በምእራብ ሸዋ ባለስልጣናት ” የክልሉ ተወላጆች ባለመሆናችው ለቃችሁ ውጡ ” የተባሉት የአማራ ተወላጆች አደጋ ውስጥ ናቸው

ነኅሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን በኖኖ አሎ ቀበሌ የሚገኙ ባለስልጣናት እና የጸጥታ ሃላፊዎች ‘ እናንተ የዚህ አካባቢ ተወላጆች ሳትሆኑ ሀብት እያፈራችሁ የአካባቢው ተወላጆች ግን ከናንተ ያነሰ ገቢ ነው ያላቸው…ይህን ገቢ ያገኛችሁት በኛ መሬት ነው፤ ስለዚህ የክልሉ ተወላጆች ባለመሆናችሁ ክልሉን ለቃችሁ ውጡ’ በማለት ቤታቸውን በማቃጠልና ንብረታቸውን በመንጠቅ ያፈናቀሉዋቸው የአማራ ተወላጆች በከፍተኛ ችግር ውስጥ ወድቀዋል ሲል የቀድመው ኢሰመጉ የአሁኑ ሰመጉ በፎቶ ግራፍ አስደግፎ ያወጣው 136ኛ ልዩ መግለጫ አስረድቷል።
የሰብአዊ መብት ጉባኤው እንደሚለው መጋቢት 27፣ 2007 ኣም አቶ ዘመዱ እንዳለ የተባለ የኦሮሞ ብሄረሰብ ተወላጅ መገደሉን ተከትሎ፣ አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ውሎ ጉዳዩ ውሳኔ ሳያገኝ ” ይህ ግድያ የተፈጸመው በአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች ነው” በማለት የኖኖ ወረዳ የፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኢንስፔክተር ሃይሉ ድሪባ፣ የኖኖ አሉ ቀበሌ ሊቀመንበር አቶ ጎሳየ ገች እና መቶ አለቃ ገነነ በየነ የተባሉ የፖሊስ አባላት የቀበሌ አመራሮችንና የፖሊስ አባላትን በማስተባበር ፣ የአካባቢው ህዝብ በአካባቢው በሚኖሩ የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች ላይ እንዲነሳ በማነሳሳት ሚያዚያ 9፣ 2007 ዓም 85 አርሶ አደር አባወራዎችን ለእስራት ዳርገዋቸዋል።
በማግስቱ ሚያዚያ 10 ደግሞ ከጧቱ 3 ሰአት አካባቢ ዘር በመምረጥ የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች መኖሪያ ቤትና ንብረት ነው ያሉትን እየመረጡ በእሳት እንዲቃጠል ፣ ከታሰሩትም አባዎራዎች ከእያንዳንዳቸው 300 ብር ለነዳጅ ብለው ከተቀበሉዋቸው በሁዋላ “ቤታችሁ ተቃጥሏል” ሂዱ በማለት ከእስር መልቀቃቸውን ሰመጉ የቀረበለትን ማመልከቻ በመንተራስ ባለሙያዎቹ ቦታው ድረስ በመሄድ አርሶ አደሮችን አነጋግረው ማረጋገጣቸውን ገልጿል።
የኖኖ ወረዳ አስተዳዳሪ ቤቶቹ ከነሙሉ ንብረታቸው በተቃጠሉበት ቦታ ላይ 24 ቆርቆሮ ቤቶች ስራ መጀመሩን ፣ ቤት ለተቃጠለባቸውና ንበረት ለወደመባቸው የአካባቢው ተወላጅ የሆኑ የኦሮሞ ብሄረሰብ አባላት በራሳቸው ተነሳስተው ገንዝብና እህል አዋጥተው እርዳታ እንዲደርሳቸው እየተደረገ መሆኑንና ተጎጂዎቹ ተረጋግተው እንዲኖሩ ለማድረግ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየሰራ መሆኑን ለሰመጉ ቢገልጹም፣ ሰመጉ ግን የአካባቢው ህዝብ በራሱ ተነሳሽነት የእርዳታ ገንዘብና እህል ማዋጣቱ ትክክል ቢሆንም፣ እርዳታው ግን ሪፖርቱ እስከተጠናከረበት ለተጎጂዎች አለመድረሱን ገልጿል።
ሰመጉ ባለስልጣኖች ባነሳሱት ብጥብጥ 1 የሰው ህይወት ማለፉን፣ 10 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ አደጋ መድረሱን፣ 99 የሳር ክዳን ቤቶች በእሳት መቃጠላቸውን፣ 25 የቆርቆሮ ክዳን ቤቶች በእሳት ተቃጥለው መውደማቸውን አትቷል።
ቃጠለውን ተከትሎ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሴቶች፣ ህጻናትና አቅመ ደካሞች የሚገኙባቸው ተፈናቃዮች ከአካባቢው በመሰደድ ወደ ደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ሀበሽጌ ወረዳ ድንኳን ውስጥ ተጠልለው ሲረዱ መቆየታቸውን ሰመጉ ገልጾ፣ ወደ አካባቢያቸው ሲመለሱ ” ለምን ከሰሳችሁን ” ያሉ ባለስልጣናት፣ ለከፋ ችግር እንደዳረጉዋቸው፣ ሪፖርቱ ከመውጣቱ ጥቂት ቀድም ብሎም በዲኮሻም ቀበሌ የአቶ ደምስ መኩሪያና የአቶ በፈቃዱ ሰጠኝ መኖሪያ ቤቶች በእሳት እንዲቃጠሉ መደረጉን እንዲሁም ከአቤቱታ አቅራቢዎች መካከል 8 ሰዎች “ሽፍቶች ናቸው ይታደኑ”የሚል ትእዛዝ ወጥቶባቸው በፍርሃት አካባቢያቸውን ለቀው ተሰደዋል።
ሰመጉ በማጠቃለያው ” በአካባቢው የቀበሌና የፖሊስ ባለስልጣናትና አባሎች መሪነት ቤቶቻቸው የተቃጠሉባቸው ነዋሪዎች፣ እንደማንኛውም ዜጋ በሀገሪቱ አካባቢ ሁሉ ተዘዋውረው ኑሮ የመመስረትና ሀብት የማፍራት መብት እንዳላቸው በህገመንግስቱ ቢደነገግም፣ ” የዚህ ክልል ተወላጆች አይደላችሁም ፣ ህገወጦች ናችሁ ተብለው መኖሪያ ቤታቸው በህገወጥ መንገድ በእሳት እንዲወድም መደረጉ ከአገሪቱ ህጎችና ከተቀበለቻቸው አለማቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎች ጋር በእጅጉ የሚቃረን ነው” ብሎአል። ይህ ችግር በዳርጌ ወረዳ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ውስጥ በወረዳ፣ በቀበሌ ባለስልጣናትና በህግ አስፈጻሚና አስከባሪ አካላት የሚፈጸም መሆኑን ሰመጉ ገልጿል።
ሰመጉ መኖሪያ ቤታቸው ለተቃጠሉባቸው እና በተለያዩ ቦታዎች ተበታትነው ለሚገኙ ዜጎች አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታ እንዲያገኙ ፣ ለወደመባቸው ንብረትም ካሳ እንዲያገኙ መንግስትን የጠየቀ ሲሆን፣ በተለይ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የጎሳና የዘር ልዩነትና አድልዎ እየተደረገባቸው እየተጎዱና እየተፈናቀሉ ያሉ ዜጎች ቁጥር በየጊዜው አሳሳቢ በሆነ መልኩ እየጨመረ በመሄዱ፣ መንግስት የተጠናና የማያዳግም የመፍትሄ እርምጃ ከህዝብ ጋር ተመካክሮ መውሰድ እንዳለበት አበክሮ ጠይቋል።

3 Comments on “በምእራብ ሸዋ ባለስልጣናት ” የክልሉ ተወላጆች ባለመሆናችው ለቃችሁ ውጡ ” የተባሉት የአማራ ተወላጆች አደጋ ውስጥ ናቸው”

  1. Are ferenjis or CIA using TPLF and stupid oromo tribalists to revenge against Ethiopian nationalists for the black African violence against ferenjis in Southern Africa ?

    We know ferenjis in South Africa, Zimbabwe and elsewhere in Southern Africa are exposed to violence by black Africans.
    And we know also that the ferenjis have made also Ethiopian nationalists responsible for the problems ferenjis are facing in Southern Africa.

    We remember Ethiopia supported ANC, Zimbabwe and other African liberation movements.

    So could the ferenjis now be revenging using Banda TPLF and stupid oromo tribalists ?

    ESAT is a dubious broadcaster, it has the habit of twisting words and interpreting events in a way to favour ferenjis and disfavour Ethiopia.

    We should perhaps consider this aspect of the ethnic cleansing in Ethiopia.

    Are ferenjis revenging on “Amaras” for black violence against ferenjis in Southern Africa ?!

  2. @ተንኮሉ

    አንተ የባንዳ ልጅ Insa ይህን ሥራ ብሎ ካሠማራህ ትውልድ ገዳይ ነው ወያኔ የታሪክ አተላ ሆናችሃል በልልኝ።
    ይህው ተግባራችሁ እውን እየታየ ነው ዘረኝነትና ጠባብነት ጎጠኛ ትምክህተኛ ድርጅታችሁ በአንቀፅ 39 ለማፍረሥ ተግባራዊ አደረጃጀት በእውን ይታያል ተንኮሎ የወያኔ ጭምብል 1ቀን ይበረተፉል አይንህን አታድክም ነፈሰባችሁ።

    ድል ለግ7 ባንዳን ለምታወግዙ!!!

    እ/ር ኢትዬ. ይባርክ

  3. @ wind of change,

    you likely reacted to ESAT critic, but you have to accept that. The broadcaster is far from perfect.

    By the way what is keeping TPLF still in power ?

    1. USA, CIA, West and ferenjis.

    Why is nobody talking about the thousands of American agent Ethiopians based in Ethiopia and abroad ? They get paid by the American government or the CIA.

    2. Eritrea.

    The opposition abroad and in Ethiopia is infiltrated by Eritrean agents. Those agents sabotage the fight against TPLF.

    3. Lack of a clear agenda and ideology.
    Our struggle should be,

    a) black nationalism vs white supremacy.
    TPLF is an agent of white supremacy. Our enemies are TPLF and tribalists. The opposition is black nationalist.

    b) our goal is to overthrow TPLF and replace it with a black nationalist government. Tribal, religious, class and regional differences will play no role in post-TPLF Ethiopia, just like in the pre-TPLF Ethiopia.

    c) by being black nationalists we are only continuing the tradition we inherited from Haile Selassie, Menelik and other leaders. As we know those leaders were black nationalists.
    Haile Selassie’s experience during a speech before the league of nations in 1936 is said to have influenced him to develop black nationalist and pan Africanist attitudes.
    https://www.youtube.com/watch?v=yb6Gul-8TG8

    d) Ethiopia was target of ferenji destabilization since at least the 1960s because of its black nationalist policies in Africa. Ethiopia was targeted by ferenjis because of its black nationalist ideology. Now we should use that history to mobilize support from blacks in our struggle against the agent of white supremacy, TPLF.

    PS

    due to Eritrea’s and ferenjis’ influence among the Ethiopian opposition like AG7 the black nationalism vs white supremacy strategy was not adopted and exploited in the past in the struggle against TPLF. And that shows how Eritrea and ferenjis are sabotaging the struggle against TPLF.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*