የግፉዓን ዕድሜ ምን ያህል ይረዝማል?

(ተመስገንደሳለኝ)

…‹‹የጣር ቀጠሮው ስንት ነው
ለሰው ልጅ ሰው ለምንለው
ላይችል ሰጥቶት ለሚያስችለው
ስንት ቀን ነው? ስንት ሌት ነው?…››
(ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ‹‹እሳት ወይ አበባ›› የግጥም መድብል)
እነሆም ለቅስቀሳ ሳይሆን፣ አንተንም እራሴንም እወቅስ ዘንድ ብዕሬን እንዲህ አነሳሁ፡- ‹‹ ገሬ መከታዬ፣ መኩሪያዬ…›› ከምትላት እናት ኢትዮጵያ ምንድር ነው የምትፈልገው? …ዳቦ፣ ማህበራዊ ፍትህ፣ ፖለቲካዊ ነፃነት፣ ቤት መስራት፣ መማር-አለመማር፣ መደገፍ-መቃወም፣ መተኛት-መነሳት፣ ፈጣሪን ማምለክ-መካድ፣ መስራት-አለመስራት፣ መምረጥ-አለመምረጥ፣ አደባባይ መዋል፣ ሰፈር መዋል፣ መደራ ት-አለመደራ ት፣ ማልቀስ-መሳቅ፣ መፃፍ፣ መናገር፣ መጮኽ-መመሰጥ፣ የግል መብት፣ የቡድን መብት?
ይህ ይሆን ዘንድ ከወዴት ትሻለህ? …ከሙት መንፈስ፣ ከውርሱ ድንዛዜ፣ ከሰማይ፣ ከምድር፣ ከፀሐይ፣ ከጨረቃ፣ ከርዕዮተ-ዓለም ወይስ….?

ሙሉውን አስነብበኝ …