የጋራ ንቅናቄው ከሰማያዊ ፓርቲ ጎን ይቆማል
Ethiopia Zare (ቅዳሜ ጳጉሜን 2 ቀን 2005 ዓ.ም. September 7, 2013)፦ ባለፈው ቅዳሜ ነኀሴ 25 የፌዴራል ፖሊስና የደኅንነት አባላት የሰማያዊ ፓርቲን ጽ/ቤት ጥሰው በመግባት የፈጸሙት ተራ የውብንድና ተግባር ብቻ ሳይሆን የህወሓት/ኢህዴግን ማንነት በግልጽ ያሳየ ለመሆኑ ከማንም በላይ ተግባሩ ራሱ ምስክር ነው በማለት ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ድርጊቱን ኮነነ።