በ19 ዓመቴ ወልጄው፣ ጠፍቶ፣ ሞቷል ያልኩትን ልጄን አገኘሁት
ፍቅሬ ቶሎሳ ጅግሳ (ዶ/ር)
ውድ አንባብያን ሆይ! የምሥራች! የምሥራች ስላችሁም በሀገራችን ባህል አጸፋውን “ምስር ብላ!” በሉኝ። ልቤን ወደ ሰማይ እያዘለለ፣ እግሮቼን ጮቤ የሚያስመታ ነገር ሰሞኑን ገጥሞኛልና። እሱውም ከአያሌ ከዘመናት በፊት ዕድሜዬ 19 ሳለ የወለድኩት ልጄ፣ ያውም የበኹር ልጄ፣ ጠፍቶብኝ “በቃ! ሞቷል፣ ተከቷል!” ብዬ እርሜን አውጥቼ እያዘንኩ እኖር ነበር።