የአኒታ ፓወል ማስታወሻ – በኢትዮጵያው ምርጫ 2007 ላይ – ግንቦት 28, 2015
Anita Powell’s Reporter’s notebook on Ethiopia’s Election 2015
Anita Powell’s Reporter’s notebook on Ethiopia’s Election 2015
መድረክ የእሁዱን ምርጫ ውጤት አልቀበልም አለ የኢትዮጵያ ፌዴራሊያዊ አንድነት መድረክ ባለፈው እሁድ የተካሄደውን አምስተኛው አገር አቀፍ አጠቃላይ ምርጫ ውጤትን እንደማይቀበል ገለፀ። የመደረክ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥ በምርጫው ሂደት ላይ ችግሮች የነበሩ በመሆኑ ውጤቱን አንቀበልም ብለዋል። መድረክ በምርጫው አጋጥመውኛል ያላቸውን ችግሮች ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማሳወቁን ነው ያመለከቱት። ማምሻውን አዲስ አበባ አፍንጮ በር […]![]()
Anna Gomez and Ted Dagne about Ethiopia’s 2015 Election, African and Ethiopian politics. 05-27-15
በዚህ በተጨማለቀ የበርጫ ቦርድ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ባላገጠ ምርጫ ሳይሆን ምርጫ የሚባለው የፈለግነውን ካልወደድነው ለይተን መምረጥና ይህም ሲከበር ስለሆነ አንድ ፓርቲ ያውም አናሳ የግለሰቦች ጥርቅም መከላከያውንም ደህንነቱንም ፌደራል ፖሊሶችንም ፋይናስና ያገሪትዋን ቁልፍ ቦታዎችን ተቆጣጥሮ ነፃ ሚዲያ ገለልተኛ ምርጫ ቦርድ ተቃዋሚዎች ያለ ተፅህኖ መንቀሳቀስና መቀስቀስ ባልቻሉበት መድረክ ላይ በሆድ አደር የምርጫ አስፈሳሚ ነን ባዮች ነገር ግን የበግ […]![]()
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ
ሚያዝያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን በሃመር ወረዳ በዲመታ ከተማ እና አካባቢዋ የሚኖሩ አርብቶአደሮች ” እኛ ድምጽ ሳንሰጥ” እንዴት ኢህአዴግ አሸነፈ ይባላል በሚል ከሰኞ ጀምሮ ከጸጥታ ሃይሎች ጋር መጋጨታቸው ታውቋል። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ነዋሪዎቹ በምርጫው ማግስት የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ሲጀመሩ በጸጥታ ሃይሎች የተከለከሉ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎ አርብቶአደሩ …
ሚያዝያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወ/ሮ ንግስት በደቡብ ክልል የምርጫ ቅስቀሳ አድርጋ ስትመለስ መታሰሩዋን ባለቤቱዋ ለኢሳት የገለጸ ሲሆን፣ የ3 አመት ህጻን ልጇም አብራ ከታሰረች በሁዋላ እንደመለሱለት አክሏል። ለምርጫ ቅስቀሳ ወጥተው የነበሩ ብዙ ወጣቶች እየተፈለጉ መሆኑን መረጃው እንደደረሳትና እርሱዋም እንደምትታሰር አውቃ ወደ አዲስ አበባ መመለሱዋን ባለቤቱ ገልጿል። በአዲስ አበባ አይ ኤስ ኤስ …
ሚያዝያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች ግንቦት 19/2007 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ አሉኝ ባላቸው ሲ.ዲዎች እና ቀሪ ምስክሮቹ ላይ ብይን ሰጥቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ ምስክሮቹን ለማቅረብ በተደጋጋሚ የሰጠውን እድል ባለመጠቀሙ እና ምስክሮቹን ላለማቅረቡ የሰጠው ምክንያትም በቂ ባለመሆኑ አቃቤ …
ርምጃው የሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ፣ አመራሩ እንዲቀየር የጻፉትን ደብዳቤ መነሻ ያደረገ ነው ለጥያቄአቸው ምላሽ ባለማግኘታቸው በፓትርያርኩ ላይ ቅሬታቸውን በመዝሙር ገልጸው ነበር ከ200 በላይ አባላት የሚማሩበት አዳራሽና የሰንበት ት/ቤቱ ጽ/ቤት ቁልፎች ተሰብሮ ታሽግዋል የደብሩ ስምንት አመራሮች ከመሳለም በቀር ወደ ደብሩ ገብተው እንዳይሰበሰቡ ተከልክለዋል * * * በካህናትና በምእመናን አንድነት መመራት ባለበት ደብር የአለቃው ዓምባገነንነት ሰፍኖበታል ሰበካ ጉባኤ …![]()
ገና ከጅምሩ፣ የተቃዋሚ ፓርቲወችን በመበታተን፣ መሪዎችንና አባላቶቻቸውን በማሰር፣ በማሳደድና በማዋከብ፤ ነጻ የሃሳብ ልውውጥ እንዳይኖርና አማራጭ ሃሳቦች ለህዝብ እንዳይደርሱ ነጻ የመገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞችንና ጦማራውያንን በግፍ ወደ እስር ቤት በመወርወርና የሚወዷትን ሀገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ በማድረግ፤ ከአገዛዙ ጋር እጅና ጓንት ሆኖ በጭቆና መሣርያነት የሚያገለግለውን የምርጫ ቦርድ በመጠቀም ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በማፈራረስ የጀመረው ምርጫ ተብየ በትናንቱ እለት ተካሂዷል። በዚህ ምርጫ […]
የ”ምርጫው” ድራማ እየተተወነ ሳለ፤ የቦርዱ ሊቀመንበር ዶ/ር መርጋ በቃና እና ምክትል ሊቀመንበሩ ዶ/ር አዲሱ ገብረእግዚአብሔር ለአቦይ ስብሃት ስልክ ደወሉ። “ሃሎ?” “ሃሎ፣ አቦይ ስብሃት ኖት?” “ነኝ፣ ምን ፈለግክ?” “ዶ/ር መርጋ በቃና እና ዶ/ር አዲሱ ገብረእግዚአብሔር ነን።” “ችግር መስማት አልፈልግም። የታዘዛችሁትን አደረጋችሁ?” “99.8% ህዝብ አልመረጠንም። ግን በታዘዝነው መሰረት ውጤቱን ገልብጠነዋል!” “0.2% ብቻ ነው የመረጠን ማለት ነው?” “አዎን […]
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአሁኑ ሰዓት እየሰጠ ባለው መግለጫ፣ እስካሁን በደረሰው ጊዜያዊ ውጤት መሠረት ኢሕአዴግና አጋሮቹ 434 የፓርላማ ወንበሮችን ማግኘታቸውን አስታወቀ፡፡ በቦርዱ ጊዜያዊ ውጤት መግለጫ መሠረት ኢሕአዴግ ከአጋሮቹ ጋር መንግሥት መመሥረት የሚያስችለው ውጤት አግኝቷል፡፡
በቦርዱ መግለጫ መሠረት ኢሕአዴግ በአዲስ አበባ ሃያ ሦስቱንም የፓርላማ ወንበሮች የተቆጣጠረ ሲሆን፣ እስካሁን በተገኘው ውጤት መሠረት ከትግራይ ክልል 38 የፓርላማ ወንበሮች 31 ማግኘቱ ተረጋግጧል፡፡

ባለፈው እሑድ ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. በተካሄደው የምርጫ 2007 የድምፅ አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ላይ የታየው ለየት ያለ ክስተት፣ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ታዛቢዎች ጉዳይ ነው፡፡
አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ ሪፖርተር በተሰማራባቸው ብዙዎቹ የክልል ከተሞች በአብዛኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ታዛቢዎችን ማግኘት አዳጋች ነበር፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በገዥው ፓርቲ ጫና ታዛቢዎቻቸው እንዳልተገኙ ቢገልጹም፣ በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች በብዙዎቹ የምርጫ ጣቢያዎች ታዛቢዎች ለማሰማራት አለመቻላቸው እንቆቅልሽ ሆኗል፡፡ በተወሰኑ ሥፍራዎች የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተወካዮች በበጀት እጥረት ምክንያት ታዛቢ ማሰማራት አለመቻላቸውን በግልጽ ሲናገሩም ተደምጧል፡፡ በአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ታዛቢ አለማስቀመጣቸው የገረማቸው ብዙ ሰዎች፣ ራቅ ወዳሉ አካባቢዎች እንዴት ሊያሰማሩ ይችላሉ ብለው ትዝብታቸውን ገልጸዋል፡፡ ብዙዎቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች ታዛቢ ላለማሰማራታቸው ምክንያቱ የገዥው ፓርቲ አፈናና ጫና ከመጠን በላይ በመሆኑ ነው ቢሉም፣ በሁሉም ሥፍራዎች የሚገኙ የምርጫ አስፈጻሚዎች ግን አስተባብለዋል፡፡ በበርካታ ቦታዎች የተቃዋሚ ፓርቲዎች ፖስተሮችና ባነሮችም አልታዩም፡፡ ከገዥው ፓርቲ ጋር ሲነፃፀሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለምርጫው ዝግጅት ያደረጉም አይመስሉም፡፡ ሪፖርተር በአዲስ አበባና በተለያዩ የክልል ከተሞች በመሰማራት የተዘጋጁ የተለያዩ የምርጫ ዘገባዎች በውስጥ ገጾች ሠፍረዋል፡፡

በምዕራብ ሸዋ ዞን በአምቦና አካባቢዋ የሚደረገው ምርጫ ጠንካራ ፉክክር የሚታይበት በመሆኑ የብዙዎችን ቀልብ ይስባል፡፡ ለዚህም የተለያዩ ምክንያቶች ይጠቀሳሉ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ)
የትጥቅ ትግል በሚያካሂድበት ወቅት በ1983 ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ ያደርግ የነበረውን ግስጋሴ፣ በአምቦ አካባቢ ሕዝብ ድጋፍ የነበረው ወታደራዊ ደርግ የኢሕአዴግን ጥቃት መመከት ችሎ ነበር፡፡ በዚያ ወቅት የአምቦና አካባቢዋ ሕዝብ ከደርግ ሠራዊት ጋር ተባብሮ በፅናት መዋጋቱ ይነገራል፡፡
ይሁን እንጂ በስተኋላ ኢሕአዴግ ኃይሉን አጠናክሮ በአምቦና በጉደር ከተሞች አካባቢ የነበረውን የደርግ መከላከያ መስመር ጥሶ አዲስ አበባን ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. መቆጣጠሩ የሚታወስ ነው፡፡ የኢሕአዴግና የአምቦ አካባቢ ሕዝብ ቁርሾ የሚጀመረው ከዚያን ወቅት ነው፡፡
ኢሕአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ በሚያካሂዳቸው አገራዊ ምርጫዎች በአብዛኛው ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሲያሸንፉ ቆይተዋል፡፡ በተለይ የአካባቢው ተወላጅ የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና ሰፊ የሕዝብ ድጋፍ የነበራቸው በመሆኑ፣ ቀደም ሲል ይመሩት የነበረው የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኦብኮ) በምዕራብ ሸዋ ዞን በአብዛኛው ጊዜ ሲያሸንፍ ቆይቷል፡፡
ይህ ታሪክ በምርጫ 2002 ተቀይሮ ኦሕዴድ/ኢሕአዴግን ወክለው የተወዳደሩትና የምዕራብ ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ዮሐንስ ምትኩ ዶ/ር መረራን አሸንፈዋል፡፡ በዘንድሮ አምስተኛ አገር አቀፍ ምርጫ በዶ/ር መረራ የኦሮሞ ሕዝቦች ኮንግረስና በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ይመራ የነበረው ኦፌዴን ጥምረት ከሆነው ከኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና ኦሕዴድ/ኢሕአዴግ ማን ያሸንፍ ይሆን የሚለው ጥያቄ በምዕራብ ሸዋ ዞን የሚካሄደውን ምርጫ አጓጊ አድርጎታል፡፡
ኦፌኮ የአራት ፓርቲዎች ጥምረት የሆነውን መድረክ ወክሎ ወደ ምርጫ ገብቷል፡፡ በዚህና በሌሎች ምክንያቶች በርካታ የአገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙኃን ዘጋቢዎቻቸውን ወደ ምዕራብ ሸዋ ዞን አሰማርተዋል፡፡
የምርጫ ዋዜማ
በምርጫው ዋዜማ ቅዳሜ ግንቦት 15 ቀን 2007 ዓ.ም. የአምቦ ከተማ ሕዝብ የተለመደውን የዕለት ተዕለት ኑሮውን በማካሄድ ላይ ነበር፡፡ በከተማው የተጠናከረ ጥበቃ መኖሩ ታይቷል፡፡ በርካታ ቁጥር ያላቸው የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት አምቦና አካባቢዋን በመዘዋወር ሲጠብቁ ነበር፡፡ የኦሮሚያ ፖሊስ አድማ በታኝ ኃይል ከነሙሉ ትጥቁ በየፖሊስ ጣቢያው ሰፍሯል፡፡
ከአምቦ በ12 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በጉደር ከተማ በተመሳሳይ የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት ሲዘዋወሩ የነበረ ሲሆን፣ አድማ በታኝ ኃይልም ዝግጁ ሆኖ ሲጠባበቅ ማየት ተችሏል፡፡ በተጨማሪም በአምቦና በጉደር አካባቢ የፌዴራል ፖሊስና የመከላከያ ሠራዊት አባላት በፒክአፕ ተሽከርካሪዎች ዋናውን አስፋልት መንገድ ፓትሮል ሲያደርጉ ተስተውሏል፡፡
የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተሞች የጋራ ማስተር ፕላን ዝግጅት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ መፍጠሩ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ በወቅቱ የአምቦ ከተማ ወጣቶች ከፀጥታ ኃይሎች ጋር ተጋጭተው የሰዎች ሕይወት መጥፋቱ በምርጫው ሒደት ላይ የራሱን ተፅዕኖ ይፈጥራል የሚል እምነት በብዙዎች ዘንድ አሳድሯል፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ምክንያቶች በአምቦ የሚካሄደውን ምርጫ ውጥረት የሰፈነበት እንዲሆን አድርገውታል፡፡
በአምቦ ከተማ በምርጫው ዋዜማ ሪፖርተር ያነጋገራቸው ባለባጃጆችና ቡና ቤቶች ሥራ ከቀዘቀዘ አምስት ስድስትና ቀናት እንደተቆጠሩ ተናግረዋል፡፡ በተለይ ከ12 ሰዓት በኋላ አብዛኛው የአምቦ ከተማ ነዋሪ ወደ መኖሪያ ቤቱ ከቷል፡፡ ምግብ ቤትና መጠጥ ቤቶች ማምሻውን ጭር ብለው ተስተውሏል፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ሆቴልና አበበች መታፈሪያ ያሉ ትላልቅና ታዋቂ ሆቴሎች የምግብ አዳራሾቻቸው ውስጥ በጣት የሚቆጠሩ ደንበኞች ብቻ ሲስተናገዱ ታይተዋል፡፡
የምርጫ ዝግጅት
የምዕራብ ሸዋ ዞን የምርጫ አስተባባሪና የአምቦ አንድ የምርጫ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሁንዴሳ ማዴሳ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በምዕራብ ሸዋ ዞን ለምርጫ የተመዘገቡ መራጮች ቁጥር 533,444 ነው፡፡ በዞኑ 11 የምርጫ ክልል 862 የምርጫ ጣቢያዎች ይገኛሉ፡፡ አሥር ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩዎቻቸውን ማስመዝገባቸውን አቶ ሁንዴሳ ተናግረዋል፡፡ ለተወካዮች ምክር ቤት 62፣ ለክልል ምክር ቤት 137 በአጠቃላይ 199 ዕጩዎች ተመዝግበዋል፡፡ ከዕጩ ተወዳዳሪዎቹ ውስጥ 176 ወንድ፣ 23 ሴቶች ናቸው፡፡
ለጋዜጠኞች መረጃ ያለመታከት ይሰጡ የነበሩት አቶ ሁንዴሳ፣ በምርጫ ዋዜማ ለምርጫ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች በሰዓቱ መድረሳቸውን አረጋግጠዋል፡፡ በከተማ ለሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ድንኳንና መብራት እንዲገባላቸው የተደረገ ሲሆን፣ በገጠር ለሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ዳስ፣ የእጅ ባትሪዎችና ሻማ ተገዝቶ መላኩን አስታውቀዋል፡፡
ከአዲስ አበባ በስተ ምዕራብ 114 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው የአምቦ ከተማ ስድስት ቀበሌዎች (ሦስት የከተማ፣ ሦስት የገጠር ቀበሌዎች) ሕዝብ ብዛት ከ100,000 በላይ ይገመታል፡፡ በአምቦ ከተማ 31 የምርጫ ጣቢያዎች ይገኛሉ፡፡ በአምቦ ከተማ 22,849 ነዋሪዎች በመራጭነት ተመዝግበዋል፡፡ በሦስቱ የገጠር ቀበሌዎች 33,169 ነዋሪዎች በመራጭነት ተመዝግበው ካርድ ወስደዋል፡፡
በአምቦ ከተማ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዘጠኝ፣ ለክልል ምክር ቤት ደግሞ 18 ተወዳዳሪዎች ቀርበዋል፡፡ ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ኦሕዴድ (ኢሕአዴግ)፣ ኦፌኮ (መድረክ)፣ የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)፣ ሰማያዊ ፓርቲ፣ ቅንጅት፣ አንድነት፣ መላው ኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (መኦሕዴፓ)፣ መኢብንና የገዳ ሥርዓት አራማጅ ፓርቲ (ገሥአፓ) ናቸው፡፡
ፀጥታን በተመለከተ ዞን፣ ወረዳ፣ ቀበሌ እስከ ምርጫ ጣቢያ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጎ የአካባቢው፣ የዞን ፖሊስና የአካባቢው ፀጥታ ዘርፍ አካላት ጋር በመቀናጀት ሚሊሻና ታጣቂዎችን በማደራጀት አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን አቶ ሁንዴሳ ተናግረዋል፡፡
ተፎካካሪ ፓርቲዎች የምርጫ ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት እስከ ግንቦት 13 ቀን 2007 ዓ.ም. ሰላማዊ የምርጫ ቅስቀሳ ማካሄዳቸውን ገልጸዋል፡፡ ከምርጫው ቀደም ሲል የዞኑ የምርጫ ቦርድ ጽሕፈት ቤት ለፖለቲካ ፓርቲዎቹ በምርጫ ሕጉ ዙሪያ ትምህርት ሰጥቷል፡፡ ‹‹የምርጫ ሥነ ምግባር ደንብን በተመለከተ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ጋር ውይይት አካሂደናል፡፡ ምንም እንኳ መድረክ የሥነ ምግባር ሕጉን ባይፈርምም በውይይቱ ተካፋይ ሆኗል፤›› ያሉት አቶ ሁንዴሳ ኢሕአዴግ፣ መድረክና ገሥአፓ የሚገኙበት የጋራ መድረክ አቋቁመው በሥነ ምግባር ሕጉ ዙሪያ ሲወያዩ ቆይተዋል ብለዋል፡፡
ተፎካካሪ ፓርቲዎች ሰላማዊ የምርጫ ቅስቀሳ ማካሄዳቸውን ገልጸዋል፡፡ በአምቦ ከተማ የኦሕዴድ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሸናፊ ጨመዳ ለሪፖርተር እንደገለጹት ፓርቲያቸው ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ነፃና ፍትሐዊ እንዲሆን አቅዶ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡ ‹‹የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ አቋቁመን የሚገጥሙንን ጥቃቅን ችግሮች በሰላማዊ መንገድ ስንፈታ ቆይተናል፤›› ያሉት አቶ አሸናፊ፣ ፖስተር ተቀዳደደብኝ የሚሉ ቅሬታዎች ከገዢው ፓርቲና ከመድረክ መቅረባቸውን፣ የምርጫ ቅስቀሳ በተከለከሉ ሥፍራዎች (እንደ ትምህርት ቤት ባሉ ቦታዎች) ማካሄድና ያልተገቡ ዘፈኖች (ግጭት ሊጭሩ የሚችሉ) ማሰማት ችግሮች በመድረክ በኩል ነበሩ፡፡ ‹‹እነዚህንና የመሳሰሉትን ችግሮች ቦርዱም ባለበት የጋራ መድረክ ተነጋግረን ፈተናቸዋል፤›› ብለዋል፡፡ ከዚህ ውጪ ቅድመ ምርጫው ሰላማዊ እንደነበር አቶ አሸናፊ አረጋግጠዋል፡፡
ኦፌኮ/መድረክ በአምቦ፣ በጉደርና በሌሎችም ከተሞች ሰፊ የቅስቀሳ ዘመቻ አካሂዷል፡፡ ከምርጫው አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ በአምቦ ከተማ በርካታ ሕዝብ የተሳተፈበት ስብሰባ አካሂዷል፡፡ የኦፌኮ ሊቀመንበርና የመድረክ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር መረራ ጉዲና ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ መድረክ የተሳካ የምርጫ ቅስቀሳ አካሂዷል፡፡ ‹‹ከምርጫ 97 የበለጠ የቅስቀሳ ሥራ ሠርተናል፤›› ያሉት ዶ/ር መረራ፣ ‹‹ሜዳው የተስተካከለ ባይሆንም ችግሮችን ተቋቁመን ሰፊ የቅስቀሳ ሥራ ሠርተናል፤›› ብለዋል፡፡
ዶ/ር መረራ በቅስቀሳ ወቅት በአምቦና በጉደር ከተሞች ችግር እንደገጠማቸው ተናግረዋል፡፡ ‹‹ትምህርት ቤት፣ ቤተ ክርስቲያን አለ እያሉ የምርጫ ቅስቀሳ እናዳናካሂድ ከልክለውናል፡፡ በገበያ ቀንም ቅስቀሳ እንዳናካሂድ ተከልክለናል፡፡ ተማሪዎች እንዳይገኙልን በዕረፍት ቀን (ቅዳሜና እሑድ) ከልክለው በሥራ ቀን እንድናካሂድ ያደርጋሉ፤›› ሲሉ ወቀሳቸውን አቅርበዋል፡፡
አያይዘውም ‹‹አጠቃላይ የምርጫውን ሒደት ያበላሸው አንድ ለአምስት የሚሉት ፖለቲካ ነው፡፡ የቀበሌ አለቆች ሕዝቡን ድምፅ የምትሰጡት በተደራጀ መልክ ነው በማለት፣ ሕዝቡ ድምፁን ለገዢው ፓርቲ እንዲሰጥ እየተደረገ ነው፤›› ብለዋል፡፡
የምርጫ ዕለት
እሑድ ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. የአምቦና የጉደር ከተማ ነዋሪዎች ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ በየምርጫው ጣቢያ ተሰልፈዋል፡፡ በተለይ በጉደር ከተማ መራጩ ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ለመምረጥ ረዥም ሠልፍ ይዞ ተስተውሏል፡፡
በአምቦ ሪፖርተር በተዘዋወረባቸው የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫው ሒደት በሰዓቱ (ከጠዋቱ 12 ሰዓት) መጀመሩን ተመልክቷል፡፡ በየምርጫ ጣቢያው አምስት የሕዝብ ታዛቢዎች የድምፅ አሰጣጥ ሒደቱ ከመጀመሩ አስቀድመው ተገኝተዋል፡፡ በእነዚህ የምርጫ ጣቢያዎች ተወካዮቻቸውን ያስቀመጡት ኢሕአዴግ፣ መድረክና ኢዴፓ ብቻ ናቸው፡፡ የተቀሩት ስድስት ፓርቲዎች በአብዛኛው ጣቢያዎች ታዛቢዎቻቸውን እንዳላስቀመጡ ታይቷል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ተወካይ አቶ አዲሱ ፈቃዱ ፓርቲያቸው በሰው ኃይልና በበጀት እጥረት ምክንያት ተወካዮቹን በየምርጫ ጣቢያው ማስቀመጥ እንዳልቻለ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ የገሥአፓ ተወካይ አቶ አሸናፊ ጅፋራ ድርጅታቸው በተቻለ መጠን በአብዛኛው ምርጫ ጣቢያቸው ታዛቢዎች የመደበ ቢሆንም፣ በሰው ኃይልና በበጀት እጥረት ሁሉንም የምርጫ ጣቢያ ማዳረስ እንዳልቻለ አስረድተዋል፡፡
በአምቦ ከተማ በእያንዳንዱ ምርጫ ጣቢያ የተመዘገበው ሕዝብ በአማካይ ከ600 እስከ 700 ነው፡፡ የምርጫ አስፈጻሚዎቹ በሚገባ የሠለጠኑ ይመስላሉ፡፡ ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. ማለዳ በአምቦ ከተማ ሪፖርተር ከደረሰባቸው በርካታ የምርጫ ጣቢያዎች መካከል በ03-ሀ-1፣ በ01-ለ-2፣ 02-ሀ-12፣ 04-ሀ-2እና በሌሎችም ጣቢያዎች መራጩን ሕዝብ በተቀላጠፈ ሁኔታ ሲያስተናግዱ ታይተዋል፡፡ በመሆኑም ማለዳ የታየው ሠልፍ ረፋዱ ላይ (ከአራት ሰዓት በኋላ) በብዙ የምርጫ ጣቢያዎች አልታየም፡፡
በየምርጫ ጣቢያው መራጮች ድምፅ ከመስጠታቸው በፊት ስለ ድምፅ አሰጣጡ በቂ ማብራሪያ የተሰጣቸው ቢሆንም፣ በዕድሜ የገፉ አዛውንቶች በድምፅ መስጠቱ ሒደት ላይ ግራ ሲጋቡ ታይተዋል፡፡ አንዳንድ አዛውንቶች የድምፅ መስጫ ወረቀቱን ምን ማድረግ እንዳለባቸው አያውቁም፡፡ አንድ እናት የድምፅ መስጫ ወረቀቱን በሚስጥር ድምፅ መስጫ ክፍል ውስጥ አስቀምጠው ሲወጡ ተስተውሏል፡፡
በአምቦ ከተማ ሪፖርተር በተዘዋወረባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ሕዝቡ በሰላማዊ መንገድ ድምፁን ሰጥቶ ሲወጣ ታይቷል፡፡ በምርጫ ጣቢያ 03-ሀ-1 ድምፃቸውን ሰጥተው ሲወጡ ሪፖርተር ያገኛቸው ሻለቃ ታምራት ዓሊ፣ በድምፅ አሰጣጡ ሒደት መርካታቸውን ገልጸዋል፡፡ የመንግሥት ሠራተኛ የሆኑት የ59 ዓመቱ ሻለቃ ታምራት በቂ ገለጻ እንደተደረገላቸው፣ ያለምንም ችግር መርጠው መውጣታቸውን ተናግረዋል፡፡ ‹‹የምርጫ ክርክሩ በቂ ግንዛቤ አስጨብጦናል፡፡ ዛሬም ያለምንም ግርግር መርጠን ወጥተናል፤›› ብለዋል፡፡ በምርጫ ጣቢያ 04-ሀ-2 የመረጡት ወ/ሮ በቀለች ታደለ ከቤተ ክርስቲያን መልስ ቁርሳቸውን ሳይበሉ ድምፃቸውን ለመስጠት እንደመጡ ገልጸዋል፡፡ የ78 ዓመቷ ወ/ሮ በቀለች በሁለት ልጆቻቸው እየተጦሩ እንደሚኖሩ ገልጸው በንጉሡ ሥርዓት እከሌን ምረጡ እየተባሉ ይመርጡ እንደነበር፣ በዘመነ ደርግ ምርጫ አለመምረጣቸውን ተናግረዋል፡፡ ‹‹ደርግ መሬት ወርሶብኝ ስለነበር ተቀይሜ መምረጥ አልፈለግኩም ነበር፡፡ አሁን ግን በነፃነት የምንፈልገውን እየመረጥን ነው፡፡ ያለምንም ችግር የምወደውን መርጫለሁ፤›› ብለዋል፡፡
በድምፅ አሰጣጡ ሒደት ላይ አንዳንድ ችግሮች መከሰታቸው አልቀረም፡፡ በምርጫ ጣቢያ 04-ሀ-2 ያገኘነው የኦፌኮ/መድረክ ታዛቢ ወጣት ዋቅጅራ ቃበታ የተማሪ መታወቂያ ይዞ በመምጣቱ ወደ ምርጫ ጣቢያው እንዳይገባ መደረጉን ለሪፖርተር ገልጿል፡፡ ‹‹ከሌሊቱ 11 ሰዓት በምርጫ ጣቢያው የተገኘሁ ቢሆንም፣ የምርጫ ኃላፊዎቹ የትምህርት ቤት መታወቂያ ተቀባይነት የለውም፡፡ የቀበሌ መታወቂያ አምጣ በማለት እንዳልገባ ከልክለውኛል፡፡ የካርድ ቆጠራ ሲካሄድና ኮሮጆ ሲከፈት መታዘብ አልቻልኩም፡፡ የምርጫ ቦርድ ኃላፊዎች መጥተው 12፡25 ሰዓት ሲሆን ነው ተፈቅዶልኝ የገባሁት፤›› ብሏል፡፡
የምርጫ ጣቢያ ኃላፊው አቶ ሊካሣ ኢርካታ ችግሩ መፈጠሩን አምነዋል፡፡ ‹‹የመድረክ ተወካይ ነኝ ብሎ ሲመጣ መታወቂያ ጠየቅነው፡፡ ያሳየን መታወቂያ የትምህርት ቤት ብቻ ነው፡፡ እኛ ደግሞ ማሳየት ያለበት የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ ነው በሚል አስቁመነዋል፡፡ በኋላ የዞኑ የምርጫ ቦርድ ኃላፊ አቶ ሁንዴሳ መጥቶ አግባብነት እንዳለው ካስረዳን በኋላ አስገብቸዋለሁ፤›› ብለዋል፡፡
በኦዶ ሊበን የምርጫ ጣቢያ የተገኘው ፌሌንበር ዲቦ የተባለ የመድረክ ተወካይ፣ የኦሕዴድ ካድሬዎችና ታጣቂዎች ወደ ምርጫ ጣቢያው በተደጋጋሚ ገብተዋል ሲል ቅሬታውን አሰምቷል፡፡ ወጣት ፌሌንበር ለሪፖርተር እንደገለጸው፣ የምርጫ ሕጉ ታጣቂዎች ከምርጫ ጣቢያው 500 ሜትር መራቅ አለባቸው ቢልም አንዳንድ ታጣቂዎች ወደ ምርጫ ጣቢያው ዘልቀው እንደገቡ ተናግሯል፡፡
‹‹ካድሬዎችም ከመረጡ በኋላ የምርጫ ጣቢያውን ለቀው መሄድ ቢኖርባቸውም በምርጫ ጣቢያው ውስጥ ሲዞሩ ይታያሉ፡፡ ታጣቂዎችም በሩ ላይ ይታያሉ፤›› ብሏል፡፡ የኦዶ ሊበን ምርጫ ጣቢያ ኃላፊ አቶ ወርቅነህ ሙሴ አቤቱታውን አስተባብለዋል፡፡ ‹‹ወደ ምርጫ ጣቢያው የገባ ታጣቂ የለም፡፡ ከ500 ሜትር ርቀት ላይ ፀጥታ ለማስከበር የተሰማሩ ፖሊሶች ይኖራሉ፡፡ ምንም የተፈጠረ ችግር የለም፤›› ብለዋል፡፡
በአምቦ ከተማ ሪፖርተር በተዘዋወረባቸው የተለያዩ ቦታዎች በምርጫ ጣቢያ አቅራቢያ የክልሉ ፖሊስ አባላት ታይተዋል፡፡ በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች በር ላይ ፖሊሶችና የአካባቢ ታጣቂዎች ተስተውለዋል፡፡ በአምቦ 03-ለ-1 የምርጫ ጣቢያ (አውራ ጎዳና ግቢ ውስጥ) የታጠቁ የፖሊስ አባላት ተስተውለዋል፡፡
ሌላው ችግር በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የምርጫ ወረቀቶች ተሟልተው አለመቅረብ ነው፡፡ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ከ5,000 በላይ ተማሪዎች የሚገኙ ሲሆን፣ 3,578 ተማሪዎች በመራጭነት ተመዝግበዋል፡፡ ስድስት የምርጫ ጣቢያዎች ተቋቁመው፣ በእያንዳንዱ ጣቢያ 700 ያህል ተማሪዎች ተመዝግበዋል፡፡ በሥፍራው የነበረች የምርጫ አስተባባሪ ዓለም አድነው በእያንዳንዱ የምርጫ ጣቢያ ከ10 እስከ 15 የሚሆኑ የምርጫ ወረቀቶች ጉድለት መታየቱን ገልጻለች፡፡ በዚህም ምክንያት 70 ያህል ተማሪዎች በወቅቱ መምረጥ ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ ጉዳዩን ለምርጫ ቦርድ አሳውቀው ከአዲስ አበባ የምርጫ ወረቀት እስኪመጣ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ዓለም ተናግራለች፡፡
በድምፅ መስጫ ዕለት የጠነከረ ቅሬታ ያሰሙት ዶ/ር መረራ ናቸው፡፡ ‹‹በተለያዩ አካባቢዎች ታዛቢዎችን በታጣቂ ኃይሎች ተባረውብናል፤›› ያሉት ዶ/ር መረራ፣ ጀልዱ፣ ጨልያና ጅባት በተባሉ ቦታዎች ታዛቢዎች በመባረራቸው ምክንያት ምርጫው የተካሄደው ታዛቢዎቻችን በሌሉበት ነው ብለዋል፡፡
‹‹ታዛቢዎቻችን ላይ ዘመቻ ነው የተካሄደው፡፡ ማስፈራራት፣ በገንዘብ ለመግዛት መሞከር፣ ከዚህ አልፎ አልበገር ያለውን በጠመንጃ የማባረር ተግባር በሰፊው ተፈጽሟል፡፡ የታሰሩና የተደበደቡ ታዛቢዎችም አሉ፤›› ብለዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጡት አቶ ሁንዴሳ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አንዳንድ የመድረክ ታዛቢዎች ተገቢውን መረጃ ይዘው ባለመቅረባቸው ከታዛቢነት ተገልለዋል፡፡ ‹‹ከተመዘገበ መታወቂያ ውጪ የተለየ መታወቂያ ይዘው በመምጣታቸው የተከለከሉ አሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ በምርጫ ቦርድ በታዛቢነት የተመዘገቡ ግለሰቦች ሳይሆኑ፣ ሌሎች ግለሰቦች ተገኝተዋል፡፡ በዚህ ምክንያት በታዛቢነት እንዳይገኙ ተከልክለዋል፤›› ብለዋል አቶ ሁንዴሳ፡፡
አያይዘውም አንዳንድ የመድረክ ተወካዮች በምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ የምርጫ ሕጉ የሚከለክለውን ድርጊት ሲፈጽሙ በመገኘታቸው፣ ከምርጫ ጣቢያዎች እንዲወጡ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ ‹‹በአንዳንድ ጣቢያዎች የመድረክ ታዛቢዎች የፓርቲውን ምልክት ለሕዝብ ሲያሳዩ በመታየታቸው በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም፣ ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ባለመቻላቸው ከምርጫ ጣቢያዎቹ እንዲወጡ ተደርጓል፤›› ብለዋል፡፡
አቶ ሁንዴሳ ከመድረክ የቀረቡትን አቤቱታዎች ለማጣራት መሞከራቸውን ገልጸው አንዳንድ ታሰሩ የተባሉ ግለሰቦች ጉዳዩ ስህተት መሆኑን፣ ሌሎች ደግሞ በግለሰብ ጠብ ታስረው የተፈቱ መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር መረራ በበኩላቸው ባቢች፣ ወልሮጌና ጨካ በተባሉ አካባቢዎች በመድረክ ደጋፊዎችና በታጣቂ ኃይሎች መካከል ፍጥጫ ተፈጥሮ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ ዶ/ር መረራ ከአምቦ አልፎ ሚዳቀኝ በሚባል አካባቢ ግጭት ተፈጥሮ ተኩስ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ አቶ ሁንዴሳ ይህን በተመለከተ የደረሳቸው ሪፖርት እንደሌለ ገልጸዋል፡፡
ቆጠራ
በአምቦ የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ከምሽቱ 12 ሰዓት በሮቻቸውን ዘግተዋል፡፡ ቆጠራው በሰዓቱ ተጀምሯል፡፡ ሪፖርተር በተገኘባቸው አንዳንድ ጣቢያዎች መድረክና ኢሕአዴግ ብርቱ ተፎካካሪ መሆናቸውን ለመታዘብ ተችሏል፡፡ ቀላል የማይባሉ የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ምንም ዓይነት ምልክት ያልተደረገባቸው በመሆኑ ሲመክኑም ታይቷል፡፡ በአምቦ 03-ለ-1 የምርጫ ጣቢያ ቆጠራው ሲካሄድ ሁለት የታጠቁ ፖሊሶች (አንድ ወንድና ሴት) ቆጠራው የሚካሄድበት ክፍል ውስጥ ገብተው የቆጠራውን ሒደት ሲከታተሉ ታይተዋል፡፡ የቆጠራው ሒደት በአንዳንድ ጣቢያዎች እስከ ሌሊቱ አሥር ሰዓት ዘልቋል፡፡
ውጤት
የምርጫ ጊዜያዊ ውጤቶች በአምቦና በጉደር ከተሞች ግንቦት 17 ቀን 2007 ዓ.ም. ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ጀምሮ መለጠፍ ተጀምሯል፡፡ ሪፖርተር በተገኘባቸው ጣቢያዎች በሮች ላይ ጥቂት ወጣቶች የምርጫ ውጤቶችን ሲያነቡ ነበር፡፡
አቶ ሁንዴሳ በፓርቲዎች አካባቢ የምርጫ ውጤትን አምኖ የመቀበልና ያለመቀበል ሁኔታ እንደሚኖር ተናግረዋል፡፡ ‹‹የቆጠራ ሒደቱ ሲጠናቀቅ አንፈርምም ብለው የወጡም አሉ፡፡ ይህን እኛ ምንም ማድረግ አንችልም፤›› ብለዋል፡፡ በምርጫው ማግስት ግንቦት 17 ቀን 2007 ዓ.ም. የክልሉ ፖሊስ በአምቦ ከተማ የተጠናከረ ጥበቃ ሲያካሂድ ነበር፡፡

በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን አምስት የፓርላማ ምርጫዎችን (1948-1965)፣ በደርግ ዘመን የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢሕዲሪ) ብሔራዊ ሸንጎን አንድ ምርጫ (1979)፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ
ሪፐብሊክ (ኢፌዴሪ) አራት የፓርላማ ምርጫዎችን (1987-2002) ያካሄደችው አዲስ አበባ ከተማ፣ አምስተኛውን ምርጫ ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. አድርጋለች፡፡
ባለፈው እሑድ በተካሄደው የተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ለመሳተፍ አዲስ አበቤዎች ማልደው ነበር ከየምርጫ ጣቢያዎች የተገኙት፡፡ የመዲናይቱ ነዋሪዎች የ1997 ዓ.ም. ምርጫ ጥሎት በሄደው ጠባሳ ምክንያት እንደሌላው ኢትዮጵያዊ በእኩል ጊዜ ሁለቱንም ማለትም የክልልና የተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ባንዴ ለማካሄድ አልታደሉም፡፡ ከሌላው ሕዝብ በሁለት ዓመት ወደኋላ ዘግይተው ነው የክልል ምርጫውን የሚያካሂዱት፡፡ በመሆኑም በዕለቱ ለተወካዮች ምክር ቤት አባልነት ይመጥናሉ የሚሏቸውን ፓርቲዎች ሲመርጡ ውለዋል፡፡
ከ2002 ምርጫ ጋር ሲነፃፀር በዛ ያለ የሕዝብ ቁጥርና ሠልፍ የታየበትም ነው፡፡ በ2002 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ምርጫ ለመዘገብ ሪፖርተር ከተዘዋወረባቸው አካባቢዎች አብዛኞቹ ምርጫ ጣቢያዎች ሠልፍም ሆነ የወጣቱ ክፍል አይበዛባቸውም ነበር፡፡ አመዝነው የሚታዩት እናቶች ነበሩ፡፡ የ2007ቱ ምርጫ ከ1997ቱ ጋር ሲነፃፀር ተቀራራቢ የሕዝብ መነቃቃት ነበረው ለማለት ባያስደፍርም ከ2002 ዓ.ም. ግን የሕዝቡ ተሳትፎ የተሻለ ነበር፡፡ መነቃቃትም ታይቶበታል፡፡
ከዚህ ቀደም በተደረጉ ሁለት ጠቅላላ ምርጫዎች ሁለት ፈጽሞ የተራራቁ ውጤቶችን ያስተናገደችው አዲስ አበባ፣ በምርጫ 2007 ተቃዋሚዎች ለማሸነፍ ተስፋ ያደረጉባት ሆና ነበር፡፡ በምርጫ 1997 ኢሕአዴግ አንድ ወንበር ከማሸነፍ ውጪ 22 ወንበሮችን ያሸነፈው በወቅቱ ጠንካራ ተፎካካሪ የነበረው ቅንጅት ነበር፡፡ በ2002 ዓ.ም. ይህ ውጤት ተገልብጦ ኢሕአዴግ 22 ወንበሮችን ሲያሸንፍ በወቅቱ ጠንካራ ተፎካካሪ የነበረው መድረክ ውስጥ የታቀፈው የአንድነት ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ ብቸኛዋን ወንበር ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡
በምርጫ 2007 ምርጫ በተደረገባቸው አብዛኛዎቹ የምርጫ ጣቢያዎች በአዲስ አበባም የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ድምፅ መስጠት ተጀምሮ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ተጠናቋል፡፡
በኢትዮጵያ በአጠቃላይ 36,851,461 ሕዝብ የምርጫ ካርድ የወሰደ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 1,481, 521 የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ናቸው፡፡ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ያገኘነው መረጃ ደግሞ፣ በአዲስ አበባ ለመምረጥ ከተመዘገቡት ውስጥ ድምፅ የሰጡት 1,342,582 እንደሆኑ ያሳያል፡፡
በሁለት መደዳ የተሠለፉት በርካታ መራጮች ድምፅ መስጫ ሰዓት እስከሚደርስ ይጠባበቃሉ፡፡ ጎህ ሳይቀድ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ (ምርጫ ክልል 26/27) ወረዳ ሰባት ምርጫ ጣቢያ አንድ ከተገኙት የመጀመርያዎቹ ተሠላፊዎች የ19 ዓመቷ ሰላም አስካለ አንዷ ነች፡፡ የመጀመርያ ዓመት ሕክምና ተማሪ ናት፡፡ ‹‹የመጀመሪያዬ ምርጫ ስለሆነ ድምፅ ለመስጠት ጓጉቻለሁ፤ በለሊት የተገኘሁትም ለዚሁ ነው፤›› ትላለች፡፡ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል በተደረገው ክርክር የምትመርጠውን እንደተገነዘበችና በፓርቲዎቹ መካከል የነበረውን ፉክክር ጠንካራ እንደነበር ትገልጻለች፡፡ ‹‹የአንድ ሰው ተሳትፎ ትልቅ ሚና ስላለው ያመንኩበትን ለመምረጥ ተዘጋጅቻለሁ፤›› ብላለች፡፡
በምርጫ ጣቢያው በተጣለው ድንኳን ድምፃቸውን ሰጥተው ሲወጡ ያነጋገርናቸው የ68 ዓመቱ አቶ ሀብተማርያም ምሕረትአብ፣ በአገሪቱ በተካሄዱ ምርጫዎች ባጠቃላይ ድምፅ መስጠታቸውንና የዘንድሮው ምርጫ ከቀደሙት የተሻለ ሆኖ እንዳገኙት ይናገራሉ፡፡ ‹‹ሰው ያለምንም ጫና እየመረጠ ነው፤›› ይላሉ፡፡
የ69 ዓመቱ አቶ ተፈራ ድሩ ሐሳቡን ይጋሯቸዋል፡፡ የዘንድሮውን ጨምሮ በሁሉም በኢሕአዴግ መንግሥት በተካሄዱ ምርጫዎች የሕዝብ ታዛቢ ሆነዋል፡፡ እንደሳቸው ገለጻ፣ የዘንድሮው ምርጫ ‹‹የተረጋጋና የሠለጠነ አካሄድ ያለው›› ነው፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከምርጫ አስቀድመው ያደረጉት እንቅስቃሴ አገርን ለማሳደግ በቁጭት እንደተነሳሱ ያሳያል ይላሉ፡፡ ‹‹እንደቀደሙት ጊዜያት መናቆር የለም፤›› በማለት የሚሸነፉ ፓርቲዎች ከአሸናፊው ጋር በሰላም እጅ ለእጅ ተጨባብጠው ኑሮ በሰላም እንደሚቀጥል እምነታቸው ነው፡፡
በምርጫ ጣቢያው የሕዝብ ታዛቢዎችና የሲቪክ ማኅበራት ተወካዮች ተገኝተው ሒደቱን ይከታተሉ ነበር፡፡ የጣቢያው የምርጫ አስተባባሪዎችም የምርጫ ቅደም ተከተል ለሕዝቡ ያብራሩ ነበር፡፡ የምርጫ ክልሉ ኃላፊ አቶ ተሾመ አበበ በክልሉ በሚገኙ 110 የምርጫ ጣቢያዎች መሰል ሒደት እንዳለ ተናግረዋል፡፡ በሒደቱ ይህ ነው የሚባል ችግር እንዳልገጠማቸውና ቅሬታዎችም እንዳልተነሱ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
ረፋድ ላይ ሳር ቤት አካባቢ በምርጫ ክልል 20 በሚገኙ 59 የምርጫ ጣቢያዎች ኢሕአዴግን ወክለው የሚወዳደሩት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታደሰ ኃይሌ ድምፅ ሲሰጡ ሪፖርተር አግኝቷቸዋል፡፡ ‹‹ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ በሰላማዊ መንገድ መምረጡ አገሪቱን ለአፍሪካና የዓለም አገሮች ተምሳሌት ያደርጋታል፤›› ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የዴሞክራሲ ባህል እየዳበረ መሆኑን አመላካች እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡
ሕዝቡ የሚመራውን ፓርቲ በራሱ ድምፅ መርጦ እንደሚያስቀምጥና በሰላማዊ መንገድ እንደሚጠናቀቅ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡ በምርጫ ጣቢያው የመኢአድ ተወካይ ታዛቢ አቶ በለጠ የሺጥላ ምርጫው በጥሩ ሁኔታ መከናወኑን ይናገራሉ፡፡ በቦታው ከገጠማቸው ችግሮች አንዱ የምርጫ ካርድ ሳይዙ ወደ ጣቢያው የሚሄዱ ሰዎች ሲሆኑ፣ ግለሰቦቹ በምዝገባ ላይ ምርጫ ካርድ መውሰዳቸው ተረጋግጦ ተስተናግደዋል ብለዋል፡፡
ተመሳሳይ ችግር የተስተዋለው የምርጫ ክልል 19 ውስጥ ከተካተቱ አካባቢዎች በአንዱ መብራት ኃይል ኮንዶሚኒየም ነው፡፡ መታወቂያ ሳይዙ ድምፅ ለመስጠት ወይም የምርጫ ካርድ ሳይኖራቸው (እንደጠፋባቸው የሚናገሩም አሉ) ድምፅ ለመስጠት ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ያመሩ ግለሰቦች ተስተውለዋል፡፡ በወረዳ 6 ምርጫ ጣቢያ 20 የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢ የነበሩና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ግለሰብ ያቀረቡት ቅሬታም ይኼው ነው፡፡
‹‹መታወቂያ የሌለው ወይም የጠፋበት ሰው የሕዝብ ታዛቢዎች የሚያውቁት ከሆነ እንዲመርጥ ይደረጋል፡፡ ሕጉ ባያስማማኝም ከምርጫ ቦርድ የወረደ ስለሆነ ተቀብያለሁ፡፡ መራጮች በዚህ ምርጫ ጣቢያ ያለመታወቂያ መምረጥ እንደማይቻል ሲገለጽላቸው፣ መጀመርያ ያለመታወቂያ ምርጫ ካርድ ሰጥታችሁናል፡፡ ስለዚህ መምረጥ እንችላለን የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፤›› የሚሉት ታዛቢው፣ በሕጉ መሠረት መታወቂያ የሌላቸውን ሰዎች እናውቃቸዋለን ብለው ምስክርነት የሚሰጡት የሕዝብ ታዛቢዎች ብቻ ሳይሆኑ የኢሕአዴግ ታዛቢዎች ጭምር እንደነበሩ ይናገራሉ፡፡ አሠራሩ የአገሪቱን ሕግ የሚፃረር መሆኑን በማስረገጥ ታዛቢው ተከራክረው ያለመታወቂያ እንዳይመርጡ ያደረጓቸው ግለሰቦች ቢኖሩም የመረጡም አሉ ይላሉ፡፡
የምርጫ ጣቢያው ኃላፊ አቶ ታደሰ አሽኔ ቅሬታውን እንደማይቀበሉት ነው የገለጹት፡፡ እሳቸው እንደሚሉት፣ መታወቂያ የጠፋባቸው ወይም ያልያዙ የኮንዶሚኒየሙ ነዋሪዎች የሕዝብ ታዛቢዎች ማንነታቸውን እስካወቁ ድረስ ድምፅ እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡ ከሕዝብ ታዛቢዎች ውጪ ግን የትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ስለግለሰቦቹ ማንነት ምስክርነት አልሰጠም ይላሉ፡፡
በጣቢያው የኢሕአዴግ ታዛቢ ወ/ሪት ጽጌ ፀጋዬ በበኩላቸው የምርጫ ካርድ ሲወስዱ መታወቂያ ኖሯቸው የጠፋባቸው ግለሰቦች በሕዝብ ታዛቢዎች እስከታወቁ ድረስ ድምፅ መስጠታቸው አግባብ ነው ይላሉ፡፡ የኮንዶሚኒየሙ ነዋሪዎች በርካታ በመሆናቸው የሁሉንም ማንነት ለማወቅ አይቻልም የሚሉት ታዛቢዋ፣ ማንነታቸው ሳይታወቅ የመረጡና ፓርቲያቸውም ጣልቃ ገብቶ እናውቃቸዋለን ያላቸው ግለሰቦች እንደሌሉ ገልጸዋል፡፡ በጣቢያው የሕዝብ ታዛቢ ወ/ሮ ዘውድነሽ ድንቁ እንደሚናገሩት፣ መታወቂያ የሌላቸውና እሳቸውና የተቀሩት የሕዝብ ታዛቢዎች ያላወቋቸው ሰዎች ድምፅ እንዳይሰጡ አግደዋል፡፡
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሳሪስ የተካሄደውን የድምፅ ቆጠራ ሪፖርተር የተከታተለው በወረዳ 10 ምርጫ ጣቢያ ሰባትና ስምንት ነበር፡፡ 12 ሰዓት ካለፈ በኋላ የድምፅ መስጫ ኮሮጆዎች ተቆልፈው በአቆጣጠሩ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች፣ የሕዝብ ታዛቢዎች፣ የሲቪክ ማኅበራት ተወካዮችና የምርጫ አስፈጻሚዎች ተወያይተዋል፡፡
መራጮች ድምፅ በሚሰጡበት ወቅት ‹‹X›› ምልክት ማድረግ እንዳለባቸው ቢገለጽም፣ በመዘንጋት ወይም በተለያየ ምክንያት ‹‹ü›› ያደረጉት ድምፅ እንደሰጡ መቆጠር አለበት የሚል ክርክር በምርጫ ጣቢያ ሰባት ቢነሳም ተቀባይነት አላገኘም፡፡ ከአሻራና ‹‹X›› ምልክት ውጪ ያሉ ወረቀቶች ፊርማ ወይም ጽሑፍ የተቀመጠባቸውና ከአንድ በላይ ፓርቲ ላይ ምልክት የተደረገባቸው ድምፅ አልባ ሆነዋል፡፡
በሁለቱ ምርጫ ጣቢያዎች ለሰዓታት የዘለቀው ቆጠራ ሁሉንም ታዛቢ አካላት ለማሳተፍ የተሞከረበት ነበር፡፡ በምርጫ ጣቢያ ሰባት ታዛቢ የነበሩት የመድረክ ተወካይ አቶ ኪሳ ተመስገን፣ ምርጫ ቦርድ ባወጣው ሕግ መሠረት ቆጠራው መካሄዱንና ሒደቱም ‹‹ፍትሐዊ ነው›› ብለዋል፡፡ በጣቢያው የኢሕአዴግ ተወካይ አቶ የሥጋት ፈጠነም ቅሬታ እንደሌላቸው ነው የተናገሩት፡፡
በዞን ሁለት ምርጫ ክልል 24 ጦር ኃይሎች አካባቢ የተወዳደሩት የመኢአድ ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሐሪ ምርጫ ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት፣ ምርጫው ካልተጭበረበረ እንደሚያሸንፉ ነው፡፡ አቶ አበባው በዕለቱ ለመምረጥ የምርጫ ካርዳቸውን ይዘው የነበረ ቢሆንም ከሚመርጡበት ጣቢያ ስምዎት የለም በመባላቸው ሲንከራተቱ ነበር፡፡ ሆኖም ተሳክቶላቸው በዞን ሁለት ምርጫ ክልል 24 ምርጫ ጣቢያ ስምንት ላይ መምረጥ ችለዋል፡፡
በዞን ሦስት ምርጫ ክልል 18 የተወዳደሩት የ32 ዓመቷ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በአዲስ አበባ ኢሕአዴግን ወክለው ለተወካዮች ምክር ቤት ከቀረቡ 23 ዕጩዎች አንዷ ናቸው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቅም ግንባታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ በመሆን እያገለገሉ የሚገኙት ወ/ሮ ዳግማዊት፣ የምርጫ ጣቢያዎቹ ሒደት ጥሩ ሊባል የሚችል፣ እናቶች፣ ወጣቶችና አዛውንቶች ያዩባቸውና ይኽም ኅብረተሰቡ ዴሞክራሲያዊ መብቱን ለመጠቀም ያለውን ዝግጅት ያሳየ ነው ብለዋል፡፡ እንደ ወ/ሮ ዳግማዊ የ2007 ዓ.ም. ምርጫ ከ2002 ጋር ሲነፃፀር በሒደቱ የተሻለ ነው፡፡
በዞን ሁለት ምርጫ ክልል 24 ጣቢያ 2 ድምፅ የሰጡት የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እውነቱ ብላታ ምርጫው ሰላማዊና ተፎካካሪ ፓርቲዎችም የሒደቱን ሰላማዊነትና አሳታፊነት በቃላቸው የገለጹበት መሆኑን ጥቃቅን ችግሮች ሲከሰቱ ወዲያው የመፍታት ሒደት እንደነበር አመልክተዋል፡፡
በአዲስ አበባ ካሉ የምርጫ ክልሎች ውስጥ በምርጫ ክልል 17 (ቦሌ) የተሻለና የተቀራረበ ውጤት እንዲጠበቅ ላደረገው ግምት መነሻ የሆነው ደግሞ በክልሉ የሚወዳደሩት እጩዎች ማንነት ነው፡፡ ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ በአዲስ አበባ አስተዳደር የኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ በአቶ ዮሐንስ በቀለ፣ ሰማያዊ ፓርቲ በሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው በአቶ ዮናታን ተስፋዬ፣ ኢዴፓ በሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው በአቶ ወንድወሰን ተሾመ እንዲሁም ኢራፓ በፕሬዚዳንቱ በአቶ ተሻለ ሰብሮ ተወክለው ነበር፡፡
ሪፖርተር በምርጫ ክልሉ በሚገኙ ጣቢያዎች ውስጥ ያገኛቸው የምርጫ አስፈጻሚዎችና ታዛቢዎች ሒደቱን ያልተረዱት መራጮች እጅግ ትንሽ እንደሆኑና አብዛኛዎቹ ግን ስለ ሒደቱ አስቀድመው ግንዛቤው ያላቸው እንደነበሩ ገልጸዋል፡፡ በምርጫ ክልሉ በሚገኘው ወረዳ 13 ውስጥ 18 የምርጫ ጣቢያዎች ያሉ ሲሆን፣ ገርጂ ታክሲ ተራ አካባቢ የሚገኘው ምርጫ ጣቢያ 4 ኃላፊ አልማዝ ደሳለኝ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በጣቢያው ድምፃቸውን የሰጡት መራጮች ያለምንም ግራ መጋባት ሒደቱን ፈጽመዋል፡፡ የወረዳ 6 የምርጫ አስተባባሪ አቶ ታምራት ፍርድአወቅ በተመሳሳይ መራጩ ሒደቱን አስቀድሞ ተረድቶ በመምጣቱ አስረዱኝ ብሎ የሚጠይቀው እጅግ ጥቂቱ ብቻ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ በምርጫ ሒደት ውስጥ ከሽግግር መንግሥቱ አንስተው ተካፋይ እንደሆኑ የገለጹት አቶ ታምራት፣ የሕዝቡ ንቃተ ህሊና ከምንጊዜውም በላይ አሁን ያደገ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
በወረዳ 3 ከሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች በአንዱ ያገኘናቸው የኢሕአዴግ ታዛቢ አቶ አዲሱ አካለ የምርጫ አስፈጻሚዎች የተሻለ አቅምና አደረጃጀት በመገንባታቸው መራጩ በቀላሉ በምርጫው ሒደት እንዲያልፉ አስችሏል፡፡ በዚያው የምርጫ ጣቢያ ያገኘናት የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ታዛቢ ወጣት ቅድስት ግርማ መራጮች ምን ማድረግ እንዳለባቸው በሚገባ የተረዱ እንደሆኑ አስገንዝባለች፡፡ ይሁንና በአብዛኛዎቹ የምርጫ ጣቢያዎች የተቃዋሚ ፓርቲዎች ታዛቢዎች አልነበሩም፡፡
በምርጫ ሒደቱ ሲሳተፉ ካገኘናቸው መካከል አቶ ገናናው ጃቢር፣ ወጣት ሔኖክ ተስፋዬና ወጣት አሰገደች አብርሃም በሒደቱ በመሳተፍ በአገራቸው ጉዳይ ላይ ውሳኔ በማሳረፋቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ የ21 ዓመቱ ወጣት ሔኖክ ለመጀመሪያ ጊዜ በምርጫ መሳተፉ ነበር፡፡ ‹‹የምፈልገውን ተወካይ በነፃነት በመምረጥ በአገሬ ጉዳይ ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ የምችልበት ዕድሜ ላይ በመድረሴ ደስተኛ ነኝ፤›› ብሏል፡፡
በምርጫ ጣቢያ 4 የድምፅ መስጠት ሒደቱ 12 ሰዓት ምሽት ላይ ተጠናቆ ቆጠራው 1 ሰዓት ተጀምሮ ከምሽቱ 5 ሰዓት ላይ እስኪጠናቀቅ ሪፖርተር ሒደቱን የተከታተለ ሲሆን፣ በጣቢያው የተቃዋሚ ፓርቲ ታዛቢዎች ተገኝተው ነበር፡፡
በምርጫ ክልል 5 መርካቶ አካባቢ በሚገኝ የምርጫ ጣቢያ ማልደው ከመጡ መራጮች ውስጥ አንዱ በሠላሳዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኘው ታሪኩ ደምሴ ነበር፡፡
ታሪኩ በ1997 ዓ.ም. እና 2002 ዓ.ም. በተደረጉት ጠቅላላ ምርጫዎች ተሳትፏል፡፡ ‹‹የሚበጀኝን ፓርቲ የመረጥኩበት መሥፈርት የፓርቲው የወደፊት ራዕይና እስካሁን ያሳያቸው ነገሮች ናቸው፡፡ ይህንንም ከተከታተልኳቸው የምርጫ ክርክሮች ተረድቻለሁ›› ሲል አስተያየቱን ለሪፖርተር ተናግሯል፡፡
በምርጫ ክልል 5 በ2002 ዓ.ም. በተደረገው ጠቅላላ ምርጫ መድረክ አብላጫ ድምፅ በማግኘት ያሸነፈበት ነው፡፡ መድረክን የወከሉት አቶ ግርማ ሰይፉ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራጭ መሆናቸው ይታወሳል፡፡
በዚሁ የምርጫ ክልል ዘንድሮ ኢሕአዴግና መድረክን ጨምሮ 12 የፖለቲካ ፓርቲዎች ተፎካክረዋል፡፡ ምርጫ ክልል 5 የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በዕጣ ከተወዳዳሪነት ውጪ በመሆናቸው ፓርቲው በዚህ ክልል ተወዳዳሪ አልነበረውም፡፡
ቲና ወልደ ማርያም፣ ከእህቷ ከቤዛ ወልደ ማርያምና ከጎረቤቷ ውድነሽ ወርቁ ጋር በመሆን ቲና የስድስት ወር ውድነሽ ዓመት ከሁለት ወር የሆናቸውን ወንድ ልጆቻቸውን ታቅፈው ድምፅ ለመስጠት ማልደው ካዛንቺስ ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው የምርጫ ጣቢያ ተገኝተዋል፡፡
ቲናና ውድነሽ በምርጫ ክልል 15 የነባር ቀበሌ 31 ምርጫ ጣቢያ አዳራሽ ውስጥ የተገኙት በዕለቱ ወንድ ልጆቻቸውን ኪዳነ ምሕረት ከማቁረባቸው በፊት ለመምረጥ እንደሆነ ነግረውናል፡፡
በእነዚህ ጣቢያዎች ከሚወዳደሩት 12 ፓርቲዎች መካከል የኢሕአዴግ፣ የሰማያዊ፣ የመድረክና የመኢአድ ታዛቢዎች የተገኙ ሲሆን፣ በድምፅ አሰጣጥ ሒደቱ ችግር እንዳላጋጠማቸው ገልጸዋል፡፡
ሾላ መገናኛ አካባቢን ከያዘው ምርጫ ክልል 16 ውስጥ ከሚገኙት የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች አንዱ የሆነውና መገናኛ የካ ተራራ ላይ የሚገኘው የወረዳ 5 ምርጫ ጣቢያ 4 የቦታው አቀማመጥና አቀበታማው መልክዓ ምድርና ወደ ጣቢያው የሚወስዱት መንገዶች በቀላሉ ለመንቀሳቀስ አዳጋች ነበሩ፡፡
ምንም እንኳ ጣቢያው የሚገኝበት ቦታ አቀማመጥ ቀና ባይሆንም መራጮችን በሰዓቱ ተገኝተው ድምፅ የመስጠቱን ሒደት እንዳልገደበው የጣቢያው አስተባባሪ አቶ ሰለሞን አሞኘ ገልጸውልናል፡፡
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በወረዳ ዘጠኝ ከሚገኘው የምርጫ ጣቢያ ሦስት ቅጥር ግቢ አጠገብ አንዲት በዕድሜ የገፉ ባልቴት በምርኩዛቸው እየተደገፉ ወደ ቤታቸው ሲያመሩ አግኝተናቸዋል፡፡ ባልቴቷ ወ/ሮ ጠይባ አቡበከር ይባላሉ፡፡ ወይዘሮ ጠይባ እንዳጫወቱን ከሆነ ዕድሜያቸው 100 ሊሞላ ሦስት ዓመት ብቻ ነው የቀረው፡፡ “ሌላ የምርጫ ካርድ ለማምጣት ወደ ቤቴ እየሄድኩ ነው፤” አሉን፡፡
ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ደበበ የጣቢያው ምርጫ አስፈጻሚ የሚሉት ደግሞ ባልቴቷ ለመምረጥ በቅድሚያ መመዝገባቸው ተረጋግጧል፡፡ ይሁን እንጂ ሳይመርጡ የተመለሱትም በ2005 ዓ.ም. በተካሄደው ምርጫ የተመዘገቡበትን የምርጫ ካርድ ይዘው በመምጣታቸው በመሆኑ የአሁኑን ምርጫ ካርድ ይዘው መጥተው እንዲመርጡ ተነግሯቸዋል፡፡
ሽሮ ሜዳ አካባቢ በሚገኘው የዞን 4 ምርጫ ክልል 11 ጣቢያ ጧት 2፡20 ሰዓት ላይ ተገኝተው ድምፅ የሰጡት የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩው አቶ ስለሺ ፈይሳ የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንትና የምርጫ ጉዳዮች አስተባባሪ ናቸው፡፡ በምርጫው ሒደት ታዛቢዎቻቸው በተዘዋዋሪ ታዛቢዎች ምርጫውን ለመከታተል እንደሞከሩ ገልጸውልናል፡፡
በወረዳ 11 ሪፖርተር በተዘዋወረባቸው የምርጫ ጣቢያዎች የተለያዩ የምርጫ ታዛቢዎችን የተመለከተ ቢሆንም፣ በ20 የምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች የተገኘው አንድ የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢን ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ የኢሕአዴግ፣ የሲቪክ ማኅበራት ጥምረትና የሕዝብ ታዛቢዎችን ተመልክቷል፡፡
በሌላ በኩልም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሚገኙ 17 የምርጫ ጣቢያዎችም የክልል ተወላጆች ሲመርጡ ውለዋል፡፡ ሆኖም እስከ ቀኑ 8፡30 ድረስ ለአንዳንዶቹ የመምረጫ ሰነድ ተማልቶ ባለመቅረቡ መራጮች ተቸግረው ነበር፡፡
በዩኒቨርሲቲው ሥር በሚገኙ 15 ካምፓሶች የሚማሩ 7,029 የክልል ተወላጆች በክልልና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ለመሳተፍ ካርድ የወሰዱ ሲሆን፣ ከነዚህ ውስጥ ከትግራይ አክሱም፣ ከጋምቤላ አንዳንድ አካባቢዎች፣ ከአማራ አምባሰል፣ ከሐረሪ አንዳንድ አካባቢ ለመጡ ተማሪዎች በምርጫው ሙሉ ለሙሉ ለመሳተፍ የሚያስችላቸው ሰነድ እስከተጠቀሰው ሰዓት ድረስ ተሟልቶ አልቀረበም፡፡
የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ኅብረት ፕሬዚዳንት አቶ ቢኒያም ጫኔ እንደሚሉት፣ ችግሩ የተፈጠረው በዩኒቨርሲቲው ሳይሆን በምርጫ ቦርድ ነው፡፡ በመሆኑም ችግሩን ለምርጫ ቦርድ አሳውቀዋል፡፡ የምርጫ ቦርድ በሰጠው መግለጫ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና በክልል በሚገኙ ከፍተኛ ተቋማት ምርጫ ሒደት ላይ ለተፈጠረው ክፍተት ይቅርታ ጠይቋል፡፡ አንድም ተማሪ ሳይመርጥ እንደማይቀርና ችግሩም እንደሚፈታ አሳውቋል፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዕለቱ ሰነድ ተሟልቶላቸው ምርጫ ያጠናቀቁ ሲሆን የክልል ተማሪዎች ግን ምርጫውን ያጠናቀቁት በማግስቱ ሰኞ ነው፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ሲመርጥ ያገኘነው የ23 ዓመቱ ይድነቃቸው ጥላሁን ውልደቱ ኢሉአባቡራ ዞን ጎሬ ከተማ ሲሆን፣ የሁለተኛ ዓመት የሶሻል ወርክ ተማሪ ነው፡፡
ለመጀመርያ ጊዜ በምርጫ እንደተሳተፈ የሚናገረው ይድነቃቸው በያሉበት ዩኒቨርሲቲ ሆነው መምረጣቸው መልካም አጋጣሚ ነው፡፡ በዩኒቨርሲቲ ተከልለው መምረጣቸውም ምንም ጫና እንደማይፈጥርበት፣ የመምረጥም ሆነ ያለመመረጥ መብቱን ሊጠቀም እንደሚችልም ነው የገለጸልን፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቢሾፍቱና በፍቼ የሚገኙት ካምፓሶችን ጨምሮ በ17 የምርጫ ጣቢያዎች የአማራ፣ የኦሮሚያ፣ የደቡብ፣ የትግራይ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ የአፋር፣ የኢትዮጵያ ሶማሌ፣ የሐረሪና የጋምቤላ ተወላጅ ተማሪዎች ድምፅ ሰጥተዋል፡፡
በተያያዘም በአዲስ አበባ ከተማ በዞን 5 የምርጫ ክልል በወረዳ 2 እና 14 ምርጫ ጣቢያ፣ በብሔራዊ ሎተሪ ግቢ ድምፅ መስጫ የተዘጋጀላቸው የሐረሪ ብሔረሰብ ተወላጆች፣ ለክልልና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች ድምፅ ሰጥተዋል፡፡ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ሦስት ቢሆኑም፣ ለውድድሩ ብቸኛ ተወዳዳሪ ሆኖ የቀረበው ሐብሊ (የሐረሪ ብሔራዊ ሊግ) መሆኑን አስተባባሪው አቶ አደም አቡበከር ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
በአዲስ አበባ ነዋሪ ለሆኑት ሐረሪዎች ክልላቸውን የሚመሩላቸው 14፣ በፓርላማ የሚወክሏቸውን አንድ ዕጩ ለመምረጥ በአዲስ አበባ በተለያዩ አምስት ጣቢያዎች ሲመርጡ መዋላቸውን አውስተዋል፡፡ ለፓርላማው ብቸኛ ተወዳዳሪ ሆነው የቀረቡት ወ/ሮ ኑሪያ አብዱራህማን ኡመር ናቸው፡፡ በአዲስ አበባ የሚኖሩ ሐረሪዎች ለሚኖሩበት ወረዳ በፓርላማ የሚወክላቸውን፣ በሐረሪነታቸውም ከሐረር በፓርላማ ለሚወክላቸው ድምፆች ይሰጣሉ፡፡
የሐረሪ ተወላጆች ከሌሎች ክልሎች በተለየ ሁኔታ በአዲስ አበባ ከተማ ከ1987 ዓ.ም. የመጀመሪያው ዙር ምርጫ ጀምሮ እንደሚመርጡ ይታወቃል፡፡
(ዘገባውን ያጠናቀሩት ምሕረተሥላሴ መኰንን፣ ምሕረት ሞገስ፣ ታምሩ ጽጌ፣ ታደሰ ገብረማርያም፣ ይበቃል ጌታሁን፣ ቴዎድሮስ ክብካብ፣ ሚኪያስ ሰብስቤ፣ ሰሎሞን ጎሹና ሔኖክ ያሬድ ናቸው)

ከምርጫው ዋዜማ ጀምሮ የባህር ዳር ከተማ ንግድ መደብሮች በጊዜ መዘጋት ጀምረዋል፡፡ በምርጫው ዕለትም የሕዝቡና የተሸከርካሪዎች ተቀዛቅዞ፣ አብዛኛው ሕዝብ በሌሊት ወጥቶ ድምጽ ከመስጠት ውጭ እንደወትሮው በባህር ዳር
ጎዳናዎች ላይ የነበረው እንቅስቃሴ ተዳክሞ ታይቷል፡፡ በቀድሞው የከተማዋ አስተዳደር በ17 ቀበሌዎች በአሁኑ አስተዳደራዊ መዋቅር ደግሞ በዘጠኝ ክፍለከተሞች የተደራጀችው ባህር ዳር ከተማ፣ ለ2007 ዓ.ም. ጠቅላላ ምርጫ በከተማው ከሚኖረው ሕዝብ ውሰጥ ድምጽ ለመስጠት ከ92 ሺሕ በላይ ነዋሪ ተዝግቦ ነበር፡፡ የከተማው ምርጫ ቦርድ ጽሕፈት ቤት ማስተባበሪያ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት 86 ከመቶ ያህል የባህር ዳር ነዋሪ ግንቦት 16 2007 ዓ.ም. ድምጽ በመስጠት ተሳትፏል፡፡
ፋሲሎ ክፍለ ከተማ ወይም በቀድሞው ጊዜ ቀበሌ 03ና 15 የነበሩት፣ ሕዳር 11 ወይም ቀበሌ 11፣ ጣና ክፍለ ከተማ (ቀበሌ 11)፣ ሽንብጥ (ቀበሌ 13)፣ በላይዘለቀ (ቀበሌ 07/08)፣ ሠፈረ ሰላም (ቀበሌ04)፣ ግሽ አባይ (ቀበሌ 12ና 16)፣ ሹም አቦክፍለከተማ (ቀበሌ 10) በሚባሉትና በሌሎችም የተደለደሉ 115 የምርጫ ጣቢዎች ውስጥ ምርጫ ሲካሔድ በዋለበት ዕለትም ሆነ ከምርጫው ዋዜማ በፊትም ቢሆን በሦስት ወገን የሚሰሙ ምርጫውን የተመለከቱ ድምጾች ነበሩ፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ገዥው ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ብአዴን/ኢሕኣዴግና ምርጫ ቦርድ በየፊናቸው በባህር ዳር ሊካሔድ ስላለው ምርጫ ተናግረዋል፡፡
በምርጫው ዋዜማ ፓርቲዎች ምን አሉ
በባህር ዳር ከሚወዳደሩ ፓርቲዎች መካከል ከምርጫው አስቀድሞ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የሰማያዊና የኢትዮጵያውያውን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) እንዲሁም የገዥው የብአዴን/ኢሕኣዴግ አመራሮች በፊናቸው የሚሉት አላቸው፡፡
በአማራ ክልል ከተወዳደሩት 16 የፖለቲካ ፓርቲዎችና አንድ የግል ዕጩ አኳያ፣ በሁሉም መስኩ ብኣዴን ፈርጣማ ነበር፡፡ በመላው አማራ ክልል ካቀረባቸው 137 ዕጩ ተወዳዳሪዎች ባሻገር የምርጫ ቅስቀሳ ሲያካሒድ፣ በጀት ሲመድብ፣ ታዛቢ ሲያሰማራ ወዘተ. ከፍተኛውን የበላይነት ይዞ ነው፡፡ በአንጻሩ የብኣዴን ተፎካካሪዎች በራሳቸው የአቅም ችግርና በገዥው ፓርቲ ደረሱብን ባሏቸው ጫናዎች ከቅስቀሳ እንከ ታዛቢ ማሰማራት ባለው ሒደት ላይ ደካማ ሆነው ታይተዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 51፣ ለክልል ምክር ቤት 82፣ ኢዴፓ ለተወካዮች 56፣ ለክልል 25፣ መኢኣድ፣ ቅንጅት ለተወካዮች 37፣ ለክልል 22፣ አምድነት ለተወካዮች ምክር ቤት 24፣ ለክልል 28 ዕጩ ተመራጮችን ካስመዘገቡ መካከል ናቸው፡፡
ኢዴፓ፣ ቅንጅት፣ ኢዴኣን፣ አገሕዴፓ/ የአገው ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/ ብኣዴን/ በየ15 ቀኑ በጋራ ይነጋገራሉ፡፡ የባህር ዳር ከተማ የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ፈንታ ደጀን ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ብኣዴን ኢሕኣዴግ እንደ ፓርቲ የተቃሚዎቹ ተወዳዳሪ ቢሆንም፣ እንደመንግሥት ግን ተወዳዳሪዎቹ ላይ ጫና ይደረግባቸው እንደሆነ፣ ተወዳዳሪ ፓርቲዎች እገዛ ይፈልጉ እንደሆነ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡ አቶ ፈንታ ደጀን በባህር ዳር ከተማ የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢና የብኣዴን አመራር ናቸው፡፡ አቶ ፈንታ ለፓርቲዎች ይህንን ማድረጋችን ለዴሞክራሲ ስንል ነው ባይ ናቸው፡፡ ‹‹ይህንን የምናደርግበት ምክንያት ለመድብለ ፓርቲ ሥርዓትና ለዴሞክራሲ መጎልበት የሚናቸውን አስተዋጽኦ ግምት ውስጥ በማገባት ነው፤›› ብለዋል፡፡
ሆኖም በባህር ዳር ምርጫ ክልል በገዥው፣ በተቃዋሚ ፓርቲዎችና በምርጫ ቦርድ ጽሕፈት ቤት አስተባባሪዎች የተነሱ ቅሬታዎች ነበሩ፡፡ የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢው አቶ ፈንታ ከሚጠቅሷቸው ችግሮች መካከል የፖስተር መቀደድ፣ የባነር ማስታወቂያ መነሳት ችግሮች ይጠቀሳሉ፡፡ ያለመጣጣም ‹‹የመገፋፋት››፣ የሥነ ምግባር ደንብ ጥሰት በፓርቲዎች ሲፈጸሙ ነበር የሚሉት አቶ ፈንታ በተለይ አገዴፓ በገበያ ቀናትና በአብያተ ክርሲያናት ውስጥ ቅስቀሳ በማድረጉ ጥሰት ፈጽሟል ብለዋል፡፡ እንዲህ ያሉ ክሶች ሲቀርቡበት የነበረው አገዴፓ ስህተቶቹን እንዲያርም መደረጉን፣ በጨለማ ስብሰባ ሲያካሒዱ የነበሩ ፓርቲዎች እንደነበሩም አቶ ፈንታ ይናገራሉ፡፡ እነዚህ ችግሮች በውይይትና በመነጋገር መፈታታቸውን አስታውቀዋል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ ከሌሎች ይልቅ በ2007ቱ ምርጫ ተራማጅ የነበረና ለመንግሥትም ስጋት መሆኑ የታየ ይመስል ነበር፡፡ በአጥፊነት መንግሥት ደጋግሞ ስሙን ሲያነሳው ከርሟል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ውስጥ አባል አይደለም፡፡ አባል ያልሆነበት ምክንያትም ምክር ቤቱ ላይ እምነት ስለሌው እንደሆነ ይገልጻል፡፡ ሆኖም ሰማያዊን ጨምሮ የምክር ቤቱ አባል የሆኑ ፓርቲዎች በባህር ዳር፣ በዘጌ መሸንቴ፣ በዘንዘልማና በጢስ አባይ ዙሪያ የታሰሩባቸው ታዛቢዎችና ዕጩ ተወዳዳሪዎች እንደነሩ ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዴምካራሲያዊ ፓርቲ(ኢዴፓ)ና የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች በባሕር ዳርና በዙሪያው በሚገኙ የምርጫ ክልሎች ለተመራጭነት ያቀረቧቸው ዕጩዎችና የምርጫ ታዛቢዎች ላይ ምርጫው ሊካሔድ አንድ ቀን እስኪቀረው ድረስ እሥራትና ድብደባ ሲፈጸምባቸው እንደነበር ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ የአካባባው ምርጫ አስፈጻሚዎች ችግሩን እንደማያውቁት አስታወቀዋል፡፡
ሻምበል ያየህይራድ ዘለቀ የኢዴፓ ተወካይና በባህር ዳር ምርጫ ክልል ፓርቲያቸውን ወክለው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚወዳደሩ ናቸው፡፡ ሻምበል ያየህይራድ በባህር ዳር ከተማ ለሪፖርተር የምርጫ ዘጋቢ እንዳስታወቁት፣ እሳቸው በሚወዳደሩበት የምርጫ ክልልም ሆነ በባህር ዳር ዙሪያ በሚገኙት ዘጌ መሸንቲ፣ ጢስ አባይ-ዘንዘልማ የምርጫ ክልሎች ውስጥ የኢዴፓ አባላት ላይ እሥራትና እንግልት ተፈጽሟል፡፡ በተለይ በዘጌ መሸንቲና በጢስ አባይ-ዘንዘልማ ምርጫ ጣቢያዎች ላይ ለታዛቢነት ተመድበው የነበሩት ሁለት የፓርቲው ተወካዮች አርብ ዕለት ታሥረው በማግሥቱ መፈታታቸውን ገልጸዋል፡፡ በምን ምክንያት እንደታሰሩ እንዳላወቁ ገልጸዋል፡፡ የፖስተሮች መቀደድ፣ የባነር ማስታወቂያዎች መነሳት ሲያጋጥሙ ከነበሩ ችግሮች መካከል የሚጠቀሱ መሆናቸውን ሻምበል ያየህይራድ አስታውቀዋል፡፡ በጎንጂ፣ በቆለላ፣ በአዴት ምርጫ ክልሎች እንዲወዳደሩ ያቀረባቸው ዕጩዎች በምርጫ ቦርድ መሰረዛቸውንና የተሠረዙበት ምክንያትም ለኢዴፓ እንዳልተገለጸት ተናግረዋል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲም ተመሳሳይ ጫና ሲደርስበት እንደቆየ አስታውቋል፡፡ የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለሪፖርተር በሰጡት ማብራሪያ፣ በምሥራቅና ምዕራብ ጎጃም ዘኖች ያቀረባቸው ዕጩዎች ላይ በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ ለበርካታ ጊዜያት እሥራትና ድብደባ ተፈጽሟል፡፡ በተለይ ሲነን በምትባለው ወረዳ በርካታ አባላቱ ሲታሰሩ እንደነበር አቶ ናትናኤል ገልጸዋል፡፡ በባህር ዳር ምርጫ ክልል እንዲወዳደሩ ካቀረባቸው ሁለት ዕጩዎች አንዱ ተሰርዘው፣ በአንድ አባል ብቻ ለተወካዮች ምክር ቤት ለመወዳደር መገደዱን አስታውቀዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ የባህር ዳር ጽሕፈት ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ ማሩ ዳኜም በርካታ እንግልት በአባሎች ላይ ሲደርስ መቆየቱን ገልጸው፣ ሚዲያው በሚደርስብን በድልና እንግልት ላይ ዝምታን መርጧል ሲሉ ወቅሰዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በአገርአቀፍ ደረጃ 200 ዕጩዎች አንደተሰረዙበት ሲገልጽ፣ ኢዴፓ በበኩሉ 90 ዕጩዎች እንደተዘሩበት ይፋ አድርጓል፡፡
የባህር ዳርና ዙሪያው የምርጫ ቦርድ ጽሕፈት ቤት አስተባባሪዎች በበኩላቸው ታሠሩ ስለተባሉት የሁለቱ ፓርቲዎች አባላት የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልጸዋል፡፡ አቶ ገረመው አሥራት የባህር ዳር ምርጫ ክልል፣ የምርጫ ቦርድ ጽሕፈት ቤት አስተባባሪ ናቸው፡፡ አቶ ገረመው ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ በምርጫ ቦርድ አሠራር መሠረት ፓርቲዎች በደብዳቤ የደረሱባቸውን ችግሮች ማሳወቅ ሲኖርባቸው፣ ቦርዱ ከሰማያዊም ሆነ ከኢዴፓ በጽሑፍ የደረሰው ምንም ዓይነት አቤቱታ የለም፡፡ በዘጌ መሸንቲ ምርጫ ክልል የምርጫ አስተባባሪዎች ኢዴፓ ታስረውብኝ ነበር ስላላቸው የምርጫ ታዛቢዎች የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልጸዋል፡፡
የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በበኩሉ ‹‹አንድም ዕጩ ሆነ ታዛቢ ስለመታሠሩ ምንም የመጣ አቤቱታ የለም፡፡ እርግጥ ቀደም ሲል በምዕራብ ጎጃም ውስጥ በምትገኝ አንዲት ወረዳ ማንነቱ ያልታወቀ ሰው ተይዞ ነበር፡፡ ማንነቱ ሲጠየቅ ዕጩ ነኝ እናንተ ልትጠይቁኝ አይገባም በማለት ግጭት ተፈጥሮ ታስሮ ነበር፡፡ ይሄ ሰው ታስሮ የነበረው በዕጩ ምዝገባ ጊዜ ሲሆን ያኔውኑ ተለቋል፤›› በማለት አቶ ፈንታ ስለፓርቲዎቹ ቅሬታ ከሪፖርተር ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ ነበር፡፡ ምርጫው ሊካሄድ አንድ ቀን እስኪቀረው ድረስ ዘጌ መሸንቲም ሆነ ጭስ አባይ ላይ አንድም ሰው አልታሰረም ካሉ በኋላ ‹‹የታሠረ፣ የተደበደበ፣ የተሰረዘ እኔ የማውቀው ዕጩ የለም፤›› በማለት በተቀናቃኝ ፓርቲዎች በኩል ለሪፖርተር ያነሷቸውን ቅሬታዎች እንደማያውቋቸው ገልጸዋል፡፡
የፓርቲዎች የዕጩ ተወዳዳሪ ወኪል ታዛቢ መመዝገብ ያለበት የምርጫ ቀን ከመድረሱ አሥር ቀናት በፊት ሲሆን፣ መመሪያ ቀጥር 3/2001 አንቀጽ 19 ላይ በሰፈረው መሠረት ፓርቲዎች ታዛቢዎቻቸውን በማቅረብ እንዲያስመዘግቡ የሚጠይቅ ቢሆንም፣ ምርጫው አንድ ቀን እስኪቀረው ድረስ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን በመወከል ለሚገኑ ታዛቢዎች መታወቂያ ሲሰጥ እንደነበር በባህር ዳር ዙሪያ ከሚገኙ ምርጫ አስተባባሪዎች ተገልጿል፡፡
በምርጫው ዕለት ያልታዩት የተቃዋሚ ፓርቲ ታዛቢዎች
የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ታዛቢ ብቻም ሳይሆን ዕጩዎቻቸውን ማስዝገብና ለምርጫ ማወዳደር እንዳይችሉ መደረጋቸውን ሲገልጹ ከርመዋል፡፡ ያለምንም ማብራሪያ ዕጩዮቼ ተሰርዘውብኛል ካለው ኢዴፓ እስከ ሰማያዊ ፓርቲ በተወዳዳሪ ዕጩ ስረዛ ምርጫ ቦርድን አጥብቀው ሲኮንኑ ከርመዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ 200 ዕጩዎቹ፣ ኢዴፓም ከ90 በላይ ተወዳዳሪዎቹ መሰረዛቸውን በማስመልከት ደጋግመው ሲጠይቁና ፍርድ ቤት ሲመላለሱ ከከረሙ ፓርቲዎች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
ድምጽ በተሰጠበት ዕለት በበርካታ የምርጫ ጣቢያዎች የተቃዋሚ ፓርቲዎች ታዛቢዎችን ማየት አልተቻለም፡፡ የምርጫ አስፈጻሚዎች ስለጉዳዩ ሲጠየቁም፣ የተቃዋሚ ፓርቲ ታዛቢዎች አንዳልመጡና እንዳላነጋገሯቸው ጠቅሰዋል፡፡ በአንጻሩ የብኣዴን/ኢህኣዴግ ታዛቢዎች በሁሉም የባህር ዳር ምርጫ ክልልና በዙሪያው በሚገኙ ምርጫ ጣቢዎች ሁሉ ላይ ተገኝተዋል፡፡
የክልሉም ሆነ የባህር ዳር ከተማ ምርጫ አሳታፊነቱና ለሌሎች ተቀናቃኝ ፓርቲዎች የሰጠው ቦታ ፍትሃዊ ነው ብሎ ብአዴን ያምናል ወይ? ተብለው የተጠየቁት አቶ ፈንታ፣ ‹‹በአማራ ክልል ለተወካዮች ምክር ቤት 137 ወንበር አለ፡፡ ለክልል ምክር ቤት 292 ወንበር አለ፡፡ ለእነዚህ ወንበሮች ዕጩ የማቅረብ ሥራ ሠርተናል፡፡ እነሱም [ተቃዋሚዎች] ዕጩ የማቅረብ ሥራ ይሠራሉ፡፡ ቀድመው ያላፈሩትን አባልና ዕጩ በዚህ ወቅት ሊያገኙ አይችሉም፡፡ ይህ ዓይነት ነገር ገጥሟቸው ሊሆን ይችላል፡፡ ብኣዴን ስለፈለገ ወይም ስላልፈለገ ዕጩ ከማቅረብ የሚያግዳቸው ነገር የለም፡፡ እስከሁን በመደበኛ ሁኔታ እየሔድን ነው የነበረው፤›› ብለዋል፡፡
በአንጻሩ ተቃዋሚዎች የሚሰረዙባቸው ዕጩዎች ብቻ ሳይሆኑ ታዛቢዎች መሆናቸውንም ሲገልጹ ተደምጠዋል፡፡ በባህር ዳር ምርጫ ክልል ከሚወዳደሩ ፓርቲዎች አንዱ የሆነው የኢትጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)፣ የታዛቢነት መታወቂያ ከሰጣቸው ከ60 በላይ ታዛቢዎች ውስጥ አብዛኞቹ እንዳልተገኙለት የባህር ዳር ከተማ የኢዴፓ አመራርና ፓርቲውን ወክለው ለተወካዮች ምክር ቤት የተወዳደሩት ሻምበል ያየህይራድ ዘለቀ ናቸው፡፡ ሻምበል ያየህራድ የፓርቲው ታዛቢዎች ያልተገኙት በፍርሃት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ባሻገር ግን ሁለት ታዛቢዎች መታወቂያችሁ ላይ ፎቶግራችሁ አልተለጠፈበትም ተብለው ወደ ምርጫ ጣቢያ እንዳይገቡ መከልከላቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ይህም ሆኖ የኢዴፓ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጫኔ ከበደ ከተወዳደሩባቸውና ጠንካራ ፉክክር ይኖራቸዋል ተብለው ከሚጠበቁት አካባቢዎች አንዱ የባህር ዳር ዙሪያ ዘንዘልማ ምርጫ ክልል ቢሆንም፣ ሪፖርተር በተገኘበት የዘንዘልማ ሚካኤል ምርጫ ቁጥር 2፣ በብኣዴንና ከሕዝብ ታዛቢዎች እንዲሁም ዘግይተውም ቢሆን ከሲቪክ ማኅበራት ጥምረት ታዛቢዎች ታይተዋል፡፡ ከዚህ ውጭ የኢዴፓ ታዛቢዎች በቦታው አልተገኙም ነበር፡፡ በባህር ዳር ምርጫ ክልል ዶክተር በቃሉ አጥናፍና አቶ ወርቁ ጥላሁን የተባሉትን ዕጩዎች በመወከል ከሰማያዊ ፓርቲ የተገኙ የምርጫ ታዛቢዎች ቁጥርም የሉም በሚያስብል መጠን ተገኝተዋል፡፡
በባህር ዳር ምርጫ ክልል ካሉት 115 ምርጫ ጣቢዎች፣ 663 መራጮች የተመዘገቡበት የሰፈረ ሰላም 04-2ለ ምርጫ ጣቢያ የብኣዴን፣ የኢዴፓና የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ታዛቢዎች ተገኝተዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢ አቶ እንደሻው አቤ ‹‹…ችግሮች አይከሰቱም አይባልም፡፡ ጥቃቅን ችግሮች ተከስተዋል፡፡ ለምሳሌ ለአረጋውያን በድምጽ መስጫ ጣቢያ ውስጥ የድምጽ አሰጣጥ ገለጻ መስጠት ተገቢ ባለመሆኑ ይህ ሒደት ከድምጽ መስጫው ውጭ እንዲደረግ ከብኣዴን፣ ከሕዝብ ታዛቢዎችና ከሲቪክ ማኅበራት ታዛቢዎች ጋር ተነጋግረን እየተስተካከለ ነው፤›› ብለው ነበር፡፡ አቶ ደረጄ ተሾመ የኢዴፓ ዕጩ ተዋወዳዳሪ ታዛቢ ናቸው፡፡ ድምጽ አሰጣጡ ጥሩ አካሔድ ማሳየቱን ገልጸው፣ ሆኖም አረጋውያንን በተመለከተ ከሰማያዊ ፓርቲ ተወካይ ጋር ተመሳሳይ ሐሳብ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ባሻገር ግን አንዳንድ አስገራሚ ክስተቶችንም መታዘብ ተችሏል፡፡ ገነቱ በላይ በሽንብጥ ክፍለከተማ ምርጫ ጣቢያ 1-ሀ-1 አስተባባሪ ናቸው፡፡ በዚህ ጣቢያ ድምጽ ለመስጠት የተመዘገቡ 851 መራጮች ድምጽ እየሰጡ በነበረበት ዕለት ያልተለመደ አሠራር ሲካሔድ ታይቷል፡፡
በምርጫ ጣቢያው አንድ ወጣት አቅመ ደካሞችና አረጋውያንን እንዲሁም የአካል ጉዳት ያለባቸውን መራጮች ለማገዝ በሚል በምስጢር ድምጽ መስጫ ቦታው አብሮ ሲገባ ታይቷል፡፡ የምርጫ አስተባባሪው የወጣቱን ገለልተኛነት፣ የትኛውንም ፓርቲ ያልወከለና ያልወገነ እንደሆነ በመግለጽ ተከራክረዋል፡፡ ይህም ሆኖ ወጣቱ አንድም የተቃዋሚ ፓርቲ ታዛቢ ባልተገኘበት ምርጫ ጣቢያ በፖለቲካ ፓርቲ ዕጩ ታዛቢዎች ወንበር ላይ ተቀምጦ ታይቷል፡፡
ምርጫው መጠናቀቁን ተከትሎ በባህር ዳር ድምጽ ይሰጣል ተብሎ ከሚጠበቀው 92, 379 መራጭ ሕዝብ ውስጥ 86 ከመቶ ያህሉ ድምጹን መስጠቱን የባህር ዳር ምርጫ ክልል አስፈጻሚ ጽሕፈት ቤት ይፋ አድርጓል፡፡ በባህር ዳር ከተማ በሚገኙት የምርጫ ጣቢያዎች በሁሉም የምርጫ ውጤቶች መለጠፋቸውም ታውቋል፡፡ እስካሁንም ከየትኛውም ተወዳዳሪ ፓርቲ አንድም ቅሬታም ሆነ ክስ እንዳልደረሳቸው ለጽሕፈት ቤታቸው እንዳልቀረበ የገለጹት በባህር ዳር ምርጫ ክልል የምርጫ አስተባባሪው አቶ ገረመው አሥራት ናቸው፡፡

ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. በተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሁለት የግል ዕጩ ተወዳዳሪዎች፣ ድሬዳዋ ከተማ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያሉትን ሁለት ወንበሮች ለመወከል ተወዳድረዋል፡፡
የድሬዳዋ ከተማ በቻርተር ራሱን እንዲያስተዳድር የተፈቀደለት የፌዴራሉ መንግሥት ግዛት ሲሆን፣ በፌዴራል ፓርላማ ውስጥ የሁለት ወንበሮች ውክልና አለው፡፡ በመሆኑም እነዚህን ሁለት ወንበሮች የሚወክሉ ዕጩዎችን ለመምረጥ ድሬዳዋ በሁለት የምርጫ ክልልና ከሁለት መቶ በላይ የምርጫ ጣቢያዎች ተከፋፍላለች፡፡
ድሬዳዋ ከተማን ለሁለት በሚከፍላት አሸዋ ተብሎ የሚጠራውን አካባቢ መሠረት በማድረግ ከአሸዋ በታች ያለውን አካባቢ ምርጫ ክልል አንድ፣ ከአሸዋ በላይ ያለውን ምርጫ ክልል ሁለት ተብሎ ተከልሏል፡፡ በእነዚህ የምርጫ ክልሎች ለመወዳደር የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦሕዴድ)፣ የኢትዮጵያ ሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሶዴፓ)፣ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ)፣ የወለኔ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ወህዴፓ)፣ ሰማያዊ ፓርቲ፣ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ (አንድነት)፣ የኦሮሞ አቦ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦአነግ) እና ሁለት የግል ተወዳዳሪዎች የምርጫ ቦርድን ዕውቅና አግኝተው በዕጩ ተወዳደሪነት ራሳቸውን አቅርበዋል፡፡
የግል ተወዳዳሪዎቹ ሙክታር ኢብራሂምና ሙስጠፌ ሞሚን የሚባሉ ሲሆን፣ እንደ ቅደም ተከተላቸው ፀሐይና ዳክዬ የምርጫ ምልክቶቻቸው አድርገው የከተማው ነዋሪ እንዲመርጣቸው ቀስቅሰዋል፡፡
ሙክታር ኢብራሂም የ30 ዓመት ወጣት ነው፡፡ ተመርጦ የፓርላማውን መቀመጫ ቢያገኝ፣ ‹‹የተሻለ ኅብረተሰብ ለመፍጠርና በተሻለ የእርሻ ኢኮኖሚ ላይ የተመሠረተ ኅብረተሰብን ማየት ነው፤›› ይላል፡፡ ሙክታር ይህን ይላል እንጂ በዋናነት ትኩረት ከሚሰጣቸው ጉዳዮች መካከል ግንባር ቀደሙ፣ ‹‹በክልላችን መንገዶች እንዲስፋፉና የኢንዱስትሪ ክልል ለማድረግ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፤›› የሚለው ተጠቃሽ ነው፡፡
ከምርጫው በፊት ሪፖርተር ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች በከተማዋ ለሚወዳደሩ አራት ፓርቲዎች ከፍተኛ ግምት ሰጥተዋል፡፡ እነዚህም ኦሕዴድ/ኢሕአዴግ፣ ኢሶዴፓ፣ መድረክና ሰማያዊ ፓርቲ ናቸው፡፡ በተለይ ኢሶዴፓና ኦሕዴድ ከፍተኛ የምርጫ ቅስቀሳ ያደረጉ መሆናቸው፣ የኢሶዴፓ የምርጫ ቅስቀሳ ደግሞ የበለጠ የተደራጀ እንደነበር ይገልጻሉ፡፡
በኢሶዴፓ በኩል በዕጩነት የቀረቡት መሐመድ የሱፍ ዑመር ናቸው፡፡ አቶ መሐመድ የሱፍ ባለፈው ምርጫ በዚሁ የምርጫ ክልል ሁለት ተወዳድረው የፓርላማ መቀመጫ ያገኙ ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የፓርላማው የአርብቶ አደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡
በኦሕዴድ በኩል የቀረቡት ዕጩ አቶ አብዱሰመድ መሐመድ ኢብራሂም ናቸው፡፡ አቶ አብዱሰመድ እንደ ኢሶዴፓው ተወካይ በ2002 ዓ.ም. በነበረው አገር አቀፍ ምርጫ የሕዝብን ውክልና አግኝተው የፌዴራል ፓርላማውን የተቀላቀሉ ቢሆንም፣ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ በመሆናቸው አብዛኛውን ጊዜ በመንግሥት ሥራ ላይ ነው የሚያሳልፉት፡፡
በሰማያዊ ፓርቲ በኩል በዕጩነት የቀረቡት ደግሞ አቶ ዳንኤል ጉግሳ ገመቹና ገዛኸኝ አሰፋ የተባሉ ግለሰቦች ናቸው፡፡ በመድረክ በኩል ደግሞ አቶ አህመድ ጀማል ብቻ ናቸው፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ተወካይ አቶ ዳንኤል ጉግሳ በምርጫ ክልል አንድ ከኦሕዴዱ ከአቶ አብዱሰመድ ጋር ለፉክክር ቀርበዋል፡፡ የሰማያዊው አቶ ገዛኸኝ አሰፋ ደግሞ ከኢሶዴፓ ተወካዩ አቶ መሐመድ የሱፍና ከመድረኩ ተወካይ አቶ አህመድ ጀማል አህመድ ጋር ቀርበዋል፡፡
የድሬዳዋን ሞቃታማ የአየር ሁኔታ ምክንያት ኅብረተሰቡ ባዳበረው ባህል መሠረት ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት ከጠዋቱ 1፡30 ሥራ እንደሚጀምር ይታወቃል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች ከዚያ ቀድመው መንቀሳቀስ የሚጀምሩ በመሆናቸው ገበያውም ይደራል፡፡ በመሆኑም የምርጫውን ዕለት ኅብረተሰቡ እንዴት እንደሚጠቀምበት ቀድሞ መገመት ይቻላል፡፡
በዚሁ መሠረት ሪፖርተር በምርጫው ዕለት ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በተዘዋዋረባቸው የምርጫ ጣቢያዎች፣ በርካታ ነዋሪዎች (አብዛኞቹ ሴቶች ናቸው) ተሠልፈው ድምፃቸውን ሲሰጡ ለመመልከት ችሏል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አሰድ ዚያድ ገንደቆሬ አካባቢ ማለትም በምርጫ ክልል አንድ ምርጫ ጣቢያ ሦስት ድምፃቸውን ለመስጠት ከጠዋቱ አንድ ሰዓት አካባቢ ተገኝተዋል፡፡ ከእሳቸው በፊት ግን 103 ነዋሪዎች ድምፃቸውን እንደሰጡ የምርጫ ጣቢያው አስተባባሪ አቶ ጃፋር አሚን ገልጸዋል፡፡
ከሌሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ የምርጫ ጣቢያው አስተባባሪዎች ተገናኝተው ዝግጅታቸውን እስከ 12 ሰዓት ድረስ አጠናቀው፣ 12 ሰዓት ላይ ድምፅ ለማሰጠት ክፍት ማድረጋቸውን አስረድተዋል፡፡
የድሬዳዋ ከንቲባ አቶ አሰድ ዚያድ ድምፃቸውን ከሰጡ በኋላ፣ ቅድመ ምርጫ ዝግጅቱ በድሬዳዋ በሰላማዊ ሁኔታ ተጠናቆ በስኬት ለምርጫው ዕለት መድረስ መቻሉን ለጋዜጠኞች ገልጸዋል፡፡
የምርጫው ሒደትም ከተጠበቀው በላይ በፍጥነት እየተከናወነ እንደነበር የገለጹት ከንቲባው፣ እንደ ቅድመ ምርጫው ሁሉ ድኅረ ምርጫውም ሰላማዊ ሆኖ እንደሚጠናቀቅ እርግጠኛ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡
ሪፖርተር በተዘዋወረባቸው 32 የምርጫ ጣቢያዎች በእያንዳንዳቸው በአማካይ የተመዘገቡ መራጮች (ካርድ የወሰዱ ነዋሪዎች) ቁጥር 650 ይሆናል፡፡ የድሬዳዋ ነዋሪዎች የዕለት ሥራቸውን በጠዋት ከውነው እንደሚፈጽሙት ሁሉ፣ ሪፖርተር በተዘዋወረባቸው የምርጫ ክልሎች ከረፋዱ 5፡30 ሰዓት ላይ 600 የሚሆኑ መራጮች በአማካይ ድምፃቸውን ሰጥተው ነበር፡፡
በከዚራ ሁለት ምርጫ ጣቢያ ለመምረጥ የተመዘገቡ መራጮች ብዛት 562 ሲሆን፣ እስከ ጠዋቱ 1፡30 ድረስ 136 መራጮች ድምፃቸውን ሰጥተዋል፡፡
‹‹በአመዛኙ ምርጫው ከእኩለ ቀን በፊት የተጠናቀቀ ቢሆንም፣ የግዴታ በሕጉ መሠረት እስከ 12 ሰዓት ድረስ መቆየታችን ግድ ነው፤›› በማለት የምርጫ ጣቢያው አስተባባሪ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
ሪፖርተር በተዘዋወረባቸው አካባቢዎች በጥቂቶቹ ብቻ የወለኔ ፓርቲ ተወካዮችን ቢመለከትም፣ ከኢሕአዴግ/ኦሕዴድና ከኢሶዴፓ ውጪ የፓርቲ ታዛቢዎችን ያሰማራ ተቃዋሚ ድርጅት የለም፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ ተወዳዳሪ የሆኑት አቶ ዳንኤል ጉግሳ ፓርቲያቸው የመደበው በጀት በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ የፓርቲ ታዛቢዎችን አበል ከፍሎ ሙሉ ቀናቸውን በመታዘብ ሥራ ላይ እንዲውሉ ለማድረግ ይቅርና በራሪ ወረቀቶችን ከመበተን ያለፈ የቅስቀሳ ሥራ እንዳላደረጉ ገልጸዋል፡፡
ከሌሎቹ የአገሪቱ ክፍሎች በተለየ የፓርላማ ዕጩዎችን ብቻ የሚመርጡት የአገሪቱ ዋና ከተማ አዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተሞች ናቸው፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ምርጫ መደረግ የጀመረው በ1999 ዓ.ም. ነው፡፡ ከዚያ ቀደም ድሬዳዋ ከተማ ተጠሪነቷ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በመሆኑ በሹመት እንጂ ድሬዳዋ ራሷን ማስተዳደር አልጀመረችም ነበር፡፡
ይህ የሆነበት ምክንያት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልላዊ መንግሥት በድሬዳዋ ላይ የይገባኛል ጥያቄ በማንሳታቸው፣ ጥያቄው እስኪመለስ ድሬዳዋ በፌዴራል አስተዳደር ሥር እንድትሆን በሽግግር መንግሥት ወቅት በመወሰኑ ነው፡፡
ይህንን ጥያቄ እስካሁን መመለስ ባለመቻሉም ድሬዳዋ በፌዴራሉ መንግሥት ሥር ሆና ራሷን የማስተዳደር ሥልጣን በፓርላማ በፀደቀ ቻርተር ያገኘች ከተማ ነች፡፡ ይህንን ዕድል ካገኘች ጀምሮ የኦሕዴድና የኢሶዴፓ ተመራጭ ከንቲባዎች እያስተዳደሯት ይገኛሉ፡፡

ሰማኒያ ስድስት የምርጫ ጣቢያዎች በሚገኙበት በኦሮሚያ ክልል በኢተያ የምርጫ ክልል ሒጦሳ ወረዳ፣ በ2007 ዓ.ም. ጠቅላላ ምርጫ ለአራተኛ ጊዜ በተከታታይ ኦሕዴድ/ኢሕአዴግን ወክለው ለምርጫ የቀረቡት የሕዝብ ተወካዮች
ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳን ለመቀበል ሲጠባበቁ የነበሩት ደጋፊዎቻቸው ያልጠበቁትን ዜና ሰምተዋል፡፡ አቶ አባዱላ የምርጫ ካርዳቸውን በአዲስ አበባ በመውሰዳቸው የሚመርጡትም እዚያው አዲስ አበባ በመሆኑ፣ በዘንድሮው ብሔራዊ ምርጫ አቶ አባዱላን ኢተያ ላይ ማግኘት አልቻሉም፡፡ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በትውልድ አካባቢያቸው በመገኘት ምርጫ ሲያደርጉ በቴሌቪዥን የተመለከቱ ደጋፊዎቻቸው የአቶ አባዱላ በወረዳቸው አለመገኘት ቅር እንዳሰኛቸው ለሪፖርተር የገለጹም ነበሩ፡፡ ‹‹እዚህ ተገኝቶ ሲመርጥ ብናየው ደስ ይለን ነበር፣›› ያሉት አቶ ቶሎሳ አዱኛ እና ወ/ሮ ደሚቱ ገመቹ፣ የአቶ አባዱላን በምርጫ ጣቢያው አለመገኘት ያልጠበቁት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በሥራ ምክንያት እንደማይመጡም ከአካባቢው የኦሕዴድ ባለሥልጣናት እንደተነገራቸው ጠቁመዋል፡፡
‹‹እሱ ሥራውን ቀድሞ ስለጨረሰ እዚህ የመምረጥ ያለመምረጡ ጉዳይ ችግር የለውም፡፡ በዚያ ላይ የሥራ ጫና አለበት፣›› ያሉት የወረዳው ኦሕዴድ/ኢሕአዴግ ተጠሪ አቶ ገመቹ አደራ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በአንፃሩ የአቶ አባዱላ በምርጫ ጣቢያው ተገኝቶ አለመምረጥ ለ28 ዓመቱ ብቸኛው ተፎካካሪያቸው አቶ ደረሠ ነገሠ መልካም አጋጣሚ እንደሆነ የተናገሩት የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኦብኮ) ታዛቢ ሻለቃ አደም ኑራ፣ በምርጫው ብዙ ችግሮችን እየተጋፈጡ ቢሆንም ብቸኛው የኦብኮ ተወዳዳሪ ውጤታማ ሊሆን የሚችልበት ዕድል መኖሩንም ተናግረው ነበር፡፡
‹‹በምርጫው ዕለት መራጮችን በድብቅ በመጥራት ትዕዛዛዊ ምርጫ እንዲያደርጉ መንገርን ጨምሮ የምርጫ ወረቀቶቹን ጥሎ የመውጣት ሒደት ነበር፤›› የሚሉት ታዛቢው፣ የምርጫ ኮሮጆዎቹ ደኅንነት፣ የምርጫ ቁሳቁሶቹ ጤናማነትና የምርጫ ሰዓቱን የመጠበቅ ሁኔታ ግን በግልጽ የታዘቡት ሀቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ቅድመ ምርጫ 2007 ኢተያ በኦሕዴድ/ኢሕአዴግ በኩል ሰፊ ሥራ የተሠራበት መሆኑን በአካባቢው የተለጠፉትን ፖስተሮች፣ መፈክሮችና ዓርማዎች በማየት መገንዘብ ይቻላል፡፡ በአንፃሩ አንድ የተቃዋሚ (ተፎካካሪ) ፓርቲ ዓርማም ሆነ ፖስተር ተለጥፎ አይታይም፡፡ ይህን በተመለከተ በሪፖርተር ተጠይቀው ምላሻቸውን የሰጡት የኦብኮው ዕጩ ተፎካካሪ አቶ ደረሠ፣ ፖስተሮቹና ዓርማዎቹ በተለጠፉበት ቅፅበት ተቀዳደው ይነሱ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ‹‹ከለጠፍን ከ20 እና ከ30 ደቂቃ በኋላ ስንመለስ በቦታው አናገኝም ነበር፤›› የሚሉት አቶ ደረሠ፣ ማን ይህን እንደሚፈጽም ግን በግልጽ እንደማያውቁ ያክላሉ፡፡ በአዳራሽ ደጋፊዎቻቸውን በመሰብሰብ ለማነቃቃት ሰፊ ጥረት ቢያደርጉም፣ የአካባቢው ባለሥልጣናት በሕዝቡ ላይ በነዙት ፍርኃትና ዛቻ አዳራሹ ቢፈቀድም ሰው ሊሰበሰብ እንዳልቻለ ገልጸዋል፡፡ አቶ ገመቹ ግን ይህንን ያስተባብላሉ፡፡ በምርጫ ጊዜ የሚደረግ የተለመደ አቤቱታ ነው በማለት፡፡
በምርጫው ዋዜማ የሒጦሳ ወረዳ እስከ ምሽቱ ድረስ ተረጋግታ የታየች ቢሆንም፣ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት በኋላ ግን ጭር ብላ አንግታለች፡፡ በኢተያ ከተማ የሚገኙ ሆቴሎችና መሸታ ቤቶች በምርጫው ምክንያት በሮቻቸውን መዝጋት እንዳለባቸው ለደንበኞቻቸው ሲናገሩ ነበር፡፡ በወረዳው የሚገኙ አብዛኞቹ የምርጫ ጣቢያዎች አስፈላጊውን የምርጫ ቅድመ ዝግጅት አሟልተው እሑድ ማለዳን ሲጠባበቁ እንደነበር መታዘብ ተችሏል፡፡ በአንዳንድ ገጠራማ ቦታዎች ግን እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት ድረስ ድንኳኖች ሲተከሉ ተስተውሏል፡፡ በምርጫው ዕለት ሕዝቡ በማለዳ ተሠልፎ ምርጫውን በሰላም ማካሄዱን በተወሰኑ የምርጫ ጣቢያዎች የተስተዋለ ሲሆን፣ ከረፋዱ አራት ሰዓት ጀምሮ ግን ብዙዎቹ የምርጫ ጣቢያዎች ጭር ብለው ታይተዋል፡፡ የኢተያ ከተማና አጎራባች ከተሞችም በምርጫው ዕለት ጭር ብለው ነበር፡፡
የኢተያ ምርጫ ክልል የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተጠሪ አቶ ቱሉ ሹሜ ምርጫው ያለምንም ችግር መከናወኑንና ከተወዳዳሪ ፓርቲዎችም የጎላ ቅሬታ እንዳልቀረበ ገልጸዋል፡፡ ሆኖም የኦብኮ ተወዳዳሪ በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች መራጮች በትዕዛዝ ምርጫ እንዲያደርጉ አቶ ከማል በሚባል የአካባቢው ባለሥልጣን በሚስጥር ይነገር ነበር የሚባለውን፣ ከኦብኮ ተፎካካሪ በቃል ሪፖርት እንደተደረገላቸው አቶ ቱሉ ገልጸዋል፡፡
በአካባቢው ለፉክክር የቀረቡት አራት ፓርቲዎች ኦሕዴድ/ኢሕአዴግ፣ ኦብኮ፣ አዲስ ትውልድና አንድነት ፓርቲ የነበሩ ቢሆንም፤ በምርጫው ሒደት ግን ተካፋይ የነበሩት ኦሕዴድ/ኢሕአዴግና ኦብኮ ብቻ ነበሩ፡፡ በአካባቢው አዲስ ትውልድ ፓርቲን የወከሉት አቶ ተሾመ ደረሰ ናቸው፣ አንድነትን የወከሉት ደግሞ ሻምበል አማን ሐሰን የተባሉ ግለሰብ ነበሩ፡፡ የአዲስ ትውልድ ፓርቲ ተወካይ አቶ ተሾመ በምርጫው ለመካፈል ምዝገባቸውን ከጨረሱ በኋላ በምርጫ ቅስቀሳውም ሆነ በውድድሩ ላይ አለመካፈላቸውን አስመልክቶ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ‹‹ለምርጫው የተመደበልን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ አቶ ሰለሞን በሚባል ሰው ስለተበላብን አቅም አጥሮን ነው፤›› በማለት መልሰዋል፡፡ እንደ አቶ ተሾመ ገለጻ፣ አቶ ሰለሞን የተባሉት ግለሰብ ነዋሪነታቸው አዲስ አበባ ሲሆን የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ አስፋው ጌታቸው ወደ ውጭ አገር ሲሄዱ፣ በጊዜያዊነት በአደራ አመራሩን የተረከቡ ናቸው፡፡ ሪፖርተር ግለሰቡን ለማግኘት ባደረገው ጥረት ግለሰቡ ስልካቸውን መመለስ ባለመቻላቸው ሳይሳካ ቀርቷል፡፡
ሰኞ ግንቦት 17 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢተያና በአጎራባች ወረዳዎች የምርጫ ውጤቱ ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ መለጠፍ የጀመረ ሲሆን፣ በአንዳንድ ቦታዎች ግን ውጤቱ በተለጠፈበት ቅጽበት ተቀዶ ታይቷል፡፡ ለምሳሌ በአሰላ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ተለጥፎ የነበረው የምርጫ ውጤት የኦሕዴድ/ኢሕአዴግን የምርጫ ውጤትና ደረጃን ብቻ ሲያሳይ፣ የሌሎቹን ተፎካካሪዎች ውጤትና ደረጃን የሚያሳየው ሰንጠረዥ ግን እንደተቀደደ ታይቷል፡፡
በአብዛኛዎቹ የምርጫ ጣቢያዎች ውጤቱ ከተለጠፈ በኋላ ግርግም አልነበረም፡፡ ከወትሮው የተለየ ነገርም አልተስተዋለም፡፡ የምርጫ ኮሮጆዎቹ ከየምርጫ ጣቢያው እየተሰበሰቡ በፖሊስ ታጅበው ወደየምርጫ ቦርዱ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ሲደርሱም ተስተውሏል፡፡ ሰኞ ዕለት በኢተያም ሆነ አሰላን ጨምሮ በሌሎቹ አጎራባች ወረዳዎች ሕይወት እንደተለመደው ቀጥላ ታይታለች፡፡ በ1992፣ በ1997፣ በ2002 እና በ2007 ዓ.ም. በኢተያ ለክልል ምክር ቤትና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኦሕዴድ/ኢሕአዴግ ዕጩ ተወዳዳሪ የነበሩት አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ በአራት ተከታታይ ምርጫዎች በመወዳደር ይታወቃሉ፡፡

በምርጫ 2007 በሰሜን ሸዋ ዞን ዘጠኝ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሕዝብ ተወካዮችና ለክልል ምክር ቤት ዕጩዎቻቸውን በማቅረብ ዝግጅት ሲያደርጉ ከርመዋል፡፡
አሉ የሚሏቸውን ችግሮች ይዘው ወደ ምርጫ የገቡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስሞታቸው ተመሳሳይ ነው፡፡
በሰሜን ሸዋ ዞን የምርጫ አስተባባሪ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተሰማ ከበደ፣ በዞኑ በሚገኙት 18 ምርጫ ክልሎች ብአዴን/ኢሕአዴግ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 17 ለክልል ምክር ቤት 36 ተወዳዳሪዎችን ማቅረቡን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ ሰማያዊ ፓርቲ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስድስት፣ ለክልል ምክር ቤት ደግሞ 16 ማቅረቡን፣ መኢአድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰባት ለክልል 14፣ ኢዴፓ ለተወካዮች ምክር ቤት አራት ለክልል ምክር ቤት አላቀረበም፡፡ ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አምስት ለክልል ምክር ቤት አንድ ተወዳዳሪ ሲያቀርብ፣ መኢብን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አንድ ለክልል ምክር ቤት ደግሞ ሁለት አቅርቧል፡፡ አዲስ ትውልድ ፓርቲ ለክልል ምክር ቤት አንድ ሲያቀርብ ለክልል ምክር ቤት አላቀረበም፡፡ አንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አራት፣ ለክልል ምክር ቤት አራት ሲያቀርብ፣ የአርጎባ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (አብዴን) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አንድ ለክልል ምክር ቤት አላቀረበም፡፡ የአርጎባ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (አሕዴድ) በተመሳሳይ ለተወካዮች ምክር ቤት አንድ ተወዳዳሪ ሲያቀርብ ለክልል ምክር ቤት አለማቅረቡን አቶ ተሰማ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
እንደ ኃላፊው ገለጻ፣ በዞኑ ባሉት የምርጫ ክልሎች ሁሉም ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ለሕዝብ ተወካዮችና ለክልል ምክር ቤት በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች የምርጫውን ሒደት ለሚከታተሉ ተቀማጭና ተንቀሳቃሾች ወኪሎች፣ በጊዜውና በሰዓቱ መታወቂያ ተሰጥቷል፡፡ ለአብነትም ሰማያዊ ፓርቲ በደብረ ብርሃን ከተማ የሚገኙትን 44 ምርጫ ጣቢያዎች ጨምሮ በሁሉም ወረዳዎች ተቀማጭና ተንቀሳቃሽ ወኪሎቹን አቅርቦ ለሁሉም መታወቂያው መሰጠቱን አስታውሰዋል፡፡ በምርጫው ዕለት ግን የተጣለባቸውን ኃላፊነት ሲከውኑ የተገኙት በደብረ ብርሃን ከተማ በሦስት ቀበሌዎች በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች ብቻ እንደነበረ፣ ቦርዱም ምናልባት ችግሩ ከገዥው ፓርቲ በሚደርስባቸው ጫናና ማስፈራት ሊሆን ይችላል በሚል ለማጣራት ባደረገው ሙከራ፣ አንድም የቀረበለት አቤቱታ እንደሌለ ነው ያስረዱት፡፡
በሰሜን ሸዋ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ምርጫ አስተባባሪ ወ/ሮ ሰርካለም ከበደ በበኩላቸው፣ የዞኑ ምርጫ ቦርድ አስተባባሪ እንዳሉት በዞኑ ደብረ ብርሃን ከተማን ጨምሮ በወረዳዎች ከጥቂቶቹ በስተቀር በአብዛኛው ለምርጫ ታዛቢ ወኪሎቻቸው መታወቂያ ተሰጥቶ ምደባውም የተከናወነ መሆኑን ገልጸው፣ በምርጫው ዕለት ግን በአብዛኛው በሚያስብል ሁኔታ ወኪሎቻቸው በየምርጫ ጣቢያው ለምን እንዳልተገኙ የደረሳቸው መረጃ እንደሌለ ነው የተናገሩት፡፡ ኃላፊዋ ከፋይናንስ ጋር የተያያዙ አንዳንድ ጥያቄዎች ይቀርቡላቸው የነበረ መሆኑን ግን አልሸሸጉም፡፡
በወረዳዎች በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች በአባሎቻቸውና በደጋፊዎቻቸው ላይ በገዥው ፓርቲ ካድሬዎችና ደጋፊዎች አልፎ አልፎ ድብደባዎች፣ ማስፈራራቶችና ወከባዎች እያደረሱባቸው መሆኑን ሪፖርቶች እንደደረሷቸው፣ በደብረ ብርሃንና በአካባቢው ግን በተለይ ጠዋት ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው መራጭ በየምርጫ ጣቢያው ተሠልፎ ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ሲመርጥ እንደነበረ መመልከታቸውን ነው ያስረዱት፡፡
በመሀል ሜዳና አካባቢው የሰማያዊ ፓርቲ ምርጫ አስተባባሪ አቶ ካሳዬ ዳኜ በበኩላቸው፣ ከምርጫ ዋዜማ ጀምሮ በገዥው ፓርቲ ካድሬዎችና ደጋፊዎች እጅግ አሳዛኝ የሆነ እንግልትና ማስፈራራት እንደደረሰባቸው፣ በዚህም የተነሳ በመሀል ሜዳና አካባቢው በነበሩ 93 ምርጫ ጣቢያ የሰማያዊ ፓርቲ ወኪሎች በሙሉ የምርጫውን ሒደት እንዳይከታተሉ መደረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ ዛቻና ማስፈራሪያውን ወደ ጎን ብለው የሄዱት ለእስራት እየተዳረጉ ማስጠንቀቂያ እየተሰጣቸው መፈታታቸውን ጭምር አስረድተዋል፡፡ እሳቸውም ቢሆኑ የገዥው ፓርቲ ካድሬዎችና ደጋፊዎች ‹‹በዚህ ምርጫ አንድ ነገር ቢከሰት የመጀመርያው ዕርምጃ በአንተ ነው የሚጀመረው፤›› ብለው ስላስፈራሯቸው ቤት ውስጥ መቀመጣቸውን በስልክ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡
የዞኑ የምርጫ ቦርድ ኃላፊው አቶ ተሰማ ከበደ በበኩላቸው፣ ምርጫው በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች በሰላም እየተከናወነ መሆኑን፣ ‹‹ችግር ተፈጥሯል›› በሚል ከየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ የቀረበላቸው አቤቱታ እንደሌለ ነው የተናገሩት፡፡
በዞኑ ከሚፎካከሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች መኢአድ ይጠቀሳል፡፡ በሰሜን ሸዋ ዞን የመኢአድ ምርጫ አስተባባሪ ሻምበል ባሻ አበበ በቀለ፣ ከምርጫ ዋዜማ ጀምሮ በገዥው ፓርቲ ካድሬዎችና ደጋፊዎች በደረሰባቸው ወከባና ማስፈራራት እንደማንኛውም የኅብረተሰብ ክፍል በምርጫ ካርዳቸው አማካይነት መብታቸውን ከመጠቀም ባለፈ፣ እንደ ፓርቲ የምርጫውን ሒደት ለመከታተልም ሆነ ለመቆጣጠር አለመቻላቸውን ነው ያስረዱት፡፡ በመሆኑም በዞኑ በሚገኙ በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች ምንም ዓይነት የምርጫ ታዛቢ ወኪሎቻቸውን እንዳልመደቡም ተናግረዋል፡፡
ኃላፊው ለዚህ ያበቃቸውን ውሳኔ ሲገልጹ፣ በባሶና ወረና በቀይት ምርጫ ጣቢያ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መኢአድ ያቀረባቸው ወ/ሮ ደስታ ካሳና በደብረ ብርሃን ከተማ በተመሳሳይ አቶ ጌራ ፍቅረ የተባሉ ተወዳዳሪዎቻቸው ከምርጫው ዋዜማ ጀምሮ በአካልም ሆነ በስልክ ሊያገኟቸው እንዳልቻሉ፣ ይህንኑም ወደ ማዕከል አስተላልፈው መፍትሔ እንዳልተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡
በወረዳ ደረጃ ከቀረቡት ተወዳሪዎቻቸው ለምሳሌ በሸዋ ሮቢት፣ በቀወት ወረዳ፣ በአጣየ፣ በጣርማ በር፣ በደብረ ሲናና በሌሎችም አካባቢዎች መኢአድ ያቀረባቸው ተወዳዳሪዎች በገዥው ፓርቲ ካድሬዎችና ደጋፊዎች በደረሰባቸው እንግልት፣ ዛቻና ማስፈራራት ሁሉም ችግሩን በመግለጽ ራሳቸውን ማግለላቸውን ተናግረዋል፡፡
ፓርቲው ከምርጫው ዋዜማ ጀምሮ እያጋጠመው ያለውን እንግልት፣ ወከባና ማስፈራት ለዞኑ ምርጫ ቦርድ ጽሕፈት ቤት በስልክና በተለያዩ አጋጣሚዎች ቢያሳውቅም ምንም ዓይነት መፍትሔ ሊያገኝ ባለመቻሉ፣ ለሁሉም አባሎቻቸውና ደጋፊዎቻቸው እንደ ፓርቲ ሳይሆን እንደማንኛውም የኅብረተሰብ ክፍል ካርዶቻቸውን ብቻ እንዲጠቀሙ ጥሪ ማድረጋቸውን አስረድተዋል፡፡ የዞኑ ምርጫ ቦርድ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተሰማ ከመኢአድም ሆነ ከሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ተቃዋሚ በመሆናቸው ምክንያት ከገዥው ፓርቲ ደርሶብናል ሲሉ በአካልም ሆነ በጽሑፍ የቀረበላቸው አንዳችም አቤቱታ እንደሌለ ነው ያስረዱት፡፡
ከዚህ ባለፈ ከምርጫው ዋዜማ ጀምሮ እስከ ምርጫው ፍፃሜ ከገዥው ፓርቲ ብአዴን/ኢሕአዴግ፣ ከሰማያዊና ከመኢአድ በስተቀር ሌሎቹን የፖለቲካ ፓርቲዎች በቅስቀሳው ወቅት መራጮች እንደማያውቋቸው ነው ለሪፖርተር የገለጹት፡፡ ከእነዚህ አንዳንዶቹ በተለይ በገጠር ቀበሌዎች ሪፖርተር በስልክ ያነጋገራቸው መራጮች በሚመርጡበት ምርጫ ጣቢያ ከብአዴን/ኢሕአዴግ ውጪ የሌሎች ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ተወካዮች እንዳልነበሩ ተናግረዋል፡፡

በደቡብ ክልል የሚገኙ 123 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎችን አሸንፎ ለመያዝ ምርጫ ከተከናወነባቸው ከተሞች መካከል አንዷ፣ በሀድያ ዞን በምሥራቅ ባደዋቾ ወረዳ የምትገኘው የሾኔ ከተማ ነች፡፡
ምሥራቅ ባደዋቾ በ30 ቀበሌዎችና በ72 የምርጫ ጣቢያዎች ሲከፋፈል፣ በዚሁ ዞን የምትገኘው ሾኔ ከተማ ደግሞ በስድስት የምርጫ ጣቢያዎች ነው፡፡ በሾኔ ለዘንድሮ አጠቃላይ ምርጫ የተመዘገቡት መራጮች ደግሞ 61,101 ናቸው፡፡
በከተማዋ የሚገኙት የምርጫ ጣቢያዎችም ጤና ኬላ፣ ፀረ ኤድስ 1 እና 2፣ ታተም፣ መናኸሪያና ማክማማ የተሰኙ ናቸው፡፡
የወቅቱ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ሊቀመንበርና በተቃውሞ ፖለቲካ ጐራው ዘለግ ያለ ዕድሜ ያስቆጠሩት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፣ በዚሁ ዞን በሚገኘው አንደኛ ሀሙበርሴ በተባለ የምርጫ ክልል አካባቢ ተወልደው ያደጉና በሥፍራውም ለሦስት ጊዜያት ያህል ምርጫውን አሸንፈው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል መሆናቸው፣ በሥፍራው የሚደረገውን ውድድር ለመዘገብ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በከተማው እንዲከትሙ አድርጐ ነበር፡፡
ፕሮፌሰሩ በ1987 ዓ.ም.፣ 1992 ዓ.ም. እና እንዲሁም በ1997 ዓ.ም. ጠቅላላ ምርጫዎች በማሸነፍ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል መሆናቸው የሚታወስ ሲሆን፣ በ2002 ዓ.ም. ምርጫ ደግሞ በገዥው ፓርቲ ደኢሕዴን/ኢሕአዴግ ተወካይ አቶ ዮሴፍ ዳኤሞ ተሸንፈው ነበር፡፡ ፕሮፌሰሩንና የገዥው ፓርቲ ተወካይ የሆኑትን አቶ ዮሴፍን ለመወዳደር ደግሞ የሰማያዊና የቅንጅት ፓርቲዎች ተወካዮቹ የሆኑት አቶ መብራቱ ተካና አቶ ያሬድ ደበበ ተመዝግበዋል፡፡
በዚሁ ከተማ ከሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች መካከል ፕሮፌሰር በየነ ድምፃቸውን የሚሰጡበት የምርጫ ጣቢያ ማክማማ የሚባል ሲሆን፣ በድምፅ መስጫው ዕለት ግን ፕሮፌሰሩ በሥፍራው ተገኝተው ድምፅ አልሰጡም፡፡ በአንፃሩ በፀረ ኤድስ አንድ የምርጫ ክልል ድምፅ የሚሰጡት አቶ ዮሴፍ ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ቀደም ብለው ድምፅ ሰጥተዋል፡፡
ፕሮፌሰር በየነ፣ ‹‹ያልመጣሁት ምርጫው ሥነ ሥርዓቱ ተጥሶ ሙሉ በሙሉ በኢሕአዴግ ቁጥጥር ሥር መዋሉን ስለተረዳሁ ወደዚያ ለማድረግ ያሰብኩትን ጉዞ በመተው፣ እዚሁ ማዕከል ሆኖ ሁኔታዎችን መከታተል የተሻለ ይሆናል በሚል ነው፤›› ብለዋል፡፡
በዞኑ ከምርጫው ጋር ለተያያዙ ጉዳዮች ደግሞ የምሥራቅ ባደዋቾ መድረክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሊቀመንበር አቶ ኤልያስ ሀደሮን ማነጋገርና መረጃ ማግኘት እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡
ምርጫ በሾኔ
የሾኔ ከተማ በምርጫው ዋዜማ በጣም ቅዝቅዝ ያለ እንቅስቃሴ የሚታይባት ነበረች፡፡ የከተማዋ ነዋሪ የሆኑ ግለሰቦችን በመጠየቅ ሪፖርተር መረዳት እንደቻለው፣ ከተማዋ ለወትሮው ሞቅ ያለች ነበረች፡፡ የምርጫ ዋዜማው ግን ከተማዋን ቀዝቀዝ እንዳደረጋት ገልጸዋል፡፡
ለዓይን ያዝ ሲያደርግ ደግሞ የከተማዋና የነዋሪዎቿ እንቅስቃሴ እጅጉን የተገደበ ነበር፡፡ ለወትሮው በክልል ከተሞች ወዲህና ወዲያ የሚሉት ባለሦስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጆች) ቢሆኑም እንኳን፣ አልፎ አልፎ ውርውር ከማለትና ከጥቂት ሞተሮች እንቅስቃሴ በስተቀር ከተማዋ ፀጥ ረጭ ብላ ከእንቅስቃሴ ነፃ ሆና ነበር ማለት ይቻላል፡፡
የምርጫው ዕለት
በዕለቱ የተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ሪፖርተር ያነጋገራቸው የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣ የምርጫውን ሒደት በንቃት እየታዘቡ እንደሆነ የገለጹ ሲሆን፣ የአብዛኛዎቹ ምላሽ ችግር እንዳላገጠማቸው የሚገልጽ ነበር፡፡
ከዚህ በተለየ ግን የወረዳው የመድረክ ሊቀመንበር የምርጫው ዕለት ቀትር ሊሆን ሲቃረብ በተለያዩ ቦታዎች የመድረክ ተወካዮች ከምርጫ ጣቢያዎች ተባረዋል የሚል ቅሬታዎችን፣ ወደ ምርጫ ጣቢያውና ወደ መገናኛ ብዙኃን እየደወሉ ያሳውቁ ነበር፡፡
ቡልጊታ በተባለው የምርጫ ጣቢያ የመድረክ ተወካይ ከምርጫ ጣቢያው እንዲወጣ ጫና እየተደረገበት እንደሆነ ለጋዜጠኞች ገልጸው ነበር፡፡ የቡልጊታ 02 የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ተረፈ ዴንሴሞ ግን የተባለውን በመቃወም የመድረክን ክስ አጣጥለዋል፡፡
በተመሳሳይ እንዲሁ መድረክን የወከሉት አቶ ዓለሙ ኦርዶሎ በጣቢያው ከፍተኛ እንግልት እንደደረሰባቸው ከመግለጽ ባለፈ፣ ‹‹አንድ ግለሰብ በርከት ያሉ የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን የምርጫ ኮሮጆ ውስጥ ሲከት አይቻለሁ፤›› በማለት በሥፍራው ለተገኙ የጋዜጠኞች ቡድን ገልጸዋል፡፡
የምርጫ ጣቢያው አስፈጻሚ አሁንም ክሱ ከእውነታ የራቀ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ሒደቱ በሥነ ሥርዓት ለመካሄዱ አባሪ የሚሆኑ አቶ ዓለሙ የፈረሙባቸውን የቃለ ጉባዔ ሰነዶችን በማሳየት የተባለው ሀሰት መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በተጨማሪም በሥፍራው የነበሩ የሰማያዊና የቅንጅት ፓርቲ ተወካዮችም አቶ ዓለሙ ያቀረቡትን ክስ አለመመልከታቸውን በመግለጽ፣ ከተወካዩ ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ ገብተው ነበር፡፡
ሲቄ 02 የምርጫ ክልል ጽሕፈት ቤት አስተባባሪ አቶ ያዕቆብ ዮሴፍ በበኩላቸው፣ ‹‹መድረክ ያቀረባቸው ክሶችና ቅሬታዎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን ችግር አለባቸው በተባሉ አካባቢዎች በአካል በመገኘትና የሌሎች ፓርቲዎችን ተወካዮች በማናገር እንዳረጋገጥነው የቀረበው ቅሬታ ተጨባጭነት የሌለውና አሉባልታ ነው፤›› በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በዕለቱ ከመድረክ ተወካይ በኩል ይቀርብ ከነበረ ቅሬታ በስተቀር ሌሎቹ ለተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ያቀረቡ ፓርቲዎች ያነሱት ቅሬታ አልነበረም፡፡ ሪፖርተር ተዘዋውሮ ባያቸው አብዛኛዎቹ የምርጫ ጣቢያዎች ከቀትር በፊት ከግማሽ በላይ የሚሆኑ መራጮች ድምፅ ሰጥተው ሄደዋል፡፡

ቅዳሜ ግንቦት 15 ቀን 2007 ዓ.ም. በአምስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ዋዜማ የደቡብ ክልል መዲና ሐዋሳ መንገዶች ከወትሮው ቀዝቀዝ ብለው ነበር፡፡ በመዝናኛዎች የነበረው ሁኔታም ተመሳሳይ ነበር፡፡
ፒያሳ የሚገኘው ሐውልት ፏፏቴ ግን ተከፍቶ ነበር፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች ትልልቅ ድንኳኖች ለድምፅ መስጫ ጣቢያነት ተጥለውም ነበር፡፡
በምርጫው ዕለት ብዙዎች ድምፅ ወደሚሰጡባቸው ጣቢያዎች ያመሩት ማልደው ነበር፡፡ በየድምፅ መስጫ ድንኳኖች ደጃፍ ላይ ሰዎች ተሠልፈው ይታይ ነበር፡፡ ደኢሕዴን/ኢሕአዴግን ወክለው ለክልል ምክር ቤት የሚወዳደሩት የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ዮናስ ዮሴፍና የ27 ዓመቱ አካል ጉዳተኛ በቃሉ አሰፋ፣ ከንጋቱ 12፡30 ሰዓት ገደማ ነበር ከታቦር ክፍለ ከተማ ሒጠታ ቀበሌ ወሜ ድምፅ መስጫ የተገኙት፡፡ ባገኘው የመምረጥ ዕድል ‹‹የመጠቀም ግዴታ አለብኝ›› የሚለው በቃሉ ምርጫው እንደ ከንቲባው አቶ ዮሴፍ ሁሉ ለእሱም በጣም አስፈላጊ መሆኑን ይገልጻል፡፡
ሪፖርተር ተዘዋውሮ ባያቸው መናኸሪያ ክፍለ ከተማ ፒያሳ ቀበሌ ቁ 4፣ ሐይቅ ዳር ጉዱማሌ ምርጫ ጣቢያ 3፣ መናኸሪያ ፒያሳ ቁጥር ሦስትና በታቦር ክፍለ ከተማ የድምፅ መስጫዎች ጨፌ ተጎዝጉዞ ቡና እየተፈላ በዓል በዓል ይመስል ነበር፡፡ ከበር የተሠለፉ ሰዎችን ስሜት መገመት ግን ከባድ ነው፡፡ ሠልፍ ላይ ጎን ለጎን ተሠልፈው ደቂቃዎችን ቢያሳልፉም ብዙዎች ሲነጋገሩ አይታይም፡፡ በዝምታ ተራቸው ደርሶ ወደ ድንኳን ውስጥ መግባትን የመረጡ ይመስላሉ፡፡ በብዙዎቹ ድምፅ መስጫዎች ስለድምፅ አሰጣጥ በመሀል በመሀል ገለጻ ሲሰጥ ተስተውሏል፡፡
በሲዳማና በሐዋሳ 1,437,697 ሰዎች ካርድ እንደወሰዱና 1,327,082 (624,72 ሴቶችና 702,361 ወንዶች) ድምፃቸውን እንደሰጡ በምርጫው ማግሥት የሲዳማና የሐዋሳ ከተማ ምርጫ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዱካሞ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በሐዋሳ 151 ድምፅ መስጫዎች የነበሩ ሲሆን፣ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በማግሥቱ ቀኑን ሙሉ ምርጫው ቀጥሎ ነበር፡፡
ምርጫ እዚህ ታዛቢ እዚያ
ከምርጫው ዋዜማ ጀምሮ ነበር ተቃዋሚ ፓርቲዎች ታዛቢዎቻቸው እየታሰሩና በተለያዩ መንገዶች ጫና እየደረሰባቸው እንደነበር ቅሬታ ማሰማት የጀመሩት፡፡ አንድነት ፓርቲን ወክለው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተወዳደሩት አቶ ሲዳ ኃይሌ፣ ‹‹የስም ፊደል ስህተት አለ›› በሚል ሁለት ታዛቢዎቻቸው መታሰራቸውን ገልጸዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተወዳደሩት አቶ ተስፋ ማርያም ጉቻ ደግሞ፣ ከሐዋሳ 27 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘውና እሳቸው በሚወዳደሩበት የቦሪቻ ምርጫ ጣቢያ 16 ወይም ሦስት አራተኛ የሚሆኑ ታዛቢዎቻቸው፣ በሐዋሳ ምርጫ ጣቢያ መድረክን ወክለው ለተወካዮች ምክር ቤት የተወዳደሩት ዶ/ር አየለ አሊቶም ቦሪቻ ላይ በርካታ ታዛቢዎቻቸው መታሰራቸውንና መደብደባቸውን ለሪፖርተር ገልጸው ነበር፡፡
ተቃዋሚ ፓርቲዎች ታዛቢዎቻቸው ለመታሰራቸውና ደረሰባቸው ለሚሉት እንግልት በምክንያትነት ካስቀመጧቸው መካከል የተቃዋሚ ፓርቲ ታዛቢ ሆነው መገኘታቸው በራሱ፣ ታዛቢ የሚሆኑባቸው ቦታዎች ላይ የተመዘገቡ ባለመሆናቸው ታዛቢነታቸው አግባብነት የለውም መባልና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡ በሌላ በኩል የሲዳማና የሐዋሳ ምርጫ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ የታሰሩ ታዛቢዎች መኖራቸውን ባይክዱም፣ ታሰሩ በተባሉት ታዛቢዎች ቁጥርና ለእስራታቸው በተሰጠው ምክንያት አይስማሙም፡፡ ቢሆንም ግን የታሰሩበት ምክንያት ምንም ይሁን ምን ከሚመለከታቸው ጋር እየተነጋገሩ እንደነበርና እንዲፈቱ ትዕዛዝ ያስተላለፉላቸው ታዛቢዎችም እንደነበሩ፣ በምርጫው ዕለት እኩለ ቀን ላይ ለሪፖርተር ገልጸው ነበር፡፡ እዚህ ላይ ታዛቢዎቹ ስንት ሰዓት ላይ ተፈቱ? ከተፈቱ በኋላስ በቀሪው ጊዜ ከታዛቢነት ኃላፊነታቸው እንዲገኙ ተፈቅዶላቸዋል? እነሱስ ከእስራቱ በኋላ ታዛቢ ለመሆን ፈቅደዋል የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡
ምሽት ምርጫ ከተጠናቀቀ በኋላ ሪፖርተር ተዘዋውሮ በተመለከታቸው የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች በአንዳንዶቹ ምንም እንኳ የሕዝብ ተወካዮች ቢኖሩም፣ አንድም የተቃዋሚ ፓርቲ ታዛቢ ያልነበረበትም አጋጥሟል፡፡ አንድ ወይም ሁለት የፖለቲካ ፓርቲ ታዛቢዎች ብቻ የተገኙባቸውም እንዲሁ፡፡ በሌላ በኩል የአፍሪካ ኅብረት ታዛቢዎች ከነበሩበት (ጉድማሌ ቁ 3) ድምፅ መስጫም ሪፖርተር ተገኝቶ ነበር፡፡
በመናኸሪያ ፒያሳ ቁጥር 3 ድምፅ መስጫ ድምፅ በመቆጠር ላይ ሳለ ሪፖርተር ያገኘውና አስተያየቱን የጠየቀው በጣቢያው ወጣቶችን ወክሎ ታዛቢ የነበረው የ12ኛ ክፍል ተማሪ፣ ሥልጠና ሲወስዱ አስተያየት እንዳይሰጡ ስለተነገራቸው ለመናገር ፈቃደኛ አለመሆኑን ገልጿል፡፡ በዚያው ጣቢያ ድምፅ በመቆጠር ላይ ሳለ ምንም እንኳ መንገዱን በድንጋዮች ለመዝጋት ተሞክሮ የነበረ ቢሆንም፣ አንድ ሞተር ድንኳኑን ጥሶ በመግባቱ አራት ሰዎች ላይ መጠነኛ ጉዳት መድረሱን የምርጫ አስተባባሪ ጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
ምርጫ በዩኒቨርሲቲ
በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ አራት ሺሕ የሚሆኑ ተማሪዎች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚገመት፣ ከዚህ ውስጥም 3,678 ያህሉ የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውን ከምርጫ አስተባባሪዎቹ አንዱ የሆነው ተስፋዬ ጥሩነህ ለሪፖርተር ገልጿል፡፡ እሱ እንደገለጸው፣ በዩኒቨርሲቲው ስድስት ድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ነበሩ፡፡ በእያንዳንዱ ጣቢያ 700 ተማሪዎች ድምፅ እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡ ብዙ ድምፅ ሰጪ የሌለባቸው እንደ አፋርና ትግራይ ክልሎች እንዲጣመሩ ተደርጎ ነበር፡፡ በዕለቱ የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ተሟልተው ቀርበው ስላልነበር፣ በማግሥቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ ምርጫው እንዲቀጥል መደረጉን ሰኞ ጠዋት በዩኒቨርሲቲው ተገኝቶ ሪፖርተር አረጋግጧል፡፡
በምርጫ ጣቢያዎቹ ረዥም ሠልፎች ታይተዋል፡፡ ጣቢያዎቹ የነበሩበት የዩኒቨርሲቲው አካባቢ በእንቅስቃሴ የተሞላ ነበር፡፡ ሪፖርተር ያነጋገራቸው በርካታ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቅጥር ተማሪዎች እንዲመርጡ መደረጉ ለአገሪቱ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ወሳኝ መሆኑን ብቻም ሳይሆን፣ በዚህ ምርጫ የግቢያቸውን ፍትኅዊነት ይገልጻሉ፡፡ ‹‹ይህ እውነት ዴሞክራሲ ስለመስፈኑ ያረጋግጥንበት ነው፤›› ያለው ከምዕራብ ሐረርጌ ገለምሶ የመጣው የአንደኛ ዓመት ጋዜጠኝነት ተማሪ ዮናስ ወንድሙ ነው፡፡ ከአርባጉና ወረዳ የመጣችው ሰላማዊት ፀጋዬ (ሲዳምኛ ቋንቋ ተማሪ) የዮናስን አስተያየት የምትጋራና የምርጫ አስተባባሪም ነበረች፡፡
የሌሎች ተማሪዎችም ሐሳብ ተመሳሳይ ነው፡፡ ምርጫው የዴሞክራሲየዊ ሥርዓት መገለጫ እንደሆነና ለሕዝብ ሰላምና ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ወሳኝ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ ሪፖርተር በግቢው በነበረው የአንድ ሰዓት ቆይታ ተዘዋውሮ አስተያየት ሲጠይቅ ለየት ያለ አስተያየት ያላቸው ተማሪዎች አላገኘም፡፡ ምንም እንኳ ተማሪዎቹ ምን ያህል ዩኒቨርሲቲውን ይወክላሉ የሚለው ጥያቄ ቢነሳበትም፣ የተገኙት አስተያየቶች ተመሳሳይ መሆን የሚናገረው ነገር ይኖራል፡፡
በኢትዮጵያ ፖለቲካ በተለያዩ ሥርዓቶች የከፍተኛ ተቋም ተማሪዎች ስለሕዝብ ጥቅም፣ ነፃነትና ሌላም ሌላም በመጠየቅ የታገሉ መሆናቸውን በማስታወስ፣ በኢሕአዴግ ሥርዓት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተማሪዎች የተለያዩ ሐሳቦች (የሚቃረኑም ሊሆኑ ይችላሉ) የሚንፀባረቁባቸው መሆን እያቆሙ ነው የሚለው ከዚህ ቀደምም በበርካታ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጭምር ይገለጽ ነበር፡፡ ይህ ደግሞ ስለዛሬው ብቻም ሳይሆን ስለቀጣዩ የአገሪቱ ፖለቲካ ብዙ የሚናገረው ሊኖር ይችላል የሚለው ብዙዎችን ያነጋግራል፡፡ በእርግጥ በተለያዩ ምክንያቶች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የኢሕአዴግ አባል መሆናቸው የአደባባይ ሚስጥር መሆኑን በተደጋጋሚ የሚገልጹ ብዙዎች ናቸው፡፡
የምርጫው ማግሥት
በምርጫው ማግሥት ጠዋት በነበረው ቅኝት በአንዳንዶቹ ጣቢያዎች ውጤት ሲለጠፍ በሌሎች ደግሞ አልተለጠፈም ነበር፡፡ የምርጫ አስፈጻሚ ከቤት ከእንቅልፉ ተቀስቅሶ እንደዋዛ አጣጥፎ የያዛቸውን ሁለት የውጤት ወረቀቶች ሲለጥፍ በአንድ የድምፅ መስጫ ጣቢያ ተስተውሏል፡፡ አንድ ምርጫ ጣቢያ ላይ ከፕላስቲክ ጠርሙስ ኮላ በእንጨት እየተሟጠጠ ውጤት ለመለጠፍ ሲሞከር፣ በቦታው የነበሩ ሰዎች የምርጫው በጀት ይህን ታሳቢ አላደረገም? በሚል ቀልድ በሥፍራው የነበሩትን ፈገግ አሰኝተዋል፡፡

የምዕራብ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እምብርት በሆነችው ጅማ፣ በተካሄደው ምርጫ የኦሮሚያ ክልል ገዢ ፓርቲ ኦሕዴድ ከመድረክ፣ ከሰማያዊና ኢዴፓን ጨምሮ ከተለያዩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ተወዳድሯል፡፡
ሪፖርተር በምርጫው ዋዜማ፣ በምርጫው ቀንና በምርጫው ማግሥት በተለይ በጅማ ከተማና በአጋሮ ከተማ የሚገኙ የምርጫ ተወካዮችን ከማነጋገሩም በላይ በምርጫ ጣቢያዎች ቅኝት አድርጓል፡፡
በምርጫው ዋዜማ የጅማ ከተማ ምርጫ ቦርድ ጽሕፈት ቤትና የዞኑ ምርጫ ጣቢያ ማስተባበሪያ ሲያካሂድ የቆየውን ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቆ ነበር፡፡ ኦሕዴድ የምርጫ ካርድ የወሰዱ መራጮች በምርጫው ቀን ጠዋት ወጥተው ድምፅ እንዲሰጡ ያሉትን አደራጃጀቶች በመጠቀም ሲያሳስብ ተስተውሏል፡፡
ነገር ግን በምርጫው ዕለት ከሌሊት ጀምሮ በጅማ ከተማና በአብዛኛው ጅማ ዞን ክልል ውስጥ የጣለው ኃይለኛ ዝናብ የመምረጫ ሰዓታትን መሸራረፉ አልቀረም፡፡ ይህም ቢሆን ግን ቁጥራቸው ቀላል የማይባል መራጮች በዝናብ ውስጥ ሲመርጡ ተስተውሏል፡፡
ረፋዱ ላይ ዝናቡ ካባራ በኋላ በርካታ መራጮች በረዣዥም ሠልፎችና በድንኳን ውስጥ በመቀመጥ ተራቸውን ጠብቀው ድምፅ ሰጥተዋል፡፡ ምርጫው በሰላም ተጀምሮ በሰላም መጠናቀቁን ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ የጅማ ዞን ጅማ ከተማን ሳይጨምር 1.9 ሚሊዮን ሔክታር ስፋት አለው፡፡ በዞኑ ሦስት ሚሊዮን ሕዝብ እንደሚኖር የዞኑ አስተዳደር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በዞኑ ውስጥ ከሚኖረው ሕዝብ 1.3 ሚሊዮን የሚሆነው በምርጫው ድምፅ ለመስጠት ተመዝግቧል፡፡
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጅማ ከተማ ምርጫ ጣቢያ ኃላፊና የጅማ ዞን ምርጫ ክልል አስተባባሪ አቶ አወጣኸኝ ኪዳነ ማርያም ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ጅማ ከተማን ጨምሮ በአጠቃላይ በጅማ ዞን 18 ምርጫ ክልሎች አሉ፡፡ በእነዚህ 18 የምርጫ ክልሎች 1,551 ድምፅ መስጫ ጣቢያዎች አሉ፡፡
በጅማ ዞን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩዎችን አቅርበዋል፡፡ ኦሕዴድ፣ መድረክ፣ ሰማያዊ፣ ኢዴፓና አንድነት በምርጫው ተሳታፊ ነበሩ፡፡
ኦሕዴድ በሁሉም መወዳደርያ ጣቢያዎች ዕጩ ሲያቀርብ መድረክ፣ ሰማያዊ፣ ኢዴፓና አንድነት በተነፃፃሪ ቁጥሩ የቀነሰ ዕጩ አቅርበው ተወዳድረዋል፡፡ ኦሕዴድ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካባ ኡርጌሳ የጅማ ከተማ የፓርላማ ተመራጭ አድርጎ ሲያቀርብ፣ 17 ነባር የፓርላማ ተመራጮችን በሌሎቹ የምርጫ ክልሎች እንዲወዳደሩ አድርጓል፡፡ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙክታር ከድርን ጨምሮ 54 አባላቶቹን ደግሞ ለክልሉ ምክር ቤት ዕጩ አድርጎ አቅርቧል፡፡
በሁለቱ የጅማ ዞን ትላልቅ ከተሞች የኦሕዴድ ፖስተሮችን በስፋት መመልከት ቢቻልም፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ፖስተር ግን ማየት አዳጋች ነበር፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ፖስተሮች ሊኖሩ ያልቻሉበትን ምክንያት በሪፖርተር የተጠየቁት የአጋሮ ከተማ ከንቲባ አቶ ሞጋ አባቡልጋ፣ በአብዛኛው በግለሰቦች በተያዙ አካባቢዎች የሚለጠፉ በመሆናቸው ግለሰቦች ሲፈቅዱ ፖስተሮች ይለጠፋሉ ብለዋል፡፡ ኦሕዴድም አስፈቅዶ መለጠፉን ተናግረዋል፡፡ ተቃዋሚዎቹ በግለሰቦች ስላልተፈቀደላቸው መለጠፍ ባለመቻላቸው ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡
በምርጫው ዕለት ልዩ ክስተት ከሆኑት መካከል በጅማ ዞን ሲግሞ ምርጫ ክልል ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ ድምፅ ተሰጥቶ መጠናቀቁ ነው፡፡ የጅማ ዞን የኦሕዴድ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ታምራት ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በሲግሞ ምርጫ ክልል 49 ሺሕ ነዋሪዎች ድምፅ ለመስጠት ተመዝግበዋል፡፡ የአካባቢው አብዛኛዎቹ ነዋሪዎች የእስልምና እምነት ተከታዮች በመሆናቸው፣ ከሌሊቱ 11 ሰዓት የሱቢህ ስግደት ከሰገዱ በኋላ ወደ ምርጫ ጣቢያ መሰማራታቸውን አስረድተዋል፡፡
‹‹በዚህ ምክንያት መራጮች ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ ድምፅ ሰጥተው አጠናቀዋል፤›› ያሉት አቶ ጌታቸው፣ የምርጫ ካርድ በሚሰጥበት ወቅት እነዚህ የሲግሞ ነዋሪዎች በሁለት ቀን ውስጥ የምርጫ ካርድ ወስደው አጠናቀዋል ብለዋል፡፡
የኦሕዴድ ጽሕፈት ቤት መቀመጫውን ጅማ ከተማ አድርጎ ከሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተቃራኒ በጠንካራ መዋቅሩ አማካይነት የዞኑን የምርጫ ሒደት በቅርበት ተከታትሏል፡፡ ሪፖርተር በኦሕዴድ ጽሕፈት ቤት ተገኝቶ መረዳት እንደቻለው፣ በተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች በመጠቀም ኦሕዴድ በእያንዳንዱ ድምፅ መስጫ የሚካሄደውን እንቅስቃሴ ከመከታተሉም ባሻገር፣ ሪፖርት በማዘጋጀት ወደ ማዕከል ኦሕዴድ ጽሕፈት ቤት ይልካል፡፡
ከተቃዋሚ ፓርቲዎች የተደራጀ መረጃ ማግኘት ባይቻልም፣ በአጋሮ ጎማ አንድ ምርጫ ክልል የፓርላማ ተወዳዳሪ የሆኑት አቶ አብዱ አባዎሪ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የምርጫው ቅስቀሳም ሆነ ሒደቱ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ነው፡፡ ‹‹ምርጫው ፍትሐዊ መሆኑን እስካየን ድረስ፣ ውጤቱን በፀጋ እንቀበላለን፤›› በማለት አቶ አብዱ ገልጸዋል፡፡
በጅማ ክልል በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች የፖለቲካ ፓርቲ ታዛቢዎች ተሟልተው አለመገኘት ተጠቃሽ ችግር ሆኖ ቀርቧል፡፡ ይኼ የታዛቢዎች አለመገኘት በብዙ የምርጫ ጣቢያዎች ተስተውሏል፡፡
በጅማ ዩኒቨርሲቲ የምርጫ ቁሳቁስ እጥረት በመከሰቱ የድምፅ መስጠት ሒደቱ ተስተጓጉሏል፡፡ አቶ አወጣኸኝ እንዳሉት ሰኞ ከሰዓት በኋላ የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶች በሔሊኮፕተር በመምጣታቸው ድምፅ መስጠቱ በምርጫው ቀን ማግሥት ተካሂዷል፡፡ ነገር ግን በወቅቱ የምርጫ ቁሳቁሶች እጥረት በመከሰቱ መምረጥ ያልቻሉ ተማሪዎች ጥያቄ አንስተው የተወሰነ አለመግባባት ተከስቶ ነበር፡፡
አቶ አወጣኸኝ ‹‹መምረጥ መብት ነው፡፡ ተማሪዎቹ ባልመረጡት አካል ሊተዳደሩ በመሆኑ ጥያቄ ማንሳታቸው አግባብ ነው፡፡ የምርጫው ሒደት በምርጫ ቦርድ የቴክኒክ ችግር መካሄድ ባለመቻሉ ድምፅ ያልሰጡ ተማሪዎች ድምፅ እንዲሰጡ ይደረጋል፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡
ከአንተነህ መርዕድ (ሚያዝያ 2007)
መሳይ መኮንንና ፋሲል የኔዓለም ወደ ኤርትራ ያደረጉት ጉዞ የብዙ ኢትዮጵያውያንን እንዲሁም የኤርትራውያን ወንድምና እህቶች ቀልብ መሳቡ እሙን ነው። በተለይም የፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ቃለ መጠይቅ በብዙ መልኩ አስደምሞናል። እድላችን የተቆራኘነውና መነጋገሩና መብሰልሰሉ የሚገባ በመሆኑ ያለፍንበትን ሁሉ በትዝታ እንድፈትሽና አሁን የደረስንበትን እንዳይ ምክንያት ሆኖኛል። ነገሮችን ውስብስብና አጠቃላይ ከሆነ መልኩ ይልቅ ተጨባጭ ከሆኑ የግል ገጠመኞች ዙርያ ማውጋቱ የበለጠ ጉልህ ያደርገዋልና አንባቢዎቼም የራሳችሁ ገጠመኝ ዙርያ እየተሽከረከራችሁ የእኔን እንድትካፈሉ እጋብዛለሁ። በዚህ መልኩ ከምን ተነስተን የት እንዳለን ይታየናል።
በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ በፌደራል አቃቤ ህግ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው እየታየ ከሚገኙት ሰባት የዞን 9 ጦማርያን እና ሶስት ወዳጅ ጋዜጠኞች ስድስቱ ጦማርን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች ዛሬ ግንቦት 18/2007 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛው ፍ/ቤት ቀርበዋል፡፡ መዝገቡ ለዛሬ ተቀጥሮ የነበረው ሁለት ጉዳዮችን ለማየት ሲሆን፣ አንደኛው አቃቤ ህግ በኤግዚቢትነት አሉኝ ያላቸውን ኤግዚቢቶችና 12 ሲ.ዲዎች መዝገብ ቁጥራቸውን በመጥቀስ […]![]()
ከአንድ ዓመት በላይ በእስር የቆዩት ጦማሪያንና ጋዜጠኞች በዛሬወእለት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ፊት ቀርበዋል። አቃቤ ሕግ ከአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን በያዘዉ ቀጠሮ መሰረት ቀሩኝ ካላቸዉ 13 ምስክሮች ዉስጥ ሶስቱን ማቅረቡን የተከሳሾቹ ጠበቃ አቶ አመሃ መኮንን ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በሰጡት ቃለ ምልልስ ገልጸዋል። ምስክሮቹ እንደቀድሞዎቹ ሁሉ ተከሳሾቹ ከተያዙባቸዉ ቦታዎች ሞባይል፣ ላፕ ቶፕ እና ሲዲ መያዙን አይተናል ማለታቸዉን ጠበቃዉ አስረድተዋል።
ከአንድ ወር ተኩል በፊት በዋለዉ ችሎት አቃቤ ሕጉ ምስክሮችን ለመስማት የተሰጠዉ ጊዜ አጭር መሆኑን፣ ለማስረጃነት ሊቀርቡ የነበሩትን ሲዲዎች የያዙት ግለሰብ ከአገር ዉጭ መሆናቸዉን እንዲሁም በእግዚቢትነት የያዛቸዉን ሞባይል ስልኮችና ላፕ ቶፖችን ለማቅረብ ረዘም ያለ ቀጠሮ እንዲሰጠዉ መጠየቁ…
ሚያዝያ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው እሁድ ግንቦት15 ፣ 2007 ዓም የተካሄደው ምርጫ ነጻና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እንደተካሄደ መንግስትና ብቸኛው የውጭ ታዛቢ የአፍሪካ ህብረት ቢገልጽም፣ በምርጫው የተሳተፉ ታዛቢዎችና መራጮች ምርጫው በአሳዛኝ ሁኔታ መካሄዱን መስክርነታቸውን እየሰጡ ነው። በአዲስ አበባ የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢ የነበረው አቶ መሰለ አድማሴ እንደገለጹት እርሳቸው በታዘቡበት የምርጫ ጣቢያ፣ …
ሚያዝያ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይ ኦም ኤም፣ የመን ውስጥ በችግር ላይ የነበሩ 2061 ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው መመለሱን አስታውቋል። ከተመሰሉት መካከል የቆሰሉ ኢትዮጵያውያንም አሉበት። አይ ኦ ኤም በአዲስ አበባ ጊዚያዊ ማቆያ ጣቢያ ተመላሾችን በማስፈር የትራንስፖርት እና የጤና አገልግሎት መስጠቱን አስታውቋል። ሃድራ የተባለች ተመላሽ በቤት ሰራተኛነት ስትሰራ እንደነበር …
ሚያዝያ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእስር ላይ በሚገኙ ዞን ዘጠኝ በሚል መጠሪያ ስም በሚታወቁት ወጣት ጸሃፊዎች ላይ ምስክሮች ቀርበው ፣ የክሱን ጭብጥ በደንብ በማያስረዳና ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት የሌላቸውን ነገሮች በመናገር ማሳለፋቸውን ችሎቱን የተከታሉት ታዛቢዎች ገልጸዋል። ችሎቱን ለመከታተል የታደሙ ታዛቢዎች ምስክሮች ሲንተባተቡ እያዩ ችሎት ውስት ይስቁ እንደነበር ታዛቢዎች ገልጸዋል። ወጣት ጸሃፊዎቹ …
የአፍሪቃ ሕብረት የምርጫ ታዛቢዎች ባለፈዉ ሕሁድ ስለተካሄደው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ቅይጥ አመለካከት የተንጸባረቀበት ግምገማ ሰጡ።
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና
የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምጽ አዳዲስ ዜና ዘገባዎችን እና ካለፈው የቀጠለ የሰሃራ በረሃ ተጓዦች ትዝታን የሚያስቃኝ ትረካ ቀጣዩን ክፍል 3 እና 4 ይዘን ልናስደምጣቹ ተዘጋጅተናል::የቀድሞ አንድነት ፓርቲ ምክትል አፈ ጉባዬ እና የፋይናንስ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ጸጋዬ አላምረው ከስደት ካሉበት ያሳለፉትን የፖለቲካ ሕይወት እና የአንድነት ፓርቲን በተመለከተ ያደረጉት ቃለመጥይቅ በዚህ ፕሮግራም ይቀርባል:: ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ!!
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ይሄ ሁሉ ናዳ ይህ ሁሉ ውርጅብኝ እንደ ዝናብ ወርዶ የሚቀጠቅጠኝ ህሊናን አስቶ የሚደበድበኝ፤ ተስፋየን አሟጦ፡ በጭካኔ ረግጦ፤ ሙቀትና ብርዱ አዘቅቱ ንዳዱ፡ ችግር ቸነፈሩ ስቃይ ግርግሩ መከራው በርትቶ የሚያደናግረኝ ምንድነው ነገሩ? ግራ ግብት አለኝ!? እኮ ለምን ሆነ?በኔ ጠነከረ፤ ጥላቻና ክፋት እየተካረረ፡ ግድያና እስራት፡ ወከባና እንግልት፡ ምነው እንዲህ ሆነ? ተደጋገመብኝ፡ በረታ ጨክነ፡፡ ዘመኑን አርዝሞ፡ ክንዱን አፈርጥሞ፡ በላዩ […]
እሁድ በመላው ኢትዮጵያ የተካሄደውን 5ኛ ሀገር አቀፍ ምርጫ ለመታዘብ የአውሮፓ ህብረት ልዑካን ወደ ኢትዮጵያ ባይሄዱም ፤ የዶይቸ ቬለን ሬዲዮ እና ቴሌቪዥንን ጨምሮ የጀርመን ጋዜጦች ስለምርጫው ዘግበዋል። የጥቂቱን የጀርመን ጋዜጦች ዘገባ እንደሚከተለው ነበር። የጀርመን ታዋቂ ዕለታዊ ጋዜጣ « ዙድ ዶይቸ ሳይቱንግ» ስለ የኢትዮጵያ ሀገር አቀፋዊ ምርጫ ሲዘግብ ርዕሱን« በጉልበት ወደ ዘመናዊነት » ነው ያለው። የጠቅላይ ሚኒስትር […]![]()
ታዛቢዎችና ተቃዋሚ ፓርቲ ኣባሎች በማዋከብ ተጀምሮ ያለ ተቀዋሚ ፓርት ታዛቢ ቆጠራ የተጠናቀቀው ምርጫ 2007 ኣምባገነኑ የሕወሓት ስርዓት ያለ ህፍረት ኣይኑን በጨው ኣጥቦ ኣሸነፍኩኝ ለማለት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦር የወያኔ ኣጋር ፓርቲ እስኪመስል ድርስ ሙሉ ድጋፉን ለወያኔ የሰጠው ቦርድ ስለ ምርጫው ዴሞክራሲነት ለማዉራት ሞራሉ እንካ ባይኖሮው ነገር ግን ወያኔ ከዓለም መንግስታት ለየት የሚያደርገው የክህደትና […]![]()
EPRDF’s Revolutionary Democracy
Human Rights in Ethiopia
Election rows in Southern Ethipoia
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና