የሚሊዮኖች ድምጽ – አንድነት ኢትዮጵያዊነት ነው – ደማቁ የአንድነት ጉባኤ

የአንድነት ጠቅላላ ጉባኤ እጅግ ደማቅ በመሆነ ሁኔታ እየተካሄደ ነው። የብሔራዊ ምክር ቤት አባላት አረንጓዴ ፤የአዲስ አበባ ምክር ቤት ቢጫ፤ የክልል ዞን ተወካዮች ቀይ ቲሸርቶችን በመልበስ ለጉባኤው ድምቀት ሰጥተውታል፡፡ udj_udj1

udj_udj2

udj_udj3

udj_udj4

udj_udj5

udj_udj6

udj_udj7

udj_udj8

udj_udj9

udj_udj12

udj_udj13

udj_udj14

ዛሬና ነገ በሚደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ምርጫ ቦርድ በድርጅቱ ደንብ ላይ የኮረም ቁጠር ይጠቀስ የሚል ጥያቄ በመቅረቡ፣ የቀረበው ጥያቄ ከሕግ ውጭ ቢሆንም ( ደርጅቶች የሚተዳደሩበትን ደንብ ምን መልክ መኖር እንዳለበት የሚወስኑት፣ እነርሱ እንጂ ምርጫ ቦርድ ባለመሆኑ) ፣ የደንብ ማሻሻያ የሚያደርግ ሲሆን፣ በዋናነት ግን በምርጫ ዘመቻው ዙሪያ ሰፊ ስልጠና እንደሚደረግም ታወቋል።

ከትግራይ፣ ከአፋር፣ ከቤኔሻንጉል፣ ከወላይታ፣ ከሲዳማ ፣ ከጉራጌ እያለ በደቡብ ካሉ በርካታ ዞኖች፣ከጎንደር፣ ከጎጃም ፣ ከወሎ፣ ከወለጋ፣ ከአርሲ፣ ከሐረርጌ.. ከመላው የአገሪቷ ክፍሎች ኢትዮጵያዉያን ለለዉጥ፣ ለነጻነት ተሰባስበዋል። ጉራጌው፣ ትግሬው፣ ኦሮሞው፣ ወላያታው፣ አፋሩ ፣ ቅልቅሉ በስብእናዉና በኢትዮጵያዊነቱ፣ በአንድ ድንኳን ሥር ስለሃገሩ ሁኔታ ተሰባስቦ እየተመካከረ ነው።