መጋቢት ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በባህርዳር ከተማ በመካሄድ ላይ ባለው 2ኛው የትምህርት ቤቶች ውድድር ተገኙት ተወዳዳሪዎች እንደተናገሩት በውድድሩ በርካታ አዳዲስ ተተኪ ወጣቶች ለማፍራት የሚያስችል  ቢሆንም ወቅቱን የጠበቀ አለመሆኑ በትምህርታቸው  ላይ ጉዳት እንደሚያደርስባቸው ተናግረዋል፡፡ ከመጀመሪያው መንፈቅ አመት ፈተና በኋላ በቀጥታ ወደ ስፖርት ውድድር ልምምድ በመግባታቸው፣  ከትምህር ገበታቸው ላይ ለሁለት ወር ያህል መለየታቸውንና …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና

አሳፋሪነቱ እየተባባሰበት የመጣው “ፍርድ ቤት” የመብት ጥሰትንም ሆነ የሲዲ ማስረጃዎች ጥያቄን አልቀበልም አለ
ሁለት የጎንዬሽ አቤቱታዎችን አስመልክቶ ዛሬ የተሰየመው ችሎት ከሌላ ጊዜው በባሰ ሁኔታ የወንጀል ስነስርአትና የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች ላይ ሲቀልድ ውሏል፡፡ ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ እና ጦማሪት ማህሌት ፋንታሁን በጎብኚዎች የመጠይቅ መብታቸው መነፈጉን በቀን 20 ደቂቃ ብቻ ከሌሎች እስረኞች ከቅርብ ቤተሰብ ውጪ ሌላ አንዳይገባ እንደተከለከሉ መሰረታዊ መብቶቻቸው እስር ቤት ውስጥ አንደሚጣሱ ባለፉት ስድስት ወራት በተደጋጋሚ አቤቱታ ሲያቀርቡ የከረሙ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ የመብት ጥሰቱን የሚያሳይ ምንም ማስረጃ አልቀረበም፣ ከማረሚያ ቤቱ ጋር ያለውን አስተዳደራዊ ችግርን የመፍቻ መንገድ አልተጠቀሙም በማለት በውሳኔው የህገ መንግስቱን አንቀጽ 21 ሽሮታል፡፡ አያያዛቸው መሰረታዊ መብቶቸን የሚያስጠብቅ ይሁን ብሎ የተለመደውን የለበጣ ትእዛዝ አንኳን መስጠት ያቃተው የዛሬው “ፍርድ ቤት” የሁለቱን ወጣት ሴቶች መሰረታዊ የመብት ጥያቄ እነደዋዛ አጣጥሎታል፡፡
ሁለተኛው ጉዳይ የነበረው አቃቤ ህግ የሲዲ ማስረጃዎቹን ለተከሳሾች ሊሰጥ አንደሚገባ ሲጠይቅ የወንጀሉ ኤግዚቢት ነው በማለት ያቀረበውን መከላከያ ፍርድ ቤቱ ተቀብሎ ለተከሳሾች ሊሰጥ አይገባም ሲል ሌላ አስገራሚ ብይን አሰምቷል፡፡ ብይኑን ተከትሎ የተከሳሽ ጠበቆች የወንጀል ኤግዚቢት ከሆነ ሲዲው በአቃቤ ሀግ እጅ መገኘት አንደማይገባና በህጉ መሰረት ፍርድ ቤቱ እጅ መቀመጥ አንዳለበት በመሆኑም ሲዲው የት አንደሚገኝ የጠየቁ ሲሆን “ፍርድ ቤቱ” በጠበቆች ስላልተጠየቀ ሲዲው ሬጅስትራር ጋር መሆኑ እና አለመሆኑን እነዳላጣራ አስገራሚ ምላሽ ሰጥቷል፡፡ ይህንን አስተያት ተከትሎ የህግ ባለሞያው ዘላለም ክብረት ለፍርድ ቤቱ አጠር ያለ የወንጀል ስነስርአት ሂደትን የሚያስረዳ ማብራሪያ ከሰጠ በኋላ “በዚህ ሂደት ፍርድ ቤቱ በግልጽ ሲዲው የማስረጃው አካል ነው ወይስ ኤግዚቢት ነው የሚለውን አሁን ይንገረን ፡፡ ኤግዚቢት ነው ከተባለም አቃቤ ሀግ የማስረጃ አካል አድርጎ እንዳያቀርበው አሁን ብይን ይሰጥልን በማለት ጠይቋል”፡፡ “ፍርድ ቤቱም” ይህንን መወሰን ያለበት አቃቤ ህግ ነው የሚል የእለቱን አስገራሚነት የጨመረ መልስ ሰጥቷል፡፡ ይህንን ተከትሎ አቃቤ ሀግ ማስረጃ ነው ካለም በማስረጃ መስማቱ ወቅት በሂደት የሚታይ ነው ያለ ሲሆን ብይኑን ከጠበቆች እና ከተከሳሾች በቀረበበት ተከታታይ ጥያቄዎች ሲያምታታ ተስተውሏል፡። ተከሳሾች ተቃውሞ ካላቸው ይግባኝ ማቅረብ ይችላሉ የተባለ ሲሆን ጦማሪ ናትናኤል በበኩሉ አቃቤ ህግ ያለውን ብቻ በመስማት ተከሳሾች ላይ ተጽእኖ እያደረጋችሁ ነው ሲል “ፍርድ ቤቱን” ከሷል፡፡
በእስር ላይ አንድ አመት ሊሞላቸው አንድ ወር የቀራቸው የዞን9 ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች በጠንካራ መንፈስ እና ፈገግታ ችሎቱን የታደሙ ሲሆን በፍርድ ቤቱ ውጥንቅጥ ምንም አይነት መገረም አልታየባቸው፡፡
የዞን9 ማስታወሻ
ከዚህ በፌት በተደጋጋሚ አንዳልነው የዞን9 ጦማርያን ፍርድ ቤት የሚሄዱት የፍትህ ስርአቱን ህጋዊ እውቅና እና ቅቡልነት ለማሰጠት ሳይሆን በቃል ስንለው የከረምነውን የፍትህ ስርአቱን ውድቀት በተግባር ለማረጋገጥ ነው፡፡ ሁሉንም የህግ አማራጮች በመጠቀም ፍርድ ቤቱን በማጋለጣችን በእስርም ሆነ በስደት የምንገኘው የዞን9 አባላት በኩራት አንገታችንን ቀና በማድረግ የምንናገረው ጉዳይ ነው፡፡ በየቀኑ የራሱን መሰረታዊ መስፈርት እና ጥቃቅን የወንጀል ስነስርአት ህግ አንኳን መከተል ያቃተውን ፍርድ ቤት የሚመሩት ዳኞች ከችሎቱ ሲወጡ እና ከህሊናቸው ጋር በግልጽ ሲነጋገሩ የስራ አስፈጻሚው መሳሪያነታቸውን ቀን ከቀን በአሳፋሪ ሁኔታ እያጠናከሩ መሆኑን እነደሚያውቁት እርግጠኞች ነን፡፡ ራሳቸውን ከችሎቱ አግልያለው ብለው አስካሁንም ችሎቱን እየሰበሰቡ ባሉት አቶ ሸለመ በቀለ ለሚመራው ችሎት በተደጋጋሚ ጥሪ ስናደርግ እነደነበረው የፍትህ ስርአቱን ስም የማደስ እድላቸውን እየተጠቀሙበት ካለመሆኑም በተጨማሪ የነርሱ ከፍትህ እና ከታሪክ በግራ በኩል መቆም ከማሳየቱም በላይ የወጣት አስረኞቹን ልእልና ቀን ከቀን ከፍ ብሎ እነዲታይ እያስቻሉ ነው፡፡
አገራቸውን በጨዋነት የሚያገለግሉ ምሁራን የዞን9 ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች አምባገነንነት እና የተቃውሞ ድምጽ ማፈኛ መሳሪያ የሆነው የፍትህ ስርአት ያልፈታቸው ጨዋዎች መሆናቸውን በማስመስከራቸው እንኮራለን፡፡ የህሊና እስረኞቹ በማንኛውም መስፈርት ቢለኩ ከደረጃቸው በታች በሆኑ ዳኞች ፌት መቆም ያልነበረባቸው የቤተሰብና የአገር ኩራቶች ናቸው ፡፡

የፍትህ ስርአቱን ውድቀት ማጋለጡ ይቀጥላል፡፡

ዞን9

በጀርመን እና በግሪክ የገንዘብ ሚኒስትሮች መካከል ንግግሩ ከሯል። ጉዳዩ በሁለት ሚኒስትሮች ብቻ የሚፈታ አይደለም። አዲሱ የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሲስ ሲፕራስ ሰኞ ወደ ጀርመን መጥተው ከጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ጋር ስለ ግሪክ የኢኮኖሚ ቀውስ ተወያይተዋል። የሚያስማማ ሀሳብ ላይ ግን አልደረሱም።

የግብፅ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታሕ ኧል ሲሲ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እና ከፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመጋ ጋር በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ተገናኝተው ዛሬ በሰፊው መወያየታቸዉ ተሰምቷል።

«ዉኃና ዘላቂ ልማት» ከአንድ ቀን በፊት በመላዉ ዓለም የታሰበዉ የዘንድሮዉ የዓለም የዉኃ ቀን መሪ ቃል ነዉ። ለጤና፤ ለአካባቢ ልማት፤ ለኢንዱስትሪ ባጠቃላይ ለዕለት ከዕለት ኑሮ ወሳኝ መሆኑን በተለያዩ መድረኮች ለማሳየትም ተሞክሯል።

March 24, 2015 አበበ ገላው (ከፌስቡክ የተወሰደ) ወያኔ ኤርትራ ውስጥ የሚገኝ አንድ የካናዳ የወርቅ ማእድን በአውሮፕላን መደብደቡን አፍቃሪ ወያኔ የሆኑ ድረ ገጾች “ወታደራዊ ምንጮችን” በመጥቀስ ዘግበዋል። ይሁንና እንኳን ድብደባው የጥቃቱን…

The post የጄት ድብደባ ወይንስ የአውሮፕላን መከስከስ? appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

Minilik Salsawi ትላንትና ከምሽቱ 2 ሰአት ላይ በኦሮሚያ ክልል አምቦ አከባቢ አንድ ከፍተኛ የወያኔ ወታደራዊ ባለስልጣን መገደሉ ታወቀ::አምቦ በከፍተኛ የጸጥታ ቁጥጥር ስር መውደቋ ተረጋግጧል::በአከባቢው የመብራት እና የስልክ አገልጎት ተቋርጦ ያደረ ሲሆን ይህንን የአከባቢው ነዋሪዎች ለሰይፈ ነበልባል ራዲዮ ጣቢያ ጋዜጠኛ እዮብ ባይሳ በሰጡት ቃለመጠይቅ አረጋግጠዋል::

በቀበሌ 2 በተባለ አከባቢ ሲያልፍ የነበረውንየወያኔ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣን የገደለው ማንነቱ ያልታወቀ ሲሆን አምቦ በከፍተኛ የደህንነት ቁጥጥር ስር ነች ያሉት ነዋሪዎቹ በጊዜው ጉዳዩን ያልተረዱና ከፍተኛ መደናገጥ እንደደረሰባቸው የተናገሩ ሲሆን ፖሊሶች እና ማንነታቸው የማይታወቁ የጸጥታ ሃይሎች ነዋሪዎችን እያስቆሙ እና እየፈተሹ እንደነበር ታውቋል::

ከአስረ አንድ ወራት በፊት ወያኔ የነደፈውን እና ገበሬዎችን የሚያፈናቅለውን የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም ከ27 00 በላይ የአምቦ ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ ወተው የነበረ መሆኑ ሲታወስ የሕወሓት አግአዚ ሰራዊት ከ30 በላይ ያልታጠቁ ተማሪዎችን እና ነዋሪዎችን የገደለ እና የቤተሰባቸውን ደህንነት ለማረጋገጥ በቦታው የነበሩ ዜጎች ሳይቀር ለሞት እና ለቁስለት መዳረጋቸው የታወቀ ሲሆን የዘጠኝ አመት ሕጻን ታዳጊ ሳይቀር በሕወሓቶች መገደሉ ይታወሳል : ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

http://ayyaantuu.com/horn-of-africa-new … mbo-today/

Image

ኢትዮጵያ፣ሱዳን እና ግብፅ ትናንት መጋቢት 14/2007 ዓም ካርቱም ላይ በአባይ ወንዝ አጠቃቀም እና በተለይ ኢትዮጵያ እየገነባችው ባለው ግድብ አጠቃቀም ዙርያ አንድ ስምምነት ተፈራርመዋል። የአባይ ጉዳይ ከአፍሪካ ቀንድ አልፎ በግብፅ ሳብያ…

The post በኢትዮጵያ፣ሱዳን እና ግብፅ መሃከል የተደረገው ስምምነት የሚጨበጨበለት አይደለም።ለኢትዮጵያ አንድ ለግብፅ ሶስት ጥቅሞችን ሰጥቷል (የጉዳያችን ልዩ ዘገባ) appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

Feven Tashome is a study in blue. The 21-year-old’s toenails are painted a rich cobalt, her scarf is baby blue and her leather handbag is ultramarine. To ordinary passersby in the Ethiopian capital of Addis Ababa, it’s a fashion statement; to members of Ethiopia’s beleaguered political opposition, it’s a secret handshake.
Feven (Ethiopians go by their first names) is showing her allegiance to an opposition party with an odd name, and an even odder theme song.
The Blue Party is one of Ethiopia’s few remaining opposition parties. Ethiopia is technically a multiparty parliamentary democracy, like Britain, but it is effectively run like a one-party state, with 99.8 percent of parliamentary seats controlled by one ruling party, the Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front, or EPRDF.
After the Blue Party was founded three years ago, it organized a peaceful anti-government protest in a country that hadn’t permitted public rallies for a decade. The parade of young Ethiopians demonstrating in jeans and blue T-shirts seemed a sign that the government was relaxing its grip. But with new elections this May, the Blue Party claims that subsequent rallies have been met violently by police. They say hundreds of their delegates have been fired from their jobs or beaten up by thugs.
Blue Party spokesman, 27-year-old Yonatan Tesfaye, says blue is a symbol of two powerful unifying images for Ethiopians: the Blue Nile, and the Red Sea (which is actually turquoise most of the year). Blue is also the color of Twitter and Facebook; social media are one of the last remaining outlets for relatively uncensored expression in the country.
But to the Ethiopian government, “blue” is a symbol of rebellion, like the “Orange Revolution” in Ukraine or the failed “Green Movement” in Iran.
A documentary, the airing of which on Ethiopian state television last year was timed with U.S. Secretary of State John Kerry’s official visit, accused Western human rights groups of trying to instigate the overthrow of the Ethiopian government in what the documentary calls a “color revolution.”
Also timed with Kerry’s visit, the government arrested and imprisoned nine bloggers and journalists critical of the regime. Kerry, who was mainly in Ethiopia to encourage American investment in the skyrocketing Ethiopian economy and to express gratitude for a military partnership (the Ethiopian army is a proxy for intervention in many African hotspots), advised the government to release the journalists and bloggers. He was ignored.
Genenew Assefa, the political adviser to Ethiopia’s minister of communication, is a chain-smoker in a black jacket with a well-thumbed paperback of Hegelian philosophy on his desk.
He dismisses the Blue Party as insignificant (he describes them as “young people running around, screaming around”) but at the same time warns that Westerners do not appreciate how Ethiopia’s “fledgling” 25-year-old democracy is under siege by ethnic separatists and Muslim extremists — some of whom he claims take shelter in the Blue Party.
Ethiopia is majority Christian, “but we have problems with radical Muslims in this country,” Genenew says slowly and deliberately. “And we will suppress. We will not tolerate.”
The Blue Party says it is not Islamist, but secular, with a peaceful and reformist platform: pro-civil rights and anti-corruption.
But the party’s PR strategy is unique in Ethiopian politics. In direct response to the government’s attempt to paint opposition groups as violent and scary, the Blue Party has, from its inception, sought to portray the opposite image.
Even Yonatan, the Blue Party spokesman, says he doesn’t expect his party to win a single parliamentary seat in the upcoming election. The ruling party, while politically repressive, has presided over the fastest growing economy in Ethiopian history. The former high school teacher says he’ll be happy if the Blue Party just becomes an umbrella for people to voice their discontent.
“People are very scared of the politics — they fear the situation,” and become disengaged and apathetic, he says. “So we’re trying to break them out of the fear.”

Source: http://www.npr.org/blogs/parallels/2015/03/10/391917530/ethiopias-blue-p…

አንዳንዴ እንዳለመታደል ነው መሰል በሌሎች ሀገሮች ተብለው ተብለው ያለቀላቸው ነገሮች እኛ ሀገር ሲገቡ ልክ በዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ እንደምንሠራቸው መስለው ቁጭ ይላሉ፡፡ ሌላ ቦታ ተሠርተው፣ ችግሮቻቸው ታውቀው፣ ልምድ ተቀስሞባቸው፣ አዳዲስ አሠራሮችና…

The post ጊፍት ሪል እስቴት ወደፊት ወይስ ወደ ኋላ – አበበ ወርዶፋ appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

ከሰሞኑ አገራችን ኢትዮጵያን በተለይም ብሄራዊ ጥቅሟንና ደህንነቷን በተመለከተ ሁለት አቢይ ዜናዎች የአገራቸን የኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ ጉዳዮች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚመለከታቸዉን አገሮች የአየር ሞገደች ተቆጣጥረዉት ነበር። ከእነዚህ ዜናዎች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ ኢትዮጵያ፤…

The post ህዳሴም ሆነ ዉዳሴ ክህዝብ የሚደበቅ ምንም ነገር የለም! አርበኞች ግንቦት7 appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

(አቶ ዮናታን ተስፋዬ የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ ናቸው። ይህ ጽሁፍም ፓርቲን ወክለው ሳይሆን ራሳቸውን ወክለው የጻፉት ነው) ወቅታዊ አጀንዳ እና በቁንፅል የሚተው ባይሆንኝ ነው – በትግስት አንቡልኝ ጭቆና ሲበዛ ሰዎች ብዙ መንገድን ተጠቅመው መታገል ይሻሉ፡፡ የጭቆናውን ቀንበር ለመስበር ጨቋኙን ከመግደል አንስቶ ራስን እስከማቃጠል ድረስ የሚደርሱ በርካታ መንገዶችን ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡ ከአገዛዝ ሰንሰለት ራስን ነፃ […]

ከምርጫ ዘጠና ሰባት በኋላ በኢሕአዴግ አደረጃጀት ዉስጥ ትልቅ ቦታ የነበራት ናት። ከሴቶች አደረጃጀት ሃልፊ ነበረች። ከዚያም በአዲስ አበባ የኢሕአዴግ ጽ/ቤት የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ሆና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ትሰራለች። በአዲስ አበባ ይለ የኢሕአዴግ አባል የማያወቃት የለም። ከአዲስ አበባ የኢሕአዴግ ጽ/ቤት የድርጅቱ ጉዳይ ሃላፊነቷ በተጨማሪ በአዲስ አበባ የሴቶች መዋቅርም የአድን ክላስተር ሃላፊም ነበረች። አበባ ገብረ ሕይወት […]

ወያኔ ኤርትራ ውስጥ የሚገኝ አንድ የካናዳ የወርቅ ማእድን በአውሮፕላን መደብደቡን አፍቃሪ ወያኔ የሆኑ ድረ ገጾች “ወታደራዊ ምንጮችን” በመጥቀስ ዘግበዋል። ይሁንና እንኳን ድብደባው የጥቃቱን ውጤት ያሳያል ተብሎ የተለቀቀውም ፎቶ የውሸት መሆኑ ተረጋግጧል። አውራንባ ታይምስ አስተማማኝ ምንጮችን ጠቅሶ ድብደባውን ማረጋገጡን የዘገበ ሲሆን ዘገባውም በፎቶ ማስረጃ የታጀበ ነው። ይሁንና ፎቶው የሚያሳው ኤርትራ ውስጥ የተኪያሄደውን የአየር ጥቃት ውጤት ሳይሆን ቢቢሲ በኦገስት 9 2013 አንድ የወያኔ አየር ሃይል የእቃ ማጓጓዣ አውሮፕላን ሞቃዲሹ ውስጥ ተከስክሶ ሲጋይ የሚያሳይ የፎቶ ማስረጃን ነው። ይህም ፎቶ የተነሳው በሮይተርስ ሲሆን በቢቢሲ ድረ ገጽ ላይ ከዜናው ጋር በክብር ታትሞ ይገኛል።

Fake TPLF bombing

አውራምባ ታይምስ ግን ዜናውን እውነት ለማስመሰል ከርክሞ እውነተኛውን ምንጭ ሳይጠቅስ ለታዳሚዎቹ አቅርቧል። በዚህም ጥፋት የሚያሳይ ፎቶ የተደነቁ በርካታ ወያኔዎች “አየር ሃይሉን” በማወደስ አስተያየት ሰንዝረዋል። የካናዳው የሚሻዕ ወርቅ ማዕድን ካምፓኒ ግን አንዳንድ ሰራተኞቹ የተወሰኑ ማሽኖች ሆን ብለው ማበላሸታቸውን እና ጥገና አድርጎ ስራ መቀጠሉን በይፋ ገልጿል። መቼም አንድ ጋዜጠኛ በጄት ድብደባና በአውሮፕላን ወድቆ መከስከስ መካከል ያለውን ልዩነት ጠንቅቆ ይገነዘባል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። አውራምባ ታይምስ ላይ በጭስ ተሸፍኖ የሚታየው ከተማ ሞቃዲሹ እንጂ አስመራ አለመሆኑን ከቢቢሲ ዘገባ በቀላሉ መረዳት ይቻላል። ነው ወይንስ ሶማሊያና ኤርትራ ሳንሰማ “ያለምንም ቅደመ ሁኔታ” ተዋሃዱ?

ለማንኛውም ቢቢሲው የአውሮፕላን መከስከስን አስመልክቶ ያቀረበው ዘገባ እስከ ፎቶው እዚህ ገጽ ላይ ይገኛል።
http://www.bbc.com/news/world-africa-23628549

(ይህንን ጥቆማ ያቀረበውን አንድ ወዳጃችንን ሳላመሰግን አላልፍም)

Live in Addis. ኑሮ በአዲስ አበባ

ነፃነት ዘለቀ (ከአዲስ አበባ)

ትናንት ሲያቀብጠኝ ከአንድ ጓደኛየ ሞባይል እነዚያ አይሲስ የሚባሉ ጉግማንጉጎች እነዚያን 21 ክርስቲያን የግብፅ ዜጎች በሊቢያ አንድ የባሕር ዳርቻ ላይ አንገታቸውን ሲቀሉ የሚያሣይ ቪዲዮ አየሁ – እስከመጨረሻው መዝለቅ አልቻልኩምና ግን ዋናው ባራኪ በግራ እጁ የያዘውን ጩቤ ወደ እኛ ወደተመልካቾቹ ዘርግቶ እያስፈራራ ሲዝት አጠፋሁት።

ሙሉውን አስነብበኝ …

መጋቢት ፲፬(አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለኢህአዴግ መንግስት ቅርበት ያላቸው የመገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያ አየር ሃይል ኤርትራ ውስጥ የሚገኘውን ቢሻ የማእድን ማውጫ ኩባንያን መደብደቡን ቢዘግቡም፣  በኤርትራም ሆነ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል በይፋ የተሰጠ ማረጋጋጫም ሆነ ማስተባበያ አልተገኘም። ይሁን እንጅ የኩባንያው 60 በመቶ የአክሲዮን ባለቤት የሆነው ተቀማጭነቱ ካናዳ የሆነው ኩባንያ ፣ በማእድን ማውጫው ላይ  ባለፈው ሳምንት …

መጋቢት ፲፬(አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ሰሞኑን በሰሜን ጎንደር አካባቢ የታየውን የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ የአገሪቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ካለፈው ሃሙስ ቀን ጀምሮ በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ታዛዋል። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የአየር ሃይል አባላት ካለፈው ሃሙስ ጀምሮ ከግቢ እንዳይወጡ ሲታዘዙ የተወሰኑት ደግሞ ከደብረዘይት እና ድሬዳዋ አየር ሃይል  ወደ መቀሌ አምርተዋል። ብዛት ያለው የእግረኛ …

መጋቢት ፲፬(አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሶስቱ ሀገራት የፈረሙት ስምምነት በተለይ ባለፉት አራት ዓመታት በግድቡ ምክንያት በግብጽና በ ኢትዮጵያ መካከል  የነበረውን ውጥረት የሚያስቀር ነው ብሏል-አህራም። “የዓባይ ወንዝ ለሺህዎች ዓመታት በእግዚአብሔር ትእዛዝ ሲፈስ ኑሯል”ብለዋል የግብጹ ፕሬዚዳንት አል ሲ ሲ -ስምምነቱን ለመስማት በካርቱም ለተሰባሰቡ የተፋሰሱ ሀገራት ልኡካን ባደረጉት ንግግር። አል ሲሲ አክለውም፦”በመተባበር ትልቅ ነገር መፈጸም …

መጋቢት ፲፬(አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ፣ የተቋረጠውን የሰላም ድርድር በኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ ለማስጀመር የነበረው እቅድ ሳይሳቃ በመቅረቱ የልኡካን ቡድኑ ከኢትዮጵያ ለቆ ወጥቷል። እንደ ድርጅቱ መግለጫ ላለፉት 2 አመታት ሲደረግ የነበረው ጥረት፣ ለወደፊቱም ይቀጥላል። ኢትዮጵያ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች የሚለው መግለጫው፣ የአገሪቱን ችግር ፈትቶ ወደ ሰላምና ዲሞክራሲ ለመውሰድ ገዢው ፓርቲ የተለየ …

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፡- ‹‹የአ/አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ልዩ ሀ/ስብከት ነው›› የሚለውን ድንጋጌ ተገን አድርገዋል የወቅቱ ዋና እና ምክትል ሥራ አስኪያጆች ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ እንዲዛወሩ አዝዘዋል የሀ/ስብከቱ ብልሹ አሠራር የቀጠለው ‹ሥዩማኖቹ› በወቅቱ ሥራ ባለመጀመራቸው ነው ብለዋል ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ማቴዎስ፡- ተጠሪነታቸው ለቅዱስ ሲኖዶስም ለፓትርያርኩም የኾኑት ረዳት ሊቀ ጳጳሱ አልተስማሙበትም የረዳት ሊቀ ጳጳሱ ድርሻ ከሌሎች …

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ትናንት መጋቢት 13 ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ አገሪቱ የርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ልትገባ ትችላለች ሲል በድጋሚ አስጠንቅቋል። የሑቲ አማጽያን በበኩላቸው ወደ ደቡብ የመን የሚያደርጉትን ግስጋሴ ቀጥለዋል።

ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች በሮም ማራቶን በወንድም በሴትም አሸናፊ ሆነዋል። በጀርመን ቡንደስ ሊጋ የዘንድሮ ውድድር ባየር ሙይንሽን በሜዳው ለመጀመሪያ ጊዜ ሽንፈት ገጥሞታል። በስፔን ላሊጋ ባርሴሎና ዋነኛ ተፎካካሪው ሪያል ማድሪድን አሸንፏል። የሊቨርፑሉ ሽቴፋን ዤራርድ ከሜዳ በቀይ ካርድ ተሰናብቷል።

ጋዜጠኝነት ትልቅ ክብር የሚሰጠው፣ የራሱ የሆነ መርህና ስነ-ምግባር ያለው፣ ጠያቂነትን ብቻ ሳይሆን ተጠያቂነትንም በውስጡ የያዘ የሙያ መስክ ነው። ለዛም ነው ጋዜጠኛ የሕዝብ አንደበት፣ አይንና ጆሮ ነው የሚባለው። ሕዝብ በሚከበርበት ቦታ ሁሉ ጋዜጠኛም ይከበራል። ሕዝብ በሚዋረድበት፣ በሚታፈንበትና በሚዋከብበት ስፍራም ጋዜጠኛ ይዋረዳል፣ ይሳደዳል፣ ይታፈናል፣ ይዋከባል፣ ይታሰራል፣ ሲከፋም ይገደላል። ይህም በሕዝብ፣ በመንግሥትና በጋዜጠኛ መካከል ያለውን ቁርኝት በደንብ ያሳያል። […]

በዓለም ታሪክ በሰው ልጆች እልቂት ( የግፍ ጥፋት ) የሚጠቀሱ ብዙ ሰዎች አሉ ። ከነዚህ ውስጥ የሚያውቀውም የማያውቀውም የሚያውቀው ምናልባት አውስትሪያዊው አዶልፍ ሂትለርን ነው ( አንዳንዶች ሂትለር ራሱ በዘሩ አይሁድ…

The post እንደ አማራ ብጽፍ (ሄኖክ የሺጥላ) appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.


የጉዞው መሥራቾች

ትናንት(እሑድ መጋቢት 13 ቀን 2007 ዓም) በጨጨሆ የባሕል ምግብ አዳራሽ በተደረገ አንድ መርሐ ግብር ተጋብዤ ተገኝቼ ነበር፡፡ ‹ጉዞ አድዋ› ይባላል መርሐ ግብሩ፡፡
 ከዛሬ 119 ዓመት በፊት ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን በዓለም ታሪክ ያልተለመደ አዲስ ታሪክ ለመሥራትና ኢትዮጵያ የምትባለውን ሀገር የማይደረስበት ከፍታ ላይ ለማስቀመጥ ሲሉ ከመላዋ ሀገሪቱ አንድ ሆነው ወጥተው፣ አንድ ሆነው ወደ አድዋ ዘምተው ነበር፡፡ ያኔ ብዙዎቹ የተጓዙት በእግራቸው ጋራ ሸንተረሩን፣ አረሁን ገደሉን እየተሻገሩ በፍጹም ኢትዮጵያዊ ወኔና ሀገራዊ ፍቅር ነበር፡፡ ያ አንድነትና የሀገር ፍቅር ስሜት ነበር ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችንን ሊደግሙት እንጂ ሊረሱት የማይገባ ታሪክ እንዲሠሩ ያደረጋቸው፡፡

ይህንን የአድዋ መንፈስና ዝና፣ ክብርና ላቅ ያለ ኢትዮጵያዊነት ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ፤ አድዋ እንደ አንድ ተራ ሥነ ሥርዓት በምኒልክ አደባባይ የአበባ ጉንጉን ከማስቀመጥና ‹አስቦ ከመዋል› የዘለለ ትውልዳዊ ፋይዳ እንዲኖረው ለማድረግ፤ አድዋ እንደ ባለሞያ ጠጅ በየጊዜው ከጥንስሱ እየተቆነጠረ በየትውልዱ እንዲጠጣ ለማስቻል፤ እንደ ሰራፕታ ዱቄት በየዘመናቱ ቡኾ ውስጥ እንደ እርሾ እየተጨመረ እንዲበላ ለማብቃት፣ አድዋ ላይ የታየው የላቀ ኢትዮጵያዊነት አንደ ሜሮን ቅብዐት ከትውልድ ትውልድ ሳይቋረጥ እየፈላ የሁሉ ማጥመቂያ እንዲሆን የተነሡ ወጣቶች ያዘጋጁት መርሐ ግብር ነበር፡፡ እንደ አድዋ ዘማቾች ወኔ እንጂ ሌላ ሀብት የሌላቸው ወጣቶች፡፡ 
እነዚህ ወጣቶች አንድ አስደማሚ ተግባር ጀምረዋል፡፡ በየዓመቱ የአድዋ በዓል ከመከበሩ ቀደም ብለው ከአዲስ አበባ በመነሣት በእግራቸው ወደ አድዋ መዝመት፡፡ አባቶቻቸውና እናቶቻቸው በእግራቸው የተጓዙትን መንገድ እነርሱም በእግራቸው መከተል፡፡ የቀድሞ የአድዋ ዘማቾችን ስሜት  እየተጋሩ፣ ታሪካቸውን እያጠኑ፣ በየደረሱበት ለሚያገኙት ሁሉ የአድዋን የላቀ ኢትዮጵያዊነት እየሰበኩ፣ የትውልድን ቃል ኪዳን ማደስ፡፡

ተጓዦቹ ከመልስ በኋላ

በድንኳን እያደሩ፣ ያገኙትን እየቀመሱ፣ ከአራዊት ጋር እየታገሉ፣ ከተራራና ገደል ጋር እየተገዳደሩ፣ እየወደቁ እየተነሡ፣ እየታመሙ እየተፈወሱ፣ እየደከሙ እየጀገኑ፣ እያዘገሙ እየፈጠኑ ከአንድ ሺ ኪሎ ሜትር በላይ የሚሆነውን መንገድ በእግር ማቆራረጥ፡፡ አድዋ ላይ ተጉዘው የታሪክ ማርሽ በዘወሩ ጀግኖች ስም ራሳቸው እየሰየሙ፣ የመንፈስ ወራሽታቸን ማረጋገጥ፡፡  
የዘንድሮ ተጓዦች ስድስት ናቸው፡፡ ከስድስቱ አንዷ ሴት ናት፡፡ ጽዮን ትባላለች፡፡ በጉዞው ስሟ ደግሞ እቴጌ ጣይቱ፡፡ ከአንድ ሺ ኪሎ ሜትር በላይ የሚሆነውን መንገድ በእግሯ አቆራርጣ እንደ እቴጌ ጣይቱ አድዋ ላይ ሰንደቋን ተክላለች፡፡ መድረኩ ላይ ወጥታ የእቴጌን ታሪክና የጉዞውን ትዝታ ስትተርክ የሆነ የሚንፎለፎል ትኩስ ወኔ ከውስጧ እየወጣ ይገርፈን ነበር፡፡ እናለቅሳለንም፣ እንገረማለንም፣ እናጨበጭባለንም፡፡ የማትነጥፍ ሀገር፡፡
ከጉዞ አስተባባሪዎች አንዱ የሆነው መሐመድ ስለ ጉዞው ዓላማና ሂደት ሲገልጥ እርሱ ራሱ ከዐፄ ምኒሊክ ሠራዊት ጋር የዘመተ ነበር የሚመስለው፡፡ መቼም መሐመድ ስለ ኢትዮጵያ ሲያወራ መስማት በባለሞያ ካህን የተከሸነ ቅዳሴ እንደመስማት ያለ ነው፡፡ ያወጣዋል፣ ይተርከዋል፣ ያውም ከዕንባና ከስሜት ጋራ፡፡
እነዚህ ወጣቶች የዛሬ ዓመት በ2008 ዓም አንድ ታላቅ ታሪክ ሊሠሩ አስበዋል፡፡ የአድዋ አንድ መቶ ሃያኛ ዓመት ሲከበር አንድ መቶ ሃያ ተጓዦችን ይዞ ወደ አድዋ በእግር ለመዝመት፡፡ ወጣቶች ናቸው፡፡ ግን ልባቸው ሸምግሏል፤ ብዙ ሊስቧቸው የሚችሉ  ብልጭልጭ ነገሮች ነበሩ፤ ነገር ግን ሀገራዊውን ታሪክ መርጠዋል፡፡ ከሺ ኪሎ ሜትር በላይ የሚሆነውን መንገድ በእግር አቆራርጠው፣ የሀገራችንን ባንዴራ ከፍ አድርገው ፣ በየደረሱበት አድዋ ላይ የተገለጠውን ያንን ሁላችንንም የሚያኮራ ኢትዮጵያዊነት እየተረኩ በእግራቸው ሊጓዙ ተነሥተዋል፡፡

ጽዮን – እንደ እቴጌ ጣይቱ

እንደ እኔ እንደ እኔ አንድ ትውልድ ታሪኩን ሲያነሣ፣ በማንነቱ ሲኮራ፣ ታሪክም ለመሥራት ሲቆርጥ መደገፍ ይገባል እላለሁ፡፡ ወጣቶች ከሥነ ምግባር ሲወጡ፣ ማንነታቸውንና ታሪካቸው ሲረሱ፣ ለሀገራዊ ነገሮችም የእኔነት ስሜት ሲያጡ እንደምንወቅሰውና እንደምናዝነው ሁሉ፤ በሀገር ፍቅር ስሜት ሲነሡና ታሪካችንን ከፍ አድርገው በአዲሱ ትውልድ አዲስ መንፈስ ውስጥ ሊጽፉት ሲተጉም አብረናቸው መሥራት ይገባናል፡፡ ታሪካችንና ማንነታችን እንደማይዘነጋ ማረጋገጥ የምንችለው ተተኪው ትውልድ የእኔ ነው ብሎ በራሱ መንገድ ሊገልጠው ሲሞክር ካየን ብቻ ነው፡፡

የጉዞው አስተባባሪ ያሬድ ሹመቴ

እናግዛቸው፣ አብረናቸውም እንቁም፤ የቻልን የጉዟቸውን ወጭ እንጋራ፣ ያልቻልን በሚደርሱበት ቦታ ሽሮ ሠርተን ውኃ ቀድተን በማስተናገድ የጥንት አያቶቻችን የአድዋ ዘማቾችን የሸኙበትን ታሪክ እንድገመው፡፡ በሚደርሱባቸው ቦታዎች ያሉ ትምህርት ቤቶች ደግሞ ወጣቶቹ ከተጓዦቹ  ጋር ስለ ታሪካቸው እንዲወያዩ መርሐ ግብር ያዘጋጁ፡፡ የእምነት ተቋማት ደግሞ በሚደርሱባቸው ቦታዎች በመቀበል ለታሪካችንና ማንነታችን ያለንን የከበሬታ ሥፍራ እናሳይ፡፡ በየቦታው የምንገኝ ኢትዮጵያውያንም በየደረሱበት ቦታ እየተቀበልን ባንዴራውን ከፍ አድርገን በማሻገር የታሪክ ተረካቢነታችን እናረጋግጥ፡፡ አንድ መቶ ሃያኛውን የአድዋ በዓል፣ በ2008 ዓም ከአበባ ማኖር በዘለለ በማይረሳ የወጣቶች ታሪካዊ ጉዞ እናክብረው፡፡  
ጠቢብ አስቦ ይሠራል
ጎበዝ ደግሞ ከሚሠሩት ጋር ያብራል፡፡     

ዱካውን በአፍጋኒስታንና ፓኪስታን አሳርፎ ሰሜንና ምዕራብ አፍሪቃ መድረስ ችሏል። ከናይጄሪያው ሌላኛው አሸባሪ ድርጅት ቦኮሃራም ጋር መወዳጀቱ፣ በሊቢያ መንሰራፋቱ ይነገርለታል። አሸባሪው ቡድን በሊቢያ የግብፅ ኦርቶዶክሶችን አንገት ለካራ መዳረጉ የቅርብ ትዝታነቱ ገና ሳይዘነጋ፤ በደም የታጠበ እጁን በንዑሷ ቱኒዝያ ለተጨማሪ ጥፋት መዘርጋቱ አልቀረም።

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ዕሁድ፡- ራዲዮ መፅሔት፣ መስተዋት (የወጣቶች ፕሮግራም) – ሁለቱ ዝግጅቶች በየሣምንቱ ይፈራረቃሉ፡፡

ከፍያለው ጌጡ ጠቅላይ ሚኒ ኃይለማርያም ደሳለኝ ትናንትና በጅማ ከተማ ተገኝተው ይህን አድርገን ነጻነት አመጣን ዲሞክራሲን እየቀዳን ለህዝቡ አከፋፈልን አሉ። የጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪወች እንዳደረሱኝ መረጃ ከሆነ ሚኒ ኃይለማርያም ኔትወርክ አዘግተው በጅማ…

The post ማንኛውም ተቃዋሚ ድርጅት ስርዓት ከለለው አቅም አለን ከርቸሌ እንከተዋለን የሚል ማስፈራርያ ወዲ ኃይለማርያም ደሳለኝ አሰሙ appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ10ኛው ዙር የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የማውጣት ሂደት 35 ሺህቤቶችን ባለ ዕድለኞች በዕጣ አስተላለፈ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ በከተማዋ ያለውን የቤት ፍላጎት ለማርካት እያስገነባቸው ካት ቤቶች ከ95 በመቶ በላይ የተጠናቀቁትንና መሰረተ ልማት የተሟላላቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ነው ለባለ ዕድለኞች ያስተላለፈው፡፡

በዕጣ የተላለፉት ቤቶች በባሻ ወልዴ፣ በልደታ መልሶ ማልማት፣በየካ አባዶ፣በቦሌ ቡልቡላ፣በገነት መናፈሻና በቱሉ ድምቱ ሳይቶች የሚገኙ ናቸው፡፡

እሁድ መጋቢት 13 ቀን 2007 በይፋ…

‹‹ቤተሰቦቻቸው ምግብና ልብስ ማስገባታቸውን ሰምተናል›› ሰማያዊ ፓርቲ የሰማያዊ ፓርቲ የአደረጃጀት ጉዳይ ምክትል ኃላፊ የነበሩት አቶ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ፣ የምክር ቤት አባል የነበረችው ወ/ሪት ኢየሩሳሌም ተስፋውና የሕዝብ ግንኙነት ኮሚቴ አባል አቶ…

The post ሦስት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል ድንበር ሊያቋርጡ ሲሉ መያዛቸው ተሰማ appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

– ጥቃቱ የውስጥ አሻጥር ይሁን የሚሳኤል አሊያም የተፈጥሮ ጥቃት እስካሁን አለየለትም::  የኤርትራ የወርቅ ማእድን ማውጫዎች በጋሽ ባርካ ቢሻ እና ማይ እንደጋ ዴፖዎች ካልታወቀ (ካለየለት)ሃይል ጥቃት እንደተፈጸመበት ተሰማ::ጥቃት የተፈጸመባቸው ዲፖዎች አርብ…

The post የኤርትራ ቢሻና ማይ እንደጋ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ዲፖዎች ጥቃት ደረሰባቸው:: appeared first on ሳተናው (Satenaw) -Latest Ethiopian News & Breaking News.

የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ በሃገራችን ኢትዮጵያ አስተማማኝና ዘለቄታዊ ሠላም፣ እኩልነት፣ ፍትህና፣ የፖለቲካ መረጋጋት ይሰፍን ዘንድ ቀና ራዕይ አንግበው በተሰባሰቡ ወጣት ኢትዮጵያውያን የተመሰረተ፤ በሃገራችን ብቸኛው በወጣቶች የተገነባና የሚመራ ንቅናቄ ነው። ንቅናቄአችን ላለፋት አመታት የንቅናቄውን አቅም ለማጐልበት፤ ሰፊና ጠንካራ መሰረት ያለው ሁለገብ ተቋም ለመገንባት፤ የድርጅታዊ መዋቅሩን ጨምሮ ሌሎች ወሳኝ መሰረታዊ የማስፋፋትና የማደራጀት ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል። በመሆኑም ዛሬ […]

ሰማያዊ ፓርቲ ባህር ዳር ቅርንጫፍ ቢሮው እንደተዘጋበት አስታወቀ:: በጋሞ ጎፋ በቅስቀሳ ላይ የነበሩ የሰማያዊ አባላት ታሰሩ:: የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍና የምርጫ ቅስቀሳ ለማካሄድ የመረጣቸውን 15 ከተሞች ይፋ አደረገ፡፡ ትብብሩ በተመሳሳይ ሰዓት በ15 ዋና ዋና የሀገሪቱ ከተሞች ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ለማድረግ ቀደም ብሎ አሳውቆ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በዚህ መሰረት የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር መጋቢት 20/2007 […]

ዘመናዊቷ እሥራኤል፣ እ ጎ አ ግንቦት 14 ቀን 1948 ዓ ም ፤ መንግሥት ከመሠረተችበት ጊዜ አንስቶ ፣ ከፍልስጤማውያንና ከዐረብ መንግሥታት ጋር ተደጋጋሚ ጦርነቶች ተካሂደው እንደነበረ የሚታወስ ነው።የኦስሎውን ስምምነት ጨምሮ በጠቅላላ ከ 14 የማያንሱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፊታችን እሁድ ለሚወጡ 35 ሺህ የ20/80 እና 10 /90 የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ውስጥ ለመካተት ብቁ የሆኑ ነዋሪዎች ቁጥር ይፋ ሆነ።

እሁድ ዕለት እጣ ከሚወጣባቸው 35 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ የ10/90 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ቁጥር 960፣ የ20/80 ስቱዲዮ 6 ሺህ 768፣ ባለ 1 መኝታ 15 ሺህ 638፣ ባለ 2 መኝታ 7 ሺህ…

ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።

ቅዳሜ፡- ከዚህም ከዚያም፤ የሙዚቃ ቃና

ከ 20 ዓመታት በላይ በሶማሊያ የተረጋጋ መንግሥት አይስተዋልም። ስለሆነም በሀገሪቱ ይፋና መደበኛ የሆነ የባንክ አሰራር ስርዓት የለም። ለአመታት በዘለቀው የርስ በዕርስ ጦርነት ምክንያት በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ሰዎች ከሀገራቸው ተሰደዋል።