የሥልጠናና የሰው ሀብት ልማት ፖሊሲው ከአፈጻጸም መመሪያው ጋራ ተዘጋጅቷል የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ ጥናታዊ ውይይቱ ተጠናቀቀ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን÷ ከአድልዎና ሙስና የጸዳ፣ ሥርዐተ እምነትዋን የሚጠብቅ፣ መንፈሳዊ ዕሴቶችዋን የሚያንጸባርቅ፣ ሞያዊ ብቃትን ማዕከል ያደረገ፣ ዘመኑን የዋጀና የተቀላጠፈ አሠራር እንዲኖራት ያስችላል የተባለ ሁለገብ የማሠልጠኛ ማእከል ለመገንባት የፕሮጀክት ጥናቱን አጠናቅቃ ማዘጋጀቷ ተገለጸ፡፡ በአዲስ አበባ ዙሪያ ካሉት የኦሮሚያ ወረዳዎች …

የቤተ ክርስቲያንን ንብረት በመሸጥ የሚታወቁት የ‹ቅሬታ› አቅራቢ ነን ባዮቹ ዋነኛ አስተባባሪ መልአከ ገነት ኃይሌ ኣብርሃ፣ በቅርቡ በ1.3 ሚልዮን ብር በገዙትና ለቻይና ተቋራጭ ባከራዩት ሲኖ ትራክ መኪና ብቻ በወር ብር 70,000 ገቢ ያገኛሉ፤ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አስተዳደራዊ ለውጥ ለማምጣት የተነሡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተንገላቱበት የግንቦት ፳፻፩ ዓ.ም. ጥቃት የተሳተፉትና ሞዴል ፴ በማቃጠል የሚታወሱት ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ …

እሁድ ታህሳስ 13/2006

በግፍ እስር ላይ የሚገኙትን ጀግኖቻችንን ንጽህና ለመመስከርና የህዝበ ሙስሊሙ ድምጽ መሆናቸውን በህግ ፊት በተጨባጭ ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በጀግኖቻችን ጠበቆች አማካኝነት እየተደረገ ያለው ይኸው ጥረት በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ሲሆን ኮሚቴዎቻችን መንግስት ከለጠፈባቸው የሀሰት ውንጀላ ፍጹም የጸዱ መሆናቸውን በፍርድ ቤት ቀርበው የሚመሰክሩ ሰዎችን የማሰባሰቡ ሂደትም የፍቃደኝነት ፎርም በማስሞላት መልክ የተጀመረ መሆኑ ታውቋል፡፡

መሪዎቻችን በተለያዩ ህዝባዊ መድረኮች ላይ ህዝበ ሙስሊሙን በሰላማዊ አካሄድ ላይ አደራ ያሉባቸው በርካታ ንግግሮቻቸው በማስረጃነት እንዲውሉ ለማድረግ እንዲሰባሰቡ እየተደረገ ሲሆን በተለይ በመጀመሪያዎቹ የአወሊያ ፕሮግራሞች እና በኋላም በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች በተደረጉት የሰደቃና የአንድነት ፕሮግራሞች ላይ የተቀዱት የድምጽና የምስል ማስረጃዎች መሰባሰባቸው በዚህ ረገድ እጅግ ጠቃሚ መሆኑ ታውቋል፡፡

መሪዎቻችን በመሳጂዶች ላይ ከተደረጉት ፕሮግራሞች በተጨማሪ በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ በመቅረብ ሲያደርጓቸው የነበሩ ንግግሮችና የህዝበ ሙስሊሙን ሰላማዊና ግልጽ ጥያቄዎች ለማብራራት ቃለ መጠይቅ የሰጡባቸው የራዲዮ ፕሮግራሞች፣ ጋዜጦች፣ መጽሄቶችና ሌሎችም የሚዲያ ውጤቶች በጠበቆች አማካኝነት እየተሰባሰቡ መሆኑ ተዘግቧል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ ለህዝብ ድምጽ በመሆናቸው ብቻ መንግስታዊ የሀሰት ፍረጃ ሰለባ የሆኑትን መሪዎቹን ንጽህና ለማረጋገጥ እስከጥግ ድረስ መልፋት ያለበት ሲሆን በመንግስታዊ ተጽእኖ ስር በወደቀው የፍርድ ሂደትም ውስጥ ቢሆን የመሪዎቻችንን ንጽህና ለመመስከር ከምንጊዜውም በላይ ቆርጦ በመዘጋጀት የሚከፈለውን ሁሉ መስዋእትነት መክፈልም በትከሻው ላይ ያረፈ ሀላፊነት መሆኑ እሙን ነው!

ድምጻችን ይሰማ!

የአ/አ ሀ/ስብከት፣ የክፍላተ ከተማ ጽ/ቤቶች፣ የልማትና በጎ አድራጎት ተቋማት፣ ደረጃ አንድና ሁለት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት የቅድሚያ ተጠቃሚ ይኾናሉ ለመንበረ ፓትርያርክ ማእከላዊ የፋይናንስና በጀት አስተዳደር መሠረት የሚጥል ነው ምእመናን ለሚከፍሉትና ለሚሰጡት ገንዘብ ደረሰኝ የመጠየቅ ልማድ ሊኖራቸው ይገባል ድብቅ ሙዳየ ምጽዋት ማስቀመጥ፣ በዣንጥላና በምንጣፍ ገንዘብ መለመን ይከለከላል (አዲስ አድማስ፤ ታኅሣሥ ፲፪ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ …

ዛሬ ዐርብ ታኅሣሥ ፲፩ – ፲፪ የሚካሄደውን የልደታ፣ አዲስ ከተማና ቂርቆስ ክፍላተ ከተማ አብያተ ክርስቲያን ልኡካን የሚሳተፉበትን ጥናታዊ ውይይት መስተንግዶ የማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም ካቴድራል እና የመርካቶ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን፤ ከታኅሣሥ ፲፫ – ፲፬ የሚካሄደውንና የቦሌ ክፍለ ከተማ አብያተ ክርስቲያን የሚሳተፉበትን ጥናታዊ ውይይት ደግሞ የቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል ስፖንሰር ለማድረግ በየሰበካ …

ሀ/ስብከቱ ከኑሮ ውድነት አንጻር በአጥቢያዎች ተሳትፎ እያስጠናው የሚገኘው ጊዜያዊ የደመወዝ ጭማሪ ማስተከከያ ጥናት በመዋቅር፣ አደረጃጀትና ዝርዝር አሠራር መመሪያ ረቂቅ ውስጥ ካለው የአብያተ ክርስቲያናት ደረጃ መስፈርት፣ የሥራ መደብ ግምገማ፣ የአገልጋዮች ጥቅምና ጫና ጥናት ጋራ አንዳችም ግንኙነት የለውም፡፡ ለፊርማ አቤቱታው የቀረቡት ጥያቄዎች ይዘት ‹ተቃዋሚዎቹ›÷ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ከቃለ ዐዋዲ ደንቡ ጋራ ያለውን ልዩነትና በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ላይ …

‹‹በነበረው ሒደት በተለያየ ምክንያት የበደላችኹንን ኹሉ ይቅር ብለናችኋል›› (በጋሻው ደሳለኝ፣ ኅዳር ፳፱ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.፤ ለሐዋሳ ደ/ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ምእመናን የተናገረው) ‹‹ይኼ ጉልበት ላይ መውደቅ፣ ይቅርታ መጠየቅ በፍጹም እንዳያደርገው፡፡ ጉልበት ላይ መውደቅ፣ ይቅርታ መጠየቅ ማለት ጥፋተኛ ነኝ፤ ተሸማቅቄ እኖራለኹኝ ማለት ነው፤››   (በጋሻው ደሳለኝ፣ በግንቦት ፳፻፬ ዓ.ም. የክብረ መንግሥት ግብረ አበሮቹን ሲመክር) ይቅርታ ጠያቂ ሳይኾን …

በዕርቀ ሰላም ሒደቱና መግለጫው ስለ በጋሻው ደሳለኝ የተጠቀሰ ነገር የለም የምእመናን ተወካዮች በጋሻው ይቅርታ እንዲጠይቅ የተሰጠውን ፈቃድ ተቃውመዋል በጋሻው ደሳለኝ ይቅርታ የመጠየቁን ፈቃድ እንዲያገኝ በፓትርያርኩና በቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤቱ ላይ የክልል እና ፌዴራል ግለሰብ ባለሥልጣናት ጫና መደረጉ ተጠቁሟል የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የሲዳማና ጉጂ ቦረና አህጉረ ስብከት ልኡክ ዛሬ፣ ኅዳር ፳፱ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. የዕርቀ ሰላም …

ዕርቀ ሰላሙን በሚያወርደው የሁለቱም ወገኖች ስምምነት መሠረት ከኅዳር ወር ፳፻፫ ዓ.ም. ጀምሮ ከሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ተለይተው ‹‹ወንዲታ›› በተባለው የግለሰብ ስቱዲዮ ውስጥ ሲሰበሰቡ የነበሩ ምእመናን÷ በሰንበት ት/ቤት፣ በስብከተ ወንጌል እና በልማት ኮሚቴዎች ውስጥ የመሳተፍና የማገልገል መብታቸው ይጠበቅላቸዋል፡፡ በዚህም መሠረት በሰንበት ት/ቤቱ አመራርና በስብከተ ወንጌል ኮሚቴ ሁለት፣ ሁለት፤ በልማት ኮሚቴ ውስጥ ደግሞ በሰበካ ሳይወሰኑ …


ወያኔ የካደው እና ግንቦት ሰባት የተነፈሰው የእንደራደር ጥያቄ የአናጎሜዝን የአዲስ አበባ ቆይታ ተከትሎ የወጣ ጉዳይ ነው::

Image

ምንሊክ ሳልሳዊ :-ይህን ሰሞን በሃገር ውስጥ እና በውጪው ሃገር ኢትዮጵያውያን ዘንድ የመወያያ ርእስ የሆነው እና ይየወያኔ ካድሬዎችን ቀልብ የገፈፈው እና ከሰል ያለበሳቸው ወያኔ ለግንቦት ሰባት ያቀረበው የድርድር ጥያቄ ነው::በስፋት አሁንም እየተከራከሩበት ያለው ይህ ጉዳይ አገሩን በጡዘት አምሶት የሃገሪቱ የፖለቲካ ሂደት አንድ ተስፋ የሰጠ ሁኔታ እንደሚታይ እየተተነበየ ነው::

ወያኔ በእርግጥ በማይጥም የፖለቲካ እሰጥ አገባ የተጠመደ ቢሆንም የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ለላውን ከማዘናጋት ውጪ ምንም አይነት ፋይዳ እንዳሌለው እና ራሱን እየፈተሸ እንደሆነ ያጋለጠ ጉዳይ ነው:: የድርድር ጥያቄ አላቀረብኩም ያለው ወያኔ እንደለመደው ከኦነግ ከኦብነግ ከሻእቢያ ጋርም እየተደራደረ ጥያቄውን እራሱ እያቀረበው ሲክድ የቆየ ሲሆን በቅርቡ እንኳን በኬንያ ከኦብነግ በጀርመን ከሻእቢያ ጋይ ያደረጋቸውን ድርድሮች እየታከካቸው አልፏል::

ወያኔ የካደው እና ግንቦት ሰባት የተነፈሰው የእንደራደር ጥያቄ የአናጎሜዝን የአዲስ አበባ ቆይታ ተከትሎ የወጣ ጉዳይ ነው:: በእርግጥ በተለያዩ ጊዜያት ለወያኔ እና ለግንቦት ሰባት የቅርብ ርቀት የሆኑ ሰዎች ይህንን ጉዳይ በግል አንስተውት የሆነ ቢሆንም ባይሆንም ግን የአና ጎሜዝ የአዲስ አበባ ምላስ ተከትሎ ግንቦት ሰባት ለህዝብ ይፋ ያደረገው ጉዳይ አሁንም ሚዛኑ ወደ ግንቦት ሰባት እንዲሆን አድርጎታል::

እንቅልፍ የነሳቸው የወያኔ ባለስልታናት የቀን ተቀን የስብሰባ መቀመጫቸው ግንቦት ሰባት ነው:; በወታደሩ በደህንነቱ እና በታማኝ ካድሬው ዙሪያ ውይይቱ ምስጢሩ ግንቦት ሰባት ነው:: እነዚህ የሚስጥር ተወያዮች እንደሚጠቁሙት ሲሰበሰቡ በውይይት ወቅት ግንቦት ሰባትን አሸባሪ ብለው አይጠሩትም:; አሸባሪ የሚለውን ቃል የሚጠቀሙት ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታቸው አደባባይ ላይ መሆኑን በይፋ የተረጋገጠ መረጃ ይጠቁማል::
በቅርቡ ከአባቱ ሻእቢያ ጋር ጀርመን ላይ የተወያየው ወያኔ ግንቦት ሰባት የራስ ምታት ስለሆነበት እንዲያደራድረው አሊያም እንዲገላግለው ተማጽኖ ቢሆንስ??? ወይኔ ሻእቢያ የሚፈልጋቸውን ተቃዋሚ ኤርትራውያንን እያፈነ እንደሚሰጥ የህን ሰሞን ሃተታዎች እየጠቆሙ ነው እንዲሁም በሱዳን በኩል እያሽከረከረም እንደሚያስረክብ::ነገሩ የጨነቀው እርጉዝ ያገባል አይነት ነው ….
የአቶ ታምራት ላይኔም ወደ ፖለቲካው ለመቀላቀል ማቆብቆብ እኮ የዚሁ የድርድር አንዱ አካል ነው:; ብኣዴን ታምራት ላይኔን ይፈልገዋል:: አገሬ በፈለገችኝ ሰአት ለማገልገል ተዘጋጂቻለሁ የሚለው ታምራት ጠጋ በል እየተባል መሆኑስ የወያኔ አንድ የጭንቀት ምልክት አይደል?! … ወደ ሚዲያዎች አያሰገገ መምጣቱ ሌላ ምስጢር የለውም::

አና ጎሜዝ ከአዲስ አበባው ቆይታቸው ሁለት ንግግሮችን ከአንደበታቸው ሰምተናል:: አንዱ “ከባለስልጣናት ጋር ያደረኩት ውይይት በጎ እና ገንቢ ነው መልካም ምላሽ እንዳገኙም በእርካታ ተናግረዋል:; በመተማመን ስሜት ደሞ “አዲስ ንፋስ አለ” ሲሉ ተስፋቸውን አብርተዋል:: ይህንን የፖለቲካ ስሜታቸውን ያልተረዱ የደፈናው ጋዜጠኞች የወያኔን የሞተ እስትንፋስ ሊያበረቱ ቢሞክሩም የሚሳካ ካለመሆኑም ሌላ ወያኔም …ጌታ….ተላላኪ…;;እያለ ቢዘላብድም ታምኝነት ሊያገኝ አልቻለም:: አና ጎሜዝ ይህንን ሲናገሩ ከባለስልጣናት አንደበት የሰሙት እና የተላኩት መልእክት እንዳለ ይጠቁማል:: አና ጎሜዝ ወደ ግንቦት ሰባት ብቻ ሳይሆን ለተለያዩ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን የለውጥ ጠያቂዎችም የብሄራዊ ድርድርን ጉዳይ አስረግጠው አዋይተዋል:;በእርግጥ ስለግንንቦት ሰባት ባያነሱም ይህ የእንደራደር ጥያቄ የመልስ ምቱን ወያኔ ለማወቅ ፈልጎ ያደረገው ሊሆን የሚችል የማጭበርበሪያ የፖለቲካ ስልት ቢሆንም የድርድሩ ጥያቄ ግን የአና ጎሜዝን የአዲስ አበባ ቆይታ እና የአዲስ ነፋስ ምልክታን ተከትሎ መነገሩ እውነታውን ያጎላዋል:; ይህ የሚያሳፍረው ወያኔን ቢሆንም ወያኔ ግን ምንተእፍረቱን አይኑን በጨው አጥቦ ቢክድም አሁንም ግንቦት ሰባትን እንዲያደራድሩት ከትን እንዲያደበጀርባ እየተለማመጠ እንደሚገኝ ለማስገንዘብ እወዳለሁ:: #MinilikSalsawiምንሊክሳልሳዊ

(ሪፖርተር፤ ኅዳር ፳፮ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.) ኄኖክ ያሬድ የኢትዮጵያው የመስቀል ክብረ በዓል በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ዩኔስኮ አስታወቀ፡፡ ዩኔስኮ የመስቀል ክብረ በዓልን (Commemoration feast of the finding of the True Holy Cross of Christ) በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ኅዳር 25 ቀን ይፋ ያደረገው፣ በኢንታንጀብል (መንፈሳዊ) ባህላዊ ቅርሶች ጥበቃና ክብካቤ ላይ የሚሠራው ኮሚቴው ስምንተኛውን ጉባኤ እያካሄደባት ካለው የአዘርባጃኗ …

ለጥናታዊ ውይይቱ÷ ካህናት፣ የአብነት መምህራን፣ መዘምራን፣ ሰባክያነ ወንጌል፣ የሰንበት ት/ቤት ተጠሪዎች እና ምእመናን የሚወከሉበት ቁጥር ተወስኗል፡፡ የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች÷ ተሳታፊዎቹ በአገልግሎት ድርሻቸው እና በተወሰነላቸው ቁጥር መሠረት መወከላቸውን የማረጋገጥ ሓላፊነት ተጥሎባቸዋል፡፡ ሀ/ስብከቱ የተሳትፎ ጥሪ ያስተላለፈበትን ደብዳቤ በማፈንና የተለያዩ ሰበቦችን በመደርደር ጥናታዊ ውይይቱን ለማኮላሸት አሻጥር የሚሠሩ የለውጡ አደናቃፊዎች (አንዳንድ አስተዳዳሪዎችና ጸሐፊዎች) በጥንቃቄ ተለይተዋል፤ በጸጥታ አካሉ […]

የኑሮ ውድነት 40% ይጨምራል የሚል ጥናት ለጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ቀረበ::
በሃገሪቱ የኢኮኖሚ ውንብድና ተስፋፍቷል::
የስራ አጦች መስፋፋት ሃገሪቱን የወንጀል መናኸሪያ እያደረጋት ነው::

የኢሕኣዴግ ኢኮኖሚስቶች በወረደላቸው መመሪያ በጋራ እና በተናጠል ባደረጉት ጥናት መሰረት በአገሪቱ በተለይ በከተሞች አከባቢ የኑሮ ውድነት በ40% ይጨምራል ሲሉ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የፖሊሲ ጥናት ቡድን የጥናት ሪፖርታቸውን ያቀረቡ መሆኑን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ተናግረዋል::

የጥናት ሪፖርቱን ያቀረቡት የወያኔው ኤክስፐርቶች መንግስት የኢኮኖሚ ፖሊሲ በድጋሚ እንዲፈተሽ እና ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ሲያሳውቁ በአገሪቱ የተንሰራፋው የሙስና እንቅስቃሴ ዋነኛው የኢኮኖሚው ማነቆ ከመሆኑም በላይ የፍትህ እና የንግድ ስርኣቱ መላሸቅ የኢኮኖሚ ቁጥጥሩን ስላላው ለዋጋ ንረቱ መንስኤ ናቸው ብለዋል::መንግስት ለግሉ ዘርፍ ያለው አመለካከት ደካማ መሆኑ እና ከፖለቲካ ባለስልጣናት ጋር ቁርኝት ያላቸው ነጋዴዎች ለመክበር የሚያደርጉት ሩጫ የህዝቡን የኑሮ ውድነት ጣራ እንዲነካ አድርገውታል::እንዲሁም የኢኮኖሚ ውንብድና በሃገሪቱ ላይ እየተፈጸመ ነው::የስራ አጦች ቁጥር መጨመር ሃገሪቱን የወንጀለኞች መናኸሪያ እያደረጋት ነው::

በአላቂ እቃዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ንረት ይከሰታል በሃገር ውስጥ ምርቶች ላይም ከፍተኛ የሆነ ጭማሪ በሚቀጥለው አንድ አመት ይመጣል ያለው ጥናት የግሉ አምራች ዘርፍ ጥሬ እቃዎችን ወደ ሃገር ውስጥ በሚያስገባበት ጊዜ የተወሰነ የቀረጥ ክፍያ አለመኖሩ እና የመንግስት ባለስልጣናት እንዳሰኛቸው በየጊዜው እየቀያየሩ የህገር ውስጥ ምርቶች እንዲጎዱ የማኑፋክቸሪውም ዘርፍ እንዲዳከም በማድረግ ችግር እንዲፈጠር አድርገዋል::

ጥናቱ የባንኮችን መዳከም የስራ አጥነትን የስደትን የፖለቲካ ተጽእኖን የህዝቡን አስተያየት እና የገበሬውን ምሬት አጠቃሎ የያዘ መሆኑ የጠቆሙት ምንጮቹ መንግስት በሞኖፖል ንግዱን ይዞታል የውጪ ዜጎች ህገወጥ የኢኮኖሚ ስርኣት ዘርግተዋል ከፍተኛ ብዝበዛ በሃገሪቱ ምጣኔ ሃብት ላይ እየተደረገ ነው የሚሉ ዝርዝር ጥናቱን አቅርቧል:: ጥናቱ ይፋ ለውይይት ይቅረብ አይቅረብ የሚለው ገና ያልተወሰነ ሲሆን የጥናቱን ዝርዝር መረጃው ከምንጮቻችን እንደደረሰን የምናቀርበው መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን::

በእስራኤል ሃገር በአቶ ፋሲል ለገሰ የሚመራው IETV ወይንም ሁለተኛው ETV ሲመሰረት አላማው ኢትዮ-እስራኤሎችን በሙሉ ልቡ ህብረተሰብ ነክ ችግሮችን በማካተት ለህብረተሰቡ ይጠቅማሉ ብሎ ዓላማ ያደረጋቸውን ለምሳሌ፤- እኛ ኢትዮ-እስራኤሎችን እንዴት ከሰለጠነው ህብረተሰብ ጋር ማቀራረብ እንዳለበት እንዲሁም ባህላችንና ቋንቋችን ለ እስራኤል ህብረተሰብ በቀላሉ እንደ ድልድይ ሁኖ ለማገልገል በ እስራኤል መንግስት አመታዊ በጀት ተመድቦለት ጣቢያው አየር ላይ ከዋለ እንሆ ሦስት አመታትን አሳልፏል።
Image
ነገር ግን ዓላማውን ስቶ ለኢትዮጵያ መንግስት ፕሮፖጋንዳነት በማዋል ጭራሽ የኢትዮጵያን አምባሳደር በየሳምንቱ እያቀረበ ስለ ኢትዮጵያ “ግምታዊ” እድገት ስለ አምስት አመቱ ትራንስፎርሜሽን ስለአባይ ግድብ እና ግንቦት 7 የአሸባሪ ቡድን እንደሆነ እነሱን ከቀረብን የኢትዮጵያ መንግስት ለፍርድ እንደሚያቀርበን ፡እንደነዚህ አይነት ገደብ የለሽ ፕሮግራሞች ይቀርቡልናል ። አቶ ፋሲል ለገሰ በመጀመሪያ ይህን አስተሳሰብዎትን መቀየር መቻል ይኖርቦታል። አንድ ህብረተሰብ ወስዶ እንደህፃን ልጅ ዋ.. ብሎ የሚያስፈራሩባት ያሻዎትን የሚያደርጉበት ኢትዮጵያ አይደለችም ። እስራኤል ዲሞክራሲያዊና ፍትሃዊ ሃገር ውስጥ ነው ያለነው፡ ምንም እንኳን የፓርቲው ደጋፊና አቀንቃኝ እንደሆኑ የታወቅ ቢሆንም ጋዜጠኛ በሚለው ሙያ ላይ ጋዜጠኛ ለመባል ከሚያስፈልጉት ነገሮች ውስጥ ትንሾችን ለማድረግ ይሞክሩ።

ስለዚህ እኔ በግሌ የምሰጥዎት አስተያየት ቢኖር ነገሩ ለኢትዮ-እስራኤላውያን በቅቷል ። ይመለሱና ህብረተሰቡን ቃል በገቡበት መሰርት ያገልግሉ አዎ ህብረተሰቡ ከኢትዮጵያ ፖለቲካ አያገባህም ከተባለ እስዎም አያገባዎትም ። ወይንም ለሁሉም የኢትዮጵያ ፖለቲካ ድርጅቶች እና ፓርቲዎች በእኩልነት አገልግሎት ይሰጥ።

የፊታችን ታህሳስ 3 የእምዬ ምኒልክን 100ኛ እረፍት በሰማያዊ ፓርቲ አዘጋጅነት እንደሚዘክር የታወቀ ነዉ፡፡ በፕሮግራሙ ላይም በርካታከሀገር ዉስጥና ከዉጪ ሀገር ምሁራን ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ይገኛሉ ተብሉ ይጠበቃል፡፡ የፕሮግራሙ አዘጋጅ ሰማያዊ ፓርቲ ለዝግጅቱ በሚያስፈልጉ ጉዳዩች ላይ ስራ እየሰራ ይገኛል! በስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ አዋጅ መሰረትም ስብሰባ እንደሚያደርግ ለስብሰባና ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ደብዳቤ በትናንትናዉ እለት ያስገባ ሲሆን ዘሬ በደብዳቤ የተመለሰዉ መልስ እጅጉን አስቂኝና አጠያያቂ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡

Image

በደብዳቤዉ ላይ ለምታደርጉት ስብሰባ እዉቅና ልነሳጥችሁ አንችልም ምክንያቱም የፖሊስ ጥባቃ መመደብ አንችልም የሚል ነዉ፡፡ የሚገርመዉ ደግሞ የፅፈት ቤቱ ሀላፊ ተብዬዉ አቶ አሰግድ በንቀት ደግሞ ማናችሁና ምኒልክ ምናምን የምትሉት ደግሞ ምኒልክ ማነዉ በሚል በእብሪት የመለሰዉ መልስ ነበር፡፡

እንኳን ድንኳን ጥሎ ለመሰብሰብ ይቅርና ጎዳና ሙሉ ህዝብ በመላበት የሩጫ የሰልፍ መሰል የገዢዉ ፓርቲ መልካም ፈቃድ ያገኙ ፕሮግራሞች ከህዝቡ እኩል ፌደራል ፖሊስ ለጥበቃ እንደሚታዘዝላቸዉ እየታወቀ ፤ በሌላ መልኩም በድፍረት እንወጣለን ብለን በተለያየ ምክንያት በተጠሩ ሰልፎች ላይ ለድብደባ የሚላከው ቁጥር ስፍር የሌለዉ የፀጥታ ሀይል አሁን ምን ቢውጠው ነዉ የጥበቃ የሚሆን የሰዉ ሀይል ልናስተባብር አንችልም ስለዚህ ዝግጅታችሁን እዉቅና አንሰጠዉም መባሉ??? ይህ ከእብሪት በላይ ምን ሊሆን ይችላል!!!?

ያም ሆነ ይህ ዝግጅቱ በታቀደለት ምልኩ እንደሚፈፀም በተለመደ ቁርጠኝነት ላይ ነን! ሲፈልጉ ለጥበቃ የከለከሉትን ሀይል ለድብደባ ይላኩት!!! እኛ የምንዘክራቸዉ ፍርሃት ካልፈጠረባቸዉ ሞተዉም መንፈሳቸዉ ካልተለየን እምቢ ባይ አባቶቻችን ተወልደናል፡፡
ድል ለኢትየጵያ ህዝብ!!!

‹‹ስደተኞችን በእንግድነት ተቀብለን እየተከባከብን አኑረናል፤ ሸኝተናል፡፡ እኛ ስደተኞች ኾነን እየተደበደብንና እየተገደልን መገኘት የለብንም፤ አይገባንም›› /ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ/ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሳዑዲ ዓረቢያ በመመለስ ላይ ለሚገኙ ወገኖች ማቋቋሚያ የሚኾን የሁለት ሚልዮን ብር ጊዜያዊ ርዳታ አበረከተች፡፡ ትላንት፣ ኅዳር ፳፬ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ከቀትር በፊት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ በተጠራ ጉባኤ ላይ …

ከአስተዳዳሪው ጋራ የጥቅም ግንኙነት ያላቸው የቅ/ላሊበላ ደብር ሰበካ ጉባኤ አባላትና የአስተዳደር ሠራተኞች፣ ለመኪና ‹ሽልማቱ› ከግማሽ ሚልዮን ብር በላይ (በአንዳንድ ምንጮች መረጃ እስከ ብር 800,000) ከደብሩ ካዝና ወጪ ማድረጋቸው ተጠቁሟል፡፡ ‹‹መነኩሴ ቢሸለም መስቀል እንጂ መኪና ምን ያደርግለታል?›› የሚሉ የቅ/ላሊበላ ደብር ካህናትና ምእመናን፣ ‹‹አባ ገብረ ኢየሱስ በሕግ መጠየቅ እንጂ ሽልማት አይገባቸውም›› በሚል ኅዳር ፲፮ ቀን ፳፻፮ ከቀትር …

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሕግ አገልግሎት መምሪያ ዋና አማካሪ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኾነው ተሾሙ፡፡ በዛሬው ዕለት የሀ/ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኾነው የተሾሙት ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ÷ በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ በነበሩበት ከ፲፱፻፺፫ …

የለውጡ ቀንደኛ ተገዳዳሪዎች፣ ‹‹ጠላቶች ነበርን፤ ዛሬ የሰማነውና ያየነው ጥናት ግን መልካም ኾኖ አግኝተነዋል፤›› ሲሉ ራሳቸውን ሒስ አድርገዋል፤ ‹‹ቤተ ክርስቲያኒቱ የተወለደችው ዛሬ ነው፤›› ሲሉም የመዋቅርና አሠራር መመሪያ ጥናቱን አድንቀዋል፤ ጥናታዊ ውይይቱ በላቀ የለውጥ መነሣሣት ቀጥሏል፤ ከፍተኛ አመራሩ የተሳተፈበት የቀዳማይ ዙር ጥናታዊ ውይይት መርሐ ግብር ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡

ጥናቱ – እያንዳንዳቸው ከ50 – 122 ገጾች ያሏቸውን 15 የፖሊሲና ማኑዋል አርእስተ ጉዳዮችን ያካተተ መኾኑ ተገልጦአል፡፡ ከእነርሱም መካከል፡- የሰው ሀብት አስተዳደር፣ የሰው ኃይል ልማት፣ የፋይናንስ፣ የኦዲትና ኢንስፔክሽን፤ የዕቅድ፣ ክትትልና ግምገማ፤ የግዥ፣ ሽያጭና ንብረት አስተዳደር፤ የኢንቨስትመንትና ምግባረ ሠናይ፤ የቅርስና ቱሪዝም፤ የመንፈሳዊ ፍትሕ፣ የአስተዳደር እና የሥራ ክርክር ጉዳዮች ችሎቶችን የተመለከቱ ፖሊሲዎች፣ መመሪያዎችና ዝርዝር አሠራሮች ይገኙበታል፡፡ ዛሬ፣ ኅዳር …

የሥራ ተቋራጩ በ2 ዓመት ጊዜና በ3 ሚልዮን ብር ወጪ ግንባታውን አጠናቅቆ ማስረከብ ነበረበት፤ ይኹንና የሥራው መጠን ከ65 በመቶ በላይ ባልተራመደበትና ከውለታ ጊዜው ውጭ ለ6ኛ ዓመት በዘገየበት ኹኔታ አላግባብ በቀረበ የተቋራጩ የይገባኛል ጥያቄ ከብር 8 ሚልዮን በላይ ወጪ መከፈሉ ተጠቁሟል፡፡ ቋሚ ሲኖዶስ መስከረም ፰ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት÷ በ3 ሚልዮን ብር በ2 ዓመት ጊዜ […]

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በሥራ አስኪያጁ ላይ የተላለፈውን የስንብት ርምጃ ውድቅ በማድረግ ወደ ሓላፊነታቸው እንዲመለሱ ለሊቀ ጳጳሱ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡ ይኹንና ትእዛዙ በ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ዘንድ ተቀባይነት አግኝቶ ተፈጻሚ ባለመኾኑ በአሜሪካ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጋራ በሐዋርያዊ ጉብኝት ላይ የሚገኙት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ እየተጠበቁ ነው፡፡ ራሳቸውን ‹‹የሊቀ ጳጳሱ የግል አማካሪ›› ብለው …

(ፋክት መጽሔት፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፲፱ ጥቅምት ፳፻፮ ዓ.ም.) ተመስገን ደሳለኝ … ኢሠፓ መራሹ መንግሥት በኢሕአዴግ ከተተካ ጥቂት ወራት ቢያልፈውም፣ የተራዘመው የእርስ በርስ ጦርነት ያልደረሰባቸው በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙ አንዳንድ ከተሞችን ገና በቅጡ አልተቆጣጠራቸውም፤ በአናቱም በኢሠፓ መንግሥት ሽንፈት ሳቢያ እንዲበተን ከተገደደው የአገሪቱ መደበኛ ወታደር አብዛኛው ከእነትጥቁ የትውልድ መንደሩንና ቤተሰቡን መቀላቀሉ በአገሪቱ ላይ ከባድ ፍርሃት አንብሯል፡፡ በሰላም …

እ.አ.አ በ፲፱፻፵፯ ዓ.ም. በአሥመራ ከተማ ተወልደው የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአሥመራ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጅማ ተከታትለዋል፡፡ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን ከአሥመራ ዩኒቨርሲቲ በሕግ አግኝተዋል፡፡ ከ፲፱፻፸፪ – ፲፱፻፸፬ ዓ.ም በአሥመራ ዩኒቨርሲቲ ያስተማሩት ፕሮፌሰር ተከሥተ በሎንዶን ዩኒቨርሲቲ ከ‹‹ስኩል ኦቭ ኦሪየንታል ኤንድ አፍሪካን ስተዲስ›› ሁለተኛ ዲግሪ ያገኙ ሲኾን የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ከስዊድን ኡፕሳላ ዩኒቨርስቲ በታሪክ ትምህርት ሠርተዋል፡፡ ፕሮፌሰሩ ዛሬ ታትሞ ከወጣው አዲስ …

ለ10 ዓመታት (ከ፲፱፻፸፬ – ፲፱፻፹፬ ዓ.ም.) በስደት ለ15 ዓመታት (፲፱፻፹፬- ፲፱፻፺፱ ዓ.ም.)  በሐዋርያዊ አገልግሎት ቆይተውበታል፡፡ በግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ድጋፍ በኒውዮርክ ከተመሠረተውና የጃማይካ ተወላጆች ከሚገኙበት የኒውዮርክ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ቀጥሎ የመጀመሪያውን የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በዋሽንግተን ዲሲ (መካነ ሕይወት መድኃኔዓለም) አቋቁመዋል፡፡ የገለልተኛ አብያተ ክርስቲያን መዋቅርንና የሁለተኛ ሲኖዶስ ምሥረታን በመቃወም የእናት ቤተ ክርስቲያን …

የለውጥ አመራር ሂደቱን የሚያስቀጥል ዋና ሥራ አስኪያጅ ይፈለጋል የአዲስ አበባ ሀ/ስብከትን የዋና ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በጊዜያዊነት የሚመሩ ሓላፊ ተመደቡ፡፡ ሓላፊነታቸውን በድንገት ለቀው ወደ አሜሪካ ባቀኑት መጋቤ ሐዲስ ይልማ ቸርነት ምትክ የተመደቡት ጊዜያዊ ሓላፊ የክህነትና መንፈሳዊ ፍትሕ ዋና ክፍል ሓላፊ ንቡረ እድ አባ ዮሐንስ ገብረ ሕይወት ናቸው፡፡ የንቡረ እድ አባ ዮሐንስ ገብረ ሕይወት ጊዜያዊ ሓላፊነት እስከ …

ግምገማውን ተከትሎ የዋና ሥራ አስኪያጅ ሹመትና መዋቅራዊ ለውጡን ለማደናቀፍ በተለያዩ የመቀስቀሻ አጀንዳዎች አሉባልታ ሲነዙ፣ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያንን ለአድማ ሲቀስቀሱ በቆዩ ሓላፊዎች ላይ የሚወሰዱ ርምጃዎች ይጠበቃሉ፡፡ ለዋ/ሥ/አስኪያጅ ሹመት÷ በጎጠኝነትና በጥቅመኝነት የማግባባት እንቅስቃሴ እየተካሄደ ነው፤ ወደ ረዳት ሊቀ ጳጳሱ እና ወደ ፓትርያርኩ የጳጳስና የባለሥልጣን አማላጅ የላኩ፣ የድጋፍ ፊርማ በማሰባሰብ የተጠመዱም አሉ፤ ከብር 6.7 ሚልዮን በላይ በኾነ የገቢ …

ቅ/ሲኖዶስ ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪካዊነትና ቀዳሚነት እውነታውንና ትክክለኛውን የሚገልጽ ጽሑፍ እንዲዘጋጅ መመሪያ ሰጠ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት ለምልአተ ጉባኤው ስብሰባ የሰጠው ሽፋን ‹‹የጉርሻ ያህል ነው›› በሚል ተነቀፈ ‹‹ጉባኤው አገር አቀፍ ብቻ ሳይኾን ዓለም አቀፍም ነው፤ የምንሰጠው ትምህርት ነው፤ የምንወድቀው የምንነሣው ስለ ሀገር ጉዳይ ነው፤ ቤተ ክርስቲያን በዐይን የሚታይ በእጅ የሚጨበጥ ታሪክ ነው …

በአገልግሎት ጥራት /በሰው ተኮር ነፍስ የማዳን አገልግሎት/ ምእመናንን ማብዛትና ማጽናት፣ ቤተ ክርስቲያንን ከባይተዋርነትና ጠባቂነት ወደነበራት ሚና መመለስ፣ አስተምህሮዋን ከማይቃረኑ ጋራ ዓለም አቀፍ አጋርነትን በማጠናከር የሰላምና አንድነት ተምሳሌት ማድረግ፣ ለሙስና ችግሮች በንስሐ መንገድ መፍትሔ ማበጀት የቤተ ክርስቲያናችን ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ማሕቀፍና ቊልፍ ጉዳዮች ኾነዋል፡፡ በቡድን እየተደራጁ የመንግሥትን ወቅታዊ አጀንዳዎች በአሉታዊ መንገድ የሚጠቀሙ አሉባልተኞችና ሙሰኞች እንዲሁም በቤተ ክህነቱ …

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው፣ ጥቅምት ፳ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም ዘጠነኛ ቀን የቀትር በፊት ውሎው የኤጲስ ቆጶሳትን ምርጫ የሚያስፈጽም አስመራጭ ኮሚቴ ሠየመ፡፡ አስመራጭ ኮሚቴው ስድስት ሊቃነ ጳጳሳት በአባልነት የሚገኙበት ሲኾን የትግራይ፣ ወሎ፣ ጎንደር፣ ጎጃም፣ ሸዋና ኦሮሚያ አህጉረ ስብከትን በመወከል የተመረጡ ናቸው፡፡ በዚህም መሠረት÷ ከትግራይ ብፁዕ አቡነ፣ ከወሎ የደቡብ ወሎ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ፣ …

የአቡነ ጢሞቴዎስ ዐምባገነንትና የኮሌጁ ጉዳይ ምልአተ ጉባኤውን ሲያወያይ ዋለ ሊቀ ጳጳሱ በበላይ ጠባቂነት ተወስነው የሽግግር ዋና ዲን እንዲሾም ሐሳብ ቀርቧል የኮሌጁ ሥራ አመራር ቦርድ ዛሬ ለምልአተ ጉባኤው ማብራሪያ ይሰጣል የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ከእናት ቤተ ክርስቲያን መዋቅር ወጥተው በገለልተኛ አስተዳደር ለሚመሩ አብያተ ክርስቲያን የአንድነት ጥሪ ሊያስተላልፍ ነው፡፡ ምልአተ ጉባኤው በትላንት፣ ጥቅምት ፲፱ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም ውሎው …

ምልአተ ጉባኤው አስመራጭ ኮሚቴ እንደሚሠይም ይጠበቃል፤ አስመራጭ ኮሚቴው ተሿሚ ዕጩ ኤጲስ ቆጶሳትን ይጠቁማል፡፡ በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ ፲፰ በተደነገገው መሠረት በአስመራጭ ኮሚቴው በዕጩነት ተመርጠው ከቀረቡት ቆሞሳት መካከል በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ ፭ ቁጥር ፺ – ፺፭ እንደታዘዘው ተሿሚ ዕጩ ኤጲስ ቆጶሳት በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በድምፅ ብልጫ ይመረጣሉ፤ ተወዳዳሪዎች ያገኙት ድምፅ እኩል ከኾነ ዕጣ የወጣለት ቆሞስ ኤጲስ […]

የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ በአጀንዳነት ተይዟል፤ ዐሥር አህጉረ ስብከት ተለይተዋል፡፡ በተጭበረበረ የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃና የዶክትሬት መመረቂያ ጥናትን አስመስሎ መቅዳት/plagiarism/ ክሥና ወቀሳ እየቀረበባቸው የሚገኙት፣ ሓላፊነትን በተገቢው ኹኔታ ባለመወጣትና በትጋት ባለመሥራት የተገመገሙት ዶ/ር አባ ኃይለ ማርያም መለሰ፣ በከባድ እምነት ማጉደል በተቀሰቀሰባቸው የካህናትና ምእመናን ተቃውሞ ከቅ/ላሊበላ ደብር አስተዳዳሪነት የሚነሡት አባ ገብረ ኢየሱስ መኰንንና የመሰሏቸው ቆሞሳት ከታሳቢ ዕጩዎች መካከል …

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በመጀመሪያው ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባው ስለሚያተኩርባቸው ጉዳዮች ዛሬ፣ ጥቅምት 13 ቀን 2006 ዓ.ም. ጥዋት በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በቅዱስነታቸው መግለጫ መሠረት ምልአተ ጉባኤው÷ ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋት ምእመናንን ስለ መጠበቅና ማብዛት፣ የቤተ ክርስቲያንን የትምህርት ተቋሞች በጥራትና አደረጃጀት በመለወጥ ከመማርና መሠልጠን አልፎ መከራን ለመቀበል የተዘጋጁ ላእካነ ወንጌልን …

‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ የአንድነት ምልክት የኾነች ሐዋርያዊት፣ ጥንታዊት፣ ብሔራዊትና ሉዓላዊት ናት፡፡ ትላንት የነበረችው ቅድስት ተዋሕዶ ሃይማኖት ዛሬም አትለወጥም፡፡ ቤተ ክርስቲያን አንዲት ናት፡፡ በመንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቷ ሕዝቡን አንድ አድርጋ ትቀጥላለች፡፡›› ‹‹ከፍተኛው የቤተ ክርስቲያን ባለሥልጣን ቅዱስ ሲኖዶስ ነው፡፡ በካህናትና ምእመናን ላይ ሁሉ ሥልጣኑ ይሠራል፡፡ ውሳኔው ይግባኝ የለውም፡፡›› ‹‹የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ ለእምነታችንና ለቤተ ክርስቲያናችን ዋስትና የሚሰጥ …

ከ29 ሚልዮን ብር በላይ የበጀት ጥያቄ ለቅ/ሲኖዶስ ቀርቧል የ49 አህጉረ ስብከትን 800 ወረዳዎች ይሸፍናል ከ21,680 በላይ የሰው ኃይል ይሳተፍበታል አጽንዖት ተሰጥቶ እንዲሠራበት አጠቃላይ ጉባኤው በጥብቅ አሳስቧል የአህጉረ ስብከት የስታቲስቲካዊ መረጃዎች አያያዝ ጥራት አሳሳቢ ኾኗል ‹‹የምእመናን ምዝገባ ለቤተ ክርስቲያን ያለው ጠቀሜታ ከመለካት በላይ የኾነ ወሳኝ ተግባር እንደኾነ የጉባኤው አባላት ተረድተናል፡፡ ያለንን አቅም በማቀናጀት በቀጣዩ ጊዜ በጥራት …

የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ጉዳዩን በጥብቅ ይነጋገርበታል በመንግሥት ባለሥልጣናት ስለሚፈጸሙ በደሎች ከአህጉረ ስብከት የሚቀርቡ አቤቱታዎች የፍትሕ አካሉን አፋጣኝ ውሳኔ ያገኙ ዘንድ ቅ/ሲኖዶሱ ግፊት እንዲያደርግ አጠቃላይ ጉባኤው ዐደራ ጥሎበታል አህጉረ ስብከት ያቀረቧቸውን የአስተዳደር፣ የፍትሕና የጸጥታ አካላት በደሎችና ተጽዕኖዎች አጣርቶ መፍትሔ የሚሰጥ÷ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ ከሃይማኖት ተቋማት ጉባኤና ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የተውጣጣ ኮሚቴ እንዲዋቀር አጠቃላይ ጉባኤው በአቋም መግለጫው …

ነገ በሚጠናቀቀው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ፴፪ኛ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ‹‹የሃይማኖት መቻቻል›› በሚለው መርሐ ግብር ‹‹የብዝኃነት አያያዝ፣ አክራሪነት/ጽንፈኝነት ዝንባሌዎቹና መፍትሔዎቹ›› በሚል ርእስ አቶ ገዛኸኝ ጥላሁን፣ አቶ ታዴዎስ ሲሳይ እና አቶ ጣሰው ገጆ በተባሉ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሦስት ከፍተኛ አማካሪዎችና ባለሞያዎች ጽሑፍ መቅረቡና ውይይት መካሄዱ ተዘግቧል፡፡ በውይይቱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ከየአህጉረ ስብከታቸው ተጨባጭ ኹኔታ …

ከጥቅምት ፬ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ እየተካሄደ የሚገኘውና ሦስተኛ ቀኑን ያስቆጠረው ፴፪ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ በዛሬው ዕለት ከቀትር በኋላ በነበረው ውሎ የተለየ ክሥተት አስተናግዷል፡፡ ‹‹የሃይማኖት መቻቻል›› በሚል ርእስ በ፴፪ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ በተካሄደው ውይይት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ባለሥልጣናት ጋራ በተለይም በመቻቻልና […]

የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ÷ በጉባኤው አዘጋጆችና ተሳታፊዎች የተለመደ አነጋገር÷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከእግር እስከ ራሷ በአንድ አዳራሽ የምትገኝበት ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ ዓመታዊ ስብሰባው÷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዓለም አቀፍ ጉባኤ ነው፡፡ ይኸውም ቤተ ክርስቲያናችን በውጭ እና በሀገር ውስጥ ካሏት የመንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት መንፈሳውያን አስተዳደር ጉባኤያት ተመርጠው የተወከሉ …

ከጉጂ ቦረናና ሊበን ዞኖች ሀገረ ስብከትና ሌሎች አብያተ ክርስቲያን በዘረፉት ገንዘብ ‹‹ሺበሺ›› በሚለው አስከፊ የሙስና ስያሜ የሚታወቁትና በነፍስ ግድያ ወንጀሎች የሚጠረጠሩት አቡነ ሳዊሮስ የሚያስተባብሯቸው የግብር አምሳሎቻቸው፣ መልአከ ገነት አባ አፈ ወርቅ ዮሐንስ እና መልአከ ገነት አባ ዮናስ ታደሰ ዋነኛ ተጠያቂዎች ይኾናሉ ተብሏል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንን ‹‹የዐፄ ምኒልክ ሥርዐት እንዲመለስና የዐፄ ምኒልክ ባንዴራ እንዲሰቀል የሚፈልጉ ናቸው›› ብለው …

    የቃለ ዐዋዲው ድንጋጌ በፍርድ ቤቶች ያለው ተቀባይነት ማነስ ያስከተለው ችግር፣ ልዩ እምነት ያላቸው አንዳንድ የመንግሥት ባለሥልጣናት በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚያደርሱት ሕገ መንግሥቱን የጣሰ ተጽዕኖ፣ ወደ ዐረብ አገሮች እየሔዱ እምነታቸውን ወደ እስልምና የሚለውጡ ኦርቶዶክሳውያን ቁጥር መበራከትና ከእኒህም የካህናት ሚስቶች መኖራቸው፤ የአብነት ት/ቤቶች ህልውና ቀጣይነትና በተለይም የመጻሕፍተ ሊቃውንት ጉባኤያት በብዛት መታጠፍ፤ የመንፈሳዊ ኮሌጆች አስተዳደር፣ የደቀ …

(አዲስ አድማስ፤ ቅጽ 13 ቁጥር 716፤ ጥቅምት ፪ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ በጥቅምት ወር አጋማሽ በሚያካሂደው የመጀመሪያ መደበኛ ስብሰባው፣ ስለ አዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ጉዳይ በመምከር የምርጫ ኮሚቴ ሊሠይም እንደሚችል ተጠቆመ፡፡ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንጮች ለአዲስ አድማስ እንደጠቆሙት፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ቀኖና መሠረት የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ የሚፈጸመው በሕገ …

ዕርግና፣ ሕመምና ኅልፈት፣ የአህጉረ ስብከት በተደራቢነት መያዝ በመነሻነት ተጠቅሷል ከ17 በላይ አህጉረ ስብከትና የሥራ ቦታዎች ክፍተት አለባቸው የተሻለ ድርጅት ላላቸው ዘጠኝ አህጉረ ስብከት ቅድሚያ ተሰጥቷል የአካባቢ ቋንቋ ችሎታ ከዐበይት መመዘኛዎች አንዱ ኾኗል የዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳት ሢመት በልደት በዓል ሰሞን ሊፈጸም ይችላል ክሥ/ነውር ነቀፋ ያለባቸው ቆሞሳት በዕጩነት እንዳይካተቱ አስግቷል በስምዖናዊነት ለመሾም ያሰፈሰፉ ‹ቆሞሳት› በማግባባት ዘመቻ ተጠምደዋል …

በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ከሠላሳ ዓመታት በላይ አገልግለዋል ‹‹በጌቴ ሰማኔ፣ በጎልጎታ፣ በዴር አብርሃም ሁሉ ሰፊ ይዞታ እንዳለን በታሪክ ሰፍሯል፡፡ ግብር ለመገበር አቅም ስላነሰን ዴር አብርሃምን ግሪኮች ወሰዱብን፤ ቤተ ልሔም ያለውን ርስታችንን አርመኖች ወስደውታል፤ በዚያ ላይ ያለንን መረጃ በሙሉ ቀደም ሲል አርመንና ግብጾች ወስደው አጥፍተውታል፡፡›› ‹‹ግብጾች በጣም ነው የሚከራከሩት፡፡ በዴር ሡልጣን ጉዳይ ግብጾች ያቋቋሙት ትልቅ ኮሚቴ አላቸው፡፡ […]

(ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ፤ 19ኛ ዓመት ቁጥር 255፤ ነሐሴ 16 – ጳጉሜ 5 2004 ዓ.ም) ዲ/ን ታደሰ ወርቁ* ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንድ መንግሥታዊ አካላት የወጡ ሰነዶችና የሚሰሙ ንግግሮች ማኅበረ ቅዱሳንን የኦርቶዶክስ ክርስትና ሃይማኖት አክራሪዎች ማንጸርያ አድርጎ የመውሰድ አዝማሚያዎች እየታዩ ነው፡፡ ይህን የተሳሳተ አቻ ፈጠራ አፅራረ ቤተ ክርስቲያን የራሳቸውን ፍላጎት ሲያራግቡበት ይታያል፡፡ ተከታዩ ጽሑፍ መንግሥት አቋሞቹን የገለጸባቸውን …

በቤተ ክርስቲያናችን ዐውደ ምሕረት ሰፍነውና በቢሮክራሲዋ ውስጥ ተሰግስገው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄን ለሚያራምዱ ድርጅቶች ተልእኮ አስፈጻሚና የቅስቀሳ ኃይል የኾኑ ሕገ ወጥ ቡድኖችና ግለሰቦች የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለመመከት በኦርቶዶክሳዊ ቀናዒነትና በበጎ ፈቃድ ተሰባስቦ በጥቅምት ወር ፳፻፫ ዓ.ም አገልግሎቱን የጀመረው የፀረ – ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ሰባክያንና ዘማርያን ጥምረት÷ ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ወቅታዊ ጉዳዮችን የገመገመበትንና ቀጣይ የአገልግሎት አቅጣጫዎችን የተለመበትን የግማሽ ቀን …

ቋሚ ሲኖዶሱ የሚያጤነውን የአካዳሚክና አስተዳደር ዲኖች ሹመት አጽድቀዋል የመምህራኑ የመብራትና ውኃ አገልግሎት ከተቋረጠ አንድ ወር ሊሞላው ነው ደመወዛቸው እንደታገደ ነው ከሥልጣናቸው ተገልለው እንዲቆዩ በተወሰነባቸው ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ እየተመራ ያለው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አስተዳደር÷ በሕንጻ እድሳት አመካኝቶ በኮሌጁ ቅጽር የሚኖሩ መምህራን ቤቶቻቸውን ለቀው እንዲወጡ ያስተላለፈው ትእዛዝና ቤቶቹን ካለቀቃችኹ በሚል በመምህራኑ ደመወዝ ላይ የጣለው እገዳ ውድቅ …