“ኢትዮጵያ ከ2ኛ የዓለም ጦርነት በኋላ የተፈጠረች ሀገር ናት!”
ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
የባሰ አታምጣ! ነው የሚባለው። መቼም የኤርትራ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋዜጣዊ መገለጫ በሰጡ ቁጥር ግርግር ሳይፈጥሩ፤ ጎረበት አገር በውስጠ ወይራ ሳይጎነትሉ፤ ምዕራባውያን መንግሥታት ግልጽና በማያሻማ ቋንቋ ሳይወርፉና ሳይዘነጥሉ፤ ብዙሐን ፈገግ ሳያሰኙ፤ በአንጻሩ ደግሞ የተማረውን ክፍል ሳያስለቅሱና እርር ድብን እስኪል ድረስ ሳያደርጉ አልፉ ማለት ዘበት ነው።