ተሸንፈን እንዳንቀር
ሉሉ ደበደ (ደራሲና ጋዜጠኛ)
አንባ ገነኖች ስልጣን ላይ የሚቆዩበት ጊዜ እየረዘመ በሄደ ቁጥር አሰራራቸውንእየገመገሙናራሳቸውንእያረሙ፤ስልጣን ላይ ለመዝለቅ ያበቋቸውን ስልቶች የበለጠ ማጠናክራቸው እንዳለ ሆኖ፤ ቆይታቸው አዳዲስ ስልቶችን ለመፍጠርና ለመሞከርምእድል ይሰጣቸዋል ። ለምሳሌ መለስ ዜናዊ አባይን እንገነባለን ብሎ ድንገት እየተጯጯኽ ህዝብን ማሯሯጥ እንደጀመረው አይነት።