ ነው እንጂ፤ አንዱን ለማሞገስ ሌላው መኮሰስምመከሰስም የለበትም።ግን አንዳንዴ ደግሞ፤ በጊዜ ያልተተቸ፤ ይለመዳል። አጉል ልማድ ይሆናል። ሁሉንም ለያይቶ ለመጻፍ ደግሞ፤ ጊዜ የለም። ስለዚህ ባንድ ወንጭፍ ሶስትወፍ ነው ለመማረክ የምጥረው። ከሀተታ ልጀምር።

ሙሉውን አስነብበኝ …

(ተመስገን ደሳለኝ)

“በእያንዳንዱም መንግስት የሚያድሩ ብዙ ልዩ ልዩ ነገዶች ይኖሩ ይሆናል፡፡ ስለ ሆነ መንግስት አንዱን ነገድ አጥቅቶ ሌላውን ነገድ ለመጥቀም ሥራው አይደለም፡፡ አስተካክለን ካሰብን ዘንድ መንግስት መቆሙ ለሕዝቡ ሁሉ ጥቅም ነው፡፡ ጥረቱም ህዝቡን ሁሉ በትክክል ለመጥቀም ያልሆነ መንግስት ሊቆም አይችልም፡፡ ለአንዱ ነገድ ወይም ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት ለመንግስት የሚገባ ሥራው አይደለም”

ሙሉውን አስነብበኝ …

(እየሩሳሌምአርአያ)

ለስድስት አመት ኤፈርትን ሲመሩ የቆዩት /አዜብ መስፍን ከሃላፊነት መነሳት ተከትሎ በሕወሐት ውስጥ ውጥረት መንገሱን ምንጮች አመለከቱ። የኤፈርት ቦርድ ሰብሳቢ በነበሩት ባለቤታቸው አቶመለስ አማካይነት ዳይሬክተር ተደርገው አዜብ መሾማቸውን ያስታወሱት ምንጮች፣ ከመለስ ሕልፈት በኋላ ቦታውን የተረከቡት ኤርትራዊው ቴዎድሮስ ሃጎስ መሆናቸውን፣ እንዲሁም ዳይሬክተር የመሾምና የመሻር ስልጣኑ የቦርዱ መሆኑን ያስረዳሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አባይ የህዝብ እንጂ የፖለቲካ መጠቀሚያ አይሆንም!

Ethiopia Zare (እሁድ ነኀሴ 19  ቀን 2004 ዓ.ም. August 25, 2013)የአባይ ግድብ ሂደት ግልጻማነት የጎደለውና ኢትዮጵያዊያን ያልመከሩበት አገዛዙ የፈጠረው የፖለቲካ መጠቀሚያ ነው የሚሉ ኢትዮጵያዊያን በቫንኩቨር ካናዳ የተጠራውን የግድብ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ምሽት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸው ታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ግርማ ሠይፉ ማሩ

“የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ ለምን ያስፈራል?” በሚል ርዕስ ሪፖርተር ጋዜጣ በእሑድ ነሓሴ 5 ህትሙ ረጅም ፅሁፍ አሰነበቦናል። ፀሐፊው በቦነያ ሰ. በሚል አቶ/ወሪት/ወሮ ይሁን በማይታወቅ ስም ነው ያወጡት። ይዘቱን ሳነበው የምናውቃቸው የኢህአዴግ ሹሞች በብዕር ስም ልከውት ያው የኢህአዴግ አቋም ነው ብዬ ለመውሰድ ዝግጁ ሆኜ ንባቤን ሳጠናቅቅ፤ ፀሐፉው የሕግ ባለሞያ እንዲሁም በተለያየ የመንግሥትና መንግታስዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ በሙያቸው ሰርተዋል የሚለው የአዘጋጁ ማስታወሻ መልስ እንድሰጥ ጋበዘኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ተመስገን ደሳለኝ

ኢህአዴግ ባለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት በስራ ላይ ካዋላቸው አዋጆች መካከል የ‹‹ፀረ-ሽብር ህጉ››ን ያህል ያጨቃጨቀ የለም ቢባል ከእውነቱ ብዙም አልራቀም፡፡ በርግጥ ከተቃውሞ አቅራቢው አብዛኛው በደፈናው ‹‹ህጉ አያስፈልግም›› የሚል አልነበረም፡፡ ህጉ ‹‹ሽብርተኝነት››ን የገለፀበት መንገድና አንዳንድ አንቀፆቹ ለትርጉም አሻሚ በመሆናቸው ከስርዓቱ ባህሪ አኳያ ለፖለቲካ ጥቅም የሚውሉበት ዕድል መኖሩ አይቀሬ ነው የሚል ስጋት ነበር፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

 ሉሉ ከበደ (ደራሲና ጋዜጠኛ)

ሙስሊም ወንድሞቻችን ሁለት አመት ለሚጠጋ ጊዜ እየተገደሉ ነው።  በጽናት፤ በጀግንነትና በብልሀት እናም በመስዋእትነት የመብት ትግላቸውን ቀጥለዋል። በለተ – አውዳመት ኢድ አልፈጥርም የመስዋእትነት ደማቸውን፤ …ኢትዮያን የተቆጣጠራት የትግራይ ዱር አራዊት መንጋ አፍሷል። የሞቱትን ሁሉ አላህ በጀነት ነፍሳቸውን ያኑር ከማለት በቀር ምን ይባላል ?  ለሁሉም ወገኖቻችን ለቤተሰቦቻቸው፤ ለዘመዶቻቸው አላህ ጥናቱን ይስጥ እላለሁ። በከንቱ ለፈሰሰ ደማቸውም እሱ በማያልቅበት ስልጣኑ ፍርዱን ይስጥ። ሳይውል ሳያድር።…አላህ ሁ አክባር!!!

ሙሉውን አስነብበኝ …

(ሊመለከቱት የሚገባ!)
በአማራ ክልል የሚገኙ በተለይም ወጣት ሴቶችን “ወረርሽኝ ገባ” በሚል ክትባት በመስጠት መውለድ እንዳይችሉ የማድረግ የዘር ማጥፋት ወንጀል በመንግሥት መፈጸሙ አይዘነጋም። የዚሁ ሰለባ የሆኑ ሴቶችን “የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ” ለፀበል ያሉበት ቦታ ድረስ በመሄድ ቃለምልልስ አድርጎላቸዋል። እነሆ!

The Secret ሚስጢሩ ወለላዬ ከስዊድን
የግጥም አፃፃፍ ዘዬን ያመጡ ነፍሳቸው ትባረክ። “ሚስጢሩ ቀላል ተደረገ” የሚለውን የሚስጢሩን ሁለተኛ ክፍል እነሆ! በአጭር መስመሮች ግጥም ማጠቃለል ቻልኩ። የዚህን ስራ የመጀመሪያ ክፍል ያነበቡ አስተያየት ሰጭዎች “አቀራረብህ መጽሐፉን ላነበቡ ይገባ እንደሆን እንጂ፤ ለሌላው አንባቢ ግልጽ ሊሆንለት አይችልም!” አሉኝ። ለትሁት አስተያየታቸው ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ታደሰ ብሩ
1. መንደርደሪያ

የወያኔ ሰዎች ጋር የፓለቲካ ሙግት መሰል ነገር ከገጠማቸው ውይይቱን ያለ ጥርጥር የሚረቱበት ወደሚመስላቸው ወደ “ሰላም” ጉዳይ ይስቡታል። ከዚያም አገራችን ለዘመናት ሰላም የራቃት የነበረ መሆኑን ያስቷውሷችሁና “እድሜ ለኢሕአዴግ ይኸው የሰላም አየር እየተነፈስን ነው” ይሏችኋል። ንግግራቸውን የመቀጠል እድል ካገኙ መረር ብለው “ነገር ግን ፀረ-ሰላም ኃይሎች አልተኙልንም። በሰሜን፣ በምሥራቅ፣ በአገር ውስጥ፣ በዲያስፓራ ….” እያሉ የፀረ-ሰላም ኃይሎች ረዥም ዝርዝር ያቀርቡላችኋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

አርኣያ ጌታቸው Araya Getachewአርኣያ ጌታቸው

የዘንደሮ ክረምት ከቀደምቶቹ በጥቂቱ ጠንከር ያለና ብዙዎችን በተለይም አዲስ አበቤዎችን እያማረረ ነው። ሌላው “በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” የሚያስብለው ደግሞ የከተማዋ መንገዶች በአብዛኛው ጥገና ላይ መሆናቸውና በዚህም ሳቢያ የበርካቶች መኖርያና የንግድ ሱቆቻቸው መፍረሳቸው ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

ዩሱፍ ያሲን

የአሜሪካ ድምፅና የዶቼቬሌ አማርኛ ራዲዮ ፕሮግራሞች ላይ የቁጫ ሕዝብ የራሱን ማንነት የመወሰን ጉዳይ አስመልክቶ ለመንግሥት ጥያቄ ያቀረቡ ሰዎች መታሰራቸው ዜና በቅርቡ ተዘግቦ ሰምተናል። 40 የሚሆኑ የአካባቢ ሽማግሌዎች እነዚህ የተሳሩ ሰዎችን ለማስፈታት አዲስ አባባ ድረስ መምጣታቸውንም ተዘግቦዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ …

በተመስገን ደሳለኝ
‹‹በድብልቅልቁ አምላክ››

መግቢያ
ዛሬ በስሱ ላነሳው ያሰብኩትን አ ንዳ አለቃ አፅሜ በምኒልክ ዘመን ካሳተሙት አንድያ መጽሐፋቸው ላይ ባገኘሁት ታሪክ ል ምር፤ እንዲህም ይነበባል፡- ‹‹በሸዋ መርድ አዝማች ኃይሌ፣ በሣህለ ሥላሴ አልጋ ከተቀመጡ በኋላ ከአቶ ሰይፉ ጋር ቂሙ የማይበርድ የቅድስት ኃይማኖት ጦርነት ተ መረ፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ …

 

ሉሉ ደበደ (ደራሲና ጋዜጠኛ)


አንባ ገነኖች ስልጣን ላይ የሚቆዩበት ጊዜ እየረዘመ በሄደ ቁጥር አሰራራቸውንእየገመገሙናራሳቸውንእያረሙ፤ስልጣን ላይ ለመዝለቅ ያበቋቸውን ስልቶች የበለጠ ማጠናክራቸው እንዳለ ሆኖ፤ ቆይታቸው አዳዲስ ስልቶችን ለመፍጠርና ለመሞከርእድል ይሰጣቸዋል ለምሳሌ መለስ ዜናዊ አባይን እንገነባለን  ብሎ ድንገት  እየተጯጯኽ  ህዝብን ማሯሯጥ እንደጀመረው አይነት።

ሙሉውን አስነብበኝ …

(ተመስገንደሳለኝ)

…‹‹የጣር ቀጠሮው ስንት ነው
ለሰው ልጅ ሰው ለምንለው
ላይችል ሰጥቶት ለሚያስችለው
ስንት ቀን ነው? ስንት ሌት ነው?…››
(ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ‹‹እሳት ወይ አበባ›› የግጥም መድብል)
እነሆም ለቅስቀሳ ሳይሆን፣ አንተንም እራሴንም እወቅስ ዘንድ ብዕሬን እንዲህ አነሳሁ፡- ‹‹ ገሬ መከታዬ፣ መኩሪያዬ…›› ከምትላት እናት ኢትዮጵያ ምንድር ነው የምትፈልገው? …ዳቦ፣ ማህበራዊ ፍትህ፣ ፖለቲካዊ ነፃነት፣ ቤት መስራት፣ መማር-አለመማር፣ መደገፍ-መቃወም፣ መተኛት-መነሳት፣ ፈጣሪን ማምለክ-መካድ፣ መስራት-አለመስራት፣ መምረጥ-አለመምረጥ፣ አደባባይ መዋል፣ ሰፈር መዋል፣ መደራ ት-አለመደራ ት፣ ማልቀስ-መሳቅ፣ መፃፍ፣ መናገር፣ መጮኽ-መመሰጥ፣ የግል መብት፣ የቡድን መብት?
ይህ ይሆን ዘንድ ከወዴት ትሻለህ? …ከሙት መንፈስ፣ ከውርሱ ድንዛዜ፣ ከሰማይ፣ ከምድር፣ ከፀሐይ፣ ከጨረቃ፣ ከርዕዮተ-ዓለም ወይስ….?

ሙሉውን አስነብበኝ …

 በክንፉአሰፋ

 “የአሲምባ ፍቅር” – መጽሃፍ ቅኝት
በክንፉ አሰፋ
ደራሲ፣ ካሕሳይ አብርሃ ብስራት
ብዛት፣ 446 ገጾች
በተስፋዬ ወልደዮሃንስ አዲስ አበባ ታትሞ የተሰራጨ
* ከስር በስእሉ እንደሚታየው ኢሲምባ 3250 ሜትር ከፍታ ላይ በትግራይ ውስጥ ያለ ተራራ ነው። አሲምባ በዚህ ከፍታው ሳቢያ ሌሊት ላይ በጉም ይሸፈናል። አሲምባ “ቀይ አንባ” ማለት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ …

 

ቤተክርስቲያናቸውቋሚቤተመቅደስአግኝታለች

በጥቅምት 2009 .. የብሪቲሽ ኮሉምቢያ ጠቅላይ ፍርድቤት 1990ዎቹ መጀመሪያ በሊቀካህናት ምሳሌ እንግዳ ቤተክርስቲያን ስር፡በነአቡነ ዜናማርቆስ ቡራኬ የተመሰረተውን የቫንኩቨር ቅድስት ማርያም ቤተክርትስቲያን አንስቶ ወደ ኢህአዴግ ለሚያጋድለው ስብስብ እንዲሰጥ ሲወስን፡ በስደተኛው ሲኖዶስ ስር የሚገኙ የቫንኩቨር ማርያም ልጆች አዝነው ነበር። የፍርድ ቤቱ ክርክር ሂደት በወቅቱበ ኢትዮጵያ ዛሬና በሌሎች ድረገጾች ላይ ተዘግቧል።ልምዱ ለሌሎችም ይጠቅም ዘንድ ወደፊትም እናትትበታለን።

ሙሉውን አስነብበኝ …

Normal
0

false
false
false

MicrosoftInternetExplorer4

/* Style Definitions */
table.MsoNormalTable
{mso-style-name:”Table Normal”;
mso-tstyle-rowband-size:0;
mso-tstyle-colband-size:0;
mso-style-noshow:yes;
mso-style-parent:””;
mso-padding-alt:0cm 5.4pt 0cm 5.4pt;
mso-para-margin:0cm;
mso-para-margin-bottom:.0001pt;
mso-pagination:widow-orphan;
font-size:10.0pt;
font-family:”Times New Roman”;
mso-fareast-font-family:”Times New Roman”;
mso-ansi-language:#0400;
mso-fareast-language:#0400;
mso-bidi-language:#0400;}

Normal
0

false
false
false

MicrosoftInternetExplorer4

/* Style Definitions */
table.MsoNormalTable
{mso-style-name:”Table Normal”;
mso-tstyle-rowband-size:0;
mso-tstyle-colband-size:0;
mso-style-noshow:yes;
mso-style-parent:””;
mso-padding-alt:0cm 5.4pt 0cm 5.4pt;
mso-para-margin:0cm;
mso-para-margin-bottom:.0001pt;
mso-pagination:widow-orphan;
font-size:10.0pt;
font-family:”Times New Roman”;
mso-fareast-font-family:”Times New Roman”;
mso-ansi-language:#0400;
mso-fareast-language:#0400;
mso-bidi-language:#0400;}

/መሰፍን/ማርያም

ቀደምሲል « እግዚአብሔርና እኛ» በሚለው ርዕስ ስር የተነገረውን አንዳንድ ሰዎች ሌላ ትርጉም በመስጠት ጸረሃይማኖት ሊያስመስሉት ይሞክሩ ይሆናል። አይደለምእንዲያውም ሃይማኖትንና ሃይማኖተኛነትን የሚያጸናነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ምንም ዓይነት ሃይማኖት ቢኖረው ለእግዚአብሔር ያለው ፍቅርና በእግዚአብሔርም ላይ ያለው እምነት ብርቱ ነው።ይህንን ከመገንዘብ የተነሳና በዚያው ፍቅርና እምነት ላይ የተመሠረተ ስለሆነ በምንም መንገድ ጸረ ሃይማኖት መስሎ ሊታይ አይገባም።

ሙሉውን አስነብበኝ …