አወይ ሶሪያ – የኢትዮጵያ ጠላት

ሰሎሞን ተሰማ ጂ.
የሶሪያ ጉዳይ ከዕለት ወደ ዕለት እየከፋ መጥቷል። በስልጣን ላይ ያለው ጎሳ “የአላዊት ጎሳ” ይባላል። አላዊቶችና በደዊኖች በሽፍትነትና በባህር ላይ ውንብድና ስማቸው የገነኑ ናቸው። በደዊኖች፣ ሶሪያን ለዘመናት ያህል ሲፈልጧትና ሲቆርጧት ኖረዋል። እንደነሱ ዘረኛ፣ እንደበደዊኖች ጠባብ፣ አክራሪና ቁመኛ ታይቶም-ተሰምቶም አይታወቅም። አላዊቶችም ቢሆኑ “አልሸሹም ዞር አሉ” ናቸው።