አንድነት አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ዛሬ አርብ (03/04/07) ጠቅላላ ጉባኤውን በደማቅ ሁኔታ ጀምሮአል፡፡
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለዛሬ አርብ (03/04/07) የጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ በደማቅ ሁኔታ ተጀምሯል። ጠቅላላ ጉባኤተኛው ወደ አዳራሹ የገባው ፓርቲው ያዘጋጀውን ነጭ ኮፍያ በአንድነት ያደረጉ ሲሆን የብሔራዊ ምክር ቤት አባላት አረንጓዴ ፤የአዲስ አበባ ምክር ቤት ቢጫ፤ የክልል ዞን ተወካዮች ቀይ ቲሸርቶችን በመልበስ ለጉባኤው ድምቀት ሰጥተውታል፡፡
የጉባኤ ጠሪ ኮሚቴው መድረኩን ተቀብሎ፤ አቶ ብሩ ብርመጂ ንግግር አድርገዋል፡ በመቀጠልም የአንድነት ብሄራዊ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አበበ አካሉ ንግግር ያደርጉ ሲሆን ለታሰሩት ጀግኖቻችን የህሊና ፀሎት ተደርጓል፡፡ በስብሰባው ላይ የልዩ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤው ሰብሳቢም አቶ አስራት ጣሴ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ለጉባኤው ተሳታፊዎች አቅርበዋል። ተያይዞ በደረስን ዚና ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣናቸውን በመልቀቃቸው ጉባኤው አመስግኗቸዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ጉባኤው በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ ሲሆን ዝርዝር መርጃዎችን እንደደረስን እናነንቀርባለን።

