የባህር ዳር ህዝብ አደባባይ ወጣ፤ ባህር ዳር በህዝባዊ ጥያቄዎች እየተናጠች ነው::
የባህዳር ነዋሪ በነቂስ በመውጣት በክልሉ ም/ቤት ፊት ለፊትና በአዲሱ ም/ቤት(ቀበሌ 10) መስቀል አደባባይ የቤተክርስያን የታቦት ማደሪያ ፣ ንብረትነቱም የቤተ-ክርስቲያን ነው ልትነጠቅ ወይም መንግስት እንደሚለው ለባለሀብት ሊሰጥ አይገባም በማለት ቁጣቸውን በማሰማት ላይ ናቸው፡፡ የባጃጅ ሾፌሮችም በየቦታው ትላክስና ጩኸት እያሰሙ ነው፡፡ የመስቀል አደባባይን መፍረስ በመቃወም በባህርዳር ከተማ የነበረው ሰልፍ ጥያቄውን አሰምቷል:: ሆኖም በአሁኑ ሰዓት በባህርዳር ከተማ በሕዝበ ክርስትያኑ የሀይማኖት ነፃነት ጥያቄ ይዘዉ በወጣ ህዝብ ላይ በተከፈተ ተኩስ እየታወከች እንደሆነ ከአካባቢው የሚመጡ መርጃዎች እየተሰሙ ነው!! ወጣቶች በተቃዉሞ እናቶችና አዛዉንቶች በእንባ ተቃዉሞአቸዉን እየገለጡ ይገኛሉ፡፡ ከቀበሌ 10 አባይ ማዶ ያለው መንገድ ተቃውሞውን በተቀላቀለው ህዝብ የተዘጋ ሲሆን ወደ ጎንደር የሚወስደው መንገድም መዘጋቱ ታውቋል፡፡ የቀበሌ 8፣ 10ና 11 ነዋሪዎች እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተቃውሞውን እየተቀላቀሉ ነው ተብሏል፡፡ የአፈ ጉባኤ ጽ/ቤት አካባቢም በርካታ ህዝብ የተገኘ ቢሆንም ርዕሰ መስተዳደሩን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናት የሉም እንደተባሉ ገልጸውልናል፡፡
የሰልፉን ፎቶዎች ይመልከቱት:
