የኢህአዴግ መንግስት በድርቅ ለተጎዱት ወገኖች የእርዳታ ጥሪ አቀረበ
ነኅሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስር የሚታተመው ሳምንታዊ የሰብአዊ እርዳታ መጽሄት እንደዘገበው መንግስት በአገሪቱ ውስጥ የታየውን የምግብ እጥረት ለመቅረፍ ለጋሽ አጋራት አስቸኳይ እርዳታ እንዲለግሱ ጥሪ አቅርቧል። ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ ሊፈጠርባቸው ይችላል ተብሎ ለተሰጋባቸው ቦታዎች መንግስት 700 ሚሊዮን ብር መመደቡን አስታውቋል። ዞን 3 በሚባለው የአፋር አካባቢ እንዲሁም ስቲ ዞን በሚባለው የሶማሊያ ክልል አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልግ ዘገባው አመልክቷል። በመላ አገሪቱ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚፈልገው ህዝብ ቁጥር 9 በመቶ ጨምሯል።
መረጃዎች እንደሚያሳዩት በኦሮምያ፣ ከፊል አማራና በትግራይ አንዳንድ አካባቢዎችም ድርቅ ተከስቷል። ድርቁ እስከ ጥቅምት ሊዝልቅ እንደሚችል የሜትሮሎጂ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ባለሙያዎች እየገለጹ ነው።
በአፋር ክልል በተለይ ዜጎች በውሃ እጥረት እየተቸገሩ ሲሆን፣ በርካታ የቀንድና የጋማ ከብቶች በድርቁ ምክንያት አልቀዋል።
በደቡባዊ ምዕራብ ኢትዮጵያ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በዶዶላ ወረዳ ዝናብ መጣሉን በማቆሙ መሬቱን ታርሶ በሰብል አለመሸፈኑን እና የአካባቢው አርሶ አደሮችም በስጋት ውስጥ እንዳሉ ፎርቹን ጋዜጣ ዘግቧል።
Hi
11% growth for ten years and the TPLF cant manage such problem.
It seems TPLF has created this problem by intention for reasons,
1. to discredit Ethiopia. That has been TPLF’s job for at least 24 years.
2. to distract from the armed and other resistance and opposition against the regime. The ethnic cleansing in Western Shewa could be also another distraction.
ለ GTP2 ገቢ ማሥገኛ እንደሆነ እንጂ ለህዝቡ አሥቦ አይደለም በልማት ሠበብ ብዙውን አርሦ አደር መንደር ለማሠባሠብ በሚል ከለም መሬቱ ደንቁሎ አባረረ ወያኔ ልማታዊ መንግሥት ድንቄም 11 ዲጅት ሥንት ትሆን ይችህ ቁጥር መቼም ከድሮም ተነቅሣችዋታል ተተልትላችሀል አሥገራሚ ነገር የለውም ጅቡቲ የደረሠው እህል ይመለሥላቸው።
ወራዶች “የምትበላው የላት ልትቀምሠው አማራት”