የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ ለምን አያስፈራ?
ግርማ ሠይፉ ማሩ
“የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ ለምን ያስፈራል?” በሚል ርዕስ ሪፖርተር ጋዜጣ በእሑድ ነሓሴ 5 ህትሙ ረጅም ፅሁፍ አሰነበቦናል። ፀሐፊው በቦነያ ሰ. በሚል አቶ/ወሪት/ወሮ ይሁን በማይታወቅ ስም ነው ያወጡት። ይዘቱን ሳነበው የምናውቃቸው የኢህአዴግ ሹሞች በብዕር ስም ልከውት ያው የኢህአዴግ አቋም ነው ብዬ ለመውሰድ ዝግጁ ሆኜ ንባቤን ሳጠናቅቅ፤ ፀሐፉው የሕግ ባለሞያ እንዲሁም በተለያየ የመንግሥትና መንግታስዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ በሙያቸው ሰርተዋል የሚለው የአዘጋጁ ማስታወሻ መልስ እንድሰጥ ጋበዘኝ።