ኢትዮጵያዊያኖች በቫንኩቨር ሰልፍ ወጡ
አባይ የህዝብ እንጂ የፖለቲካ መጠቀሚያ አይሆንም!
Ethiopia Zare (እሁድ ነኀሴ 19 ቀን 2004 ዓ.ም. August 25, 2013)፦ የአባይ ግድብ ሂደት ግልጻማነት የጎደለውና ኢትዮጵያዊያን ያልመከሩበት አገዛዙ የፈጠረው የፖለቲካ መጠቀሚያ ነው የሚሉ ኢትዮጵያዊያን በቫንኩቨር ካናዳ የተጠራውን የግድብ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ምሽት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸው ታወቀ።