የአሜሪካ ፤ የብሪታኒያ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት የፖለቲካ አመራሮች አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር እንዲፈቱ ለጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ደብዳቤ መላካቸውን አልጀዚራ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘገበ።

የፖለቲካ አመራሮች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፉት ደብዳቤ አቶ አንዳርጋቸው ለብቻቸው 24 ሰአት የተፈጥሮ ብርሀን በማያገኙበት ሁኔታ እስር ላይ መሆናቸውን እንደጠቀሱ አልጀዚራ በብቸኝነት ማግኘት ችያለሁ ያለውን መረጃ ዋቢ በማድረግ አስነብቧል። ለኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄያቸው ያቀረቡት እነዚህ አካላት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የያዙበት ሁኔታ አሳሳቢ እና በሀገሪቱን ከአለም አቀፍ ማህበረሰብ የሚነጥል እንደሆነ ገልጸዋል። በአሜሪካ የውጪ ጉዳዮች ኮሚቴ አባል እና የካሊፎርኒያ […]