የአንድነት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው ውሎ ሁለት አጀንዳዎችን አፀደቀ፡፡
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በጠራው ልዩ ጠቅላላ ጉባኤ ሁለት አጀንዳዎችን በመወያየት አፅድቋል፡፡ በመጀመሪያ አጀንዳነት የተነሳው የኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ ብሔራዊ ምክር ቤቱ የሰየመውን ፕሬዝደንት ተወያይቶ ያፀደቀ ሲሆን በሁለተኛ አጀንዳነት የተያዘው እና ምርጫ ቦርድ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ቁጥራችሁን አሳውቁኝ ባለው መሰረት የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ቁጥርን ወስኗል ፡፡ ጠቅላላ ጉባኤው በዛሬው ስብሰባ ከሁለቱ አጀንዳዎች በተጨማሪ በተጓደሉ የኦዲትና ኢንስፔክሽን አባላት ምክንያት የማሟያ ምርጫንም ማድረጉ ታውቋል፡፡የአንድነት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔ በነገው እለትም ቀጥሎ ይውላል፡፡













