ሰበር ዜና – ‹‹አቦይ ስብሐት ጎበዝ ነኽ አለኝ›› ያሉት ፓትርያርኩ የማኅበራትን ተጠሪነትና የገንዘብ እንቅስቃሴ በሚመለከተው የሕጉ ረቂቅ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ተፋጠው ዋሉ
- ፓትርያርኩ የማኅበራት ገንዘብ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ገቢ ኾኖ በማእከል ካልተመራ በሚል ከማኅበራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ጋራ የሚቃረን ግትር አቋም ይዘው ውለዋል፡፡
- አቋማቸው ተቀባይነት ካላገኘ ስብሰባውን ለመምራት እንደሚቸገሩ በመግለጽ ምልአተ ጉባኤን ለማስገደድ ያደረጉት ሙከራ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ጽኑ አቋም ሳቢያ አልተሳካላቸውም፡፡
- ጉዳዩ ‹‹ከአዲስ አበባ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ጋራ ብዙ የሠራኹበትና የደከምኩበት ነው፤ በቀላሉ የምተወው አይደለም›› በሚል ከአክራሪነት ጋራ የተገናኘ ጽሑፍ ሲያነቡ ውለዋል፡፡
