ሰብአዊ መበቶችን በመጣስ፣ ግፍ በመፈጸምና አፈናን በማጠናከር እደሜ የሚሸምት የአገዛዝ ሥርዓት የእያንዳንዱን ሰው መንፈሳዊና አካላዉ ጥንካሬ የማዳከም፣ ቅስምን የመስበርና ፍርሃትን የማንገስ ከፍተኛ አቅም እንዳለው ሁሉ በብሶት የሚወለዱ፣ እምቢኝ ለግፈኞች፣ እምቢኝ ለአንባገነኖች፣ እምቢኝ ለነጻነቴ የሚሉ መንፈሰ ጠንካራ ጀግኖችንና ታጋዮችንም ይወልዳል:: የአለማችን ስመ ጥርና ዘመን የማይረሳቸው የነጻነት ታጋዮች እነ ማህተመ ጋንዲ፣ ማርቲን ሉተር ኪነግ፣ ማንዴላ፣ ኡንግ ሳን […]

የባህዳር ነዋሪ በነቂስ በመውጣት በክልሉ ም/ቤት ፊት ለፊትና በአዲሱ ም/ቤት(ቀበሌ 10) መስቀል አደባባይ የቤተክርስያን የታቦት ማደሪያ ፣ ንብረትነቱም የቤተ-ክርስቲያን ነው ልትነጠቅ ወይም መንግስት እንደሚለው ለባለሀብት ሊሰጥ አይገባም በማለት ቁጣቸውን በማሰማት ላይ ናቸው፡፡ የባጃጅ ሾፌሮችም በየቦታው ትላክስና ጩኸት እያሰሙ ነው፡፡ የመስቀል አደባባይን መፍረስ በመቃወም በባህርዳር ከተማ የነበረው ሰልፍ ጥያቄውን አሰምቷል:: ሆኖም በአሁኑ ሰዓት በባህርዳር ከተማ በሕዝበ […]

ምርጫ በአንባገነን መንግስት ውስጥ? ምርጫ የዴሞክራሲያዊ ስርአት መገለጫ የሚሆነው ነጻ፣ ፍትሃዊና ተወዳዳሪ (free, fair and contested) ባህሪያትን የተላበሰ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ በኢ-ዴሞክራሲዊ መንግስት ውስጥ የሚደረጉ ምርጫዎች በምንም መመዘኛ የዴሞክራሲ ስርዓት መገለጫዎች አይሆኑም፡፡ በሀገራችን በአጼው፣ በደርግ እና በኢህአዴግ ዘመነ-መንግስታት ተደርገው የነበሩ ምርጫዎች የአጼውን፣ የደርጉንና የኢህአዴግን የአገዛዝ ስርዓቶች የስልጣን ዘመን ለማራዛም የተደረጉ (“mechanism of regime maintenance”) ምርጫዎች […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ፣ ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ በስንት ውጣ ውረድ ያገኙትን ሥልጣን ጥርሳቸውን ነክሰው ከያዙ ሁለት ዓመት ከሁለት ወርና 26 ቀን አስቆጥረዋል። በእነዚህ ወራት ውስጥም፡ ኃይለማርያም ሥልጣን የረገጡ ቀን ስለራሳቸው ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሰጡት ምስክርነትና ግምት ከዛሬው ኃይለማርያም በአያሌው የተለያዩ ናቸው። ገና መጀመሪያ ላይ ከመለስ ጀርባ ከጦር አዝማችነታቸው ወጥተው (በካድሬነታቸው) በሙቱ ማግሥት የሥልጣንን በር ሲይንኳኩ፣ […]

ከ250 አመታት በፊት ፣ 13 ኮሎኒዎች፣ ተብለው የሚታወቁት የአሜሪካ ግዛቶች በእንግሊዝ ሥር ነበሩ። አሜሪካኖቹ የግብር ጫና ስለበዛባቸው ለነጻነት መታገል ጀመሩ። በአሜሪካኖች እና በእንግሊዞች መካከል ጦርነት ተጀመረ። የአሜሪካኖች መሪ ጀነራል ጆርጅ ዋሺንግተን ነበሩ። እንግሊዞች ብዙ ጦር አሰልፈው ያመጹ አሜሪካዉያንን ለማስገበር ተንቀሳቀሱ። በኑዮርክ አሜሪካኖች ትልቅ ሽንፈት ደረሰባቸው። የእንግሊዝን ጦር መቋቋም አልቻሉም። ጆርጅ ዋሽንግተን፣ በሌሊትና በጉም ወደ 9 […]

ሃገሪቱን የሚያሰጋት የሃይማኖት አክራሪነት/አሸባሪነት ሳይሆን የፖለቲካ የበላይነት የፈጠረው አሸባሪነት ጽንፈኝነት እና አክራሪነት ነው:: ጥላችሁን እንዳታምኑ እየተባለ ሃይማኖት መንግሥታዊ ቅርጽ ይዞ እንዲወጣ ለማድረግ መሞከር አክራሪነት ነው፡፡ «መጾም፣ መጸለይ፣ ሥርዓተ-አምልኮን መፈጸም ሃይማኖታዊ አልባሳትን መልበስ ለሃይማኖቱ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንጂ አክራሪነት ሊባል አይችልም፤»…የአክራሪ ክርስትና ወይንም እስልምና ቡድን መኖር የክርስትና እና እስልምና ተከታዮችን በሙሉ «አክራሪ» አስብሎ ሊያስፈርጃቸው አይችልም::አክራሪ ተብሎ […]

* የገቡት ይወጣሉ ፣ የወጡት ተመልሰው ይመጣሉ * የሳውዲ መንግስት “ህገ ወጦችን” የማጽዳቱ ዘመቻ ቀጥሏል * ስፍር ቁጥር የሌላቸው ዜጎች ከሞት ጋር ተፋጠው እየተሰደዱ ነው * የሳውዲ መንግስት ማስጠንቀቂያና እርምጃ … የሳውዲ መንግስት የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውንና ህጉ በማይፈቅደው መንገድ የመኖሪያ ፈቃዳቸው ካለው ሙያ ውጭ የሚሰሩ የማናቸውንም ሀገር ዜጎች በመላ ሀገሪቱ ለማጽዳት የተደራጀ ዘመቻ ከተጀመረ ወር […]

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ሰማያዊ ፓርቲ እና ሌሎች በትብብሩ ውስጥ የታቀፉ ፓርቲዎች በጠሩት የአዳር ሰልፍ ላይ የወጡ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የተወሰደውን አሳፋሪ እርምጃ ሰምቻለሁ፡፡ እርምጃው ሁለት ነገሮችን በጉልህ ያሳዬ ነበር፡፡ አንደኛ የኢህአዴግ መራሹ መንግስት ሽንፍትን ያሳየ ነው፤ ሁለተኛው ደግሞ ሰላማዊ ትግሉ እየተጠናከረ መምጣቱን ያመላከተ ነው፡፡ አንተ ባዶ እጅህን መብትህን ለመጠየቅ ስትንቀሳቀስ፣ መሳሪያ ወደታጠቀ አካል በሰላም ስትገሰግስ […]

“ሰማያዊ/ትብብሩ ምርጫዉን ያለ ቅድመ ሁኔታ ለመሳተፍ መወሰናቸው ታወቀ” በሚል የትብብሩን ዋና ጸሐፊ አቶ ግርማ በቀለን በመጥቀስ መዘገባችን ይታወቃል። አቶ ግርማ በቀለ “NO Precondition is set by members of Tibibir. We decided to be part of the election and advised all members to take their election Sign. Believe me, it is all the decision of Tibibir […]

ፓርቲያችን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ አንድነት ፓርቲ ከአሁን በፊት ቀደም ብሎ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት በሚል ሰፊ የሆነ ህዝባዊ ንቅናቄ ማድረጉ የሚታወቅ ነው። በመቀጠል ደግሞ የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነትና የሚሊዮኖች ድምፅ ለህሊና እስረኞች የሚሉ ዘመቻዎች በተከታታይ አካሄዷል። የዚህ ዘመቻ የመጨረሻው ምዕራፍ የሆነው የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃና ፍትሀዊ ምርጫ በዚሁ እጅግ የተሳካ ጉባኤ ባካሄድንበት ማግስት የሚካሄድ በመሆኑ ፓርቲያችን ባሁኑ […]

በቅርቡ የአንድ ወር መርሃ ግብር አዉጥቶ ሲንቀሳቀስ የነበረው የሰማያዊ ፓርቲና የዘጠኝ ድርጅቶች ስብስብ፣ ትብብር፣ ያለ ቅድሜ ሁኔታ በመጪው የ2007 ምርጫ እንደሚሳተፍ አሳወቀ። ትብብሩ ለምርጫ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጡን የምገልጹ አንዳንድ ዘገባዎች በተለይም በዳያስፖራ አካባቢ የሚሰሙ እንደሆነ ቢታወቅም፣ የትብብሩ ዋና ጸሃፊ አቶ ግርማ በቀለ በፌስ ቡክ በግልጽ በሰጡት አስተያየት፣ ትብብሩ ለምርጫ ቅድመ ሁኔታ አለማስቀመጡን ገልጸዋል። “NO Precondition […]

እንደ መነሻ ከሁለት ወር በፊት አንድነትን እንዲመሩ በጠቅላላ ጉባዔ የተመረጡት ኢ/ር ግዛቸው ሺፈራው ጥቅምት ሁለት ቀን 2007 ዓ.ም ካቢኔያቸውን በትነው ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው ለብሔራዊ ምክር ቤቱ አስረከቡ፡፡ የቀድሞው ፕሬዘዳንት ኢ/ር ግዛቸው ለምክር ቤቱ ባሰሙት ንግግር በአመራራቸው ያልተደሰቱ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎችን የ‹‹ልቀቅ›› ጫና መቋቋም እንዳልቻሉና ከህሊናቸው ጋር ተማክረው ለፓርቲው ጥቅም ሲባል በፈቃዳቸው ሃላፊነታቸውን […]

አንድነት በነገው ዕለት ተደራጅ 2007 ለለውጥ የሚል ዘመቻ በሶሻል ሚዲያና መዋቅሩ በዘረጋባቸው የሀገሪቱ አከባቢዎች ሁሉ ይጀምራል! የዚህ ዘመቻ ዓላማ በቀጣዩ ምርጫ ፓርቲው አሸናፊ ሆኖ አንዲወጣ የሚያደርጉት ህዝባዊ ንቅናቂዎች ለመፍጠር ያለመ ሲሆን፤ ህዝቡ በምርጫው ሂደት ከመጀመሪየው ጀምሮ ተሳታፊ እንዲሆን በፓርቲው በአባልነትና በደጋፊነት እንዲደራጅና በንቃት እንዲሳተፍ ያደርጋል። ህዝቡ ተደራጅቶ ታህሳ 12 በሚደረገው የህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ ላይ ቤቀበሌው […]

(ጨዋታው ተጀምረ፡፡ ይህ ጨዋታ ለሕዳሴው ግድብ ድጋፍ ሲባል የሚደረግ መሆኑን ያለማሳወቅ አያስፈልግም፡፡ ያለእንደዚህ ያሉ የድጋፍ ሰጪ ጨዋታዎች የህዳሴው ግድብ ፕሮጄክት አይጠናቀቅም ሲሉ ቃል አቃባዩ እንጂነር ስመኘው ገልፀዋል፡፡) በሃገራችን ኢትዮጵያ እንደ ውሃ ወለድ በሽታዎቻችን ብዛት ሁሉ ሁኔታ-ወለድ የሆኑ ብዙ ክስተቶች ያጋጥማሉ፡፡ከነዚህ መሃል በተለይ በፖለቲካው መስክ ሰዎች የሚያገኙት ስፍራ ከማንነታቸው ጋር የማይገጥም እየሆነ ተቸግረናል፡፡ አሁን ባለው ነባራዊ […]

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የጠራው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ እጅግ ደማቅ በሆነ ሁኔታ ያካሄደ ሲሆን፤ በጠቅላላ ጉባኤው ሶስት ዋና ዋና ተግባራት ተካሄደዋል፤ የመጀመሪው አጀንዳ ኢር ግዛቸው በራሳቸው ፍቃድ ስልጣናቸውን በለቀቁ ጊዜ የአንድነት ብሄራዊ ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤው በሰጠው ስልጣን መሰረት አዲስ የፓርቲው ፕሬዚደንት መምረጡ ጉባኤው ተቀብሎ ያፀደቀ ሲሆን፤ በዚህ መሰረትም አቶ በላይ ፍቃዱ የፓርቲው ፕሬዚደንት ሆነው […]

የጠ/ሚ/ር ስልጣን ወደ ሕወሐት ለመመለስ የፓርቲው ቁልፍ አመራሮች በምስጢር ሲመክሩ መስንበታቸውን የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። በአቶ ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል፣ አባይ ፀሐዬ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ጄ/ል ሳሞራ የኑስ፣ ፀጋይ በርሔ፣ አርከበ እቁባይና ስብሃት ነጋ የሚመራው የሕወሐት ከፍተኛ አመራሮች ከዚህ ቀደም ሲካሂዱት በነበረውና ህወሀት የጠ/ሚ/ ርነት ስልጣን መልሶ መያዝ ይኖርበታል፣ የሚለውን ምክክር ከዳር ለማድረስ አቋም መያዘያቸውን ያስታወቁት ምንጮቹ በተለይ በቅርቡ […]

መሐሙድ የሱፍ የተወለደው በ1980ዓ.ም ከሶማሌ ክልል ርእሰ-መዲና ጅጅጋ 500 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘውዶሀን ከተማ ነው፡፡ ለቤተሰቡ ሰባተኛ ልጅ ሲሆን፤ አምስት እህቶችእና ሦስት ወንድሞች አሉት፡፡ በጅጅጋ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እስከ አስረኛ ክፍል ድረስ መዝለቁቢሳካለትም፤ ከዚህ በላይ ግን ሊቀጥል አልተቻለውም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የኢትዮጵያመንግስት የደህንነት ሠራተኞች የ1999ዓ.ም የግንቦት ሃያ በዓል በጅጅጋ ከተማ ስታዲዬም በተከበረበት ዕለት፣ የኦጋዴን ነፃአውጪ ግንባር […]

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በጠራው ልዩ ጠቅላላ ጉባኤ ሁለት አጀንዳዎችን በመወያየት አፅድቋል፡፡ በመጀመሪያ አጀንዳነት የተነሳው የኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ ብሔራዊ ምክር ቤቱ የሰየመውን ፕሬዝደንት ተወያይቶ ያፀደቀ ሲሆን በሁለተኛ አጀንዳነት የተያዘው እና ምርጫ ቦርድ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ቁጥራችሁን አሳውቁኝ ባለው መሰረት የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ቁጥርን ወስኗል ፡፡ ጠቅላላ ጉባኤው በዛሬው ስብሰባ ከሁለቱ […]

“ዘ ጋርዲያን” (The Guardian) በተሰኘው ታዋቂ ጋዜጣ እ.አ.አ ነሐሴ 15 ቀን 2006 እንደ ተዘገበው፤ የጀርመን መንግሥትን በመወከል፤ ወ/ሮ ሔይደማሪ ዊዞረክ-ዜዩል (Mrs. Heidemarie Wieczorek-Zeul)፤ የጀርመን የልማት ሚኒስትር፤ ሐገራቸው እ.አ.አ. በ1904 በናሚቢያ ነዋሪዎች (ሔሬሮዎች) ላይ ስለ ፈጸመችው የዘር ማጥፋት ወንጀል ይቅርታ ጠይቀዋል። ለዚህም ወንጀል፤ ናሚቢያውያን (ሔሬሮዎች) ከይቅርታ መጠየቁ በተጨማሪ $4 ቢሊዮን ካሣ እንዲከፈል የጀርመን መንግሥትን መጠየቃቸው ተገልጿል። […]

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና በማኅበረ ቅዱሳን የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ክፍል ሓላፊ የሆኑት ዲ/ን ዶ/ር መርሻ አለኸኝ ከጥቂት ወራት በፊት በስምዐ ጽድቅ ጋዜጣና በማኅበረ ቅዱሳን ድረ ገጽ ላይ በተከታታይ ‹‹የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በዘወርት›› በሚል ዐቢይ ርእስ ያቀረቡትን ጥናታዊ ጽሑፋቸውን ተከታትያለኹ፡፡ ዶ/ር መርሻ በተለይም ደግሞ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በዓለም አቀፍ ደረጃ በዓለም የክርስትና መድረክ የነበራትንና አሁንም ያላትን ልዩ […]

የአንድነት ጠቅላላ ጉባኤ እጅግ ደማቅ በመሆነ ሁኔታ እየተካሄደ ነው። የብሔራዊ ምክር ቤት አባላት አረንጓዴ ፤የአዲስ አበባ ምክር ቤት ቢጫ፤ የክልል ዞን ተወካዮች ቀይ ቲሸርቶችን በመልበስ ለጉባኤው ድምቀት ሰጥተውታል፡፡ ዛሬና ነገ በሚደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ምርጫ ቦርድ በድርጅቱ ደንብ ላይ የኮረም ቁጠር ይጠቀስ የሚል ጥያቄ በመቅረቡ፣ የቀረበው ጥያቄ ከሕግ ውጭ ቢሆንም ( ደርጅቶች የሚተዳደሩበትን ደንብ ምን […]

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለዛሬ አርብ (03/04/07) የጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ በደማቅ ሁኔታ ተጀምሯል። ጠቅላላ ጉባኤተኛው ወደ አዳራሹ የገባው ፓርቲው ያዘጋጀውን ነጭ ኮፍያ በአንድነት ያደረጉ ሲሆን የብሔራዊ ምክር ቤት አባላት አረንጓዴ ፤የአዲስ አበባ ምክር ቤት ቢጫ፤ የክልል ዞን ተወካዮች ቀይ ቲሸርቶችን በመልበስ ለጉባኤው ድምቀት ሰጥተውታል፡፡ የጉባኤ ጠሪ ኮሚቴው መድረኩን ተቀብሎ፤ አቶ ብሩ ብርመጂ ንግግር አድርገዋል፡ […]

ቅዳሜ ትብብሩ በጠራው ሰልፍ ለማገዝ ወደ ሰማያዊ ቢሮ ሄዶ ነበር። አግዞ ከዚያ ሲመለስ ይታሰራል። የመኢአድ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ የነበረው ወጣት ተስፋሁን አለምነህ ነው። የሰማያዊ አመራር አባላት በሙሉ ሲፈቱ አቶ ተስፋሁን ስለመፈታቱ የደረሰን ምንም አይነት መረጃ የለም። ሌላው ሕወሃቶች በአንድ በኩል የሰማያዊ አባላትን በመፍታታትቸው ምናልባት ልቦኖ መግዛት ጀመረው ይሆን እያሉ አንዳንዶች ማሰብ በጀመሩ ሰዓታት ሳይሞላ […]

በዛሬው እለት 2/4/2007 ዓ.ም ከክልል የመጡ የአንድነት አመራሮች እንዲሁም የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ጋዜጠኛ ስለሺ ሀጎስ፤ ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ፤ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና ታዋቂ ብሎገር እዩኤል ፍሰሀ በዛሬው እለት አንድነት ፓርቲን ተቀላቀሉ ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ ከሚባሉት ፓርቲዎች አንዱ አንድነት መሆኑን ጠቅሰው ፓርቲውን በመቀላቀላቸው የተሰማቸውን ደሰታ የላቀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ነገ አርብ (03/04/07) ጠቅላላ ጉባኤውን ያደርጋል፡፡ ፓርቲው ከዚህ ቀደም በታህሳስ 19/20/2007 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን አመት ሳይሞላ ሌላ ጠቅላላ ጉባኤ ለማድረግ ለምን እንዳስፈለገ የጉባኤ ጠሪ ኮሚቴ የሆኑትን አቶ አስራት ጣሴን አነጋግረን ነበር፡፡ አቶ አስራት እንዳብራሩት በታህሳስ 2006 ዓ.ም ተካሂዶ በነበረው ጠቅላላ ጉባኤ ምርጫ ቦርድ ማብራሪያ ጠይቆ ነበር፡፡ አቶ አስራት […]

በቦረና ዞን ገላን ወረዳ የአንድነት አባላት መታሰራቸውን ከአከባቢው በደረሰን ሪፖርት አረጋግጠናል። የታሳሪዎቹ ስም ዝርዝር አቶ በድሉ መንግስቱ በቦረና ዞን ገላን ወረዳ ሰብሳቢ፣ አቶ ቆንጨሪ ሳፋይ አባል አቶ ንጉሴ ገልገሎ አባል አቶ ብርሃኑ ሳፋይ አባል ሲሆኑ፤ ሰብሳቢው አቶ በድሉ መንግስቱ የታሰሩት የመንግስትን ስም አላግባብ አጥፍተሀል ተብለው ነው። በተያያዘ ዜና በምስራቅ አሩሲ የኦሆዴድ አባል፣ የጢዮ ወረዳ የሲቪል […]

ኢትዮጵያችን ከምትታወቅባቸው ዘርፈ ብዙ ገዥ- ወለድ ችግሮች መካከል ስደት አንዱ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ ዜጎቻችን በሀገራቸው ላይ ሰርተው የመኖር ዋስትና በመነፈጋቸው፤ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸው እናስተዳድራችኋለን በሚሉ ገዥዎች በመጨፍለቁ የተሸለ ነፃነትና ኑሮ ፍለጋ እግራቸው በመራቸው መሰደድ የተለመደ ሁኗል፡፡ ገዥው ፓርቲም ከራሱ የስልጣን ቆይታ በስተቀር ሀገራዊ አደጋ እየሆኑ የመጡና የዜጎችን ስነ-ልቡና የሚጎዱ ሁነቶችን እንደማንኛውም ዜጋ አድማጭ ከመሆን በዘለለ ችግሩን […]

ዛሬ ዛሬ ከረጅም አመታት ጀምሮ በሃገራችን የተነሳው የሴቶች መብት ይከበር የሚለውን ይህዝብ ጥያቄ ለመቃረን እስኪመስል ድረስ ከባለፉትም ጊዜያቶች በባሰ ሁኔታ የሴቶች መብት እየተጣሰ ይገኛል። ከዛም አልፎ ተቆርቋሪ አካል የሌላቸው የሃገራችን ሴቶች ህይወታቸው አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል። ለዚህም በየጊዜው ወደ ተለያዩ አፍሪካና አረብ ሃገራት በተለይም በሱዳን በየመን የሚፈልሰው የኢትዮጵያውያን ሴቶ ች ቁጥር መጨመር ማረጋገጫ ነው። በተለያዩ […]

‹‹አገዛዙ የወሰደውና ወደፊት የሚወስደው ከእስካሁኑ የባሰ አረመኔነት እርምጃ ይበልጡን ያጠናክረናል›› የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ትናንት ህዳር 30/2007 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ትግሉን ያጠናክራሉ ያላቸውን ውሳኔዎችን አስተላለፈ፡፡ ብሄራዊ ምክር ቤቱ ያስተላለፋቸው ውሳኔዎች ‹‹ህወሓት/ኢህአዴግ በፈፀመው ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ እና እስር ምክንያት ክፍተት ሳይፈጠር የፓርቲው እንቅስቃሴ እንዲቀጥልና ትግሉም እንዲጠናከር የሚያስችሉ ናቸው›› ሲሉ የብሄራዊ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ሰይድ […]

ህዝብን በማይሽር ቁስል አየጎዱ በፕሮፓጋንዳ ማከም አይቻልም:: የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ጥያቄና የኮሚቴው መፈታት ጥያቄ በአስቸኳይ ሊመለስ ይገባል:: ሙስሊም ወገኖቻችን ለሃገራቸው እና ለነጻነታቸው ምን ያህል ቀናኢ መሆናቸውን በተግባር አስመስክረዋል:: ወቅሰን ወቅሰን ወንጅለን ወንጅለን የሰለቸን ለመስማትም የታከተን ነገር ቢኖር ያለፉት ስርአቶች ላይ እና ሌላው ላይ ማሳበብን አንዱን ከአንዱ ለማፋጀት ማፈራረጅን መጠቋቆምን የመሳሰሉት ኢሕአዴጋዊ ባህርያት ናቸው::ወያኔ ኢሕኣዴግ የጭንቅ ነገር […]

በመቀሌ ዞን የአንድነት አመራር አባል የነበረው ወጣት ሺሻይ አዘናው ጥቅምት 22 በደህንነት ኃይሎች ታፍኖ ከተወሰደ በኋላ በመቀሌ በሚገኝ አንድ እስር ቤት ኮማንደር ሰዓረ በሚባል የፖሊስ አዛዥና እርሱ በሚመራቸው ፖሊሶች ከፍተኛ የሆነ ድብደባ ተፈፅሞበታል። ከዚያ በኋላ የት እንዳለ ሳይታወቅ ተሰውሮ ቢቆይም፤ በአሁኑ ሰዓት ማዕከላዊ እየተባለ በሚጠራው የማሰቃያ እስር ቤት እንደሚገኝና በዚህም ቦታ በተከታታይ ለአራት ቀናት ሌሊት […]

በዘጠኙ ፓርቲዎች ትብብር ላይ የተወሰደውን እርምጃ ተከትሎ አንድነት ፓርቲ መግለጫ አወጣ፡፡ አንድነት በመግለጫው በትብብሩ አመራሮችና አባላት ላይ የተወሰደውን እርምጃ አውግዟል፡፡ ፓርቲው በዘጠኙ ፓርቲዎች ትብብር አመራሮችና አባላት ላይ የተወሰደውን ህገ-ወጥ እርምጃ ተከትሎ አስፈላጊውን መረጃዎች ካሰባሰበ በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡ ሙሉውን መግለጫ ከታች ተመልከቱ፡፡ በዘጠኙ ፓርቲዎች ሰልፍ ላይ የተወሰደውን ህገወጥ እርምጃ እናወግዛለን! አምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት ሰላማዊ […]

በሰላማዊ ሰልፉ ታፍሰው አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ (ሶስተኛ) ታስረው የሚገኙት የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር አመራሮች፣ አባላትና የሰልፉ ተሳታፊዎች ‹‹ህገ መንግስቱን በኃይል በመናድ›› ወንጀል ተከሰው 14 ቀን ተቀጠረባቸው፡፡ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት፣ አቶ አርጫፎ ኤርዳሎ፣ አለሳ መንገሻና ሌሎቹም የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር አመራሮች፣ አባላትና በሰልፉ ላይ የታፈሱ ዜጎች አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው ለታህሳስ 13/2007 ዓ.ም ተቀጥሮባቸዋል፡፡ ችሎቱ በዝግ የታየ […]

የአንድ ‹‹ህዝብ›› የእምነት፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ… መብቱ በግለሰብ ደረጃ ካልተጠበቀለት በስተቀር የ‹‹ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ…›› መብት ሊጠበቅ አይችልም፡፡ ችግሩ የ‹‹ብሄርና›› ሌሎች ማንነቶችን የሚጠቀሙ የፖለቲካ ቡድኖች ከግለሰብ ማንነት ይልቅ ጥቅል ማንነትን የሚያስቀድሙት ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ መሆኑ ነው፡፡ ከፊሉን በእምነቱ፣ ከፊሉን በኢኮኖሚው፣ ከፊሉን እናከብርልሃለን በሚሉት ቋንቋው፣ ከፊሉን በነጻነቱ…. እያሉ ግን ሁሉንም ይጨቁኑታል፡፡ ሁሉንም ይጎዱታል፡፡ መስፈርቱ በብሄር ሳይሆን በግለሰብ ቢሆን […]

በዘመነ መሳፍንት ወቅት፤ ለስሙ በዙፋኑ ላይ የዘር ግንድ ያለውን ሰው አስቀምጠው፤ ራሳቸውን እንደራሴ በመሾም፤ ጉልበተኞች ያደረጉት ሁሉ ግልጽ ነው። የውጭ ሀገር መንግሥታት ደግሞ በወኪሎቻቸው አማካኝነት ፀረ-ኢትዮጵያ ሚና ተጫወቱ። በደንብ በዝርዝር የሚያስረዳ መዝገብ ግን አላገኘሁም። ከዚህም ከዚያም ለቃቅሜ የተገነዘብኩትን ይዣለሁ። የእስክንድርያውን የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን በመጠቀም፤ ግብፅና ቱርክ በአንድ በኩል፣ በፖርቹጋሎች የተጀመረውን ግንኙነት በመጠቀም፤ የካቶሊክ ቤተክርስትያን በሌላ በኩል፣ […]

በአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት እየተካሔደ በሚገኘው የክርክር መድረክ ላይ ተሳታፊ የሆኑ የአንድነት ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በትላንትናው እለት የ9ኙ ፓርቲዎች ህብረት የጠራውን የ24 ሰዓት ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ የመንግስት ሀይሎች የወሰዱትን ኢ-ህገመንግስታዊ እርምጃ አጥብቀው እንደሚያወግዙ ገልፀዋል፡፡ በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የወጣቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ‹‹ምርጫ 2007 የኢህአዴግ መጨረሻ ወይስ የመጨረሻው መጀሪያ››በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ክርክር በትዝጋጅው ፕሮግራም መሰረት ተካሂዱዋል፡፡ […]

9ኙ ፓርቲዎች በጠሩት ሰላማዊ ሰልፍ በፓርቲ አመራሮች እና የሰልፉ ተሳታፊዎች በፌዴራል ፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ የደረሰባቸው ሲሆን በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የታፈሱትና ጨርቆስ ፖፖላሬ እስር ቤት ታስረው የነበሩት የፓርቲ አመራሮች፣ አባላትና የሰላማዊ ሰልፍ ተሳታፊዎች ማዕካለዊ ጥግ ወደሚገኘውና በተለምዶ ሶስተኛ ተብሎ ወደሚጠራው እስር ቤት መዛወራቸው ታወቀ፡፡ ታሳሪዎቹ ከጨርቆስ ፖሊስ ጣቢያ ወደ ሶስተኛ የተዛወሩት ከምሽቱ አንድ ሰዓት በኋላ ሲሆን […]

ወደ አውሮፓ የሚያስገባውን ቪዛ እና ትኬት ይዞ ከወዳጆቹ ጋር ጉዞውን ለመጀመር ወደ ቦሌ አለም-ዓቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ አቀና። እዚያው እንደደረሰ የተለመደው የፓስፖርትና ትኬት ቁጥጥር ተደረገ። ሁሉም የተሟላ ነበር። ቴዲ ሸኚዎቹን ተሰናብቶ ወደ ውስጥ ጋባ። እለተ ሐሙስ፣ ህዳር 28 ቀን 2007 ዓ.ም.። የአውሮፓው ኮንሰርት በፊንላንድ፣ ሄልሲንኪ ቅዳሜ፤ ህዳር 28 ቀን ይጀምራል። ፊንላንድና አካባቢው ያሉ የቴዲ አድናቂዎች ትኬት […]

* ስለ ሰራተኞች መብት ጥበቃ መነሳቱ አልተዘገበም * በተወያይ ኤጀንሲዎች በኩል ግን ረቂቁ ውዝግብ አስነስቷል * ከዚህ ቀደም ያለ በኮንትራት ለተበተኑትስ ዜጎችስ ምን ታስቧል ? አዲሱን መረጃ ያገኘሁት ሃገር ቤት ከሚታተመው ከአድማስ ጋዜጣ ላይ ነው ፣ እንዲህ ይላል ” ወደ አረብ አገራት የሚሄዱ ሰራተኞች ላይ የሚደርሰውን ችግርና እንግልት ለማስቀረት በሚል ከአንድ ዓመት በላይ ተቋርጦ የቆየውን […]