በአዲስ አበባ እና በሐረር ከተሞች ከ310 ያላነሱ የተወረሱ የቤተ ክርስቲያኒቱ ቪላ ቤቶችና ሕንፃዎች አልተመለሱም፤ ለተመለሱት ቤቶችና ሕንፃዎች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ለማውጣት የተያዘው ዕቅድ በተሟላ ኹኔታ ተሳክቷል፡፡ ለቤተ ክርስቲያኒቱ የተመለሱት 16 ሕንፃዎች፣ 12 መጋዘኖች፣ 110 ቪላ ቤቶች ዓመታዊ የኪራይ ገቢ ከ23 ሚልዮን ብር በላይ ደርሷል፤ የኪራይ ተመን ማስተካከያ ለማድረግ ጥናት እየተካሔደ ነው፡፡ የኢሕአዴግ ዋና ጽ/ቤትን ጨምሮ …

በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ሰብሳቢነት የተመራው ኮሚቴ በ80 አንቀጾችና በ99 ገጾች አዘጋጅቶ ያቀረበው የ፲፱፻፺፩ ዓ.ም. ሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ ረቂቅ የተጠናቀቀው፣ ምልዓተ ጉባኤው በሰጠው አስተያየትና ባደረገው ማስተካከያ መሠረት ከአርቃቂ ኮሚቴው ጋራ ሠርቶና አሟልቶ ለቀጣዩ ስብሰባ የሚያደርስ የሊቃነ ጳጳሳት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና የሕግ ምሁራን ኮሚቴ በማቋቋም ነው፡፡ *** የፓትርያርክ እንደራሴ ምደባ እንዳስፈላጊነቱ ሲሠራበት የቆየ መኾኑን በመጥቀስና ለወደፊቱም …

የቅዱስ ሲኖዶሱን የአመራር፣ የአስተዳደር፣ የቁጥጥርና የመወሰን ብቃት ያግዛሉ የቅዱስ ሲኖዶሱን አካላት ለማቀናጀትና አሠራራቸው ጥንካሬ እንዲኖረው ያስችላሉ ምልዓተ ጉባኤው በአጭር ጊዜ የሚይዛቸው በርካታ አጀንዳዎች የተጠና ውሳኔ ያገኛሉ የኦዲትና ኢንስፔክሽን አገልግሎት ተጠሪነት ለቅዱስ ሲኖዶሱ ይኾናል (አዲስ ጉዳይ፤ ቅጽ ፰ ቁጥር ፪፻፲፮፤ ግንቦት ፳፻፮ ዓ.ም.) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመጨረሻውና ከፍተኛው የሥልጣን ባለቤት ለኾነው ቅዱስ ሲኖዶስ÷ ቤተ …

‹‹የፓትርያርኩን ሥልጣን ይገድባል›› በሚል ተተችቷል ‹‹አመራራቸውን በብቃት እንዲያከናውኑ የሚያግዝ ነው›› /የሕግ ረቂቁ/ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ የሚያስተላልፉት በብሔራዊ ቋንቋ ብቻ ይኾናል (አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፫ ቁጥር ፯፻፵፰፤ ግንቦት ፱ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፣ ፓትርያርኩ የተጣለባቸውን አባታዊ ሓላፊነትና መንፈሳዊ አመራር በሚጠበቀው ብቃትና ደረጃ ለማከናወን እንዲችሉ የሚያግዝ እንደራሴ እንደሚመደብ በሚገልጽና …

(ሎሚ መጽሔት፤ ቅጽ ፫ ቁጥር ፻፮፤ ከግንቦት ፰ – ግንቦት ፲፬ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.) ሎሚ፡- እንደሚታወቀው እርስዎ በቤተ ክህነት አካባቢ ብዙ አስተዋፅኦዎችን አበርክተዋል፡፡ ከዚህ አንጻር በቤተ ክህነቱ አካባቢ ብዙ ተደማጭነት አልዎት ይባላል፡፡ ቤተ ክህነት ስላለችበት ኹኔታና ከማኅበረ ቅዱሳን ጋራ ተያይዞ ስለሚነሡ ‹‹ወሬዎች›› የሚሉን ነገር ካለ? ኢ.ር ታደለ፡- ቤተ ክህነታችን ወደድንም ጠላንም ማንም ምን ይበል የኢትዮጵያ …

ዛሬ፣ ረቡዕ ግንቦት ፮ ቀን የሚጀመረው የ፳፻፮ ዓ.ም. የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ኹለተኛ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ የመክፈቻ ሥርዓተ ጸሎት በትላትናው ዕለት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተካሒዷል፡፡ ከቀኑ ፲ ሰዓት ጀምሮ በተከናወነው በዚኹ የመክፈቻ ሥርዓተ ጸሎት፣ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ ከሀገር ውስጥና ከውጭ አህጉረ ስብከት የተሰበሰቡ ከሠላሳ በላይ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ተገኝተዋል፤ …

ፓትርያርኩ ዛቻ ያሰሙበትን ድንገተኛ ስብሰባ ያስተባበሩት የፅልመታዊው ቡድን ቀንደኞች እነንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ፡- ‹‹ቅዱስ አባታችን አይዞዎት፤ እኛ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ እንድንገኝ መድረክ ይፍጠሩ፤ እስከ መጨረሻው እንታገላለን›› በማለት አጋርነታቸውን ገልጸውላቸዋል፡፡ የቅ/ሲኖዶሱ ጽ/ቤት የፓትርያርኩ አካሔድ የምልዓተ ጉባኤውን ውሳኔ እንደሚጋፋ በመጥቀስ የተቃወማቸው ሲኾን የጠቅ/ቤተ ክህነቱ ዋ/ሥራ አስኪያጅም ለኹለት ዓመት የዘገየው የደንቡ ማሻሻያ ረቂቅ በመጪው ምልዓተ ጉባኤ ጸድቆ …

‹‹ግለሰቦቹ ጉዳዩን ፖለቲካዊ በማድረግ ከተጠያቂነት ለማምለጥ እየተሯሯጡ ነው›› /የደብሩ አስተዳደር/ ላልተጠናቀቀው ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ወጪ የተደረገው 8 ሚሊዮን ብር የተጋነነ ነው ተብሏል (ኢትዮ – ምኅዳር፤ ቅጽ፪ ቁጥር ፷፮፤ ረቡዕ ሚያዝያ ፳፱ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.) በሚሊዮን የሚቆጠር የምእመናን ገንዘብ ለብክነትና ዘረፋ እንደተዳረገበት የተጠቆመው የድሬዳዋ ቅዱስ ገብርኤል ደብር ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ግንባታና ሒሳብ እንዲመረመር ከቅዱስ ሲኖዶስ የተላለፈውን …

የክልከላው መንሥኤ ‹‹የሥልጣን ተዋረድንና የዕዝ ሰንሰለትን ባልተከተለ መልኩ በቀጥታ የአድባራትንና የገዳማትን አስተዳዳሪዎችና ሠራተኞች እንዲሁም በቤተ ክርስቲያኒቱ ዙሪያ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ስብሰባ መጥራት›› የሚል ነው፡፡ ለጥናታዊ ጉባኤው የተጠሩት የገዳማትና አድባራት አለቆች ቤተ መዘክር ያላቸው ሦስት አብያተ ክርስቲያን ብቻ መኾናቸውን የገለጹት የጉባኤው አስተባባሪዎች በበኩላቸው÷ ለቤተ ክርስቲያን አባቶች፣ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ባለድርሻዎች፣ ምሁራንና እንግዶች ጥሪ የተደረገው ዕቅዱና አስፈላጊነቱ ለብፁዕ ዋና …

የአቡነ ማትያስ የመነጋገርና የመደራደር አቅም ለጉብኝቱ መሰረዝ በምክንያትነት ተጠቅሷል የግብፁ ፓትርያርክ በስድስት ወራት ውስጥ ሦስት ጊዜ የጉብኝት ጥያቄ አቅርበዋል የአቡነ ታዎድሮስ ተደጋጋሚ ውትውታ ጉዳዩ ከሕዳሴው ግድብ ጋራ መያያዙን አመላክቷል የጉብኝቱ መሰረዝ በአቡነ ታዎድሮስ ጥያቄ እንደኾነ መዘገቡ ከመቅለል መጥቅለል እንዲሉ ነው ‹‹መንግሥት የግብፆችን ያህል ቤተ ክርስቲያኒቱን የዲፕሎማሲው አካል አላደረገም›› (ፋክት፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፵፫፤ ፳፻፮ ዓ.ም.) …

ውይይቱ ቀጣዩ የአሰላለፍ ስልትና የምት አቅጣጫ የሚወሰንበት ሊኾን ይችላል ተሳታፊዎች ፍረጃዎችንና ክሦችን በመረጃና በሐሳብ የበላይነት ማጋለጥ ይገባቸዋል (አፍሮ ታይምስ፤ ቅጽ ፩ ቁጥር ፯፤ ማክሰኞ እና ረቡዕ፤ ሚያዝያ ፲፬ – ፲፭ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.) ገዥው ግንባር ኢሕአዴግ በሃይማኖት ይኹን በማንኛውም ሽፋን የሚደረግን የፖሊቲካ ግጭት ለመመከት በሚል በአዲስ አበባ በተለያዩ አደረጃጀቶች ውስጥ ከታቀፉ አባሎቹ ጋራ ውይይት በማካሔድ …

ቅዳሴው በቤተ መንግሥት ደብረ ገነት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ይከናወናል ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ‹‹ከኹለት ጊዜ በላይ›› በጸሎተ ቅዳሴ አገልግለውበታል የግብጽ ፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎች በትንሣኤ ሌሊት ጸሎተ ቅዳሴ ላይ ተሳተፉ (ቅጽ ፩ ቁጥር ፯፤ ማክሰኞ እና ረቡዕ፤ ሚያዝያ ፲፬ – ፲፭ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.) ከዕለተ ሢመታቸው አንሥቶ ኢአማኒ (non-believer) እንደኾኑ በተለያዩ ሚዲያዎች ሲነገርባቸው የቆዩት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር …

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያየ አህጉር የምትኖሩ፣ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችኹ፣ በሕመም ምክንያት በየሆስፒታሉ ያላችኹ፣ እንዲኹም የሕግ ታራሚዎች ኾናችኁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ፤ እርሱ ሕያው ኾኖ ሕያዋን መኾናችንን በትንሣኤው ላበሠረን ለጌታችን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሣኤ እንኳን በሰላም …

በመኾኑም ታጋዮቹ የመንግሥትነት ሥልጣንን ሲቆናጠጡ ቤተ ክርስቲያንን የማጥቃት የቀደመ ሕልማቸውን አሐዱ አሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ከዚህ ቀደም ይዛ የነበረውን መሬት መንጠቅ፣ በግፍ የተነጠቀቻቸውን ቤቶችና ሕንፃዎች አሟልቶ አለመመለስ፣ ቤተ ክርስቲያኗ በማኅበረ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በተለይም የማስታረቅና ግጭቶችን በሰላም የመፍታት ተልእኮዋን በመንጠቅ አዲስ ለተመሠረቱት ፖሊቲካዊ ማኅበራት መስጠት፤ ከዚኽም ባሻገር ከትጥቅ ትግል አንሥቶ በስለላና በሌሎች ተግባራት ህወሓትን ሲያገለግሉ የነበሩ ‹‹ታጋይ …

(አዲስ ጉዳይ፤ ቅጽ ፰ ቁጥር ፪፻፲፪፤ ሚያዝያ ፳፻፮ ዓ.ም.) ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እስከ አሁን በታተሙ ቅዱሳት መጻሕፍትም ኾነ ለጥምቀት በታተሙ ካኔቴራዎች ላይ በኤፌሶን ፬÷፬ ላይ ያለው ጥቅስ ከነመገኛው ተጠቅሶ ከመታተሙ በቀር አንድ ሀገር የሚል የለውም፡፡ ከእውነታ አንጻር ይህን ጥቅስ መጥቀስ በራሱ ስሕተት ነው፤ የሌለን ነገር እንዳለ አድርጎ ማቅረብ ነውና፡፡ ‹‹ጥቁር ድመትን በጨለማ ውስጥ መፈለግ አስቸጋሪ …

ማኅበሩ ትውልዳዊ ተልእኮውን ለአባቶች በመታዘዝና በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በመወሰን የመፈጸም አሠራሩና ፍላጎቱ እንደጸና መኾኑንና ከዚኽ ውጭ በሌላ መንገድ የሚመጣ መፍትሔ ይኖራል ብሎ እንደማያምን የሥራ አመራር ጉባኤው አስታውቋል፡፡ መንግሥት አካሒዳለኹ ከሚለው የፀረ አክራሪነት ትግልና ቤተ ክርስቲያኒቱ በቅዱስ ሲኖዶስ ወስና የአፈጻጸም አቅጣጫ ከሰጠችበት የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ አፈጻጸም ጋራ በተያያዘ በተለያዩ አካላት የሚሰነዘሩበትን የስም ማጥፋት ዘመቻዎችና መሠረተ ቢስ …

በማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ በአክራሪነት የተፈረጁት ‹አንዳንድ ግለሰቦች›÷ ‹‹አንዲት ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት›› የሚሉቱም ናቸው፡፡ ታዲያ ምን ይበሉ?! ‹‹በይፋ አክራሪ ናችኹ ያለን አካል የለም፡፡›› /ተስፋዬ ቢኾነኝ፤ የማኅበር ቅዱሳን ዋና ጸሐፊ/ ‹‹በጉዳዩ ላይ የጠራ ነገር የለም፤ ነገር ግን ጢስ አለ፡፡ ከጢሱ በስተጀርባ ያለው እሳት ይኹን እሳተ ገሞራ ባይታወቅም ለጊዜው ግን ማኅበሩን በተመለከተ ግልጽ የኾነ ነገር የለም።›› /ዲ.ን ዳንኤል ክብረት/ …

ከሓላፊነታቸው ውጭ የሚንቀሳቀሱ ፕሮቴስታንትና ጉዳዩን ፖሊቲካዊ ያደረጉ የደኅንነት አባላት ነን ባዮች የኮሌጁን ሓላፊዎች በመጫን ተጠርጣሪዎቹን ከተጠያቂነት ለማዳን እየሠሩ ነው፤ ተጠርጣሪዎቹ በኮሌጁ አስተዳደር የተከለከለ ስብሰባ በግቢው እንዲያካሒዱ ረድተዋቸዋል፡፡ በ‹ደኅንነት አባላቱ› የሚደገፉትና ‹‹የኢሕአዴግ ተወካዮች ነን›› የሚሉት ተጠርጣሪዎቹ፣ ለሃይማኖታቸው የቆሙትን ብዙኃኑን የኮሌጁን ደቀ መዛሙርት በስለትና በፌሮ ብረት የታገዘ ዛቻና ማስፈራራት እያደረሱባቸው ነው፤ ደቀ መዛሙርቱና የኮሌጁ አስተዳደር ጉዳዩን ለጸጥታ …

የኮሌጁ የደቀ መዛሙርት ም/ቤት ችግሩ በአስቸኳይ እንዲጣራ ከኹለት ወራት በፊት ያስገባው ደብዳቤ ለተጠርጣሪ ደቀ መዛሙርት ሽፋን በሚሰጠውና ተጠርጣሪዎችን በቢሮው እየጠራ በሚያበረታታው የአስተዳደር ዲኑ ያሬድ ክብረት ተቀብሮ መቆየቱ ተገልጦአል፡፡ በቅ/ሲኖዶስ ከተወገዙ ግለሰቦችና ፕሮቴስታንታዊ ድርጅቶች የኑፋቄ አስተምህሮና ተልእኮ የሚሰጣቸው ኅቡእ አንቀሳቃሾች ትኩረታቸውን በአዲስ ገቢ ደቀ መዛሙርት ላይ አድርገዋል፤ በመምህራን ምደባ ተጽዕኖ እስከ መፍጠርና የማስተማር ክፍለ ጊዜዎችን በጋጠ …

ቁጥጥር ከሚደረግባቸው ሕገ ወጥ ተግባራት መካከል÷ ያልተፈቀደላቸው ሰባክያን ስምሪትና የኅትመት ውጤቶቻቸው፣ የአስመሳይ ባሕታውያንና መነኰሳት ነውረኛ ድርጊቶች፣ ሕገ ወጥ ልመና፣ የአጥቢያ አስተዳደር ሙስናና የወጣት ሱሰኝነት ይገኙበታል፡፡ ማዕተብ ያለው ኦርቶዶክሳዊ ምእመን በተለይም ወጣቱ ከሱስ ነጻ መኾን አለበት፤ መስቀሉን አንጠልጥሎ በየባንኮኒውና በየዳንኪራው ከመታየት መጠበቅ አለበት፤ ዶግማውን፣ ቀኖናውንና ትውፊቱን ያወቀና የጠነቀቀ፣ በኢኮኖሚያዊና ፋይናንሳዊ አቅሙም ጠንካራና እርስ በርሱ መደጋገፍ ይገባዋል፡፡ …

ሊቃነ ጳጳሳቱ ቅሬታቸውን ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሓላፊዎች ገልጸዋል የቤተ ክርስቲያንን እንጀራ እየበሉና በጀቷን አውጥታ እያስተማረቻቸው የሌላ እምነት በሚያራምዱ የስም ደቀ መዛሙርት ላይ ርምጃ እንዲወሰድ ተጠየቀ (አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፫ ቁጥር ፯፻፵፩፤ መጋቢት ፳ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.) የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ የኾኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የቤተ ክርስቲያኒቱን እምነትና ሥርዐት እንዲማሩ፣ ዕውቀታቸውንና ገንዘባቸውን በማቀናጀት ሞያዊ ድጋፍ …

(ፋክት፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፴፱፤ መጋቢት ፳፻፮ ዓ.ም.) ተመስገን ደሳለኝ በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም አዝማችነት በማኅበሩ ላይ የደቦ ዘመቻ ከተከፈተ ሰነባብቷል፡፡ በጥናት ስም በተከታታይ የሚወጡና በየመድረኩ የሚቀርቡ ወረቀቶች ማኅበሩን የኦርቶዶክስ አክራሪ ከማለት አሻግረው ‹‹የግንቦት ሰባት መንፈሳዊ ክንፍ/የግንቦት ሰባት ከበሮ መቺ/›› ሲሉ ይወነጅሉታል፡፡ የማኅበሩ አመራሮች እንዲኽ ዓይነቱን ውንጀላ በተመለከተ በተለያየ ጊዜ ከአቶ …

ሥርዐቱ በተለይም መንግሥታዊ ሥልጣናቸውን ለሃይማኖታዊ ተልእኮ የሚጠቀሙ ሓላፊዎችና አማሳኝ የደኅንነት ግለሰቦች አሁን በተያዘው መንገድ ቀጥለው ማኅበረ ቅዱሳንን አላግባብ ወደ መገዳደር ብሎም ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አማሳኝ ግለሰብ ሓላፊዎች ጋራ ተባብረው ወደ ማፍረስ የሚሸጋገሩ ከኾነ ያለምንም ጥርጥር የተቃውሞው ጎራ ይጠናከራል፡፡ ይህም አገሪቱን በልማታዊ ዴሞክራሲያዊ የአውራ ፓርቲ ሥርዐት ለአርባና ኃምሳ ዓመታት እመራለው ለሚለው ገዥው ፓርቲ ግብዓተ መሬት አፋጣኝ …

በቅ/ሲኖዶሱ በይፋ ከተወገዙና በኑፋቄ አራማጅነት ከሚጠረጠሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ጋራ ግንኙነት ያላቸውና በኅቡእ በሚንቀሳቀሱ ጥቂት ተማሪዎች የሚራመድ ነው ‹‹ችግሩን በዝምታ ለመመልከት ኅሊናችም ሃይማኖታችንም አይፈቅድልንም›› /ብዙኃኑ ደቀ መዛሙርትና የደቀ መዛሙርት ምክር ቤት አባላት ለእምነትና ሥርዓት የሚቆረቆሩ መምህራንና ተማሪዎች ‹ማኅበረ ቅዱሳንና ፖሊቲከኞች ናችኹ› በሚል እንዲሸማቀቁ ይደረጋሉ (ዕንቊ፤ ቅጽ ፮ ቁጥር ፻፲፬፤ መጋቢት ፳፻፮ ዓ.ም.) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን …

(የምዕራብ ጐጃም ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት – ፍኖተ ሰላም) የብፁዕነታቸው ልደትና ዕድገት ብፁዕ አቡነ ቶማስ በቀድሞው አጠራር በጎጃም ጠቅላይ ግዛት በቆላ ደጋ ዳሞት አወራጃ በደጋ ዳሞት ወረዳ በመንበረ ስብሐት ዝቋላ ፬ቱ እንስሳ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ውስጥ ከአባታቸው ብላታ ተገኘ ይልማ ገብረ ሕይወት ከእናታቸው ከወ/ሮ ውድነሽ ቸሬ መጋቢት 14 ቀን 1935 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ‹‹ዘእንበለ እፍጥርከ አእመርኩከ ወዘእንበለ …

በሕወሓት/ኢሕአደግም ይሁን በተቃዋሚዎች በረት እና ማደሪያ …….
እየከፋ ያለን ጉዳይ እየተሻሻለ ነው ማለት = እያወቁ ማለቅ ……. ‪

= ሥልጣንህን አድን = ኢሕአደጋዊ አጀንዳ ወደ = አገርህን አድን = ሕዝባዊ አጀንዳ ይቀልበስ።
እየተሻለኝ ነው እያለ ከሚሞት፣ በጣም ጥሩ ምልክት ነው እያለ ከሚገድል ያድነን ፡፡ ደግ ደጉን ማውራት የተሻለ ዓለም ለማየት ይጠቅማል የሚለው ብሂል እንደተጠበቀ ሆኖ፤ እየከፋ ያለን ጉዳይ እየተሻሻለ ነው ማለት ግን እያወቁ ማለቅ ዓይነት ነው፡፡

ምንሊክ ሳልሳዊ ዕውነቱን ተናግሮ የመሸበት ማደር ለአገርና ህዝብ ይበጃል እንጂ ጐጂ አይደም፡፡ የማይሰጋ ተስፋ የሌለው ሰው ነው ፡፡ አይመጣምን ትተሽ ይመጣልን ጨምሪበት” የሚሉት ዓይነት::
በየኑሮ መስኩ ያለውን ህመም፣ በየሙያ መስኩ ያለውን ተወሳክ፣ በየፖለቲካ መስኩ ያለውን ወረርሽኝ በጊዜ መመርመር ዋና ነገር ነው፡፡ እኛ የወደድነውን እያጐላን በየሚዲያው ብንለፍፍ ለሀገርና ለህዝብ ፋይዳ አይኖርም።

ለምርጫ እወዳደራለሁ የሚል ፓርቲም ይሁን ፕሮፓጋንዳ የሚረጭ ሚዲያ ፍትሐዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ሰላማዊና ሕዝባዊ ሥርዓት ለመገንባትና በዚህ መንገድ ለመምራት ከፈለገ፣ ሕዝብን ማክበርና ማዳመጥ ጥበብ መሆኑን፣ አማራጭና ተለዋጭ የሌለው መርህ መሆኑን ለመግለጽና አፅንኦት ለመስጠት ነው፡፡
የሕዝብን ብሶት ማዳመጥና ለሕዝብ ከበሬታ የመስጠት ጉዳይ ጥበብ መሆን ብቻ ሳይሆን፣ ጊዜ የማይሰጥና በእጅጉ አንገብጋቢ ሕዝብ አድን እና አገር አድን አጀንዳ እየሆነ ነው፡፡ሥልጣንህን አድን ከሚለው ኢሕአደጋዊ አጀንዳ በላይ፡፡

በኢትዮጵያችንም እንደዚሁ ሕዝብን የማክበርና የማዳመጥ ጉዳይ ተገቢና አስፈላጊ ተብሎ ብቻ የሚታለፍ ሳይሆን፣ አንገብጋቢ ሆኖ የተግባር ያለህ እያለ በመጮህ ላይ ያለ አጀንዳ ነው፡፡ ላለው ችግር ብቸኛው ፍቱን መድኃኒትና ጥበብ ሕዝቡን ማክበርና ማዳመጥ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ እየጠየቀ ነው፡፡ አቤት እያለ ነው፡፡ እየጮኸ ነው፡፡ ጥያቄው ማነው ሕዝቡን እያከበረና እያዳመጠ ያለው ? የሚል ነው፡፡ ምንሊክ ሳልሳዊ

ሸዋ በር እና አከባቢው ስጋት ነጋደው ጭንቀት እንዳጠላበት ነው።”…አዘናግቶ ሊያጋየን ነው::”
የእሳት ማጥፊያ አዘጋጁ እሳት ሊነሳ ይችላል የሚለውን ወያኔያዊ ሽብር በነጋዴዎች ዘንድ ጥርጣሬ አጭሯል::

ምንሊክ ሳልሳዊ:-በሃረር ለረዥም ጊዜ ታፍኖ የቆየው ብሶት ባለፈው ሰሞን የተነሳውን የእሳት ቃጠሎ ተከትሎ ሕዝቡ አደባባይ እስከመውጣት ደርሶ ነበር::የወያኔው መንግስት ካለፉት አመታቶች ጀምሮ በተለያየ ጊዜ የሃረር ነጋዴዎችን መደብሮች ሲያቃጥል እንደ ዋናው ምክንያት ተደርጎ የተወሰደው አከባቢው ለልማት ስለሚፈለግ ከቦታው ተነሱ የሚለው የቅድመ ማስጠንቀቂያ ነጋዴዎቹ በምትኩ ቦታ ይሰጠን የሚሉትን አስታኮ የሚመጣ ቃጠሎ መሆኑ እና ከቃጠሎ በፊት ወደ መደብሮች መጋዘን የሚገቡ ነዳጅ የተሞሉ ጀሪካኖች ሕዝቡ ጣቶቹን በወያኔ ላይ እንዲጠቁም አድርጎታል::

ወያኔ የሃረር ህዝብ ላይ ያደረሰውን ሰቆቃ እና በደል ለመሸፈን ሰላማዊ ሰልፍ በመጥራት ነገሮችን በሙሉ አሸባሪ ብሎ በሚጠራቸው በመላከክ ህዝቡን ለመሸወድ ቢሞክርም አልተሳካለትም:: በየመንገዱ ቢያፍስ ቢያባርር ቢደበድብ ቢያስር ስብሰባ ቢጠራ ያልተሳካለት ወያኔ ከዚህ በመቀጠል ምን ሊያመጣ እንደሚችል እስካሁን የታወቀ ነገር የለም:: ምናልባት ይላሉ የሸዋ በር እና አከባቢው ነጋዴዎች ስጋታችንን እና ጭንቀታችን መደብሮቻችንን እንዳያቃጥልብን ነው ሲሉ ሃሳባቸውን አካፍለውናል::

በውሃ እጥረት እና በሌሎች የአገልግሎት አቅርቦት የምትታመሰው ሃረር በሕወሓት ሰራሾች ደባ እየተደረገባት ያለው የሰብኣዊ መብት ገፈፋ እና በደል እየጨመረ እንዲ እየቀነሰ አለመሆኑ የሰሞኑ ምስክር ሂደት ምስክር ነው::በዚህ ሰሞን ከክልሉ ምክር ቤት እስከ ቀበሌ ካድሬዎች ስብሰባ ከሕዝቡ እስከ ነጋዴው ቢሰበሰብም በሰብሳቢዎች እና በተሰብሳቢው ሕዝብ መካከል አለመተማመን እንደነገሰ ተበትኗል:: በትላንትናው እለት በሸዋ በር አከባቢ ጀጎል ግንቡን አስታኮ ያሉ ባለመደብሮች ስብሰባ ተጠርተው እንዲሁም የእህል እና የቅመማ ቅመም ነጋዴዎች በስብሰባው ተጋብዘው የተገኙ እና በተሰብሳቢው እና በሰብሳቢዎች ሕወሓት ሰራሽ የከተማው ባለስልታናት መካከል ስጋት እና ሽንቀት ወጥሮት የተካሄደ እንደነበር ነጋዴዎቹ ጠቁመዋል::

የሸዋ በር አከባቢ ነጋዴዎች ባለፈው በመብራት ሃይል እና በሲጃራ ተራ አከባቢ የደረሰውን የእሳት ቃጠሎ ከተመለከቱ በኋላ ነግ በኔን በማሰብ ንብረታቸውን ከአከባቢው በማሸሽ ስጋታቸውን በተግባር ለወያኔ ሰራሽ አካላቱ ያሳዩ ሲሆን ይህንን የተመለከተው መንግስታዊ አካል ነኝ ያለ ክፍል ነጋዴው እቃውን ከማውጣት ከመንግስት ጋር በጠረጰዛ ዙሪያ እንሰብሰብ እቃችሁን አታሽሹ ቢልም ነጋዴዎቹ አዘናግቶ ሊያጋየን ነው በሚል እቃቸውን ወደቤታቸው ጭነው ወስደዋል::

ንብረታችን ቤታችን እንዳለ ስብሰባ እንቀመጣለን ብለው የቆረጡት ነጋዴዎች በተጠሩበት ስብሰባ በመሄድ ዋና ዋና የተባሉ ነጥቦችን አንስተዋል::ከተነሱት ነጥቦች በእሁድ ቀን ማንም ሰው በገበያ ቦታዎች ውስጥ መገኘት እንደማይኖርበት;እሁድ ቀን ጠቅላላ መደብሮች ዝግ መሆን እንዳለባቸው:የዘበኞች ቁጥር መጨመር እንዳለበት:ወዛደሮች መታወቂያ እና ባጅ ሊኖረው እንደሚገባ እና መቆጣጠር አስፈላጊ መሆኑን:በንግዱ አከባቢ ዳር ዳሩን የመኪና መንገድ ላይ ያሉ በረንዳዎች እና መደቦች መጽዳት እንዳለበት በገበያ ውስጥ እሳት ማጥፊያዎች እና የውሃ ታንከሮች እንዲዘጋጁ ተወያይተውባቸዋል:; በዚህም መሰረት ነጋዴዎቹ የመተማመን መንፈስ ባይታይባቸውም ወኪሎቻቸውን መርጠው ስራውን ሊሰሩ የተስማሙ ሲሆን እስከዛሬ ያልታሰበ የእሳት ማጥፊያ እና የውሃ ታንከር አዘጋጁ እሳት ሊነሳ ይችላል የሚለውን ወያኔያዊ ሽብር በጥርጣሬ ተመልክተውታል::ምንሊክ ሳልሳዊ

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከታች በአስተያየት መስጫ ውስጥ የምትመለከቱት ምስል ከሶስት አመት በፊት ቦታው ለኢንቨስትመት ይፈለጋል ተነሱ የተባሉ ነጋዴዎች ምትክ ቦታ ይሰጠን እያሉ ሲከራከሩ የወያነ ሰራሽ የክልሉ ባለስልጣናት በድንገት የነጋዴዎችን መደብሮች ያቃተሉት ቦታ ሲሆን ይህ ቦታ ወደ መብራት ሃይል ሂደው ባለፈው ሱቆቻቸው የተቃተሉባቸው ነጋዴዎች ቦታ የነበረ ነው:: መንግስታዊ እሳት እየተከተለን ነው የሚሉ የመብራት ሃይል መደብር ባለቤቶች እና ተጎጂዎች ከ3 አመት በፊት የተቃጠለባቸው ቦታ ሕንጻ ለማሰራት ለአንድ ኢንቨስተር ተሰቶት ጥናት ተካሂዶ ቦታው ለኮንስትራክሽን አመቺ እንዳልሆነ እና አከባቢው ውሃ የሞላበት እና ሕንሳ ሊያሰራ የማይችል አፈሩም ለሕንሳ ግንባታ ተስማሚ እንዳልሆነ ይህ ቦታ ላይ ህንጻ ለማስገንባት ከፍተኛ ወጪ እና ዲዛይን የሚጠይቅ በመሆኑ ቦታው በዚህ ምክንያታዊ ጉዳዮች ለ3 አመት ያህል በምስሉ እንደምታዮት ታጥሮ የነበረ ሲሆን በአሁን ሰአት የተቃጠለው የሲጃራ ተራ እና የመብራት ሃይል ከቃጠሎ የተረፉ ቆርቆሮዎች እና ሌሎች ማቴሪያሎች መከመሪያ እየሆነ ነው::ምንሊክ ሳልሳዊ

Image

Image

Image

Image

March 24, 2014 08:11

ለግልጽነትና ለተጠያቂነት ብሎም ለህዝቦች ጥቅም ቅድሚያ እንደሚሰጥ ህግ ደንግጎ የተቋቋመው ዓለም ዓቀፋዊ ተቋም ኢህአዴግ ያቀረበውን የይግባኝ ማመልከቻ ተቀብሎ ማጽደቁ አነጋጋሪ ሆኗል። በ2009 ኢህአዴግን “ያወጣሁትን መስፈርት አታሟላም” በማለት እውቅና የከለከለው ይህ ተቋም፣ ኢህአዴግ በሚከሰስባቸው ዋና ጉዳዮች ለውጥ ሳያደርግ የራሱን ውሳኔ የገለበጠበት አካሄድ እየተመረመረ እንደሆነ የጎልጉል ምንጮች ጠቁመዋል።

የኢህአዴግን የእውቅና ይግባኝ ጥያቄ ተቀብሎ ያጸደቀው የተፈጥሮ ሃብትን በትክክለኛ መንገድ ለሕዝብ ጥቅም መዋሉን በመከታተል ለአገራት እውቅና የሚሰጠው The Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) የሚባለው ዓለም ዓቀፋዊ ተቋም ነው። ተቋሙ ኢህአዴግ በ2009 አቅርቦት የነበረውን የእውቅና ጥያቄ ውድቅ ሲያደርግ የሰጠው ምክንያት “የመያዶች ህግ የተሰኘው” አዋጅ ተግባራዊ እንዳይሆንና በአገሪቱ የተተከሉት አፋኝ ህጎች እስካልተወገዱ ድረስ ማመልከቻው እንደማይታይ በማሳወቅ ነበር።

በ2009 ጠ/ሚኒስትር የነበሩት አቶ መለስ “መሰዋት” በስተቀር ኢህአዴግ አንዳችም ለውጥ ባላደረገበት ሁኔታ ባለፈው ረቡዕ መጋቢት 19፤2006 (March 19፤2014) ይኸው እውቅና ሰጪ ተቋም የራሱን ውሳኔ ቀልብሶ ለኢህአዴግ እውቅና መስጠቱ የብዙዎችን ቀልብ ስቧል። ከውሳኔው ቀናት በፊት በጓሮ የሚወጠን ድርጊት እንዳለ መረጃ ደርሶት የማሳሰቢያ ተቃውሞ ያሰራጨው ሂውማን ራይትስ ዎች የተሰኘውየሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እንዳለው ከሆነ ከተገለበጠው ውሳኔ በስተጀርባ ሚስ ክሌር ሾርት ከፊት ረድፍ ተቀምጠዋል።

ማመልከቻው እንደገና እንዲታይና የቦርዱ የቀድሞ ውሳኔ እንዲገለብጥ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት የቀድሞ የእንግሊዝ ዓለምአቀፍ ትብብር ሚ/ር የሆኑት ክሌር ሾርት መሆናቸውን የድርጅቱ መግለጫው ይፋ አድርጓል። እኚህ ግለሰብ የአፍሪካ አምባገነኖችን በመደገፍ የሚታወቁ ሲሆን ይህ ከጥቅማቸው ጋር የተሳሰረው ግንኙነታቸው አሁንም ኢህአዴግን እንዲደግፉ እንዳደረጋቸው ይነገራል፡፡ እንዲሁም በሌሎች ኢህአዴግ ባቋቋማቸው ዓለምአቀፋዊነት ሽፋን በተላበሱ ድርጅቶች ውስጥ የአመራር አባል በመሆን ሚስ ሾርት እንደሚያገለግሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የእንግሊዝ ፓርላማ አባል በነበሩበት ወቅትም ያላወጡትን ወጪ አውጥቻለሁ በማለት በብዙ ሺዎች የሚገመት ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው ያዋሉ መሆናቸው በወቅቱ ዴይሊ ቴሌግራፍ ባወጣው መረጃ አጋልጦ ነበር፡፡ የተወሰነውን ገንዘብ የመለሱ ቢሆንም ጋዜጣው በወቅቱ ያወጣው መረጃ ግለሰቧ የሕዝብን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው የተጠቀሙ “ሙሰኛ” መሆናቸውን ያስረዳል፡፡

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው እንደሚሉት ከሆነ ባለፈው ረቡዕ ኦስሎ፤ ኖርዌይ ላይ ውሳኔው በተላለፈበት ወቅት ሚስ ሾርት በግልጽ የኢህአዴግ ደጋፊ በመሆን ተጽዕኖ በማድረግ ወደ ውሳኔ እንዲደረስ ግፊት አድርገዋል፡፡ ግለሰቧ ባላቸው ኃላፊነት በመጠቀም (የEITI የቦርድ ኃላፊ ናቸው) እንዲህ ዓይነቱ ግልጽና ወገናዊነት የታየበት ድጋፍ በማድረግ ከድርጅቱ አሠራር ውጪ ውሳኔ እንዲሰጥ ማድረጋቸው ለወደፊት በሚቀርቡ ማመልከቻዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የአሠራር ችግር እንደሚያስከትል ካሁኑ እየተጠቆመ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ከማዕድን ኢንቨስትመንት ጋር በተያያዘ ማህበራዊ ቀውስ የደረሰባቸው አካባቢዎች እንዳሉ የሚታወቅ ነው። በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት አካባቢዎች መካከል በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ባልጸዳ የሽያጭ ሂደት ሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ የገዙት ሻኪሶ የወርቅ ማዕድን በህዝብ ላይ እያደረሰ ችግር የሚዘገንን ነው። በየጊዜው ግልጽ ባልሆነ የማስፋፊያ ውል የሚፈናቀሉና ከፋብሪካው በሚወጣው ዝቃጭ ለከፍተኛ ብክለት የተጋለጡ ዜጎች ድምጻቸውን ሲያሰሙ መታሰራቸው፣ መገረፋቸው፣ ለይስሙላ በተቋቋሙ ፍርድ ቤቶች የተፈረደባቸው እንዳሉ ታዛቢዎች ያስታውሳሉ።

በጋምቤላ ኢንቨስትመንት ህዝብን እየበላ እንደሆነ የሚጠቁሙት ክፍሎች “ኢንቨስትመንት በከፍተኛ ደረጃ የሚደገፍና የሚበረታታ ተግባር ቢሆንም፣ ኢህአዴግ ፍትሃዊ በሆነ ደረጃ መጠቀም፣ ማስተዳደር፣ መምራትና ኢንቨስትመንቱን ህዝብ “የኔ” ብሎ በመቀበል እንክብካቤ እንዲያደርግ የሚያስችል ስርዓት አለማበጀቱን እንደ ዋንኛ ችግር ያነሳሉ። ኢህአዴግን ያዘጋጀው ህወሃት በራሱ ሰዎች አማካይነት ከውጪ ሰዎች ጋር እየተሻረከ ለህዝብ ጥቅም ሊውል የሚገባውን ሃብት ወደ ውስን ቋት እንደሚያግዝ የሚገልጹት እነዚሁ ክፍሎች” ይህ ዓለም የሚያውቀውን፣ ራሳቸው ህወሃቶችም የማይክዱትን እውነት ነው ብለዋል። ዜጎች የአገራቸው ሃብት ተጠቃሚ ከመሆን ይልቅ አካባቢያቸው ባደላቸው የተፈጥሮ ሃብት ሳቢያ መከራ ሲደርስባቸው፣ ሲሰቃዩ፣ ሲገረፉና፣ ሲገደሉ ማየት በተለመደባት ኢትዮጵያ ውስጥ ለኢህአዴግ የማይገባውን ካባ መደረብ ውሎ አድሮ የሚጋለጥ ክፉ ተግባር እንደሆነም አመልክተዋል።

አነስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙና ኢህአዴግ “ልማታዊ” የሚላቸው ኢንቨስተሮች ሳይሆኑ በከፍተኛ ደረጃ የሚመደብ መዋዕለ ንዋይ የሚያፈሱ ባለሃብቶች ኢንቨስት የሚያደርጉበትን አገር ለመምረጥ የመጀመሪያው መለያቸው የEITI ድረገጽ የአባል አገራት ዝርዝር እንደሆነ ስለ አሰራሩ የሚያውቁ ይናገራሉ። ኢህአዴግም አስፈላጊውን የምዝገባና የማመልከቻ መስፈርት በማሟላት የተቋሙን እውቅና የጠየቀው በድርጅቱ ድረገጽ ላይ ለመመዝገብ ነበር። የሁለት ጊዜ ሙከራው ቢከሽፋም በመጨረሻ ተሳክቶለታል። ስኬቱንና የስኬቱን መንገድ፣ በተለይም የዳይሬክተሯ ክሌር ሾርት ጉዳይና የተዘጋውን ፋይል በማንሳት ውሳኔው የተገለበጠበት አካሄድ ኦስሎ በሚገኘው ሃያ የቦርድ አባላት ባሉበት ተቋም ውስጥም ግራ ያጋባቸው እንዳሉ መረጃዎች አሉ።

ኢህአዴግ አጓድለሃል ተብሎ የሚከሰስባቸውን የዴሞክራሲ ግባቶችና የሰው ልጆች የተፈጥሮ መብቶች፣ አንዲሆም አፋኝ የተባሉትን ህጎች አጠናክሮ ተግባር ላይ ባዋለበት ሁኔታ፣ የዚሁ የአፈናው ሰለባዎች በተለያዩ ማጎሪያዎች ውስጥ ሆነው ድምጻቸውን በሚያስተጋቡበት ወቅት፣ EITI ከተቋቋመበት ዓላማና “መሰረቴ” ከሚለው የግልጽነትና ተጠያቂነት መርህ በተጻራሪ ግልጽነትና ተጠያቂነት በጎደለው መልኩ ለኢህአዴግ የደረበው ብሉኮ ጉዳይ እየተመረመረ አንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። ጉዳዩን የሚከታተሉ “ግልጽነትና ተጠያቂነት በኦስሎ ተፈረደባቸው” ሲሉ ምጸት ሰጥተዋል፤ የክሌር ሾርትንም አካሄድ በEITI የህወሃት/ኢህአዴግ ተወካይ በማለት ተችተዋል። ይህንኑ ጉዳይ እመልክቶ ከሳምንት በፊት ለሪፖርተር አጭር መልስ የሰጡት የማዕድን ሚኒስትሩ EITI ውሳኔውን ያነሳል የሚል ጥርጣሬ እንዳለባቸው የሚያሳብቅባቸው መልስ ሰጥተው እንደነበር ይታወሳል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ዳያስፖራው እንደሚገባው አለመንቀሳቀሱ እንደ ሽንፈትና አቅጣጫ መሳት እንደሚቆጠር ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡ ጠቁመዋል፡፡ ዳያስፖራው ከጥቃቅንና ስሜታዊ ጉዳዮች በማለፍ በከፍተኛና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት የማድረግ አመለካከቱን ማስፋት እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡ አለበለዚያ ኢህአዴግ እንደዚህ ዓይነቱን አጋጣሚ በመጠቀም የራሱን ገጽታ በዓለምአቀፍ መድረኮች እየወለወለ በማቅረብ የሥልጣን ዘመኑን እንደሚያራዝም ጠቁመዋል፡፡

golgul
http://raheltakele.wordpress.com/2014/0 … %E1%89%A0/

(አዲስ ጉዳይ፤ ቅጽ ፰ ቁጥር ፳፻፰፤ መጋቢት ፳፻፮ ዓ.ም.) ሃይማኖት ከአስተዳደሩ የተለየ በጣም ጥልቅ ነገር ነው፡፡ ሃይማኖት ማለት ከአንድ ግለሰብ ኾነ ከጥቂት ሰዎች አመራር የተለየና የራሱ የኾነ ዶግማ፣ ቀኖና እና ትውፊት፣ ባህልና ሥርዓት ያለው መኾኑ መታወቅ ይኖርበታል፡፡ በሥነ ምግባር ደረጃ እኔን ጨምሮ ኹሉም ሰው ችግር ሊኖርብን ይችላል፡፡ ይኹንና ይኼ የሥነ ምግባር ጉዳይ ሊፈታ የሚችለው በመነጋገርና …

ዶክመንተሪው የ2007 ሀገራዊ ምርጫ ቅድመ ዝግጅት አካል እንደኾነ ተጠቁሟል ‹‹ማስረጃ አቅርቡና እንነጋገርበት›› ለሚለው የማኅበሩ ጥያቄ ምላሽ አልተሰጠም (ፋክት፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፴፰፤ መጋቢት ፳፻፮ ዓ.ም.) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሲኖዶሱን ይኹንታ አግኝቶ በመላው አገሪቱ የሚንቀሳቀሰውን የማኅበረ ቅዱሳንን አመራርና አባላት በአክራሪነት የሚከስ ነው የተባለ ዶክመንተሪ ፊልም ለማዘጋጀት መታቀዱ ተጠቆመ፡፡ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አንዳንድ ሓላፊዎች …

ህወሓቶች በዓረና እንቅስቃሴና በትግራይ ህዝብ የተቃውሞ መንፈስ በጣም ደንግጠዋል። የዓረና ተከታታይ ህዝባዊ ስብሰባዎችን ተከትሎ ህወሓትም ተከታታይ ህዝባዊ ኮንፈረንስ ለማድረግ ወስኗል፤ ጀምሯልም። የህዝብ ተወካዮች ተብለው የተመረጡ የየአከባቢያቸው ህዝብ እንዲሰበስቡ መመርያ ተሰጥቷል። ይቅርታ የህዝብ ተወካዮች ሳይሆኑ የፓርቲ ተወካዮች መባል አለባቸው፤ ምክንያቱም የተመረጡት በህዝብ ሳይሆን በህወሓት ነው። የሚያገለግሉትም ለህዝብ ሳይሆን ለህወሓት ነው። ምክንያቱም በህዝብ ተመርጠው ተብለው የህዝብ ችግር ከመናገር ይልቅ የህወሓት አጀንዳ ደግፈው የሚያጨበጭቡ ናቸው። እስካሁን የመረጠውን ህዝብ ችግር የተናገረ የህዝብ ተወካይ የህወሓት አባል አላገኘሁም። በህወሓት የፖለቲካ ፍልስፍና የተማእከለ ዴሞክራሲ መሰረት አንድ አባል ከፓርቲው አስተሳሰብ ወጥቶ የፓርቲው ብልሹ አሰራሮች ባደባብይ ወይ በፓርላማ ማጋለጥ አይችልም። ካጋለጠ ከፓርቲው ይባረራል። ለዚህም ነው የህዝብ ተወካዮች ተብለው ፓርላማ ይገቡና የፓርቲው ተወካዮች ሁነው የሚቀሩ።

የህዝብ ወይም የህወሓት ተወካዮች ህዝብ ሲሰበስቡ ፈተና እያጋጠማቸው ነው። የሽረ ተወካይ ህዝቡ ሰድቦ አባሯታል። ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ በዓድዋ ህዝብ ተሰድባለች። የዓድዋ ህዝብ ለቅዱሳን “እናንተ ቤተሰቦቻቹ ለመርዳት እንጂ መቼ ለህዝብ ደህንነት ሰርታቹ ታውቃላቹ?” የሚል አስተያየት ሰጥቷል። በመቐለም አዲሳለም ባሌማ ህዝብ (ይቅርታ በመቐለ ህዝብ ተብለው የተሰበሰቡ ካድሬዎች ነበሩ) ሰብስቦ እርዱን ማለቱ ታውቋል። የመቐለ ዉሃ በ2007 ዓም ፕሮጀክት ቀርፀን እንፈተዋለን፤ ብቻ እኛን ምረጡ ብሎ ተማፅኗል። የመቐለ ነጋዴዎች ሰብስቦ ችግሮቻቹ ለመፍታት ተዘጋጅተናል ብሎዋል።

አጠቃላይ የህወሓት ስትራተጂ ህዝብን ለመሸወድ ያለመ ሲሆን የሚያጠነጥነውም “ህወሓት ካልተመረጠ የትግራይ ማንነት ይጠፋል” የሚል ነው። “ጠላቶቻችን እየመጡ ናቸው፤ ከህወሓት ጎን ተሰለፉ! ጦርነት ሊከፈትና ልጆቻችሁ አደጋ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ” እያሉ ይገኛሉ።

ግን የትግራይ ማንነት በህወሓት ህልውና የተንጠለጠለ አይደለም። እንኳን የህዝብ ማንነት የአንድ ግለሰብ ማንነትም ሊጠፋ አይችልም። ምክንያቱም የህዝብ ማንነት ቀርቶ የአንድ ሰው ማንነት ከጠፋ የሰውየው መብትና ነፃነት ተጥሷል ማለት ነው። መብቱ ወይ ነፃነቱ ከተጣሰ ደግሞ አዲስ የመጣ ስርዓት ልክ እንደ ህወሓት አምባገነናዊ ስርዓት ነው ማለት ነው። የህውሓትን ያህል አምባገነን ስርዓት ከመሰረትን ደግሞ ህወሓት አልተቀየረም ማለት ነው። ህወሓት ካልተቀየረ የፖለቲካ ለውጥ አልመጣም ማለት ነው። የፖለቲካ ለውጥ ካልመጣ ደግሞ ትግላችን ይቀጥላል (ለውጥ እስኪመጣ ድረስ)። ስለዚህ እኛ የምንታገለው ከህወሓት የተሻለ ስርዓት ለመመስረት እንጂ ህወሓትን በሌላ አምባገነን ስርዓት ለመተካት አይደለም። ስለዚህ ላረጋግጥላቹ የምፈልገው ነገር ቢኖር የማንም ህዝብ ወይ ግለሰብ ማንነት ይከበራል እንጂ አይጠፋም።

“ጠላቶቻችን እየመጡ ነው” የሚለው ዉንጀላ ግዜው ያለፈበት ፕሮፓጋንዳ ነው። የህዝብ ጠላት ጨቋኝ ስርዓት ነው። ህዝብ ከጨቋኝ ስርዓት ዉጭ ሌላ ጠላት የለውም። ጨቋኝ ስርዓት የህዝብ ጠላት እስከሆነ ድረስ እንታገለዋለን። ጨቋኝ ስርዓት ምን ግዜም አንቀበልም። ጨቋኝ ስርዓት ስለማንቀበል ነው አሁን ህወሓትን የምንቃወመው። ስለዚህ ዓላማችን የስርዓት ለውጥ ማምጣት እስከሆነ ድረስ ለጨቋኞች ቦታ የለንም፤ ህወሓትም ሌሎችም። እኛ የምንቀበለው ዴሞክራሲያዊ የህዝብ መንግስት ብቻ ነው።

ህወሓቶች በዓረና አጀንዳዎች በመስጋታቸው ምክንያት የዓረና ሐሳቦችን ለመቀበል እየተገደዱ ነው። በቅርቡ በህዝብ ፊት እየቀረቡ የመሬት ይዞታ ጉዳይ በዓረና እየቀረበ ያለውን ሐሳብ እንደሚደግፉ እየገለፁ ነው። (የዓረና ሐሳብ እንደግፋለን እያሉ ሳይሆን የህዝብን ፍላጎት ለማሟላት እንሞክራለን በሚል ነው። የህዝቡ ፍላጎት ደግሞ የዓረና የመሬት ፖሊሲ ነው)። የዓሰብ ወደብም በሰለማዊ መንገድ ለማስመለስ እንሞክራለን በማለት እየተመፃደቁ ነው። ለነጋዴዎችም ግብር እንቀንሳለን በሚል ምክንያት ለመጀንጀን እየሞከሩ ነው።

አሁን ግራ ሲገባቸው ስራ የሌላቸው ወጣቶች ለውትድርና ለመመልመል እየሞከሩ ሲሆን ማንም ወጣት ፍቃደኛ ሊሆን አልቻለም። በወጣቶቹ ዉሳኔ የተደናገጡ ህወሓቶች የጎዳና ተዳዳሪ የነበሩ ህፃናት ልጆች አታለው (ስራ እንሰጣቸዋለን በሚል ምክንያት) ለዉትድርና መመልመላቸው ታውቋል። ለምሳሌ በመቐለ ከተማ የነበሩ ብዙ የጎዳና ተዳዳሪ ህፃናት ተወስደዋል (ማረጋገጥ ይቻላል፤ አሁን በመቐለ ከነበሩ ህፃናት አንድ የቀረ የለም)። ግን አብዛኞቹ ህፃናት ከ16 ዓመት በታች ናቸው። ከ16 ዓመት በታች ህፃናት ለውትድርና የሚመለምል የቸኛ ሕገወጥ መንግስት ኢህአዴግ መሆኑ አይቀርም። ምክንያቱም በማንኛውም ሕግ ከ16 ዓመት በታች ህፃናት ለውትድርና መመልመል ሕጋዊ ሊሆን አይችልም። ጉዳዩ የሚከታተለው ካገኘ በዓለም አቀፍ ሕግ ወንጀል ሊሆን ይችላል።

በዓዲግራት የፈፀሙብንን ድብደባ በጣም አክስሮባቸዋል። የትግራይ ህዝብ ሙሉበሙሉ እንዲጠላቸው ሁነዋል። እናም በጣም ሰግተዋል። በቅርቡ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ሊጀምሩ ይችላሉ። በወታድሩም ቢሆን ህወሓቶች ድጋፍ የላቸውም።

It is so!!!
አብረሃ ደስታ

Image

መለስ በመጀመሪያው የኤርትራውያን ነፃነት ቀን ዝግጅት ላይ ለኤርትራውያን እንዲ ብሎ ነበር። «ቁስል እንዳለባችሁ አውቃለው። ለምን? ብትሉ ጀርባችሁ ላይ ያለው ቁስል በእኔ ጀርባ ላይም አለ። ይህንን ያለፈ ምህራፍ እርሱት አልላችሁም። ነገር ግን ቁስላችንን ማከክ የለብንም አሁን ሁሉ ነገር አልቋል (ተውዲኡ ኣሎ)ክፉ፣ ክፉውን ቀብረነዋል!!» ነበር ያለው።

ይህንን የመለስ ዜናዊ አነጋገር አንድምታ ስናይ «ይኸው ደረስንላችሁ! ጠላት ተቀበረ! መቀበር ብቻ አይደለም አስተሳሰቡንም አዛብተነዋል! ያለበት ነበር። እንግዲህ ማነው ጠላት? ኢትዮጵያ? የማን አስተሳሰብ ነው? የኢትዮጵያ! ምን አይነት አስተሳሰብ? እንግዲህ እንደምናውቀው በተለየ ጊዜ የኢትዮጵያን ሳይኮሎጂ የሚያዛቡ ነገሮችን ሲናገሩ ነበር። ለምሳሌ፦ «ባንዲራ እኮ ጨርቅ ነው!» ይሄ አባባልን ለሚያይ ሌላ ሰው በቀላሉ የአፍ ወለምታ ሊመስለው ይችላል።ነገር ግን ሆን ተብሎ የኢትዮጵያውያንን አስተሳሰብ ለማዛባትና ለማሽመድመድ የሚደረግ ሴራ ነው።

በባንዲራችን እንደምንኮራ ያውቃሉ! የሶስት ሺህ አመት ታሪክ አለን ብለን እንደምንኮራ ያውቃሉ! ነገር ግን ይህንንም ታሪካችንን ወደ መቶ አመት ዝቅ ለማድረግ ይጥራሉ፤ ባለፉት መሪዎቻችን በአጼ ምንሊክ ፣ በነ አጼ ቴዎድሮስ፣ በነ አጼ ዩሐንስ፣ በነ አሉላ እንደምንኮራና እንደምንወዳቸው ከእነሱ ጋርም ያለንን ትስስር ያውቃሉ! ወያኔዎቹ ባንዳዎች ግን በየጊዜው ቴሌቭዥን ላይ እየወጡ «የኢትዮጵያ አጼዎች እኮ ጊዜያቸውን ያሳለፉት በጦርነት ነበር።» ይላሉ። ይሄን መናገር በተለይ አቶ መለስ እንደሆቢ ነበር የወሰዱት የሚመስለው። እንግዲህ የኢትዮጵያ ህዝብ መሪዎቹ «ለካ እንዲህ ነበሩ» ብሎ እንዲያፍር! የዛሬውም ቅጥ ያጣ ድህነት «እነሱ ያመጡት ጣጣ ነው!» ብለውም ለመናገር ይሞክራሉ።

እንደዚህ አይነት ቀጣይ ነገሮችን አምጥተን አገጣጥመን «ባንዲራ ጨርቅ ነው!» ካሉበት ጊዜ ጀምሮ ያሉትን ሰብስበን ብናያቸው መለስ የተያያዘው ኢትዮጵያዊ አንገቱን ደፍቶ፣ በኢትዮጵያዊነቱ አፍሮ፣ ድህነትን እንዲቀበል፣ ከኋላ ቀርነት ጋር ተቆራኝቶ እንዲኖርና የበታችነት ስሜት እንዲኖረው አድርገዋል እየተደረገም ነው»

Image

በቅርቡ ባህርዳር ላይ በተካሄደው የኢትዮጵያ ስፖርት በአል ሼኽ አልሙዲ በክብር እንግድነት ተጋብዘው ነበር። የበአሉን መክፈቻ በቲቪ ስከታተል አንድ ጥያቄ ወደ በአእምሮዬ መጣ። አልሙዲንን የክብር እንግዳ አድርጐ መጋበዙ ለምን አስፈለገ?..ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ። “የገዢው ፓርቲና የባለስልጣናቱ ታማኝ ወዳጅ ስለሆኑ፣ በባህርዳሩ ስታዲየም ግንባታ ድርጅታቸው ስለተሳተፈ ወይም ሼኹ ለስፖርት ያላቸውን ፍቅር በማየት..” የሚሉ ነገሮችን መደርደር ይቻላል።

በእኔ ግምት አልሙዲ በባህርዳሩ በአል በእንግድነት የተጋበዙት በሰሜን አሜሪካ ስፖርት በአል ላይ ስለተዋረዱ የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት የፈጠርዋት ማፅናኛ ትመስለኛለች። ባለፈው አመት እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በአንድ ሳምንት ሁለት የኢትዮጵያ ስፖርት በአል ተከበሮዋል። አንድኛው በሼኽ አልሙዲና የዳይስፖራውን ማንነትና ፍላጐት ባልተገነዘቡ ወዳጆቻቸው የተዘጋጀ ነበር። በነዚህ ወገኖች ግምት “ዳያስፖራው በተወሰኑ የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅት ካድሬዎች የሚሽከረከር የዋህ ህዝብ” አድርገው ይወስዱታል።

አሜሪካ ሀገር ከኅይለስላሴ ጀምሮ በደርግ ጊዜ ከዛም በኋላ የመጣው አብዛኛው ኢትዮጵያዊ (በምንም መንገድ አሜሪካ ይምጣ) ለዘሩ፣ ለጐሳው ሳይሆን ለኢትዮጵያዊነቱ ጥልቅ የሆነ ፍቅርና ክብር አለው። በዚህ ምክንያት የኢህአዴግን የዘር ፖለቲካ አይደግፍም። ከደጋፊዎቹም ጋር የማይታረቅ ቅራኔ ውስጥ የገባው በዚህ አገር ወዳድ አቋሙ ነው። ይህ እውነት ያለገባቸው አልሙዲና ተከታዮቻቸው በስፖርቱ አስታከው ዳያስፖራውን እንቆጣጠራለን በማለት በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ቢከሰክሱም አልተሳካላቸውም። ባዶ ስታዲየም ታቅፈው ነው የቀሩት። ሁለተኛው ኢ.ኤስ.ኤፍ.ኤን የሚባለው ኢትዮጵያዊ ፌዴሬሽን የነሱን ያክል ገንዘብ ሳይኖረው በርካታ ህዝብ ከጎኖ ማሰለፍ ችሎዋል። እንዲያውም ስታዲየሙ ሞልቶ ሰው እስኪመለስ ድረስ። በዚህ በአል ከፍተኛ የሆነ የአንድነትና የአገር ፍቅር ስሜት የታየበት፣ የኢትዮጵያ ባንዲራ ከፍ ብሎ በብዛት የተውለበለበበትና ያሸበረቀበት፣ ሰዎች ከብሄራቸው ይልቅ ኢትዮጵያዊነታቸውን ያገነኑበት ትልቅ በአል ነበር።

ባዶ ስታድየም የታቀፉትና አፍረው በውርደት ለተመለሱት አልሙዲ የባህርዳሩ እድል በማፅናኛነት ተሰጣቸው። ኢትዮጵያዊያን በነፃነት በሚኖሩበት አሜሪካ ግን አልሙዲ በገንዘባቸው የህዝብን ድጋፍ መግዛት አይችሉም። በገንዘብ ምንም ማድረግ እንደማይችሉም ሊያውቁት ይገባል።

በአ/አ የሚገኙት ተከሳሹ ከፓትርያርኩ ጋራ በቅዳሴ እየተሳተፉ በመታየት ለማምታት እየሞከሩ ነው የግለሰቡን ኑፋቄ አስመልክቶ ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በተደጋጋሚ የተላኩ ማስረጃዎች ‹እንደጠፉ› ሲገለጽ መቆየቱ ተከሳሹ ከዓላማ ተባባሪዎቹ ጋራ የጥቅም መረብ ለመዘርጋቱ ማሳያ ኾኗል በእልቅና ካባ ፓስተር መቅደስ ገባ?! በጀርመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቪዝባደን ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር አስተዳዳሪ የኾኑትና በመናፍቅነት አቤቱታ የቀረበባቸው የ«ቄስ» ገዳሙ ደምሳሽ …

ምንሊክ ሳልሳዊ :- በዚህ ሳምንት አትክሮት ማግኘት ከሚፈልጉ ወገኖቻችን በዋነኝነት በኩዌት የሚኖሩ እና በስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ናቸው:: ባሳለፍነው ቀናት በዋና ዜናነት በአገሪቱ የስፖርት ሚኒስትር መኖሪያ ቤት ውስጥ የምትሰራ ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ የአሰሪዋን ሴት ልጅ ገላለች ተብሎ የተዘገበውን ዜና ተከትሎ ኢትዮጵያውያን በስጋት ላይ ሲሆኑ እንዲሁም ተከራካሪ የዜግነት መብታቸውን የሚያስከብር ኤምባሲ መጥፋቱ እና በኤምባሲው የሚፈጸመውን ደባ በከፊል ለማየት እንሞክራለን::

የዚህ ዘገባ ምንጮች በኩዌት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ተጨማሪ መረጃ ያላቸው ሊልኩልን የሚችሉ መሆኑን ለመግለጽ እወዳለሁ:: መረጃውን ላደረሱን ወገኖች ምስጋና አቀርባለሁ::
ምንሊክ ሳልሳዊ
በአሁኑ ወቅት በኩዌት ለኢትዮጵያውያን ነገሮች ሁሉ አስቀያሚ እና አስቸጋሪ እየሆኑ እንደሆን ለኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ቅርብ የሆነ ኢትዮጵያዊ ገልጿል::ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደረጉ በደሎች ተከራካሪ የመንግስት አካል እና የኤምባሲ ሰው መጥፋቱ ለአሁኑ ወንጀል መፈጸም እና ስጋት መንስኤ እንደሆነ ጠቁሟል::በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሱ በደሎች እና ከአሰሪዎቻቸው እና ከቀጣሪ ድርጅቶች ጠፍተው የሚመጡ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሃገራቸው መመለስ ሲገባው ከደላሎች ጋር በመመሳጠር ሌላ ስራ በማስገባት ችግሩ እንዲሰፋ ያደረገው እምባሲው እና ሆዳም ዲፕሎማቶቹ ናቸው ሲል ይኸው የኮሚኒቲው ሰው ገልጿል::

ኢትዮጵያውያን በኩዌት እስር ቤት እየተሰቃዩ ከፍተኛ ወጪ ከኤምባሲው እና ከኮሚኒቲው በማውጣት ደግሰው በመጨፈር ላይ በነበሩበት ሰአት ከኢህ ቀደም ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠማቸው ሲሆን ወገኖቻችን በእስር ቤት እየተሰቃዩ ለምን እንዲህ አይነት ድግስ ይደገሳል:: አስፈላጊውን ወጪ በማድረግ ወደ ሃገራቸው የሚመለሱ ይመለሱ ያሉ ወገኖችን የተለያየ የኤምባሲ ትብብር በመከልከል ወደኤምባሲው በር እንዳይደርሱ በማገድ ከፍተኛ የሆነ የግል ጥቅምን ያማከለ በደል እየተፈጸመ መሆኑን የኮሚኒቲው ሰው አጫውቶናል::ለማንም ተደግሶ የማያውቅ ኮሚኒቲው የኢትዮጵያ ሆኖ እያለ ለሌሎች ኢትዮጵያውያን እና ግለሰቦች ሳያገለግል የትግራይ ልማት ማህበር አላማን ሲያስተምር ይውላል ሲሉ አባላቱ ይተቹታል:: የታሰሩትን ለጊዜው ተወት አድርጓቸው እና የሃገራችንን መልካም ገጽታ እናስተዋውቅ እያሉ ለዜጎች አትኩሮት በመንፈግ አሁን ላለንበት ስጋት አብቅተውናል ሲሉ ኢትዮጵያውያን በማማረር ይናገራሉ::

ኮሚኒቲው ሲቋቋም ለታሰሩ እና ለተቸገሩ መፍትሄ ይሆናል ተብሎ የነበረ ቢሆንም በስሙ መካከል ህዳሴ የሚል ቃል በመጨመር ቢሮውን ከነበረበት ቦታ ወደ ኤምባሲው ውስጥ በማዘዋወር ፖለቲካ እየሰበከ ኢትዮጵያውያንን ረስቷል ሲሉ ይናገራሉ::ሌላው ነገር ይላሉ ኢትዮጵያውያኑ ማንኛውንም ደብዳቤ በኤምባሲውም ይሁን በኮሚኒቲው ማህተም ተደግፎ ቢጻፍ በኩዌት ውስጥ ተቀባይነት የለውም ሲሉ ይገልጻሉ::የመኖሪያ ፈቃድ ለማሳደስ በእጃችን ፓስፖርት እያለ ፓስፖርቱን ለመቀበል የኩዌት መኖሪያ ፈቃድ የሚያድሰው አካል ብዙ መጉላላት እና ወከባ እንደሚፈጽምባቸው እና ይህንንም ለኤምባሲው ሪፖርት ቢደረግ የራሳችሁ ጉዳይ የሚል ዘለፋ አዘል መልስ እንደሚሰጡ ታውቋል::

በግድያ ወንጀል ተጠርጥራ የተያዘችው ኢትዮጵያዊት ተከትሎ የመኖሪያ መታወቂያዎች እንዲታደሱ መደረግ የጀመረ ሲሆን ካሁን በፊት NON KUWAITI የሚል ሲጻፍ የነበረ ሲሆን በኣሁን ሰአት ለኢትዮጵያውያን በተለየ መልኩ Ethiopian ኢትዮጵያዊ የሚል መጻፍ የተጀመረ መሆኑ ታውቋል::

የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ምንም መከራከር የማይችል እና በመኪና ተገጭተው የሞቱ ታንቀው ራሳቸውን ከፎቅ ወርውረው የሞቱ ኢትዮጵያውያን ደብዛቸው እና የሞት ጉዳያቸው እንዳይነሳ ኮሚኒቴው በመሸፋፈን ለችግር እየዳረገን ነው ሲሉ በኮሚኒው ላይ አማረዋል::በ17 አመቷ ወደ ኩዌት የገባችው እና በአሁን ሰአት የ22 አመት ወጣት የሆነችው በግድያ ተጠርጥራ የተያዘችው ኢትዮጵያዊት በአሰሪዎቿ ልጆች የተደፈረች መሆኗን ለኤምባሲው ቅርብ የሆነ ግለሰብ ተናግሯል::ግድያውን ከመፈጸሟ በፊት በልጁ የተደፈረች እና ይህንን ጉዳይ ለሴት ልጂቷ ብትናገር የሚሰማት ያጣት እና የደበደቧት መሆኗን እና ይህንን ተከትሎ ወንጀሉን ፈጽማው ይሆናል የሚሉ ግምቶች በስፋት ይነገራል::

በኢምባሲው ውስጥ የሚደረገው ከፍተኛ በደል በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ሲሆን በኤምባሲው ውስጥ ከ400 እስከ 500 የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን የሚገኙ ሲሆን: ከፍተኛ የሆነ መጉላላት እየደረሰባቸው ለኣእምሮ ጉዳት ለጭንቀት ለድብርት እና ለእብደት መዳረጋቸውን የገለጹ ሲሆን በኤምባሲው ውስጥ ከፍተኛ የምግብ እጥረት ያለ ሲሆን ኤምባሲው ግን በድግስ እየተንበሸበሸ ኮሚኒቲው በየድህረገጹ የፌሽታ ፎቶዎችን በመርጨት ከፌሽታው ጀርባ ግን የኢትዮጵያውያን ሞት እና ሰቆቃ ለእይታ እንዳይበቃ እያደረገ ሲሆን አንድም ቀን የሞቱ እና የተበደሉ ኢትዮጵያንን ቦታ ሳይሰጥ የኢትዮጵያውያን መብት እና ነጻነት ሳያስከብሩ በአደባባይ ስንገላታ እያዩን ያላግጡብናል ያመናጭቁናል ከፖሊስ ጋር ይተባበሩብናል በማለት አቤቱታቸውን የሚሰማ አካል እንዳላገኙ እና በስጋት አጣብቂኝ ውስጥ መግባታቸውን ኢትዮጵያውያን ተናግረዋል:: ተጨማሪ ዘገባዎች ካሉ እንመለሳለን:: ምንሊክሳልሳዊ

በማስመሰል ታጥሮ መሆን በጠፋበት
ምን አገባኝ የሚል በተከማቸበት
የባይተዋር መንፈስ ከሞላ ባገሩ
ዘመኑን ማወቂያ ይሄ ነው ሚስጥሩ
ይሄን ጊዜ ጠርጥር እንደጠፋ ዘሩ፡፡
(ገጣሚ ደምሰው መርሻ/ያልታተመ)

አዎን፣ ገጣሚ ደምሰው እንዳለው እኔም በዚህ ዘመን “ዘሩ እንደጠፋ” አሊያም ሊጠፋ እንደተቃረበ እጠረጥራለሁ፡፡
ስለምን? ቢሉ …በኢትዮጵያችን ለህሊናው፣ ለሕዝብና ለሀገሩ የሚቆረቆር፣ የእውነት ተሟጋችና የሞራል ልዕልናን የተቀዳጀ ሙሉ ሰው ፈልጎ ማግኘት እጅግ አተካች ሆኗልና፡፡ የግል ጥቅም አሳዳጅ፣ አፋሽ-አጎንባሽ በሞላበት፣ እንደ ቴዎድሮስ ለሀገር ቤዛ መሆን፤ እንደ ግርማሜዎቹ እና ወርቅነህ የራስን ምቾት ወዲያ ጥሎ በጠገበ ሆድ ከወገን ጋር መራብና ከጎኑ መቆም፤ እንደ አቶ ሽፈራው ደሳለኝ አስፈሪ ሞት ከከበበው ሸለቆ ውስጥ በህይወት ለመውጣት ሲባል የጠላትን ጫማ ከመላስና ያላመኑበትን ተናግሮ ምህረት ከመጠየቅ ይልቅ በድፍረት ሞትን ፊት ለፊት መጋፈጥ ወይም ግንባርን ለአረር መስጠት እንደ ተረታ-ተረት ከተቆጠረ ዘመናት አልፏል (አቶ ሽፈራው ደሳለኝ ማን ናቸው? ለሚለኝ አንባቢዬ ‹‹የታኀሣሡ ግርግር እና መዘዙ›› የተሰኘውን የብርሃኑ አስረስ መጽሐፍ ገፅ 302ን እንዲያነብ እጋብዘዋለሁ) አሊያም ደግሞ የሰው ዘር በመሆን ብቻ የሚገኘውን የሞራል ልዕልና ከትውልድና ሀገር ጥቅም አኳያ ለማጠየቅ በዚህ አውድ ለማነሳው ተጠየቅ በአንፅሮ ለማፍታታት ይጠቅመኝ ዘንድ እኔው ራሴ እዚሁ ጠቅሼው አልፋለሁ፡፡
የመጽሐፉ ደራሲ ‹‹በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ጊዜ የድጋፍ ንግግር አድርጋችኋል በማለት በመንግስት ተይዘው ከድሬዳዋ ወደ አዲስ አበባ ከተላኩት አንዱ የሆኑት…›› ብለው ከአቶ ሽፈራው ደሳለኝ ጋር ከአስተዋወቁን በኋላ እንዲህ በማለት ትርክታቸውን ይቀጥላሉ፡- ‹‹…አቶ ሽፈራው ከድሬዳዋ ወደ አዲስ አበባ ተልከው ለፖሊስ ቃላቸውን ሰጥተው ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡ የእምነት ክህደት ቃል ሲጠየቁ ዳኛው ‹ሠርተሃል ለተባለው ወንጀል ጥፋተኛ ነህ፣ አይደለህም?› ይላቸዋል፡፡ ‹የቱን ወንጀል?› ሲሉ አቶ ሽፈራው ዳኛውን ይጠይቃሉ፡፡ ዳኛው አቶ ሽፈራው ሠርተዋል የተባለውን የወንጀል ቃል ሊናገሩት አልወደዱም አልደፈሩምምና ‹አንተ የሠራኸውን?› ብለው ጠየቁ፡፡ አቶ ሽፈራው ‹እስቲ ወንጀል የተባለው ይነበብልኝ› ብለው አጥብቀው ይጠይቃሉ፡፡ ይሄን ጊዜ ዳኛው ሳይወዱ ‹ይህን ጣሳ እግዚአብሔር ገላገለን፣ አወረደልን ማለትህን፤ …ለዚህ ጥፋተኛ ነህ አይደለህም?› ይሏቸዋል፡፡ ‹የለም ተስተካክሎ ይጻፍልኝና እምነት ክህደቴን ልናገር› ይላሉ፡፡ ‹የለም በዚህ ላይ ጥፋተኛ ነኝ በል› ይሏቸዋል፡፡ ‹ትክክለኛ ቃሌ ይጻፍና ነው እንጂ እንዲሁ ጥፋተኛ ነኝ፤ አይደለሁም፤ አልልም› ብለው ይመልሳሉ፡፡ ‹እሺ ምን ተብሎ ይስተካከል› ሲሏቸው፤ ‹ይህን የበሰበሰ የተጠረማመሰ አሮጌ ጣሳ እግዚአብሔር ገላገለን ነው ያልኩት› ሲሉ ዳኞቹ የተባለውን አልሰማንም ለማለት ራሳቸውን ጠረጴዛ ስር አግብተው ተደበቁ፡፡››
በዚህ ዘመን ራሳቸውን ጠረጴዛ ስር አግብተው እንደ ሰጎን አንገታቸውን ቀብረው በፍርሃት የሚኖሩ አድር፣ እበላ-ባይ፣ ፈሪ ሰዎች የአቶ ሽፈራውን ባመኑበት መቆም እንደ አጎል ጀብደኝነትና ሞኝነት ቢቆጥሩት አስገራሚ አይሆንም፡፡ የሆነው ሆኖ እንደ ብልህነት አሊያም ብልጥነት ተደርጎ የሚወሰደውን የአድርባይነት ‹‹ስልት›› ለማሳየት አንዲት ሀገርኛ ምሳሌ እዚህ ጋ ለንፅፅር ላቅርብና እንደ ፕሮፌሰር መስፍን ለራሴ ጽሑፍ ‹‹F›› ከመስጠቴ በፊት ወደ አጀንዳዬ ልዝለቅ፡፡
ታሪኩ ዝናው በስፋት የናኘ ሽፍታ የመሸገበትን (ግዛቱ ያደረገ) ጥቅጥቅ ያለ ጫካ አቋርጦ ስለሚያልፍ መንገደኛ ገጠመኝ ነው፡፡ መንገደኛው ለሰዓታት ከተጓዘ በኋላ ድንገት ሽፍታው እጅ ይወድቅና ስንቅ የቋጠረበትን ስልቻ ጨምሮ ከላይ እስከታች ይበረበራል፤ ሆኖም ሰባራ ሳንቲም ሊያገኝበት ባለመቻሉ ከመጠን በላይ የተበሳጨው አያ ሽፍታ ሆዬ ንዴቱን ለማብረድ ሲል ‹‹ውዳሴ ዜማ አቅርብልኝ!›› በማለት ቀጭን ትዕዛዝ ይሰጠዋል፤ በፍርሃት ነፍሱ እጉሮሮው የተወተፈችበት መንገደኛም ተንፈስ ብሎ ለመረጋጋት እየሞከረ እንዲህ ሲል አቀነቀነለት ይባላል፡-
‹‹አይኑ የተኳለ ጠላት የሚጋረፍ
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ 2
ጠብ-መንጃ ገስጋሽ ጉብታ ተሻግሮ
ከዘብጥ የሚናደፍ
እንደሚካኤል ነህ ጠላትህም አይተርፍ!››
እነሆም የሀገሬ ምድር እንዲህ ባሉ ሀሞተ-ቢስ አወዳሾችና አስመሳዮች ተጥለቅልቃ እጆቿን ወደ ሰማይ ከዘረጋች (ሱባኤ ለመግባት) ሰነበተች፡፡ በርግጥም ከብዙሀኑ በተሻለ ማንሰላሰል ይሳናቸዋል ተብለው የማይታሰቡ ‹‹ምሁራን››ም ሆኑ ‹‹መንፈሳዊ››ነታቸው የበዛ የኃይማኖት መሪዎች በግል ጥቅመኝነት ታውረው ከስርዓቱ ጋር እጅና ጓንት በመሆን የጭቆና አገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም በሀሰት መስካሪነት የቅጥፈት ምላሳቸውን ሲያንበለብሉ መስማት ‹እግዚኦ› የሚያስብል አስደንጋጭ መናፍቅነት መሆኑ ቀርቶ እንደ ተራ ነጋዴ ንግግር፣ ተራ የዕለት ተዕለት አጋጣሚ ከሆነ ዘመናት ተቆጠሩ፡፡ ‹‹መንፈሳዊያን›› አባቶች በተከበረው ቤተ-መቅደስ ምኩራብ ላይ ከመእምናኑ ፊት ለፊት ቆመው ቃየልን ‹‹አቤል››፣ በርባንን ‹‹መሲህ›› በማለት ሲሰብኩም ለአመል እንኳ ድንቅፍ አያደርጋቸውም፤ ከግላዊ ጥቅማቸው አሻግረው የግፉአንን የስቃይ እሮሮ ማድመጥም ሆነ ለሌላው ማሳወቅ ጭራሹንም አይሞክሩትም፡፡ ‹‹ምሁራን›› ተብዬዎቹም አርቲስት ሰለሞን ተካልኝ ‹‹ውበት ከቅንድቡ የሚፈስ›› እንዲል፤ ‹አይኑ የተኳለ› እያሉ በሕፃናት ደም ሳይቀር የጨቀየውን ኢህአዴግ መራሹን መንግስት እንዴት እንዴት ‹ብፁእ› አድርገው የውዳሴ ከበሮ ሲመቱለት እንደሚያድሩ እዚህ ጋ ዘርዝሮ ለማቅረብ ማሰብ አባይን በጭልፋ አጋብቶ ለመጨረስ እንደመሞከር ያለ ዕብደት ያስቆጥራል፡፡
ወጣም ወረደ እንዲህ አይነቱ የሞራል ዝቅጠት በትላንት ወይም በዛሬ የእድሜ ገደብ የሚለካ አለመሆኑን በድፍረት መናገር ይቻላል፤ ምክንያቱም በነገሥታቱ የአገዛዝ ዘመን የጀመረና በጣሊያን የአምስት ዓመቱ የወረራ ወቅት እንደወረርሽኝ የተስፋፋ ስለመሆኑ በቂ ማሳያዎች አሉ፡፡ ይህ እንግዲህ ‹‹ሀገር›› ለተሰኘ ማህተም መስዋዕት የሆኑትን አቡነ ጴጥሮስን የመሳሰሉ ታሪክ በታላቅ አክብሮት የሚዘክራቸውን ቀዳማይ አባቶችና እናቶችን ሳንዘነጋ ነው፡፡ እናም የሩቁን ትተን ከ1983ቱ የመንግስት ለውጥ ወዲህ ያለውን እንኳ ብንመለከት ይህን መሰሉ ክስረት ዙሪያችንን ከቦ ሊውጠን የቀረው ስንዝር ታህል ርቀት ብቻ መሆኑን ለመረዳት የማሕበራዊ ሳይንስ ምሁራን ትንታኔን ማገላበጥ አይጠይቅም፡፡ ያኔ ገና በለውጡ ማግስት ህወሓት እና ሻዕቢያ በአንድ አንቀልባ ካልታዘልን በሚሉበት የ‹‹ጫጉላ›› ዘመን፣ ከኤርትራ ምድር የወርቅ ጥርሳቸው ሳይቀር በጭካኔ ወልቆ ባዶ እጃቸውን የተባረሩ ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ በጉምቱው ምሁር ፕሮፌሰር እንድሪያስ እሸቴ የተመራው አጣሪ ቡድን ‹‹ውሸት ነው! ይህ አይነቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ኤርትራ ይኖሩ
በነበሩ ኢትዮጵያውያን ላይ አልተፈፀመም!!›› በማለት አይኑን በጨው አጥቦ በድፍረት ሲያስተባብል፣ አንጀታችን እያረረ ‹‹ይሁና!›› ብለን በትዝብት ማለፋችን እውነት ቢሆንም፤ የዝምታችን ውስጠ-መልዕክት ያልገባው ፕሮፌሰሩ ግን ያረረው አንጀታችን ይበልጥ እርር ይል ዘንድ በተለመደው ቅጥፈቱ ታላቁ የዐድዋ ድል ባለቤትነትን ከሀገር ከፍታ፣ ቁልቁል ወደ ጎጥ ለማውረድ ያልፈነቀለው ቋጥኝ፣ ያልማሰው ስር አልነበረም (በነገራችን ላይ ህወሓት ዛሬም ከዐድዋ ድል ጀግኖች ጋር ጥቁር ደም እንደተቃባ በግላጭ የሚያመላክተው በዘንድሮው 118ኛው ክብረ በዓል ላይ የተስተዋለው አሳፋሪ ትእይንት ነው፡፡ ይኸውም በታሪካዊቷ ዐድዋ ከተማ በሚገኘው ሶሎዳ ተራራ ስር ‹ድሉን ለመዘከር› ከተሰቀሉት የእቴጌ ጣይቱ፣ የራስ አሉላ አባነጋ፣ የባልቻ አባነፍሶ እና የባሻ አውዓሎም ግዙፍ ምስሎች መሀል የተሸናፊው ሀገር ህዝብ ሳይቀር በድሉ ዕለት ሮማ በተሰኘው አደባባዩ ‹‹ቪቫ ምኒሊክ›› እያለ በታላቅ ጩኸት ያወደሰው የታላቁ ንጉሠ ነገሥት ምስል አለመካተቱ ነው፡፡ …መቼም ይህ ለምን ሆነ? ብለን የክልሉን አስተዳዳሪ ጓድ አባይ ወልዱን ብንጠይቀው ‹‹በጦርነቱ ወቅት ምኒሊክ መሸሽ ጀምሮ ነበር›› የሚለውን ዝነኛ ህወሓታዊ ትርክት ገልብጦ፣ ‹‹በስራ መደራረብ በተፈጠረ ስህተት ነው›› ብሎ በክፍለ ዘመኑ ታላቅ ሽርደዳ አንጀታችንን ይበልጥ ድብን እንደሚያደርገው ቅንጣት ታህል አትጠራጠሩ)
ለማንኛውም እንደ ፕሮፌሰር እንድሪያስ ያሉ በድሃው ሕዝብ ጥሪት የከፍተኛ ደረጃ የትምህርት ዕድል ማግኘት የቻሉ በርካታ እበላ-ባይ ‹‹ምሁራን›› ስርዓቱ የሥልጣን ዘመኑን ለማራዘም የሚያምታታበትን ‹‹የሁለት ዲጂት የኢኮኖሚ ዕድገት›› የፈረንጅ ጥናቶችን በጥራዝ-ነጠቅነት እያጣቀሱ ምክንያታዊ መስለው ሊያሳምኑን በከንቱ ብዙ ደክመዋል፡፡ በአናቱም የመከላከያ ሠራዊቱ ለባዕድ ሀገር ጥቅም ሲባል ሶማሊያን በወረረበት ወቅት አንዳንድ የዩንቨርስቲ መምህራን እና ‹‹የፖለቲካ ተንታኞች›› በመሬት ያለውን ተጨባጭ እውነታ ይሁነኝ ብለው ወደጎን ገፍተው አገዛዙ ቀን ከሌት ‹‹እመኑኝ!›› በሚል ጩኸት ያሰለቸንን ሰበብ፣ በጥናት እንደተረጋገጠ አስመስለው ለመተንተን ያደርጉት የነበረው እሽቅድምድም ሁሌም በሀዘን የምናስታውሰው ነው፡፡
የኃይማኖት መሪዎችም ምንም እንኳ በነቢብ የአገልግሎታቸው ዋጋ በፈጣሪ መንግስት መሆኑን ደጋግመው ቢነግሩንም፣ በሀልዮ የሚታየው የአሸርጋጅነት ግብራቸው ግን ምድራዊውን ጨቋኝ ስርዓት ደግፎ የሚይዝ ምሰሶና አቅፎ የሚያሞቅ ክንድ ከሆነ በርካታ አስርታት ተቆጥረዋል፡፡ የእስልምና እምነት የበላይ ወሳኝ አካል የሆነው መጅሊስ መእምናኑ ያነሱት ፍትሃዊው የመብት ጥያቄ ተቀልብሶ፣ ሕዝባዊ ውክልና የተሰጣቸው የኮሚቴ አባላት ለአስከፊው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት የተዳረጉበትን መንግስታዊ ሽብርተኝነት ለመሸፋፈን ከመተባበርም አልፎ ቅዱስ ቁራንን አዛብቶ እስከመጥቀስ መድረሱ በትዝብት ያሳለፍነው የትላንት ኩነት ነው፡፡ የክርስትና እምነት መሪዎችም በተመሳሳይ ሁናቴ የስርዓቱን የጭካኔ እርምጃዎች እንደ ቅዱስ ተግባር ለማፅደቅ ያልረጩት ጠበል፣ ያልጠቀሱት የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አልነበረም፡፡ ሌላ ሌላውን እንኳን ትተን በቅርቡ ህይወቱ ያለፈው የኦሮሚያ ክልል አስተዳዳሪ የአለማየሁ አቱምሳ ስርዓተ ቀብር ላይ ፓትርያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ‹ዲሞክራሲን ለማስፈን መስዋዕትነት የከፈለ፤ ሩጫውን የጨረሰ፤ ተጋድሎውን
በብቃትና በንቃት የተወጣ…› እያሉ አፋቸውን ሞልተው የምስክርነት ቃላቸውን ሲሰጡ ሀፍረት ብሎ ነገር ለቅፅበት እንኳን ዝር 3 አላለባቸውም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ በሰውየው ህልፈት እጃቸው እንዳለበት የሀሜት ወሬ የሚናፈስባቸው እነዚያ ጲላጦሳውያን ጓዶቹ እንዳሻቸው ቢያንቆለጳጵሱት መቼስ የፕሮፓጋንዳ ስራ ነው ብሎ በቸልታ ማለፍ ይቻል ይሆናል፡፡ ነገር ግን የሰማዩን መንግስት ብቻ ያገለግሉ ዘንድ በቃሉ እንዲመላለሱ ግድ የሚላቸው ‹‹መንፈሳውያን››፣ እንዲያ የገዛ ወገኑን ‹‹ኦነግ!›› በሚል የሀሰት ውንጀላ በጥይት ሲደበድብና ሲያስደበድብ፤ መከራን በሕዝብ ላይ እንደምርጊት ሲለስን፤ አምባገነን ስርዓቱን በታማኝነት ሲያገለግል… ያለፈን ሰው ‹‹ዲሞክራት›› እያሉ በአደባባይ ማወደስ በቤተ-ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ ራሱ የተነቀፈውን ለእግዚአብሔርና ለቄሳር ዕኩል መገዛትን እንደትክክለኛ ተግባር አምኖ መቀበል ነው ወደሚል ጠርዝ መገፋታችን አይቀርም፡፡
በግልባጩ በሁሉም እምነት ያሉ ‹‹መንፈሳዊ›› መሪዎች ስርዓቱ በድህረ-ምርጫ 97ም ሆነ በተከታዮቹ ዓመታት የተቃዋሚ ፓርቲ የአመራር አባላትን እና ጋዜጠኞችን እንደ ጥጃ እያሰረ በግፍ ሲያሰቃይ ድርጊቱን ለመንቀፍም ሆነ ዘላቂ ዕርቅ እንዲወርድ ለመማለድ አንዳች ሙከራ አለማድረጋቸው በታሪክ ጥቁር መዝገብ በጉልህ ቀለማት ሰፍሮ የሚኖር ሀጢያታቸው ነው (የቅንጅት እስረኞችን ለማስፈታት የተሄደበት የ‹‹ሽምግልና›› መንገድ የአቶ መለስ ዜናዊ ቧልት ስለመሆኑ ከቶም ማንም ሊጠራጠረው አይችልምና እዚህ መጥቀሱ አስፈላጊ አይመስለኝም)
ሌላው የማሕበረሰባችን የሞራል እሴት በእጅጉ መዝቀጡን የሚያስረግጥልን ብዙሀኑ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በተዘፈነበት ለመደነስ፣ በተደገሰበት አሳላፊ ለመሆን የሚያደርጉትን መገፋፋት ስናስተውል ነው፡፡ ስርዓቱ ከሚያራምደው ‹‹አብዮታዊ ዲሞክራሲ›› ርዕዮተ-አለም የተቀመረውን ‹‹ፌደራሊዝም አወቃቀር››ን ተንተርሶ ሀገሪቱን በዘውግ ከፋፍሎ እና በሕዝብ መካከል የጥርጣሬ መንፈስ አንብሮ የሥልጣን ዕድሜ ማራዘሙን በግጥምና ዜማ ማወደስ የእህል-ውሃ ጥያቄ ካደረጉት በርካታ ዓመታት ነጉደዋል፡፡ እንዲህ አይነት የሙዚቃ ስራ በአንዳንድ ክልሎች መሬት የሚያሸልም ፈጣን አዋጪ አድርባይትመንት (ኢንቨስትመንት ላለማለት ነው) እስከ መሆን መድረሱ ከታፊና ነጋዴ አርቲስቶች በዘውጉ ዙሪያ ይረባረቡ ዘንድ ታላቅ ልማታዊ አብነት ሆኗቸዋል፡፡ ይህ ሁናቴም በኢትዮጵያ ኪነ-ጥበብን የንፁሃን መታጣት ከድንጋይ ወገራ የታደጋትን የኦሪቷ ዘማዊት ከማስመሰልም አልፎ እንደ ነገሥታቱ ዘመን የአዝማሪ ጨዋታ፤ የቤተ-መንግስቱ መዝናኛ እና አጀንዳ ማራገቢያነት እስከ መሆን ሞዴል ተሸላሚ አድርጓታል፡፡ ይሁንና ቁጥራቸው ጥቂት ቢሆንም ቴዎድሮስ
ካሳሁንን (ቴዲ አፍሮን) የመሳሰሉ መክሊታቸውን እንደ ጉሊት ሽንኩርት ለሽያጭ ያላቀረቡ ከያኒያን፣ ደራሲያን፣ ገጣሚያን… የመኖራቸውን እውነታ ሳንዘነጋ፤ ሀገሪቱ ‹‹ሰው አይብቀልብሽ!›› ተብላ የተረገመች እስኪመስል ድረስ ብሔራዊ ጥቅም፣ ህሊና፣ ሞራል፣ እውነት የረከሱበትና የተዋረዱበት ዘመን ላይ መድረሷን የሚያስረግጡልን በርካታ ማሳያዎች አሉ፡፡
ከጥቂት ወራት በፊት በብአዴኑ ካሳ ተክለብርሃን ፊት-አውራሪነት የሶማሌ ክልልን የጎበኙት አርቲስቶቻችን፣ ገና ድሮ ጆርጅ ኦርዌል ‹‹Animal Farm›› ብሎ በሰየመው መጽሐፉ ‹‹አራት እግር ጥሩ፤ ሁለት እግር መጥፎ›› እያሉ በመንጫጫት ስብሰባን ለመረበሽና ተቃውሞን ለማጨናገፍ አሳማው ናፖሊዮን እንዳሰለጠናቸው አይነት በጎች፤ ኢህአዴግ በጎጥ የካፋፈለውን ሕዝብ ‹‹በታሪኩ ከመቼውም ጊዜ በላይ አሁን አንድ ሆኗል!!›› በማለት በሬ ወለደ የሀሰት ምስክርነታቸውን አምነን እንድንቀበል ለማድረግ ለሳምንታት ተንጫጭተው ሊያደነቁሩን ሞክረዋል፡፡ እነዚህ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የክልሉ ነዋሪዎች ገና ዛሬ (በኢህአዴግ እፁብ ድንቅ እና ፍትሀዊ አስተዳደር) ኢትዮጵያዊነት እንደተሰማቸው፤ ገና ዛሬ በፍቃደኝነት ኢትዮጵያውያን እንደሆኑ አስመስለው ለማሳመን የሄዱበት የቁልቁለት መንገድ አጥንት ድረስ በሚዘልቅ ሀዘን እንዳኮራመተን እነርሱም ይጠፋቸዋል ብዬ አላስብም፡፡ ጉዳዩ ሆድ ሌላ፣ እውነት ሌላ ሆኖባቸው እንጂ፡፡ ግና፣ የቄሳሩ ጲላጦስም ‹‹እውነት ምንድር ነች?›› እንዲል፣ እውነት ለእነርሱ ዋጋዋ ስንት ነው? መቼም ከእውነት ይልቅ ግድ የሚሰጣቸው የሆድ ነገር ነው፤ እበላ አዳሪዎች ናቸውና፡፡
በጥቅሉ በኢትዮጵያችን ከምሁር እስከ ተርታው፤ ከጳጳሳት (ፓስተራት) እና ሼሆች እስከ መናፍቃውያን፤ ከልሂቅ እስከ ደቂቅ፤ ከጄነራል እስከ ወታደር፤ ከከያኒ እስከ ጽሑፍ ገልባጭ፤ ከቱጃር እስከ ጥሮ-ግሮ አዳሪ፤ ከመምህር እስከ ተማሪ… ስር የሰደደ አድርባይነት እና የሞራል ክስረት ለመንሰራፋቱ አይነተኛ ማሳያው አምባገነኑ ኢህአዴግ እንዲህ ሚሊዮኖችን ረግጦ እየጨፈለቀ፣ አስሮ እያንገላታ፣ ከሀገር እያሰደደና እየገደለ… ከሁለት አስርት በላይ መቆየት የመቻሉ ምስጢር ነው፡፡ ግና፣ የሕዝብን መከራ በማራዘም ኪስን ማደለብ፣ ግላዊ ፍላጎትን ማርካት ሁሌም አትራፊ ሊሆን እንደማይቻል መዘንጋት የለበትም፡፡ ማን ነበር ‹የተከፋፋለና አድርባይ ሕዝብን ከጭቆና ማላቀቅ፣ ሰማይን የማረስ ያህል አዳጋች ነው!› ያለው?
አዎን፣ ከ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ጀምሮ በጉልበታም ስርዓታት የጭካኔ መዳፍም ሆነ በግላዊ ጥቅመኝነት እየተናዱ የመጡት የባህል እና የሞራል እሴቶች ትውልዱን ዛሬ ላይ ለደረሰበት አስከፊ ማሕበራዊ ቀውስ መዳረጋቸው አሌ የማይባል ነው፡፡ ርግጥ ነው የችግሩ ስፋትና ጥልቀት እንደ ስርዓቱ የፖለቲካ ፍልስፍና በዘውግ የተከፋፈለ አይደለም፤ ብዙሀን እና ህዳጣን የሚል መስፈርትንም የተከተለ አይደለም፤ ኃይማኖታዊ መለያም የለውም፤ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች አለቅጥ መንሰራፋቱ በግላጭ ይታያልና፡፡ ይህም ነው መፍትሔውን ስር ነቀል የማሕበራዊ አብዮት (ለውጥ) ብቻ እንዲሆን ያስገድደው፡፡
የቀደሙት ሁለት አብዮቶች በዋናነት ያነሷቸው የብሔር እና የመሬት ጥያቄ መክሸፋቸው (መቀልበሳቸው) ዛሬም ሶስተኛ አብዮትን የማይቀር ዕዳ አድርጎ የመውሰዱ ሁነት እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ሥራ-አጥነት፣ ከነባሩ ባህል ማፈንገጥ፣ ሙስና፣ በሕብረተሰቡ ዘንድ አክብሮትና 4 ተሰሚነት ያላቸው ታላላቆችን አለማደመጥ፣ አድርባይነት፣ ደንታቢስነት፣ ዶሮ ሳይጮኽ ደጋግሞ መክዳት፣ የ‹‹ስቀሎ፣ ስቀሎ…›› ሀሰተኛ ድምፅ መበራከት፣ ኢ-ሞራላዊ ድርጊቶች እና የመሳሳሉት ትውልድና ሀገር ገዳይ ደዌዎችን ለመፈወስ ከማሕበራዊ አብዮት ያነሰ መፍትሔ እንደሌለ ከተለያዩ ሀገራት ታሪክ መረዳት ይቻላል፡፡ በነገራችን ላይ ኢህአዴግ በየትኛውም የዓለማችን ሀገራት የተከሰተ ሕዝባዊ አብዮት እንቅልፍ እንደሚነሳው በርካታ ማሳያዎች አሉ፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ለተከታታይ ቀናት ‹‹ተንታኝ›› ጭምር በመጋበዝ፣ ምስራቅ አውሮፓ ድረስ ተጉዞ የተሳካውን የዩክሬን አብዮት ከቀለም ጋር በማያያዝ ለማውገዝ ያቀረባቸው ፕሮግራሞች የፍርሃቱ መጠን አንዱ ማሳያ ተደርገው ሊወሰዱ ይችላል፡፡ ግና፣ እውነት እውነት እልሀለሁ በመቶ ሺህ የሚቆጠር የታጠቀ ኃይል ቢሰለፍ፣ እልፍ አእላፍ ፊርማቶሪዎች በሕዝብ መሀል ቢሰገሰጉ፣ ሚሊዮናት ካድሬዎች ሀገር-ምድሩን ቢያጥለቀልቁ፤ አገዛዛዊ ጭቆና እና ማሕበራዊ ክስረት እስካለ ድረስ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ፣ የትኛውም ምድራዊ ኃይል ሊያመክነው የማይችል አብዮት መቀጣጠሉ የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ በመጨረሻም ይህንን ጽሑፍ ጄነራል መንግስቱ ነዋይ በተለምዶ ‹‹የታሕሳስ ግርግር›› እየተባለ የሚጠራውን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መክሸፍ ተከትሎ ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት በሰጠው ቃል እቋጨዋለሁ፡-
‹‹…ዋ! ዋ! ዋ! ለእናንተም ለግዥአችሁ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሀሳቤ በዝርዝር ገብቶት በአንድነት በሚነሳበት ጊዜ የሚደርስባችሁ መዓት የሚያሳቅቅ ይሆናል፡፡››
ትንቢቱ ከ13 ዓመት በኋላ ከእጥፍ በላይ መፈፀሙን ስናስታውስ፣ በጥቅመኝነት ስሌት ከስርዓቱ ጋር ተወዳጅተው የግፉአንን የመከራ ዕድሜ የሚያራዝሙ አድርባዮችም ሆኑ የአገዛዙ ልሂቃን ሕዝቡ ‹‹ሆ!›› ብሎ በአንድነት የተነሳ ዕለት ከመዓቱ ያመልጡ ዘንድ አይቻላቸውምና ዛሬውኑ ‹ንሰሀ ግቡ!› ብሎ ማሳሰብ ግድ ይላል፡፡ …ዋ! ዋ!! ዋ!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

ይድነቃቸው ከበደ

Image

ሰብአዊ መብቶች እያንዳንዳችን ሰው በመሆናችን ብቻ የሚገቡን ከሰብአዊነታችን ተለይተው ሊታዩ የማያችሉ መብቶች ናቸው፡፡ መንግስታት እነዚህን በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተሰጣቸውን ሰብአዊ መብቶች ለማክበር ለማስከበርና ለማሟላት በቀዳሚነት ኃላፊነት አለባቸው፡፡ በዚህም መሰረት ኃላፊነት ከፈረሙ ቀደምት አገራት መካከል ኢትዩጵያ ትገኝበታላች፡፡

ይሁን እንጂ የሴቶች ሰብአዊ መብቶች በሚፈለገው መልኩ ተግባራዊ ካለመሆኑ ባሻገር ኢ-ፍትሃዊነት እጅግ የበዛ ነው፡፡ ይህም በመሆኑም እ.ኤ.አ. በ1908 በአሜሪካ ኒወርክ ከተማ በጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ይሰሩ የነበሩ ላብአደር ሴቶች ‹‹ለእኩል ሥራ እኩል ክፍያና የተመቻቸ የሥራ ሰዓት ለሴቶች›› በሚል መፈክር የሥራ ማቆም አድማ በማካሄድ የሴቶች ድምፅ እንዲስተጋባ አድርገዋል፡፡ ይህን ተከትሎ የዓለም ሴቶች በማህበር በመደራጀት ትግላቸውን በማጠናከራቸው የዓለም መንግስታትን አስተሳሰብ በመለወጥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል አገሮች የሴቶች መብት ስምምነት/ኮንቪክሽን/ እንዲፈራረሙ እብይ ምክንያት ሆነዋል፡፡
እ.ኤ.አ. በ1910 በኮፕን አገር ከተማ በተደረገው ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የሴቶች ጉባሄ ላይ የመነሻ ሃሳብ በማቅረብ ማርች 8 በየዓመቱ እንዲከበር ያደረጉት ሴቶች ለመብታቸው ያደረጉትን አስታውጾ ለመዘከር ዓለም አቀፍ መድረክ ለማመቻቸት በመቻላቸው ስማቸው በአክብሮት ይነሳል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓሉን ያከበሩት ጀርመን፣አውስትራሊያ፣ሲውዘርላንድ እና ዴንማርክ ለመሆናቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ከዚሁ የአንድነት ተምሳሌትነት በመነሳት በዓለማ አቀፍ ደረጃ ማርች 8 የሴቶች ቀን በማድረግ ዓለም አቀፍ ስያሜዎችን በመስጠት አገራችን ኢትዮጵያ ጨምሮ በተለያየ መልክ ሲከበር አመታትን እቆጥሯል፡፡ የዘንድሮዉም ማርች 8 አለም አቀፍ የሴቶች ቀን እስከ ዛሬ በአገራችን በተከታታይ የኢትዮጵያ ሴቶች ካከበሩት በዓላት የሚለየው ሁሌም የምኮራባቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሠላማዊ ታጋይ ሴቶች የፈፀሙት ገድል ነው፡፡
በአገራችን ኢትዮጵያ የዜጎች መብት በእኩልነት ተጠብቆ በሴቶች ላይ አጥልቶ የኖረው የጾታ ጭቆና እስከዛሬ ምላሽ ያላገኘ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡በተለይ በወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት የስልጣን ዘመን የሴቶች ጭቆና እና የመብት እረገጣ በህግ ማቀፍ ውስጥ መሆኑ ይብልጥ አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡ ይህን ለማለት የሚያስደፍረው የህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ነው በሚባለው ህገመንግሰት የፆታን አድልዎ የሚቀርፍ እና የሴቶችን መብት የሚያመላክት ድንጋጌዎች በውስጡ አካቶ የያዘ ቢሆንም ተግባሪዊነቱ ፕ/ር መስፍን እንዳሉት ‹‹የተፃፈበትን ወረቀት ያህል ዋጋ የማያወጣ ነው››፡፡ ዋጋ አለው እንኳን ከተባለ የትርፉ ተካፋይ የሆኑት የገዥው መንግሰት አጨብጫቢዎች እና የጡት ልጆች ብቻ ናቸው፡፡
በአገራችን መከበር ከጀመረ ከሦት አስርታት በላይ ያስቆጠረው ማርች 8 ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ለሴቶች በሴትነታቸው ከሚደርስባቸው ጾታዊ በደል እና የሰብአዊ መብት ጥሰት ያስቀረላቸው አንድም ነገር የለም፡፡ በተለይ ከላይ እንደተገለፀው በወያኔ/ኢህአዴግ መንግሰት ሴቶች በህግ እና በመብት ጥላ ስር ከፍተኛ የሰብአዊና የዲሞክራሲ ጥሰት እየተፈፀመባቸው ይገኛል፡፡
እጅግ አስገራሚው ክስተት ደግሞ የኢህአዲግ ሴቶች ሊግ ፣ የሴቶች ፎረም ኢህአዲግ የሚያዘው እና አገዛዙ ያስተባበራቸው በርካታ የሴት ማህበራት ተጠሪነታቸው በቀጥታ ለወያኔ መንግስት ስርአት ነው፡፡ ስርአቱ ደግሞ የመላው ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ እና ይሁንታ ያላገኘ መሆኑ ነው፡፡ ነገሩን ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርገው ደግሞ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ከመንግስት ድጋፍ ውጪ በራሳቸው ፍቃድና አቅም አንድም የተደራጀ ማህብር የሌላቸው መሆኑ ነው፡፡ እርግጥ ነው የሴቶች የፅዋ እና የእድር እንዲሁም የዕቁብ ማህበራት በአገራችን ለቁጥር የሚታክቱ ነው፤ግን እነዚህ ማህበራት የሴቶችን ሁለንተናዊ ችግሮችን የሚቀርፉ አይደለም፡፡
ለመደራጀት ሳይሆን ለማደራጀት ትኩረት እና ድጋፍ የሚሰጠው መንግሰት በሴቶች ላይ ማላገጥን ስራዬ ብሎ ተያይዞታል፡፡ለዚህም እንደማሳያ ከታችኛው የቀበሌ ባለስልጣን ጀምሮ እስከላይኛው የአገር መሪ የሴቶች እኩልነት እና የመደራጀት መብት በህግ የተጠበቀ እንደሆነ ሳይታክቱ የሚገልፁት ነገር ነው፡፡ይሁን እንጂ የሴቶች እኩልነት እና የመደራጀት መብት ለኢህአዴግ አባልነት እና ቤት ለቤት ቡና እያጣጡ የተነገራቸው መልሰው ከማውራት ከቅያስ ወይም ከጎሮ ከድሬነት ያለፍ ተሳትፎ ከተደራጁበት ሳይሆን ከደራጃቸው አካል ያተረፉት ነገር የለም፡፡ ከላይ የተጠቀሰው አሳብ ለመረዳት እና ለመታዘብ ብዙ መራቅ አያስፈልግም በህገመንግስቱ መሰረት ተደራጅተዋል የተባሉ ማናቸውም እንዲሁም በየትኛውም ቦታ የሚገኙ የሴት ማህበራት ከመንግሰት ተፅኖ ውጪ ላለመሆናቸው ከማህበራቸው የስም አወጣጥ ጀምሮ ተግባራቸው በመመልከት በቀላሉ ማህበሩ እና ማህበርተኞችን እነማን እንደሆኑ ለመረዳት ይቻላል፡፡
ለዚህ ፁሑፍ መነሻ የሆነው አሳብ ዘንድሮ ተከብሮ ሳይሆን ተደፍሮ ለማለት በሚያስችል ሁኔታ ማርች 8 መሰረት ያደረግ ነው፡፡ እንደሚታወቀው የባለፈው እሁድ ማርች 8 አስመልክቶ የሴቶች 5 ሺህ ኪ.ሜ ሩጫ ውድድር ተካሂዶአል፡፡ በውድድሩ ላይ ቁጥራቸው የበዛ ሴቶች ተሳትፈዋል ፤ከተሳታፊዎቹ ብዛት ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ በአነስተኛ እና ጥቃቅን መንግስት ያደራጃቸው ሴቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ሴቶች አደባባይ ይዘው የወጡት አሳብ ጥቃቅን መሆኑ በእርግጥም ማህበርተኞቹ ምን ያህል አንድ ለአምስት ‹‹እደተጠረነፉ›› የሚያሳይ ነው፡፡ የጉዳዩ አሳሳቢነት የሚጀምረው እነኚህ ጢቂት ‹‹የተጠረነፉ›› ሴቶች በነፃነት ቀናቸው ነፃነት የተነፈጋቸው መሆኑ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ እሩጫው ላይ የተሳተፉት በራሳቸው ፍቃድ ሳይሆን በድረጅታቸው ትዕዛዝ ነው ሊያስብል የሚያስችል የተለያየ ‹‹ልማታዊ›› የሆነ መፈክሮችን ሲያሰሙ ተደምጠዋል፡፡በመንግሰት ልዩ ድጋፋ የተደረገላቸው እነኚህ ሴቶች ለሚደግፉት ሳይሆን ለተገደዱበት ዓላማ የመሰላቸውን መፈክር እና ቀረርቶ በማሰማት እንዲሁም የተለያዩ ፖስተሮችን በመያዝ በዕለቱ ሲንቀሳቀሱ ታይተዋል፡፡
ይሁን እንጂ ለመንግስት ደጋፊዎች የተፈቀደው ለሌሎች ለመንግሰት ተቃዎሚ ሴቶች ፖሊስ ያደረገው ክልከላ እና እስራት ክስተቱን አስገራሚ ብቻ ሳይሆን አሳሳቢያ ደርገዋል፡፡ እንደሚታወቀው ማርች 8 ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ነው፤ ይህ ቀን ሴቶች ተሰባስበው ከበሮ ይዘው የሚደልቁበት ቀን ሳይሆን ለነፃነታቸው ቀደምት ሴቶች ያደረጉትን ተጋድሎ በመዘከር ያሁኖቹ ሴቶች ለበለጠ እኩልነት እና ነፃነት በጋራ የሚቆሙበት የቃል ኪዳን ቀን ነው፡፡ ይህም እንደሆነ የተረዱ ሴቶች በነፃነት ቀናቸው ስለነፃነታቸው ከፍ ባለ ድምፅ ሲዘምሩ ማየት ምንኛ መታደል ነው ! ይህን በድፍረት ላደረጉት የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶች አድናቆት ሊቸራቸው እና ድጋፍ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ሴቶች በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ በአደባባይ ታፍሰው ለእስር የበቁት በእኔ ዘመን ይህ የመጀመሪያ ነው ፡፡የኔ ዘመን ደግሞ 23 ዓመት ሙሉ የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ የበላው ጅብ አልጮው ብሎ ተቸግረን የከረምንበት ወቅት ነው፡፡ እርግጥ ነው ይህ የሆነበት ምክንያት ለማወቅ እና ለመዘርዘር ሰፊ ጥናት ያስፈልጋል፡፡ የችግሩ አሳሳቢነት እንደተጠበቀ ሆኖ እንቢ ለነፃነቴ በማላት አደባባይ በመውጣት የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ሴቶች ‹‹ እኔ የጣይቱ ልጅ ነኝ ! እስክንድር ይፈታ ! እርዮት ትፈታ ! አብበከር ይፈታ ! አንዱአለም ይፈታ ! መብራት እና ውሃ ናፈቀን ! ፍትህ እንፈልጋለን ! ›› እና የመሳሰሉትን መፈክር በልበ ሙሉነት በማሰማት ያሳዩት ቆራጥነት ታሪክ መቼም የሚዘነጋው አይደለም፡፡ በይበልጥ ደግም በዚሁ የፖለቲካ አመለካከታቸው ምክንያት ብቻ ለእስር መዳረጋቸው የመንግስት ስርዓት ምን ያህል አምባገነን እና ጨቋኝ እንደሆን በግልፅ የሚያሳይ ነው፡፡

አቡነ ጳውሎስን ሲያሳስቱና ሲያጋጩ የነበሩ ጎሰኛ እና አማሳኝ ግለሰቦች አኹን ምናልባት ከዚያ ቦታ ሳይነሡ እርስዎንም ወደዚያ የጥፋት ሣጥን አስገብትዎት መውጫ አሳጥዎት ከኾነ እባክዎ ወደ ልቡናዎ ተመልሰው ቃል የገቡባቸውን የለውጥ ተስፋዎች ለመተግበር ይነቃቁ፡፡ የመንግሥት ፖሊቲካዊ ጫና ሳያስፈራዎ፣ መንፈሳዊ የለውጥ አባትነትዎን በተግባር ያሳዩን፡፡ የለውጥ ሥራዎ አብቦና ፍሬ አፍርቶ ለማየትና ለመጠቀም ጉጉት አለን፡፡ (ሪፖርተር፤ ይድረስ ለሪፖርተር፤ ቅጽ 19 …

ምርመራው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ተባርኮ ታቦቱ ከመግባቱ በፊት ይከናወናል የጠ/ቤ/ክህነቱ የቁጥጥር አገልግሎት ከምእመናኑ ጥረት ጎን በመቆም ከፍተኛ ድጋፍ አድርጓል በሀ/ስብከታቸው አስተዳደር ጣልቃ መገባቱን ሊቀ ጳጳሱ ለቋሚ ሲኖዶስ አባላት አስታውቀዋል መዝባሪዎቹ ‹‹አንመረመርም›› በሚል በሊቀ ጳጳሱና በደብሩ አስተዳዳሪ ላይ እየዛቱ ናቸው የጠ/ቤ/ክቱ ምሕንድስና ዘርፍ ሓላፊ ኢ/ር ሰሎሞን ካሳዬ ብቃት እንዲመረመር ተጠይቋል ለቤተ ክርስቲያናችን የታቀደውን የአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ …

ምንሊክ ሳልሳዊ ፦ህዝብ በኢኮኖሚ ሲጐሳቆል፣ በፖለቲካ በደል ሲሰማውና በማህበራዊ ህይወቱ ያልተረጋጋ ከሆነ ደግ አደለም፡፡ በጥንቱ ማርክሳዊ አካሄድ ፖለቲካ ማለት የተጠራቀመው የኢኮኖሚ ይዘት ነፀብራቅ/መገለጫ እንደማለት ነው፡፡ በግድ አራምደዋለሁ ካሉ አንገት መቀጨት፣ መሰበር፣ መውደቅ፣ አልጋ ላይ መቅረት ይከተላል ማለት ነው፡፡ ለማደግ አቅጣጫ ያስፈልጋል፡፡ ከመዓቱ ለማምለጥ መፍጠንም ያስፈልጋል፡፡ አቅጣጫ ማወቅ ብቻ ሳይሆን መሮጥና መፍጠን ያስፈልጋል ስንል ግን፣ ከምን አቅም? በምን ነፃነት? በምን ፍትሐዊ እርምጃ? በምን ዓይነት ቢሮክራሲያዊ ተቋም? በምን ዓይነት እርስበርስ መተማመን? በምን ዓይነት የገዢ ተገዢ ግንኙነት? ብሎ መጠየቅ ያባት ነው፡፡

የአስተዳደር ነገር መቼም ዋና ጉዳይ ነው፡፡ ኢኮኖሚያችን በኑሮ ውድነቱ መነጽር ሲታይ ዛሬ አሳሳቢ ነው፡፡ የሁሉም ነገር ዘዴው ተገኝቷል እንዴት እንደምንኖር መላው ከመጥፋቱ በስተቀር ፡፡ለፍቶ ለፍቶ፣ ዳክሮ ዳክሮ ኑሮ ጠብ አልል ያለው ሰው ከምሬት ሊወጣ አይችልም፡፡“እምዬ ኢትዮጵያ ሥራሽ ብዙ ፍራንክሽ ትንሽ” አለ አሉ አንድ ሠራተኛ! በእርግጥ በሊቀ – ሊቃውንት አስተሳሰብና ስሌት “ከአምስት አመት በኋላ ሠንጠረዡ ከፍ ይላል”፤ “በ2017 ዓ.ም አያሌ ፕሮጄክቶች ስለሚጠናቀቁ የተለየ ዓለም ይታያል” ወዘተ ይባላል፡፡ ምንሊክ ሳልሳዊ ችግሩ ህዝባችን “ሰብል በጥር ይታፈሳል” ቢሉት “ሆዴን እስከዚያ ለማን ላበድረው” አለ፤ የሚባለው ዓይነት ችግር ውስጥ ይገባል፡፡ አጣብቂኙ ከባድ ነው፡፡ ያለፈው ዘመን መሪ “የወረቀቱ ገብቶኛል፡፡ የገበያውን፣ የመሬት ያለውን ጉዳይ አስረዱኝ” አሉ አሉ፡፡ በግራፍ (ሠንጠረዡ ላይ) ሰብሉ ሰማይ ነክቶ፣ ከገበያው ግን ጠፍቶ ሲያዩት ቢጨንቃቸው ነው፡፡

የአመራራችንን ጉዳይ ችላ ብለን፣ የቢሮክራሲውን አካሄድ ወደጐን ትተን፣ ወደየትም የተሻለ ህይወት መዝለቅ አንችልም፡፡ በአካላችን እያወደስን በሆዳችን እየሰደብን የቱንም ወንዝ አንሻገርም፡፡ የምርጫችንን የዲሞክራሲያችንን ነገርም አደራ መባባል ያለብን ጊዜ ነው፡፡ መጽሐፍ ከመፃፍ፣ አዋጅ ከማወጅ፣ መመሪያ ከማውጣትና ጋዜጣዊ ጉባዔ ከማካሄድ አልፈን በቀናነት ለህዝባችን የሚበጀው ማንኛው መንገድ ነው? ማለት በጐ ነገር ነው፡፡

በኢኮኖሚያዊ ገቢያችን፣ በፖለቲካዊ መልካም አስተዳደራችን፣ በማህበራዊና ባህላዊ ማንነታችን የሚደርስብንን ጉስቁልና አሸንፈንና ድህነታችንን ታግለን በሁሉም አቅጣጫ ለውጥ እናመጣ ዘንድ፤ የህዝብ መነሳሳትን የሚያህል ካፒታል የለም፤ መነሳሳት ተገቢ ነው! አለበለዚያ ትላንት የነበርንበት ቦታ እንደተመቸን ቆጥረን መቀበል “ያደሩበት ጭቃ ከጭድ ይሞቃል” የሚለውን ተረት ከማረጋገጥ በቀር ፋይዳው በድን ነው፡፡

በትዕዛዝ እንግዳ ከመቀበል ይሰውረን፡፡ ባህላዊ እንግዳ – ተቀባይነታችንን ይባርክልን፡፡ ከጐረቤት ጋር ከመጣላት ይሰውረን፡፡ ተጣልተን ከታረቅንም ዕውነቱን የሚነግረን አያሳጣን፡፡ ስንጣላ መፈክር ከማስነገርና ከመራገም፤ ስንታረቅ ከማጨብጨብ ይሰውረን፡፡ የመንግስታችንን ልብና ልቦና እናውቅ ዘንድ የመረጃ ደሀ አያድርገን! የምንሰማውን በሌላ እንዳንተረጉም ንቃተ – ህሊናውን ያድለን ዘንድ፤ የሰላምና የማስተዋል ያድርግልን፡፡ ብሶት ሁሉ የፈጠራ፣ ጩኸት ሁሉ የሁከት፣ ሥጋት ሁሉ የትርምስ፤ እንዳያስመስልብን አስተዋይ ተመልካች ይሰጠን፡፡ ማየት – የተሳነው ተመሪ እንዳይሸበር ነገሩን ግልጥልጥ የሚያደርግ መሪ ይባርክልን፡፡ምንሊክ ሳልሳዊ

በጅጅጋ 300 እስረኞች መንገድ ላይ ተጣሉ

በጅጅጋ እስር ቤት ውስጥ ታስረው ከነበሩ ቁጥራቸው በውል ከማይታወቅ እስረኞች መካከል 300 ያክሉ ከአራት ቀናት በፊት በጅጅጋ መንገድ ላይ መጣላቸው ታውቀ።

የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት ያላከውን መረጃ በመንተራስ ኢሳት ባደረገው ማጣራት፣ ባለፈው ሃሙስ ለአርብ አጥቢያ አካላቸው በምግብ እጦት የከሳ፣ አይናቸው የታወረ፣ እግሮቻቸው ሽባ የሆኑ፣ የአእምሮ መታወክ የደረሰባቸውና አሰቃቂ የእስር ቤት ህይወት እንዳሳለፉ የሚናገሩ እስረኞች በጅጅጋ ጎዳናዎች ላይ ተጥለዋል።
ከተጣሉት መካከል ወላጅ አልባ የሆኑ ምናልባትም በእስር ቤት ውስጥ የተወለዱ ህጻናት፣ ወጣቶችና አዋቂዎች ይገኙበታል።

አብዛኞቹ እስረኞች ከሰውነት ተራ የወጡና በበሽታ የተጠቁ እንዲሁም ለረጅም ጊዜ በእስር ቤት ውስጥ የቆዩ ናቸው። ኢሳት ለማረጋገጥ ባይችልም፣ የኦብነግ መረጃ እንደሚያሳየው ከተፈቱት እስረኞች መካከል 20ዎቹ በሶስት ቀናት ውስጥ በበሽታ ሞተዋል።
ከአንድ ወር በፊት ኢሳት ከጅጅጋ ከተማ 25 ኪሜትር ርቆ በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ በኮሌራ በሽታ ከ40 በላይ ሰዎች ሞተው በእስር ቤቱ አካባቢ አግባብ ባልሆነ መንገድ በመቀበራቸው አስከሬናቸውን ጅቦች እያወጡ በመብላታቸውና እና አካባቢው በበሽታ በመበከሉ በድጋሜ እንዲቀበሩ መደረጉን ዘግቧል።

የክልሉ መንግስት አሁን የወሰደው እርምጃ በእስር ቤቶች ውስጥ የተነሳውን የኮሌራ በሽታ ለመከላከል እንደሆነ እየተነገረ ነው።
በሶማሊ ክልል የተካሄደውን የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን አስመልክቶ የክልሉን ገጽታ ያበላሻሉ የተባሉ ከ700 በላይ የጎዳና ላይ ተዳዳሪዎችና መታወቂያ የሌላቸው ሰዎች እንዲታሰሩ መደረጉ ይታወቃል።በጉዳዩ ዙሪያ የክልሉን የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። ማጋቢት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና

Image
እንደልቡ/ዳግም (ከቫንኮቨር፣ ካናዳ)

አባ መላ ማን ነው?

በቅጽል ስሙ “አባ መላ” በእውነተኛ ስሙ ደግሞ ብርሃኑ ዳምጤ ተብሎ ይጠራል፣ በ60ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ አዛውንት ነው (ምንም እንኳ ስራው እንደ እድሜው ባይሆንም)። ፓልቶክ የሚባለውን የማህበራዊ መገናኛ መድረክ በመጠቀም በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዲስኩር በማሰማት ይታወቃል። በወጣትነቱ ኢህአፓ ውስጥ ነበር የሚባለው ብርሃኑ ዳምጤ ወዲያውም የኢህአፓን መዳከም አይቶ ወደ ደርግ ቡድን መቀላቀሉን የሚያውቁት ይናገራሉ። በወቅቱ አብረውት በኢህአፓ ውስጥ ይሳተፉ የነበሩ ወጣቶችን ለደርግ በእጅ መንሻ መልክ አሳልፎ ሳይሰጥ እንዳልቀረ በደርግ ካድሬነት ቆይታው የሚያውቁት ይጠረጥራሉ አንዳንዶች ደግሞ አፋቸውን ሞልተው ይናገሩታል።

ብርሃኑ ዳምጤ ከደርግ መውደቅ በኋላ በስደቱ ዓለም (ዳያስፖራ) ፖለቲካ መድረክ ብቅ ያለው በምርጫ 97 ወቅት የዝነኛውን ቅንጅት ማልያ ለብሶ ነበር። ይሁንና በስልጣን ላይ ያለው የህወሃት/ወያኔ መንግስት ምርጫውን አጭበርብሮ፣ የምርጫውን መጭበርበር የተቃወሙትን በገፍ በአደባባይ በጥይት ደብድቦ፣ ህዝቡ የመረጣቸውን የቅንጅት አመራሮች፣ ጋዜጠኞችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን ጨመሮ ከ50 ሺህ በላይ ባብዛኛው ወጣቶችን አስሮና በየጦር ካምፖቹ አጉሮ በአምባገነንነቱ ለመቀጠል ሲወስን ብርሃኑ ዳምጤም ባፋጣኝ የቅንጅትን ማልያ አውልቆ የህወሃት/ኢህአዴግን ማልያ ለብሶ ቁጭ አለ።

ሰሞኑን ደግሞ ብርሃኑ ዳምጤ አስደናቂ መገለባበጥን ፈጽሞ የህዝብን አይን አስበልጥጧል። እነዚህ ብርሃኑ ዳምጤ (አባ መላ) ሰሞኑን የሚፈጽማቸው መገለባበጦች በ1960ዎቹ እና 70ዎቹ ከነበሩት የመገለባበጥ ትሪኢቶቹ ለየት የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር አሁን መገለባበጡን የሚፈጽመው በቀጥታ ስርጭት ወቅት (በፓልቶክ) መሆኑና ጉዳዮን በመሪ ዜና መልክ የሚዘግብለት የቴሌቪዥን ጣብያ “ኢሳትን” ማግኘቱ ነው።

ብርሃኑ ዳምጤ ከጥቂት ወራቶች በፊት ነበር የተሰለፈበት የህወሃት/ኢህአዴግ ጎራ በተለይም ከወያኔው ቁንጮ መለስ ዜናዊ ሞት በኋላ እየተዳከመ መምጣትን አይቶና ገምቶ ወያኔዎችን “አፍንጫችሁን ላሱ፣ እኔ ከአሁን ብኋላ የድሮው አባ መላ አይደለሁም፣ እንዲያውም ጉዳችሁን አዝረጠርጣለሁ…” በማለት ፉከራ ቢጤ አሰምቶ የዲሞክራሲና የነጻነት ታጋዮችን ጎራ መቀላቀሉን ያበሰረው።

መንፈቅ እንኳ ሳይሞላ አባ መላ በመጣበት አይነት መንገድ ተመልሶ ህወሃት/ኢህአዴግን ለማገልገል መወሰኑን ይፋ አደርጓል። ለሱ እምብዛም አዲስ ያልሆነውን የክህደት ቁልቁለትም ዳግም ተያይዞታል።

አባ መላ፣ ኢሳትና ዳያስፖራው

የኢሳት ጋዜጠኞች፣ አንዳንድ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና የተቃዋሚ ፖለቲከኞችም ጭምር ይህ አባ መላ የሚባለውን ቦታ እየቀያየረ ይሚጫወት ዝቅተኛ ካድሬ ከሚገባው በላይ ቦታ ሰጥተውት እንደነበር እገምታለሁ፣ በውጤቱም ተከታዮቻቸውን ያሳሳቱና ያዘናጉ ይመስለኛል። ይህንን ጉዳይ ማንሳቴ “ብዬ ነበር” ለማለት ሳይሆን ይልቁኑም ይህ ክስተት እንደ መማሪያ ሆኖ እንዲያልፍ በመፈልጌ መሆኑን አባብያን እንዲረዱልኝ እፈልጋለሁ።

እንደ አባ መላ አይነቱ ቀደም ሲል በተደጋጋሚ የመገለባበጥ ብቃቱን ያሳየ ወለፈንዴ ተቃዋሚ ጎራ ገብቻለሁ ሲል አያያዛችን ጥንቃቄ የተሞላበት፣ ሊሆን ይገባል። በቅርቡ ተገልብጦ ሊያሳፍረን ይችላል ብሎ መስጋት፣ ለጉዳዩ መጠነኛ የአየር ሰዓት መስጠትና ውሎ አድሮ ደግሞ መርጋቱን እያዩ ወደሌላው መተላለፍ ተገቢ ነው። እንደው በአንድ ጊዜ ይህን ከምላስ በስተቀር ቁም ነገር የሌለው ተራ ካድሬ ወደላይ ቆልሎ አንድ ጊዜ “አክቲቪስት” ሌላ ጊዜ ደግሞ “የፖለቲካ ተንታኝ” እያሉ በኢትዮጵያውያን ስም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቋቋመ ግብረ ሰናይ ድርጅትን እንዲመራ ማጨት ድረስ መጓዙና አሉ ከሚባሉ ፖለቲከኞች ጋር መድረክ እንዲጋራ ሁኔታዎችን ማመቻቸቱ አገባብ አልነበረም።

የኢሳት ባልደረባ ደረጀ ሃብተወልድ የአባ መላን መገልበጥ አስመልክቶ በፌስቡክ ገጹ ላይ እንዳሰፈረው ከሆነ ግን ኢሳቶች ከስህተቶቻቸው ሊማሩ የተሰናዱ አይመስልም ይልቁኑም አባ መላን አስመልክቶ ሊቀርቡ የሚችሉ ትችቶችን ቀድሞ ለመከላከል ነው ሙከራ የሚያደርጉ ያሉት። ደረጀ ሃብተወልድ እንዲህ ነበር ያለው፣

“ነገሩ ወዲህ ነው። አባ መላ ኢህአዴጎችን እየሰደበ ወደ ተቃዋሚው ጎራ ሲቀላቀል “አገኛለሁ” ብሎ ያሰላው ጥቅም ነበር። ሆኖም ሀሳብን በነፃነት ለመግለጽ ከሚያስችል ነፃ መድረክ ውጪ ሌላ ነገር ሊያገኝ አልቻለም። ባገኘው ነፃ መድረክም ማንም ሳይቆነጥጠው ከትንሽ እስከ ትልቅ የቀድሞ አለቆቹን እስከ ዶቃ ማሰሪያቸው ነግሯቸዋል። እኛንም አስቆናል። ስንስቅለት ጨምሮ ጨማምሮ አቅምሷቸዋል። እኛም፦“የአገሩን ሰርዶ ባገሩ በሬ” እያልን ተዝናንተናል። ከዚያ ባለፈ ግን ለቁም ነገር ያሰበው ሰው ስለመኖሩ እጠራጠራለሁ።”

የደረጀን አባባል ሁሉም ሰው የተቀበለው አይመስልም ይህን ለማሳየት ከተቃውሞ ሃሳቦች መካከል አንዱን ከዚያው ከደረጀ ሃብተወልድ የፌስቡክ ገጽ ልበደር፣

“የአባ መላን መገልበጥ ተከትሎ ኢሳቶች ከተወቃሽነት ለመዳን የዘየዳችሁት ይሄው ነው? ደረጀ “አባ መላን ለቁም ነገር ያሰበው ያለ አይመስለኝም” ያልከው ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ነው፣ በሳውዲ ወገኖቻችንን ለመታደግ በተቋቋመው አለም አቀፍ ድርጅት ውስጥ ከታማኝ እና አበበ ገላው ቀጥሎ ሶስተኛ ሰው ተደርጎ አልነበረም? በጣም ብዙ ማለት ይቻላል… “እጄን በጄ” ሆኖብን እንጂ። ለማንኛውም ከስህተቶቻችሁ ተማሩ፣ በጣምም አንፍጠጥ ያስተዛዝባል።” ethiopian unity

ለማጠቃለል ያህል የሚሰራ ጋዜጠኛ፣ ለውጥ ለማምጣት የሚተጋ ፖለቲከኛና የዲሞክራሲ ታጋይ በሂደት ውስጥ ስህተት ሊሰራ ይችላል፣ ከስህተቶች ትምህርት ወስዶ ለሁለተኛ ጊዜ ተመሳሳይ ስህተትን ላለመድገም ጥረት ማድረግ ግን ሊለመድ ይገባል። ነገሮቻችን ሁሉ “ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ” እንዳይሆኑ ሃላፊነት ወስደን ከስህተቶቻችን ለመማር ዝግጁ እንሁን።

Image

(ሁኔ አቢሲኒያዊ ከፒተርቦሮው ዩ.ኬ) :-አቶ ስብሃትን ጠጋ ብለው የሚያውቁት ሰዎች “አቦይ ብላችሁ አትጥሩት። አባታዊ አንደበትና ምግባር የለውም እርሱን አቦይ ማለት ትግራይ የሽማግሌ መሀን እንደሆነች መቁጠር ነው” ይሉታል፡፡

ሰውዬው ስብሐት ነጋ የህወሓትን አመሰራረት ቅድመ ታሪክ ለሚያውቅ ሰው ምን ያህል ተንኮለኛ እና በዘር ልክፍት የተለከፈ እንደሆነ ግልጽ ይሆንለታል፡፡ በ1963 ዓ.ም እንደተመሰረተ የሚነገርለት ማገብት (ማህበር ገስገስቲ ብሔረ ትግራይ) የተመሰረተው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የትግራይ ተወላጅ ተማሪዎች ነበር፡፡ የማህበሩ ተልእኮም የተለያዩ የበጐ አድራጐት ስራዎችን በክረምት ወደ ትግራይ በመሄድ ማከናወን የሚል ነበር፡፡ በሂደት ሙሉ በሙሉ ወደ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ በመቀየር ለተሐህት/ህወሓት መመስረት መሰረት ሆነ ለዚህ ዓላማ የማስቀየር ስራ ትልቁን አስተዋፅኦ ካደረጉት መካከል ደግሞ ዛሬ ታሞ የሚማቅቀው ስብሐት ነጋ አንዱ ነው፡፡

ስብሐት ነጋ የህወሀትን መስመር እና ዓላማ መሀንዲስ ከመሆንም አልፎ እስከዛሬ ለብዙ ሰዎች ምስጢር በሆነ መልኩ መለስ ዜናዊንም ወደ ህወሀት ሊቀመንበርነት ብሎም የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስተር ያደረገ እና በህወሀት ክፍፍል ወቅትም ትልቅ ሚና ከነበራቸው ቀደምት የህወሀት ታጋዮች አንዱ ነው፡፡

ለባለፉት 23 ዓመታት የኢትዮጵያን ህዝብ ከጀርባ ሆነው ሲያንቀጠቅጥ የነበረው አይተ ስብሐት ነጋ እርሱም ተራው ደርሶ ቤልጅየም ብራሰልስ በሚገኘው ሴንት ሚካኤል ሆስፒታል Hôpital Saint Michel – (Brussels) መመላስ ከጀመረ 11 ዓመታት እንደሞላው የውስጥ አዋቂዎች ቢገልፁም የበሽታው አይነትና የሰውዬው የጤንነት ሁኔታ እስካሁን ድረስ ከቅርብ ሰዎች ውጪ ሳይወጣ ቀርቷል ሆኖም የህወሀት የውስጥ ሹኩቻን ተከትሎ ሚስጥሮ እያፈተለኩ መውጣታቸውን ቀጥለው ዛሬ ስለ ስብሀት ነጋ ጤንነት በተመለከተ ለዚህ ጽሁፍ ፀሀፊ አፈትላኪ መልዕክት ደርሷል፡፡

ከታማኝ ምንጮች የተገኙት መረጃዎች እንደሚያሳዩት ሰውዬው ማለትም ስብሐት ነጋ brainstem glioma በተባለ የካንሰር አይነት መጠቃቱን ገልፀዋል፡፡ ይህ የካንሰር አይነት በብዛት በህፃናት ላይ የሚታይ ሲሆን በአዋቂዎች ዘንድ ግን በዚህ የካንሰር ዓይነት የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከ100,000 አንድ እንደሆነ የሳይንስ ማስረጃዎች ያሳያሉ፡፡

Brainstem glioma ስለተባለው የካንሰር አይነት መንስዔ እስካሁን የህክምና ባለሙያዎች ምንም ያሉት ነገር ባይኖርም በካንሰሩ የተጠቃ ሰው ግን ከፍተኛ የሆነ የራስ ህመም፣ ራስን የመቆጣጠር እና የማስመለስ ችግር እንደሚያጋጥመው ያስረዳሉ፡፡

በዚህ ካንሰር ተጠቅተው ወደ ህክምና ከሄዱ ሰዎች መካከል 37% የመኖሪያ እድሜያቸው ቢበዛ ዓንድ ዓመት 20% ያህሉ ሁለት ዓመት 13% ቢበዛ ቢበዛ ከሶስት አመት በላይ በህይወት የመኖር እድላቸው አነስተኛ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ከህወሀት አፈትልኮ የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ስብሐት ነጋ ባለፉት 11 ዓመታት ቤልጂየም ሲመላለስ የነበረው በዚሁ የካንሰር ምክንያት እንዳልነበረ እና የዚህ አይነት የካንሰር ተጠቂ እንደሆነ የተነገረው ፌብራዋሪ 9 እለተ እሁድ ቀን እንደነበር ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የአቶ ስብሐት ነጋን መታመም ተከትሎ በሰውዬው ላይ በየዕለቱ የተለያየ ባህሪ እንደሚመለከቱ ገልፀው በተደጋጋሚ ከተለያዩ ስብሰባዎች ላይ አቋርጠው እየሄዱ እንደሚገኙ አክለው ገልፀዋል፡፡

በጦርነቱ ዘመን የትግራይ ህዝብ እጅግ የከፋ ድርቅና ረሀብ ሲፈራረቅበት፤ ከመሀል አገር የእርዳታ እህል እንዳይደርሰው መንገድ በመዝጋት፤ እነሱ በተቆጣጠሩት አካባቢና ባልተቆጣጠሩትም አካባቢ “እኛ ነን ለህዝባችን ረድኤት ድርጅቶች የሚያቀርቡትን እርዳታ ማደል ያለብን” ብለው የተባበሩት መንግስታትን ግራ አጋብተው ለረሀብተኛው እንዲያከፋፍሉ መድሀኒትና ምግብ ይሰጣቸው የነበሩ ሲሆን ያንን በብዙ ሚሊዮን የሚገመት የእርዳታ እህልና ቁሳቁስ ከአረብ ነጋዴዎች ጋር በመመሳጠር በቀጥታ ባህር እያሻገሩ በመሸጥ፤ በኩንታሎች አሸዋ እየሞሉ ለጋሾችን በማታለል እንዲገዙአቸው በማድረግ፤ በሚሊዮን ዶላር ሲንበሸበሹ፤ የጦር መሳሪያ ሲሸምቱ፤ የትግራይ ህዝብ እንደቅጠል ይረግፍ ነበር። እነሱ በየጫካው ከሰራዊቱ እየተሸሸጉ አረቄ ጠግበው ከውሽሞቻቸው ጋር ከበሮ እየደለቁ እየጨፈሩ ይዳሩ እንደነበር ህወሀትን ጥለው የኮበለሉ የቀድሞ አባላቶች የሚገልፁ ሲሆን ለእነዚህ ሁሉ ግፍ እና በደል መፈፀም ከፍተኛ ሚና የነበራቸው እኚሁ የካንሰር ተጠቂ ነበሩ፡፡

ሞት ፍትሃዊ ነው በቅርቡ እንኳን አፈ ቀላጤ መለስ ዜናዊን ከህወሀት አለማየው አቶምሳን ከኦህዴድ ( ኦህዴድ ብዬ ስጠራው የዋሸው ይመስለኛል) የወሰደ ሲሆን አሁን አፉን ከፍቶ ከስብሐት ነጋ ደጃፍ ደርሷል ስብሀት ነጋም ሞትን ወደ ቤቱ ላለማስገባት ከአዲስ አበባ ወደ ብራሰልስ በየዕለቱ እየተመላለሰ ይገኛል ግና ሞትን ሸሽቶ እስከመቼ ሊደበቅ እስከ አንድ ወር ወይስ?

መላዋ ኢትዮጵያ እንደ አንድ የኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሀገረ ስብከት ትቆጠር የነበረችበት የ1600 ዓመታት የሞግዚትነት ታሪክ ከብዙ ተጋድሎና እልክ አስጨራሽ ጥረት በኋላ አክትሞ የመንበረ ፕትርክናውን ነጻነት መቀዳጀቷ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን የተበሠረበት ዘመን ነው – በዓለ ሢመተ ፓትርያርክ፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በመንበረ ተክለ ሃይማኖት የመጨረሻውን የክህነት ማዕርግ መብቷን (የኤጲስ ቆጶስነት፣ የሊቀ ኤጲስ ቆጶስነትና የፓትርያርክነት ጸጋን) ለማረጋገጥ …

አፈንዲ ሙተቂ
———-
ኤርትራ ዛሬ ራሷን የቻለች ሀገር ናት፡፡ ትናንት ግን የኛው አካል ነበረች፡፡ አጼ ኃይለ ሥላሤ ብልጥ የሆኑ መስሎአቸው ለሁላችንም አስፈላጊ የነበረውን የፌዴሬሽን ፎርሙላ ሰረዙትና ህዝቡን አስቀየሙት፡፡ ደርግ ደግሞ የራሳችንን ህዝብ እንደ ባዕድ እየቆጠረ በመትረየስ አጨደው፡፡ በታንክ ደመሰሰው፡፡ በዚህም የተነሳ ወጣቱ “አደይ ኤሪቲሪያ”ን እየዘመረ ወደ ባርካና ሳህል ነጎደ፡፡ ራሱን አደራጅቶ ጀብሃና ሻዕቢያ ሆኖ መጣ፡፡ ውጤቱም 1983 ላይ ታየ፡፡

የደርግና የኃይለ ሥላሤ መንግስታት ያደረጓቸው ነገሮች ሲገርሙን በጣም ግራ የሚያጋባው ሶስተኛው መንግሥታችን መጣ፡፡ ይህ የኛ መንግሥት “የተበላሸውን ሁሉ አስተካክለን አብረን መኖር እንችላለን” ብሎ መከራከር ሲገባው ጭራሹኑ “ኤርትራ ካልተገነጠለች ኢትዮጵያ ሰላም አታገኝም” ባይ ሆኖ ተገኘ፡፡ ክፍለ ሀገሩ ወደዚያ ከሄደ በኋላም መንግሥቱ ከሚከተለው ግልጽነት የጎደለው አሰራር የተነሳ በ1990 ዓ.ል. ሺዎችን ያረገፈ ግዙፍ ጦርነት ተቀሰቀሰ፡፡ ከአንድ ምንጭ የተቀዱ ህዝቦች ተጋደሉ፡፡ እነሆ ዛሬም ድረስ ነገሩ ሳይለይለት በጨለማ ውስጥ ነው ያለነው፡፡

እኛ ግን ተስፋ አንቆርጥም! በአያያዝ ጉድለት የተለየንን ወገናችንን መመለስ እንፈልጋለን፡፡ ህዝቡ ለጊዜው ሪፈረንደም አድርጎ ነጻነቱን ማወጁን ብንደግፍለትም አንድ ቀን ተቀራርበን በጋራ ስለመስራት እንወያይ ይሆናል ብለን እናልማለን፡፡ የኛ ልጆች ደግሞ በኮንፌዴሬሽን ስለመስራት ያስቡ ይሆናል፡፡ የልጅ ልጆቻችን በፈቃደኝነት ስለመዋሃድ ያስቡ ይሆናል፡፡ በዚያን ጊዜም አሁን የምንመኘው በአንድነት ውብ የመሆን ሚስጢራችን ይመለስልናል ብለን እናልማለን፡፡ ምን ይታወቃል?

ወገኖቼ ደጉን ነው የተመኘሁት፡፡ በቅን ልቦና በርትተን ከጸለይንና ከኛ የሚጠበቀውን ካደረግን ሁሉንም የሚችለው ፈጣሪ ህልማችንን እውነት ያደርግልናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡
——-
ምን እንደጣለብኝ እንጃ! ያንን ምድር እጅግ ሲበዛ እወደዋለሁ፡፡ እኔ ለተወለድኩበትና አብዛኛውን ዘመኔን ለጨረስኩበት የምስራቅ ኢትዮጵያ ክልል ጎረቤት ከሆነችው ሶማሊያ ይልቅ በ1600 ኪ.ሜ. የምትርቀው አስመራ ናት የምትናፍቀኝ፡፡ ስለሶማሊያ የተጻፈ መጽሐፍ ማንበብ ብዙም አይማርከኝም፡፡ ስለ ኤርትራ የተጻፈ መጽሐፍ ካጋጠመኝ ግን ሳላየው አላልፍም (ይህ ግን ሶማሊያን ከመጥላት እንደማይቆጠርብኝ ተስፋ አደርጋለሁ)፡፡

ታዲያ በርካቶቻችሁም እንደኔው ትመስሉኛላችሁ፡፡ ለምሳሌ ከ1970ዎቹ ጀምሮ ሲታተም የቆየው የቤኒ አምሩን ወጣት የሚያሳየው ፖስተር ዛሬም ድረስ ከኛ ጋር ተሳስሮ ነው ያለው፡፡ አሁንም ድረስ በበርካታ ስፍራዎች ተለጥፎ አይቼዋለሁ፡፡ በፌስቡክም እርሱን እንደ ፕሮፋይል ፒክቸር የሚጠቀም ኢትዮጵያዊ ሞልቷል፡፡ በሌላ በኩል የኤርትራን ሙዚቃ የሚያዳምጡ ሰዎች በሽ ናቸው፡፡ ደራሲ መሐመድ ሳልማን መቐለ ሄዶ ያየው ነገር ቢያስገርመው “በኤርትራ ሙዚቃ የምትጨፍር ከተማ” የሚል አስደናቂ ወግ ጽፎ እውነቱን አስረድቶናል፡፡ መንግሥታት ቢጣሉ እንኳ ህዝቦች ምንጊዜም እንደሚነፋፈቁ ከዚህ በላይ የሚያስረዳ ዋቢ ያለ አይመስለኝም፡፡
——–
ማርታ ሀይሉን አስታወሳችኋት? አዎን! ማርታን “ብራ… ነው… ብራ ነው”፤ “አዘዞ”፤ “ሎጋ ..ና እናውጋ” በተሰኙት ዘፈኖቿ እናውቃታለን፡፡ ከማርታ ዘፈኖች ዘወትር ቀልቤን ይገዛ የነበረው ግን የትግርኛ ዜማዋ ነው፡፡ አዝማቹ እንዲህ ይመስለኛል፡፡

ካብ አስመራ ድንገት ርእዮ
ምጽዋ ገባሁ ልበይ ሕብዮ

እንተርጉመው እንዴ?… ግድ የለም ማርታ ራሷ እንዲህ እያለች በአማርኛ ተርጉማዋለች፡፡

“ከአስመራ ድንገት አይቼው
ምጽዋ ገባሁ ልቤን ሰጥቼው”፡፡

አዎን! ትናንት የኛ ናት ስንላት ለነበረችው ኤርትራ ነው እንዲህ የዘመርንላት፡፡ ዛሬም ብንዘምርላት እንከበራለን እንጂ አንወቀስም፡፡ ምክንያቱም በመንግሥት ደረጃ ነው የተለያየነው፡፡ ሁለት ፓስፖርት እንዲኖረን ነው የተደረግነው፡፡ ሁለታችንም ግን አንድ ህዝቦች ነን፡፡ በደምም ሆነ በባህል በጣም የተዋሃድን የአንድ መሬት ብቃዮች ነን፡፡ ሁለታችንም የተዋብን የሴምና የኩሽ ህዝቦች ውቅር ነን፡፡ እንደኛ የሚያምር ህዝብ በትኛውም ዓለም የለም፡፡ የጀበና ቡና፣ ዶሮ ወጥ፣ ድፎ ዳቦ፣ የስጋ ፍትፍት፣ አምባሻ፣ ወዘተ…. ሁለታችን ዘንድ ብቻ ነው ያለው፡፡
—–
በርግጥ እላችኋለሁ፡፡ በምንባብና በወሬ እንጂ በአካል የማላውቃት ኤርትራ ትናፍቀኛለች! ያ በታሪክ ምዕራፎች “ምድሪ ባህረ ነጋሽ” እየተባለ ሲጠራ የኖረው ጀግና መሬትና ህዝብ ይናፍቀኛል፡፡ ያ የሰሜኑ በረኛ እያልን እንመካበት የነበረው ህዝባችን ይናፍቃል፡፡
እውነትም ኤርትራ ! የዳማት ታሪክ ውቅር! የመጠራ አብያተ መንግሥታት ከርስ! የሀውልቲ ፍርስራሾች ቀብር! የአዱሊስና የዙላ ወደቦች መዘክር! የሱዋኪምና የዳህላክ ሱልጣኖች ደብር!
ኤርትራ የአብረሃ ደቦጭ ሀገር! የሞገሥ አስገዶም ሀገር! የዘርዓይ ደረስ ሀገር! የሎሬንዞ ታዕዛዝ ሀገር! የደጃች ሀረጎት ሀገር! በአይበገሬ ጀግንነታቸው ድፍን አፍሪቃን ያኮሩ አርበኞች የበቀሉበት ምድር!
ኤርትራ የበረከት መንግሥተ አብ ሀገር! የአብረሃም አፈወርቂ ሀገር! የአሕመድ ሼኽ ሀገር! የሄለን መለስ ሀገር! የየማነ ባሪያው ሀገር! የሄለን ጳውሎስ ሀገር! በስርቅርቅ ድምጻቸው የሰውን ልብ እየሰረሰሩ የመግባት ሀይል ያላቸው የጥበብ ከዋክብት የወጡበት መንደር!
ኤርትራ የፊያሜታ ጊላይ ሀገር! የስዕላይ በራኺ ሀገር! የኦቦይ ተኽሌ ሀገር! የተክላይ ዘድንግል ሀገር! የሆቴል ፓራዲዞ ሀገር! የዕቁባይ ሲላ ሀገር! የምንወደው ደራሲያችን በዓሉ ግርማ በ“ኦሮማይ” መጽሐፉ እንደ ፊልም ግልጥልጥ አድርጎ እየተረከልን ዝንተ-ዓለም እንድንወዳት ያደረገን የቀይ ኮከብ ትዝታ ወመዘክር!
ኤርትራ የፊዮሪ ሀገር! የሳባ ሀገር! የማርቲና ሀገር! የብርኽቲ ሀገር! ፊያሜታ ጊላይን የመሳሰሉ “ሽኮሪናዎች”ን ያበቀለች ውብ የውቦች እመቤት!
—–
ኤርትራን ስንጠራ በቅድሚያ ወደ አዕምሮአችን የምትመጣው አስመራ ናት፡፡ የአስመራ ናፍቆት ይገድላል፡፡ አስመሪና፣ አስመሪቲ፣ አቲ ጽብቕቲ!…
ውይ ስታምር! “ቀሽቲ” እኮ ናት፡፡ ያኔ በልጅ አዕምሮአችን በዘምባባ ጥላዋ ተሸክፋ በፖስትካርድ ስትቀርብልን “የኛ ውቢት” እያልን እንመጻደቅባት ነበር፡፡ እንቆቅልሽ ስንጫወትና መልሱ ጠፍቶን “ሀገር ስጠኝ” ስንባል እርሷን ለመስጠት እንሰስት ነበር፡፡ ጠያቂውም የዋዘ ስላልሆነ “አስመራ” ካላልነው ለጠየቀን ጥያቄ ትክክለኛውን መልስ አይነግረንም ነበር፡፡ ከማናውቃቸው “ዋሽንግተንና” ሮማ አስመራ ነበር የምትበልጥብን፡፡ በትምህርት ቤት መዝሙራችንም እንዲህ እንል ነበር፡፡
ኦኬ ኦኬ ኦኬ ስራ
ሰላም ሰላም ወደ አስመራ
አዲስ አስተማሪ ከጃፓን የመጣ
ማስተማሩን ትቶ በቦክስ የሚማታ
አናግረኝና አናግርሃለሁ
በአሜሪካ ሽጉጥ አዳፍንሃለሁ፡፡

ግጥሙ “አንታራም” የሚሉት የህጻናት ጨዋታ ዓይነት ነው፡፡ ነገር ግን አስመራ ከልባችን እንዳትጠፋ አድርጓል፡፡ ዛሬም በልባችን ነግሳለች አስመሪና!
—-
አስመሪና! እንተይ ሽኮሪና! ሰሜናይት ጽብቕቲ! በዓሉ ግርማ ላንቺ ክብር የጻፈው ትዝ ይልሻል? እስቲ እናስታውሰው!

አስመሪና አስመራዬ
ካብ ሐንቲ ንግሥቲ ይበልፅ መልክእኪ
አማአድዬ ክርእየኪ ከሎኹ ኽአ
አብ ኢደይ ዘሎ ነገር ይወድቕ፡፡
——
ጸጸራት፤ ፎርቶ፣ ሐዝሐዝ፣ አርበእተ አስመራ፣ እምባጋሊያኖ፣ ኮምቢሽታቶ፣ አዲጓእዳድ፣ ቃኘው፣ ማይተመናይ፣ ሰምበላይ፣ ጎዳይፍ፣ ገጀረት፣ ወዘተ…በጽሑፍ የማውቃቸው የአስመራ ሰፈሮች ናቸው፡፡ አንድ ቀን በሆነልኝና ባየኋቸው እያልኩ አልማሁ፡፡ እነዚህ አስገራሚ የአስመሪና ሰፈሮች ብዙ ባለታሪኮችን አብቅለዋል፡፡ ብዙዎች ገድላቸው እየተደጋገመ ሲነገርላቸው እሰማለሁ፤ አነባለሁ፡፡ ለኛ ቅርብ የነበረ አንድ ውድ ልጅ እየተረሳ በመሆኑ ግን አዝኛለሁ፡፡

አማኑኤል እያሱ ይባላል! አስታወሳችሁት አይደል? አዎን! አማኑኤል በኛ ዕድሜ ዘመን ኢትዮጵያ ዋንጫ መብላት እንደምትችል ያስመሰከረው የታላቁ የ1980 የእግር ኳስ ቡድናችን ቋሚ ተሰላፊ ነበረ፡፡ የማሊያ ቁጥሩ 2 ይመስለኛል፡፡ አማኑኤል የያኔው ቡድናችን ባደረጋቸው ሁሉም ጨዋታዎች ተሰልፏል፡፡ ቡድኑ ዋንጫውን ሲበላም ከጓደኞቹ ጋር ቤተመንግሥት ድረስ ተጋብዞ ተሸልሟል፡፡ አማኑኤልን ያስገኘው ከዚያ ዘመን ዝነኛ ቡድኖቻችን መካከል አንዱ የነበረው የኤርትራ ጫማ ቡድን ነው፡፡ ይህ ቡድን የኤርትራ አንደኛ ዲቪዚዮን ዋንጫን በተደጋጋሚ ያሸነፈ ነው፡፡

አማኑኤል እያሱ በኢትዮጵያ ትቅደም አንደኛ ደረጃ ዋንጫም ለኤርትራ ክፍለ ሀገር ምርጥ ቡድንም ተሰልፎ ተጫውቷል፡፡ ባልሳሳት የ1981 የኢትዮጵያ ዋንጫን ያሸነፈው እነ አማኑኤል የነበሩበት የኤርትራ ክፍለ ሀገር ቡድን ነው፡፡ የአማኑኤል እያሱን ወሬ ለመጨረሻ ጊዜ ያነበብኩት በ1988 ለወዳጅነት ጨዋታ አዲስ አበባ መምጣቱን በማስመልከት በርካታ የግል ጋዜጦች ቃለ-መጠይቅ ባደረጉለት ጊዜ ነው፡፡ ከዚያ ወዲህ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ መረጃው የለኝም፡፡ እስቲ የአስመራ ልጆች ወሬው ካላችሁ ስለአማኑኤል እያሱ አንድ ነገር በሉን፡፡
—–
ወደ ምዕራብ ኤርትራ ተሻግረናል! ባርካና ጋሽ የሚባሉት የኤርትራ ቆላዎች እዚህ ነው ያሉት፡፡ አቆርዳት፣ ተሰነይ፣ አሊጊደር፣ ባሬንቱ የተሰኙት ከተሞችም በቆላው ውስጥ ተዘርግተዋል፡፡ ኩናማ፣ ናራ እና ቤጃ የተሰኙት ብሄረሰቦች እዚህ ነው የሚኖሩት፡፡ የአካባቢው ዋነኛው ህዝብ ግን ለኛ በጣም ቅርብ ሆኖ ዓመታትን ያስቆጠረውን ሳቂታውን የቤኒ አምር ወጣት ያስገኘው የትግረ ህዝብ ነው፡፡

የትግረ ህዝብ በውስጡ በርካታ ጎሳዎች አሉት፡፡ ከሁሉም የሚበረክተው ግን የቤኒአምር ጎሳ ነው፡፡ ህዝቡ የሚነጋገርበት የትግረ ቋንቋ ከሴማዊ ቤተሰብ ነው የሚመደበው፡፡ ለዚህ ቋንቋ በጣም የሚቀርበው በደጋው ኤርትራና በኛዋ የትግራይ ክልል የሚነገረው ትግርኛ ነው፡፡ እነዚህ ሁለት ቋንቋዎች ከጥንታዊው የግዕዝ ቋንቋ ነው የተወለዱት፡፡ የትግረ ቋንቋ ከኤርትራ ሌላ በሱዳንም (ከሰላ አካባቢ) በስፋት ይነገራል፡፡

ትግረና ትግርኛ በጣም ከመመሳሰላቸው የተነሳ እንግዳ ለሆነ ሰው አንድ ዓይነት ቋንቋዎች ሊመስሉት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ለትግርኛ ተናጋሪዎች የትግረ ቋንቋን መልመድ በጣም ቀላል ነው ይባላል፡፡ የትግረ ተናጋሪም ትግርኛን በቶሎ መልመድ ይቀለዋል፡፡ በመሆኑም በዛሬዋ ኤርትራ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ህዝብ ሁለቱንም ቋንቋዎች መናገር ይችላል፡፡

ምዕራባዊው ቆላ ኤርትራዊያን በጣም የሚያደንቋቸውን እንደ ሃሚድ ኢድሪስ አዋቴ፣ ሙሐመድ ኢድሪስ እና ኢድሪስ ገላውዴዎስን ያፈራ መሬት ነው፡፡ በዚህ ሰሞኑን ልቤን ያሸፈተው የትግረ ልጅ ግን “አሕመድ ሼክ” ነው፡፡ አሕመድ ሼክን አወቃችሁት አይደል? አዎን! “ባቡሬይ”፣ “ኢላ ሰርጎ” ወዘተ.. እያለ በማይጠገበው የትግረ ምት የሚያዜመው ተወዳጅ ድምጻዊ ነው፡፡ አንድ ኤርትራዊ ወዳጃችን “ኤላ ሰርጎ”ን ሲፈታልን `ከጀርባው ፌሎሶፊ አለው” ነው ያለኝ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡

የትግረ ሴት ለምትወደው አንድ ሰው (ለባሏ) እንጂ ለማንም ጸጉሯን አትገልጠውም፡፡ ስለዚህ ጉብሊቷን ልጅ የወደደው አሕመድ ሼክ በተዋቡ ግጥሞች እያወደሳት ዘፈነላትና ፍቅሩ ልቧ ውስጥ ዘልቆ መግባቱን ለማረጋገጥ ጸጉሯን ማየት ጀመረ፡፡ እርሷም ግጥሞቹን ከሰማችለት በኋላ ጸጉሯን ገልጣ አሳየችው፡፡ ድል አድራጊው ወዲ ሼክም ይዟት በረረ፡፡ ኤላ ሰርጎ! ኤላ ሰርጎ” እያለ ነጎደ!
——
ሰሜን ኤርትራ!
ተወዳጇ የከረን ከተማ እዚህ ነው ያለችው! የሀረርጌዋ የድሬ ዳዋ ከተማ መንትያ እህት የምትመስለው ውቢቷ የሰሜን ፈርጥ! በቪዲዮ አይቻት ውበቷን አደነቅኩላት! አበቦቹ! ቤቶቹ! መንገዶቹ ሁሉም ውብ ናቸው፡፡ ከትግራይ የተገኘው ዝነኛው ብርሃነ ሃይለ አንድ ላይ በነበርነት ዘመን ለከረኗ ጉብል እንዲህ ብሎላታል፡፡

ሸው በሊ ብለነይ ብለነይ
ዝለሊ ብለነይ ብለነይ
አሊሊ ብለነይ ብለነይ
አቲ ጓል ከረነይ ብለነይ

አዎን! ቢለን ከከረን ከተማ ጋር ስሙ የሚጠቀስ ብሄረሰብ ነው፡፡ ቋንቋው ከኛው የአገው ቋንቋ ጋር አንድ ዐይነት ነው፡፡ እንግዲህ እዚህ ላይ ነው አንባቢ ሊመራመር የሚገባው፡፡ በወሎና በጎጃም የሚኖረው አገው ምን ሊያደርግ እዚያ ሄደ?… መቼ ነው እዚያ የሄደው?… መላምት ከመዘብዘብ በስተቀር ማንም ሰው ይህንን እንቆቅልሽ በሚያመረቃ ሁኔታ ሊፈታው አልቻለም፡፡ ኤርትራና እኛ አንድ ነን የሚያሰኘኝ እንዲህ ዓይነት ተጨባጭ ማስረጃ ስላለን ነው፡፡

ቢለን ውብ ባህል ያለው ህዝብ ነው፡፡ በዚህ ህዝብ ባህል መሰረት ሴቶቹ ካገቡ በኋላ ጸጉራቸውን መሰተር ግድ ነው፡፡ ህዝቡ የቢለን ቋንቋ ተናጋሪ ቢሆንም የትግረ ቋንቋንም ይጠቀማል፡፡ ትግርኛም በስፋት ይነገራል፡፡ እጅግ ታዋቂ የሆነው የቢለን ተወላጅ “ዑመር እዛዝ” ነው፡፡ የጀብሃ ጦር ከመፍረክረኩ በፊት የሁለተኛው ዞን አዛዥ እንደነበረ ከዚህ በፊት ጽፌ ነበር፡፡

ከከረን ሽቅብ ወደ ሰሜን ስናመራ ታሪካዊቷ አፋቤት አለች፡፡ ጄኔራል ታሪኩ አይኔ የሚመራው ናደው እዝ እዚህ ነበር የሰፈረው፡፡ የቀይ ኮከብ ዘመቻ ዋና አምባም ይህ ነበር፡፡ ከአፋቤት ወደ ሰሜን ስንበር ንዳዳማውና አስቸጋሪው የሳህል መሬት አለ፡፡ በዓሉ ግርማ እንደተረከልን ከሆነ ሳህል ማለት እሳት ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች ይኖሩበታል፡፡ ከብቶች ይሰማሩበታል፡፡ ተክልም ይበቅልበታል፡፡ እዚህ አካባቢ በብዛት የሚኖረው ህዝብ “ረሺዳ” ይባላል (አንዳንዶች “ራሻይዳ” ይሉታል፤ ስህተት ነው፤ ትክክለኛው አጠራር “ረሺዳ” ነው)፡፡

የ“ረሺዳ” ህዝብ ከሌላው የኤርትራ ህዝብ የሚለይበት በርካታ ነገሮች አሉት፡፡ ለምሳሌ ይህ ህዝብ ከሳዑዲ ዐረቢያ ተነስቶ ወደ ኤርትራ የገባው በቅርብ ዘመን (በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ) ነው፡፡ በዚያ ወቅት የአሁኗ ሳዑዲ ዐረቢያ አልነበረችም፡፡ ሀገሩ ሁሉ በጎሳዎች የተከፋፈለ በረሃማ ምድር ነበር፡፡ ከነዚህ ጎሳዎች አንዱ አል-ረሺድ ይባላል፡፡ ይህ የአል-ረሺድ ህዝብ የአካባቢው የበላይ እንዲሆን በኦቶማን ቱርክ ተወሰነ፡፡ አብዛኛው ህዝብም ለነርሱ አደረ፡፡ “አል-ሱዑድ” የሚባለው ቤተሰብ ግን “አሻፈረኝ” አለ፡፡ “ራሴ በረሃውን ጠቅልዬ መግዛት ስችል ለምን በአል-ረሺድ ጎሳ የበላይነት አድራለሁ” በማለት አንገራገረ፡፡ በሁለቱ መካከል ጠብ ተነሳ፡፡ በመጀመሪያው ላይ የአል-ረሺድ ጎሳ አሸነፈ፡፡ አል-ሱዑዲዎች ወደ ኢራቅ ሸሹ፡፡

ከጥቂት ዓመታት በኋላ ግን የአል-ሱዑድ ቤተሰብ በእንግሊዞች ደጋፊነት ራሱን አጠናክሮ መጣ፡፡ በአል-ረሺድ ጎሳ ላይም ድልን ተቀዳጀ፡፡ በዚህም የተነሳ የዐረቢያ በረሃ ለአል-ረሺድ ጎሳ አባላት ሲኦል ሆነ፡፡ ረሺዳዎች እየተያዙ በጅምላ ታረዱ፡፡ ንብረታቸው ተዘረፈ፡፡ በፊት ይረዳቸው የነበረው የቱርኮች መንግሥት በራሱ ችግር በመወጠሩ ምንም ሊያደርግላቸው አልቻለም፡፡ በመሆኑም ከእልቂቱ ለመዳን ሲሉ ባህር እያቋረጡ ወደ አፍሪቃ ምድር ተሰደዱ፡፡ በሱዳንና በኤርትራ መኖሪያቸውን ቀለሱ፡፡

እንግዲህ ረሺዳዎች ከዘር ማጥፋት ወንጀል ለመሸሽ ወደ ኤርትራ የመጡ ተፈናቃዮች ናቸው ማለት ነው፡፡ በኤርትራ ውስጥ ንጹህ የዐረብ ዝሪያ የሚባሉት እነርሱ ናቸው፡፡ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸውም ዐረብኛ ነው፡፡ በረሺዳ ባህል መሰረት ለአካለ መጠን የደረሰች ማንኛዋም ሴት ፊቷንም ሆነ ጸጉሯን መሸፈን ግዴታዋ ነው፡፡ በዓሉ ግርማ በኦሮማይ ውስጥ ሲተርክልን “ማንኛውም የረሺዳ ባል የሚስቱን ፊት ገልጦ የሚያይበትን ሰው አይፈልግም” በማለት የተናገረውም የባህላቸው አንድ አካል ነው፡፡
—————–

Image

ከዚህ ቀደም የብርሃኑ አባነጋን መንሸራተት አስመልክቶ የፖለቲካ ሽርሙጥና እንደሆነና ግለሰቡም የፖለቲካ ዝሙት በመፈጸም ላይ እንደሆነ ቢገለጽም ሰሚ ጆሮ ለማግኘት አልታደልንም :: አዎ እንደ ግንቦት ሰባት እና እንደኢሳት ያሉ የዲያስፖራው መስታዎቶች ሊያዳምጡን ፍቃደኛ ካለመሆናቸውም በላይ እነሱ የሚያዳምጡት የወያኔን ዝሙተኛ ፖለቲከኞችን ስለሆነ መለማመጥን አንፈልግም:; ደስ ካላቸው ደስ ይበላቸው ደስ ካላላቸው ገደል ይግቡ ….. እኛ ግን ኢትዮጵያዊነታችንን የሚነጥቀን በነጻነት የምንተነፍሰውን ሃሳብ የሚገድብ ምንም ነገር አይመጣም…. እኛም አናቆምም …

በመጀመርያ ደረጃ ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር በሻእቢያ እና በወያኔ መካከል ከፍተኛ የሆነ የመረጃ ልውውጥ በፓርቲ ደረጃ እንደሚካሔድ እና ሁለቱ ጸረ ኢትዮጵያ አቋማቸው ያንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ መሆኑ ልንቀበለው የሚገባ ጉዳይ ነው:: አለም ሰልጥኖ ወደ አንድነት በማምራት በሰው ልጆች መካከል ያለ የቀለም እና የዘር ልዩነትን ለማጥፋት እና በቴክኖሎጂ እውቀት ተመንጥቆ ለመሄድ በሚሰራበት ዘመን በኢትዮጵያ ውስጥ ባረጀ እና ባፈጀ የጎሳ ፖለቲካ ጥያቄ ህዝብም ውስብስብ መንገድ ላይ በመጠላለፍ ለመከፋፈል እና ጠንካራ ሃገራዊነትን ለማዳከም የሚሰሩ ስራዎችን ልብ ብለን ማጤን እንዳለብን ለማስታወስ እገደዳለሁ:;

ብርሃኑ ዳምጤ አሊያም አባመላ በመባል የሚታወቀው የፖለቲካ ግልሙተኛ እና ሴሰኛ ግለሰብ ማረፊያ ያጣበትን ተሌኮ ለማስፈጸም በሚያደርገው መራወጥ ውስጥ ራሱን ግንቦት ሰባት ብሎ ከሚጠራው ድርጅት ጋር የፖለቲካ ዝሙት ሲፈጽም ቆይቶ በሁለት ስለት ቢላዋ በማረድ የራሱን እና የሌሎችን ደም በአደባባይ ለማፍሰስ ቆርጦ የተነሳ እና ያልተሳካለት ግለሰብ ነው::
ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር ይህ ግለሰብ ትክክል ነው ይህ ግለሰብ ትክክል አይደለም የሚለው ነገር እንደተጠበቀ ሆኖ የደፈረሰው መጥራት እንዳለበት በግልጽ ለመናገር እፈልጋለሁ::

ብርሃኑ ዳምጤ አባመላ በሚለው የፓልቶክ ፕሮግራሙ አጀማመሩ የወያኔን በልማታዊነት ሽፋን የሚሴረውን የጎሳ ፖለቲካ እና የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ በዲያስፖራው ውስጥ ለማስረጽ የፕሮፓጋንዳ ስራ ሲሰራ ቢቆይም ሊሳካለት አለመቻሉ ጸረ ወያኔ አቋም እንደያዘ ተደርጎ በሰርጎ ገብነት ከወያኔ በወረደለት ትእዛዝ አባካኝነት እና ከሻእቢያ ጋር በተደረገ የመረጃ ልውውጥ በሻእቢያ የነገር አባትነት ከግንቦት ሰባት ንቅናቄ ጋር የፖለቲካ ዝሙት እንዲፈጽም ተደረገ:: የፖለቲካ ዝሙቱ በእርካታ ታጅቦ በኢሳት የሳምንቱ እንግዳ ሆኖ ወያኔ በማሳጣት እና በመዝለፍ በሰርጎ ገብ የቆረጣ ታክቲክ የኢሳት ጋዜጠኞችን በማወዳደስ ግንቦት ሰባትን በማንቆለጳጰስ ራሱን ከተቃዋሚዎች ጎራ አሰልፎ የነበር ሲሆን እንዲሆን አክራሪዎች አሸባሪዎች ሲላቸው የነበረውን የኢትዮጵያውያንን ሙስሊሞች ትግል ለመጠጋት በመሞከር ቢያሞጋግስም አናቱን በፍልጥ ስላልነው ሳይሳካለት ቀርቶ አፉን ይዞ ተቀመጠ:: ዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሲኖር ከነበረው ከጃዋር መሃመድ ጋር ማታ ማታ ሻይ ቡና እያለው የኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎችን ፖለቲካ በማጥላላት እና በወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ሲያጠምቀው የነበረው አባመላ ዞር ብሎ አዛኝ በመምሰል በጃዋር መሃመድ ላይም ጸር የሆኑ ቃላቶችን ሲተፋ እንደነበር ሲታወቅ አባመላ ራሱ ጃዋርን በጥላቻ ሲያሰለጥነው እንደነበር የማይዘነጋ እውነት ነው::

ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ብሎ ራሱን የሚጠራው ድርጅት ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንን እንደማይወድ እና ከጀርባው በሻእቢያ እየተጠመዘዘ የጸረ ኢትዮጵያ አቋም ማራመጃ መሆኑ የማይካድ ሃቅ ነው:: እንደ ኢሳት ባሉ በዲያፖራው ሃብት በሚተዳደሩ ሚዲያዎች የፖለቲካ ትግል እና የለውጥ አማራጭ ሃሳብ ያላቸው ኢትዮጵያውይና እንዳይቀርቡ እና እንዳይጠቀሙ በማገድ የወያኔ ትርፍራፊ የፖለቲካ ጋለሞታዎች እንዲዘፍኑበት መደረጉ አሌ የማይባልበት ጉዳይ ሲሆን በዚህ ጉዳይ ላይን ራሱ የሚዲያ ነጻነቶችን በመጋፋት ለውጥ ከማምጣት ይልቅ ነጻነቶች በሻእቢያና ወያኔ ተላላኪዎች በተዘዋዋሪ ሲቀበሩ እያየን ነው::

እንደ ግንቦት ሰባት ያሉ ድርጅቶች በፖለቲካ አማራጭ ሃሳብ የያዙ እና ለውጥ በማምጣት ረገድ ሚና መጫወት የሚችሉ ኢትዮጵያውያንን በመግፋት የወያኔ ሰርጎ ገብ ወንበዴዎችን በአመራር እና በድርጅታቸው የደህንነት መዋቅር ውስጥ በማስገባት ራሳቸውን ከትግሉ ውጪ ለመጠለዝ እየተወራጩ ይገኛሉ:; ኢሳት የሚዲያ ተቋም ተብሎ እስከተቋቋመ ድረስ ማድረግ የሚገባውን የማያውቅ እና ባልበሰሩ ሰዎች እና የጋዜጠኝነት ልምድ ባሌላቸው እንዲሁም በሳል እና ሚዛናዊ መረጃዎችን ባልያዙ ደረቅ ተንታኞች ታጅቦ የሞት ጉዞውን እያፋጠነ ነው::

ወያኔ በብርሃኑ ዳምጤ በኩል በአባቱ ሻእቢያ አዝማችነት የመጀመሪያ ዙር ስራውን አጠናቆ ብርሃኑ ዳምጤን ወደ ልማታዊ ጋዜጠኝነት መልሶታል:; በሃገር ወዳድነት ሽፋን በማስመሰል የተካነው ብርሃኑ ዳምጤ ድራማውን አጠናቆ ዲያስፖራ ተቃዋሚዎችን በመዝለፍ ስራ ላይ ተመልሶ ተሰማርቷል:: ካሁን በኋላ የአባመላ ፓልቶክ እንግዶች እንደ ጃዋር እና ዘርኣይ ያሉ የጥላቻ ፖለቲካ ስልጥኡኖች ናቸው:;ከሃገር ቤት የተሰራውን የወያኔን ድራማ እና የሚሚ ስብሃቱን ጸረ ግንቦት ሰባት እና ኢሳት ውንጀላ እና ትችት ተከትሎ የብርሃኑ ዳምጤ ትፋት ምን እየተሰራ እናዳለ እና የዲያስፖራውን የለውጥ ፖለቲካ ገደል ለመክተት በህዝብ የመኖር ህልውና ላይ ፍርሃት እና ሽብር ነዝቶ ወያኔን በስልጣን ለማቆየት የተሸረበውን ሴራ በገሃድ ያሳያል::

ከዳዊት ከበደ እና ከጃዋር የሰርጎ ገብ ፖለቲካ ያልተማሩት ግንቦት ሰባት እና ኢሳት ሃገር ወዳድ እና ብዙ ስራዎችን ሊሰሩ የሚችሉ ኢትዮጵያውያንን ወደ ጎን በማግለል በዙሪያቸው እንደብርሃኑ ዳምጤ ያሉትን ሰርጎ ገቦች በመኮልኮል ያላዋቂ ሳሚ … ሆነው ህዝቡን … በመለቅለቅ ላይ ይገኛሉ::ኢሳት አንድ ሃገር ወዳድ የሆነ ኢትዮጵያዊ በፕሮግራሞቹ ላይ ከማቅረብ ይልቅ የወያኔ ኮልኮሌ የመረጃ ሰዎች እና ሰርጎ ገቦችን ቢያቀርብ ያተረፈ እየመሰለው በፖለቲካ ኪሳራ ውስጥ ገብቶ ከሕዝብ ልሳንነት ይልቅ የግንቦት ሰባት ልሳን እንደሆነ እያንጸባረቀ ነው:: ኢህኣፓ በተፋቻቸው እንደ ብርሃኑ ነጋ ባሉ የፖለቲካ ሰልባጆች ትእዛዝ የሚመራ አስመስሎበታል:: እንደ ነእመን ዘለቀ ባሉ በሻእቢያ እና ወያኔ ትራፊዎች የሚመራው ኢሳት አጀማመሩ መልካም ቢመስልም ግን በጀት አይለቀቅልህም ከወያኔ ከዳሁ የሚሉ ግለሰቦችን እያባዛህ ካላቀረብክ የተባለ ይመስል ነጋ ጠባ የምናያቸው የወያኔ ሰዎችን መሆኑ አሳሳቢ አድርጎታል::ስለዚህ ግንቦት ሰባት እና ኢሳት ከወያኔ ሰርጎ ገቦች ጋር የፖለቲካ ዝሙት እየፈጸሙ የህዝብን ትግል እየገደሉት ነው ቢባል ድፍረት አይሆንም:: ለዛሬ በዚህ ይብቃ ጹሁፉ ቀጣይ ነው ይጠብቁት::

የአመራርና የውሳኔ ሰጭነት አቅማቸው አጠያያቂ ኾኗል (ፋክት፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፴፮ የካቲት ፳፻፮ ዓ.ም.) ከዓመት በፊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፮ኛው ፓትርያርክ ኾነው የተመረጡበት አንደኛ ዓመት በዓለ ሢመት፣ የካቲት ፳፬ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. የተከበረላቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ በሕገ ቤተ ክርስቲያን ከሚታወቀው አስተዳደራዊ መዋቅር ውጭ ለአማካሪነት አቅርበዋቸዋል በተባሉ አካላትና ግለሰቦች ማንነት ሳቢያ በአንድ የቅዱስ …

ስለ ማኅበራት የሰጡትን አስተያየት መልሰው እንዲያጤኑት ተጠየቀ ‹‹ማኅበራት በትኩረት ሊመሩና ጉዟቸውም እየተፈተሸ ሊስተካከል ይገባል›› መንግሥት (አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፫ ቁጥር ፯፻፴፰፤ የካቲት ፳፱ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ‹‹ከዩኒቨርስቲ ተመርቀው ቤተ ክርስቲያንን እንምራ እያሉ ነው፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ ትውፊትና ሥርዓት አላት፤ እንዲህ ማለት አይችሉም›› በማለት የሰጡትን አስተያየት መልሰው …

ናትና ህጻን ልጅዋን ገድሎ የተሰወረው ሰውዬ ትውልዱ ኢትዮጵያዊ ሲሆን በፈረንሳይ ፓሪስ ክርተማ የጎዳና ላይ ተዳዳሪ ነበር:: ሟች ወ/ሮ ክውን ገዳሙ ትባላለች:: ከቤትዋ ወደ ስራ ቦታ ሲመላለሱ ተጠርጣሪውን የዩታል:: በጎዳናው የተጎሳቆለውን ሰው(ጉዳዩ በህግ ስለተያዘ ስሙን እዚህ ላይ አንጠቅሰውም) ስለሚያሳዝናቸው ባለፉ ባገደሙ ቁጥር እጃቸውን ይዘረጉለት ነበር::

ከግዜ በኋላ ከክረምቱ ብርድ እንዲገላገል ሲሉ ይህንን የጎዳና ተዳዳሪ ለግዜው በቤታቸው አስጠጉት:: የአቅማቸውን እየረዱት አብረው ለወራት ኖሩ::

ባለፈው ሳምንት አንድ አስደንጋጭ ክስተት በቤተሰቡ ውስጥ ተፈጸመ:: በችግሩ ያስጠጉት ሰው ከተኙበት በጭካኔ ገድሏቸው አመለጠ::

ወ/ሮ ክውን ገዳሙ የሶስት ልጆች እናት ሲሆኑ በፈረንሳይ ፓሪስ ለረጅም ግዜ ኖረዋል:: የሶስት ልጆች እናትም ናቸው:: ያለአባት ከሚያሳድጓቸውን ሶስት ልጆች ውስጥ አንደኛዋና የሁሉም ታናሽ ከሆነችው ጋር ላይመለሱ ይህችን አለም ባለፈው ሳምንት ተሰናበቱ::

ገዳዩ ጭካኔ በተሞላበት መንገድ በጩቤ ሰነጣትቆ ነው እናትና ልጅን ለህልፈት የዳረገው- እንደ ፈረንሳይ የዜና ምንጭ:: ባጎረሱት እጅ ተነከሱ:: ደግ ባደረጉ ምላሹ ግድያ ሆነ: ለዚያውም አረመኔያዊ ግድያ::

ነብሰ ገዳዩ ለግዜው ተሰውሯል:: የፈረንሳይ ፖሊስ ከኢንተርፖል ጋር በመሆን ጉዳዩን በጥብቅ ይዞታል:: እኛም እየተከታተልን ጉዳዩ ምን እንደደረሰ እናቀርብላችኋላን::
ክንፉ አሰፋ