የመቅደላው ዮሐንስ እሸቴ በሎንዶን
ይመኩ ታምራት ከሎንዶን
መቶ አርባ-አምስት ዓመት ያስቆጠረውን መቅደላን ስናነሳ መቼም ዓፄ ቴዎድሮስና ታላቁ ጀብዷቸው፤ ሮበርት ናፒዬር እና እንግሊዞች በሀገራችን ላይ ያካሄዱት ከ’ግዳጅ ወሲብ’ ጋር የማይተናነስ ደፈራ እና ብዝበዛ፣ የነደጃች ካሣ ምርጫ ሴራ፤ የልጅ ዓለማየሁ መሰደድና በለጋ ዕድሜው ከሀገርና ከዘመድ ተለይቶ ሳለ የሕይወቱ በአጭሩ መቀጠፍ፣ ወ.ዘ.ተ. ይታወሱናል። ስለዚያ ወቅት ታሪክ በጥልቀት ለሚያጠና፣ አያሌ መጻሕፍትና ማስታወቻዎች፤ አብዛኞቹ በነጮቹ፣ አንዳንድም በኛው ሰዎች ተጽፈው በታሪክ ማኅደር ውስጥ ይገኛሉ።