ብክነቱን በአውራነት በማጋለጣቸው የታገዱት ተቆጣጣሪ የከፈሉትን መሥዋዕትነት አድንቋል የብር 110 ሚሊዮን ጭማሪ ሲደረግ ሀገረ ስብከቱ አያውቀውም፤ ሊቀ ጳጳሱም አልፈቀዱትም የብር 103 ሚ. ጠቅላላ በጀት በሚመደብበት ተቋም በብር 110 ሚ. አለመወሰኑ አነጋጋሪ ነው ግለሰቦችን በመጥቀም ራሱን ያበለጸገው አለቃው፣ አድባራትን ባለዕዳ በማድረግ ይታወቃል *           *           * የደብሩ ዋና ጸሐፊ በሀገረ ስብከቱ በዋና …

       *እስክንድር ገብረ ክርስቶስ ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ፣ ሰኔ ፳፻፭ ዓ.ም /መጠነኛ አርትዖት ተደርጎበት የቀረበ/ በቤተ ክህነታችን አሠራርና አደረጃጀት ውስጥ የሚታየውን የሙስናና የጎጠኝነት ችግሮች በተመለከተ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ በቤተ ክርስቲያኒቱ ልሳናት በመጠቀም ያልጠቆመው ያላመላከተውና በመረጃ በማስደገፍ ይፋ ያላደረገው ብልሹ አሠራር ይኖራል ተብሎ አይገመትም፡፡ ከቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮዎች እጅጉን በተቃራኒው መንገድ የሚገለጹት የብልሹ አሠራር ምንጮች እንዲወገዱም ምንጮችን …