አንድነት ጠቅላላ ጉባኤውን በድል አጠናቀቀ!

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የጠራው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ እጅግ ደማቅ በሆነ ሁኔታ ያካሄደ ሲሆን፤ በጠቅላላ ጉባኤው ሶስት ዋና ዋና ተግባራት ተካሄደዋል፤ የመጀመሪው አጀንዳ ኢር ግዛቸው በራሳቸው ፍቃድ ስልጣናቸውን በለቀቁ ጊዜ የአንድነት ብሄራዊ ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤው በሰጠው ስልጣን መሰረት አዲስ የፓርቲው ፕሬዚደንት መምረጡ ጉባኤው ተቀብሎ ያፀደቀ ሲሆን፤ በዚህ መሰረትም አቶ በላይ ፍቃዱ የፓርቲው ፕሬዚደንት ሆነው እንዲቀጥሉ ወስነዋል። ሁለተኛው አጀንዳ ደግሞ በምርጫ ቦርድ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ቁጥር በህገ ደንቡ ላይ አልተቀመጠም በሚል ሽፋን በፓርቲው ላይ እየፈጠረ የሚገኘውን እንቅፋት ለማቅለል ያግዝ ዘንድ የህገ ደንብ ማሻሽያ አደርገዋል። የመጨረሻው አጀንዳ በተጉዋደሉ የኦዲትና ኢንስፐክሽን አባላት የማሟያ ምርጫ አድርገዋል። እነዚህ ታህሳስ 3 ተከናወኑ ሲሆን በነጋታው ታህሳስ 4 ደግሞ በቀጣዩ ምርጫ ፓርቲው አሸናፊ ሆኖ አንዲወጣ የሚያደርጉት የምርጫ እስትራቴጂዎች ላይ ሰፊ ስልጠና ተስጠተዋል።
በመጨረሻም የጉባኤውን መዝጊያ በማስመልከት የተለያዩ የሙዚቂ ዝግጅቶች ቀርበዋል፡፡udj_udj14

udj_udj13

udj_udj12

udj_udj9

udj_udj8

udj_udj7

udj_udj6

udj_udj5

udj_udj4

udj_udj3

udj_udj2

udj_udj1

10846215_387439034753787_52815730277175743_n

10420285_387439031420454_8297638254245030052_n