Tag: Ethiopians
ኦህዴድ፣ብአዴንና ደኢህዴን የሚባሉ ህያዋን የሉም
መቶ ከመቶ ደፈንኩ ያለን ‹‹ሰነፉ››ተማሪ ኢህአዴግ በቀጣይ በሚያደርገው የግምባሩ ጠቅላላ ጉባኤ በኃይለማርያም ደሳለኝ ወንበር ላይ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡ወርሃ መስከረም የሚሰየመው ‹‹የኢህአዴግ መንግስታዊ ጉባኤም››(ፓርላማ ለማለት ቢቸግረኝ ያወጣሁለት ስያሜ ነው) የሚቀርብለትን እንደወረደ ያጸድቃል፡፡ ይህንን የሚጠብቁ ፌስ ቡከሮች በበኩላቸው የራሳቸውን ጥንቆላ እያስነበቡን ነው፡፡ማንም ይምጣ ያው ነው ያሉ ወገኖችም ቢሆኑ ቢያንስ በወንበሩ ላይ የሚቀመጠው ግለሰብ ‹‹ጉልቻው››በመሆኑ መቀያየሩ […]![]()
ኦብነግ “ተጠልፈው ነበር” ያላቸው ተደራዳሪዎቹ መለቀቃቸውን አስታወቀ – ሰኔ 04, 2015
onlf-kidnapped-negotiators-released-06-03-15
ስለፊፋ የሰሞኑ ግርግር – ሰኔ 04, 2015
fifa-in-crisis-news-and-analysis-06-03-15
ደቡብ ሱዳን – እንደገና ጦርነት፤ እንደገና ስደት … – ሰኔ 04, 2015
South Sudan – renewed fighting and new refugee crisis 06-02-15
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በ2006 በጀት ዓመት ያለምንም ማስረጃ ገንዘብ ከሚያወጡ መንግስታዊ ተቋማት መካከል የደህንነት ተቋም ዋንኛው መሆኑን አጋለጠ፡፡
ግንቦት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዋና ኦዲተር የ2006 ዓ.ም የመንግስት መ/ቤቶች የሂሳብ ሪፖርት ትላንት ለፓርላማው ያቀረበ ሲሆን በዚህ ሪፖርቱ ያለምንም ማስረጃ ገንዘብ ያወጡ 19 መንግስታዊ ተቋማት የተገኙ ሲሆን እነዚህ ተቋማት በድምሩ ከ473 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ አውጥተው ተገኝተዋል፡፡ ከዚህ ገንዘብ ውስጥ ላቅ ያለውን ድርሻ ማለትም 274 ሚሊየን ብር ያወጣው የብሔራዊ መረጃና …
በኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች ተጠልፈው የነበሩት የኦብነግ ባለስልጣናት በኬንያ መንግስት እና በአለማቀፍ ማህበረሰብ ጥረት መፈታታቸውን ግንባሩ አስታወቀ
ግንቦት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ለኢሳት በላከው መግለጫ ፣የኦብነግ ሁለቱ ተደራዳሪዎች አቶ ሱሉብ አህመድና አቶ አሊ ሁሴን ፣ እኤአ ሰኔ 1 ቀን 2015 በኢትዮጵያ የደህንነት ባለስልጣን አጃቢነት የኢትዮጵያ እና ኬንያ ድንበር ከተማ የሆነችው ሞያሌ ደርሰዋል። ሁለቱ ልኡካኖች ናይሮቢ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተገናኝተዋል። ኦብነግ ተወካዮቹ በኬንያ መንግስት እና በአለማቀፍ …
ፍርድ ቤት ከእስር እንዲፈቱ የወሰነላቸው አቶ ማሙሸት አማረ በ ፖሊስ እምቢተኝነት ተመልሰው ታሰሩ
ግንቦት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምርጫ ቦርድ ትእዛዝ ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ የተደረጉት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ፕሬዝዳንት አቶ ማሙሸት አማረ ፣ ግንቦት 25/2007 ዓም ፍርድ ቤት ከእስር እንዲለቀቁ ቢወስንም ፣ ፖሊስን ግን መልሶ አስሯቸዋል። አቶ ማሙሸት ሚያዚያ 14፣ 2007 በአይ ኤስ የተገደሉ ኢትዮጵያውያንን በማስመልከት ድርጊቱን ለማውገዝና ኢትዮጵያውያኑንም ለመዘከር በተጠራው የተቃውሞ ሰልፍ …
በጅማ ዩኒቨርሲቲ የኦርቶዶክስ አማኞች ከዩኒቨርስቲ አስተዳደሩ ጋር እየተወዛገቡ ነው።
ግንቦት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የውዝግቡ መነሻ ተማሪዎች የሰኔ ጾምን ለመጾም በመፈለግ ዩኒቨርሲቲው የጾም ምግብ እንዲያዘጋጅላቸው በመጠየቃቸውና ዩኒቨርስቲው ፍቃደኛ ሳይሆን በመቅረቱ ነው፡፡ የዩኒቨርስቲው አስተዳደር ተማሪዎች ላቀረቡት ጥያቄ ዳቦ እየበላችሁ መጾም ትችላላችሁ የሚል መልስ ሰጥቷቸዋል። ዩኒቨርሲቲው ለስጋ የሚወጣውን በጀት ለሽሮ ቢወጣ ይቀንስ እንደሆን እንጂ ተጨማሪ ወጪ አያስከትልበትም ያሉት ተማሪዎቹ በግዳጅ እምነታችንን እንድንተው …
አርበኞች ግንቦት 7 በሜልቦርን አውስትራሊያ የተሳካ የገንዘብ ማሰባሰብ ዝግጅት አካሄደ
ግንቦት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ላለፉት 3 ሳምንታት በአውስትራሊና ኒውዚላንድ የተለያዩ ከተሞች የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻ በማድረግ ላይ የሚገኘው አርበኞች ግንቦት 7 ባለፈው ዕሁድ ሜይ 31ቀን በሜልበርን ከተማ የተሳካ የገንዘብ ማሰባሰብ ዝግጅት ማካሄዱን ሃና ጋረደው ከስፍራው ከላከችልን ሪፖርት ለመረዳት ተችሎአል በርካታ የሜልበርንና አካባቢዋ ነዋሪዎች በተገኙበት በዚህ ታላቅ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ የአርበኞች …
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ሰኔ 03, 2015
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ረቡዕ፡- ዴሞክራሲ በተግባር፣ ሴቶችና ቤተሰብ፣ አሜሪካና ሕዝቧ፣ ኢትዮጵያዊያን ባሜሪካ
የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መታሠር
ሰማያዊ ፓርቲ በድህረ ምርጫ ሰማንያ አባላቶቹ እንደታሠረበት አመለከተ። ፓርቲዉ ታሰሩብኝ ያላቸዉ አባላቱ በምርጫዉ ጊዜ ታዛቢዎች የነበሩ መሆናቸዉንም አስታዉቋል። ፓርቲዉ አክሎም ከታሳሪዎች አንዳንዶቹ ከስድስት ወር እስከ አንድ ዓመት እንደተፈረደባቸዉ ለዶይቼ ቬለ ገልጿል።
የአለም ሀገራት ባሰፈኑት የህግና ፍትህ ስርአት ምዘና ኢትዮጵያ ከ102 የአለም ሀገራት 94ተኛ ደረጃ ተሰጥቷታል
ዎርልድ ጀስቲስ ፕሮጀክት የተባለው በአለም ላይ ፍትህና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እሰራለሁ የሚል ተቋም የ 102 የአለም ሀገራትን የፍትህና ህግ ስርአት ደረጃ ይፋ አድርጓል፡፡ ከተለያዩ ሀገራት ከ 100 ሺህ የማያንሱ ህዝቦችን መጠይቅ በማድረግ ጭምር የተጠናቀረው ይህ የተቋሙ ሪፖርት በዚህ ረገድ የኢትዮጵያችንንም ደረጃ ይፋ አድርጓል፡፡ … የፍትህና ህግ የበላይነት ጉዳይ ብዙ ጊዜ የህግ ሰዎች ስራ ብቻ ተደርጎ […]![]()
ሰንበት ት/ቤቶች መልካም አስተዳደር እና ፍትሕን የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ሊያደርጉ ነው
ፓትርያርኩ የሀገር አቀፍ ጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊዎችን ባለማነጋገራቸው ማዘናቸውን ገልጸዋል ከገቢያቸው በላይ ሀብት ያከማቹ ሓላፊዎችን በሕግ ለመጠየቅ ዝግጅት እየተደረገ ነው (ሰንደቅ፤ ፲ኛ ዓመት ቁጥር ፭፻፰፤ ረቡዕ ግንቦት ፳፮ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.) ሙስና እና ብልሹ አሠራር እንዲወገድ፣ ሃይማኖት እንዲጠበቅ በተደጋጋሚ ያቀረብነው አቤቱታ መፍትሔ አላገኘም ያሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች፣ …![]()
“ኢትዮዽያዊው በአሜሪካ 122 አመት ተፈረደበት!”
በአሜሪካን ሀገር በሚሊየን የሚቆጠሩ ኢትዮዽያዊያን ስደተኞች ይኖራሉ! እነዚህ ስደተኞች ከጥቃቅን ስራዎች አንስቶ እስከ_ታላላቅ ካምፓኒዎች በወዛቸው ያገኙዋትን ዶላር አጠራቅመው… አንድ ቀን ሀገሬ እገባለው ከሚል ተስፋ ጋር ሕይወትን ይገፋሉ! ህልሙ የሞላለት ጥቂቱ ጠቅልሎ ሲመጣ አብዛኛው ግን በዥዋዥዌው የአሜሪካ ህይወት ባለበት ሰምጦ ይቀራል! ስደት የእድሜ ወፍጮ ነው! በአምስት አመት ውስጥ ሀገሬን አያታለው ያለ ዲያስፖራ ሳይታሰብ ስምንት የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች […]![]()
የፊፋው ፕሬዝዳንት ሴፕ ብላተር ስልጣን ለቀቁ!
ለ17 ዓመታት ያህል ፊፋን በፕሬዝዳንትነት የመሩት ስዊዘርላንዳዊው ሴፕ ብላተር አሁን ስልጣናቸውን እንደሚለቁ አስታውቀዋል። በሳቸውና በተቀሩት ጓደኞቻቸው ላይ አሜሪካ የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል በማለት ከቀናት በፊት ምርመራ መጀመሯን ተከትሎ ፊፋ እየታመሰ ነው። ደቡብ አፍሪካም የዓለም ዋንጫን በሃገሯ ለማካሄድ ለፊፋ 10ሚሊዮን ዶላር ጉቦ መስጠቷን አምናለች። አሜሪካ የወንጀል ምርመራ መክፈቷን ተከትሎ የፊፋ ዋና መስሪያቤት የሚገኝበት ስዊዘርላንድ ወንጀል መርማሪዎችም በተናጥል […]![]()
የጀርመን ሬድዮ ስለምርጫው ከሶስት ጋዜጠኞች ጋር ያደረገው ውይይት (+Audio)
የጀርመን ሬድዮ አማርኛ አገልግሎት አምስተኛውን ዙር የፌዴራልና የክልል ምርጫ በተመለከተ ከሶስት ጋዜጠኞች ውይይት አድርጎ ነበር። የራዲዮ ጣቢያው ጋዜጠኛ ሂሩት መለሰ፡- ከየማነ ናግሽ (ሪፖርተር ጋዜጣ)፣ ከ.ይልማ ኃ/ሚካኤል (የጀርመን ሬድዮ የበርሊን ወኪል) እና ከገበያው ንጉሴ(የጀርመን ሬድዮ የብራስልስ ዘጋቢ) ጋር፤ ስለቅድመ ምርጫውና ድምፅ የተሰጠበት ሂደትና ውጤቱ እንዲሁም የወደፊት ዕጣፈንታና የውጭ ኃይሎች ሚና አስመልክቶ ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይቱ ከተነሱት መህል፡- 1/የማነ ናግሽ (ሪፖርተር ጋዜጣ):- *የተቃዋሚ ተወካዮች እንዳይታዘቡ ተከልክለዋል። ውጤቱ ለጥርጣሬ ክፍት ያደርጓል። *አባሎቻቸውን ገለልተኛ ታዛቢ ሆነው የቀረቡት የአገርውስጥ ማህበራት የፓለቲካ ድጋፍ እንዲሰጡ የተደራጁ እንጂ ገለልተኛ አይደሉም። *የውጭ ኃይሎች ላይ መንጠልጠል ጥገኛ አስተሳሰብ ነው። የጉዳዩ ዋና ባለቤት ህዝብ ነው። ህዝቡ ድምፄን ተሰርቋል ብሎ ካመነ እስከመቼ(ለምን) ቁጭ ብሎ ያያል? *ተቃዋሚዎች በራሳቸው ለማሸነፍ አልገቡም። ተበታትነውና ዓቅመቢስ ሆነው ነበር የቀረቡት። አንድም ተቃዋሚ በተወዳደረባቸው ቦታዎች በሙሉ ቢያሸንፍ መንግስት ለመመስረት የሚችል አልነበረም። * በእኛ ዓይነት ብዝኃ-ህብረሰብ ውስጥ በዚህ ደረጃ ማሸነፍ አይቻልም። አንድም ድርጅት እንዲህ ዓይነት የአስተሳሰብ አንድነት መፍጠር አይቻለውም። ውጤቱ ለኢህአዴግ አስደንጋጭ እንጂ መልካም ነገር አይደለም።ድርጅቱ ያየዘው አቋም መፈተሽ አለበት። *ተቃዋሚዎችን በማድቀቅ ሳይሆን ሜዳውን ክፍት አድርጎ በተሻለ አስተሳሰብ ለመብለጥ መስራት አለበት። *ነገሩ ሂዶ ሂዶ ወዴት እንደሚያደርሰን አይታወቅም። —– 2/ ይልማ ኃ/ሚካኤል (የጀርመን ሬድዮ የበርሊን ወኪል)፡- *ማን አሸናፊ ሆኖ እንደሚወጣ ሳይታለም የተፈታ ነበር። *የሸንጎ ምርጫ ከኳስ ጨዋታ ጋር እኩል ነው። ገለልተኛ ዳኛና ሜዳ በሌለበት አይደረግም። *ተቃዋማ ፓርቲዎች ምንም ተስፋ አልነበራቸውም። *ዕርዳታ ሰጪ […]
የፌዴራል ዋና ኦዲተር የፋይናንስ ሕጋዊነትን ያልተከተሉ ቢሊዮን ብሮች መኖራቸውን ይፋ አደረገ

–እየተገነቡ ያሉ የባቡር ፕሮጀክቶች ችግሮችን ጠቆመ
-የደመወዝ ማስተካከያ እንዲደረግለት ፓርላማውን በአፅንኦት ጠየቀ
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የፋይናንስ ሕጋዊነትን ያልተከተሉ ቢሊዮን ብሮችን ለፓርላማው ግንቦት 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ይፋ አደረገ፡፡
የተሟላ ማስረጃ ሳይኖር በወጪ የተመዘገበ 368 ያልተወራረደ ሒሳብ መገኘቱን፣ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ውዝፍ ገቢ መኖሩንና ሌሎችንም ዋና ኦዲተሩ አቶ ገመቹ ዱቢሶ ለምክር ቤቱ አሳውቀዋል፡፡
ዋና ኦዲተር በ2006 ዓ.ም. የፌዴራል መንግሥት በጀት ተጠቃሚ የሆኑ 135 መሥሪያ ቤቶችን ኦዲት ማድረጉን ገልጸዋል፡፡ በዚህም መሠረት የፋይናንስ ሕጋዊነት ኦዲትን ያልተከተሉ 78 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች በሕጉ መሠረት ያላወራረዱት ሁለት ቢሊዮን ሃያ አምስት ሚሊዮን ብር መኖሩን ጠቁሟል፡፡ በዚህ ያልተወራረደ ሒሳብ ተጠያቂ ከሆኑት መሥሪያ ቤቶች መካከል የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 666.4 ሚሊዮን ብር፣ የትምህርት ሚኒስቴር 433.4 ሚሊዮን ብር፣ የአገር መከላከያ ሚኒስቴር 144.2 ሚሊዮን ብር ሕጉን ባልተከተለ መልኩ ወጪ ማድረጋቸው ተጠቅሷል፡፡
ገቢ ሰብሳቢ መሥሪያ ቤቶችና ድርጅቶች በወጣው ሕግና ደንብ መሠረት የመንግሥት ገቢ በወቅቱና በአግባቡ መሰብሰባቸውን ለማረጋገጥ፣ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣንና በሌሎች 12 ገቢ ሰብሳቢ መሥሪያ ቤቶች ላይ በድምሩ አንድ ቢሊዮን ብር ሰላሳ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር ያልተሰበሰበ ገቢ መኖሩንም ዋና ኦዲተር ይፋ አድርጓል፡፡
በወጪ ለተመዘገቡ ሒሳቦች የተሟላ መረጃ መኖሩን ለማረጋገጥ ባደረገው ኦዲት በ29 መሥሪያ ቤቶች የተሟላ ማስረጃ ሳይቀርብ፣ 368 ሚሊዮን ብር በወጪ ተመዝግቦ መገኘቱን ኦዲተሩ አቶ ገመቹ ዱቢሶ ገልጸዋል፡፡
ተሟልተው ካልቀረቡ ማስረጃዎች መካከልም ከዕቃ አቅራቢው የተሰጠ ማስረጃ ሳይቀርብ፣ ላቀረበው የክፍያ ጥያቄ ብቻ በወጪነት የተያዘ፣ ተራና አግባብነት የሌላቸው ደረሰኞች ማለትም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የሌላቸው ደረሰኞችንና የመሳሰሉትን ሕጋዊ ያልሆኑ ማስረጃዎች በመያዝ የተከፈሉ ወጪዎች እንደሚካተቱም ዋና ኦዲተሩ ገልጸዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ (በ2006) መሥሪያ ቤቶች የፈጸሙት ክፍያ ትክክለኛነትን ለማጣራት ኦዲት ሲደረግ በ19 መሥሪያ ቤቶች በተለያዩ ምክንያቶች የወጪውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ያልተቻለ 473.469 ሚሊዮን ብር መኖሩን የዋና ኦዲተሩ ሪፖርት ያሳያል፡፡ ከእነዚህም መሥሪያ ቤቶች መካከል ትልቁን ድርሻ ማለትም የ273.845 ሚሊዮን ብር ትክክለኛነቱ ያልተረጋገጠ ወጪ የተመዘገበበት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት መሥሪያ ቤት ነው፡፡
ይህ መሥሪያ ቤት ከደኅንነት ጋር የተያያዙ ግዥዎችን በተመለከተ ኦዲት ያለማስደረግ ሥልጣን ከዓመት በፊት በአዋጅ የተሰጠው ሲሆን፣ የዋና ኦዲተር የኦዲት ግኝትም ይህንን መብቱን ያልጣሰ እንዲያውም ራሱ መሥሪያ ቤቱ ኦዲት መደረግ ይችላል ብሎ ያቀረበው ሰነድ ላይ የተደረገ ኦዲት ውጤት መሆኑን ዋና ኦዲተሩ አቶ ገመቹ ለፓርላማው ግልጽ አድርገዋል፡፡
የዕቃ አገልግሎትና ግዥ በመንግሥት ደንብና መመርያ መሠረት የተፈጸመ መሆኑን ለማጣራት ኦዲት ሲደረግ፣ በ63 መሥሪያ ቤቶች ሕግን ያልተከተለ የ957.5 ሚሊዮን ብር ግዥ መፈጸሙን ዋና ኦዲተሩ ገልጸዋል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት በአሁኑ ወቅት 98 በመቶ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ኦዲት የማድረግ አቅም ቢፈጥርም፣ ከዚህ ቀደም በኦዲት ያገኛቸው ችግሮች ዛሬም አለመፈታታቸው አሳሳቢ እንደሆነ አቶ ገመቹ ለምክር ቤቱ አስረድተዋል፡፡
‹‹በተለይ ረጅም ዓመታት ያስቆጠሩ ተሰብሳቢ ሒሳቦች፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚከናወኑ ግንባታዎችና ግዥዎች በልዩ ሁኔታ ሊታዩ የሚገቡ ጉዳዮች መሆናቸውን ማስገንዘብ እወዳለሁ፤›› ሲሉ ዋና ኦዲተሩ አሳስበዋል፡፡
የዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ከፋይናንስ ሕጋዊነት በተጨማሪ የክዋኔ ኦዲት ማለትም የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሥራ አፈጻጸምን ከተሰጣቸው ኃላፊነትና ከአገሪቱ ሕጐች ጋር ያለውን መጣጣም በመገምገም ሪፖርት ያደርጋል፡፡ በዚህም መሠረት በ2006 ዓ.ም. የክዋኔ ኦዲት ከተከናወነባቸው መሥሪያ ቤቶች መካከል የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የመሠረተ ልማት ግንባታ አፈጻጸም ይገኝበታል፡፡
በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የመንግሥት ፕሮጀክቶች አፈጻጸም መመርያ መሠረት መጀመርያ የፕሮጀክት ምርመራ እንደሚደረግ፣ ፕሮፋይል በተዘጋጀላቸው ፕሮጀክት ሐሳቦች ላይ ዝርዝር ጥናት ከመደረጉ አስቀድሞ የፕሮጀክት ረቂቅ ሰነድ ይዘጋጅና ቅድሚያ የሚሰጣቸው የፕሮጀክት ሐሳቦች ወደ ዝግጅት ሒደት እንዲገቡ ይደረጋል ቢልም፣ በኮርፖሬሽኑ እየተተገበሩ ያሉ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች በ1999 ዓ.ም. በትራንስፖርት ሚኒስቴር መሪነት አጥኚ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ አማራጭ የየብስ ትራንስፖርትን አስመልክቶ ያደረገው ጥናት እንጂ፣ እያንዳንዱን ፕሮጀክት አስመልክቶ የተጠና የፕሮጀክት ጥናት ሰነድ አለመኖሩን ዋና ኦዲተሩ ይፋ አድርገዋል፡፡
የባቡር መሠረተ ልማት ግንባታ ፕሮጀክቶች ክትትል፣ ቁጥጥርና ድኅረ ትግበራው በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የፕሮጀክት አዘገጃጀት ማኑዋል መሠረት ሊካሄድ የሚገባው ቢሆንም፣ በዚያ መልኩ እየተካሄደ አለመሆኑን የዋና ኦዲተሩ ሪፖርት ያስረዳል፡፡
በመሆኑም በአዲስ አበባ ከተማ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት ግንባታ የሚያገለግል በኮንትራት ውሉ ውስጥ የተጠቀሱ ለግንባታ ሥራ፣ ለቁጥጥርና ክትትል አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችና ማኑዋሎች ለምሳሌ የጥራት ማረጋገጫ ማኑዋል የመሳሰሉትን ኦዲቱ እስከተከናወነበት ጊዜ ድረስ ኮርፖሬሽኑ ማቅረብ ባለመቻሉ፣ የፕሮጀክት ውሉ በሚለው የጥራት መሥፈርት መሠረት ፕሮጀክቱ እየተከናወነ መሆኑን ለማረጋገጥ አስቸጋሪ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በፕሮጀክቶች የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ውስጥ የሚጠቀሱ ምክረ ሐሳቦች ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ሊደረጉ የሚገባ ቢሆንም፣ ኮርፖሬሽኑ በሚዘረጋው የአዲስ አበባ ሚኤሶ መስመር ይህ እየሆነ አለመሆኑን የክዋኔ ኦዲት ሪፖርቱ ይገልጻል፡፡
ለአብነትም የባቡር መስመሩ በሚያልፍበት በአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ በርካታ የቱሪስት መተላለፊያ መንገዶችን ሳያስፈቅዱ መዘጋት፣ ያለፈቃድ መንገዶችን በፓርኩ ውስጥ እየቀደዱ ማውጣት፣ በፕሮጀክቶቹ የሚሠሩ የውጭ አገር ባለሙያዎች የዱር እንስሳትን ያለ ፈቃድ እያደኑ ለምግብነት የሚጠቀሙ መሆኑን ሪፖርቱ ይፋ አድርጓል፡፡
በሚኤሶ-ደወሌ የባቡር መስመር ዝርጋታ ያለውን የእሳተ ገሞራ መከሰት ሁኔታ ሊገመግም የሚችል ጥናት እንዲደረግ ኮንትራቱን የወሰደው ድርጅት ቢጠይቅም፣ በአካባቢው የላይኛው የመሬት ክፍል ላይ የመሬት መሰንጠቆች እየታዩ እሳተ ገሞራ የመከሰቱን ሁኔታ ሳያጠኑ ፕሮጀክቱ ተግባራዊ እንዲደረግ መፍቀዱ ተገቢ አለመሆኑን ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡
የባቡር ፕሮጀክቶች ሲተገበሩ ከኮንትራት ውሉ ውጪ ለሚጨመሩና ለሚቀነሱ ጉዳዮች ኮርፖሬሽኑ ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር አቅርቦ እንዲፈቀድ ማድረግ ሲገባው፣ ኮርፖሬሽኑ ግን የሰበታ ሚኤሶ ፕሮጀክት ከ1.639 ቢሊዮን ዶላር ወደ 1.841 ቢሊዮን ዶላር የኮንትራት ዋጋው ከፍ ሲል ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ቀርቦ ያልተፈቀደ መሆኑን ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡
ዋና ኦዲተሩ አቶ ገመቹ ዳቢሶ የሪፖርታቸው ማጠናቀቂያ ላይ የቀረቡት የኦዲተር መሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች የደመወዝ ማስተካከያ እንዲደረግላቸው ፓርላማው መንግሥትን በማሳመን እንዲተባበር ነው፡፡
በፓርላማውና በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በኩል በተደረጉ ጥረቶች ከሐምሌ 2006 ዓ.ም. ጀምሮ የመሥሪያ ቤቱ የደመወዝ ስኬል ከምርጫ ቦርድ እኩል እንዲሆን ቢወሰንም፣ በተመሳሳይ ጊዜ በተደረገው አጠቃላይ የሲቪል ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት እንዳይካተት በመደረጉ የተፈቀደው የደመወዝ ማስተካከያ የነበረውን ሠራተኛ የማረጋጋት ፋይዳ ሳያስገኝ መቅረቱን ገልጸዋል፡፡
በዚህም የተነሳ ከ60 በላይ የመሥሪያ ቤቱ ከፍተኛ የሒሳብ ባለሙያዎች በአብዛኛው ቁልፍ ቦታ ላይ ይገኙ የነበሩ መሥሪያ ቤቱን ለቀው መሄዳቸውን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ጥራት ያለውና በርካታ መሥሪያ ቤቶችን የሚሸፍን የኦዲት ሥራ እንዲሠራ የሚፈለግ ከሆነ፣ መንግሥት የደመወዝ ማስተካከያ ማድረግ ይኖርበታል ያሉት ዋና ኦዲተሩ አቶ ገመቹ፣ ‹‹ፓርላማው በዚህ ጉዳይ ላይ ጣልቃ እንዲገባ›› በይፋ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አንድ ባለሙያ ኦዲት የሚደረገው ሥራ አስፈጻሚው የመንግሥት አካል ሆኖ ሳለ ለዋና ኦዲተር የደመወዝ ጭማሪ የሚያደርገው ሥራ አስፈጻሚው መሆን እንደሌለበት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ስለሆነም ነፃነቱን ጠብቆ ሥራውን እንዲሠራ ጭማሪው ውሳኔ ማግኘት ያለበት በፓርላማው መሆን እንዳለበት ተከራክረዋል፡፡
ዋና ኦዲተሩ ላቀረቡት ፓርላማው ጣልቃ እንዲገባ የሚል ጥሪ ወዲያውኑ ምላሽ የሰጡት አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ፣ በጉዳዩ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትና ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር ላይ እንደሆኑና በቅርቡ ይፈታል ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ አባል ጽኑ እስራት ተፈረደበት

–ሰባት አባላቱ ተከላከሉ ተባሉ
አይኤስ በሊቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸመውን አረመኔያዊ ግድያ ለማውገዝ፣ መንግሥት ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ጠርቶ በነበረው የተቃውሞ ሰላማዊ ሠልፍ ላይ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ ፈጥረዋል›› ከተባሉት የሰማያዊ ፓርቲ
አባላት መካከል ናትናኤል ያለምዘውድ የተባለው አባል፣ በሦስት ዓመታት ከሦስት ወራት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ግንቦት 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ተፈረደበት፡፡
በፌዴራል ዓቃቤ ሕግ የቀረበለትን የወንጀል ክስ ሲሰማ የከረመው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ መናገሻ ወንጀል ችሎት በፍርዱ እንዳብራራው፤ ፍርደኛው ናትናኤል ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን፣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ አብዮት አደባባይ ሁከትና ብጥብጥ ፈጥሯል፡፡ ‹‹ወያኔ አረደን፣ ኢቲቪ ሌባ›› የሚል መፈክር በማሰማት፣ ከግብረ አበሮቹ ጋር መረበሹንም አመልክቷል፡፡ በፌዴራል ፖሊሶች ላይ ድንጋይ መወርወሩም ተመልክቷል፡፡ የሰዎችና በዕለቱ በሞባይል የተቀረፀ የቪዲዮ ማስረጃ ቀርቧል፡፡ ዓቃቤ ሕግ ሁለት ምስክሮችን ካሰማ በኋላ ናትናኤል ተከላከል ቢባልም መከላከያ ምስክር እንደሌለው በመግለጹ፣ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ እንዳለው በፍርዱ ገልጿል፡፡ ፍርድ ቤቱ ሁለቱም ወገኖች የቅጣት አስተያየት እንዲሰጡ ጠይቆ፣ ዓቃቤ ሕግ የቅጣት ማክበጃ ሐሳብ አቅርቧል፡፡
ተከሳሽ ናትናኤል በሰላማዊ ሠልፉ ላይ ብጥብጥ የፈጠረውን ቡድን መምራቱን፣ በሠልፉ ላይ የተገኙት ብዛት ያላቸው ስለነበሩ ብጥብጡ በፖሊስ ኃይል ባይበተን ኖሮ፣ ውጤቱ የከፋ ሊሆን ይችል እንደነበር ተጠቅሷል፡፡ ብጥብጡ ጠቅላላ ምርጫው ሊደረግ በነበረበት ዋዜማ የተደረገ ስለነበር ብጥብጡ አገር አቀፍ ሊሆን ይችል እንደነበር በመግለጽ፣ ቅጣቱ ከብዶ እንዲወስንለት ዓቃቤ ሕግ የክስ ማክበጃ ሐሳቡን ማቅረቡን ፍርዱ ያስረዳል፡፡
ፍርደኛው ናትናኤል ግን ‹‹ትምህርቴን አቋርጫለሁ፡፡ ለሚቀጥለው ዓመት እንድጀምር ይፈቀድልኝ፤›› ከማለት ባለፈ ያቀረበው የቅጣት ማቅለያ እንደሌለ ፍርድ ቤቱ ፍርዱን ሲያነብ ተሰምቷል፡፡
ፍርድ ቤቱ በሰጠው ፍርድ ላይ እንደገለጸው፣ ፍርደኛው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 490 (3) ማለትም፣ ስብሰባን ወይም ጉባዔን የማወክ ጥፋት የተፈጸመው በቡድን ወይም የጦር መሣሪያ በመያዝ ከሆነ፣ ከሰባት ዓመታት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እንደሚቀጣ የሚደነግገውን መተላለፉን ጠቁሟል፡፡ ፍርደኛው መንግሥት በሊቢያ ኢትዮጵያውያን የተፈጸመባቸውን አሰቃቂ ግድያ በተመለከተ ሕዝቡ ሐዘኑን እንዲገልጽና ተቃውሞውን እንዲያሰማ በጠራው ሠልፍ ላይ ድርጊቱን በመፈጸሙ፣ ብጥብጡ የተፈጠረው አገራዊ ምርጫ በሚደረግበት ዋዜማ ከመሆኑ አንፃር ሊያስከትል የሚችለው አደጋ ቀላል ሊሆን እንደማይችል የሚያመለክት መሆኑን ጠቁሞ፣ የወንጀሉን ደረጃ ከባድ ብሎታል፡፡
ዓቃቤ ሕግ ፍርደኛው ከግብረ አበሮቹ ጋር በሚል ለማክበጃ የተጠቀመበትን ሐሳብ የወንጀሉ ማቋቋሚያ መሆኑን በመጠቆም፣ ማክበጃውን ውድቅ አድርጐበታል፡፡ ፍርደኛው የወንጀል ሪከርድ የሌለበት በመሆኑ አንድ ቅጣት ተቀንሶለት በሦስት ዓመታት ከሦስት ወራት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ፍርድ ሰጥቷል፡፡
ማትያስ መኩሪያ፣ ብሌን መስፍን፣ ተዋቸው ዳምጤ የተባሉ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና መሳይ የሚባል አንድ ወጣት በተመሳሳይ ወንጀል ክስ ቀርቦባቸው ዓቃቤ ሕግ ሁለት የሰው ምስክሮች ካሰማባቸው በኋላ፣ ፍርድ ቤቱ እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል፡፡
ተከሳሾቹ የመከላከያ ምስክር ለማቅረብ የፈለጉት እርስ በርሳቸው ለመመሰካከር የነበረ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ በተመሳሳይ የክስ መዝገብ የተከሰሱ ምስክር መሆን እንደማይችሉ በመግለጽ ሌላ መከላከያ ካላቸው እንዲያቀርቡ አዟል፡፡ የመከላከያ ምስክሮችን ለመስማት ለሰኔ 4 ቀን 2007 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ ወንጀል ችሎት ክስ የተመሠረተባቸው የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ወይንሸት ሞላ፣ ዳንኤል ተስፋዬ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ማስተዋል ፍቃዱና ቤተልሔም አካለ ወርቅ በቀረበባቸው ተመሳሳይ፣ ‹‹ሰላማዊ ሠልፍን ማወክና ብጥብጥ ማስነሳት ወንጀል›› የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን በመከላከያ ምስክርነት ለማሰማት ለሰኔ 8 ቀን 2007 ዓ.ም. ተቀጥረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስድስት ሠራተኞች በጥይት ተገደሉ
–ግድያውን ፈጽሟል የተባለው ተጠርጣሪ እጁን ሰጥቷል
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመቀሌ ዲስትሪክት የማይፀብሪ ቅርንጫፍ ዋና ሥራ አስኪያጅን ጨምሮ፣ ስድስት የባንኩ ሠራተኞች ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. በባንኩ የጥበቃ ሠራተኛ በጥይት ተገደሉ፡፡
ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. የተለመደ ሥራቸውን በማከናወን ላይ እያሉ፣ በባንኩ የጥበቃ ሠራተኛ በጥይት ተደብድበው የሞቱት የቅርንጫፉ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ወልዳይ ገብሩ፣ የባንኩ ኮንትሮለር አቶ አትንኩት ደምሴና የደንበኞች አገልግሎት ኦፊሰሮች የነበሩት ወ/ሮ ለምለም ግደይና አቶ አስማማው ገብረ ማርያም መሆናቸውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮሙዩኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤፍሬም መኩሪያ አረጋግጠዋል፡፡ አቶ ንጉሤ ግርማና አቶ ጌትነት ባዩ የተባሉ በኮሜርሻል ኖሚኒስ አማካይነት የተቀጠሩ የባንኩ ሠራተኞችም መገደላቸውን አቶ ኤፍሬም አክለዋል፡፡
የባንኩ ሠራተኞችን በመግደል የተጠረጠረው የጥበቃ ሠራተኛ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ሆኖ፣ ግድያውን ሊፈጽም የቻለበት ምክንያት እየተጣራ መሆኑን የገለጹት አቶ ኤፍሬም፣ ግድያውን የፈጸመው ግለሰብ የሥራ አፈጻጸሙን በሚመለከት ምክር፣ ተግሳጽና ማስጠንቀቂያ ከተሰጠው ከደቂቃዎች በኋላ መሆኑን መረዳታቸውን ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጥበቃና የፅዳት ሠራተኞችን የመቅጠርና የመቆጣጠር ሥራን ለኮሜርሻል ኖሚኒስ መስጠቱን የጠቆሙት አቶ ኤፍሬም፣ የባንኩን ሠራተኞች በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብም የተቀጠረው ከዚያው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ተጠርጣሪው በሥራው ላይ ተገቢ ያልሆነ ባህሪያትን በማሳየቱ በባንኩ ኃላፊዎች ቢመከርም ሊስተካከል ባለመቻሉ፣ የቅርንጫፍ ዋና ሥራ አስኪያጁ መቐለ ለሚገኘው የኮሜርሻል ኖሚኒስ ጽሕፈት ቤት ደብዳቤ በመጻፍ፣ የጥበቃ ሠራተኛውን በሌላ እንዲተካላቸው ጠይቀው እንደነበር ገልጸዋል፡፡
የኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃላፊዎች በሠራተኞቻቸው ላይ ቅሬታ ሲደርሳቸው በቦታው በመገኘትና ሠራተኞቹንና የተቋሙን ኃላፊዎች በማነጋገር፣ ሠራተኛው ተገስጾና ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ሥራውን እንዲቀጥል ወይም እንዲባረር እንደሚያደርጉ የገለጹት አቶ ኤፍሬም፣ ተጠርጣሪውም በዕለቱ ተመክሮ፣ ተገስጾና ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት በዕለቱ ተረኛ ስለነበር መሣሪያውን ይዞ ወደ ሥራው መሰማራቱን ተናግረዋል፡፡ ከደቂቃዎች በኋላ ግን ሁለት የፍተሻ ሠራተኞችን አቁስሎ ሌሎቹን መግደሉን አስረድተዋል፡፡
የተገደሉት የባንኩ ሠራተኞች የቀብር ሥነ ሥርዓት መፈጸሙን ያስታወቁት አቶ ኤፍሬም፣ ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ወልዳይ ገብሩ ቤተሰቦቻቸው በሚኖሩበት በዓደዋ ልዩ ስሙ ወርኢ ዳጋብር ቀብራቸው እንደተፈጸመም አክለዋል፡፡ ኮንትሮለሩ አቶ አትንኩት ደምሴ በትውልድ ሥፍራቸው ባህር ዳር የቀብራቸው ሥርዓት ተፈጽሟል፡፡ ወ/ሮ ለምለም ግደይና የኮሜርሻል ኖሚኒስ ሁለቱ ሠራተኞች አቶ ንጉሤና አቶ ጌትነት፣ በዚያው በማይፀብሪ ቀብራቸው ሲፈጸም፣ አቶ አስማማው ከማይፀብሪ በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ዲማ በሚባለው አካባቢ ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡
ባንኩ በሠራተኞቹ ላይ በደረሰው ያልታሰበና ድንገተኛ አደጋ ጥልቅ ሐዘን እንደተሰማው የገለጹት አቶ ኤፍሬም፣ ሠራተኞቹ መገደላቸው ከተሰማበት ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ቀብራቸው እስከተፈጸመበት ዕለት ድረስ፣ የመቀሌ ዲስትሪክት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አሻግሬ አስመላሽ በሥፍራው ተገኝተው ያደረጉት አስተዋጽኦም ከፍተኛ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ የንግድ ባንክ ጠቅላላ የጥበቃዎች ሥራ አስኪያጅም እዚያው ሆነው ጉዳዩን እየተከታተሉ መሆኑን አቶ ኤፍሬም አስታውቀዋል፡፡
መኢአድና ኢራፓ የምርጫውን ውጤት አንቀበልም አሉ
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. የተካሄደውን ጠቅላላ ምርጫ ውጤት እንደማይቀበሉት፣ ግንቦት 25 ቀን 2007 ዓ.ም. በየጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ፡፡
መኢአድ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው ዋና ጽሕፈት ቤቱ ምርጫውን አስመልክቶ በፕሬዚዳንቱ አቶ አበባው መሐሪና በሌሎች የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች መግለጫ ሲሰጥ፣ በምርጫው ወቅት ገጠመኝ ያላቸውን ችግሮችና ጫናዎች ዘርዝሮ አቅርቧል፡፡
‹‹ባለፉት አራት ምርጫዎች በተከሰቱ ችግሮች ዙሪያ መፍትሔ አስቀምጦ ሙሉ በሙሉ ተሻሽሎ ይካሄዳል የሚል ዕምነት ቢኖረንም፣ ራሱን ሙሉ በሙሉ ወደ አምባገነንነት በቀየረው ገዥ ፓርቲ አፈና፣ ወከባ፣ እስራትና ግድያ የተነሳ ምርጫው ሳይሳካ ቀርቷል፤›› በማለት መኢአድ አስታውቋል፡፡
መኢአድ በምርጫው ዕለትና ከዚያ ቀደም ብሎ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ደረሰብኝ ያላቸውን ችግሮች ዘርዝሯል፡፡ ከአዲስ አበባ በስተቀር ኦሮሚያ፣ አማራና ደቡብ ክልሎችን ጨምሮ አባላቱ መታሰራቸውንና ታዛቢዎቹ ከምርጫ ጣቢያ መባረራቸውን ገልጿል፡፡
‹‹ምርጫው ነፃ፣ ፍትሐዊና፣ ሰላማዊ እንደሆነ ይገለጽ እንጂ በተግባር የታየው ግን የዚህ ተቃራኒ ነው፤›› ብሏል፡፡ ‹‹ሰው እየደበደቡ፣ እያሰሩ፣ እያንገላቱ፣ ከመኖሪያ እያፈናቀሉና የግድ ንብን ምረጡ ብለው ለማስፈራራታቸው ተጨባጭ መረጃ ባለበት ሁኔታ እንዴት ብሎ ነፃ፣ ፍትሐዊና ሰላማዊ ምርጫ እንደተካሄደ የሚያውቀው አፋኙ ሥርዓት ብቻ ነው፤›› በማለት መኢአድ በመግለጫው አስታውቋል፡፡
በምርጫው ምክንያት የታሰሩ የፓርቲ አባላትና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል፡፡ ‹‹ምርጫው ታዋቂ የሆኑ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎችና ከፖለቲካ ገለልተኛ የሆኑ የሲቪክ ማኅበራት ባልተገኙበት ኢሕአዴግ ባደራጃቸው የሲቪክ ማኅበራትና አባብሎ ወደ ታዛቢነት ያሰማራቸው የምርጫ ታዛቢዎች በተገኙበት የተካሄደ በመሆኑ፣ ይህንን የፖለቲካ ድራማ የተከናወነበት ምርጫ የማንቀበለው መሆኑን እናስታውቃለን፤›› በማለት መኢአድ መግለጫውን አጠቃሏል፡፡
የፓርቲውን የወደፊት አቅጣጫ በተመለከተ የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ አበባው ሲገልጹም፣ ‹‹ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር መክረን ዘክረን ወደፊት የምናሳውቀው ይሆናል፤›› ብለዋል፡፡
በተመሳሳይም በዋና ጽሕፈት ቤቱ መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ)፣ የዘንድሮው ምርጫ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መካሄዱን ያስረዱልኛል ያላቸውን የተለያዩ ክስተቶች በማንሳት አስረድቷል፡፡ በፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ ተሻለ ሰብሮና በሌሎች ኃላፊዎች በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተገለጸው፣ ለምርጫ ቦርድ ፓርቲው ያቀረባቸው ዕጩዎች ቁጥራቸው ያለምንም አሳማኝ ምክንያት ተቀንሶ ፓርቲው በተወሰኑለት ዕጩዎች ብቻ እንዲወዳደር መደረጉ ከፍተኛ ጫና ፈጥሮበታል፡፡
እንዲሁም በአማራ፣ በደቡብና በኦሮሚያ ክልሎችና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዕጩ ምዝገባ ወቅት፣ በቅስቀሳና በምርጫው ዕለት አጋጠሙኝ ያሏቸውን ችግሮች በባለ 6 ገጽ መግለጫው አስታውቋል፡፡ አብዛኛዎቹ ችግሮችም ከዕጩዎች አለመመዝገብ፣ ከአባላት መዋከብና መታሰር እንዲሁም የታዛቢዎች በሥፍራው ተገኝተው መታዘብ ከመከልከላቸው ጋር የሚያያዙ ናቸው፡፡
‹‹ጠጣር ግድፈቶች በተንፀባረቁበትና በተስተዋሉበት ሁኔታ የሕግ የበላይነት ተሟልቷል ተብሎ ከነጉድፉ መቀበል የፖለቲካ ቃር የሚያስይዝ ከመሆኑም በላይ፣ ከቀደምቶቹ ምርጫዎች 2002 እና 2005 (ማሟያና አካባቢያዊ) ባልተለየ መልኩ በአንድ ቅርጫት የተቀመጠ የቅድመ ምርጫ ሒደትና ውጤት በመሆኑ ፓርቲው አልተቀበለውም፤›› በማለት አስታውቋል፡፡
ቀጣይ አቅጣጫቸውን በተመለከተ ከሪፖርተር ለቀረበላቸውም ጥያቄ፣ ‹‹በትግል ደክመን ሳይሆን በመንግሥት ጫና ምክንያት መፈናፈን ባለመቻላችን ምንም እንኳን ዛሬ በዝረራ ብንወጣም፤ ዝረራው ግን ለነገው ቁጭት ጭሮብናል፤›› በማለት መልሰዋል፡፡
ፓርቲው ለወደፊቱ ሁለት አቅጣጫዎች ማዘጋጀቱን ገልጿል፡፡ አንደኛው ብሔራዊ መግባባትን ማስገኘት የሚል ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር አብሮ መሥራት የሚሉ ናቸው፡፡
ሚድሮክ አጥሮ በያዛቸው 13 ቦታዎች ላይ ግንባታ ለማካሄድ 18 ቢሊዮን ብር መመደቡ ተሰማ
በቅርቡ ተጨማሪ የግንባታ ጊዜ የተሰጠው ሚድሮክ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ለዓመታት አጥሮ ባስቀመጣቸው 13 ቦታዎች ከመስከረም 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ግንባታ ለማካሄድ 18 ቢሊዮን ብር መመደቡ ታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እነዚህን ቦታዎች በሕጉ መሠረት መንጠቅ ቢኖርበትም፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በጉዳዩ ጣልቃ በመግባት በልዩ ሁኔታ ተጨማሪ የግንባታ ጊዜ እንዲሰጥ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ በዚህ መሠረት የግንባታ ጊዜ የተጨመረለት ሚድሮክ በቦታዎቹ ላይ ግንባታ ለማካሄድ ዝግጅት እያደረገ ነው ተብሏል፡፡
የሚድሮክ ባለቤትና ሊቀመንበር ሼክ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ የ13 ቦታዎች ግንባታ በመስከረም 2008 ዓ.ም. እንዲጀመር፣ ለሚድሮክ ኮንስትራክሽን መመርያ መስጠታቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
በ13ቱም ቦታዎች ላይ የሚሠሩት ሕንፃዎች ዲዛይንን ናሽናል ኮንሰልት ኩባንያ ከጣሊያንና ከስፔን ኩባንያዎች ጋር በጋራ የሠራ ሲሆን፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድ ለማግኘት ጥያቄ እያቀረበ መሆኑ ታውቋል፡፡
የደርባ ሚድሮክ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኃይሌ አሰግዴ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የፕሮጀክቶቹን ግንባታ በመስከረም ወር ለማስጀመር ሙሉ ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡ ሚድሮክ ለዓመታት አጥሮ የያዛቸው ቦታዎች ካዛንቺስ፣ ሜክሲኮ፣ ሳር ቤት፣ ፒያሳና ጉርድ ሾላን ጨምሮ በተለያዩ የከተማው ክፍሎች ይገኛሉ፡፡
እነዚህ ቦታዎች ቀደም ሲል የተሰጣቸው የግንባታ ጊዜ በማለፉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዲነጠቁ የውሳኔ ሐሳብ አቅርቦ ነበር፡፡ አስተዳደሩ እነዚህን የሚድሮክ 13 ቦታዎች ጨምሮ ታጥረው የተቀመጡ 109 ቦታዎች ላይ ስለሚወስደው ዕርምጃ ጥናት ማስጠናቱ ይታወሳል፡፡ ነገር ግን አስተዳደሩ በሚድሮክ የተያዙትን ቦታዎች በተመለከተ መውሰድ ያለበትን ዕርምጃ እንዲያጠና ልዩ የባለሙያዎች ኮሚቴ አዋቅሮ አስጠንቷል፡፡
ኮሚቴው ባጠናው ጥናት ሚድሮክ በተወሰኑ ቦታዎች ላይ ብቻ መሠረት ያወጣ ቢሆንም፣ በአብዛኛዎቹ ቦታዎች ምንም ዓይነት ግንባታ አለማካሄዱን በመግለጽ ቦታዎቹ ለሌሎች አልሚዎች እንዲሰጡ የውሳኔ ሐሳብ አቅርቦ ነበር፡፡
በዚህ መሠረት በተለይ በልደታ ክፍለ ከተማ ሜክሲኮ ዋቢ ሸበሌ አጠገብ የሚገኘውን ቦታ፣ በየካ ክፍለ ከተማ ደግሞ ጉርድ ሾላ በሻሌ ሆቴል አካባቢ የሚገኘውን ቦታ ካርታ አምክኗል፡፡
ነገር ግን ሼክ አል አሙዲ በቦታዎቹ ላይ ግንባታ ያልተካሄደው በሚድሮክ ብቻ ሳይሆን በከተማ አስተዳደሩ ጥፋት ጭምር ነው በማለት ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡ በእነዚህ ቦታዎች ላይ የሚያካሂዷቸው ግንባታዎች ግዙፍና ውብ በመሆናቸው ለከተማው ከፍተኛ ጠቀሜታ ስለሚኖራቸው የግንባታ ጊዜ እንዲራዘም ጠይቀዋል፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ከመከረ በኋላ የሼክ አል አሙዲ አላሙዲ ጥያቄ በልዩ ሁኔታ እንዲስተናገድ ወስኗል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ለአዲስ አበባ ከተማ በሰጠው መመርያ መሠረት ሚድሮክ የውል ማሻሻያ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ለቀጣዩ ዓመት ከ35 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት ጠየቀ
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በ2008 በጀት ዓመት ለማከናወን ላቀዳቸው የመንገድ መሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ከ35 ቢሊዮን ብር በላይ የበጀት ጥያቄ አቀረበ፡፡
ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ለ2008 ዓ.ም. የተጠየቀው በጀት ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር ከአምስት ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ አለው፡፡ በ2007 በጀት ዓመት ተፈቅዶለት የነበረው በጀት 30 ቢሊዮን ብር ነበር፡፡
የባለሥልጣኑ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሳምሶን ወንድሙ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ለ2008 ዓ.ም. ከተጠየቀው በጀት ውስጥ ከ24 ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆነው በኢትዮጵያ መንግሥት ይሸፈናል ተብሎ የሚጠበቅ ነው፡፡ ወደ 11 ቢሊዮን ብር የሚሆነው በጀት ግን በውጭ የፋይናንስ ተቋማት የሚሸፈን ይሆናል ተብሎ የተቀመረ እንደሆነ አቶ ሳምሶን ገልጸዋል፡፡ መንግሥት ለዘርፉ የሚመድበው በጀት ማደግ የአገር ውስጥ ኮንትራክተሮች የበለጠ እንዲሳተፉ ይረዳል ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በመንግሥት ከፍተኛ በጀት ከሚበጀትላቸው ተቋማት መካከል በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት ውስጥ አንዱ ሲሆን፣ ተጨማሪ በጀት በማስፈቀድም የሚታወቅ ነው፡፡
በየዓመቱ የሚፈቀድለት በጀት እየጨመረ የመጣው የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን፣ ለ2008 በጀት ዓመት እንዲፈቀድለት ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ያገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ አቶ ሳምሶን አስረድተዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በ2007 በጀት ዓመት በአሥር ወራት ውስጥ 19 የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለኮንትራክተሮች አስተላልፏል፡፡ እነዚህ ፕሮጀክቶች ከ25.3 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቁ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 1,529.4 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ ናቸው፡፡ በ2008 በጀት ዓመትም ከ25 ያላነሱ አዳዲስ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ያስጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ምርጫው ከምንጊዜውም የተሻለ ቢሆንም የሕግ ጥሰቶች እንደነበሩበት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ገለጸ

ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. የተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም ቢጠናቀቅምና በአንድ ምርጫ ጣቢያ 1,000 ሰዎች ብቻ መመረጥ ቢኖርባቸውም፣ ሕጉ ከሚያዘው በተቃራኒ በአንዳንድ ጣቢያዎች ከ1,000 በላይ ድምፅ ሰጪዎች
መመዝገባቸውና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተወካይ ታዛቢዎች መጓደል፣ ከታዩ ችግሮች መካከል እንደሚጠቀሱ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ ግንቦት 22 ቀን 2007 ዓ.ም. የምርጫውን መጠናቀቅ አስመልክቶ በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የዘንድሮው ምርጫ ከዚህ በፊት ከተካሄዱት ሁሉ የተሻለና ሰላማዊ እንደነበር ገልጾ፣ ከሁለት ሺሕ ጣቢያዎች በላይ ባደረገው ክትትል የተወሰኑ ስህተቶችን ማስተዋሉን ገልጿል፡፡
ዋና ኮሚሽነሩ አምባሳደር ጥሩነህ ዜና በሰጡት የቅድመ ሪፖርት መግለጫ፣ ኮሚሽኑ ከ45,000 በላይ የምርጫ ጣቢያዎች በ2,000 ያህሉ 200 ሠራተኞችን አሰማርቶ የምርጫውን ሒደት መገምገሙን ገልጸዋል፡፡
ኮሚሽነሩ በተለያዩ ጣቢያዎች በሕጉ መሠረት በአንድ ጣቢያ ከ1,000 ያልበለጡ ተመዝጋቢዎች ድምፅ መስጠት ሲገባቸው፣ ከዚያ በላይ ድምፅ የተሰጠባቸው አካባቢዎችን መታዘቡን በመግለጽ ለወደፊቱ መስተካከል እንደሚገባው በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት አስታውቀዋል፡፡
በተጨማሪም በተወሰኑ የምርጫ ጣቢያዎች የተቃዋሚ ፓርቲዎችን የወከሉ ታዛቢዎች መጓደል በኮሚሽኑ ሠራተኞች ከተስተዋሉ እንከኖች እንደሚካተት ጠቁመዋል፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎች ዕጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባን በሚመለከት በምርጫ ሕጉ መሠረት በቂ ጊዜ ተሰጥቶት መከናወኑን፣ በአንዳንድ ፓርቲዎች ከሒደቱ ጋር ተያይዞ የቀረቡ ቅሬታዎችን ለመፍታት ቦርዱ ያደረገውን ጥረት በቅድመ ምርጫ ወቅት በበጐ ከታዩ ጥረቶች እንደሚካተት ኮሚሽኑ አውስቷል፡፡ በተጨማሪም በዘንድሮው ምርጫ የሴቶች ተመራጭነት ተሳትፎ በገዢው ፓርቲ ተወዳዳሪዎች ባለፈው ምርጫ ከነበረበት 28 በመቶ ወደ 37 በመቶ ከፍ እንዲል መደረጉ፣ ለዚህም ደግሞ ቦርዱ በገንዘብና በተለያዩ ድጋፎች ማበረታቻ መስጠቱንም በኮሚሽኑ ከተገለጹ በጎ ጎኖች ውስጥ ተካቷል፡፡
እንዲሁም ለፓርቲዎቹ የምርጫ ቅስቀሳ እንዲረዳ የአየር ጊዜና የኅትመት ሚዲያ ድልድል መደረጉ ለምርጫው መልካም አስተዋጽኦ ማድረጉን አምባሳደር ጥሩነህ አስረድተዋል፡፡ በአንፃሩ አንዳንድ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተሰጣቸው የአየር ጊዜና የጋዜጣ ዓምዶችን በአግባቡ መጠቀም ያለመቻላቸው በቅድመ ምርጫ ወቅት ከታዩ ችግሮች ውስጥ እንደሚካተቱ ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል፡፡
በምርጫው ዕለትም ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት የምርጫ አስፈጻሚዎች ድምፅ የሚሰጠቱንም ሆኑ ሌሎች የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነቶች መወጣታቸውንና በአግባቡ ማጠናቃቃቸውን የኮሚሽኑ ቅድመ ሪፖርት ገልጿል፡፡ በተመሳሳይም በተለይ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተፈጠረውን የምርጫ ወረቀት እጥረትም በኮሚሽኑ ሪፖርት ተካቷል፡፡
በምርጫ ወቅት ለመራጩ ሕዝብ ስለአመራረጥ ግንዛቤ መስጠቱን ያወሱት ኮሚሽነሩ፣ አልፎ አልፎ ድምፅ አልባ የምርጫ ወረቀቶች እንደነበሩም ገልጸዋል፡፡
በድኅረ ምርጫ ወቅት በሁለት ምርጫ ጣቢያዎች የኮሚሽኑ የክትትል ሥራን ባለመረዳት ባለሙያዎች የድምፅ ቆጠራውን መከታተል ባይችሉም፣ በሌሎች ኮሚሽኑ በመረጣቸው ጣቢያዎች የድምፅ ቆጠራውን በሚገባ ለመታዘብ ችሏል ሲሉ አምባሳደር ጥሩነህ ገልጸዋል፡፡
የድኅረ ምርጫ ሒደቱን አሁንም ቢሆን በኮሚሽኑ ክትትል እያደረገበት መሆኑን፣ እስካሁን ያለው ሒደትም ከምንጊዜው በበለጠ ሰላማዊ እንደሆነ ኮሚሽነሩ ማስተዋላቸውን አመልክተዋል፡፡
ነገር ግን በመላው አገሪቱ ከነበሩ ጣቢያዎች አምስት በመቶውን ብቻ ተከታትሎ ምርጫው ፍትሐዊና ነፃ ነው ብሎ መደምደም ተዓማኒነቱን ሊያመለክት ይችላል ወይ? የሚል ጥያቄም ለኮሚሽነሩ ቀርቦ ነበር፡፡ እሳቸውም ሲመልሱ፣ ‹‹በስታትስቲክስ የአሠራር ሕግ መሠረት አምስት በመቶ የሚሆን ናሙና በመውሰድ አጠቃላይ ድምዳሜ መድረስ ስለሚቻል፣ ባሰማራናቸው 200 ሠራተኞች 2,000 በሚሆኑ ጣቢያዎች ክትትል በማድረጋችን አጠቃላይ አገራዊ ምርጫ ውጤት ላይ መደምደም ያስችላል፤›› ሲሉ መልሰዋል፡፡ ኮሚሽኑ የምርጫውን አጠቃላይ ሪፖርት በሰኔ ወር መጨረሻ ይፋ እንደሚያደርግም አስታውቀዋል፡፡
ጦማሪ አቤል ዋበላ የእስራት ቅጣት ተፈረደበት

ፍርድ ቤት በመድፈር ወንጀል ግንቦት 19 ቀን 2007 ዓ.ም. ጥፋተኛ የተባለውና በሽብር ወንጀል ተከሰው በክርክር ሒደት ላይ ከሚገኙት ጦማሪያን መካከል አንዱ የሆነው ጦማሪ አቤል ዋበላ፣ በአራት ወራት እስራት እንዲቀጣ ግንቦት 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ፍርድ ተሰጠ፡፡
ተከሳሹ በሌሎች ቀጠሮዎች መልካም ፀባይ እንደነበረው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ጠቁሞ፣ የአራት ወራት እስራቱን በሁለት ዓመታት ገድቦለታል፡፡
ጦማሪ አቤል ጥፋተኛ የተባለው ግንቦት 19 ቀን 2007 ዓ.ም. ዓቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ አዲስ ሲዲ ለፍርድ ቤቱ ሲያቀርብ፣ የቀረበው ሲዲ ‹‹የሚመለከተው ሶሊያና ሽመልስን ብቻ ነው? ወይስ እኛንም ያካትታል?›› የሚል ጥያቄ ሲያቀርብ ፍርድ ቤቱ እንዳይናገር ሲከለክለው በመናገሩና ፍርድ ቤቱን ‹‹ራሳችሁ ሥነ ሥርዓት›› በማለት ኃይለ ቃል ተናግሯል ተብሎ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
ተጨማሪ የኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይል ወደ ሶማሌ ክልል መሰማራቱ ተገለጸ
ኢሳት ዜና (ግንቦት 25, 2007) በኢትዮጵያና ጎረቤት ሶማሊያ ድንበር አካባቢ የተቀሰቀሰዉን ግጭት ተከትሎ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ወታደራዊ ሃይል ወደስፍራው ማሰማራቷ ተገለፀ። በእስካሁኑ የኢትዮጵያ ልዩ ሃይሎችና በሶማሊያ የጎሳ ታጣቂዎች መካከል በተካሄደዉ ግጭት በትንሹ ከ50 በላይ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፤ የሶማሊያ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ የፀጥታ ሃይሎች የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅመዋል ሲሉ ተቃዉሞ ማሰማታቸውን ሶማሊ ከረትን የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል። የጋልጋይዱድ ክልል …
ከሽህ ጦረኛ አንድ ወረኛ ትጥቅ ያስፈታል! በበርናባስ ገብረማሪያም
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ኦነግ ‘አጠቃሁ’ አለ – ሰኔ 02, 2015
olf-ethiopia-clashes-the-standard-06-02-15
ዞን ዘጠኝ – ቅጣት – ሰኔ 02, 2015
zone-9 verdict 06-02-15
መኢአድ ከፍተኛ በደል ተፈፅሞብኛል ይላል – ሰኔ 02, 2015
aeup complains about elections 06-02-15
ከኬንያ ተጠልፈው የነበሩት ሁለቱ የኦብነግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ወደ ናይሮቢ ተመለሱ
ግንቦት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአንድ ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የደህንነት ሃይሎች ከኬንያ ተጠልፈው ወደ ኢትዮጵያ ተወስደው የነበሩት አቶ ሱሉብ አብዲ አህመድና አቶ አሊ አህመድ ሁሴን ትናንት ምሽት ኬንያ ናይኖቢ መግባታቸውን ለኢሳት ደረሰው መረጃ አመልክቷል። ሁለቱ ከፍተኛ አመራሮች በምን ሁኔታ ወደ ናይኖቢ እንደተመለሱ የታወቀ ነገር የለም። የድርጅቱ የውጭ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አብድረህማን …
የመንግስትና የፖሊስን መልካም ስም አጥፍተዋል የተባሉ ወጣቶች ተፈረደባቸው
ግንቦት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አይ ኤስ የተባለው አሸባሪ ቡድን በኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደውን ዘግናኝ እርምጃ ለማውገዝ በተጠራ ሰልፍ ላይ የመንግስትንና የፖሊስን ስም አጥፍተዋል የተባሉ ወጣቶች በእስርና በገንዘብ ተቀጥተዋል። አስማማው ወልዴ፣ የማነ ወርቅነህ፣ ስንታየሁ ታሪኩ፣ ያሲን ቃሲምና ይግረማቸው አበበ ሚያዚያ 14 ቀን 2007 ዓም ጠ/.ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት ድምጻቸውን ከፍ …
የግል ድርጅቶች ሠራተኞች አዲስ የተረቀቀውንና የፕሮቪደንት ፈንድ የሚያሳጣቸውን ሕግ በመቃወም ገንዘባቸውን እያወጡ ነው።
ግንቦት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅን በማሻሻል ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ ፕሮቪደንት ፈንድ ሲያጠራቅሙ የቆዩ የግል ሠራተኞችን በጡረታ እንዲታቀፉ በማድረግ ሰበብ ፕሮቪደንት ፈንዳቸውን ለመውረስ የሚያስችል ሕግ ሰሞኑን ለፓርላማ መቅረቡ ከተሰማ ወዲህ በርካታ ሠራተኞች ከአሰሪዎቻቸው ጋር በመነጋገር ገንዘባቸውን ሕጉ ከመተግበሩ በፊት እያወጡ መሆኑን ዘጋቢያችን ገልጿል፡፡ ፓርላማው የቀረበለት የግል ድርጅት …
በአማራ ክልል የጀልባ አገልግሎት ሰጪ ነጋዴዎች ለረዢም ጊዜ በመታገዳቸው ችግር ላይ መሆናቸውን ተናገሩ
ግንቦት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጣና ሃይቅ ላይ በቱሪስት ጀልባ ትራንስፖርት የሚያገለግሉ የጀልባ ባለሃብቶችና ካፒቴኖች፣ “የአማራ ክልል ንግድና ትራንስፖርት ቢሮ ‘ህገ ወጥ’ ናችሁ በሚል ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ አስራ ሰባት ጀልባዎችን ከሶስት ወር በላይ በማሰሩ ቤተሰቦቻቸውንና ራሳቸውን ለማስተዳደር መቸገራቸውን ተናግረዋል፡፡ ሶስት መቶ ያህል ቤተሰብ የሚያስተዳድሩት ቅሬታ አቅራቢዎች ፣ ለአመታት በስራው ላይ ሲቆዩ …
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ሰኔ 02, 2015
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ማክሰኞ፡- ሐኪሙን ይጠይቁ፣ ንግድ፣ ምጣኔ ኃብትና ግብርና
በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በቀዶ ጥገና ስህተት የ 5 ልጆች እናት ህይወት አለፈ
ዘውዲቱ ሆስፒታል የመህፀን እጢ እንዳለባቸው የተነገራቸው የ 5 ልጆች እናት እጢው ወደ ካንሰር እንዳይለወጥ አስቸኳይ ቀዶ ጥገና እንዲደረጉ ይታዘዛሉ ። ለዚህም ቀዶ ጥገና ሆስፒታሉ መሳሪያ ስለሌለው ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የምርመራ ውጤታቸውን አባሪ በማድረግ ይልካቸዋል። የተጠቀስው ሆስፒታል እደደረሱም እናት ለህክምና ከአቅማቸው በላይ የሆነ ክፍያ ሰለተጠየቁ «ያለአባት የሚያሳድጓቸው የ 5 ልጆች እናትና የቤተሰብ ሃላፊ መሆናቸውን ጭምር […]![]()
ፎቶ ላይ የምትታየው ሴት ካትሊይን ጄነር የምትባል ሲሆን , ብሩስ ጄነር ፆታውን በቀዶ ጥገና በመቀየሩ ምክንያት የተፈጠረች ሴት ናት!
በመጀመርያው ምስል ላይ የሚታየው ሰው ብሩስ ጄነር ይባላል, በፈረንጆቹ 1976 በክረምት ኦሎምፒክ ለአሜሪካ በዴካትሎን ስፖርት የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘ ስፖርተኛ ነው :: በሁለተኛም ምስል ላይም ሙሉ ልብስ ለብሶ የሚታየው ይኸው ብሩስ ጄነር ሸምገል ብሎ ነው , ከኦሎምፒክ ስፖርቱ በሁውላ , በቀጣይ ህይወቱ የመኪና እሽቅድድም ስፖርት ላይም ተሳትፎ ነበረው , እውቅናውን ተጠቅሞም የተለያዩ የቴቬ ሾዎች ይሰራል .. […]![]()
አምባገነኑ የህወሓት አገዛዝ ለስልጣኑ መጠበቂያ ያቋቋመው መከላከያ ሠራዊት እየፈረሰ የትጥቅ ትግሉን በመቀላቀል ላይ ነው፡፡
የህዝብ ጠላት የሆነው ህወሓት ከህዝብ አብራክ የተከፈለውን መከላከያ ሠራዊት በፀረ-ህዝብነት ሙሉ ለሙሉ የማሰለፉ ዓላማው ሲከሽፍ በዓይኖቹ በብረቱ በመመልከት ላይ ነው፡፡ ምክንያቱም ሰሞኑን በርካታ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው በመኮብለል አርበኞች ግንቦት ሰባትን ተቀላቅለዋል፡፡ ህዝብን ለማጥፋት የቆመውን ህወሓትን ከድተው ለህዝብ ከቆመው አርበኞች ግንቦትት 7 ጎን ከተሰለፉት ከእነዚህ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል የአግአዚ ኮማንዶ ክፍለ ጦር አባላት […]![]()
ኢትዮጵያና ኤርትራ ለማስታረቅ ሱዳንና ኳታር እቅድ መያዛቸውን ተሰምተዋል።
የሱዳኑ ፕሬዝደንት ዑማር ልበሽር የአገሪቱን ምርጫ በማሸነፋቸው በነገው ዕለት የቃለመሃላ ሥነ ሥርዓት ያካሂዳሉ። በዚህ በዓል የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝና የኤርትራው ፕሬዝደንት አቶ ኢሳያስ አፍወርቂ ፊት ለፊት ይገናኛሉ። የሱዳንና የኳታር መሪዎች ይህን አጋጣሚ በመጠቀም በከረረ ጥላቻ የሚገኙት ኤርትራና ኢትዮጵያን ለማስታረቅ ሙከራ ያደርጋሉ ተብሏል። የኢትዮጵያና የኤርትራ ጥል በአፍሪካ ቀንድ ብሎም በምሥራቅ አፍሪካ ሠላም ለማስፈን ማነቆ መሆኑን የተረዱት መሪዎቹ ችግሩን ለመፍታት በቁርጠኝነት […]![]()
እነ ወይንሸት ሞላ ለሰኔ 8 ተቀጠሩ •የፓርቲ አመራሮችን በመከላከያ ምስክርነት ጠርተዋል
መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም መስቀል አደባባይ ጠርቶት ከነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ጋር በተያያዘ በእስር ላይ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው ክስ ላይ መከላከያ ምስክሮቻቸውን ለማሰማት ለሰኔ 8/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በእነ ወይንሸት ሞላ የክስ መዝገብ የተካተቱት ወይንሸት ሞላ፣ ዳንኤል ተስፋዬ፣ ኤርሚያስ ጸጋዬ፣ ማስተዋል ፍቃዱ እና ቤተልሄም አካለወርቅ በአቃቤ ህግ ‹‹ሰላማዊ ሰልፍን በማወክና ሁከትና ብጥብጥ […]![]()
ከምሽቱ ሦስት ሰዓት የአማርኛ ዜና – ሰኔ 01, 2015
ቪኦኤ በየዕለቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት በኢትዮጵያ ኣቆጣጠር ጀምሮ በአማርኛ፣ በአጭር ሞገድ 22፣ 25 እና 31 ሜትር ባንድ የ60 ደቂቃ ሥርጭቱ ዜና፣ አበይት ዜናዎች ትንታኔና ሌሎችም ወቅታዊ መረጃዎችን የያዙ ፕሮግራሞች ያስተላልፋል።
ሰኞ፡- ስፖርት፣ አፍሪካ ነክ ርዕሶች፣ ጤና
የመንግስት ወታደሮች በሞያሌና በኦጋዴን ሃይላቸውን እያጠናከሩ ነው
ግንቦት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፉት ሁለት ሳምንታት የኢትዮጵያ እና የኬንያ ድንበር የተለያዩ ግጭቶችን አስተናግዷል እንደ አይን ምስክሮች ገለጻ። ዩኒፎርም የለበሱ የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደ ኬንያ በመግባት የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር አባላትን ለማደን ቢሞክሩም እስካሁን አልተሳካላቸውም። የመንግስት ወታደሮች ወደ ኬንያ ሞያሌ ከተማ በመግባት ቦሩ ሁካ የተባለ የ55 ዓመት የትምህርት ቤት ዘበኛ በጥይት …
ከአርበኞች ግንቦት7 ጋር አብራችሁዋል በሚል የተያዙት ክስ ተመሰረተባቸው
ግንቦት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ዞን ማክሰኝት ከተማ ነዋሪ መሆናቸው የተነገረው አቶ ዘመነ ምህረቱ እና ሌሎች የመከላከያ ሰራዊት አባላት የሽብርተኝነት ክስ እንደተመሰረታባቸው ሪፖርተር ዘግቧል። አቶ ዘመነ የመኢአድ ምክትል ፕሬዚዳንት መሆናቸው በክሱ የተመለከተ መሆኑን የዘገበው ጋዜጣው፣ መስከረም 18፣ 2007 ዓም በጎንደር በሚገኘው የመኢአድ ጽ/ቤት ውስጥ አባላትን በመሰብሰብ ” የወያኔ መንግስት …
፬ኛው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ የጋራ አቋም መግለጫ
በሐዋርያዊት፣ ጥንታዊት እና ብሔራዊት ቤተ ክርስቲያናችን ህልውና እና ዕድገት ፊት ከተጋረጡትና አፋጣኝ እልባት ከሚሹት የዘመናችን የውስጥ ችግሮች እና የውጭ ተግዳሮቶች ውስጥ ሙስና እና ኑፋቄ ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡ አንዱ የሌላው መተላለፊያ፣ መንሥኤ እና ውጤት እየኾኑ ለቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ ለውጥ የተደረጉ ጥረቶችን ሲያመክኑ፤ የመዋቅር እና የአደረጃጀት አቅሟን ሲያዳክሙ ቆይተዋል፡፡ በአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የሚያዝያ ፳፯ ቀን ፳፻፯ …![]()