የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ በሃገራችን ኢትዮጵያ አስተማማኝና ዘለቄታዊ ሠላም፣ እኩልነት፣ ፍትህና፣ የፖለቲካ መረጋጋት ይሰፍን ዘንድ ቀና ራዕይ አንግበው በተሰባሰቡ ወጣት ኢትዮጵያውያን የተመሰረተ፤ በሃገራችን ብቸኛው በወጣቶች የተገነባና የሚመራ ንቅናቄ ነው። ንቅናቄአችን…

The post ሠላማዊ ትግላችን ነፃነት እስኪታወጅ እኩልነት እስኪሰፍን ይቀጥላል! የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

ሰማያዊ ፓርቲ በባህር ዳር ከተማ የከፈተው ቢሮው በአከራይ ላይ በተፈጸመ ከፍተኛ ወከባና ማስፈራሪያ ምክንያት እንደተዘጋበት በስፍራው የፓርቲው አስተባባሪ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጸ፡፡ በባህር ዳር የፓርቲው አስተባባሪ አቶ አዲሱ ጌታነህ እንደገለጹት ቅርንጫፍ…

The post ሰማያዊ ፓርቲ ባህር ዳር ቅርንጫፍ ቢሮው እንደተዘጋበት አስታወቀ appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

አፈና በማናቸውም መልኩ በሰብዓውያን ላይ ሲፈፀም የፀያፍ ድርጊቶች ጊዜያዊ ማሰንበቻ እኩይ ተግባር ነው። ይህ ደሞ ለራሱ የመንግስትን ገጽታ በሰጠ ቡድን ሲከወን መጠኑ እጅግ ይከፋል፤ ይገዝፋልም…። የሚገለፀውም በተለያዩ ዓይነቶች የግፍ መሥፈርቶች…

The post አፋኞች የሚፈሩት የታፈነ ድምፅ በዓለም አደባባዮች ሲደመጥ appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

ነብሱን ይማረውና ነውጠኛው ቅንጅት በ1997ዓ.ም የማይናቅ የህዝብ ድምጽና ድጋፍ ያገኘው ከኢህአዴግ የተሻለ ብቃት ስለነበረው ወይም ያቀረበው የፖሊሲ አማራጭ ሳቢ ስለነበረ እንዳልሆነ ሁላችንም እናውቀዋለን፡፡ ወይም የህዝባችን ኑሮ ሊቀይር የሚችል የመነጠቀ ሐሳብ በማቅረብ አልነበረም፡፡ ጅብ በቀደደው ውሻ ይገባል እንደሚባለው የኢህአዴግ ንዝህላልነትና ቸልነትነት እንጂ! ይህን ያልኩት ያለምክንያት አይደለም፡፡ ኢህአዴግ ከቅንጅት ቡድን ጋር ለክርክር ሲቀርብ ማሰብ እና ማድረግ የነበረበት ብዙ ስትራተጂዎች ነበሩ፡፡ እንደምናስታውሰው ቅንጅቶች በነበረባቸው የብልጣ ብልጥነት (ተራ የአራዳነት) ስብእና በከፍተኛና በሚያስገርም ጥበብ የኢሀአዴግን ደካማ ጎን ተጠቅመውበታል፡፡ የኢህአዴግ ቸልተኝነት፣ በክርክር ታክቲክ በልጦ አለመገኘት እንዲሁም እዚህም እዛም ይታዩ የነበሩ የመልካም አስተዳደር እጦት ፣ የአፈጻጸም ግድፈቶች እና የልማት እጥረቶችን በሚሊዮን ግዜ በማጋነን ፣ ልብ የሚነኩ ቃላቶች በመደርደር የተወሰነ ህብረተሰብን በማሳመን ረገድ ቅንጅቶች ከፍተኛ ብልጫ አሳይተዋል፡፡ በኔ ግምት ይህን ሊያደርጉ የቻሉበት ዋናው ምክንያት 1ኛ የኢህአዴግ ጠንከር ላለ ፖለቲካዊ ክርክር በቂ ዝግጅት አለማድረግ እና የሰራውን ስራ በሚማርክ ቃለት እና በሚመጥን መልኩ መግለጽ አለመቻሉም ጭምር ነው፡፡ 2ኛ ደግሞ መቶ በመቶ በሚያስብል መልኩ አጀንዳው በኢህአዴግ የፖለቲካ መስመር ፣ ርእዮት ዓለምና ኢህአዴግ በሚመራው የመንግስት የፖሊሲ አፈጻጸም ዙርያ መሆኑ ነው፡፡ ታድያ ብልጣ ብልጦች የቅንጅት ተከራካሪዎች እነሱ ገምጋሚዎች ኢህአዴግዬ ደግሞ ተገምጋሚ ሆና መቅረብዋ ምን ያህል ለነሱ አመቺ ሜዳ እንደነበረ ማንም ሰው ሊስተው አይችልም፡፡ ቅንጅቶች ይህን ክፍተት በመጠቀም ኢህአዴግ የሰራውንና ያልሰራውን ስራ አፈር ድሜ አበሉት፡፡ ኢህአዴግ በትምህረት ፣ በልማት ፣ በጤና ፣ በድህነት ቅነሳ […]

የጎንደር ሕዝብ ካልደፈረሰ አይጥራም ማለት በሕወሓት ጁንታ የሚደረግበትን ጭቆና መከፋፈል እና የመስፋፋት ፖሊሲ በመቃወት ታጥቆ መነሳቱ ሲታወቅ ሕዝብን በመበደል የሚታወቅ አንድ የሚሊሻ ሃላፊ በጎንደር ቀበሌ 15 ውስጥ ሕዝቡ እርምጃ እንደወሰደበት…

The post ጎንደር ውጥረት ላይ ነች appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

አረጋሽ በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ – ህወሓት – ሲታገሉ ከቆዩት ነባር ታጋይ ሴቶች አንዷ ናት:: በትጥቅ ትግሉ ሂደት በነበራት ንቁ ተሳትፎ፣ ጀግንነትና የአመራር ብቃት መሰረት በየደረጃው ከተራ ተዋጊነት እስከ ማእከላይ…

The post በመቀሌ አንዱ ወረዳ የመድረክ ተወዳዳሪ – አረጋሽ አዳነ (በላይ ገሰስ) appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

መጋቢት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የጎንደር ከተማ የሚሊያሻዎች ሃላፊ ኮማንደር መጋቢት 11 ቀን 2015 ዓም ቀበሌ 15 ወይም ፋሲለደስ ትምህርት ቤት አካባቢ ከምሽቱ 2 ሰአት አካባቢ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድሏል። ገዳዮቹም መሳሪያውን ማርከው ከእነ ትጥቃቸው ወደ አርማጭሆ ጫካ መግባታቸው ታውቋል። የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊው ግንባሩ አካባቢ በጥይት የተመታ ሲሆን …

መጋቢት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞ መንግስት ወታደሮች የነበሩ ግለሰቦችን በማሳባሳብ በህወሃት አማካይነት የተመሰረተው የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ለ25ኛ ኣመት የምስረታ በዓሉን ያሰራውን የሰማእታት ሃውልት ቅዳሜ መጋቢት 12 ቀን 2007 ዓ.ም በጨለንቆ ከተማ ያስመርቃል። ህወሃት እንደ ኦነግ ካሉ ድርጅቶች ጋር ግንባር ለመፍጠር የነበረው ፍላጎት ከከሸፈ በሃላ በ1982 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዐርብ፡- እሰጥ አገባ፣ አፍሪካ በጋዜጦች፡ አጥቢያ ኮከብ (የማኅበረሰብ ጀግኖች)

ባለፈው እሁድ በአዲስ አበባ ከተማ ቁጥራቸው በሺ የሚቆጠሩ ሴቶች ሮጠዋል። ከነዚህም ውስጥ 700 የሚሆኑት የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ናቸው። የሴቶችን ተሳትፎ እና መብት ለማበረታታት በየዓመቱ ስለሚካሄደው የሩጫ ውድድር በዛሬው የወጣቶች ዓለም እንመለከታለን።

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፣ ፓትርያርኩ ከሕግ አግባብ ውጭ ለሾሟቸው ዋና እና ምክትል ሥራ አስኪያጆች የምደባ ደብዳቤ እንደማይጽፉ በዛሬው የቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባ አስታውቀዋል፡፡ ቋሚ ሲኖዶሱ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ አስተያየታቸውን በጽሑፍ እንዲያቀርቡ አዝዟቸዋል፡፡ አሠራሩ፣ ምርጫው እና መመሪያው ተቀባይነት የሚኖረው ሥራ አስኪያጆቹ ‹‹በሀገረ ስብከቱ የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ተመርጠው ቀርበው ከጠቅላይ …

የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋምን አሠራር በተመለከተ ለተዘጋጀው ጉባኤ የቀረበ ባሕር ዳር የካቲት 3-5 ቀን 2007 ዓም የአማርኛ ቋንቋ ታሪካዊ ጉዞ የአማርኛ ቋንቋን ጉዞ በአጭሩ ለመመልከት እንድንችል፣ የዚህን ታላቅ…

The post የአማርኛ ቋንቋ ከየት ወዴት፤ ተግዳሮቶቹና መፍትሔዎቹ – የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋምን አሠራር በተመለከተ ለተዘጋጀው ጉባኤ የቀረበ appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋምን አሠራር በተመለከተ ለተዘጋጀው ጉባኤ የቀረበ
 ባሕር ዳር
 የካቲት 3-5 ቀን 2007 ዓም


የአማርኛ ቋንቋ ታሪካዊ ጉዞ
የአማርኛ ቋንቋን ጉዞ በአጭሩ ለመመልከት እንድንችል፣ የዚህን ታላቅ ጉባኤ ጊዜንም ላለመውሰድ በአምስት ምዕራፍ ማየቱ ይጠቅማል ባይ ነኝ፡፡ እነርሱም
1.    ከጥንት እስከ 13ኛው መክዘ
2.   ከ13ኛው መክዘ እስከ 16ኛው መክዘ
3.   ከ16ኛው መክዘ እስከ ዘመነ ቴዎድሮስ
4.   ከዘመነ ቴዎድሮስ ዘመነ ምኒሊክ
5.   ከዘመነ ምኒሊክ እስከ አሁን

 

 1.   ከጥንት እስከ 13ኛው መክዘ
አማርኛ በዚህ ዘመን እንዲህ በሚባል ሕዝብ መነገር ጀመረ ብሎ ለማስቀመጥ አስቸጋሪ መሆኑን ያጠኑት ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ አገኛኘቱን በተመለከተ እስካሁን ቦታ ይዘው የሚከራከሩ ሁለት ዓይነት አመለካከቶች አሉ፡፡ የመጀመሪያው፣ በሰፊው የሚነገረውና ለብዙ ዓመታት የቆየው አመለካከት አማርኛ ከሌሎች ቋንቋዎች ተቀይጦ ምናልባት በ4ኛው መክዘ አካባቢ ከአኩስም ወደ ደቡብ በመጡ ዘማቾችና አዝማቾች አማካኝነት የተፈጠረ(pidgin theory) ነው የሚል ሲሆን በዚህ መላ ምት መሠረት ከሰሜን ወደ ደቡብ እየተስፋፋ የመጣ፤ ከግእዝ ትንሽ ለየት ያለ ሴማዊ ቋንቋ በሚናገሩ አዝማቾችና የኩሽ፣ የኦሞና የዓባያዊ ቋንቋዎች በሚናገር ዘማች ሠራዊት አማካኝነት የተፈጠረ ነው፡፡
 አዝማችና ዘማች በአገዎች ምድር ሲቀመጡ ልዩ ልዩ ቋንቋ ይናገር የነበረው ዘማች የአዝማቾቹን ሴማዊ ቋንቋ መናገር ይጀምራል፡፡ ሲናገር ግን ከራሱ ቋንቋ ጋር እያስማማ ነበር፡፡ በዚህም የተነሣ የሴማዊ ቃላትን ከራሱ ቃላት እያመሳሰለና እያዳቀለ ይናገር ነበር፡፡ በዚህም የተነሣ የቃላቱ ቅርጽና የመዋቅሩ ሥርዓት ቀስ በቀስ እየተለወጠ መጣ፡፡ ሴማዊ ጠባዩን እየተወም ‹ኩሾ ኦማዊ› እየመሰለ መጣ፡፡ እየቆየም ራሱን የቻለ ቋንቋ ሆኖ በስፋት በሚነገርበት አካባቢ ስም ‹አማርኛ› ተባለ የሚለው ነው፡፡
የዚህን መላ ምት ዝርዝር የፈለገ የባየ ይማምን(2000) እና የቤንደርን(1983) ማንበብ ይጠቅመዋል፡፡
ሁለተኛው መላ ምት ከመጀመሪያው ጋር ሲነጻጸር  የቅርብ ዘመን ሲሆን አማርኛ ከአማርኛ በፊት ከነበረ የአርጎባ – አማርኛ እናት ቋንቋ በተለምዶ ከሚታወቅበት የጥንቱ አምሐራ አካባቢ በስተ ደቡብ የተገኘ ቋንቋ ነው የሚል ነው(proto Amharic- argoba, theory)፡፡ በዚህ መላ ምት መሠረት ስሙን በትክክል ዛሬ ለመጥራት ባንችልም ራሱን የቻለ አማርኛን የሚናገር ሕዝብ ነበረ፡፡ ይህ መላ ምት በኢትዮጵያ ታሪክ የተለመደ ትርክት የምንሰማውን የኢትዮ ሴማውያን ቋንቋ ተናጋሪዎችን የሰሜን – ደቡብ የፍልሰት አቅጣጫ በመቀየር ከደቡብ ወደ ሰሜን የሚያደርግ ነው፡፡ ለዚህም ዋና መከራከሪያው አብዛኞቹ የኢትዮ ሴማውያን ቋንቋ ቤተሰቦች የሚገኙት በደቡቡ ክፍል በመሆናቸው፣ ‹የሚሰደደው ጥቂቱ ነው› በሚለው መሠረተ ሐሳብ መሠረት የኢትዮ ሴማዊ ቋንቋዎች ከደቡብ ወደ ሰሜን የፈለሱ ናቸው ይላል፡፡ የአማርኛ እናት ቋንቋና ራሱ አማርኛም ኦሮምኛ በ16ኛው መክዘ እንዳደረገው ከደቡብ ወደ ሰሜን የተጓዘ ቋንቋ ነው ይላል፡፡ ይህንን መላ ምት በሚገባ ለማወቅ የግርማ አውግቸውን መጽሐፍ (The Origin of Amharic, 2009) እና የአየለ በከሪን (1997) መጻሕፍት መመልከቱ ይጠቅማል፡፡
እስከ 13ኛው መክዘ ያለው የአማርኛ ቋንቋ ታሪክ በሚገባ ሊታወቅ አልቻለም፡፡ በቂ መረጃዎችም አልተገኙም፡፡ በተለይ ከአርጎባ፣ ከሐረሪና ከዛይ ቋንቋዎች ጋር በጋራ የሚደረጉ የሥነ ልሳን ጥናቶች፣ ከዚህም ባሻገር ብዙ ጠባያቱን ከሚጋሩት የኩሽና የኦሞ ቋንቋዎች ጋር በማነጻጸር ቢጠና ዕውቀታችን ከዚህ የተሻለ ሊሆን የሚችልበት ዕድል አለው(ባየ፣ 2000፣ xviii & xix):: የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋምን የሚጠብቀው አንዱ ሥራም ይኼው ይመስለኛል፡፡
2.    ከ13ኛው እስከ 16ኛው መክዘ
ይህ ዘመን ከአማርኛ ቋንቋ ቀደምት ዘመናት መካከል የተሻሉ መረጃዎች የተገኙበት ዘመን ነው፡፡ በአንድ በኩል አማርኛ  በዛጉዌና እንደ ገና በመጣው ‹ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት› ውስጥ ልሳነ መንግሥት ሆኖ የወጣበት( ባየ፣ 2000፣ xvii-xviiiGirma, 2009,210) ሲሆን በሌላ በኩልም በዋናነት ይነገርበት የነበረው አካባቢና የሚነገርበት ደረጃም  በውል ተለይቶ መታወቅ የጀመረበት ዘመንም ነው፡፡ የዛግዌ ነገሥታት የአኩስም መንግሥት ጠንካራ መሠረት ከሆነው የዛሬው ኤርትራና ትግራይ አካባቢ ይልቅ ደቡቡን በመጠቀም ጠንካራ አጋርና መሠረት ለማግኘት ባደረገው ጥረት አማርኛ ተናጋሪዎቹ የመንግሥቱን ቦታ እያገኙ ሲመጡ አማርኛም ልሳነ ንጉሥ መሆን ጀመረ፡፡ ይህም በንጉሥ ላሊበላ ዘመን መሆኑ ይታመናል (Sergew,1972,278):: በነገራችን ላይ የኢትዮጵያ ነገሥታት ( ከሸዋ ወደ ጎንደር ከመጣው ከሠርፀ ድንግል በቀር፣) አዳዲስ ሥርወ መንግሥት ሲመሠርቱ ከሰሜኑ እየራቁ ወደ ደቡብ ነው የሚመጡት፡፡ ዛግዌ ላስታን ይዞ ወሎን በጌምድርና ጎጃምን፣ ይኩኖ አምላክ ሸዋን ይዞ ዳሞትን፣ ምኒሊክ ሸዋን ይዞ ደቡብ፣ ምዕራብና ምሥራቅን ነው ደጀን ያደረጉት፡፡ ይኼም የቀድሞው ሥርወ መንግሥት ከነበረው ጠንካራ መሠረት ለቅቆ ሌላ ጠንካራ መሠረት ለመፍጠር ነው፡፡  
በዐፄ ይኩኖ አምላክ ጊዜ በጥበበ እድ ሥራቸው የበለጸጉትን የጋፋት ሕዝቦችን ድጋፍ አግኝቶ የዛግዌን ነገሥታት ድል ሲነሣና ከዛግዌ ነገሥታት ዋና መሠረት ላስታ መንግሥቱን የጋፋቶች ዋና ቦታ ወደ ሆነው ሸዋ ሲያዛውር ለአማርኛ የበለጠ ዕድል ተፈጠረለት፡፡ ቋንቋውም ይበልጥ ከኦሞ ኩሽቲክ ቋንቋዎች ጋር ለመገናኘትና ለመወራረስ በቃ፡፡
ምንም እንኳን አማርኛ የግእዝን የሥነ ጽሑፍና የትምህርት ቋንቋነት ባይረከብም፤ የቤተ መንግሥቱ የፕሮቶኮል ቋንቋ ባይሆንም የዐፄ ዓምደ ጽዮን(1314-1344)፣ የዐፄ ዳዊት(1375-1404)፣ የዐፄ ይስሐቅ(1413-1430)፣ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ(1434-1468)ና ዐፄ ገላውዴዎስ(1540-1559) ወታደሮች የዘፈኗቸውና ‹የወታደሮች ዘፈኖች› የሚባሉትን ግጥሞች ስናይ አማርኛ በመካከለኛው ዘመን ይበልጥ እየዳበረ መምጣቱን ያሳያል፡፡ በዚህ ጊዜ በብዙ የቋንቋው ጥናት ሊቃውንት ግምት ውስጥ የማይገባውና ለአማርኛ ደቡባዊ ዕድገት የማይናቅ አስተዋጽዖ ያደረገው የሀገራዊ ትምህርቱ ማዕከል ወደ ደቡብ እየተቀየረ መምጣት ነው፡፡
 እስከ ቅድመ 12ኛው መክዘ ድረስ የሀገራዊ ትምህርት ማዕከላት የሆኑት ‹ሰሜን ሴማዊ› ቋንቋዎች የሚነገሩባቸው ትግራይና ኤርትራ ነበረ፡፡ አብዛኞቹ ገዳማትና አድባራት፣ ምሁራንና ሊቃውንት የነበሩት እዚያ ነው፡፡ መጻሕፍት ይጻፉና ይተረጎሙ የነበረውም እዚያው ነው፡፡
የአኩስም ዘመን በ8ኛው መክዘ አካባቢ ሲዳከም ከምእተ ዓመታት በኋላ አቡነ ኢየሱስ ሞአ አምሐራ እየተባለ ይጠራ በነበረው አካባቢ የሐይቅ እስጢፋኖስን ትምህርት ቤት በ1243 ዓም አካባቢ ሲጀምሩ የትምህርት ማዕከሉ ወደ ሀገረ አምሐራ መጣ፡፡ በዚህም የተነሣ ሐይቅን ተከትሎ ወለቃ ሌላው የትምህርት ማዕከል ሆነ፡፡ ወለቃ – ሐይቅም ደቡቡን ከሰሜን የሚገናኝ የትምህርትና የባሕል ድልድይ ሆነ፡፡ የ13፣ 14ና 15ኛው መክዘ ቅዱሳን ገድላትን ስንመለከት ይህን ይገልጡልናል፡፡ ይህ መሥመር ደግሞ አማርኛ የሚናገር ማኅበረሰብ የነበረበት በመሆኑ አማርኛ ቋንቋ ይበልጥ እንዲያድግ ረድቷል፡፡ ግእዝ ላዕላዩን ቦታ ቢይዝም ግእዝን በአማርኛ መማርም አንደኛው መንገድ ነበር፡፡  
በ13ና 14ኛው መክዘ በበጌምድር፣ በጎጃም፣ ሐረርጌና በደቡብ የተደረጉትን የክርስትና ማስፋፋቶችና የገዳማትና ትምህርት ቤቶች አተካከል ስንመለከት የአርጎባን፣ የጋፋትን፣ የዛይን፣ የሐረሪንና ሌሎች ሴማውያን ቋንቋዎችን ዱካ ተከትሎ እናገኘዋለን፡፡ የዚህ ዝምድና ጉዳይ ይበልጥ ሊጠና የሚገባ ይመስለኛል፡፡ በ14ኛውና በ15ኛው መክዘ ደብረ ሊባኖስና ከገዳሙ ጋር በተተያያዘ ታሪክ የተመሠረቱት የሸዋ፣ የጎጃም፣ የጎንደርና የወሎ አካባቢዎች የአማርኛ ቋንቋ ዋና መነገሪያዎች ሆነው እናገኛለን፡፡ የመጀመሪያዎቹን የአማርኛ ጽሑፎችንም የምናገኘው በዚህ አካባቢ ነው፡፡ በተለይ እነዚህ የትምህርትና የገዳማዊ ሕይወት ማዕከላት ከአርጎባ፣ ከዳሞትና ከጋፋት ሕዝቦች ጋር የነበራቸው ግንኙነት እንደገና ማጥናቱ የቋንቋው ዕድገት ከትምህርት ማዕከላትና ከሌሎች ሴማውያን ቋንቋዎች ጋር ያለውን ትግግዝ ያሳየናል፡፡ በዚህ ረገድ ታደሰ ታምራት በጋፋት ላይ የሠሩት ምሳሌ የሚሆን ነው (Taddesse Tamrat, 1988)፡፡
3.  ከ16ኛው መክዘ እስከ ዘመነ ቴዎድሮስ
በ16ኛው መክዘ አካባቢ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የካቶሊክ ሚስዮናውያን ከኦርቶዶክስ ሊቃውንት ጋር የነበራቸው ክርክር አማርኛ ቋንቋን በሁለት መንገድ ጠቅሞታል፡፡ በአንድ በኩል ሚስዮናውያኑ ከነባሩ ግእዝ ይልቅ አማርኛ ቋንቋን ለሃይማኖት ትምህርት ማስተማሪያነት ተጠቀሙበት(አምሳሉ አክሊሉ፣ 1975)፡፡ በዚህም አማርኛ የማስተማሪያ ቋንቋ ሆነ፡፡ ይህንን ተከትሎም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትም በአማርኛ ማስተማር ጀመሩ፡፡ ይኼ ለሕዝቡ በአማርኛ ማስተማር አድጎና ዳብሮ በኋላ ላይ ወደ ትምህርት ማዕከላት በመግባት ጎንደር ላይ አንድምታ ትርጓሜው ንባቡ በግእዝ ትርጓሜው በአማርኛ እንዲሆን ያስቻለውም ይኼው ሂደት ነበር፡፡
 በሌላም በኩል ሚስዮናውያን መልእክቶቻቸውን በአማርኛ ቋንቋ እየጻፉ በማስተላለፋቸው ነባር ሊቃውንትም በአማርኛ ቋንቋ መልስ መስጠት ጀመሩ፡፡ ይኼ ሂደትም አማርኛን የሃይማኖት ትምህርት መጻፊያ ቋንቋ እንዲሆን አስቻለው፡፡ በተለይም ፓኤዝ ብዙ የካቶሊክን እምነት የሚገልጡ መጻሕፍት ወደ አማርኛ እንዲተረጎሙ አደረገ (The missionary Factor, Merid Wolde Aregay, 47, 1996)፡፡ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትም ለዚህ አዲስ እንቅስቃሴ መጻሕፍትን ከግእዝ በመተርጎምና በአማርኛ አዳዲስ መጻሕፍትን በመጻፍ መልስ ሰጡ፡፡ እነ አንቀጸ አሚን፣ ጠቢበ ጠቢባን፣ ሥነ ፍጥረት፣ ምሥጢረ ጽጌያት ከግእዝ ወደ አማርኛ የተተረጎሙት በዚህ ዘመን ነበር ((Nostnitisn, 2003, 238)::  እነ ‹ነገረ ሃይማኖት›ና ‹ትምህርተ ሃይማኖት›ም ተዘጋጁ(Getachew Haile, 1980)፡፡ በጀርመን ሚሲዮናውያን አማካኝነት የዮሐንስ ወንጌል ወደ አማርኛ ተተርጉሞ በ1647 ታተመ (አምሳሉ አክሊሉ፣ 1976)፡፡ ሉዶልፍም የአማርኛ ሰዋስውን በ1698 አሳተመ፡፡ ከ16ኛው መክዘ ወዲህም በኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ዘንድ የአማርኛ ሰዋስውን መጻፍ ተጀመረ(Getachew Haile, 1970)::
ምንም እንኳን የቃል መረጃዎችና አንዳንድ መዛግብት (EMML 2117) የአማርኛ የአንድምታ ትርጓሜ ቀደም ያለ ታሪክ እንዳለው ቢገልጡም ንባብ በግእዝ፣ ትርጓሜ በአማርኛ ሆኖ ይበልጥ መሰጠት የጀመረው ግን በ17ኛው መክዘ እና በ18ኛው መክዘ በጎንደር ነው፡፡   
ከዚህም በተጨማሪ ምንም እንኳን ግእዝ የትምህርትና የሥነ ጽሑፍ ቋንቋነቱን እንደጠበቀ ቢሆን፣ በብራና መጻሕፍት ላይ አማርኛና ግእዝ ጎን ለጎን መታየት የጀመሩት ከ17ኛው መክዘ በኋላ ነው፡፡ ግእዝ ዋናውን የጽሑፍ ቦታ (ገድሉና፣ ዜና መዋዕሉን፣ ጸሎቱን፣ ወዘተ) ሲይዝ አማርኛ ደግሞ የዕለት ተዕለት ማኅበራዊ ኑሮውን ቦታ ያዘ፡፡ በጎንደር ዙሪያ አድባራት የምናገኛቸው የ17ኛው፣ 18ኛውና ከዚያ በኋላ ያሉት መጻሕፍት በኅዳጋቸው የሚጽፉት የውርስ፣ የርስት፣ የሽያጭና ግዥ፣የውልደት፣ መዛግብት በአማርኛ ቋንቋ የሚጻፉ ናቸው፡፡ ይህም አማርኛ ከግእዝ ቀጥሎ የጽሑፍ ቋንቋነቱ እያደገና በቤተ ክህነቱና በቤተ መንግሥቱ ጸሐፍትም ዘንድ ተቀባይነት እያገኘ መምጣቱን ያሳየናል፡፡ በዘመነ መሳፍንት የነበሩት እነ ራስ ዓሊ፣ ደጃች ውቤ፣ ደጃች ጎሹ፣ ይጻጻፉ የነበረው በአማርኛ እንደነበረ ዛሬ ለዘር ተርፈው ያገኘናቸው ደብደቤዎቻቸው ያሳዩናል(Rubenson, 1987)
የዐፄ ቴዎድሮስ ወደ ሥልጣን መምጣት ለአማርኛ ቋንቋ ዕድገት አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል፡፡ በአንድ በኩል ዜና መዋዕላቸው በአማርኛ እንዲጻፍ ማድረጋቸው ግእዝ ይዞት የነበረውን አንድ የሥነ ጽሑፍ መንገድ አማርኛ እንዲረከበው አደረጉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የቤተ መንግሥቱን የሥራ ግንኙነት በንጉሥ ደረጃ በአማርኛ መጻፍ መጀመራቸው ግእዝ የፕሮቶኮል ቋንቋነቱን ለአማርኛ እንዲያስረክብ አደረገው፡፡ (የዐፄ ቴዎድሮስ ደብዳቤዎች Sven Rubenson, Acta Aethiopica, vol. II)በርግጥ በዚህ ጉዳይ ላይ የሸዋው ንጉሥ ሣሕለ ሥላሴም በአማርኛ የመንግሥቱን የመጻጻፍ ሥራ በመሥራት ታሪኩን ይጋራሉ፡፡ የደብተራ ዘነብ መጽሐፈ ጨዋታ ሥጋዊ ወመንፈሳዊም የዚህ ዘመን ፍሬ ነው፡፡ ደብተራ ዘነብ የጻፉት የቴዎድሮስ ታሪክ፣ የኢዘንበርግ የዓለም ታሪክ(1842) እና የአማርኛ የጂኦግራፊ መጽሐፍ (1842) የዚህ ዘመን ማስታወሻዎች ናቸው፡፡ የእንግሊዝ የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበርም በ1842 የአርባዕቱን ወንጌል የግእዝና አማርኛ እትም አሳተመ (Pankhurst, 1976,3110)::
4. ከዘመነ ቴዎድሮስ እስከ ዘመነ ምኒሊክ
ዐፄ ዮሐንስ ዐፄ ቴዎድሮስ የጀመሩትን፣ ንጉሥ ሣሕለ ሥላሴ ቀደም የበረቱበትን፣ የቤተ መንግሥቱን ሥራ በአማርኛ ቋንቋ ማከናወንን አጠንክረው ቀጠሉበት፡፡ የዐፄ ዮሐንስ ደብዳቤዎቻቸው በአማርኛ ይጻፉ ነበር፡፡ (Rubenson, 2000)
አማርኛ ይበልጥ የመስፋፋትና የማደግ ዕድሉን ያገኘው በዐፄ ምኒሊክ ዘመን ነው፡፡ ዐፄ ምኒሊክ እንደ ቴዎድሮስና ዮሐንስ ሁሉ አማርኛን የቤተ መንግሥቱ የሥራ ቋንቋ አድርገውታል፡፡ ይህንንም የዐፄ ምኒሊክን ዐዋጆች (ጳውሎስ ኞኞ፣ ዳግማዊ ዐጤ ምኒሊክ፣1984) ደብዳቤዎቻቸውንም (ጳውሎስ ኞኞ፣ የምኒሊክ ደብዳቤዎች፣2003) መመልከቱ ጠቃሚ ነው፡፡ ይህ ዘመን ለአማርኛ ሦስት ዕድሎችን አምጥቷል፡፡ 
የመጀመሪያውየዐፄ ምኒሊክ የመንግሥት ሥልጣን ወደ ደቡብ፣ ምዕራብና ምሥራቅ መስፋፋቱ አማርኛ በእነዚህ አካባቢዎች ይበልጥ እንዲስፋፋ ረድቶታል፡፡ አማርኛ በእነዚህ አካባቢዎች ቀድሞ ከነበረበት ቦታ ላቅ ባለ ሁኔታ መስፋፋት ብቻ ሳይሆን ከእነዚህ አካባቢዎችም ብዙ ጠባዮችን እንዲወስድ ሆኗል፡፡ ሁለተኛው ዕድል አማርኛ የጋዜጣ፣ የሥነ ጽሑፍና የፍርድ ቋንቋ መሆኑ ነው፡፡ አእምሮ ጋዜጣ የታተመው በአማርኛ ነው፡፡ ጦቢያ ልቦለድ የተጻፈው በአማርኛ ነው(1908)፤ የምኒሊክ ዐዋጆችና የዘመኑ ፍርዶች የሚሰጡትና የሚጻፉት በአማርኛ ነው፡፡ ሦስተኛውዕድል ደግሞ አማርኛ በትምህርት ደረጃ መሰጠት መጀመሩ ነው፡፡ በዐፄ ምኒሊክ ዘመን በተከፈተው የዳግማዊ ምኒሊክ ትምህርት ቤት አማርኛ በትምህርትነት መሰጠት ጀመረ፡፡ ይኼም ለአማርኛ ሰዋስውና ሥርዓተ ጽሕፈት ማደግ አስተዋጽዖ አድርጓል፡፡ በርግጥ በዚህ ረገድ ሚሲዮናውያን ከምኒሊክ ዘመን ቀደም ብለው የመሠረቱን ድንጋይ ጥለዋል፡፡ ትምህርት ቤት በከፈቱባቸው ቦታዎች ሁሉ የአማርኛ ቋንቋን ያስተምሩ ነበር፡፡ ለምሳሌ ላዛሪስቶች በ1870ና 80ዎቹ በከረንና አካባቢው በከፈቷቸው ትምህርት ቤቶች አማርኛ ማንበብና መጻፍ ያስተምሩ ነበር (Pankhurst, 1976,314)::
5. ከዘመነ ምኒሊክ እስከ አሁን
አማርኛ ከዐፄ ምኒሊክ ዘመን በኋላ የመንግሥት የሥራ ቋንቋ፣ ብሔራዊ ቋንቋ፣ የሚዲያና የኅትመት ቋንቋ፣ የሥነ ጽሑፍና የማስተማሪያ ቋንቋ ሆኗል፡፡ ከዐረብኛ ቀጥሎ በስፋት የሚነገር ሴማዊ ቋንቋ የሆነው አማርኛ (Girma, 2009, 2) በአሁኑ ዘመን ከ80 በመቶ በላይ በሚሆነው ኢትዮጵያዊ ዘንድ የመጀመሪያ ወይም ሁለተኛ ቋንቋ ሆኖ ይነገራል (Ibid; Meyer and Richter, 40):: የአማራ፣ የደቡብ፣ የጋምቤላና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች፣ የአዲስ አበባና የድሬዳዋ መስተዳድሮች የሥራ ቋንቋ ነው፡፡ በእሥራኤል ከ80 ሺ በላይ ተናጋሪዎች አሉት፡፡ በአሜሪካ፣ በአውሮፓ፣ በእስያና በአፍሪካ የሚገኙ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ይናገሩታል፡፡ በዋሽንግተን ዲሲ ከተናጋሪው መብዛት የተነሣ የከተማው መንግሥት እንደ አንድ የመሥሪያ ቋንቋ ተቀብሎታል፡
ተግዳሮቶቹና የመፍትሔ ሐሳቦች
1.     ተቋማዊ ባለቤት የሌለው መሆኑ
የአማርኛ ቋንቋን የሚያጠና፣ ደረጃዎችን የሚያወጣ፣ አዳዲስ ቃላትን የሚመዘግብ፣ ስያሜ ቃላትን የሚያዘጋጅ እኔ ባይ ተቋም የለውም፡፡ ግእዝን በዚህ ረገድ የጠቀመው ሁለት ነገር ነው፡፡ በአንድ በኩል እኔ ባይ ተቋም ቤተ ክህነት አለቺው፡፡ በሌላም በኩል ደግሞ በትምህርትነት ከጥንት ጀምሮ ይሰጣል፡፡ እኔ ባይ ተቋም መኖሩ ዕውቀቱ እንዲከማች፣ እንዲጠበቅና እንዲዳብር አድርጎታል፡፡ በትምህርትነት መሰጠቱ ደግሞ ሕግና ሥርዓቱ የታወቀና የተረዳ እንዲሆን፣ ደረጃውና መልኩ በተግባቦት ደረጃ እንዲታወቅ ረድቶታል፡፡
ለእንግሊዝኛ ኦክስፎርድና ካምብሪጅ በእንግሊዝ፣ ሐርቫርድ በአሜሪካ የዋሉለትን ውለታ ለአማርኛ በኢትዮጵያ ውስጥ  የሚውልለት ተቋም የለውም፡፡ ሲቋቋም ከሌሎች ጋር ተደርቦ ወይም ‹የኢትዮጵያ ቋንቋዎች› በሚል ተከብቦ ነው፡፡ የመዝገበ ቃላት ዝግጅቱን እንኳን ስናየው በየጊዜው የሚጨምር፣ የሚሻሻልና ቅደም ተከተል (Series) ያለው አይደለም፡፡ የቋንቋ አካዳሚዎችም አንዴ አንድ ሥራ ይሠራሉ ከዚያ ያቆማሉ፡፡ በየጊዜው የሚፈጠሩትን ቃላት መዝግቦ ለመዝገበ ቃላት የሚያበቃ እንደ ማርያም ዌብስተር ያለ አላገኘም፡፡ ስያሜ ቃላት ሲያስፈልጉ የሚጠየቅ፣ በቋንቋው ላይ የሚደረጉ ጥናቶችን የሚያከማች፣ እኔ ባይ ተቋም አላገኘም፡፡
በመሆኑም ልክ እንደዚህ አሁን እንደተሰበሰብንበት ያለ ቋንቋውን ማጥናትና ማበልጸግ ዋና ዓላማው የሆነ ምሁራዊና ሳይንሳዊ ተቋም ያስፈልጋል፡፡ ተቋሙም እንዲሁ ዐጽመ ስም ያለው ብቻ ሳይሆን በአካዳሚያዊ ነጻነት የሚሠራ፣ ለውጥ ለማምጣት የሚተጋ የዕውቀት ቦታ መሆን ይገባዋል፡፡ ሌሎች የግልና የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎችና ተቋማትም ይህንን መሰል አካላትን እየፈጠሩ በተለይም በሴማዊ ቋንቋዎች(አንዳንዶቹ እየጠፉ በመሆኑ) ላይ ጥናት ማድረግና በአብዛኛው ከሀገሪቱ ውጭ የሚደረገውን የሴማዊና ኦርየንታል ጥናትን ወደ ሀገሪቱ ማምጣት አለባቸው፡፡  
2.  ቅቡልነት ያለው መለኪያ አለመኖር
አማርኛን በመጻፍና በመናገር ረገድ ሀገራዊ ቅቡልነት ያለው የአሠራር ደረጃ አለ ለማለት አያስደፍርም፡፡ አንድን ሥነ ጽሑፍ በእንግሊዝኛ ስንጽፍ ሥርዓቱን በተመለከተ የሚመሩን የታወቁ ደረጃዎችና ደረጃ አውጭዎችም አሉ፡፡ በዚህ ረገድ የቺካጎ ማኑዋል ተጠቃሽ ነው፡፡ ድርጅቶች፣ የትምህርት ተቋማትና የኅትመት ተቋማት ሥራችሁን በዚህ ደረጃ መሠረት አቅርቡ ይላሉ፡፡ አማርኛ ግን ሀገራዊ ቅቡልነትን ያተረፈ ደረጃ አውጭም ሆነ ደረጃ አለው ለማለት አስቸጋሪ ነው፡፡ ይህ መሆኑ ደግሞ አጠቃቀማችን አንድ ወጥ እንዳይሆን፣ በተለይም በትምህርት ተቋማት የሚሰጠው የቋንቋ ትምህርት እንደየመምህሩ እንዲለያይ አድርጎታል፡፡ ሚዲያዎቹም አንድ ወጥ የሆነ አጠቃቀም እንዳይከተሉ መረን ለቋቸዋል፡፡ በተለይ በሁለተኛ ቋንቋነት ለሚማረው ሰው ደግሞ እጅግ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ በርእስ፣ በዐንቀጽ፣ በመረጃ አሰጣጥ፣ በዋቤ አመዘጋገብ፣ በግርጌ ማስታወሻ አሰጣጥ፣ በፊደል መጠን፣ ወዘተ አንድ የሚያግባባ ደረጃ ያስፈልገን ነበር፡፡ ሌላው ቀርቶ የአጻጻፍ ሥርዓቱ ወጥ እንዲሆን ባለመሠራቱ ‹ጠዋት፣ ጥዋትና ጡሃት›፣ ‹መስተዋትና መስታውት›፣ የመሳሰሉትን ለመተራረም እንኳን አቅቶናል፡፡
ምሁራን፣ ተቋማት፣ መንግሥታዊ አካላትና ሌሎች ከተግባቦት ላይ የሚደርሱበት፣ በዕውቀታዊና ምሁራዊ ደረጃው፣ በባሕላዊና ማኅበራዊ ዐቅሙ ከፍ ያለ የአማርኛ ቋንቋ ሥርዓተ ጽሕፈት፣ መልክዐ ፊደል፣ ሰዋስው፣ ስያሜ ቃላት፣ የመጻሕፍት፣ የጥናታዊ ወረቀቶች፣ የማስታወቂያዎች፣ የዜናዎች፣ ወዘተ አጻጻፍ ደንብ ሊኖረን ይገባል፡፡ ይህንን የሚጠኑ፣ የሚተገብሩና የሚከታተሉ ተቋማትም ያስፈልጋሉ፡፡ በየጊዜውም ማንዋሎችን ማዘጋጀት አለባቸው፡፡ 
3.  ቋንቋውን ሰው ወይም ሥርዓት ማድረግ
በተለይ ከቅርብ ዘመናት ወዲህ አማርኛን ይናገሩ የነበሩ ሥርዓቶችና የሥርዓት መሪዎች ለሚፈጥሩትና ለፈጠሩት ችግር አማርኛ ቋንቋም አብሮ ተጠያቂ እየሆነ ነው፡፡ የሥርዓት መስፋፋት ለቋንቋ መስፋፋት ፣ የቋንቋ መስፋፋትም ለሥርዓት መስፋፋት መጥቀማቸው የየትም ሀገር ነባራዊ ሁኔታ ነው፡፡ በእንግሊዝ ግዛት ፀሐይ አትጠልቅም ባይባል ኖሮ እንግሊዝኛ በተአምር የዓለም መነጋገሪያ ባልሆነ ነበር፡፡ እንጂማ የቻይና ቋንቋ በተናጋሪዎች ብዛት እንግሊዝኛን ይበልጠው ነበር፡፡ የእስልምናና የዓረብ ግዛት መስፋፋት ለዐረብኛ ቋንቋ መስፋፋትና ማደግ ያበረከቱትን አስተዋጽዖ ማንም አይክደውም፡፡ እነ ፈረንሳይኛና ስፓኒሽ ያለ ግዛት መስፋፋት አልተስፋፉም፡፡ አማርኛም እንዲሁ ነው፡፡
ዛሬ እንግሊዝኛ

‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ብቸኛው አሸባሪ ህወሓት/ኢህአዴግ ነው›› አብርሃ ደስታ ‹‹የጦር ችሎት በሚመስል ችሎት እየተንገላታን ነው›› የሺዋስ አሰፋ በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና ሌሎች በተመሳሳይ መዝገቡ የተካተቱ ተከሳሾች በተከሰሱበት ድርጊት ላይ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ፣ የአንድነት እና የዓረና ትግራይ አመራሮችን ጨምሮ 10 ተከሳሾች ዛሬ መጋቢት 10/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ […]

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ግልገል ጊቤ 3 በያዝነው ዓመት መጨረሻ ሀይል ማመንጨት ይጀምራል ተባለ።

ግልገል ጊቤ 3 በያዝነው ዓመት መጨረሻ ላይ ሀይል ማመንጨት እንደሚጀምር የውሀ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ አለማየሁ ተገኑ አስታወቁ።

ከሰኔ ወር ጀምሮ እስከ ነሃሴ ባለው ዝናባማ…

መጋቢት ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምእራብ አርማጭሆ ወረዳ በአብርሃ ጅራ ከተማ ተቃዋሚ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩት ሁሉ እየተያዙ በመታሰር ላይ ናቸው። ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ እየተካሄደ ባለው ጥብቅ ፍተሻ በርካታ የኢህአዴግ አባላትና የጸጥታ ሃይሎች ተይዘው ሲታሰሩ፣ ቁጥራቸው በውል ያልተወቀ ነዋሪዎች ደግሞ አፈሳውን በመፍራት እያመለጡ የትጥቅ ትግል የሚያደርጉ ተቃዋሚዎችን በመቀላቀል ላይ ናቸው። እስካሁን በተደረገው አፈሳ …

መጋቢት ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዘላለም ወርቅአገኘሁ መዝገብ የተከሰሱ የቀድሞው የአንድነት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው፣  ምክትል የድርጅት ጉዳይ ሃላፊው አቶ ዳንኤል ሽበሺ፣ የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ የሽዋስ አሰፋ እንዲሁም የአረና ፓርቲ አመራር መምህር አብራሃ ደስታ ከሌሎች 6 ተከሳሾች ጋር መጋቢት 10 ቀን 2007 ዓም ፍርድ ቤት ቀርበው …

Ethiopian Movie Trailer Feker Ena Genzeb 2 Coming Soon “ፍቅር እና ገንዘብ-2” ፊልም ለዕይታ ሊበቃ ነው YouTube Trailer

Ethiopian Movie Trailer Feker Ena Genzeb 2 Coming Soon “ፍቅር እና ገንዘብ-2” ፊልም ለዕይታ ሊበቃ ነው YouTube Trailer :
በአሸናፊ ደምሴ
በጋላክሲ ፊልም…

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ሐሙስ፡- ባሕልና ማኅበረሰብ፣ ሕይወት በቀበሌ፣ የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት

የጀርመኗ ፍራንክፉርት ከተማ ትናት በዓመጽ ስትናጥ ነበር። መኪናዎች እና ጎማዎች አደባባዮች ላይ ሲነዱ፣ ቁሳቁሶች ሲወረወሩ የተቃውሞ ሰልፉ የተኪያሄደበት የከተማው ክፍልም በጥቁር ጢስ ተውጦ ታይቷል። የግጭቱ መንስዔ ደግሞ በፍራንክፉርት ከተማ አዲስ የአውሮጳ ማዕከላዊ ባንክ መከፈት ነው።

የኢትዮጵያ ጦር በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ከአሸባብ ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን የእስልምና ሃይማኖት መምህር ፍለጋ ወደ ሰሜን ሶማሊያ ገብቶ እንደ ነበር ተሰማ። ጦሩ ከገባበት አካባቢ ወዲያው ለቆ መውጣቱ ተዘግቧል።

በምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት /ኢጋድ/ አማካኝነት ሲካሄድ የከረመው የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ሃይሎች ድርድር አለመሳካቱን ተከትሎ በአገሪቱ ሁለት ግዛቶች ተቀስቅሶ የነበረው ግጭት ወደ ሌሎች አራት ግዛቶች መስፋፋቱን የአገሪቱ ባለስልጣናት አረጋግጠዋል። ግጭቱ በተቀሰቀሰባቸው አካባቢዎች ነዋሪዎች ቀያቸውን ጥለው እየተሰደዱ ነው።

«በቆዳ ቀለማችን ለየት ብንልም ልባችን ኢትዮጵያዊ ነዉ ፤ ኢትዮጵያን፤ ኢትዮጵያዉያንን በኔና በቤተሰቤ ስም በጣም ማመስገን እፈልጋለሁ» ትዉልደ አርመኑን ኢትዮጵያዊ ሙዚቀኛ ቫሄ ቲልብያን የዛሬ ወር ኢትዮጵያን፤ አፍሪቃን ብሎም አርሜንያን ወክሎ በግዙፉ የአዉሮጳ ሃገራት የሙዚቃ ዉድድር ላይ ሙዚቃ እንዲያቀርብ ተመርጦአል።

Raya Jemal. ራያ ጀማልየማለዳ ወግ

ነቢዩ ሲራክ

ወንድም ራያ ጀማል የ5 ወንድ እና የ3 ሴት ልጆች ጎልማሳ አባት ነው። ወደ ሳውዲ የመጣው ድህነት፣ የኑሮ ውድነት፣ የፖለቲካው ሙቀት አልያም የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ገፍቶት አይደለም። ሳውዲ የመጣው፣ የእስልምና እምነቱ በሚያዘው መሰረት በህይወት ዘመኑ የሚጠበቅበትን ለማድረግ ከብቶቹን ሽጦ የሃጅ ጸሎት ለማድረግ ነበር …

ሙሉውን አስነብበኝ …

መጋቤ ብሉይ አእመረ አሸብር በምክትል ሥራ አስኪያጅነት ተመድበዋል ብፁዕ ጠቅ/ሥራ አስኪያጁ ውሳኔውን በአስቸኳይ እንዲያስፈጽሙ በሹመት መመሪያ ታዝዘዋል ሊቀ ማ/ን የማነ ሥራን በመበደል፣ አእመረ አሸብር በሃይማኖታቸው ርቱዕነት ነቀፌታ አለባቸው የፓትርያርኩ አካሔድ በረዳት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቀሌምንጦስ ከፍተኛ ተቃውሞ እየቀረበበት ነው ቋሚ ሲኖዶስ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚነጋገርበት ይጠበቃል *      *     * ተተኪው ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ በወቅቱ በዋና ጸሐፊነት …

(ትርጉም ጌታቸው ረዳ ኢትዮጵያን ሰማይ ድረገጽ አዘጋጅ) የወያኔ እገዛ የሚደረግለት ኢትዮጵያ ውስጥ መሰረቱ ያደረገ “የኤርትራ አገራዊ ደህንነት ግምባር” ብሎ ራሱን የሚጠራ ኢሳያስ አፈወርቂን ከሥልጣን ለማስወገድ የተቋቋመ ሽምቅ ተዋጊ ሃይል በፈረንጆች…

The post አስመራ ከተማን ያጠቃው “የኤርትራ አገራዊ ደህንነት ግምባር” መግለጫ ሰጠ! appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

ኢያን ካምፕቤል ፋሽስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በወረረች ጊዜ በደብረ ሊባኖስ ገዳም ላይ ስለ ፈጸመቺው አሰቃቂ እልቂት የሚተርክ ‹The Massacre of Debre Libanos, Ethiopia 1937› የተሰኘ መጽሐፍ አሳትመዋል፡፡ ይኼ ብዙ ጊዜ የማይነገርለት…

The post የደብረ ሊባኖሱ እልቂት – ዳንኤል ክብረ appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

የምታስፎክር ሰንጋ ገለሌ
በጦር መካከል ሳይሆኑ አያሌ
በጥይት ገዳይ ነጭ ብርገድሌ
የሴት ወንድ ናት ሸዋረገድ ገድሌ
ተብሎ የተገጠመላቸውን፣ በአምስት ዓመቱ የጠላት ወረራ ጊዜም አኩሪ ጀብዱ የፈጸሙትን የአርበኛዋን የሸዋረገድ ገድሌን ታሪክ የሚተርክ መጽሐፍ ሰሞኑን ቀርቧል፡፡ ‹ሸዋ ረገድ ገድሌ፣ የአኩሪ ገድላት ባለቤት ይሰኛል፡፡ ሺበሺ ለማ ጽፎት ዶክተር ክፍሌ ማርቆስ ገድሌ አሳትመውታል፡፡
በአምስት ዓመቱ የፋሽስት ወረራ ጊዜ ለሀገራቸው አኩሪ ገድል በመፈጸምና ለነጻነታችን ዋጋ በመክፈል ስማቸው ከሚነሡ ሴቶች ሸዋረገድ ገድሌ ግንባር ቀደም ናቸው፡፡ በ1878 ዓም የተወለዱት ወ/ሮ ሸዋ ረገድ ገድሌ ሁለገብ እንደነበሩ ታሪካቸው ያሳያል፡፡ የቤተ ክህነቱን ትምህርት ተምረዋል፡፡ ትዳርን አልፈልግም ብለው ምናኔን መርጠው ኢየሩሳሌም ድረስ ተጉዘዋል፡፡ ከመጀመሪያዎቹ የባንክ ተጠቃሚዎች፣ የአክሲዮን ገዥዎች፣ የፋብሪካ ተካዮች መካከል አንዷ ነበሩ፡፡ የጉለሌ ቅዱስ ገብርኤልንም ያስተከሉት እርሳቸው ነበሩ፡፡ 

የሸዋረገድን ስም ይበልጥ ከፍ አድርጎ ያስጠራው አርበኛነታቸው ነው፡፡ የኢጣልያ ጦር ሊጎርሰን ማሰፍሰፉ ሲሰማ በአዲስ አበባ ከተማ በሀገር ተቆርቋሪ ዜጎች በተቋቋመው የሀገር ፍቅር ማኅበር አባልነት መጀመሪያ ከተመዘገቡት ጥቂት ሴቶች መካከል አንዷ እርሳቸው ነበሩ፡፡ ወራሪው ፋሽስት አዲስ አበባ ሲገባና የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ወርዶ የኢጣልያ ባንዴራ ሲተካ ወ/ሮ ሸዋረገድ ገድሌ ስቅስቅ ብለው አለቀሱ፡፡ በዚህ ምክያትም በኋላ  ‹የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ወርዶ የገናናው የኢጣልያ ሰንደቅ ዓላማ ሲውለበለብ በማየትሽ አልቅሰሻል›› በሚል ተከሰው ነበር፡፡ ሸዋረገድም ያለምንም ፍርሃት ‹አዎ አልቅሻለሁ፤ ያገሬን መወረርና መዋረድ ያወቅሁት የኛ ሰንደቅ ዓላማ ወርዶ የናንተ ሲውለበለብ በመታየቱ ነው፡፡ ሰው ለእናት ሀገሩ ቢያለቅስ ነውሩ የት ላይ ነው?›› ብለው ነበር የመለሱት፡፡ 
 
ወ/ሮ ሸዋረገድ ለአርበኞች ስንቅ በማቀበል፣ መሣሪያ በመግዛት፣ መረጃ በማሰባሰብ፣ መድኃኒት በመላክና ሞራል በመስጠት አምስቱን ዓመት በተጋድሎ ነው ያሳለፉት፡፡ በዚህ ምክንያት በተከሰሱ ጊዜም ‹‹ለአርበኞች ስንቅ ማቀበሌ እውነት ነው፤ይህንንም ያደረግኩት ለሀገሬ ክብር ብዬ ነው፡፡ ሰው እንኳን ለሀገሩ የእናንተ ወይዛዝርት ሀገራቸው ያልሆነቺው ኢትዮጵያን ለመውረር የጣታቸውን ቀለበት ሳይቀር መስጠታቸውን ትናገራላችሁ፡፡ እኔም ለሀገሬ የሠራሁት ሲያንሰኝ እንጂ አይበዛብኝም›› ነበር ያሉት፡፡
ወ/ሮ ሸዋረገድ ከሚጠቀሱላቸው ሥራዎቻቸው አንዱ ለቀይ መስቀል ማኅበር የነበራቸው ድጋፍ ነው፡፡ በጦርነቱ ዋዜማ ሐምሌ 1 ቀን 1927 ዓም ለተቋቋመው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ንብረታቸውን ሸጠው አስረክበዋል፡፡ እሥር ቤት በገቡ ጊዜ ከተከሰሱበት ወንጀል አንዱም ‹ቀይ መስቀልን ትረጃለሺ› የሚል ነበር፡፡ ሸዋረገድ ቀይ መስቀልን ከመርዳትም ባሻገር ኢትዮጵያውያን ወይዛዝርት እራፊ ጨርቅ እንዲያሰባስቡ በማድረግ ለአርበኞች ቁስል ማሸጊያ ይልኩላቸው ነበር፡፡ 
 
ሸዋረገድ ከርዳታው ጎን ለጎን ለአርበኞቹ የመረጃ ምንጭም ነበሩ፡፡ በከተማው የሚገኙ የጠላት መረጃዎችን በማሰባሰብና ወደ አርበኞች በምሥጢር በመላክ አርበኞች እንዲጠቀሙባቸው አድርገዋል፡፡ በዚህና በሌሎች ገድሎቻቸው ምክንያትም የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ነበር፡፡ በፈጣሪ ቸርነት ግን ሳይፈጸምባቸው ቀርቷል፡፡ የሞት ፍርዱ ባይፈጸምባቸውም የኢጣልያን እሥር ቤት ከሚያዘወትሩት አንዱ ሸዋረገድ ሆነዋል፡፡ በየጊዜው ይታሠራሉ፤ ይፈታሉ፡፡ በመጨረሻ ግን አዚናራ ወደምትባል ከሰርዲኒያ ሰሜናዊ ምዕራብ ወደምትገኝ ደሴት ታሥረው ተልከዋል፡፡ 
 
እዚያም ቢሆን ጽናታቸው አልተሰበረም፤ ወኔያቸውም አልተሰለበም፡፡ የሚያደርጉት ቢያጡ በእሥር ቤት የሚቀርብላቸውን የተበላሸ ምግብ በአሣሪዎቻቸው ፊት በመድፋትና ጦማቸውን በመዋል ፋሽስትን ይቃወሙ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታም ለአንድ ዓመት ከመንፈቅ ታሥረው ተፈቱ፡፡ አዲስ አበባ ሲገቡ ግን ትግላቸውን ቀጠሉ እንጂ አላቆሙም፡፡ ሕዝቡም
 
የዘበኛ ሱሪ ካኪና ገምባሌ
እንኳን ደኅና መጣሺ ሸዋረገድ ገድሌ
 ብሎ ተቀበላቸው፡፡ 
 
በተለይም በጅቡቲ የነበረ አንድ ኢትዮጵያዊ የሰጣቸውን ‹የይሁዳ አንበሳ› የሚል ጽሑፍና ዓርማ ያለበትን ወረቀት ከንጉሡ የተላከ የሚመስል መልእክት እየጻፉ ወደ በረሐ በመላክ አርበኞችን አበረታተውበታል፡፡ የአዲስ ዓለም የጣልያን ምሽግ ኅዳር 5 ቀን 1933 ዓም በአርበኞች ሲሰበር ዋናውን መረጃ የሰበሰቡትና ዐቅድ የነደፉት ሸዋረገድ ነበሩ፡፡ ከምሽጉ ሰበራ በኋላም ደጀን መሆኑን ትተው ራሳቸው ወደ ውጊያ ዐውድማ ገቡ፡፡ በተለይም መቂ አካባቢ ከሻለቃ በቀለ ወያ ጦር መካከል ተሰልፈው ተዋግተዋል፡፡ በኋላም ጅማ አካባቢ ከነበረው ከገረሱ ዱኪ ጦር ጋር ለመገናኘት ተጓዙ፡፡ በዚያ እያሉም ጠላት ድንገተኛ አደጋ ጥሎ ገጠማቸው፡፡ ለአራት ሰዓት ያህልም ተዋግተው ተማረኩ፡፡ ወደ እሥር ቤት ተወስደውም የፊጥኝ ታሠሩ፡፡ 
 
በ1933 ዓም ሀገሪቱ ከፋሽስት ኢጣልያ ወረራ ነጻ ስትወጣ ሸዋረገድ ገድሌ አርበኞችን ወደመርዳትና የበጎ አድራጎት ሥራን ወደ መሥራት ገቡ፡፡ በንግዱም መስክ ተራመዱ፡፡ ሀገራቸውን እስኪበቃቸው አገልግለው፤ ግሼን ማርያም ሄደው ሥጋወደሙን ተቀብለው፤ ከዚያም ወደ ላሊበላ ተጉዘውና ተሳልመው፤ የመጨረሻቸው መሆኑን እየተናገሩ ጥቅምት 22 ቀን 1942 ዓም ዐረፉ፡፡ ሕዝቡም 
 
እናንት ወጥ ቤቶች በርበሬ ቀንጥሱ
እናንት ሥጋ ቤቶች ሰንጋውን ምረጡ
ሸዋረገድ ገድሌ ለገና ሲመጡ፡፡
ቤተሰቧ ሰፊ ገናና ጥምቀት
ሸዋረገድ ገድሌ እንደምን ትሙት፡፡ ብሎ ገጠመላቸው፡፡ 
 
ሰፊ ነው ታሪካቸው፡፡ ልብ የሚያሞቅ፤ ወኔ ቀስቃሽ፤ አስደማሚ፤ ከዐለት የበረታ ጽናት፤ ከእቶን የጋለ አርበኝነት፤ ከትንታግ የተንቀለቀለ የሀገር ፍቅር ታገኙበታላችሁ፡፡ ምናለ አደባባዮቻችን በንግድ ኩባንያዎች ስም ከሚጠሩ በነ ሸዋረገድ ገድሌ ስም ቢሰየሙ ብላችሁም ትቆጫላችሁ፡፡

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመሬት፣ የሕንጻ እና የልዩ ልዩ ገቢ ማስገኛ ተቋማት አጠቃቀምና የኪራይ ተመን ጉዳዮችን በመፈተሽ የቤተ ክርስቲያንን መብትና ጥቅም የሚያስከብር ፖሊሲ ለማውጣት የሚያስችል ዝርዝር የመፍትሔ ሐሳብ እንዲያቀርብ በቋሚ ሲኖዶስ ተወስኖ በፓትርያርኩ በተሰጠው መመሪያ መሠረት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የተቋቋመው ኮሚቴ በወርኃ ታኅሣሥ መባቻ የጀመረውን ጥናት እንደቀጠለ ነው፡፡ ከጠቅላይ ጽ/ቤቱ እና ከሀገረ …

ኢትዮጵያውያን ለውጥ እንፈልጋለን:: ለውጥ እንፈልጋለን ብለን ለትግል ስንነሳ መንገድ ሁሉ አልጋ በአልጋ ይሆንልናል ማለት አይደለም::በትግሉ ውስጥ የሚከሰቱ እሾህ እና አሜኬላዎች እንቅፋት ሆነው ከስንዴው እኩል እንደ እሸት የሚያብቡ እንክርዳዶች እየሰረጉ በመግባት ትግሉን ለማኮላሸት አሊያም ደሞ ተያይዘው ለመጥፋት በሚያሴሩት ደባ የህዝብ ልጆች በሚያደርጉት ተጋድሎ እነዚህን እንቅፋቶች ማስወገድ እና በጥንካሬ ጋሬጣውን ማለፍ የሚጠበቅበት ወቅታዊ አጋጣሚዎች ሳንዘናጋ ልንጠቀምበት ይገባል:: […]

 

በየዓመቱ በፈረንጆች ማርች ስምንት ወይም በኢትዮጵያ የካቲት 29 የሚውለው የዓለም የሴቶች ቀን ባለፈው ሣምንት በተለያዩ ዝግጅቶች በዓለም ዙሪያ ተከብሯል።

በዩናይትድ ስቴትስ ደግሞ ማርች ስምንት ብቻ ሳይሆን ወሩ በሙሉ የሴቶች ታሪክ ይወሳበታል።

አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ይህንኑ ምክንያት በማድረግ ለኢትዮጵያ ሴት ሰዓሊያን እና ቀራፂያን አንድ ልዩ ውድድር ማሰናዳቱን በኤምባሲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ባዘጋጀው ሥነ-ሥርዓት ላይ ይፋ አድርጓል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡