አንድነቶችን ማሰሩ ቀጥሏል፣ ተስፋሁን አለምነህ መፈታቱን ማረጋግገጥ አልተቻለም

ቅዳሜ ትብብሩ በጠራው ሰልፍ ለማገዝ ወደ ሰማያዊ ቢሮ ሄዶ ነበር። አግዞ ከዚያ ሲመለስ ይታሰራል። የመኢአድ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ የነበረው ወጣት ተስፋሁን አለምነህ ነው። የሰማያዊ አመራር አባላት በሙሉ ሲፈቱ አቶ ተስፋሁን ስለመፈታቱ የደረሰን ምንም አይነት መረጃ የለም።

ሌላው ሕወሃቶች በአንድ በኩል የሰማያዊ አባላትን በመፍታታትቸው ምናልባት ልቦኖ መግዛት ጀመረው ይሆን እያሉ አንዳንዶች ማሰብ በጀመሩ ሰዓታት ሳይሞላ ፣ የአንድነት አባላት ደግሞ መታሰር ጀምረዋል። በቦረና ዞን ገላን ወረዳ የአንድነት አባላት እየታሰሩ ንነው። ታሣሪዎቹ አቶ በድሉ መንግስቱ በቦረና ዞን ገላን ወረዳ ሰብሳቢ፣ አቶ ቆንጨሪ ሳፋይ አባል፣ አቶ ንጉሴ ገልገሎ አባል፣ አቶ ብርሃኑ ሳፋይ አባል ሲሆኑ፤ ሰብሳቢው አቶ በድሉ መንግስቱ የታሰሩት የመንግስትን ስም አላግባብ አጥፍተሀል ተብለው ነው።

ብዙ ሰው ቦረና ሲባል የት እንደሆነ ላያወቅ ይችላል። የቦረና ከኦሮሚያ ዞኖች መካከል አንዲ ሲሆን ከጎጂ ዞን በታች በኬንያ ድንበር ላይ (ሞያሌ) የሚገኝ ዞን ነው።10847802_10205289035976174_4574284799120465000_n