በቦረና ዞን ገላን ወረዳ የአንድነት አባላት ታሰሩ – አንድነት
በቦረና ዞን ገላን ወረዳ የአንድነት አባላት መታሰራቸውን ከአከባቢው በደረሰን ሪፖርት አረጋግጠናል። የታሳሪዎቹ ስም ዝርዝር
አቶ በድሉ መንግስቱ በቦረና ዞን ገላን ወረዳ ሰብሳቢ፣
አቶ ቆንጨሪ ሳፋይ አባል
አቶ ንጉሴ ገልገሎ አባል
አቶ ብርሃኑ ሳፋይ አባል ሲሆኑ፤ ሰብሳቢው አቶ በድሉ መንግስቱ የታሰሩት የመንግስትን ስም አላግባብ አጥፍተሀል ተብለው ነው።
በተያያዘ ዜና በምስራቅ አሩሲ የኦሆዴድ አባል፣ የጢዮ ወረዳ የሲቪል ሰርቢስ ምክትል ሀላፊና የወረዳው የካቢኔ አባል የሆኑት ወሮ ሰኣዳ አብድርሃማን የምስራቅ አሩሲ የምርጫ ቦርድ ምክትል ሀላፊው ሆነው መሾማቸውን ተረጋግጧል፤ ይሄ ዓይነቱ አሰራር ምርጫውን ለኢህአዴግ ልጁ ቀማኛ አባቱ ዳኛ እንዲሆንለት ታስቦ የተደረገ ህገወጥ ተግባር ነው እንላለን።
