በአፍሪካ በቁመቱ ረጅም የሆነው ግልገል ጊቤ 3 በያዝነው ዓመት መጨረሻ ሀይል ያመነጫል Africa’s tallest, Ethiopia’s Largest Hydro Plant Gibe III to Produce Power This Year

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ግልገል ጊቤ 3 በያዝነው ዓመት መጨረሻ ሀይል ማመንጨት ይጀምራል ተባለ።

ግልገል ጊቤ 3 በያዝነው ዓመት መጨረሻ ላይ ሀይል ማመንጨት እንደሚጀምር የውሀ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ አለማየሁ ተገኑ አስታወቁ።

ከሰኔ ወር ጀምሮ እስከ ነሃሴ ባለው ዝናባማ ጊዜ ውስጥ ከ10 ተርባይኖች አንዱ በሆነው 187 ሜጋ ዋት ሀይል ማመንጨት እንደሚጀምር ተገጿል።

የመጀመሪው ሃይል ማመንጨት እንደተጀመረም ሌሎቾ ተርባይኖች በየወሩ ሀይል ማመንጨት ስራ ይጀምራሉም ብለዋል።

በአፍሪካ በቁመቱ ረጅም የተባለው እና 243 ሜትር እርዝመት ያለው ግልገል ጊቤ 3 የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ግድብ 1 ሺህ 870 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ለው ሲሆን፥ ኢትዮጵያ መንግስት እያስገነባቸው ካሉ ታላላቅ ፕሮጄክቶች ውስጥ አንዱ ነው።

የግልገል ጊቤ 3 ግድብ በአጠቃላይ 11 ነጥብ 8 ቢሊየን ኩቢክ ሜትር ውሃ የመያዝ አቅም አለውም ተብሏል።

የግድቡ ሀይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታም ከኢትዮጵያ እሰከ ኬኒያ ድረስ ሚዘረጋው እስከ ፈረንጆቹ 2018 ይጠናቀቃል በማሉን ብሉምበርግ ዘግቧል።

Watch Ethiopian movies legally. Up to 5 movies added daily. Here are the top 10 most viewed movies today.

Receive Ethiopian News, Movies and Videos by email. Sign up for Email alerts ፊልሞች፣ ዜናዎችና ቪድዮዎችን በኢሜል አድራሻቹ እንልካለን። ኢሜላችሁን አስመዘግቡ።