በአዲስ ዓመትም ያላባራው ሰቆቃ
ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ እና ልናገረው የከበደኝ ሮሮ
ነቢዩ ሲራክ
በግልም ቢሆን አዲሱን ዓመት በሠላም እና በደስታ መቀበሌ እውነት ነው! መስከረም ጠብቶ ብዙ ቀናት ሳንቆጥር ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚደርሱኝ የስደተኛ ወገን መከራ ግን ከአዲሱ ዓመት ዋዜማ ጀምሮ እስከ መባቻው አላባራም። እያንዳንዱን የወገን ስደት ሰቆቃ መከራ ጨክኜ ከመናገር ለመቆጥብ ያደረግኩት ትግል ላንዲት ቀን ቢሳካም፤ ህሊናዬ ግን እረፍት አላገኘም። በተለይ በአዲሱ ዓመት ዋዜማ “ብሪማን” ተብሎ በሚጠራው የጅዳው ትልቅ ማረሚያ ቤት የደረሰኝ መረጃ ያማል …